Friday, July 9, 2010

በሰይጣን እጅ የወደቀ ቅርስ

ከአርባ ዓመት በፊት በተመሠረተው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ገብታችሁ ወደ ዋናው ሕንፃ ስትዘልቁ፣ በስተ ግራ በኩል አንድ ታሪካዊ፣ ግን ደግሞ ብዙም ተመልካች የሌለው ቅርስ ታያላችሁ፡፡ ሦስት ሥዕሎች ጎን ለጎን በግድግዳው ላይ ተለጥፈዋል፡፡

ሥዕሎቹን የሳሏቸው ታዋቂው ሰዓሊ ሜትር አርቲስት ሎሬት አፈወርቅ ተክሌ መሆናቸውን በሥዕሉ ላይ ባሠፈሩት ፊርማ ማወቅ ይቻላል፡፡ የተሳሉት ደግሞ የዛሬ አርባ ዓመት በ1962 ዓም ነው፡፡

የመጀመርያው ሥዕል ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ሕመምተኞችን ሲጎበኙ የሚያሳይ ሲሆን ሁለተኛው ሥዕል ደግሞ ሆስፒታሉ ሲከፈት፣ ከሆስፒታሉ በላይ ክንፉ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የሆነ መልአክ፤ በመካከል ላይም ዐፄ ኃይለ ሥላሴ የሆስፒታሉን መከፈት ሲያበሥሩ፤ ሕዝቡም ለሕክምና ወደ ሆስፒታሉ ሲሄድ የሚያሳይ ነው፡፡

ሦስተኛው ሥዕል ግን በቦታው የለም፡፡

አሳዛኙ ነገርም የሚጀምረው ከዚህ ነው፡፡

ሥዕሉን የሚያውቁት የሆስፒታሉ ባለሞያዎች እንደነገሩኝ ከሆነ ሦስተኛው ሥዕል ዐፄ ኃይለ ሥላሴ አረጋውያንን ሲያለብሱ የሚያሳይ ሥዕል ነበረ፡፡ ይህ ሥዕል ንጉሠ ነገሥቱን አምርሮ በሚጠላው በደርግ ዘመን እንኳን ከቦታው ማንም አልነካውም ነበር፡፡ ከስድስት ወር በፊት ግን ማንም ሳያውቅ ሥዕሉ በድንገት ተሠወረ፡፡

የት ገባ? ተብሎ ተፈለገ፣ተፈለገ፣ ሊገኝ ግን አልቻለም፡፡ ምናልባት የጥንት ቅርስ ዘራፊዎች ሰርቀውት ይሆናል የሚል ጥርጣሬ በሆስፒታሉ ኃላፊዎች ዘንድ አደረ፡፡ ነገር ግን የተፈራው ነገር አልነበረም፡፡

ሥዕሉ በሆስፒታሉ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ ተጨመዳድዶ ወድቆ ተገኘ፡፡ የሆስፒታሉን ኃላፊዎች የገረማቸው ሁለት ነገር ነው፡፡ መጀመርያ ይህንን አድራጎት የፈጸመው ሰው ለብዙ ሰዓታት ያንን ሥዕል ሲፍቅ እንዴት አንድ ሰው እንኳን አላየውም? ሁለተኛ ደግሞ እንዴት ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ሊጥለው ቻለ? እነዚህን ነገሮች ዛሬ ድረስም መመለስ አልተቻለም፡፡

እኔ ግን በሰይጣን እጅ የወደቀ ቅርስ ብየዋለሁ፡፡ ይህ ሰው ዐፄ ኃይለ ሥላሴን ይጠላቸው ይሆናል፤ በርሳቸው ዘመንም ግፍ ተፈጽሞበት ይሆናል፡፡ ይህንን ስሜቱን ግን ቅርስ በማጥፋት አይደለም መበቀል የሚችለው፡፡ ክፉ ተግባር ዳግም እንዳይፈጸም በማድረግ እንጂ፡፡

ቅርስ የምንወዳቸውን ሰዎች ብቻ የሚወክል አይደለም፡፡ ክፉ ታሪክም ቢሆን ቅርስ አለው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን የግራኝን ካባ ያስቀመጠችው ስለምትወድደው አይደለም፡፡ ታሪክ ስለሆነ እንጂ፡፡

እንደኔ እንደኔ የሌኒን ሐውልትም መፍረስ አልነበረበትም፡፡ ልጆቻችንን ዓላምን ስለበጠበጠው ሌኒን ስለሚባል ሰው በተረት ከምንነግራቸው ሐውልቱን እያሳየን ብንነግራቸው ይበልጥ ይገባቸው ነበር፡፡

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የነበረውን የዐፄ ኃይለ ሥላሴ ሥዕል የገነጠለውን ሰው ሰይጣናዊ ሃሳብ የምንቃወመው እና ለሌሎች መሰሎቹም ትምህርት የምንሰጠው ያንን ሥዕል መልሰን በቦታው ከሰቀልነው ብቻ ነው፡፡

የሆስፒታሉ ምንጮች እንደነገሩኝ ከሆነ ሜዲካል ዳይሬክተሩ ዶክተር መስፍን ሥዕሉን ለማስጠገን ሎሬት አፈወርቅ ተክሌን አነጋግረዋቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ሊጠገን የሚችለው በብሔራዊ ሙዝየም ብቻ መሆኑን ነግረዋቸዋል፡፡

ሙያው ወይንም ገንዘቡ ያላችሁ፤ የቅርስ ተቆርቋሪዎች እባካችሁ ይህንን በሰይጣን እጅ የወደቀ ቅርስ እንታደገው፡፡


16 comments:

 1. it is good idea.But yewahohus???

  ReplyDelete
 2. Kale Hiwoten Yasemlen Bedme Betsgea Yetbklen Dakon Daneil Eshi Teru Asbe New

  Gien Banke Kuter Weteo Bezi Leay Bikmte Yakmchnen Bendrge Beant Bewendmchen Terit EGZIABHER Yebrkneal EGZIABHER Yerdean Yebnke Kutruen Entbeklen!

  ReplyDelete
 3. Dear Dn Dani, afereso mejemere demachene wesete yale chegere sayehone yikerale belehe newe?

  ReplyDelete
 4. Hi Dani,

  Thank you for bringing this issue. You may right devil did that because those pictures survived even from Durg. I was reading a couple of days ago from Addis Admass news paper about what is happening to our Ethiopian children in their own country .
  በሳምንት ከ 30 በላይ ህጻናት የወሲብ ጥቃት እየደረሰባቸው ወደየካቲት 12 ሆስፒታል ይወሰዳሉ፤ ወደዚህ ሆስፒታል ያልመጡት ማን ይቁጠራቸው ? እነዚህ ህጻናት ከነዚህ ቅርስ ይበልጣሉ። የሰውነት ክብራቸው የተጠበቁ ህጻናት ካላሳደግን ፤ ነገ እነዚህ አሉ የምንላቸውን ቅርሶች የትኛው ትውልድ ነው የሚተብቃቸው? እባክህን በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ በል። ባለውበት አገር እንዲህ አስነውሪ ነገር የሚያደርጉ ከሌሎች እስረኞች ጋር ከታሰሩ፤ ሌልው እስረኛ አያስተርፋቸውም። እኛ ግን ህጻናቱ ላይ ግፍ ሰደርግ ዝም እንላልን።

  ReplyDelete
 5. አይ ምስኪኒቷ እምዬ ኢትዮጵያ፣ ከታሪክ ከመማር ይልቅ ታሪክን በማጥፋት ለመማር ጥረት የሚያደርግ ሕዝብ ያለሽ ምስኪን አገር!!! በኃላፊዎች ካልተቀነባበረ በስተቀር ሰው እንደ ጉንዳን በበዛበት ሆስፒታል ውስጥ እንዴት ይህን ያህል ዓመት የቆየ ቅርስ ሊገነጠል ይችላል?

  አንድ የሚገርመኝ ነገር አለ፤ እስካሁን ካየኋቸው የመገበያያ ገንዘቦች ውስጥ የሀገሪቱን ንጉስ ወይም አንድ ታላቅ ሰው ሥዕል ያልያዘው ገንዘብ የኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው:: የቀድሞ ታላላቅ ሰዎች ከሠሯቸው ብዙ ታላላቅ ሥራዎች ይልቅ ትንሿን ጥፋት በማጉላት የራሳችንን/የአሁኑን ዘመን ታላቅነት ለማሳየት የምንጥር ምስኪናን ስለሆን ይመስለኛል....::

  ሰላም

  ReplyDelete
 6. Dear Dn. Danny
  Thank you for the information.It is realy a bad news but usual in ethiopian...why we do it is a challenging question if you say so...out awareness about heritage, our value of life, living standard,...and total political dissatisfactions are some factors I can mention for such destructions...
  Any ways you give us a nice klick to value national heritages.
  GOD MAY BLESS YOU

  ReplyDelete
 7. hi dani it is nice

  ReplyDelete
 8. I think first of all, to keep my heritage safe, I shuld know, What hertiage is? What is the use?
  If I am able to answer those questions I would be able to keep my heritage period. I need lesson and I need someone who can tell me the truth about my country. I need somone who can treat me well without criticism. Anyways....
  I think you guys will understand my ideas what I am trying to say. Thank u 4 all ur didicatio work.

  ReplyDelete
 9. This is to anonymous who ask about what a heritage is and its use.

  I hope we all know that a house will not be built starting from the roof then the walls and the foundation. What first comes is the foundation, then the walls and the roofs.

  History is also like that, a society who knows the past could live the present and shape the future. Our heritages are one of the tools who tell us about the past. For instance, if your father passes while you are young then what will you do to know about him? Or you say why should I Know about my father? No you should know about your father because you are his genetic successor. Then you will try to see his photos, listen about him from mother and others, etc.

  Likewise, our heritages tell us about our forefathers in a bigger scale and we need and study them. our heritages are like roots of a plant.
  survival, strength, identity, character, ope and uniqueness are deeply rooted under such tools.

  We need keep, study, maintain and pass to the next generation our heritages!!! But not only that we should also create our heritage for our successors, otherwise who knows who were we?

  Thanks

  ReplyDelete
 10. ሰላም ዲ.
  በጣም ጥሩ ነገሮችን ጽሑፎችን እያስነበብከን ነውና በርታ ለዚህ ሥራህ ብዙ ጊዜ እንደምታጠፋ አውቃለሁ የመንሰዊ ጽሑፎችህን ጊዜ እንዳይሻማብህ እፈራሁና አስብብበት

  ReplyDelete
 11. አባግንባር( ከሮማ)July 12, 2010 at 6:47 PM

  ውድ ዲን. ዳንኤል ሰላምታዬ ላንተና አንተን በተለያየ አስተዋጽኦ ለሚረዱ ሁሉ ይድረስ እላለሁ፡፡

  ጥሩ ትዝብትና ጥሩ እይታ ነው፤ ካሜራህም አሁን አሁን ልክ እንደ ብዕርህ ሁሉ ጥሩ ኣዳኝ ሆኖኣል፡፡

  ያነሳኸው ጭብጠ-ሐሳብ ወደ አንድ ትዝብት አመራኝ እኔንም፤ አሁን በምኖርበት ከተማ ውስጥ አልፎ አልፎ የመጓጓዣ አግልግሎት ላይ አመጽ ይካሄዳል፡፡ የሚገርመው የአመጹ ጉዳይ ሳይሆን ሂደቱ ነው፡፡ የመሬት ውስጥ ለውስጥ አገልግሎት የሚሰጠው ባቡር (በሀገሬው አጠራር “ሜትሮ”) የሚባለው አገልግሎት ላለመስጠት አድማ ሲያደርግ መጀመሪያ አድማ እንዳለ አስቀድሞ ይነገራል፡፡ በየባቡር ጣቢያው፤ በየጋዜጣውና በማንኛቸውም የመገናኛ ዘዴዎች ይገለጻል፤ ቀጥሎ የአድማው ሰዓት በቀን ውስጥ የተወሰነ ጊዜ ቢቻ ነው ሚደረገው፤ ከዚያ ውጪ ለሎች የመጓጓዥ አገልግሎት ሰጪ አውቶቡሶች ምንም ዓይነት ትብብር ኣያደርጉም፤ ካደረጉም የእነርሱም አስቀድሞ ይገለጻል፡፡ በተጨማሪ በተወሰኑ ሰዓታት ልዩነት አገልግሎቱ እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡ እና ይኸንን ጉዳይ ሳስብ የኛው ሀገር አድማ ትዝ አለኝ ፤ ሕምምም….መጀመሪያ አድማው የሚነሳበት ጉዳይና ሂደት ትቶ ፍፃሜውን ቢቻ መታዘቡ በቂ ነው፡፡ እሱም አንድና አንድ ነው፤ የመጓጓዣውን አግልግሎት የሚሰጡትን ተሽከርካሪዎች በማቃጠልና ቢቻል የሚጠገኑበትንም ቦታ በማውደም ይደመደማል፡፡ ከዚያ ሀገሪቷ ለሌላው ልማት ማዋል የሚገባትን እሱን ለማስጠገን ስታውለው የእኮኖሚው ጥያቄ የእያንዳንዳችንን ደጂ ማንኳኳት ይጀምራል፡፡

  እንዳልከውም አንድ መሪ እኔን ወይም ሀገሬን በድሏል ብዬ ሃሳቡን ልጠላው እችላለሁ እሱን ማጥፋት ወይም እሱ የሰራውን ማጥፋት ግን ሀገሬን እወዳለሁ በምለው በራሴ ላይ ሌላ ሥራን መጨመር ይመስለኛል፡፡

  እኔ ግን ይገርምሃል ዳኒ እንደዚህ አይነቱን ከአጥፍቶ ጠፊ ነው የማመሳስለው፡፡ ትንሽ ልዩነታቸው የጊዜ ጉዳይ ነው፡፡ ቦምብ የሚያፈነዳው ቶሎ ይገድላል ጥፋቱም ወዲያው ይታያል፡፡ የኛው ዓይነቱ ግን ያጠፋው ጥፋት ወዲያው ቢታይም የእርሱ መጥፋት ግን ይዘገያል፤ ሲመጣ ግን ሌላውንም ይዞ ይጠፋል፡፡ ብቻ ልብ ይስጠን እኛንም ከመተቸት ወደ ሠራተኝነት ያሻግረን እላለሁ፡፡

  ሌላው የጥገናው ዋጋ ምን ያህል እንደሆነ አልጠቆምክም፤ ስንት ይሆን? ሰዎችስ እንዴት ሊተባበሩ ይችላሉ? መስመር መስጠት ትችላለህ?

  አባግንባር ከሮማ

  ReplyDelete
 12. ዳኒ ቢቸግርህ ነው!
  አታስታውስምን የዓደዋውን ጀግና የእምዬ ምኒልክን ሃውልት ምን ሊያደርጉት እንደነበር!
  ደኑን መነጠሩት እነ ቀን አያውቁ
  ምን ያፈራ ነበር ብለው ሳይጠይቁ ይሏችኋል ይህንን አይደል
  ለጥፋት የተሰለፉ እጆች መች ይሆን .....

  ReplyDelete
 13. እጅግ በጣም አስተማሪ ፅሁፍ ነው፡፡ ዳኒ እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡ ባህልናቱሪዝም ትዝ ያላለውን ነገር በማንሳትህ እናመሰግናለን፡፡ባህልናቱሪዝም ሚኒስቴር ልብ ይስጥህ....

  ReplyDelete
 14. ዳኒ እይታህ እጅግ በጣም ጥሩ ነው፡፡ ባህልና ቱሪዝም እንዲህ ያለ እይታ ቢኖረው ኖሮ አገራችን የት በደረሰች ነበር፡፡ ለማንኛውም ባህልና ቱሪዝም ይህንን አንብቦ ልብ ቢገዛ መልካም ነው...

  ReplyDelete
 15. ዳኒ ጥሩ እይታ ነው ቅርሶቻችን ልነጠብቅ ይገባል ።

  ReplyDelete