Tuesday, June 8, 2010

አለቃ ገብረ ሐና ተረት ናቸው ወይስ እውነት ? ክፍል ሁለት

ብዙዎቻችን ስለ አለቃ ገብረሐና ከልጅነታችን ጀምሮ ሰምተናል፡፡ አለቃ እንዲህ አሉ፣ይህንን መልስ ሰጡ፣እገሌን እንዲህ ብለው ቀለዱበት ወዘተ እየተባለ ተነግሮናል፡፡ታድያ ዘመኑ እየረዘመ ሲመጣ በብዙዎች ዘንድ አለቃ በተረት እንደነ ስንዝሮ የምናውቃቸው ሰው ናቸው ወይስ በዚህች ምድር አካል ነሥተው፣ነፍስ ዘርተው ተመላልሰዋል? የሚለው ጥያቄ ይነሣል፡፡ የዚህ ጥያቄ መነሻ ምክንያቱ ሁለት ይመስለኛል፡፡ አንዱ የታላላቅ ሰዎችን ሥራ በሚገባ መዝግቦ፣መታሰቢያቸውን አደራጅቶ፣ሥራቸው በተገቢው መንገድ ለትውልድ እንዲተላለፍ የማድረግ ልማዳችን እጅግም በመሆኑ አለቃ በቃል ብቻ በሚነገረው ሥራቸው እና ታሪካቸው የተነሣ ወደ ተረትነት በመቀየራቸው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በዘመናችን ከኮምፒውተር፣ ከስልክ፣ ከመኪና እና ከአውሮፕላን ጋር የተያያዙ ቀልዶች ሁሉ በስማቸው ሲነገሩ ጊዜ አለቃ ገብረ ሐና እግዚአብሔር የፈጠራቸው ሰው ከመሆን ይልቅ በየዘመኑ የተነሣ ትውልድ ማለት የሚፈልገውን ሁሉ በስማቸው የሚልባቸው የተረት ገጸ ባሕርይ መስለው ታዩ፡፡

አለቃ ገብረ ሐና ግን በዚህች ምድር በኢትዮጵያ በደቡብ ጎንደር ዞን፣ፎገራ ወረዳ ፣ናበጋ ጊዮርጊስ አጥቢያ ተወልደው ያደጉ የተፈጥሮ ሰው ናቸው፡፡ይህንን በተመለከተ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ያገኛቸውን ያህል ማስረጃዎች ቀጥሎ ያቀርባል፡፡

1. ትውልዳዊ

ከአለቃ ገብረ ሐና የተወለዱ፣ ዘራቸውንም ከእርሳቸው ጀምረው የሚቆጥሩ ትውልዶች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ይህንን ያደረጉት ለተለየ ጥቅም ነው እንዳንል በዚህ ምክንያት ያገኙት ጥቅም የለም፡፡ ይህን የሚሉት የትውልድ እና ቀደምትን አክብሮ የማንሣት ኢትዮጵያዊ ባሕል አስገድዷቸው ብቻ ነው፡፡ ናባጋ ሄደን ብንጠይቅ የአለቃ ገብረ ሐና ዘር በዝቶ ተባዝቶ እናገኘዋለን፡፡ አለቃ ገብረ ሐና አለቃ ሥኑን ወለዱ፣ አለቃ ሥኑ ደግሞ አለቃ ኃይሉን ወለዱ፣ አለቃ ኃይሉም ዛሬ ናባጋ የሚኖሩትን ቄስ አሰጌን ወለዱ፡፡ የልጃቸው የወይዘሮ ጥሩነሽ ትውልድም እዚያው ፎገራ ይገኛል፡፡ እኔ አግኝቼ ለማናገር አልቻልኩም እንጂ፡፡ በእርግጥ የአቋቋሙ ሊቅ ተክሌ ልጅ እንዳልነበራቸው ከደብረ ታቦር ሊቃውንት እና ከተወላጆቻቸው ተነግሮኛል፡፡ ይህንን ትውልድ ስንመለከተው ከሦስቱ ልጆች እና የልጅ ልጆቻቸው መካከል ሁለቱ እንደ ገብረ ሐና «አለቃ» የሚለውን መዓርግ ደርሰውበት ነበር፡፡ቄስ አሰጌም ቢሆኑ የቤተ ክህነቱን ትምህርት ተምረውታል፡፡

ናበጋ ወርጄ የአካባቢውን ሕዝብ ስጠይቅ የአለቃ ገብረ ሐና መንደር መሆኑን፣ ትውልዶቻቸው እነ ማን እንደሆኑ ነግረውኛል፡፡ የቄስ አሰጌ ልጆችም ዘራቸውን ሲቆጥሩት አለቃን ያነሷቸዋል፡፡

2.አካባቢያዊ

ናበጋ ጊዮርጊስ አለቃ ገብረ ሐና ቤት ሠርተውበት የነበረው ቦታ ዛሬ ሸንበቆ እና ቡና በቅሎበት ይታያል፡፡ እኔ እንዲያውም ይህ ውኃ ተከትሎ የሚበቅል ሸምበቆ አለቃን አይለቃቸውም ወይ አሰኝቶኛል፡፡ያኔ ከዐፄ ቴዎድሮስ ሸሽተው ዘጌ ደሴት ሲገቡ ያገኙት እና እንቅስቃሴውን ተመልክተው የአቋቋሙን ሥርዓት የቀመሙበ ሸምበቆው ነበር፡፡ ዛሬም በቤታቸው በቅሎ ይታያል፡፡ በናባጋ ጊዮርጊስ ደብር አለቃ የሕይወታቸውን የመጨረሻ ዘመናት የጸለዩበት ቦታ፣ ያድሩበት የነበረው ጥንታዊው ዕቃ ቤት፣ የተቀበሩበት ቦታ ዛሬም ይታያል፡፡ በመቃብራቸው ላይ የአካባቢው ሰዎች አክብረው ቤተ ልሔም ሠርተውበታል፡፡ ከዚሀም በተጨማሪ በዐፄ ምኒሊክ ተሾመው ያገለገሉበት እንጦጦ ራጉኤል፣ ጎንደር በኣታ ለማርያም ደብር የአለቃ ገብረ ሐናን አገልግሎት እና ማንነት ይመሰክራሉ፡፡

3.ቅርሶች

ከአለቃ ገብረ ሐና ጋር የተያያዙ ቅርሶች ዛሬም ይገኛሉ፡፡ ይለብሱት የነበረው እና የፈትሉ እና የጥልፉ ውበት የዚያን ዘመን ጥበብ የሚያሳየው ቀሚሳቸው ቅዳጅ፣ የመጽሐፋቸው ማኅደር በናበጋ ጊዮርጊስ፤ያሠሩት ከበሮ በጎንደር በኣታ ለማርያም የአቋቋም ት/ቤት ዛሬም ይገኛል፡፡

4.የዘመነኞች ምስክርነት

አለቃ ገብረ ሐና ጋር በአንድ ዘመን የመኖር እድልን ያገኙ ሰዎች አለቃ ገብረ ሐናን በተመለከተ የገለጿቸው ነገሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ ከጣልያናዊው አንቶንዮ ዲ አባዲ ጋር ደብዳቤ ይለዋወጥ የነበረው የዋድላው አሰጋኸኝ ጥር ስድስት ቀን 1858 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ «አለቃ ገብረ ሐናን ንጉሥ መቱ ዋቸው በሽመል፡፡ ወደ ትግሬ ወደ ላስታ ተሰደዱ፡፡ እጅግ ተዋረዱ፡፡ እኔም በዋድላ አገኘኋቸው ወደ ቆራጣ ሄዱ፡፡» በማለት መግለጡ በዘመኑ አለቃ ገብረ ሐና እንደነበሩ የሚያመላክት ነው፡፡ በአለቃ ገብረ ሐና ዘመን የነበሩት አለቃ ለማ ኃይሉም ስለ አለቃ ገብረ ሐና ልዩ ልዩ መረጃዎችን ይሰጡናል፡፡

5. የትምህርት ቤት የዘር ሐረግ

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርት ቤት ትውፊት መሠረት የታላላቅ ትምህርቶች ምስከሮች የዘር ሐረግ አላቸው፡፡ የድጓ፣ የቅኔ፣ የቅዳሴ፣ የአቋቋም፣ የትርጓሜ ወዘተ...፡፡ አለቃ ገብረ ሐና በአቋቋም ትምህርት ቤት በጎንደር በኣታ የመምህራን የዘር ሐረግ ውስጥ ስማቸው ይወሳል፡፡

6. ፎቶ

አለቃ ገብረ ሐና ፎቶአቸው ለትውልድ ከተቀመጠላቸው ጥቂት የጥንት ሊቃውንት አንዱ ናቸው፡፡ በ1890 ዓም ሙሴ ሜንሮስ የተባለ ኢጣልያዊ ያነሣቸው ፎቶ ግራፍ እና አንድ እስካሁን ፎቶ አንሺውን ማወቅ ያልቻልኩት በኢንተርኔት የተለቀቀ ፎቶ ግራፍ አግኝቻለሁ፡፡

የአለቃ ቀልደኛነት ከየት መጣ?
የአለቃ ገብረ ሐና ቀልደኛነት ከየት መጣ? የሚለው ጉዳይ የብዙዎች ጥያቄ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን የተሟላ መልስ ለማግኘት ያስቸግራል፡፡ ነገር ግን የተሻለ ግምት ለማቅረብ ብቻ እንሞክራለን፡፡ በአንድ በኩል የደብተራ ዘነብ፣ የአለቃ ገብረ ሐና፣ የዲማው ካሣ ጉዱ በአንድ ተመሳሳይ ዘመን መገኘት ያ ዘመን ሊቃውንቱ በአዲስ መሥመር /አፈንግጦሽ/ የተጓዙበት ዘመን ይሆን? ያሰኘናል፡፡ ደብተራ ዘነብ ያዘጋጁት መጽሐፈ ጨዋታ ቅኔውን እንዴት አድርገው እያዋዛ ለሚያስረዳ አገላለጥ እንደተጠቀሙበት፣ አለቃ ለማ ኃይሉ ሕልውናውን የመሰከሩለት፣ በኋላም ታላቁ ኢትዮጵያዊ ደራሲ ክቡር ዶክተር ሐዲስ ዓለማየሁ በፍቅር እስከ መቃብር መጽሐፋቸው የኪነ ጥበብን መልክ ቀብተው ያቀረቡት ጉዱ ካሣ ቅኔውን ሥርዓቱን ለመተቸት እንዴት እንዳዋለው ስናጤን እነዚህ ሰዎች የጎጃምን ቅኔ ሲቀምሱ ማን? ምን? አቀመሳቸው እንድንል ያደርገናል፡፡ ምናልባትም አንድ ተመሳሳይ መምህር ገጥሟቸው ይሆን ያሰኘናል፡

በሌላ በኩል ደግሞ ፎገራን የሚጎበኝ ሰው ስለ አለቃ የሰላ ቀልድ አንድ ነገር ይጭርበት ይሆናል፡፡ ፎገራ ከኦሮምያዋ ግንደ በረት ጋር የተያያዘው የባርያ ንግድ አንዷ መተላለፍያ ነበረች፡፡ ወደ ደብረ ታቦር መንገድ ወጣ ብላ የምናገኛት «ኢፋግ» የባርያ ንግድ ማረፊያ ነበረች፡፡ ወረታ ፣በጠቅላላውም ፎገራ በጥንቱ የሲራራ ንግድ ዋነኛ መናኸርያ ነበረች፡፡ ታድያ በዚህ ምክንያት ይመስለኛል በፎገራ የትግራይ፣የኦሮሞ እና የአማራ ሕዝቦች ተጽዕኖ ይታይ በታል፡፡ አለባበሱን፣ የፀጉር አቆራረጡን፣ ከወገብ በላይ ራቁት መሆንን ስትመለከቱ የእነዚህን ሕዝቦች አሻራ ታያላችሁ፡፡ በአካባቢውም በልዩ ልዩ ሕዝቦች የሚጠራ መንደርም አለ፡፡ለምሳሌ የትግሬ መንደር፡፡ ይህ ሁኔታ በአለቃ ገብረ ሐና ሕይወት ውስጥ ተጽዕኖ አሳድሮ ይሆን? አለቃ አማርኛም ኦሮምኛም ትግርኛም የተቀላቀለበት ቀልድ የሚቀልዱት በዚህ ምክናያት ይሆንን አሰኝቶኛል፡፡

ሌላም ነጥብ እናንሣ፡፡ የፎገራ ገበሬዎች ከዘመን የመፍጠን ጠባይ ይታይ ባቸዋል፡፡ ለምሳሌ ከኮርያ ባለሞያዎች የሩዝን ሁኔታ ተረድተው ለገበሬዎች ያስፋፉት አንድ የፎገራ ገበሬ ናቸው፡፡ ዛሬ የፎገራን መሬት ያለበሰው ሩዝ የኒህ ትጉ ገበሬ የአሠረጫጨት ዘዴ ውጤት ነው፡፡ የግብርና ባለሞያዎች በአዳዲስ ዘር አሠረጫጨት እና ገበሬውን ከአዳዲስ ቴክኖሎጂ ጋር በማለማመድ ጉዳይ ከኒህ ገበሬ የሚቀስሙት ይኖር ይሆን? አስቲ እንጨምር፡፡ የፎገራ ገበሬ የሚያመርተው ሩዝ ዘለላው እሾህ ስላልነበረው ወፍ እየጠረጠረ ያስቸግረው ነበር አሉ፡፡ ታድያ ከዘመን የቀደሙ አንድ ገበሬ ዛላው እንደ ገብስ እሾሃማ የሆነ ዘር በምርምራቸው ማግኘታቸውን፣እንዲያውም በስማቸው ይህንን ዘር ለመሰየም እንቅስቃሴ መጀመሩን ከባለሞያዎች ሰምቻለሁ፡፡ ይህ ከዘመን አፈንግጦ መጓዝ የሀገሩ ልማድ ይሆን? ገና ብዙ የአንትሮፖሎጂ፣የግብርና እና የታሪክ ምርምር የማሻው በመሆኑ ከኔ ይልቅ በዚህ ሞያ ልሒቅ ለሆኑት እንዲቀጥሉበት አደራ እላለሁ፡፡

የአለቃ ገብረ ሐናን ቀልዶች ስንመለከት ቅኔያውያን ናቸው፡፡ በኋላ በዝር ዝር ለማስረዳት አንደምሞክረው የአለቃ ቀልዶች አመራማሪ፣ አስደናቂ፣ እንደ ጥቅስ ሁልጊዜ ሊነገሩ የሚችሉ፣ ፈጣን ናቸው፡፡ ይህ የአለቃ ቀልዶች ጠባይ ከምሁርነታቸው የመነጨ ይመስላል፡፡ አንድን ነገር ገልብጠው ማሰብ ይቸሉ ነበር፡፡ ጣና ሐይቅ ወስጥ የሸንበቆውን ንቅናቄ ተመልክተው ከዝማሜው ጋር ማዋሐዳቸው የአእምሮአቸውን ስለት ያስረዳናል፡፡ ከተሰጥኦዋቸው ጋር ቀልዳቸውን ያስዋበው የመላው ዕውቀታቸወ ነው፡፡

የአለቃ ገብረ ሐና ሰብእና እና አስተዋጽዖ

ሰብእና

ብዙዎቻችን በቀልዳቸው ብቻ የምናውቃቸው አለቃ ገብረ ሐና በብዙ ሞያዎች የተካኑ ነበሩ፡፡ ባለ ቅኔ፣ የአቡሻክር እና የመርሐ ዕውር ሊቅ፣ የድጓ ምሁር፣ የፍትሐ ነገሥት ሊቅ፣ የአቋቋም ዐዋቂ፣ የትርጓሜ መጻሕፍት መምህር ነበሩ፡፡ታደያ በሥራዎቻቸው እና በቀልዶቻቸው የእነዚህን ነፀብራቅ እናገኛለን፡፡ አለቃ ለማ ኃይሉ ስለ ሊቅነታቸው ሲመሰክሩ «የሞያ መጨረሻ እርሳቸው አይደሉም ወይ? የሐዲስ መምህር ናቸው፣ ፍታነገሥትን በርሳቸው ልክ የሚያውቀው የለም፤ ይኸ የቁጥሩን ÷መርሐ ዕውሩን፣ አቡሻከሩን የሚያውቅ ነው ባለሞያ፡፡ መቼም ለዚህ ለዝማሜ እሚባለው፤ ለመቋሚያ፤ እገሌ ይመስለዋል አይባልም፤ ከገብረ ሐና ፊት የሚዘም የለም» ይላሉ፡፡ ብላቴን ጌታ ኀሩይ ወልደ ሥላሴም «አለቃ ገብረ ሐና እጅግ የተማሩ የጎንደር ሊቅ ነበሩ፡፡ በዚህም ላይ ደግሞ ኃይለ ቃልና ጨዋታ ያውቁ ነበር» በማለት ይገልጧቸዋል፡፡ በጎንደር አድባራት ሊቀ ካህንነት፣ በአዲስ አበባ እንጦጦ ራጉኤል እና በአቡነ ሐራ ገዳም ተሾመው ማገልገላቸውን ስናይ ይህንን ዕውቀታቸውን ያስረዳልናል፡፡ እንዲያወም በዚያ ዘመን ከከበሩት አድባራት አንዱ አቡነ ሐራ ደንግል ገዳም ስለነበር ለዚያ አለቃ ሆኖ መሾም የታላቅነት ምልክት መሆኑን አለቃ ለማ ገልጠዋል፡፡

.አለቃ ገብረ ሐና የድኾች ጠበቃ

አለቃ ገብረ ሐና ምንም ከመኳንንቱ እና ከመሳፍንቱ ጋር ቢውሉ፣ምንም እንኳን የእንጦጦ ራጉኤል ሰዎች እንደሚናገሩላቸው በዐፄ ቴዎድሮሰ ቤተ መንግሥት ከምኒሊክ እና ከእቴጌ ምንትዋብ ቀጥለው ግብር የሚቀመጡት ገብረ ሐና ቢሆኑም ድኾች ሲጨቆኑ እና ሲያዝኑ ግን አይወዱም ነበር፡፡ በአንድ ወቅት የአቡነ ሐራ ገዳም አካባቢ ርሃብ ገብቶ ገበሬው ሲቸገር ቢያዩ «እናንተ ባገኛቸሁ ጊዜ ለአቡነ ሐራ እንደሰጣችሁ ሁሉ እናንተ ሲቸግራችሁ ደግሞ አቡነ ሐራ ይሰጧችኋል» ብለው ከሥዕለት የተሰበሰበውን ገንዘብ አውጥተው ለገበሬዎች አከፋፈሉት፡፡ በዚህ ጉዳይ ተከስሰው ከፍርድ ሚኒስቴሩ ከአፈ ንጉሥ ነሲቡ ዘንድ ቀርበው ሊፈረድባቸው ነበር፡፡ በኋላ ግን ሊቀ መኳስ አባተ ቧ ያለው ዐፄ ምኒሊክ አለቃ ገብረ ሐናን ሲያደነቁ እንደሚሰሙ እና አፈንጉሥ ለሚሰጡት ፍርድ እንዲጠነቀቁ በማመልከታቸው ጉዳዩ ወደ ዙፋን ችሎት ተመራ፡፡ ዐፄ ምኒሊክም አለቃ ገብረ ሐናን የፍትሐ ነገሥቱ ሊቅ አንተ አይደለህም ወይ? እስቲ ምን ይላል ንገረን? አሏቸው፡፡ አለቃም «ፍትሐ ነገሥቱማ ሲሦውን ለካህናት፣ሲሦውን ለሠራያን ይገባል ይላል፡፡ እኔም ክፉ ቀን ስለሆነ ለሕዝቡ አካፍየዋለሁ፡፡ አቡነ ሐራ አባታቸውን አይጦሩበት፣ልጃቸውን አይድሩበት» ሲሉ መለሱላቸው፡፡

አለቃ ገብረ ሐና ከምኒሊክ ባለሟሎች ጋር ተጣልተው ለመጨረሻ ጊዜ አዲስ አበባን ለመልቀቅ ያበቃቸውም መኳንንቱ እና መሳፍንቱ ግብዝናውን እየተሾሙ የድኻውን ካህን መሬት እየወሰዱ ካሀኑን በቶፍነት ስም ጭሰኛ ማድረጋቸውን በመቃወማቸው ነበር፡፡ አለቃ ይህንን አሳዛኝ አሠራር ፊት ለፊት ተቃውመውታል፡፡ በዚህም ምክንያት ከአዲሰ አበባ ይወጡ ተብለው ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በቅተዋል፡፡

ለ. አለቃ ገብረ ሐና ንጉሥ የማይፈሩ

ንጉሥ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ በሚባልበት በዚያ ዘመን ነገሥታቱን እና መኳንንቱን በመገሠጽ አለቃን የሚወዳደር አልነበረም፡፡ ለአንድ ቤተ ክርስቲያን አምስት ልዑክ ይበቃል ብለው ዐፄ ቴዎድሮስ ያነሡትን ሃሳብ አለቃ ገብረ ሐና አልተቀበሉትም፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስ ያሠሩት ቤተ ክርስቲያን ሲመረቅ አለቃ ተጋብዘው ነበር፡፡ ዐፄ ቴዎድሮስም እንዴት ነው ቤተ ክርስቲያኑ ብለው ቢጠይቋቸው ማነሡን ለመግለጥ «ለሁለት ካህን እና ለሦስት ዲያቆን በቂ ነው» አሏቸው፡፡ በዚሀም ከቴዎድሮስ ጋር ተኳረፉ፡፡

አስተዋጽዖ

1.ዝማሜ

አለቃ ገብረ ሐና ለቤተ ክርስቲያን እና ለኢትዮጵያ ካበረከቱት ነገር አንዱ «የተክሌ ዝማሜ» የሚባለው ነው፡፡ አለቃ ገብረ ሐና ይህንን የመቋሚያ ስልት ያዘጋጁት ከዐፄ ቴዎድሮስ ሸሽተው ዘጌ በገቡ ጊዜ ነበር፡፡ በዚያ የነበረውን የሸንበቆ ውዝዋዜ ተመልክተው ከአቋቋሙ ስልት ጋር አዋሕደው ከባሕታዊ ጸዐዳ ገብረ ሥላሴ ጋር በመሆን ነበር፡፡ ባሕታዊ ጸዐዳ ገብረ ሥላሴ ወደ ዓለም ስላልተመለሱ አለቃ ገብረ ሐና ይህንን አዲስ ዝማሜ ይዘው ጎንደር ገቡ፡፡ ወዲያወም የአቋቋሙ መምህር አለቃ ገብረ ሐና ለተማሪዎቻቸው አዲሱን ዝማሜ ማስተማር ጀመሩ፡፡ጎንደሮች ሲያገለግሉ ሸማቸውን ታጥቀው ስለነበር በሚያዘሙበት ጊዜ በተመስጦ ወዲያ እና ወዲህ ሲሉ ሸማቸውን እያስጣለ ቢያስቸግራቸው ካህናቱ ተመካክረው አለቃ ይህንን ዝማሜ እንዳያስተምሩ ወሰኑባቸው፡፡ በዚሀ ጊዜ አለቃ ለልጃቸው ለተክሌ ደብቀው ማስተማር ጀመሩ፡፡

ተክሌ የደርቡሽን ወረራ ሸሽቶ ወሎ ራስ ሚካኤል ዘንድ በሄደ ጊዜ ተንታ ሚካኤል ሲመረቅ ያንን ተደበቆ የኖረ ዝማሜ አወጣው መኳንንቱ እና መሳፍንቱ ፣ሕዝቡ እና ካህናቱ ተገርመው ያዳምጡት እና ያዩት ጀመር፡፡ ሲጨርስም ራስ ሚካኤል በተንታ ሚካኤል ይህንን ዝማሜ እንዲያሰተምር አደረጉ፡፡ በኋላም የደብረ ታቦሩ ራስ ጉግሣ ራስ ሚካኤልን ለምነው ለደብረ ታቦር ኢየሱስ አለቃ አድርገው ተክሌን ወሰዱት እርሱም በዚያ ሲያስተምር ቆይቶ እዚያው ዐረፈ፡፡ ዝማሜውም በስሙ «ተክሌ» እየተባለ ተጠራ፡፡

እንዲያውም ተክሌ በሞቱ ጊዜ

ተከሌ ገብረ ሐና ተከተተ ጣቱ
መንክሩን ክሥተቱን የዘመመበቱ

ብላ አልቃሽ ገጥማ ነበር፡፡ ራስ ጉገሣም «ምን ተክሌ ሞተ ትሉኛላቸሁ ደብረ ታቦር ኢየሱሰ ፈረሰ በሉኝ እንጂ፤ደብረ ታቦር ኢየሱስ ቢፈርስ ከዚህ አስበልጬ እሠራው ነበር ተክሌን ግን ከየት አገኘዋለሁ» ማለታቸው ይነገራል፡፡

2. ሰም እና ወርቅ ቀልድ

ብዙዎቻችን አለቃን የምናውቃቸው በሰም እና ወርቅ ቀልዳቸው ነው፡፡ ሌቨን ዶናልድ የተባሉ ደራሲ «ሰም እና ወርቅ»» Wax and gold በተሰኘው መጽሐፋቸው አለቃ ገብረ ሐና በሰም እና ወርቅ ቅኔያቸው፣ በቀልዳቸው እና በፈጣን መልሳቸው እንዲሁም በሂሳቸው የታወቁ መሆናቸውን ገልጠዋል፡፡ የአለቃ ገብረ ሐና አብዛኞቹ ቀልዶች ሰም እና ወርቅ ቅኔ ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ የኢትዮጵያን የግእዝ ቅኔ ስልት የተከተለ ነው፡፡

ምንጭ  ዐረፈ ዓይኔ ሐጎስ፣ አለቃ ገብረ ሐናና አስቂኝ ቀልዶቻቸው፣ አዲስ አበባ፣1979 ዓም፤ አዲስ ዘመን ጋዜጣ፣ታኅሣሥ 10፣1978 ዓም(ምን ሠርተው ታወቁ) ዓምድ) መንግሥቱ ለማ፣ መጽሐፈ ትዝታ ዘአለቃ ለማ ኃይሉ ወልደ ታሪክ፣ አዲስ አበባ 1959 ዓም፣ገጽ 137-138፤ኅሩይ ወልደ ሥላሴ፣የሕይወት ታሪክ፣አዲስ አበባ፣1918 ዓም፣ገጽ 89፤ ኤልሳቤጥ ገሠሠ፣ በአለቃ ገብረ ሐና የሚነገሩ ቀልዶች፣ ለኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ ክፍል ለዲግሪ ማሟያ የቀረበ፣ አአዩ፣ 1974 ዓም፤ Sven Rubenson, ed. Acta Ethiopica: Tewodros and His Contemporaries 1855-1868, p259አለቃን የተመለከቱ የፎቶ ማስረጃዎች

ሳምንት እንገናኝ

46 comments:

 1. Selam Dn Daniel;
  Thank you for this detailed description of Aleqa GH. I suspect that you may have pictures too. It would be great to insert a picture here and there.

  ReplyDelete
 2. ያስደስታል፡ ቀጥልበት።

  ReplyDelete
 3. It is always great to read your presentation keep it up.I think you have been keeping this all t`ll the time comes and know it is about time give it away.I always can`t wait Tuesday and Friday to learn some thing new.It is so interesting.God is great which allows you to do this for us and God bless you and keeps you save all the time.

  G MN,USA

  ReplyDelete
 4. ዳንኤል በዚህ ብሎግ በሚያቀርባቸው ሃሳቦች ብንስማማም፣ ባንስማማም ነገር ግን ይህንን መሰሉን መድረክ እንፈልገዋለን፡፡ ጊዜውን ሠውቶ ማኅበረሰቡን ለማገልገል የሚነሣን ሰውም የማገዝ ግዴታ እንዳለብን አስባለሁ፡፡ በመሆኑም ለምን እኛ አንባቢዎች ዳንኤልን እንዲህ ወይንም እንዲያ አድርግ ከምንለው የበኩላችንን አስተዋጽዖ በማድረግ ብሎጉን አናስተዋውቅም፡፡ እኔ የሚከተሉትን ሃሳቦች አቅርቤያለሁ፡፡

  1.በሀገር ውስጥ በሚገኙ ጋዜጦች ከፍለን ብናስተዋውቅ፡፡ ይህንን ሥራ ለመሥራት ለአንድ ማስታወቂያ 900 ብር ማለትም 80 ዶላር ያህል ብቻ ያስፈልገናል፡፡ በአምስት ቦታዎች ብናስተዋውቅ 4500 ብር ወይንም 300 ዶላር ያህል ብቻ ያስፈልገናል፡፡

  2.ለምናውቃቸው ሰዎች መንገር፣ ኢሜይል ማድረግ

  3.ብሎጉን የሚያስተዋውቅ ካርድ አዘጋጅተን ለምናውቃቸው ሰዎች መስጠት፡፡
  4.ሌሎች ዌብሳይቶች ሊንክ እንዲያደርጉት ማድረግ

  እስኪ ሌሎቻችሁም ጨምሩበት፡፡ ሌላ ሰው እንዲሠራ ሃሳብ ከምንሰጥ በጎ ፈቃደኞች ተነጋግረን አንድ ነገር እናድርግ

  ReplyDelete
 5. ሰው ሲቸገር ከመርዳት እንዳይቸገር ማገዝ ማለት ከፍ ብሎ የተገለጸው ሃሳብ ነው፡፡ የሚሰራን ማበረታተት ተገቢ በመሆኑ ድረ ገጹን በልዩ ልዩ መንገዶች አቅም በፈቀደ መንገድ ማስተዋወቅ ጥሩ ሃሳብ ነው፡፡

  ReplyDelete
 6. ውድ ወንድማችን፣
  እባክህ የአለቃን ፎቶ ማየት ስለምንፈልግ ጫንልን፣ እናመሰግናለን፡፡
  እህቶችህ

  ReplyDelete
 7. i share this idea.
  let us do our own part

  ReplyDelete
 8. ስለ እኝህ ታላቅ አባት እንድናውቅ ስላደረከን እናመሰግናለን ብሎጉን ለማስተዋወቅ አንድ አስተያየት ሰጨ ያቀረበው ሐሳብ በጣም መልካም ነው፡፡ እኔ በራሴ ለማውቃቸው ሰዎች ብሎጉን ኢሜል አድርጌላቸዋለሁ እነሱ ደግሞ በተራቸው ቢያንስ እያንዳንዳቸው ለ10 ለ10 ሰዎች እንዲሰጡ እነግራቸዋለሁ እርግጠኛ ነኝ በእኔ በኩል 20-30 ላሉ ሰዎች ይዳረሳል ብሎ አምናለሁ፡፡ አገር ውስጥ ያለን እያንዳንዳችን እንዲህ ብናደርግ ብሎጉ ብዙ አንባቢ እና ተማሪ ያገኛል ብዬ አስባለሁ፡፡ እ/ር ይጨመርበት ዳኒ በጣም እናመሰግናለን እ/ር ያበርታህ

  ማኪ
  አ.አ

  ReplyDelete
 9. Thank you anonymous for your promotion ideas. I am always doing what you mention on No. 1 and 4.

  Long live to Dn.Daniel.

  ReplyDelete
 10. በጣም አስደሳች ብሎግ ነው ከልቤ ወድጄዋለሁ በአአዩ የምንገኝ ተማሪዎች በጣም እየተከታተልነው ነው ዳኒ እናከብርሃለን በርታ
  እግዚአብሔር ካንተ ጋር ይሁን
  ፍፁም

  ReplyDelete
 11. nice danie , i think you are one of his generation. isn't it right

  ReplyDelete
 12. DN. DAINEL thankyou for ur information KEEP IT UP!

  ReplyDelete
 13. 1. መልካም ሐሳብ ነው! ብሎጉን ለማስተዋወቅ የተደረገው ያለው በተጨማሪ አብሮ መታሰብ ያለበት ነገር ቢኖር ኢንተርኔት መጠቀም የማይችሉ የማንበብና የማወቅ ፍላጎትና ጥረት ያላቸው ወገኖቻችንንም ማሰብ ይገባል እኔ የበኩሌን አንደ ማስተር ፐሪንት አድርጌ በሰንበት ት/ቤታችን የሚገኙ ተማሪዎች በየሳምንቱ እንዲያነቡት በቤተ መፃህፍታችን እንዲቀመጥ አድርጌአለሁ፡፡ የፈለገውም ፎቶ ኮፒ እያደረገ ይወስደዋል፡፡ ልምዴንና ያገኘሁትን ማስተላለፍ እንዳለብኝ አውቃለሁ፡፡ ምክንያቱም ውይይቶች፣ጥናታዊ ጸሁፎች ለቤ/ክርስትያን ያለቸውን ፋይዳ ከህፃናትና ከታዳጊዎች መጀመር አለበት ብዬ ስለማምን ነው፡፡ ልምዳችንን እንድንለዋወጥ ሐሳቡን ያቀረብከው/ሽው እግዚአብሔር ይባርክሽ፡፡

  2. ለዲ. ዳንኤል ክብረትም ለጥናቱ ያስፈልጎታል ብለን የምናስበውን መረጃዎችም ብናቀርብ ወይም የተደረጉ ጥናቶችን በእርሱ አማካኝነት ቢወጣም መልካም ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

  3. በዚሁ ርእስም ሁሉም ሰው አስተያየት እንዲሰጥበት የመወያያ ርእስ ቢከፈት፣መጠይቆች ቢኖሩ/በዌብ እንደየቅዱስ ያሬድን 1500ኛ ዓመት ለማክበር የበኩልዎንለማድረግ ዝግጁ ነዎት አይነት፡፡

  እግዚአብሔር በአንድም በሌላም ያስተምራል
  ኪዳነማርያም ዘደብረ ይድራስ

  ReplyDelete
 14. "ነገርን ከስሩ ውሃን ከጥሩ" አይደል የሚባለው በርታ ቀጥልበት፡፡

  ReplyDelete
 15. All the above comments are crucial need to be encouraged ..good idea ..i hope also this kind of encouragement give Dani moral strength to go ahead ..me i agree specially on promoting the blog ..i started to print the articles and go home give friends ...i will strongly do the same for the future...God may support us and bless Ethiopia ..and also good health ,long live for dani who take the initiative

  ReplyDelete
 16. በጣም የሚገርም ቅንብር:: እግዚአብሔር ሥራህን ይባርክ:: ከዚህ በላይ የተሰጡትን አስተያየቶች እደግፋለሁ የበኩሌን ለመወጣትም እራሴን አዘጋጃለሁ::ሌላው መስጠት የምፈልገው አስተያየት ለዳንኤል:
  1.የአለቃን የመጨረሻ ህይወት መረጃ ካለህ ብታቀርበው መልካም ነው:: በተለይ አሟሟታቸውና የቀብር ስርዓታችው ምን ይመስላል::
  2."የአለቃ ቀልደኛነት ከየት መጣ?" የሚለውን ለመመለስ ያቀረብከው ትንታኔ በጣም ግሩም ነው:: አንድ ነገር መጨመር የምፈልገው ቢሆር ግን ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው ልዩ ስጦታ ወይም ሳይንሱ እንደሚለው ልዩ ጅን ኖሯቸው ሊሆን እንደሚችልም ከሀሳብህ ብትጨምርበት መልካም ነው::

  ReplyDelete
 17. GOOD JOB KEEP IT UP...WE ARE WAITING..

  ReplyDelete
 18. በስመ ስላሴ
  ዲ/ን ዳኒ በእውነት እኝህን ኢትዮጵያዊ ሊቅ እና ባለ ብዙ ስራ አባት ዳግም ወለድካቸው! በጣም ነው የገረመኝ ፣በቅርብ ዘመን ነበሩ ሊያውም ታላቅ ስራ የሰሩ አባት ከምኔው የተረት አባት አደረግናቸው? የአያሌ ታሪክ ባለቤቶች ግን ያላወቅናቸው ስንቶች አበው ቀርተው ይሆን? ወይኔ ትውልዱኮ ‘የፕሮፌሰር ሳቤክ’ አይንት ነገር ተጠናውቶት ነው፤ ደግሞምኮ ‘ተሳቢም’ ሆነን ነው፤ አለምን ያስደመመ ስራ የሰሩ አባቶቻችንን ፤ሊያውም ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነን ምንም ሳናውቃቸው በፈረንጆች ተስበን ዛሬ ስለ አንድ ነጭ ስ ተጫዋች ብንጠየቅ ምን ያህል ልንናገር እንደምንችል ሁሉም ‘ኢትዮጵያውያን’ እናውቀዋለን፡፤ ትውልድ ሆይ ታሪካችንን እንወቅ ፤ ጥናት እናድርግ ፤ እንመራመር፤ የተሰወሩትን ገልጠን በስራቸው እንጠቀም ፤ያለዚያ መማራችን ምኑ ላይ ነው፤፤ የታሪክ ተጠያቂ አንሁን እባካችሁ!

  ዲ/ን ዳኒ ቃለ ህይወት ያሰማህ፣ሌሎችም ስራህን ይከተሉ ዘንድ አመኛለሁ
  ደረሰ ዘባህርዳር

  ReplyDelete
 19. Dn.Daniel
  Egziabeher Kalehiwoten Yasemalin
  I will do from my side what I can advertising the site using sms,email,facebook,and also sharing the ideas to my friends. Thank you for those who supports the above comments!!

  ReplyDelete
 20. DN. DAINEL thank you for the information you haven given us . I think this informatoin is very importatant to undestand about our previous wrong attitudes towards the different intellectuals in the past.

  ReplyDelete
 21. እግዚአብሔር ቃለህይወት ያሰማልን
  እስከ መጨረሻዋ ህቅታ ድረስ በአገልግሎት እንዲያጸናህ አምላከ ቅዱሳን ይርዳህ: ይጠብቅህም።

  ReplyDelete
 22. Please continue like this history so we will now to many things.

  ReplyDelete
 23. be sehaqe wbe selaqe yebewee seytane belawal aned ye hadis memhir.Yehayse negere endate new????

  ReplyDelete
 24. I do not have a word to say something about Aleka. I already convinced myself that Aleka Gebrehana is imaginary guy. Thanks for Daniel you make it clear. please keep it in hard copy to pass it for generation.

  ReplyDelete
 25. አለቃ ገ/ሃና ሀገር እኔ ሰራ እሰራለሁ
  ታሪኩን ከናበጋ ህዝብ በላይ ታውቀዋለህ
  እግዚአብሄር ይስጥልን
  ዲ/ን አበበ ዘ ደ/ጎንደር,ባ/ዳር ዩኒቨርሲቲ

  ReplyDelete
 26. We know you are trying to renew your name and later you will change all the comments for trade center.

  ReplyDelete
 27. Gn Yaleka Gebrehanan Tarik lemetsaf mn anesasah Wondme Daniel.

  ReplyDelete
 28. Gn yand sew tarik lemetsaf mn anesasah wondmachn Daniel.

  ReplyDelete
 29. 10q dani ! Longlive...

  ReplyDelete
 30. ታድያ ዘመኑ እየረዘመ ሲመጣ በብዙዎች ዘንድ አለቃ በተረት እንደነ ስንዝሮ የምናውቃቸው ሰው ናቸው

  ReplyDelete
 31. What a hilarious presentation! I know that Dn Daniel has got unwavering stamina to depict those of our Icons! I found the view on Aleka G/Hanna quite informative and of intellectual value. I would like to have it in a form of academic journal with all necessary text citations etc and posted for such purposes thereof!
  Thanks Dn Daniel,
  With Love & Respect!

  ReplyDelete
 32. It is wonderful, God bless you.
  እግዚአብሄር ይባርክህ ረጅም እድሜ ይስጥልን፡፡

  ReplyDelete
 33. Dear Dn.
  Thanks for such extensive work on 'aleka gebrehana'. entiftif yibelbih.silasie bezihim beziam alem ende tsehay ende kokeb yabruh,
  kezemenu buda yitebikih

  ReplyDelete
 34. እግዚያብሄር ይስጥልን መልካም ነው ይቀጥሉበት::

  ReplyDelete
 35. thankyou! kalehiwot yasemalin..

  ReplyDelete
 36. keep up dani its interesting!!

  ReplyDelete
 37. I want to inform everybody concerned about the issue that Debre tabor university instructors are on the way to study this and other historical sites scientifically. any support for that would be highly appreciated.

  ReplyDelete
 38. i did not suspect such,but AL/GH has other crusial contribution
  regarding to religious prosperity ,so if it is possible to get such info easly, thos are the main intonation for current fractered citizen.
  the rest is amended by the allowance of GOD.
  mechereshahn yasamirlih mechem ...........

  ReplyDelete
 39. really you are a man of Ethiopian.i wonder you for your deep explanation about 'Aleka Gebrehana'. keep it up on.

  ReplyDelete
 40. በአለቃ ገብረሐና ላይ በፃፍከው ፅሑፍ በጣም ተደስቻለሁ! እግዚአብሔር ሥራህን ይባርክ!

  ReplyDelete
 41. If you can post pictures of his descendants (family)

  ReplyDelete
 42. ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የሃገራችንን ቱባ ታሪክ በተፈጠሩ መድረኮች እና በጥረትህ ቴክኖሎጅን ተጠቅመህ ለማስተዋወቅ የምታደርገው ተጋድሎ እጅግ ደስ የሚልና የሚበረታታ ነው፡፡ስለሀገር እውነተኛ ታሪክ ምንነት ለማወቅ ና ለማሳወቅ የሚጥር ሰው ሃገሩን የሚወድ ሰው በመሆኑ ይህን ብሎግ ከፍተህ የታሪካችንን እውነታዎች ከአንተ እይታ እና መረጃ አንፃር ማቅረብህ ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል፡፡ በርታ ቡዙሃኖች ላይክ እንዲያደርጉት እናስተዋውቃለን፡፡  ReplyDelete
 43. አለቃ ገብረሃናን ፍለጋ!!
  ✍የሺሀሳብ አበራ
  አለቃ ገብረሃና የልብወለድ ገፀባህሪ አሊያም ተራ የተረት ማሟያ አይደሉም፡፡ ተፈጥሮን የመመረመሩ፣ፖለተካን ያመሰጠሩ፣ፍርሃት ና አድርባይነትን ገድለው ነገስታቱን የሞገቱ ባለምጡቅ ምናብ መምህር ናቸው፡፡ አለቃ ገብረሀና ደስታ ህዳር ወር ላይ በ1814 በደብረታቦር አውራጃ ፎገራ ወረዳ ተወለዱ፡፡አባታቸው፣ደስታ ተገኝ፣እናታቸው ደግሞ መልካሜ ለማ ይባላሉ--ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፡፡
  ❖❖❖
  አቡጊዳ ፊደልን በጎንደር፣ቅኔን እስከ አቋቋም አባይን ተሻግረው በጎጃም ተምረዋል፡፡መማር ብቻ አይደለም የተማሩትን ተንትነው በ19ኛው መቶ ክፍለዘመን አስደማሚ ፍልስፍና ይዘው መጥተዋል ፡፡ ነገስታቱን ተችተዋል፡፡አምላክን ሳይቀር"ጠላታችሁን ውደዱ ካልክ፣አንተም ሰይጣንን ወደህ አሳየን?" ሲሉ በአመክንዮ (logic) ጠይቀዋል ፡፡
  """"""'
  የአፄ ቴወድሮስን ባለሟል ብላታ አድጎን "አድግ" እያሉ እንደተኮላተፉ በግዕዝ ይጠሩት ነበር፡፡አህያ ነህ ማለት ነው፡፡በዚህም መይሳው ተቆጥተው"" ፍትሀነገስት ፃፍ፡፡ፍርድ ስጥ፡፡ቀልድ ተው፡፡ገንዘብ ይሰጥሃል"ሲሉ መከሯቸው፡፡ አለቃ ግን የአፄ ቴዎድሮስን ተግሳፅ አቃለው በመኳንንቱ ማሽሟጠጣቸውን ቀጥለውበታል፡፡
  """"""""
  ጎንደር የአቡነ ሀራ ገዳም ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አለቃ ገብረሃና፣አፄ ቴወድሮስ የካህናትን የቤተክርስቲያን የአገልግሎት ምጣኔ እና መሬት ሲያስተካክሉ፣አለቃ ካህናቱ በአፄ ቴወድሮስ ላይ እንዲዘምቱ አድርገዋል- አረፋይኔ ሀጎስ፡፡
  """""'
  አፄ ቴወድሮስን በክፋት መተናኮል፣ ሞትን በደላላ የማፈላለግ ያህል ከባድ እንደሆነ ስለገባቸው ወደ ትግራይ ኮበለሉ፡፡ግን መይሳው እንኳንስ ትግራይ እየሩሳሌም አትርቀኝም ስለሚሉ እንደማያመልጡ አውቀው ወደባህር ዳር መጥተው ዘጌ ገዳሙ ውስጥ ተደበቁ፡፡ መይሳውም ለገዳሙ ክብር ሲሉ ማሯቸው፡፡ የፍትሀነገስት የህግ ተመራማሪ፣የፍልስፍናና የቅኔ ቀንዲል የሆኑት አለቃ በጣና ገዳማት ውስጥ እያሉ "ዝማሜ" የተባለውን ያሬዳዊ ወረብ ከሸንበቆ ውዝዋዜ ተመልክተው ፈጥረዋል ፡፡ዛሬ ዝማሜው ተክሌ ዝማሜ ይባላል በልጃቸው ስም- ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፡፡
  """"""'"
  በነገራችን ላይ መልከቀና የነበሩት አለቃ፣በጨዋታ አቂነታቸው ና በመልካቸው በሴቶች ዘንድ ሲበዛ ይወደዱ ነበር፡፡ዳሩ ግን ለሀይማኖታቸው ሲሉ ያለወሲብ ብዙ ዓመት ከቆዮ በኃላ የጎንደሯን ወይዘሮ ማዘንጊያን አግብተው ተክሌ፣ጥሩነሽ....የሚባሉ ልጆችን ወልደዋል፡፡
  """""""''''''''''''
  ያለቃ ገብረሀና ዘመን የአፈንጋጮች ዘመን ነበር፡፡ የአፄ ቴዎድሮስ ደጎነ ምናባዊ እይታ፣የአፄ ቴዎድሮስ ዜና መዋዕል ፃህፊ ና ተመራማሪው አለቃ ደብተራ ዘነበ ኢትዮጵያዊ ፍልስፍና ፣የዲማው አፈንጋጩ ና የሀሳብ ነፍሰጡሩ ካሳ ጉዱ ርዕዮት...በአብነት ይጠቀሳሉ ፡፡( ካሳ ጉዱን ሀዲስ አለማየሁ ጉዱ ካሳ ብለው በፍቅር እስከ መቃብር በገፀባህሪነት ተጠቅመውበታል፡፡)
  """""""""""""""""""
  በአፄ ቴዎድሮስ ፣በአፄ ዮሃንስ እና በአፄ ሚኒሊክ ዘመን የነበሩት አለቃ ገብረሀና በተለይ አፄ ሚኒሊክ በተለየ ሁኔታ ይቀርቧቸው ነበር፡፡
  """""""""
  ግን ከአድዋ ጦርነት በኃላ፣አፄ ሚኒሊክ ለደጃዝማች ባልቻ ልዮ ጎራዴ ሽልማት ሲያበረክቱ አለቃ ሽልማቱን ክፍኛ አፊዙ፡፡"ወይ ጎራዴ፣ ጎራዴስ ከቤቷ ገባች"አሉ፡፡ባልቻ በጦርነት ተማርኮ የወንድነት ብልት ስላልነበረው በአሽሙር ለመንካት አስበው፡፡እትጌ ጣይቱን ሳይቀር ያሽሟጥጣሉ፡፡የአድዋ የጦሩ ገበሬ ደጃዝማች ባልቻ ብልታቸውን በማጣታቸው ልጅ አልወለዱም፡፡ሚስታቸውንም ራሳቸው ድረዋል፡፡ከዚህ ብሶ የአለቃ ገብረሀና አሽሙር የእግር እሳት ሁኖባቸው ለመግደል ሙከራ አድርገዋል፡፡ የማታ ማታ ግን በእምየ ሚኒሊክ ሸምጋይነት፣ ሁኔታው ተረጋግቶ፣የእንጦጦ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ ሁነው እየመሩ አቋቋም፣ዜማ፣ቅኔ ና ፍልስፍናን አስተምረዋል- አለቃ ገብረሀና፡፡
  """"""
  የሰዓሊ ና የደራሲ መንግስቱ ለማ አባት አለቃ ለማ ሀይሉ አባ ገብረሀናን""የሙያዎች ሁሉ ራስ፣ የጥበብ ዳርቻ፣የፈጠራ ባለቤት ልዮ ፍጡር!"ሲሉ ይገልፇቸዋል፡፡ ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደስላሴም"""የቅኔ እና የታሪክ፣የሰሞ ና የወርቅ አንጥረኛ፣የፖለቲካ ሀያሲ......."ሲሉ ያሞካሿቸዋል፡፡
  ............
  አለቃ ገብረሀና በኢትዮጵያ ውስጥ ከአፄ ሚኒሊክ ቀጥለው ፎቶ የተነሱ ቴክኖሎጂ ወዳድ ሰውም ነበሩ፡፡ እምየ ሚኒሊክ ቴክኖሎጂን በሀገራቸው ሲያላምዱ የአለቃ አሻራ ጉልህ ነበር፡፡
  የፍግ ተውኔት(commedy) መምህርም ናቸው፡፡የአለቃ ቀልድ ዘመን የማያዝገው፣ቁምነገርን ያቀፈ፣በሰሞና ወርቅ የቆነጀ ወዛም ወግ ነው፡፡
  """""
  አለቃ ገብርሀና፣ወደ መጨረሻ ዘመናቸው ቀልዳቸውን ትተው ወደ ነፍሳቸው ዙረው ነበር፡፡በየገዳማቱ በፆም በፆሎት ቀሪ ዘመናቸውን አሳልፈው፣በተወለዱ በ 84 ዓመታቸው ከዛሬ 111 ዓመት በፊት በ1898 ዓም አርፈዋል፡፡
  """"""''''
  የአለቃ ገብረሀና ስም መንግስታትን በአሽሙር ለመተቸት ዛሬም ድረስ ማምለጫ ሁኗል፡፡ ብዙ ቀልዶችም በአለቃ ገብረሀና ስም እሱ ሳይቀልዳቸው አለ አባ ገብረሀና ተብሎ ይቀለዳሉ፡፡
  --የቅርብ ዘመዶቻቸው ደቡብ ጎንደር ዛሬም ፎገራ- ወረታ አካባቢ ይኖራሉ፡፡

  ReplyDelete