Wednesday, July 7, 2010

ጤፍ እና እንጀራ

በኢትዮጵያውያን የዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ታላቅ ቦታ ካላቸው ትውፊታውያን ምግቦቻችን መካከል እንጀራ አንዱ ነው፡፡ እንጀራ ለኢትዮጵያውያን ምግባቸው ብቻ ሳይሆን የባሕላቸው፣ የርእዮተ ዓለማቸው፣ የታሪካቸው፣ የማንነታቸው እና የሕይወ ታቸው መገለጫም ነው፡፡ ኑሮውን ለማሳካት ውጣ ውረዱ የከበደው ወገን

እንጀራ በሰማይ እኔ በእግሬ ሆኜ
አልደርስበት አልኩኝ ባክኜ ባክኜ

በማለት ኑሮን እንጀራ ብሎ ሲጠራው፡፡ በበጋ እህሉን ጨርሶ ክረምትን በቀጠና ያሳልፍ የነበረው የጥንቱ ገበሬ ደግሞ የችግሩን ስፋት

እኛስ ይህችን ክረምት ወጣናት በመላ
በኩርማን እንጀራ ጎመን ተጠቅልላ

ብሎ ነበር የሚገልጠው፡፡

ሽማግሌዎቻችን ሕይወትን እንጀራ ብለው ይጠሯትና ሕይወቱ የተቃና የተሳካ እን ዲሆን የሚፈልጉትን «እንጀራ ይውጣልህ» ብለው ይመርቁታል፡፡ እኛም «የዕለት እን ጀራ ስጠን» ብለን እንጸልያለን፡፡

ትውፊታዊው እንጀራ ክብ ነው፡፡ መጋገርያውም ምጣድም ሆነ ማቅረቢያው ሞሰብም ክብ ናቸው፡፡ የጥንት ቤቶቻችን፣ ቤተ መንግሥቶቻችን እና አብያተ መቅደሶቻችንም በአብዛኛው ክቦች ናቸው፡፡ «ቤተ ንጉሥ ቅርጽ» ይባላሉ፡፡ ሰፌዱም፣ ድስቱም፣ ሞሰበ ወርቁም፣ ሙዳዩም፣ አውድማው፣ ክምሩ፣ ጎተራው፣ ክብ ናቸው፡፡ ምናልባት የእንጀ ራችን ተጽእኖ ይሆን በእነርሱ ላይ ያረፈው? የሚለው ጥናት የሚፈልግ ይመስለኛል፡፡

ኢትዮጵያውያን ዓለም ክብ ናት ብለው ያምኑ ከነበሩት ቀደምት ሕዝቦች መካከል ይመስሉኛል፡፡ በ13ኛው መክዘ መጻፉን የሚናገረውና በዳጋ እስጢፋኖስ ገዳም የሚገኘው /እኔ ከዐሥር ዓመት በፊት ነበር ያነበብኩት/ መጽሐፈ ማስያስ «ምድር ጋን ትመስላለች» ይላል፡፡ የጋን ቅርጽ ያለውን ሞላላ የክበብ ቅርጽ ላስተዋለ የደራሲው ሃሳብ ከዘመናዊው ሃሳብ ጋር ያለውን አንድነት ይገነዘባል፡፡ ኢትዮጵያውያን ዓለም ክብ ናት ብለው ያምኑ እንደነበር የሚያሳየን ሌላው ሥዕላዊ ማስረጃ ደግሞ የቅድስት ሥላሴን ሥዕል ሲስሉ ሥላሴ ዓለማትን በእጃቸው እንደያዙ ለማመልከት ይጠቀሙ የነበሩት ዓለምን ክብ አድርገው ሥለው በሥላሴ እጅ በማስያዝ ነው፡፡

ጥንታውያኑ ሊቃውንት ሰባቱ ሰማያትን ሲስሉ እንኳን በሰባት ክበቦች እያደረጉ ነበር የሚያመለክቷቸው፡፡ በጥንታውያን ሥዕሎቻችንም የሰዎችን መልክ በክበብ ቅርጽ ተስለው ነው የምናገኛቸው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም ነገሥታቱ ራሳቸውን የዓለም ገዥዎች አድርገው በሚቆጥሩበት ዘመን ከነገሥታቱ ቀለበት ላይ ለገዥነታቸው ምልክት የምትቀመጠው ሉል እንኳን ክብ ነበረች፡፡

የእንጀራችን ክብነቱ ከባሕላችን እና አስተሳሰባችን ጋር መስተጋብር አለው፡፡ ኢትዮጵ ያውያን ተሰባስበው በአንድነት የመመገብ ባሕል አላቸው፡፡ እንደ አሁኑ እየተቆረሰ መቅረብ ከመጀመሩ በፊት ደግሞ ሁሉም በየደረጃው እና በየመደቡ ሰብሰብ ብሎ ነው የሚቀርበው፡፡ ለማዕድ የሚቀርቡ ሰዎች ለምግቡ የሚኖራቸው ርቀት ተመሳሳይ እንዲሆን ይመስለኛል እንጀራችን ክብ የሆነው፡፡ በክብ ነገር ዙርያ የሚቀመጡ ሰዎች የትም አቅጣጫ ላይ ቢቀመጡ ለዚያ ነገር የሚኖራቸው ቀረቤታ እኩል ነውና፡፡ በተለይም የወጡን በመካከል መቀመጥ ስናየው ከየትም አቅጣጫ የሚቆርስ ሰው ለወጡ እኩል ተሳታፊነት ይኖረዋል፡፡

ይህም ብቻ ሳይሆን ክብ የሆነውን እንጀራ ከየትኛውም አቅጣጫ የተቀመጡ ሰዎች እየቆረሱ ሲመገቡት በስተ መጨረሻ መካከለኛው ነጥብ ላይ እጆቻቸው ይገናኛሉ፡፡ ይህም የአንድነትን እና የመቀራረብን ብሎም የመፋቀርን ስሜት ያመጣል፡፡ ጉርሻ ትልቅ ሥፍራ በያዘበት በቀደመው ባሕላችን ውስጥ ክቡ እንጀራ አስፈላጊ ነበር፡፡ የሚጎ ራረሱት ሰዎች በክቡ እንጀራ ዙርያ ሲቀመጡ ወደየትኛውም ጎራሽ ይደርሳሉ፡፡ ከአንዱ አቅጣጫ ወደሌላው አቅጣጫ ለመጎራረስም ከአራት መዓዝኑ ይልቅ ክቡ አመቺ ነው፡፡

ክብ ነገር ይበልጥ የመቀራረብን እና የመወያየትን ስሜት ስለሚፈጥር በሚል ሃሳብ ነበር የአርሴናሉ አሠልጣኝ አርሴን ቬንገር ጃፓንን ጎብኝተው ከተመለሱ በኋላ አራት መዓዝን ሆነው ተሠርተው የነበሩትን የኤምሬትስ ስታዲዮም የመልበሻ፣ የመታጠቢያ እና የመዝናኛ ቦታዎች እንደገና አስፈርሰው የክበብ ቅርጽ እንዲኖራቸው ያስደረጉት፡፡

ለአመጋገባችን ብቻ ሳይሆን ወጋዊ ለሆነው ባሕላችንም የእንጀራችን ቅርጽ ስምሙ ነው፡፡ ክብ ሠርቶ ወግን እየሰለቁ ለመመገብ እና ምግቡ ካለቀም በኋላ በዚያው ለመቀጠል የሞሰቡም ሆነ የእንጀራው ቅርጽ ማኅበራዊ መስተጋብርን የሚፈጥር ነው፡፡

የኢትዮጵያውያን ሕይወት ከእንጀራ ጋር የተያያዘ መሆኑን ከሚያሳዩን ነገሮች አንዱ የጤፍ አመጣጥ ራሱን የቻለ ትውፊታዊ ታሪክ ያለው መሆኑ ነው፡፡ አንድ ነገር በሕዝብ ሕይወት ውስጥ ቦታ ሲኖረውና ከሕዝቡ ባሕል ጋር የተዋሐደ ሲሆን የየት መጣ አፈ ታሪክ እና ትውፊት ባለቤት ይሆናል፡፡ እንጀራም የዚህ ባለቤት ነው፡፡

በትግርኛ ‘ጣፍ’፣ ‘በኦሮምኛ ‘ጣፊ’ በአማርኛ ‘ጤፍ’ እየተባለ ለሚጠራው ለእንጀራ አባቱ የሆነውን ጤፍ አመጣጥ በተመለከተ ታሪከ ነገሥታችን የመዘገበው አፈ ታሪክ እንዲህ ይላል፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት 2000 ዓመት አካባቢ አንዲት ልጃገረድ ነበ ረች፡፡ ይህች ልጃገረድ አንዲት ሴት ልጅ ከሰው፣ አንድ ዘንዶ ደግሞ ከዘንዶ ወለደች፡፡ ዘንዶውም ሰውን ሁሉ እያሳደደ ይበላ ጀመር፡፡ ሕዝቡም እኅቱን አማላጅ አድርገው አጋቦስ ለተባለው ለዚህ ዘንዶ በየጊዜው ሊገብሩለት፣ እርሱም እያሳደደ መብላቱን ሊተው ተዋዋሉና ዕርቀ ሰላም ወረደ፡፡

አራት መቶ ዓመታት ያህል በዚህ ሁኔታ እንደኖሩ ገብጋቦ ወይም አንጋቦ የተባለ ሰው ከሐማሴን መጣ፡፡ የሕዝቡን መከራም ተመለከተ፡፡ ለምን ትገብሩለታላችሁ? ቢላቸውም ያለበለዚያ ይጨርሰናል፡፡ ለመገበር የተገደድነውም ለመግደል ቢያቅተን ነው አሉት፡፡ አንተ ግን ብትገድለው ገዣችን ትሆናለህ ብለው ቃል ገቡለት፡፡

እርሱም አጋቦስ የተባለው ዘንዶ ከሚተኛበት ቦታ ሄዶ ሰባት ዙር አጥር በደረቅ እንጨት አሳጠረ፡፡ ከዚያም በአራት መዓዝን እሳት ለቀቀበት፡፡ አጋቦስ የተባለውም ዘንዶ ሙቀት ተሰምቶት ቢነሣ ዙርያውን በእሳት ተከብቧል፡፡ ዘንዶው ብርቱ ስለነበር እንደምንም እሳቱን እያለፈ እስከ ሰባተኛው አጥር ደርሶ ነበር፡፡

ነገር ግን የእሳቱ ወላፈን እና ጭስ መፈናፈኛ ባሳጣው ጊዜ ገብጋቦ ጋሻ እና ጦር ይዞ ወይንም እንደ አንዳንዶቹ መጥረቢያውን አንሥቶ ጦርነት ገጠመውና መሐል አናቱን ፈለጠው፡፡ ከተፈለጠው የዘንዶ ጭንቅላትም ደም እና እዥ መሬት ላይ ፈሰስ፡፡ ያም ደም እና እዥ የፈሰሰበት መሬት ዕለቱኑ ዝናም ቢዘንብበት በቦታው ላይ ጤፍ በቀለ፡፡ ዘንዶውንም እኅቱ አልቅሳ ቀበረችው፡፡ የተቀበረበትም ሥፍራ «ተመን ዜውዖ» ተብሎ በአኩስም ምዕራብ እስከ ዛሬ አለ ይባላል፡፡

አንጋቦ ግዱርን፣ ግዱር ሰባትሶን፣ ሰባትሶ ተዋስያን፣ ተዋስያ ማክዳን ወይንም ንግሥት ሳባን ወለዱ ይለናል ታሪከ ነገሥታችን፡፡ የጤፍን ታሪክ ከንግሥተ ሳባ ታሪክ ሲያስ ቀድመው፡፡

ጤፍ በኢትዮጵያውያን አፈ ታሪክ ውስጥ ይህንን ያህል ቦታ ያለው፣ ለአመጣጡ ራሱን የቻለ የየት መጣ ታሪክ የሚተረክለት ባለ መዓርግ ምግብ ነው፡፡ የሚገርመው ግን ጤፍ ተገኘ የሚሉበት መንገድ ቢለያይም ሳይንቲስቶቹም ጤፍ ተገኘ የሚሉት በሰሜን ኢትዮጵያ ከ4000 እስከ 1000 ዓመት ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ባለው ጊዜ ውስጥ ነው፡፡

ካሕሳይ ገብረ እግዚአብሔር «ኅብረ ብእር» በሚለው አንደኛ መጽሐፉ ዓይነቶቹን እስከ 32 የሚያደርስለት ጤፍ፣ ከ1800 እስከ 2100 ሜትር ከፍታ፣ ከ450 እስከ 550 ሚሊ ሜትር በሚደርስ ዝናብ፤ከ10 እስከ 27 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በሚሆን ሙቀት ይበቅላል፡፡

ጤፍ ዛሬ ዛሬ ለብዙ ኢትዮጵያውያን የእህል ውድነት ማሳያ ነው፡፡ እህል ተወደደ ማለት ጤፍ ተወደደ፣ እህል ረከሰ ማለትም ጤፍ ረከሰ ማለት ነውና፡፡ ዐፄ ምኒልክም ዛሬ የአድአ በርጋ ማኛ ጤፍ የሚባለውን የጤፍ ዓይነት ከደቡብ ጎንደር ስማዳ ጋይንት አስመጥተው እንዲበቅል ያስደረጉት ቤተ መንግሥቱም ያለ ጥሩ ጤፍ አልሆን ብሏቸው መሆን አለበት፡፡ በሀገሩ እያለ «ስይት» ጤፍ ይባል የነበረው ነጭ ጤፍ ከስማዳ እየመጣ አላረካቸው ቢል ተመሳሳይ አፈር እና አየር አፈላልገው አድአ ላይ ስለዘሩት ይሄው ዛሬ አድአ በርጋ የነጭ ጤፍ ሀገር ሆነ፤ ስይት የሚለው ስሙ ተቀይሮም ማኛ ተባለ ይሉናል ሟቹ መሪጌታ ተስፋ ጥሩነህ «አማርኛ በአማርኛ መፍቻ መዝገበ ቃላት» በተሰኘ ያልታተመ መጽሐፋቸው፡፡

እንጀራ ፍቅር የሚያስይዝ ምግብ ይመስለኛል፡፡ ከጎረቤታችን ኬንያ እስከ አሜሪካ ባሉ የኢትዮጵያውያን ምግብ ቤቶች የሚመገቡ የውጭ ሀገር ዜጎች በዋናነት የሚመርጡት እንጀራ መመገብን ነው፡፡ ኬንያ በአንድ ምግብ ቤት የምትሠራ ወጣት «በጣም የሚገር መው ነገር አንድ ጊዜ እንጀራን የቀመሰ የውጭ ሀገር ሰው ከዚያ በኋላ ከምግብ ቤታችን አይጠፋም» ብላኛለች፡፡

ይህንን ነገር ይበልጥ ያየሁት ኢየሩሳሌም ነው፡፡ የትንሣኤን በዓል ለማክበር በኢየሩ ሳሌም ዴር ሡልጣን ገዳም የሚሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን ከዚሁ ተዘጋጅቶ የሚሄድ የትንሣኤ ድግስ አላቸው፡፡ በፋሲካ ዋዜማ እኩለ ሌሊት፣ ቅዳሴው ካለቀ በኋላ በገዳሙ ግቢ ውስጥ ራት ይበላል፡፡ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ፍልስጥኤማውያን በጉጉት ከሚጠ ብቋቸው ቀናት አንዱ ኢትዮጵያውያን ትንሣኤን የሚያከብሩባት ይህቺ ሌሊት ናት፡፡

ፍልስጥኤማውያኑ ወደ ዴር ሡልጣን ገዳም በዚያች ሌሊት የሚመጡት ትንሣኤን ከኛ ጋር ለማክበር አይደለም፡፡ ለምን እንደሚመጡ ምክንያቱን የምታውቁት ከዴር ሡልጣን ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ካለቀ በኋላ ዘግይታችሁ ከወጣችሁ ነው፡፡ እንጀራው እና ወጡ አልቆ ይጠብቃችኋል፡፡ ምነው? ስትሉ መልሱ አንድ ነው፡፡ በዚያች ሌሊት በጉጉት ሲጠባበቁ ያደሩት ፍልስጥኤማውያን ዓመት ሙሉ የጓጉለትን እንጀራ ለማግኘት ተሻም ተው ጨርሰውታል፡፡

እንጀራ እንኳን እኛን ምዕራባውያንን እና ፍልስጥኤማውያንን እንኳን በፍቅር ጥሏቸዋል፡፡

አይ የእንጀራ ነገር፡፡35 comments:

 1. This comment has been removed by a blog administrator.

  ReplyDelete
 2. This comment has been removed by a blog administrator.

  ReplyDelete
 3. ይስጥህ ዘአርሴማJuly 7, 2010 at 4:56 PM

  ሰላም ውድ ትልቅ ውንድሜ ዳኒ ስለ ጽሁፍህ እግዚአብሔር ይስጥልን።
  ዳኒ ላሳስብህ የምፈልገው፡- ብሎግህ ላይ እንደጻፍከው በሳምንት 2 ጊዜ ጽሁፍህን ብታዘጋጅልን ።ይመስለኛል ያንን አስበህ ነውና የጀመርከው ብዙ አትቆይብን በጥም እኮ ተቃጠልን።
  ሌላው ስለ እንጀራ አንድ ያነበብኩት ጽሁፍ አለ። እዚህ መጸሃፍ ላይ እንዲህ ይላል "የ ዘንዶውን ራስ ቀትቅጠህ ....ለኢትይዮጲያውያን ምግባቸውን ሰጠሃቸው" የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል በአንድምታ ሲተርጉሙት ጤፍን ነው ትብሎ ቀርባል።በርግጥ የመጀመሪያ ትርጓሜው ሌላ .......ቢያስቀምጥም።በሁለተኛ ደረጃ ይህ የኢትዮጲያውያን ምግብ ጤፍ ነው ብሎ አስቀምጦታል።ዘርዘር ሲያደርገውም የዘንዶውን ራስ ቀጥቅጠህ ሲል ጤፍ ሲያድግ እና በነፋስ ሲንቀሳቀስ ከሩቅ ላየው ሰው ዘንዶ እንደሚንቀሳቀስ ይመስላልና ቀጥቅጥውህ ሲል የጤፍ ፍሬ ራሱ ላይ ነው ያለው ሲወቃም ራሱን ነው የሚቀጠቀጠው(የሚወቃው) በአጠቃላይ ያቃል ስለጤፍ ነው የተነገረው ተብሎ ተተርጉሟል። ዳኒ ምን አይነት አስተያየት አለህ በዚህ ላይ።
  በተረፍ በርታልን ጽሁፍህን በጣም እንናፍቃለንና እባክህ አትዘግይብን።

  እግዚአብሄር ብርታቱን

  ReplyDelete
  Replies
  1. ልክ ነው። የአለም ጌታ ተአምሩን ያሳየበትና ህዝቡም ዘንዶ ከማምለክ ተላቀቀ

   Delete
 4. አባግንባር( ከሮማ)July 7, 2010 at 5:26 PM

  አንድ የፌስ ቡክ ጓደኛዬ ላይ ያገኘሁት ትዝ አለኝ፤ እንዲህ ይላል፡

  "ወይ እንዠራ"

  ይዤ ስፈልገው
  ተመልክቼ ከሰው
  ከሰው ተራ አቆመኝ
  ስደተኛ አረገኝ
  የበልጡን ለማግኘት
  እጅጉን አጣሁት
  ክረምት የለ በጋ
  ቆላ ወይና ደጋ
  ይህን ተቋቁሜ
  ፍቅሩን ተሸክሜ
  ከበደኝ ሃሳቡ
  እንዴት ነው ጥጋቡ
  ከዴንማርክ ብነሳ
  እሱኑ አሰሳ
  ብጓዝ ወደ ጀርመን
  አሱኑ ለማደን

  እንዴትም ቢጋገር እንዴትም ቢሰራ
  የሚመስለው የለም የገሬን እንጀራ፡፡

  በዚሁ አርእስት ላይ በሌላ አስተያየት ተመልሼ እመጣለሁ፡ እስከዚያው ሰላም ያገናኘን፡፡

  አባግንባር

  ReplyDelete
 5. Thanks dani!
  One thing that admire me always is the size and the thickness of enjera.you know buildings are designed on ultimate capacity of failure with ductlity.but enjera was more than ultimate state and has incideble ductlity.the size is so perfect to hold the mass,the thickness and mosture content makes it un britil or ductile.Enjera is the ultimate technology no further modification is possible.etc.........

  ReplyDelete
 6. Hi D/n Daniel.

  I just come to say one thing! Primarily, I appreciated your dedicated contribution to our society. But...One thing i see here is: you should pay attention on comments! please remove the repeation comments and we can learn from them too.

  golgule.

  ReplyDelete
 7. Hello Dn. Dansile. It realy good observation. But, specially in urban areas we los all those 'circle' culture. We are moving towards rectangle. Anyone seeking a corner for himself not to have conversation. Due to technological advance, invidualism is getting more importance than dialogue. I hope this article will rimnd us something that we are losing.
  Thethings that amazes me from this article is the ealy belief of Ethiopian about spherical shape of the earth. We did we get lost? What detached us from our brilian anscestores?

  May God give more grace and Wisdom to continue in this service.

  P.S. Some comments are posted again and again. Coul you please control this?

  ReplyDelete
 8. Thanks Dn Daniel .
  when i was a child, my high school science( biology) teacher used to tell us that the only nutrient Teff had was iron( the black teff), and he used to advise us we should stop or modify our habit of eating teff.
  decades later, science journals revealed that Teff do an amazing variety of nutrients and it is found to be gluten free.
  Recently ,United Sates farmers have started growing teff aggressively because Teff flour is one of the high moving product in many big stores of USA.
  Funnily enough, some western companies are trying their level best to have the patent right( some have already claimed) for Teff due its growing market .
  Please read the claim of one company hereunder
  http://tigraionline.com/Patentsoilcropvoll.pdf

  ReplyDelete
 9. Dear ZeArsema:
  We already knew you looooove Dn Daniel's articles ...OK! But do you have to post your comment 7 times. Eeeeeew! don't you think it is tooooo much ? Please, once is enough, OK!!?

  Dn Daniel: great article, as always - informative and well written, keep it up!

  God bless

  Ankiro

  ReplyDelete
 10. I read one reaserch done in england about the benefit of teff & it is important for some patients who can not eat wheat & barley(ciliac disease). In addition it fills your stomach but does not make you fat like western foods.'Cause does not have too much carb or salt. It is good for those with diabetes too.I think it is God's gift.We need to do more reaserch.
  Any ways thank you much

  ReplyDelete
 11. Dn Daniel: I loved this article. I have read some versions on this topic before but this is deep...Qale Hiwot yasemalin!

  But I have one question. Since the history of Queen Sheba/Makeda is a well documented history of Ethiopia in general, is the story of the 'Zendo' real? Or we have to take it as a 'folks tale' or 'teret' ? In some discussions and books, some say it is real and others claim it is just a 'fairy tale'. What do you say ? Hope you can come up with an answer ?
  Thanks,

  God bless

  BG from USA

  ReplyDelete
 12. ዲ /ዳንኤል

  የእግዚአብሔር ሰላም
  ለአንተ ይሁን

  እንዲህ ስትል አንድ ነገ ትዝ አለኝ

  አንዳንድ ባሕታውያን ነን የሚሉ ሰዎች
  ቡናን መጠጣት እንደማይገባ ሲያስተምሩ

  "ቡና የበቀለው ከአርዮስ ፈርስ ላይ ነው "

  ይላሉ

  ከላይ ያቀረብኸው የታሪከ ነገሥት (ስለ ጤፍ ያለው) አገላለጽም :
  ከባሕታውያኑ ንግግር ጋር ተያየዘብኝና ትንሽ ፈገግ አልሁኝ

  እርግጥ ነው : ለማንኛውም ነገር : የተሻለ መልስ እስኪገኝለት ድረስ (ትክክል ቢሆንም ባይሆንም) የራሱ የሆነ መልስ አለው ::

  እንደኔ እምነት ግን

  ፍጡራን ሁሉ የተፈጠሩት በመጀምሪያዎቹ ስድስት ቀናት ውስጥ በመሆኑና ::

  ጤፍም የተፈጠረው (እንደ ጓደኞቹ ዕፅዋት , አዝርዕትና አትክልት ሁሉ) በዕለተ ሰሉስ /ማከስኞ ቀን መሆኑ ግልጽ ነው ::

  ይሁን እንጅ : ከታሪክና ከትውፊት ጠቅሶ : ያለውን ሁኔታ ለአንባብያን ማቅረቡ ደግ ቢሆንም ::

  ሰዎች ግን እንዲህ ዓይነቶችን አፈ ታሪክ ይዘው : በዚያው አቅጣጫ እንዳይሳሳቱ ሁኔታዎችቹን ገልጾ ማስቀመጡ ጥሩ ይመስለኛል ::

  ስለ ብርታትህና ቅን አሳቢነትህ
  የማከብርህ

  አክባሪህ

  ReplyDelete
 13. Eleni ke-SyracuseJuly 8, 2010 at 6:36 AM

  + + +

  Dear Dn.Daniel, thank you very much for reminding us the history & the life we have which is inseparable from Injera where ever we go. But the only problem it is creating now is, these days we are confused in separating spiritual service with getting injera.

  God be with you & the writings brother!

  ReplyDelete
 14. No , never, teff should never get out of our hand, but is it already being taken . we need to protest !!!!
  http://www.wipo.int/pctdb/en/wo.jsp?IA=NL2004000524&DISPLAY=STATUS

  ReplyDelete
 15. እግዚአብሔር ይስጥልን::

  ReplyDelete
 16. "ሰላም ውድ ትልቅ..." ብዬ ብጀምር ሰው የማደናግር ስለሚመስልኝ(ለስምንተኛ ጊዜ ብሎ) ዝምብዬ እነደምን አላቹ ብያለው ሁላቹንም
  አይ ጤፍ እና እንጀራ የሁሉ ታሪክ ያላቸው አይመስለኝም ነበር አንድ ቃል ልጨምር በጉራግኛም "ጣፊ" ነው የሚባለው፡፡
  "ነገር...ውሃ...." ይባል አይደል ተመችቶኛል

  ReplyDelete
 17. እንጀራ በውስጡ ካሉት ንጥረ ነገሮች አንጻር ዳቦን ከያዘው ንጥረ ነገር (ፕሮቲን)አንጻር ዳቦን ሊመገቡ ለማይችሉ ሰዎች በጣም ተስማሚ ነው፡፡ ለዚህም ነው ከኢትዮጵያ ሃገራችን የቤልጂየም ሰዎች ሰርቀው ወስደው ዛሬ ‹‹ከብት ባልዋለበት ኩበት ለቀማ›› እንዲሉ የሃገራቸው ንብረት ባልሆነው የራሳቸውን ካምፓኒ በሃገራቸው ከፍተው እየተጠቀሙ ያሉት፡፡ በዚሁ ከቀጠለ ጤፍ የኛ ነው ማለታቸው አይቀርምና ጎበዝ በዓለማችን የኢትዮጵያ ሃገራችን ብቸኛ ንብረት የሆነውን ጤፍ እንጠብቅ እንንከባከብ፡፡

  ReplyDelete
 18. Dn Daniel

  Thank for your articl, it is good sometimes to write about good things, next that was my previous comment...

  ReplyDelete
 19. Ze Debre Libanos
  pretty nice article. But i am confused of some of the comments forwarded. Who took tef patent right and why? Is there any nation than Ethiopians who used to produce teff?. If so how come teff patent is taken by others? I am really upset and confused.
  Would any one say something bout it.

  ReplyDelete
 20. I hope that is not what you really believe about 'Teff'.

  ReplyDelete
 21. D/Daniel
  I have a question for you. Who prepared this tiny seed which is teff to be enjera. I mean which ethnic. I remember that when I read one book, it stated that, Agew or Awi was the first ethnic to make as enjiera. How much this is true?

  ReplyDelete
 22. ጥሩ ጥሩ ግንዛቤዎችን እያስጨበጥከን ስለሆነ በዚሁ ቀጥልበት።
  ዳኒ እንወድሃለን
  ብቸኛ ያገራችን ፈላስፋና ታሪክ አዋቂ፣
  እንዲሁም የአባቶቻችንን ትውፊት ጠባቂ።

  እግዚአብሄር ይባርክህ!!

  ReplyDelete
 23. ጤፍ እንዲህ ያለ ታሪክ ያላት አይመስለኝም ነበር ለካ ብዙ ታሪክ አላት፤፤
  ዻኒ እግዚአብሔር ይስጥልኝ፤፤

  ReplyDelete
 24. Thank you Dn.Danny
  One of my freind told me that Injera has 98% Yehager fikir and only 2% Yenefis makoya...it has been said a lot about the history of Teff. People has it that there was a great famine during the time of Quine Sheba, and her majisty has ordered the people to sustain its life on this grass that resisted the famine...since then it has become a staple food for Ethiopians.
  GOD MAY BLESS YOU.

  ReplyDelete
 25. I read all the articles u posted on this blog so far. And I like all of them, specially those about the culture and attitude of our people. but I don't think u need to spend ur precious time writing about "teff" or sth insignificant. U better spend ur gift and time on other issues that can change the society's attitude and that hopefully with God lead to a better generation. Knowing about where and when or how "teff" emerged doesn't help or change any one's life, my dear friend.

  tsegawu yibizalih

  ReplyDelete
 26. The reason why foreigners get addicted to Injera so much, according to some of my non-habesha friends who became addicted to Injera, is its alcoholic content. It is like addiction to alcohol! Could it be? Everybody say they enjoy that bitter taste and they miss that taste!! Ayetafeteme lemalete 'alecha' or 'tasteless' enele yele egnase? Anybody who has a better reason?

  ReplyDelete
 27. Dear 'Wassihun':
  Stop being negative/critical for the wrong reasons. Knowledge about any (evenif you call it minor stuff)is always not a bad thing. Knowing about 'enjera' might encourage a'person' to do research and improve the on it, who knows ?

  So, pls be more +ve, and for argument sake, what is 'important' according to you ?

  Ankiro

  ReplyDelete
 28. እንሰት (warka)July 15, 2010 at 6:07 PM

  ስለ እንጀራ ስርወ ቃል ሳስብ ከጋገረ የመጣ ይሆን እላለሁ።
  እንጀራ = ባንዳንድ ዘዬዎች እንጌራ ሲሆን የእንጀራ እን- እን-ጌራ የጌራ ጋገረ ውጤት አመላካች ትሆን? ሌሎች ተመሳሳይ ቃላትም አሉ። እን-ስራ እን-ቢልታ እን-ቆቅልሽ እን-ጉር እን-ጉት (እን-ጎቻ ) እን-ግብ ወዘተ

  ReplyDelete
 29. Infat teff has got appriactions including from the western where I live.However , teff production is realy tough and needs full attention. The time that is spent to teff can be used to produce 10 fold of wheat.I know, that I used to by 1000g of teff for 5.5 euro becuse I have almost adicted to injera. But , for our people in Ethiopia , it seems better if they could focus to other less laborous products.

  Indeed , I admire the writer for his concern to describe te way teff has to be.

  ReplyDelete
 30. Hi dani,i like your article but i have one question to you:from the biollogical or reliogious prespective, is it possible for human beings to concive from zendo.where is the source you found this history.i got confused that is why i ask.

  ReplyDelete
 31. Hi Dani,
  It is so enjoyable and informative to read your article. I am hoping to read one of your great book one day.

  What a history of Teff and it social connection.We Ethiopians have a lot to offer for others. But we have lost our confidence being us many decades before. We used to accept Westerns as the ultimate solution for our problems and relying on their ideas which never worked for us. For example, My teachers have been teaching me Teff has nothing to do with nutrition and we need to eat other such as pasta ....because Teff was unknown for westerns and no scientific work done about it. Now, We say Teff has good nutation because the westerns are turned on it. I don't know when such mind set will be solved.

  ReplyDelete
 32. አኔ መቼም የምለው ቢኖር እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ ከማለት ውጪ የምለው የለኝም፣ እንደው ስለ እንጀራ ክብነት፣ ስለ ቤተ-መቅደስ ክብነት፣ ስለ ቤተ-ምንግስት ክብነት ስትጠቅስ አንድ ነገር ትዝ ብሎኝ እሷን ለማካፈል ነው ብቅ ያልኩት፣
  በጣም የሚገርመው ሰው ከተቃራኒ ጾታው ጋር ወደ ትዳር አለም ሲገባ ህንኑ ክብ ቅርጽ ያለውን ቀለበት ሁለቱ ተጫጪዎች በጣታቸው ላይ ለምልክት ማድረጋቸው፣ ይህ እስከ ህይወታችን መጨረሻ በድካምሽ፣ በህመምሽ፣ በችግርሽ፣ እንዲሁም እስከ እለተ ሞታችን ላንለያይ ብለው የሚያደርጉት ቃል ኪዳን ነው። የሚገርመው ግን ይህ ክብ ቀለበት ትልቅ ትርጉም አለው እሱም “ክብ” የማያልቅ፣ ቢዞር መጨረሻ የሌለው መሆኑ ዘሪያው በሕይወታችን ፈተናው፣ ችግሩ፣ ደስታወ፣ የተለያየ ውጣውረዱ፣ በአጠቃላይ እሾህ አሜኬላውን አልፈው መሄዳቸውን ያሳይል፤ ቀለበቱ ክብ መሆኑ ምንም ፈተና እና እሾህ አሜኬላው ቢበዛ ዙሪያ መሆኑ ፍቅራችን፣ ሕይወታችን ግን አይቋረጥም ማለታቸው ይመስለኛል ስለዚህም ቀሪ ህይወታችንም እንደዚህ ይሁን ሲሉ መመኘታቸው ይመስለኛል፣ ታዲያ ይሄ ነገር በእውነት ከእንጀራችን ጋር የተያያዘ ነገር አለው ማለት ነው እንዴ? ብዪ እራሴን ጠይቄ ነበር፣
  እስቲ ለማንኛውም ቸር ይግጠመን
  ለወንድማችን ዲ/ን ዳንኤልም እረጅም የአገልግሎት ዘመን እመኛለሁ፣
  ቸር ይግጠመን

  ReplyDelete
 33. Dn.Daniel may god help you to teach us more!i hope we will have chance to get more from you in the new year!
  Besrat.y

  ReplyDelete
 34. Dear Daniel , midenq new bewunet! Berta
  Ke Netherlands

  ReplyDelete