እንደ እኔ ውጭ ሀገር መሄድ የሚወድ ሰው አልነበረም፡፡ ከቻልኩ እንደ ሰው ቪዛ አግኚቼ ካልቻልኩም እንደ በርበሬ እና ሽሮ ተፈጭቼ አሜሪካ መሄድ አለብኝ ብዬ ቁርጥ ሃሳብ ነበረኝ፡፡ ያውም ደግሞ አሜሪካ ገብቼ ዜጋ መሆን ነው የምፈልገው፡፡እዚህ ሀገር መማር፣ መሥራት፣ መኖር ፈጽሞ አልቻልኩም፡፡ ሕልሜም እውኔም አሜሪካ ነው፡፡ ስለ ጤንነቴ ከሚጠይቀኝ ሰው ይልቅ ስለ አሜሪካ የሚነግረኝ ሰው ነበር የምወ ድደው፡፡ ያ በጣም የሚወድደኝ እና የምወድደው አጎቴን እንኳን አስቀይሜዋለሁ፡፡ እርሱ ዜግነቱን የሚለውጥ ሰው ደመኛው ነው፡፡ ከወንድሞቼ እና እኅቶቼ ጋር ምነው ምንስ ቢሆን እንዴት ዜግነት ይቀየራል ?እያለ ይጣላል፡፡ እኔ ደግሞ ካልቀየርኩ ሞቼ እገኛለሁ ብዬ ተነሣሁ፡፡
ቤተ ሰቦቼ ቢሉኝ ቢሠሩኝ ይህንን ሕልም መተው ስላልቻልኩ አለ በሚባለው መንገድ ሁሉ እኔን አሜሪካ ለመላክ ሞከሩ፡፡ ከአጎቴ በቀር፡፡ አንድን ነገር ሙጭጭ ስትልበት ጥምም ነው የሚልብህ፡፡ ለጓደኞቼ የተሳካው መንገድ ሁሉ ለእኔ ጠመመ፡፡ ሌላው ቀርቶ ኬንያ ሄጄ ፕሮሰስ ጥበቃ ሦስት ዓመት ተቀመጥኩ፡፡ ጠብ የሚል ነገር አልነበረም፡፡
የኬንያው አልሳካ ሲል ዑጋንዳ ገባሁ፡፡ እዚያ እንዲያውም የተሻለ ነገር ማየት ችዬ ነበር፡፡ አንድ ፕሮሰስ ገዝቼ አንድ ስድስት ወር ጠበቅኩና ተሳካ፡፡ ለኢንተርቪው ተጠርቼ ስገባ ሰውነቴ ይንቀጠቀጥ ነበር፡፡ የማውቀውን ነገር እንኳን መናገር አቃተኝ፡፡ የኔ መውደቅ ሳያንስ ባለ ፕሮሰሱንም አዘጋሁበት፡፡
እንደገና አገሬ ገብቼ ሌላ ነገር ጀመርኩ፡፡ ዲቪ ገዝቻለሁ፤ ፎርጂድ ፓስፖርት ለማሠራት ሞክሬያለሁ፤ ለባዛር እና ለኤግዚቢሽን በሚል ቪዛ ለማሠራት ገንዘብ ከሰክሻለሁ፡፡ ብቻ ተወው፤ ጓደኞቼ «ዋልያ» እያሉ ይቀልዱብኛል፡፡ እንደ ዋልያ ከሀገሬ ውጭ እንድኖር አልተፈቀደልኝማ፡፡ ያልተሳልኩት ታቦት፤ ያልሄድኩበት ጠበል፣ ያላማከርኩት ባሕታዊ፣ ያልከፈልኩበት ኤምባሲ የለም፡፡ ሁሉም ጭጭ ምጭጭ አሉ፡፡
ሲጨንቀኝ ከእግዚአብሔር ጋር ተጣላሁ፡፡ ባይኖር ነው እንጂ ቢኖርማ እንዴት ይህንን ሁሉ ጸሎት፤ ይህንን ሁሉ ሥዕለት አይሰማም፤ ቢያዳላ ነው እንጂ ባያዳላማ ለሌሎች ያደረገውን ለእኔ ማድረግ እንዴት ያቅተዋል ብዬ ተቀየምኩት፡፡
ቀና ብዬ ባየው ሰማዩ ቀለለኝ
አላህን ሠፈራ ወሰዱት መሰለኝ
ያለውን ወሎዬ ታስታውሰዋለህ፡፡ በ1977 ከድርቁ በኋላ ነበር እንዲህ ያለው፡፡ እኔም እንዲያ ነው የሆነብኝ፡፡
አንዷ እንደኔ የጨነቃትም
አለህም እንዳልል እንዲህ ይደረጋል
የለህም እንዳልል ይመሻል ይነጋል
ብላለች አሉ፡፡
በመጨረሻ በኑሮዬ ተስፋ ቆረጥኩና ከማይሆኑ ልጆች ጋር ገጠምኩ፡፡ የሕይወቴ መመርያ መቃም፣መጠጣት፣መጨፈር ሆነ፡፡ ተያይዘን ከከተማ እንወጣለን፡፡ እንቅማለን እንጠጣለን፡፡ ከዚያም ሊደረግ የሚቻለውን ሁሉ እናደርጋለን፡፡ ላይፍ እንቀጫለን፡፡
እናቴ አዘነችብኝ፡፡ ውጭ ያሉት ወንድሞቼ እና እኅቶቼም እየደወሉ ሊመክሩኝ ሞከሩ፡፡ ማን ሊሰማቸው፡፡ አጎቴማ ዘወትር ኀዘን ብቻ ሆነ ሥራው፡፡ ዘመዶቼ ሁሉ ለምክር ተሰለፉ፡፡ እነርሱ ሊመክሩኝ ባሰቡ ቁጥር እኔ ከእነርሱ ራቅሁ፡፡ በኋላ ላይ አጎቴን «እንደዚያ ስሆን እያየኸኝ ለምን ነበር እንደ ሌሎቹ ያልመከርከኝ» ብዬ ጠይቄው ነበር፡፡ ያለኝን አልረሳውም፡፡ «ሰው በኑሮው ተስፋ በቆረጠበት ሰዓት፣ ሰው ጥፋትን እያወቀ በሚሠራበት ሰዓት፣ ጸሎት እንጂ ምክር አይመልሰውም» ነበር ያለኝ፡፡
አንድ ሁለት ዓመት በዚህ ሁኔታ ከቀጠልኩ በኋላ ደግሞ እርሱም ሰለቸኝ፡፡ ጓደኞቼን ሁሉ ዘጋኋቸው፡፡ በሬን ዘግቼ ቤቴ መዋል ጀመርኩ፡፡ አሁን እናቴ ይበልጥ ጨነቃት፡፡ ልጄን ምን አስነኩብኝ ማለት ጀመረች፡፡ ውጭ መውጣት አስጠላኝ፡፡ ሙዚቃ እና ፊልም ከፍቼ ቤት ውስጥ መዋል፣ ማደር ጀመርኩ፡፡
አንድ ቀን ምን እንደነካኝ አላውቅም በድንገት ተነሥቼ እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ሄድኩ፡፡ ተሳለምኩና እዚያው ቁጭ አልኩ፡፡ የተቀመጥኩት ከዋናው የግቢው በር አጠገብ ነበር፡፡ አንድ መንፈሳዊ ትምህርት ይሰማኛል፡፡ ድምፁን ወደምሰማበት ዘወር ስል አንድ ልጅ በትንሽ ቴፕ ነበር የሚያሰማው፡፡ ሄጄ ጠየቅኩትና በአሥር ብር ሸጠልኝ፡፡ የሕይወቴ ለውጥ ያኔ ተጀመረ፡፡
ይቀጥላል
አረ ዳኒ ምነካህ ሰስፔንስ ፊለም አደረከው እኮ
ReplyDeleteSelam lante yihun Dn.Daniel.Eskezare minm comment setche alawkim mikniyatum malet yemfeligachewn kedmeh keleloch anbabiwochih siletenegereh zare gin yemegemeriya sew ehonalehu bye yehen byalehu. ስላላደረግክልኝ ነገር አመሰግንሃለሁ bemil arest yetsafkilin tarik keskezarewochu yemileyew wanegnaw neger lib anteltay madregih new ena yhen akahed lehulgizem tetkemibet. satinikegn hasaben silanebebkew egziabher yakbrlign!
ReplyDeleteEmebete maryam bewuluneger atleyh!!
Minew mine Dani zarem Yeketilal?????????
ReplyDeletez word of God definetly changes her direction
ReplyDelete«ሰው በኑሮው ተስፋ በቆረጠበት ሰዓት፣ ሰው ጥፋትን እያወቀ በሚሠራበት ሰዓት፣ ጸሎት እንጂ ምክር አይመልሰውም»በከፊል ብስማማበትም ሁለቱንም መሞከር ግን / ከተሞከሮ አንጻር /ተገቢ ይመስለኛል፡፡ "የሕይወቴ ለውጥ ያኔ ተጀመረ...." ለሁሉም ጊዜ አለው እንዳለው ጠቢቡ፡፡ ደግሞስ ለኛ የሚያስፈልገውን ከእኛ በላይ ያስብልን የለ እንዴ!
ReplyDeleteእውነተኛ ትረካ ሰለሆነ መጨረሻውን በጉጉት እንጠብቀዋን፡፡
ሰላመ እግዚአብሔር አይለየን
ደረሰ ዘባሕር ዳር
Selam Dn. Daniel
ReplyDeleteMinew?! Kehulu yemitelaw endezih ayinet lib manteltel yemilutin atsatsaf newu Ebakih... Tolo bel.
menem lemalet yekebdal
ReplyDeleteandegnahen cheresewna....
በጣም የተዋጣልህ ደራሲ ነህ ምናለበት መንፈሳዊ ድራማዎችን ደርሰህ ለእይታ ብታቀርብልን ጽሁፎችን እየቆራረጥክ ልበችንን ከምታንጠልጥለው…
ReplyDeleteወይ ዲ/ን ዳንኤል .. አሁን ምን አለበት ብትጨርሰዉ... እሺ ይሁን ግን ታሪኩ የቆመበትን ቦታ እንዳትረሳ።
ReplyDeleteከብሪታኒያ
dear brother pls finish it soon it is extremly suspensing! Tsegawin yabzalih !
ReplyDeleteYemitcherisew Kehone Cehrisewuna Andi gize Enanibibew Enji. Min nekah Dn. Daniel...
ReplyDeletebetam enji, this is a story of our lives though. i like it, i can't wait to hear what that sibket had done for this poor lost soul...Amlak cher yakoyen dani brother.
ReplyDeleteውድ ወንድማችን፤
ReplyDeleteምንም እንኳን እኔ የኦርቶድክስ እምነት ተከታይ ባልሆንም ድረገጽህን(ጡመራህን) በየጌዜው እከታተላለሁ።መሰረታዊውን እምነትህን ባልጋራም የአጻጻፍ ስልትህንና የማህበረ-ሰብ አመለካከትህን አደንቃለሁ። አንዳንድ ትምህርቶችንም አግኝቼበታለሁ።
በርግጥ በየጊዜው የበሰሉ ጽሁፎችን ማውጣት ቀላል አይደለም:: እኔም በዚሁ አገልግሎት ላይ የተሰማራሁ በመሆኔ ችግሩ ይገባኛል። ቢሆንም እንደዚህ ባጭሩ ሃሳብ እያለቀብህ ትቸገራለህ ብዬ መገመት ክብዶኛል። ካልሆነ በእውነት ይሄ ጽሁፍ ረዝሞ ነው የከፋፈልከው?!
በርታ!
ኸረ ተው ዳኒ........
ReplyDeleteበጣም አስተማሪ ትረካ ስለሆነ ወድጀዋለኩ! በዚሁ ቀጥሉበት!
ReplyDeleteችል-ጌት
ከባህር ዳር
I live outside Ethiopia, I like the way you write now days I mean in this blog. I like the stories being short because if it is too long I don't read the whole article. I read only some parts. If its short, I read the whole part. So please don't make it long as some people advising you.
ReplyDeleteGod bless you.
From Canada
ሰው በኑሮው ተስፋ በቆረጠበት ሰዓት፣ ሰው ጥፋትን እያወቀ በሚሠራበት ሰዓት፣ ጸሎት እንጂ ምክር አይመልሰውም»
ReplyDeleteDan, oh my God, please Continuous......
ReplyDeleteAdey from Awassa
በጣም አሰተማሪ ትረካ ነው ቀጥልበት፡፡አሁን ያለሁት ደ/ጎንደር ውስጥ ሲሆን 1999 ዓ.ም ለ1፡00 ያክል ደሴ መ/ዓለም ቤ/ቲያን ስላስተማርከኝ ሁሌም ከህሊናየ አትጠፋም፡፡
ReplyDeleteአግዚአብሄር ይርዳህ