እነሆ ታክሲ ይዤ ከሲ ኤም ሲ ወደ መገናኛ ለመሄድ መንገድ ዳር ቆሜ ነው፡፡ እነዳጋጣሚ አንዲት ዲ ኤክስ መኪና ከፊቴ ቆመች፡፡ የምታሽከረክረው ልጅ በእጇ እንድገባ ጠቆመችኝ፡፡ «ስታስተምር ስለማውቅህ ነው» አለችኝ፡፡ አመስግኜ ጋቢና ተቀመጥኩ፡፡ የተቀመጥኩበት ወንበር ላይ በመስተዋት የተለበጠ ጥቅስ ነበረበት፡፡ መስተዋቱ የተያያዘበት ፍሬሙ በአበባ ያጌጠ ነው፡፡ ምናልባት ለሰው ልትሰጠው ያዘጋጀችው መሆን አለበት፡፡ እንዳጋጣሚ ጥቅሱን አንሥቼ ከኋላ ወንበር ላይ ሳደርገው «ስላላደረግክልኝ ነገር ሁሉ አመሰግንሃለሁ» ይላል፡፡
የጻፈው ሰው ስሕተት ሠርቷል፡፡ መሆን የነበረበት «ስላደረግክልኝ ሁሉ» ነው፡፡ በስሕተት አንድ ተጨማሪ «ላ» አስገብቶበታል፡፡ ልንገራት ወይስ ልተወው እያልኩ አመነታሁ፡፡ ነገር ግን ይህንን ስሕተት ላታስተውለው ትችላለች ብዬ ስላሰብኩ መንገሩን መረጥኩ፡፡ «ጥቅሱን የጻፈልሽ ሰው ሳይሳሳት አይቀርም» አልኳት ቀስ ብዬ፡፡ «እውነትክን ነው» አለችና አንድ እጇን ወደ ኋላ ልካ ጥቅሱን ወደ አምጥታ አየችው፡፡ «የቱ ጋ ነው ባክህ የተሳሳተው» አለችኝ፡፡ «ስላደረግክልኝ ለማለት ፈልጎ ስላደረግክልኝ ብሎታል» አልኳት በጣቴ ፊደሉን እያሳየሁ፡፡ «እርሱን ነው እንዴ፤ አይ ፈልጌው ነው» አለች ጥቀሱን ወደ ቦታው እየመለሰች፡፡
«ስላላደረግክልኝ የሚለውን ነው የፈለግሽው?»
«አዎ፤ አይባልም እንዴ»
«ሰምቼ አላውቅም»
«ለሌላ ሰው ላይሠራ ይችላል፡፡ ለኔ ግን ይሠራል»
«እንደዚህ የሚል ጥቅስ ግን ያለ አይመስለኝም»
«ይህ ከሕይወት መጽሐፍ የተገኘ ጥቅስ ነው» አለችና ፈገግ አለች፡፡
«የቱ ነው ደግሞ የሕይወት መጽሐፍ?»
«እያንዳንዱ ሰው የየራሱ የሕይወት መጽሐፍ አለው፡፡ በዚያ መጽሐፍም በሕይወቱ ያገኛቸው ነገሮች ተመዝግበዋል፡፡ በዚያ መጽሐፍ በሕይወት ተፈትነው የነጠሩ ምርጥ ምርጥ ጥቅሶች ይገኛሉ»
«ፈላስፋ ነገር ሳትሆኚ አትቀሪም»
«አንተም የሕይወት መጽሐፍህን ካነበብከው፤ ፈላስፋ መሆንህ አይቀርም፡፡»
«ግን ለምንድን ነው ስላላደረግክልኝ ሁሉ አመሰግንሃለሁ ያልሽው»
አየህ እያንዳንዱ ጥቅስ ከጀርባው የሚጠቀስ ታሪክ አለው፡፡ ታኩን ካላወቅከው ጥቅሱ በደንብ አይገባህም»
«እስኪ በደንብ እንዲገባኝ ታሪኩን ንገሪኝ»
«እንዲህ በቀላሉ ያልቃል ብለህ ነው»
«አንድ ቦታ አቁመን ለምን አትነግሪኝም»
«ይህንን ያህል ያስፈልግሃል?»
«በጣም አጓጓኛ፤ ስላላደረግክልኝ ሁሉ አመሰግንሃለሁ የሚል ሰምቼ አላውቅማ»
መገናኛ ስንደርስ ወደ አንድ ጥግ አቆመች፡፡ እናም እንዲህ ነገረችኝ፡፡
ይቀጥላል
ምነው ምነው አጉል ቦታ ቆረጥከው ።መጨረሻውን ለማወቅ ጓጓሁ ።
ReplyDeleteይባላል፡፡!!! አባባሉ እምብዛም ባይለመድም ምክንያቱም ስላደረገልህ ብቻ ሳይሆን ስላላደረገልህም ማማስገን አለብህ፤ ያላደረገልህ ላንተ(ላንቺ) የማያስፈልግ(የሚጎዳ) ይሆናልና፡፡ ስለዚህም ልጅቷ ‹‹ስላላደረግክልኝ ነገር አመሰግናለሁ›› ማለቷ እጅግ እጅግ እጅግ በጣም ትክክል ነች፡ ይኼውም በጣም የረቀቀ የፈላስፋዎች ንግግር(አባባል) ነው፡፡
ReplyDeleteትክክለኛ የሕይወት ጥቅስ!
ReplyDeleteበጣም ወድጄዋለሁ
ታሪኩን ለመስማት ጉዋጉቻለሁ!
tanks DANI! berta itis exactly true tiks new!
ReplyDeleteያጎጎል
ReplyDelete"እግዚአሔር አምላካችን ስላደረገልን ብቻ ሳይሆን ስላላደረገልንም ነገር ማመስገን አለብን ያለደረገው እኛን የማይጠቅም ስለሆነ እንጂ ለሌላ አደለም" ድምጸ ተዋህዶ ቁጥር 2 ቁጥር አራት SEMAETENETE ...
ReplyDeleteወስብሃት ለእግዚአሔር
Hi daniel i am so eager about what she will say ,come to think of it i agree with her ,there are somethings we beg God to do for us but he might not do it and after sometimes we thank God for not giving us that wish this happend to me so----
ReplyDeleteI am waiting what she gonna say
ReplyDeleteShe was Correct!!
ReplyDeletethis is an interesting story . i apprecaiate your creativity otherwise it is a common quatation which u want to teach us. any ways i am eager to read the real or created story. Let God bless u!!
ReplyDelete«ስላላደረግክልኝ ነገር ሁሉ አመሰግንሃለሁ» Amen Mecheme Yetederegelete bezu yetekebele newe ena i say again «ስላላደረግክልኝ ነገር ሁሉ አመሰግንሃለሁ» Will be looking forward to hear from the story!!!
ReplyDeletekezas men hone....? wey leb sekela
ReplyDeletedani ye ante neger betam yemigerim new gin egziabherin yetyekeciwin yemitawikew ersua nat gin bene bekuil alismamam gin lemefired mecheresawi min yihon yezia sew yibelen dani ye account neger endatresa
ReplyDeletethat is very nice, behulum ende-eyob mamesgen malet endezihe new especially showing it in practice looks challenging & painful but for those who really do it, they will get the grace of God abundantly.
ReplyDeleteAmlak yatsinash our sister!
ዳኒ
ReplyDeleteቀጣዩን ልጅቷ የነገረችህን ገጠመኟን ሳትተርከው ብትተወው, በጣም ጥሩ ነበር
ምክንያቱም : ዋናው መልእክቱ በበቂ ሁኔታ ስለተላለፈ ነው ::
ይህ ጥቅስ : የሁሉንም ሰዎች ማንነት ያሳያል
የልጅቷ ነገር ከተተረከበት ግን :
ወደሷነቷ ያደላልና
Geta hoye seladerekelegne ena selaladerekelegne negere hulu amesegenehelahu
ReplyDeleteምነው አጉል ቦታ ቆረጥከው ነበር ያልኩት ግን ማንኛውም ሰው በህይወቱ ዙርያ አምላክ ባደረገለትም ባላደረገለትም፡፡
ReplyDeleteከራሱም ሆነ ከሌላ ሰው በዚሁ ጥቅስ እንዲወያይ መሰለኝ
አምላክ ኢትዮጵያን ይባርክ
አሜን::
ፍቅርተ ማርያም
Hi hi there really i apriciate the explanation , some time such unusuall terms has a great meaning throught our life so i like the topic it is good prespective....thanks.
ReplyDeleteAnaniya
በጣም የሚገርመው ልጅቱን ትክክል ነች ትክክል አይደለችም ከማለት ይልቅ አባባሉ ከአባባልነት አልፎ ከዚህ በፈት የምታውቁትም አሁን ያነበብነውም፡
ReplyDelete1ኛ.የህይወት ፍልስፍናችን ነው ወይ?
2ኛ.ለማድረግ ምን ያህል ቆርጠናል?(ቢያንስ በአሳብ)
የህይወት ተምክሮዋ ያስተምረናል ብዬ አስባለው በጉጉት እጠብቃለው
አመሰግናለው፡፡
ዕፁብ ድንቅ ውእቱ!!!
ReplyDeleteHi dani I am also eager to know what she is going to say because it is also new to me.
ReplyDeleteመቼም የሚያብረቀርቅ ሁሉ ወርቅ አይደለም። በራሳችን እይታ የሚያምር መስሎን እንዲደረግልን የጠየቅነው ሁሉ እንደማይጠቅመን ቀድሞ የሚያውቅ እግዚአብሔር ባያደርግልን ለጊዜው ባያስደስተንም ጊዜው አልፎ ስናየው ግን የለመንነው ባለመደረጉ እናመስግናለን።
ReplyDeleteብልህ ያመቱን ሞኝ የለቱን... ይባል የለ።
I would say God has to be thanked for all the things He is doing to us and for those things He does not do. Because we dont know why He didnt offer us. May be it is because we wish something which is not appropriate to us(or bad to us). At least I know in my life, I wished something which I now regret for wishing...I now thank Him for He didnt do it as to my wish...I am now in fair mind to judge my wish that time and to say "that was the wrong wish I ever asked God to do me"
ReplyDeleteYakoyen!
Blesses!
I am sure she has a story behind it. It absolutely makes sense to me. Sometimes we desperately wish something to happen for us because we think that is the best thing. When God doesn’t make it happen, we realize later though that we were wrong and God in fact did the best thing for us by not letting that "best" thing to happen to us.
ReplyDeleteየቅዱስ ያሬድን 1500ኛ ዓመት ለማክበር የበኩልዎን ለማድረግ ዝግጁ ነዎት?
ReplyDelete87%+1%+10%=98% ሁለቱ ፐርሰንት የት ነው(2%)
ያገራችን ሰው እኮ ባንድ በኩል የ ያሬድ በሌላ ወገን ደግሞ የነፑሽኪን ዘር አይደል …..ይሄኛውም ለምስጋናህ አመሰግናለሁ እንደማለት መሆኑ ነው፡፡ መጨረሻው ናፍቆኛል…
ReplyDeleteDear Dn Daniel,
ReplyDeleteAddis Neger gazeta lay "kalmotk Ayigedluhem" yemilewn tsihuf lemin ena leman endetsafkew ebakihin astawkegn. email: zerihun2992@yahoo.com
Betam asfelagi silehone new::
selatadaragalen becha sayhone selaltadaragalenem nagare benamasagen awakenate neaw.b/se ledaragelene kaltagaba aydaragelnemena.
ReplyDeleteብዙ ጊዜ የማናደርገው ነገር ግን መሆን ያለበት ነገር ነውና ልጅቱ የጠቀሰችው ጥቅስ በጣም ደስ ይላል፡፡ ሊያድነንም ይሁን ሊገድለን ያላደረገልንን ሲመስለን እንኳንስ ልናመሰግነው ያላደረገበትን ምክንያት እንኳን አንጠይቀውም አንጠብቀውምም፡፡
ReplyDeletedoes it have another version? I mean for Ladies if so I want to have one
ReplyDeletethanx
የምንፈልገውን ሳይሆን የሚያስፈልገንን የሚሠጠን እግዚአብሔር ይመስገን
ReplyDeleteየልጅቷ ታሪክ በጣም ያሳዝናል ማለት እግዚአብሄርን ከሱ በላይ ለኔ ራሴ አውቃለሁ ብለን ስናስጨንቀው መልካሙን የሚሰጥ ደግ አባት መሆኑን አይቼበታለሁ በራሴ ልብ የሚነካ ታሪክ ነው፡፡ መልካም ነገር ስላዘጋጀላት ዛሬ ደስ በሚል ህይወት ውስጥ አለች ፡፡ ዳንኤል እንደዚህ ዓይነት ጥሩና አስተማሪ ታሪኮችን ብታስደመምጠን ጥሩ ነው፡፡
ReplyDeleteI know Im very slugish to say even U think what type of person he is? But no matter how i delay and whomever im realy touched when I saw the story! Daniel! I agree, completely with this sister's idea!Yea some times the Almighty God does not answer all our requests of our life cause He knows they would not be good for us! So we thank Him that He didnt do that and not allow it happend!keep our prayer life! Glory to him!
ReplyDelete