Sunday, July 11, 2010

በአንድ ሱቅ ታዛ ሥር

ሲ ኤም ሲ፣ ከሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት፣መንገዱን ተሻገርኩና፣ ቆምኩ፡፡ ዓላማየ ሰው መጠበቅ ነበርና ሲዘገይብኝ ጊዜ ጋዜጣ ገዛሁና ከፀሐዩ ለማምለጥ ወደ አንድ ሱቅ ታዛ ተጠጋሁ፡፡

በሱቁ ውስጥ አንዲት ሴት እና አንድ ወንድ ቆመዋል፡፡ ከውጭ ደግሞ አንድ ሌላ ሰው የሱቁን መስኮት ተደግፎ ወደ ውስጥ ጫቱን እየቃመ ያወራቸዋል፡፡ ከዚያ ደግሞ አንድ ደንበኛቸው መጣ፡፡

«አንተ ፔጅ ከማድረግ ውጭ አታውቅም እንዴ? ምናለ አንዳንድ ቀን እንኳን ብትደውል» አለው በሱቁ ውስጥ ያለው ሰው በወዳጅነት ስሜት፡፡

«ካርድ ስላልሞላሁኮ ነው» አለው ትከሻውን በመስኮቱ ዘልቆ በትከሻው እየገጨ፡፡

«ያደላቸው መንፈስ ይሞላሉ፤ አንተ የሃያ አምስት ብር ካርድ መሙላት ያቅትሃል?» አለችው በሱቁ ውስጥ ያለችው ልጅ፡፡ ሁሉም ሳቁ፡፡

«ሲያቀብጠኝ ትናንት ኳስ አያለሁ ብዬ ገንዘቤን ጨረስኩ» አለ የመስኮቱን መደገፊያ እየደበደበ፡፡

«ቤትህ አታይም ምን ሌላ ቦታ ወሰደህ?» አለችው ሻጯ

«የተመታ ኳስ እናቀብላለን ትላላችሁ አሉ፡፡ »

«ማን»

«እዚያ በትልቅ ስክሪን የምታዩት ናችኋ፡፡ ኳስ ተመትቶ ፊት ለፊት ሲመጣ ወደ እናንተ የመጣ መስሏችሁ ልታቀብሉ ትነሣላችሁ አሉ፡፡»

«የዓለም ዋንጫ አይደለምኮ ሰበታ ወርጄ ነው» አለ እንግዳው ከሚወርድበት ትችት ለመራቅ ብሎ፡፡

ሰበታ ሜዳ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ደደቢት መጫወታቸውንና በጨዋታውም ችግር መፈጠሩን ሰምቼ ነበር፡፡ ይህ ሰው የሚያወራው ይህንን መሆን አለበት፡፡

«ዳኛ በቴስታ ሲመታ ለማየት ነው የሄድከው» አለና የሱቁን መደገፊያ ተደግፎ ጫት የሚያመነዥከው ሰው ሳቀበት፡፡

«ኳስ በቴስታ መትተው ጎል ማግባት ሲያቅታቸው ዳኛ በቴስታ መማታት ጀመሩ፡፡ እግር ኳስ እና ቦክስ ተቀላቅሎባቸዋል»

«እንኳንም በዓለም ዋንጫ አልተሳተፍን» አለች ሴትዮዋ፡፡

«እንዴት?» አላት ሱቁ ውስጥ አብሯት የቆመው ሻጭ፡፡

«ዳኛውን ሁሉ በቴስታ እየመቱ ሀገሪቱን ጭራሽ ከእግር ኳስ ያስባርሯት ነበራ»

«እኔኮ የማይገባኝ ሰው በዚህ ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ በማስረዳት፣በመከራከር እና በሕግ መሥመር በመሄድ ሃሳቡን ያራምዳል እንጂ እንዴት በኃይል ያምናል፡፡» በሱቁ ውስጥ ያለው ሰው ነበር ይህንን የተናገረው፡፡

እንግዳው ሰውዬ እጆቹን አወናጨፈና «ባካችሁ እርስሱን ተውት የኢትዮጵያ ኳስ እንደሆነ አያልፍለትም፡፡ ምን እንደ ተባለ ታውቃላችሁ፡፡»

«ደግሞ ምን ተባለ? አታመጣው የለህ» አለ ጫቱን የሚቅመው ሰው፡፡

«ኢትዮጵያ፣ኬንያ፣ዑጋንዳ እና ቻይና ለዓለም ዋንጫ የሚበቁበትን ዘመን ለመጠየቅ ወደ አንድ ጠቢብ ዘንድ ሄዱ አሉ፡፡ ኬንያ ጠየቀች፡፡ ከሃያ ዓመት በኋላ የባለች፡፡ ዑጋንዳ ጠየቀች፡፡ ከአሥር ዓመት በኋላ ተባለች፡፡ ቻይና ጠየቀች ከአምስ ዓመት በኋላ ተባለች፡፡ በመጨረሻ ኢትዮጵያ ጠየቀች፡፡ ያን ጊዜ ጠቢቡ መልስ መስጠቱን አቆመና አለቀሰ ይባላል፡፡

ያን ጊዜ ኢትዮጵያ ገረማትና «ለምን አለቀሱ» አለችው ጠቢቡን «የተጨዋቾቻችሁ ጠባይ እና የፌዴሬሽናችሁ አሠራር ዘመኑን ለማየት ስለ ጋረደኝ ነው» አለ ይባላል፡፡

«አታመጣው የለህ፤ ለመሆኑ ያ ነገር ዋጋው ወረደ ወይስ እንደ ወጣ ነው» አለው ወንዱ ባለ ሱቅ፡፡

«አንተ ደግሞ እዚህ ሀገር ላይ የሚወርድ ባለ ሥልጣን እንጂ የሚወርድ ዋጋ አይተህ ታውቃለህ? ይልቅስ አሁኑኑ ብትገዛ ይሻልሃል» አለው እየሳቀ፡፡ «አንዱ ምን እንዳለኝ ታውቃለህ? መኪና ልገዛ ሄጄ አሁንኮ ገበያው ቀንሷልና ትንሽ ቀንስልኝ ስለው እዚህ ሀገር የሚቀንስ ነገር የለም፤ የሚቀንሰው ፍቅር ብቻ ነው አለኝ እውነቱን ነው፡፡

«ያ ጓደኛህ ሊሄድ ነው አሉ?»

«የት?»

«አሜሪካ ነዋ»

«አልሰማሁም፤ ማን ነገረህ?»

«ራሱ ነው የነገረኝ»

«እርሱንኮ ስትሰማው ቫቱን እየቀነስክ መሆን አለበት»

«እንዴት?»

«ትንሽ ይሰጣላ፤ በቫት ነው ያለ ቫት ብለህ ማጣራት አለብህ»

/ይህ ነገር እኔንም ገረመኝ፡፡ እውነትምኮ አንዳንድ ነገሮችን ከቫት ጋር እና ያለ ቫት መሆናቸውን ማጣራት ያስፈልጋል፡፡ አንዳንዱኮ 15 % እየጨመሩ ሊያወሩ ይችላሉ፡፡ እናም ዋጋውን ከቫቱ ለይቶ መስማት ያስፈልጋል/

«እውነትህን ነው፤ እርሱኮ ሁል ጊዜ ማማረር ነው የሚወድደው፤ እንደ እርሱኮ ኢትዮጵያ ሲዖል ናት፡፡ ጨለምተኛ ነው» ጫት ቃሚው ነው ይህንን የሚለው፡፡

«እዚህ ሀገር ሰው ሆኖ ከመኖር አሜሪካ ሄዶ ውሻ ሆኖ መኖር ይሻላል ካለኝ ወዲህ ጠልቼዋለሁ፡፡» አለች ልጂቱ፡፡

«ተይው ባክሽ እዚህ በየሜዳው መጸዳዳት ለምዶ፣ አሜሪካ ገብቶ እንደ ቡችላ በፖፖ ተቀመጥ ሲባል ምን ሊል ነው?» በእንግዳው ንግግር ሁሉም ሳቁ፡፡

«እኔኮ የማይገባኝ ነገር እዚያ ሀገር ደርሰው የሚመጡት አትምጡ ይቅርባችሁ ማለት ነው የሚወዱት፡፡ ታድያ እነርሱ ለምን ጠቅልለው አይመጡም፡፡ እኛን አትምጡ ብለው እነርሱ ይሄዳሉ፡፡ »

«እሱና ይኼ ተቃራኒ ናቸው» አለች ልጂቱ በግራ እጇ ጫት ቃሚውን እየጠቆመች፡፡ «ይሄ ለራሱ ያለ ኢትዮጵያ አገር የለም፡፡ ገነት ያለችው ኢትዮጵያ ነው፡፡ ሰው ለምን ሀገሩን ለቅቆ ይሄዳል፤ ምናምን ይላል፡፡ ያኛው አገር አያሳየኝ ይላል፡፡ እኔስ ጠይም ሰው አማረኝ»

«እኔ አለሁልሽ አይደል እንዴ?» አላት ሱቁ ውስጥ ያለው ጎልማሳ፡፡

«እኔ መች የሰው ጠይም ፈለግኩ፤ የሃሳብ ጠይም እንጂ»

«ደግሞ የሃሳብ ምን ጠይም አለው» አለ ጫት ቃሚው ሰው ጢሙን እያፍተለተለ፡፡

«አለው እንጂ፡፡ ጥቁርም ያልሆነ፣ ነጭም ያልሆነ ሃሳብማ አለ፡፡ የጥቁሩንም ንጣት፣ የነጩንም ጥቁረት የሚያሳይ ጠይም ሃሳብማ አለ፡፡ ስለ ጥቁሩ ጥቁረት፤ ስለ ነጩ ንጣት ብቻ ሳይሆን ሌላውንም ገጽታቸውን የሚያሳይ ጽንፈኛ ያልሆነ ጠይም ሃሳብማ አለ፡፡»

«አፌ ቁርጥ ይበልልሽ የኔ ፈላስፋ፤ በስሕተት ነው አንቺ ሸቀጥ ሻጭ የሆንሺው፤ መጽሐፍ ሻጭ ነበር መሆን የነበረብሽ» አለ ባለ ጫቱ እየሳቀ፡፡

/ ጠይም ሰው አማረኝ? አባባሏን ወደድኩላት፡፡ ጽንፍ በበዛበት ቦታ ጠይም ያምራል፡፡ እኔም ብዙ ቦታ ወይ ነጭ አለያም ጥቁር ነው የሚያጋጥመኝ፤ መሐል ቦታ ቆመው ሁለቱንም አይተው ሊገልጡ የሚችሉ ጠይሞች ያስፈልጉናል፡፡/

በዚህ መሐል አንድ የሰማይ ስባሪ የሚያህል ሰው ወደ ሱቁ ታዛ ገባ፡፡ ከዚያም ሲጋራ ጠየቀ፡፡ ሰውየው መስኮቱን ሲደገፍ ሁሉም መስኮቱን ለቀቁለት፡፡ ሰውዬውም ብቻውን መስኮቱን ሞላው፡፡ ይባስ ብሎ ደግሞ በእጁ ዳቦ ይገምጣል፡፡

ሰውዬው ሲጋራውን ገዝቶ እንደሄደ ጫት ቃሚው ሰውዬ «ይሄ ሰው ግን የዘመዶቹን ሁሉ ኪሎ በአደራ አስቀምጦ መሆን አለበት» አለ ሰውዬው የሄደበትን መንገድ በጎሪጥ እያየ፡፡

«ባክህ ሲርበው ከራሱ ሥጋ እየበላ ነው፡፡»

«በምግብ እህል ራስን መቻል ማለት ይሀሄ ነዋ» ዘሁንም ተሳሳቁ፡፡

እንደ ሰውዬው ሲጋራ ሊገዛ የፈለገ ደንበኛ ወፍራሙ ሰውዬ እልፍ ከማለቱ መጣ፡፡

«ሳቢ እስኪ» አላት ልጅቱን፡፡

«እዚህ ቤት ዛሬ ተቃራኒ ብቻ ነው እንዴ የሚመጣው» አለች ልጅቱ እየተንፈ ቀፈቀች፡፡

«እንዴት ማን መጣ ደግሞ» ሲጋራ ገዥው ጠየቀ፡፡

«ቅድም ለምድር ለሰማይ የከበደ ሰው መጥቶ ሱቁን ዘጋው፤ አሁን ደግሞ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ሽቦ የመሰለ ሰው መጥቶ ልብስ ልናሰጣበት ነበር፡፡»

«ያ ሰውዬ የሆነውን ታውቂያለሽ?»

«ምን ሆነ ደግሞ? ቀጭኔዎች ቀንታችሁበት ነው?» ልጅቱ መለሰችለት፡፡

«ላይተር ስጭኝና እነግርሻለሁ» ላይተሩን አውጥታ ለኮሰችለት፡፡ እኔም ጢሱ አላስቀምጠኝ ሲል ፈቀቅ አልኩ፡፡

«አንድ ጊዜ» አለ በሲጋራው ጢስ ክብ እየሠራ፡፡ «ሰውዬው በሬ አርዶ ቅርጫ ሊያከፋፍል ይነሣል፡፡ በሬውን ከካራ ገዝቶ በሌሊት ለማረድ አራጅ ይነጋገራል፡፡ ሌሊት አስራ አንድ ሰዓት ከአራጁ ጋር ይነሣና ወደ ቅርጫ ቦታው ይሄዳል፡፡ እዚያ እንደ ደደረሰ ለካስ አራጁ ሌሊት ሲቀመቅም አድሮ አንጎበሩ አልለቀቀውም፡፡ በሬውን ለመጣል አናቱ አካባቢ በትክክል ሳይወጋው ይቀርና በሬው መልሶ ይነሣል፡፡ በዚህ ጊዜ ይሄ ወፍራም ሰውዬ ተዋረድኩ ይልና የበሬውን ሁለት ቀንዶች ጥርቅም አድርጎ ይይዛል፡፡

በሁለት እጁ ቀንዱን ጥርቅም አድርጎ እንደያዘ እንደምንም ታግሎ በሬውን ይጥለዋል፡፡ በሬው መሬት እንደ ወደቀ ወፍራሙ ሰውዬ እየጮኸ «እረደው ቶሎ እረደው» ይለዋል አራጁን፡፡ አራጁ ግን ቢላዋውን እያፋጨ ዝም ብሎ በሬውን ይዞረዋል፡፡ ወፍራሙ ሰውዬ «ኧረ እባክህ እረደው ደከመኝ» ይለዋል አንጎበሩ ያልለቀቀው አራጅ በሬውን እየዞረ ቢላዋውን ያፋጫል፡፡

በዚህ መካከል አንድ ጓደኛው ይደርሳል፡፡ በሬ ከሥር ወፍራሙ ሰውዬ ከላይ አንደሆኑ፡፡ የጓደኛውን መምጣት ሲያይ ወፍራሙ ሰውዬ «ኧረ እባክህ እረደው በለው» ይለዋል፡፡ ጓደኛውም አራጁን «እረደው እንጂ ለምን ትዞረዋለህ?» ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ አራጁም «እኔኮ ከሁለቱ በሬው የትኛው እንደሆነ መለየት አቅቶኝ ነው» አለው ይባላል፡፡ »

«ይኼ አንድ ሲጋራ ያሸልማል» ብሎ ጫት ቃሚው እየሳቀ ጋበዘው፡፡

እኔም የቀጠርኩት ሰው መጣና ቀጣዩን ሳልሰማ ጥያቸው ሄድኩ፡፡


ይህ ጽሑፍ ባለፈው ቅዳሜ በሮዝ መጽሔት ላይ ወጥቷል

22 comments:

 1. +++

  Awo Dani, Sent Ale Be Menderu,Be Menged,Yemibale Leb Belo Lesemaw Yemiyasik, Timhertem Yemihone Endih Endante Degemo Sinageru Yesema Bicha Sayihone Kale Meteyik Endarege Sew Beleb Ketbo Yizo Lelelawe Madrese..Lemen Endene Yalew Endezih Bele Tebelo Telko Enquan Betkekle Melket Ayadersem...Bel Amelak Ahunem Tsegawen Berketun Abezeto Yistihe....Ante Bicha "Tsegahen Getalegni" Endatle Gena Bizu Entebekalen.

  Kemidre Germany

  ReplyDelete
 2. Thank you Dn Daniel.

  Entertaining and educative satire.

  ReplyDelete
 3. I missed everything, i mean EVERYTHING. Home sweeeeeet home!

  ReplyDelete
 4. dani it is serious we need to know about the current condition of our church about pops prize and kesis solomon try to tell us in irony about your opinion

  ReplyDelete
 5. Dear Dn. Daniel, Thank you for another magnificent issue!
  "ጠይም ሃሳብ"? ለዛ አለው ውበት አለው፡፡ It reminds me of something I read on one of Bewketu Seyoum's books, where one of his characters was saying something like this "በነሡ እይታ ብርሓን ካልሆነ ጨለማ ነው ይላሉ ድንግዝግዝ ያለ መኖሩን አያውቁም, ቀኝ ካልሆነ ግራ ይላሉ መካከለኛን አላስተዋሉም..." ገጸ-ባህሪው ይቀጥላል እኔ ግን ጥቅሴን በዚእ ልወሥን፡፡ የበውቀቱም ሆነ ሱቅ ውስጥ ያለችዋ ልጅ ሐሳብና ምኞት እንድ ይመስለኛል, "ከሁለት ጎን ያሉ እይታዎችን ያገናዘበ, ከወገንተኛነት የራቀ, ፅንፈኛነት ያልወረሰው የሐሳብ መድረክ ማግኘት፤ ነጭ ካልሆነ ጥቁር ነው መባሉ ቀርቶ መሃል ላይ ያሉ የቀስተ ደመና ቀለሞች የሚታዩበት አለም" ነው የተመኙት። ጵንፈኛነት (or extrimism) የተወደደበት አንድ ቦታ መኖሩን አንዘንጋ, መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ (ካልተሳሳትኩ በብሉይ ኪዳን)እግዚያብሄር ከነገስታት ወይንም ካገልጋዮቹ ለአንዱ በላከው መልእክት ሙቅ ወይንም ቀዝቃዛ አልሆንክምና ለብ ያለ በመሆንህ አዝኜብሃለው ያለው አስረጅነት አለው (would you please add the Bible book and verse where God had said such a thing? I'm also ready to be corrected.
  Thank you again for raising an important issue, thank you for making us discuss it!
  Stay Blessed!

  ReplyDelete
 6. Dn.Dani hulun beyebotaw tastewulaleh,
  yesew hulu amelekaket beteleyayu gudayoch min yahil yileyayal? adamachena asteway sew kale keyebotaw ayale kum neger yemihonu gudayoch ayitefum. "Mastewal yalebin gin ende aredadachin meten betsuhufu wust bizu mistirawi kum nederoch magnet endeminichil new "
  sirahin bebizu nafkot entebikalen ....
  amilak yitebikih
  Ethiopiawiw negn

  ReplyDelete
 7. EgziAbher yistlin D/n Daniel. Fegeg yemiyareg chewata new yasnebebken .

  ReplyDelete
 8. በጣም ተመችቶኛል በጣም እየሳኩኝ ነው ያነበብኩት
  ግን አንዳንዴ የሚገርመኝ ነገር እኛ ቃሚ፣ጠጪ፣አጫሽ ከምንላቸው ሰዎች እንዲ ከልብ የሚያስቅና ቁም ነገሮች(መውሰድ ለቻለ)ይገኛል፡፡ እንደኔ ግምት አሳባቸው "ጠይም" ስለኦነ ይመስለኛል፡፡ እኔ አስተሳሰቤ ጠይም ስላሎነ ቀልዶቹን ለመሸምደድ እየሞከርኩኝ ነው፡፡ ቁም ነገሩን በጥቂቱ........
  ሰላም
  እናመሰግናለን

  ReplyDelete
 9. Would you like to go back to the arcade of that shop and record the second part of their dialogue?

  Just to humor! anyways we can see that how our people could create and escalate ideas.

  But what is our missing file??

  ReplyDelete
 10. Hi Danny

  Just read this in the morning at the office before I started work. The whole day I was laughing. Thank you for sharing such a delightful occurrence of your day that was full of humour.

  Refreshing

  ReplyDelete
 11. አይ ዳኒ፡
  መችም አያልቅብህ? እንዳለፉት ባይሆንም ያዝናናል። በርታልን።

  ReplyDelete
 12. እንኳን ለሁለቱ የወንጌል ገበሬዎች የሰማዕት ቀን በሰላም አደረሰህ፡፡አይ ዳኒ እንዲያዉ ጸጋዉ እግዚአብሔረ እዲያበዛልህ ጸሎትና ምኞቴ ይሁንልኝ እንጂ እኔማ ደካማዉ ምአለኝ፡፡ ሁልጊዜ የምትነግረን ሁሉ አዲስና አዝናኝ እንዲሁምአስተማሪዎች ናቸዉ፡፡ሁሌም ከስራ ስገባ እና ስወጣ ብሎግህን ሳላየ አልወጠም ዳኒ ብዙ የማላዉቃቸዉን አሳዉቀኸኛል፡፡ለምሳሌ አለቃ ገብረ ሃና ተራተ ይመስሉኝ ነበረ ይኸዉ ከአንተ እዉነታዉን ተመገብሁ፡፡በተለይማ ስለ እፄ ቲዎድሮስ ያስነበብኸኝ በጣም ነዉ በዉስጤ ሲመላለስብኝ የነበረን ቁስል የነካህብኝ፡፡ለማነኛዉም ብሎግህን ከአንደ ዲያቆን ጋጓደኛየ ነዉ ያገኘሁ እናመም ብሎግህን ብዙ ሰዉ ቢያዉቀዉ ሊርበት ይችላል ብየ አስባሉ እግዚአብሔር ያበርታህ፡፡

  ReplyDelete
 13. Dani,
  endhe aynete ye ager bete wegoche yenfekunale ena ke kume negeru bashager endhe aynet wegochen jeba belen yemechalu.
  Azeb ze Minnesota

  ReplyDelete
 14. ayimetinim, please focus on more serious matters and bigger issues. yihenima manim yitsifewal eko...bekeldim enisemawalen.

  focus on politics, attitude, religion, family etc issues.

  ReplyDelete
 15. dear anonymous,

  I think this satire has lots of serious issues. It is our responsibility as reader to dig out what is inside this funny like article. Do not expect everthing in bold.

  Thanks bro for this educative and entertaining content. I just went back home in my memory.......

  Tesfa
  Seattle

  ReplyDelete
 16. @ July 13, 2010 2:40 AM

  Endenie endenie yih tsihuf keminim belay asfelagi ena astemari new biye asibalehu.Ke kelidoch bashger yalewn kum neger sinmeleket new yechiwuwutun firie neger magignet yeminchilew. Tsihufu beteley '...teym hasab..' bemilew tikil hassab yalebinin lezemenat tenserafto yekoye ahun ahun degimo betam adigo ye and ager lijoch honen be teqarani chafoch lay leminigegn abzagnaw ye Ethiopia hizb chigrachinin yetekome yimesilegnal.

  Dn. Daniel Berta Eg/hr astewulot yadilih asiteway libh bekelidoch tetekilew yemiwordu kum negerochin tikuret setichie endayachew aschilonalina ameseginihalehu.

  ReplyDelete
 17. አምደ ሚካኤልJuly 16, 2010 at 12:07 PM

  Dany it is good ur way of writing
  Keep it up

  ReplyDelete
 18. it is really fasinating how you always come accross with such insidents. you are lucky ! may God Bless you. I got so many important concepts and i had fun too. keep on the good doing !
  *****

  ReplyDelete
 19. Oh Dn Daniel God bless u ,U r the current true apostle. keep on!

  ReplyDelete
 20. በጣም ጥሩ እና ትምህርት የሚሠጥ ኘሮግራም ስለ ሆነ ሊበረታታ ይገባዋል፡፡

  ReplyDelete
 21. ዳኒ በጣም እ/ግ ይባረክህ

  ReplyDelete