ቤቴ ገብቼ እየደጋገምኩ አዳመጥኩት፡፡ ውስጤን ነበር የነካው፡፡ በነጋታው ወደ እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ሄጄ ሌሎች ሁለት ካሴቶች ከልጁ ገዛሁ፡፡ ልጁ ሌላ ካሴት ከፈለግሽ ብሎ አንድ ሱቅ ጠቆመኝ፡፡ እዚያ ሄጄ ሌሎች ሁለት ጨመርኩ፡፡
በትምህርቱ ውስጥ ራሴን ነበር የማየው፡፡ ውስጤን ነበር የምመረምረው፡፡ መንገዴን ቁልጭ አድርጎ አሳየኝ፡፡ እናም ከፈጣሪ ጋር መሟገቴን ተውኩ፡፡ ውጭ ስለመሄድ ማለሜን ተውኩ፡፡ ለብዙ ሰዓታት ከራሴ ጋር ከተሟገትኩ በኋላ ከስድስት ዓመት በፊት ወደ ተውኩት ትምህርቴ ተመለስኩ፡፡ ያኔ ቢዝነስ አስተዳደር የሚባል ትምህርት ጀምሬ አንድ ሴሚስተር እንደተማርኩ ነበር ውጭ ውጭ የሚል ዛር ለክፎኝ ያቋረጥኩት፡፡
እናቴ ማመን አልቻለችም፡፡ ቤተ ሰቦቼ ሁሉ ተገረሙ፡ ግን ደግሞ ይመለስባታል ብለው ፈርተው የምላቸውን ከመፈጸም ውጭ ሊናገሩኝ አልደፈሩም፡፡
ላሳጥርለህና ትምህርቴን ላጠናቅቅ አንድ ወር ያህል ሲቀረኝ አጎቴ አስጠራኝ፡፡ ቅድም እንዳልኩህ በጣም ነበር የሚወደኝ፡፡ እንዲያውም እናቴ ቤት ከኖርኩበት ዘመን እርሱ ቤት የኖርኩበት ዘመን ይበልጥ ነበር፡፡ ልጅ ስላልነበረው በእርሱ ስም ነበር የምጠራው፡፡ የእኔ ሕይወት በጣም ነበር የሚያሳስበው፡፡ በዚያ ላይ የደም ብዛት በሽታ አለበት፡፡ የኔን እንደዚያ መሆን ሰምቶ ለብዙ ቀናት አልጋ ላይ መዋሉን ሰምቻለሁ፡፡ ርግጠኛ ነኝ የመለሰኝ የርሱ ጸሎት ነው፡፡
እግዚአብሔር ሲወድድህ የሆነ ቦታ ስለአንተ የሚጨነቁ ሰዎች ይሰጥሃል፡፡ ጸሎታቸው የሚደርስላቸው፣ጩኸታቸው የሚሰማላቸው ሰዎች ያዘጋጅልሃል፡፡ ላታውቃቸው ወይንም ላትገምታቸው ትችል ይሆናል፡፡ ግን ስለሚወድድህ ያዘጋጅልሃል፡፡
እቤቱ ስደርስ እናቴ፣ አባቴ፣ ሌላው አጎቴ እና ሁለት አክስቶቼ፣ ከውጭ የመጡ ሁለት ወንድሞቼ እና የአጎቴ የንስሐ አባት ሳሎን ተቀምጠዋል፡፡ ሊመክሩኝ ነው ብዬ ፈራሁ፡፡ ይገርምሃል አንዳች የሕይወትክን መሥመር በተስፋ መቁረጥ ስትስት ምክር ትጠላለህ፡፡ እኔም እንደዚያ ሆኜ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ተለውጫለሁ ምን ፈልገው ነው ? እያልኩ ገባሁ፡፡
የሁሉም ዓይን እኔ ጋ ማረፉን ሲቆጠቁጠኝ ይታወቀኛል፡፡ ካህኑ ጸሎት አደረሱ፡፡ ከዚያም አጎቴ ከተቀመጠበት ተደላደለ፡፡ «እንደምታውቁት እኔ ልጅ የለኝም፤ ባለቤቴም ከሞተች ሦስት ዓመት አለፋት፡፡ እንግዲህ የሚቀረኝ ሞቴን መጠበቅ ነው» እንዲህ ሲናገር ሳላስበው እንባዬ ከዓይኔ ይፈስ ነበር፡፡ «አሁን የጠራኋችሁ ሀብቴን ሁሉ ለልጄ ማውረሴን ለመንገር ነው፡፡ ያለችኝ ልጅ እርሷ ብቻ ናት፡፡» አልቻልኩም ተነሥቼ ተጠመጠምኩበት፡፡ ተያይዘን ተላቀስን፡፡ ካህኑ ነበር ያላቀቁን፡፡
«እንደምታውቁት አንድ ቃል ነበረኝ፡፡ የእኔን ሀብት የሚወርሰው ሀገሩን ለቅቆ ያልሄደው ኢትዮጵያዊው ልጅ ነው፡፡ ከድሮ ጀምሮ ቦታችሁን እንጂ ዜግነታችሁን አትለውጡ እላችሁ ነበር፡፡ መቼም የእኛ እና የናንተ አስተሳሰብ ይለያያል፡፡ ከእርሷ በቀር ሁላችሁም ሄዳችሁ፡፡ ሁሉም ልጆች ዜግነታቸውን ቀየሩ፡፡ ነገሩ በዚህ ጉዳይ ከልጆቼ ብቻ ሳይሆን ከወንድሞቼም ጋር አልተስማማሁም፡፡
እንደኔ ቃል ከዚህ ሀገር ያልወጣችው ብቸኛ ተስፋዬ እርሷ ናት፡፡ እርሷንም የናንተ ዛር ለክፏት ካልሄድኩ ብላ ነበር፡፡ የእግዜር ነገር አሥሮ ያዘልኝ እንጂ»
የአጎቴን ፋብሪካ እና ሱፐር ማርኬት ወረስኩ፡፡ ለተወሰነ ጊዜ ወደ አንድ ገዳም ሄድኩና የእግዚአብሔርን ሥራ ለብቻዬ አስብ ነበር፡፡ እኔ ልሄድበት የፈለግኩትን እና እግዚአብሔር የመረጠልኝን መንገድ እያሰላሰልኩ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ንግግር የማይገልጠው ምስጋና አጋጥሞህ ያውቃል? ዝምታ ብቻ የሚገልጠው፡፡ እኔ እግዚአብሔርን ለማመስገን ንግግር አለቀብኝና ዝምታን መረጥኩ፡፡ አንድ ገዳም ሄጄ ቀኑን በሙሉ ዝም ብዬ እውል ነበር፡፡ እይውልህ ትናንት በመከራ ያላገኘኋቸውን ቪዛዎች ዛሬ በክብር ሄጄ እወስዳቸዋለሁ፡፡ ዛሬ አሜሪካ ካልኖርኩ አልልም፡፡ የምሄደው ለሌላ ጉዳይ ነው፡፡ እግዚአብሔር በሀገሬ እንድሠራ፣ እንድከበር፣ ፈለገ፡፡ እኔ ደግሞ በሰው አገር መከራ ካልተቀበልኩ አልኩት፡፡ በግድ ጠምዝዞ ወደ ተሻለው መንገድ ወሰደኝ፡፡
ዮሴፍን ታስታውሰዋለህ፡፡ የእግዚአብሔር ዕቅድ ዮሴፍ የግብፅ ንጉሥ እንዲሆን ነው፡፡ የዮሴፍ ፍላጎት ደግሞ ቶሎ ከእሥር ቤት ለመውጣት ነው፡፡ ዮሴፍ በሰው በኩል ከእሥር ሊወጣ ሞከረ፡፡ እግዚአብሔር ግን በእሥራቱ ላይ ሁለት ዓመት ጨመረበት፡፡ አሁን ለዮሴፍ ከእሥራቱ ራሱ በመረጠው መንገድ መውጣቱ ነበር ጥሩ? የዚያን ጊዜ ፍላጎቱን እግዚአብሔር ቢፈጽምለት ነበር ጥሩ ? እንኳንም አላደረገው፡፡ እንኳነም አልፈጸመለት፡፡ የዮሴፍ ዕቅድ ቢፈጸም ኖሮ ያንን የመሰለ ተአምር፣ያንን የመሰለ ታሪክ የት ይገኝ ነበር፡፡
አንዳንድ ጊዜ በቀላሉ በመዶሻ የሚፈረከስ ድንጋይ አለ፡፡ እምቢ ካለ ግን በድማሚት ይመታል፡፡ የኔ ልብ እምቢ አለ፡፡ ስለዚህ በድማሚት ተመትቶም ቢሆን ተመለሰ፡፡ ርግጠኛ ነኝ በሄድኩበት የኃጢአት መንገድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጥበቃው ነበር፡፡ ፍላጎቴን አልከለከለኝም፤ ነገር ግን ለክፉ አልሰጠኝም፡፡ እግዚአብሔር እና አጎቴ ተግባብተዋል፡፡ እኔ እና እግዚአብሔር ግን አልተግባባንም ነበር፡፡ እኔ ከእግዚአብሔር ጋር ለመግባባት ይህንን ሁሉ መንገድ መሄድ ነበረብኝ፡፡
እስኪ አስበው፡፡ የለመንኩትን ቢያደርገው ኖሮ፤ አሜሪካ ሄጄ አንድ ሱፐር ማርኬት እቀጠር ነበር፤ ወይንም የአንድ ፓርኪንግ ሠራተኛ እሆን ነበር፡፡ ምንም እንኳን ይህ በራሱ መጥፎ ባይሆንም እግዚአብሔር ግን ይህንን አልፈለገም፡፡ ከእኛ ይልቅ ለኛ ያውቃልና፡፡ እኛ ከመረጥነው እርሱ የመረጠው ይበልጣልና፡፡ የጠየቅኩትን ከለከለና የመረጠልኝን ሰጠኝ፡፡ እኛ የሚያምረንን፣ እርሱ ግን የሚያምርብንን፤ እኛ የምንፈልገውን፣ እርሱ ግን የሚያስፈልገንን ያደርግልናል፡፡
ለዚህ ነው «ስላላደረግልኝ ሁሉ አመሰግንሃለሁ» የሚል ጥቅስ ያስጻፍኩት፡፡ ዛሬ ላይ እቆምና «እንኳንም የጠየቅኩህን አልሰጠህኝ፤ እንኳንም የለመኩህን አላደረግከው፤ እንኳንም እምቢ አልከኝ፤» እለዋለሁ፡፡
ስለያት
«ለርእስዬ እም ርእስዬ እስመ አንተ ትቀርቦ» አልኩ፡፡ «ለእራሴ ከእራሴ ይልቅ አንተ ትቀርበዋለህ» ማለት ነው፡፡
ይህ የእርሷ ታሪክ ግን ከስድስት ዓመታት በፊት የተፈጸመ ሌላ ታሪክ አስታወሰኝ፡፡
አግዚአብሄር ይስጥልን ዲ/ን ዳንኤል: ድንቅ አጋጣሚ ነው ያስነበብከን:: እኛንም ቅዱስ እግዚእብሄር ወደሚሆነን የሂወት ጎዳና ይምራን::
ReplyDeleteOh! God, the Almighty,...when shall our ways go with Yours..."Selaladerkelen hulu Enameseginehalen"....Dani...Kale Hiwot Yasemalen
ReplyDeleteAntenim Keriwun zemenihinim Egziabher yibarik. I do thank you!
ReplyDeletegb22
ReplyDelete*KE EGZIABHER ANIKDEM* YEMIL YE Daniel kibret sibket tiz alegn.Ebakachihu internet yalachihu youtube lay hagerbet yalachihu degimo mahibere kidusan suk hedachihu ye timirtun caset gizut.Dani yihin sitilegn tiz yalegn yih casett new.EBAKACHIHU YALSEMACHIHUT SIMUT BE VIDIOM ALE.YEWICHI BESHITA YEYAZEN WEYIM BESHITAW YEYAZEW WENDIM,EHIT,ZEMED YALEN WEYIM YEBESHITAW MILIKIT EYETAYEBET YALE SEW KAWEKIN YICHIN CASSET FELIGO MESTET NEW MEDHANITU.
Great story & teachs me a lot I am on her previous postion today eventhogth i am living in USA a lot of things are not going as i planned.May God give me the wisdom.
ReplyDeletehi dn bewnet igzi'abhern metebek witetu min indehone yasayen new,akerarebu betam des yilal ke ri'isu jemro,
ReplyDeleteigzi'abher agelgilotijn yibark
Incredibly surprising !!!!!!! May God widen your spiritual insights to see deep into our hearts !! I think we are blinded by our fleshy deeds. Emiye Maryam titebikih !!!
ReplyDelete"እኔ እግዚአብሔርን ለማመስገን ንግግር አለቀብኝና ዝምታን መረጥኩ፡፡" What a story!!! Dn Daniel, Thanx for sharing this interesting and educational story. May God bless u! At last u said her story reminded u another story that happened before 6 years, what would that be?
ReplyDeleteዉድ ወንድማችን፤
ReplyDeleteአዎ እንዲህ ጨርሰዉ እንጂ! እግዚአብሔር አምላክ ብርታቱን ይስጥህ፤ ላስተዋለ ሰዉ ብዙ ትምህርት ይሰጣል፤ በተለይ በአካል ብቻ አገር ቤት ላሉትና ዉጭ አገር ላለነዉ። ... ብቻ እርሱ ልብ ይስጠን።
ከብሪታኒያ
Thanks Dn Danile
ReplyDeletePlease write only spiritual messages and events
and stop! to write such as, sports, poletical, and others messages are not in spirite
God Bless you
D. Daniel, Kale Hiwote Yasemalin!!!it is such an uplifting story "ይህ የእርሷ ታሪክ ግን ከስድስት ዓመታት በፊት የተፈጸመ ሌላ ታሪክ አስታወሰኝ፡፡" Are you going to tell us about what took place six years ago? Please share it with us if the story as inspiring as this one...Bedigami Kalehiwot Yasemalin!
ReplyDeleteAmeha Giyorgis & Fikrte Mariam
From DC/VA area
mulu lemulu ewinet new! kegna belay askedimo sanifeter yemiyawiken esu kegna belay silegna yawikal, filagotachin alemederegu mikniyatawi endehone teredto ye-amlakin fekad metebek mechal berasu tilik tsega new egziabeher yatsinash ehitachin bizu temirenibishal
ReplyDeleteDn. Dani
ReplyDeleteI love it.
Thnk you.
ግሩም ና አስተማሬ ታሪክ። እግዚአብሔር ጸ(ፀ)ጋውን ያብዛልህ።
ReplyDeletedani dani dani god bless you & your family
ReplyDeleteልበ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት “በልዎ ለእግዚአብሔር ግሩም ግብርከ” ያለው ለእንደዚህ አይነቱ አይነቱ አይደል፡፡ ዳኒዬ እግዚአብሔር ጥበቡን የበለጠ ይግለጥልህ፡፡
ReplyDeleteየእግዚያብሔር ስራ ድንቅ ነው::
ReplyDeleteትልቅ ትምርት ነው:: በኔም ህይወት እግዚያብሔር ትልቅ ስራ ሰርቶዋል::
በህይወት ትልቅ ችግር ነው ብለ ያሰብከውን በፈለግነው ወቅት ስላልተሳካ እንደዚ ነው የምንለው እግዚያብሔር "ባይኖር ነው እንጂ ቢኖርማ እንዴት ይህንን ሁሉ ጸሎት፤ ይህንን ሁሉ ሥዕለት አይሰማም፤ ቢያዳላ ነው እንጂ ባያዳላማ ለሌሎች ያደረገውን ለእኔ ማድረግ እንዴት ያቅተዋል ብዬ ተቀየምኩት፡፡" ውስጣችን ቶሎ ይሸነፋል ግን እኛ ባሰብነው መንገድ ሳይሆን
እግዚያብሔር በፈቀደውና በወደደው መልኩ ማመን እስኪያቅተን ድረስ ተከናውኖ እኛ ካሰብነው በላይ ተደርጎልን እናያለን በዚን ጊዘ እንዴት እንደምታመሰግን ግራ ይገባአል በቃ ዝም..........ዝም....ምንም ቃላት ታጣለ::
ዲ/ዳኒ እግዚያብሔር ከዚህ በላይ የምትሰራበትን እድሜ እና ብሩ አይምሮ ይስጥእ::
አዎ! የምንፈልገውን ሳይሆን የሚያስፈልገንን ከምስጋና ጋር እግዚአብሔርን እንለምን፡፡
ReplyDeleteዲ. ዳንኤል እግዚአብሔር እድሜ እና ጤና ይስጥህ፡፡ በርታ በርታ፡፡
ግሩም ና አስተማሬ ታሪክ። እግዚአብሔር ጸ(ፀ)ጋውን ያብዛልህ።
ReplyDeleteአንተሰ አንተ ክመ
ReplyDeleteየእግዚአብሔር ቸርነት እነዲህ ነው
ወንደሜ ዲ ዳንኤልን ከዚህ በላይ ማስተዋሉን ያድልልን
እግዚአብሔር ከክፉ ነገር ይጠብቅልን
አሜን
Egziabhair awaki new!!!!!!!!!!!
ReplyDeleteEgziyabher yistelen...des yemil ena yemiyastemir tarik new.
ReplyDeleteBless you Daniel!
"እኛ የሚያምረንን፣ እርሱ ግን የሚያምርብንን፤ እኛ የምንፈልገውን፣ እርሱ ግን የሚያስፈልገንን ያደርግልናል፡፡" what a saying!But we're not always willing to hear it.Even if we hear it,we don't percieve it.Because most of us do not relay on God surely!we hesitate! Let God grant us the mental strength to relay on him certainly!Thank u Dani may God bless u!
ReplyDeleteየህይወት ቃል ያሰማልን፡፡
ReplyDeleteእኛ ከመረጥነው እርሱ የመረጠው ይበልጣልና፡፡ የጠየቅኩትን ከለከለና የመረጠልኝን ሰጠኝ፡፡ እኛ የሚያምረንን፣ እርሱ ግን የሚያምርብንን፤ እኛ የምንፈልገውን፣ እርሱ ግን የሚያስፈልገንን ያደርግልናል፡፡
ሁለቹንም በህይተችን ለሚያጋጥመን ነገር ሁሉ እንደዚ ለማለት ያብቃን፡፡ አሜን
የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል። 2ኛ ጢሞ 3፡16-17
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማልን
Endiet des yemilna asitemari tarik new. Dn Daniel ahunim lewodefitum tsegawn yabizaliz. Ante yihn medirek batifetir noro yihien yemesele asigerami na sebaki tarik keyet enagegnew neber?
ReplyDeleteKALE HIWOT YASEMALIN
«ለእራሴ ከእራሴ ይልቅ አንተ ትቀርበዋለህ»ማለት ነው፡፡
ReplyDeleteKale hiwot Yasemalene
ReplyDeleteEgezabhr Yestelene rely nice.
ReplyDeleteMenetemarku enase kezhee??????
kalehiwot yasemalin
ReplyDeleteGOD IS GREAT!!
እኛ የሚያምረንን፣ እርሱ ግን የሚያምርብንን፤ እኛ የምንፈልገውን፣ እርሱ ግን የሚያስፈልገንን ያደርግልናል፡፡
ReplyDeletebetam astemari new becous ytekmegna biye ymlew legodabet selmichel yegziabhr kehon gen alegodam.
ReplyDeleteDaniel i know your talent since you wrote Merzamaw Ebab in early times .thank GOD for giving you such gift and write more more ,it touches my heart a lot .Especially write true stories like this as she said 'yehiwot metsehaf'
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይባርክህ ዳንኤል .. ትልቅ ቁምነገር ነው የነገርከን በተለይ በመከራ አልፎ ይህንን የምስጋና ቃል ለመናገር ምብቃት እንዴት መታደል ነው
ReplyDeleteThan you dani! So marvelous a history! Berta sew adirgen!
ReplyDeleteLib Yemineka tarik.
ReplyDeleteDEar D/N Daniel Selam Le hulachenem Yehun . It's really lessonfull.But I used this word"SElaladerekelegne negere hulu Amesegenalehu" Since I heard Ye memehere Pawlos "Godolyas ". Sibket. all of us should pray "seladerekelen Bereket bechcha Sayhon Selaladerekelenem Chimer" Every thing is for good (Hulum negere lebego newe )
ReplyDeleteGodolyas(Egziabher Talak newe)
Sami Neda Ke Abware
ሰላም ዳንኤል.
ReplyDeleteእውነት ነው አንዳንዴ ስንፈልግ ብንደክም አይሰጠንም ሳንፈልግም የምንታደለው ነገርም አለ. ታሪኩ ልቤን ነካው ሳነበውም ውስጤ እየተሰማኝ ነበር። ዛሬ ላይ ሆነን ስለነገ ማውቅ ብንችል እንዴት አመስጋኝ እንሆን ነበር።ትልቅ ቁምነገር አለው። እኔ የርሷ ተቃራኒ ነበርኩ ውጪ ሀገር ማለት መጥፊይ እግዚአብሔር የማይመለክበትና ሰው ለስጋው ብቻ የሚደክምበት አርጌ ነበር እማስበው እናማ እኔ ስሸሸው ሲከተለን ሰዎች በስለት፣በእግር በፈረስ እሚፈልጉት የውጪ ነገር እኔ ጋር ግን ሰሸሸው እሚከተለኝ ፈተናዬ ሆኖ ሲመጣ ከእግዜር ጋር ጠብ የያዝኩበትን ግዜ አልረሳውም ። ግን ሁሉንም ነገር አምኜ እምቀበልበትን ግዜ መጣ። ሀገሬ ላይ ብሆን ከአምልኮተ እግዚአግሔር የምወጣበት ፈተና እና አንድ እና አንድ የፈተናዬ መውጫ ደግሞ የምወዳትን ሀገሬን ትቼ መሄዴ ብቻ ሆነ። ታዲያ እግዚአብሔርን አማርሬ ያለቀስኩበት ግዜ ዛሬ ዛሬላይ ለሚገርም አላማው መሆኑን ሳይ ሰለራሴ ምንም እንደማላውቅ በህይወት ልምድ አስተማረኝ። እኛ ስንፈልገው እርሱ ደግሞ ያላደረገልን ነገር እንዴት ታላቅ በረከት አለው!!!
DANIE betame konjo tarik new
ReplyDeletethanks
It is amazing. Let God Keep u safe. Dn. Daneil please post such interesting blessings.Come with another lesson again.Egziabher Zewetir antenina betesebihin yitebik.
ReplyDeleteDear Daniel
ReplyDeleteEgziabhere Yageliglot Zemenihin Yarzimilin
Betesebihin Antenim Betena yetebikachu , DINGILE Atileyeh .
egziabhere mastewalun yisten !!!
ReplyDeletethanks d/n Daniel
በስመስላሴ!
ReplyDeleteእግዚአብሔር ከስንት ነገር፣ እንዴት እና መቼ እንዲሁም ስንት ጊዜ እንደጠበቀን አናውቅም፡፡ አልፎ አልፎ ግን የሆነ ነገር ሊሆንብን ብሎ (ልክ እንደ ነነዌ እሳት) ነካ አድርጎን ሲያልፍ ነው ጠብቆቱን የምናየው፤ በተመሳሳይም እንዲሆን የምንፈልገው የሚያምረንን ሲሆን እግዚአብሔር ግን በልካችን የሆነውንና የማንጠፋበትን መርጦ ይሰጠናል፡፡ የአብዛኞቻችን ታሪክ ከጽሁፉ ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ በነገሮች ሁሉ “ነገር ሁሉ ለበጎ ነው” ብሎ ማለፍ ምንኛ መልካም ነው፡፡
ወስብሀት ለእግዚአብሔር!
ገነት ቀፀላ (ወንጂ)
በስመስላሴ!
እግዚአብሔር ከስንት ነገር፣ እንዴት እና መቼ እንዲሁም ስንት ጊዜ እንደጠበቀን አናውቅም፡፡ አልፎ አልፎ ግን የሆነ ነገር ሊሆንብን ብሎ (ልክ እንደ ነነዌ እሳት) ነካ አድርጎን ሲያልፍ ነው ጠብቆቱን የምናየው፤ በተመሳሳይም እንዲሆን የምንፈልገው የሚያምረንን ሲሆን እግዚአብሔር ግን በልካችን የሆነውንና የማንጠፋበትን መርጦ ይሰጠናል፡፡ የአብዛኞቻችን ታሪክ ከጽሁፉ ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ በነገሮች ሁሉ “ነገር ሁሉ ለበጎ ነው” ብሎ ማለፍ ምንኛ መልካም ነው፡፡
ወስብሀት ለእግዚአብሔር!
ገነት ቀፀላ (ወንጂ)
when I read it I am so glade.thank you
ReplyDeleteit is interesting real stiry. thanks. KHY
ReplyDeleteakalu wondemachen danaiel kebret bemgemria yamlakachen yeysus kerstos tega yebzalehna lemsraw sera hulu egziabher kenatu kekdest dengel maryam gar yechmerleh zemenu newna men yedregal sewoch gena bezu enaweralen lemen bebal dekamoch nenna sew yemilewen kefu wory satesma ende betkrstyan legenteh yebtekrstyanen seratna tarik sera gezen legziabher mestet telk hawaryanet newna egziabherem besrah yektleh elalehu !
ReplyDeleteabetu Getahoy ye anten hasab man yawukewal, ke ante endanmuwaget libona siten.
ReplyDeleteDani may the blessing of God pour on u.
Yegrmal
ReplyDeleteDani,
ReplyDeleteThis is really an impressive story ,it really tells us the one thing that we should never forget i.e to ask God "atetewen ateraqenem" because it is only His presence in our life that protect us from making the mistakes we would commit if we were on our own.There could be many unanswered questions in life still at this moment there are such unanswered prayers.
From this true story of this woman I have learned that those unanswered prayers are maybe meant to remain answered or even not the right time to be answered ,this is my take for what it worths Daniye
Thank God for my unanswered prayers
እኛ የሚያምረንን፣ እርሱ ግን የሚያምርብንን፤ እኛ የምንፈልገውን፣ እርሱ ግን የሚያስፈልገንን ያደርግልናል፡፡ Wow it is Great Advice! God Bless U Forever!!
ReplyDeleteChil_Get
Bahir Dar
በእውነት ታሪኩ የሚመስጥ እና እጅግ አስተማሪ ነው፡፡ ሁላችንንም ህይወታችንን እንድንመረምር ይረዳናል፡ እግዚአብሔር ይባርካችሁ! እንደተጨማሪ አስተያየት ግን ልጅቷ “ስላላደረክልኝ አመሰግንሃለሁ” ያለችው በመጨረሻው ሰዓት አጎቷ ሀብታቸውን ሲያወርሷት ከአገር አለመውጣቷ እንደጠቀማት ስታውቅ ማለትም እግዚአብሔር መልካም ነገር እንዳደረገላት ልክ ሲገባት ነው፡፡ ስለዚህ “ስላደረክልኝ አመሰግንሃለሁ” ማለትስ አትችልም? እንደክርስቲያን እግዚአብሔር ፀጋውን የበለጠ ቢያበዛልን ግን ሰዎች መከራን ካለፍነው በኋላ ብቻ ሳይሆን በመከራ ውስጥም ሆነን የፈለግነው ነገር አልሳካ ሲለን እግዚአብሔር በዚህ ላይ ዓላማ እንዳለው በማሰብ አስቀድመን “ስላላደረክልኝ አመሰግንሃለሁ” ማለት ብንችል ምን ያህል ደስ ይላል?
ReplyDeleteከእኛ ይልቅ ለኛ ያውቃልና፡፡ እኛ ከመረጥነው እርሱ የመረጠው ይበልጣልና፡፡ የጠየቅኩትን ከለከለና የመረጠልኝን ሰጠኝ፡፡ እኛ የሚያምረንን፣ እርሱ ግን የሚያምርብንን፤ እኛ የምንፈልገውን፣ እርሱ ግን የሚያስፈልገንን ያደርግልናል፡፡
ReplyDeleteወንድማችን ዳንኤል አመሰግንሃለሁ፡፡ አንብቤ ስጨርስ አንተ ያልከዉን ብቻ ማለት ለኔ በቂ ሆኖ አገኘሁት፡፡
ReplyDelete«ለርእስዬ እም ርእስዬ እስመ አንተ ትቀርቦ - ለእራሴ ከእራሴ ይልቅ አንተ ትቀርበዋለህ»
ለካ እኔ ለእኔ አላዉቅም፡፡
ግሩም ግብርከ ...