ታሪክ ራሱን ይደግማል ይባላል፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፉ ምሳሌዎች በአንድ ወቅት ብቻ ተፈጽመው የቀሩ ታሪኮች አይደሉም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ በየዘመናቱ የሚከሰቱ የቤተ ክርስቲያን ጉዞ አካላት ናቸው፡፡ እነዚህ ለክፉም ሆነ ለበጎ ምሳሌ ሆነው የተጻፉ ታሪኮች፣ ቤተ ክርስቲያንን የመከራ እና የደስታ ዘመናት ተከትለው ይፈጸማሉ፡፡ የዮሐንስ ራእይን ለመተርጎም ከተጻፉ ከግሪክ እና ሶርያ የጥንታውያን መዛግብት ያገኘሁትን ይህንን ትርጓሜ እስኪ ተመልከቱት፡፡
ነገር ግን አንተን የምነቅፍበት ነገር አለኝ፡፡ ሳትሆን ራስዋን ነቢይት ነኝ የምትለውን አገልጋዮቼንም ለጣዖት የተሠዋውን እንዲበሉ እና እንዲሴስኑ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ዝም ብለሃታልና (ራእይ 2÷20)
ኤልዛቤል ማናት?
በብሉይ ኪዳን
በብሉይ ኪዳን የአክአብ ሚስት፣ የሲዶናዊው የኤትበኣል ልጅ ናት (1ኛነገሥ.16-31)፡፡ ባልዋን አክአብን የበኣልን ጣዖት እንዲያመልክና ክፉ ሥራ እነዲሠራ ትገፋፋው የነበረች እርሷ ነች፡፡ በእሥራኤል አምልኮ ባዕድ እንዲስፋፋ ያደረግችና ኤልያስን ያሳደደችው ኤልዛቤል ነበረች፡፡ በቤተ መንግሥቷ አራት መቶ የበኣል፣ አራት መቶ ሃምሳ የአሸራህ ነቢያትን ትመግባቸው ነበር (1ኛ ነገሥ.18-19)፡፡
ባልዋ አክአብ የየዋሑን ሰው የናቡቴን የወይን እርሻ ለመውሰድ አስቦ ናቡቴ ርስቴን አልሸጥም ባለው ጊዜ ተናደደ፡፡ አልዛቤልም ይህንን አይታ ናቡቴን በግፍ አስገደለችው፡፡ እርሻውንም ቀማችው (1ኛ ነገሥ.21÷1-19)፡፡
በሐዲስ ኪዳን
በዮሐንስ ራእይ አልዛቤልን የተጠቀሰችውን የትያጥሮኗን ኤልዛቤል በተመለከተ ለቃውንት ልዩ ልዩ ሐተታ አቅርበዋል፡፡
የመጀመርያው ሐተታ ኤልዛቤል የተባለችው የጳጳሱ ሚስት ናት የሚለው የሶርያን እና የግሪክ ጥንታዊ መዛግብት መሠረት ያደረገው ትርጉም ነው፡፡ በእነዚህ መዛግበት «ሚስትህን ኤልዛቤልን» ይላል፡፡ ይህች የጳጳሱ ሚስት የጥንቷን ኤልዛቤል መንገድ ተከትላ አምልኮ ጣዖትን እና ዝሙትን እያስፋፋች ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነግሣ ትኖር ነበር፡፡ በነገራችን ላይ እስከ ሦስተኛው መክዘ መጨረሻ ድረስ ጳጳሳት ሚስት ያገቡ ነበር፡፡
ይህች የጳጳሱ ሚስት ቤተ ክርስቲያኒቱን ተረከበቻት፡፡ ማንኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳይ በእርሷ በኩል ብቻ ነበር የሚያልፈው፡፡ ደግሞም ምግባረ ብልሹ እና ሕይወቷ በዝሙት የተነከረ በመሆኑ ምእመናኑን ለሥነ ምግባር ብልሹነት አጋለጠቻቸው፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሚመጡ አሕዛብም የርሷን ምግባር በማየት «ክርስትናማ እንዲህ ከሆነ» ማለት ጀመሩ፡፡
ሊቀ ጳጳሱ ይህንን ሁሉ ክፉ ሥራ እያዩ በቸልታ ያልፏት ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቱ መደፈር እና የምእመናኑ ሕይወት አላሳሰባቸውም፡፡ በዚህም ምክንያት «ዝም ብለሃታልና» ተብለው ተገሠጹ፡፡
ቅዱስ ኤጲፋንዮስን የመሳሰሉ ሌሎች መተርጉማን ደግሞ በትያጥሮን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ትኖር የነበረች፣ ክርስቲያን መስላ ጳጳሱን ያታለለችና ብዙ ክርስቲያኖች ከዝሙት ጋር የተቀላቀለውን አምልኮ ባዕድ ችግር የለውም ብለው እንዲቀበሉት ያደረገች ኃይለኛ ሴት ናት ይላሉ፡፡
እንደ ኤጲፋንዮስ ሐተታ ይህች ሴት ሀብታም እና ኃይለኛ፣ በዘመኗም በዘርዋ የምትመካ የልዑላን ቤተሰብ ነበረች፡፡ ክርስቲያን ነኝ ብላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ብትጠጋም አምልኮ ባዕዷን እና ዝሙቷን አላቆመችም ነበር፡፡ በዚህ ጠባይዋም ለጳጳሱም ሆነ ለብዙ ምእመናን መሰናከያ ሆነች፡፡
የኤልዛቤል ፍጻሜ
እግዚአብሔር ታጋሽ ነው፡፡ ለሰው የንስሐ ዕድል ሳይሰጥ አይቀጣም፡፡ አሁንም ለዚያች ክፉ ለኤልዛቤል የንስሐ ዕድል ሰጥቷት ነበር፡፡ ነገር ግን አልተጠቀመችበትም፡፡ በመሆኑም የሚመጣባቸውን ቁጣ ነገራቸው፡፡ አስቀድሞ ቅዱስ ጳውሎስ «የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሐ እንዲመራህ ሳታውቅ የቸርነቱንና የመቻሉን፣ የትዕግሥቱንም ባለጠግነት ትንቃለህን? ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሐ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቁጣ ቀን ቁጣን በራስህ ላይ ታከማቻለህ፡፡ እርሱ ለእያንዳንዱ እንደ የሥራው ያስረክበዋል፤ በበጎ ሥራ በመጽናት ምስጋናንና ክብርን፣ የማይጠፋንም ሕይወት ለሚፈልጉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸዋል፤ ለዐመፃ በሚታዘዙ እንጂ ለእውነት በማይታዘዙትና በአድመኞች ላይ ግን ቁጣና መቅሰፍት ይሆንባቸዋል» በማለት እንዳስተማረ (ሮሜ 2÷4‒8)፡፡
የብሉይ ኪዳኗ ኤልዛቤል ከስሕተቷ ልትመለስ ባለመቻሏ የኢዩ ሠራዊት በክፉ ሞት እንድትሞት፣ ለቀብርም ሬሳዋ እንዳይገኝ አድርጓታል (2ኛ ነገሥ.9÷30‒37)፡፡ ሰባዎቹ የእርሷ እና የአክዓብ ልጆችም በሰይፍ ተገድለዋል (2ኛ ነገሥ.10÷1‒11)፡፡ በዚሁ አንፃርም የሐዲሷ ኤልዛቤልም «እርሷም ትቀጣለች ልጆቿም ይቀጣሉ» ተብሏል፡፡
እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን ከኤልዛቤል ያድናት፡፡
i think i know Elzabel of today Man benegerat fitsamewan
ReplyDeleteHi Dani!
ReplyDeleteThank you for your constructive,and instructive contribution.I'm obtaining great deals of information on this blog.Keep it up!!
It is not a comment but I listened your article on Gibot 7 radio program today without mentioning your name.The reader said as if he has got it somewhere.i think they need to acknowledge you.I consider it as plagarism in case they fail to admit that. I read it last year on Addis Neger;I'm sure that artcile is yours.It was on Ethiopians who are migrating 'MEFERSH,MEDEBL,MEMERSH";
WISH YOU ALL THE BEST
dani, so sweet, but too short. 'Letebib tinish yibekawal' endatilegn-tebib aydelehum. I read the story so much interested-but finally i felt there is some kind of missing link.
ReplyDeleteI usually feel as i have attended a short sermon after reading these articles, but when it finihes as short as this my satisfacation will not be complete
d dani egzibher yistilin yebalefewin endatizenega meredadat yeminchilibetin meftihe benore melkam new egzibher antenim betesebihinim yibark amen
ReplyDeleteAmen Dn, the truth of the matter is may God help us also not to turn out to be enemies of our church!
ReplyDeleteAmen Bete krstiyanachinn Amlak Yitebqlin! Lantem kale hiwotn yasemaln, mengste semayatn yawrsln.
ReplyDelete+ + +
ReplyDeleteAmen!!! ye-Egziabeher kal hulem addis new, hulem yalenibetin tikikilegna maninet ende-mestawet yasayenal. Bezer be-poletica ena beteleyayu sigawi tikimoch yetetebetebin elizabel-woch bete-kiristianin beteleyaye akitacha eyeweganat yeminigegnibet zemen lay nen, meche endeminineka meche endemigeban ayitawekim, minalbatim cherisen eskeminitefa ena sigachinin wushoch eskilisut eyetbekin yihonal.
Amlake kidusan ke-elzabelinet tebiko ke-elzabelawiyan gar endanitebaber hail ena birtatun yadilen!
Thanks Dany, I don't know before there is Other lady except the wife of Akab. These days I've noticed many nonprist people who's trying to led the church. Yes you'r right may the Almighty safeguard the church from such evil people.
ReplyDeleteAmen Kalehiwot yasemaln
ReplyDeleteበስመስላሴ!
ReplyDeleteውድ ዲ/ን ዳኒ እንዴት ነክ? እግዚአብሔር አገልግሎትህን ይባርክ፡፡ እውነት ነው እግዚአብሔር ከአሁን ዘመን ኤልዛቤሎች (አንድ ብቻ ኤልዛቤል ስላልሆነች) ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን፡፡ የግላጭ ጠላትን ይቋቋሙታል፤ የስውር (የውስጥ) ጠላትን እግዚአብሔር በቶሎ ካላጋለጠ እንዴት ያውቁታል? ብቻ ቅዱሳን ስጋቸውን ገድለው ያቆዩዋትን ቤተክርስቲያን ከኤልዛቤሎች ይታደግልን፡፡ አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ገነት ቀጸላ (ወንጂ)
በስመስላሴ!
ReplyDeleteውድ ዲ/ን ዳኒ እንዴት ነክ? እግዚአብሔር አገልግሎትህን ይባርክ፡፡ እውነት ነው እግዚአብሔር ከአሁን ዘመን ኤልዛቤሎች (አንድ ብቻ ኤልዛቤል ስላልሆነች) ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን፡፡ የግላጭ ጠላትን ይቋቋሙታል፤ የስውር (የውስጥ) ጠላትን እግዚአብሔር በቶሎ ካላጋለጠ እንዴት ያውቁታል? ብቻ ቅዱሳን ስጋቸውን ገድለው ያቆዩዋትን ቤተክርስቲያን ከኤልዛቤሎች ይታደግልን፡፡ አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
O Daniel it is a great history of the truth church challenges of in the history of churches.
ReplyDeleteNow a days there is the same as IZABEL" the churches difficult challenges inside and outside.
Most of the time inside challenges coming according to
the lack of money and the wealth womans coming to the father of churches and it says we help by money any thingAfter that the is different types of challenges coming
according to the love of MONEY.
for the church and the fathers.
please DANIEL CONTINUE to CLICK the BELL.
ZAREAYAKOB YIHUN
አሜን
ReplyDeleteእግዚአብሔር ይስጥልን
"እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን ከኤልዛቤል ያድናት"፡፡Amen
ReplyDeleteAmen!
ReplyDeleteThank you Dn. Danny
ReplyDeleteThis is an impressing story...There are alot of stories that never been told sofar it is my first time to read that Pops were married in the old days...
GOD MAY BLESS YOU.
ዳኒ ተስገብግቤ ነበር ረጅም ስብከት መስሎኝ ምነው እንዲህ አሳጠርካት የሀጢያት ትንሽ የለውም ብለህ ይሆንን፡፡ ለሁሉም በርታ ድንግል አትለይህ፡፡
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን!
ReplyDeleteብዙ ጊዜ በዚህ ዘመን ያለን በክርስትና ስም የተጠራን ነገር ግን ኤልዛቤሎች የሆንን ይመስለኛል፡፡
በቤተክርስቲያን አገልግሎት አምባገነኖች፣ በትዳራችን አባገነኖች፣ በጓደኞቻችን ላይ አባገነኖች፣ በመሥሪያ ቤት አባገነኖች መች ይሆን ከዚህ የምንፀዳው
ንስሐ ተሰጥቶናል ባለን ጊዜ እንጠቀምበት
እግዚአብሔር በቸርነቱ ያስተካክለን
የእናታችን ድንግል ማሪያም ትህትና ይደርብን አሜን!
በዘመናት ሂደት ውስጥ ቤተ ክርስትያን ኤልዛቤሎች አጋጥመዋታል ያጋጥሞታልም ትልቁ ነገር እግዚአብሔር አምላክ እንደ እባታችን ቅዱስ ዮሐንስ አፍወርቅ ያለ አድር ባይ ያልሆነ መካሪና ገሳፂ አያሳጣት:: ሁላችንም በታሪክ እንደምናውቀው እባታችን ቅዱስ ዮሐንስ አፍወርቅ በ 398 ዓ.ም የቁስጥንጥንያ ፓትርያሪክ ሆኖ በተሾመበት ወቅት በግዜው የነበረችውንና የደሀይቱን መበለት ሀብት በገፍ የነጠቀችውን በብተ ክርስትያን ላይ ልዩ ልዩ ግፍ ስትፈፅም የነበረችውን ንግስት ኤውዶቆስያንን ከንግስት ኤልዛቤል ህገወጥ ተግባር ጋር በማነፃፀር በይፋ ገስፆት ነበረ እግዚብሄር አምላክ እንደአባታችን ቅዱስ ዮሐንስ አፍወርቅ የለ መካሪ ለቤተ ክርስትያናችን ያድላት::
ReplyDeleteአሜን
Thanks Dn. Daniel!
ReplyDeleteThere are many women today they pretend to be spritual, they approach our Holy fathers as true children and then they twist the arm of our fathers. I know many Deacons and priests have to get approval from those women to get promotion. I know many things ... May God safeguard our church.
በእራስ ላይ ሀጢያት መስራት በእርግጥ በደል ነው ንስሀ ከገባን ግን ይቅር ባይ ነውና ይቅር ይለናል በአገልግሎት መልክ ግን በተለይ የግል ጥቅምን አስቀድሞ ለመንጋው ያለማሰብ ወንጀል ነው ይህ ሁሉ የሚመጣው የእግዚአብሄርን ምህረት በማቃለል ነውና ለሁላችንም ልቦና ይስጠን እላለሁ ቤተክርስቲያንንም እግዚአብሄር ከኤልዛቤል ይከላከልልን ኤልዛቤል የጠፋችው ብቻዋን ሳይሆን ሌሎቹንም ይዛ ጠፍታለችና ወገኖቻችንም እንዳይጠፉብን እግዚአብሄር የሚያስብ ልቡና ይስጠን
ReplyDeletewho is elzabel in our church? do you remember the problem between our fathers(members of holy synod)? I think elzabel was/is between them....
ReplyDeleteLet us pray for our church!!
ዳኒ በመጀመሬያ እግዚአብሔር ፀጋዉን አብዝቶልህ ሌሎች ቁም ነገሮችንም እድታስተምረን እፀልይልሃለሁ፡፡ ዳኒ የምታቀርባቸዉ ፅሑፎች በሙሉ በጣም አዝናኝ እና አስተማሪዎች ስለሆኑ በዚሁ ቀጥልልን፡፡
ReplyDeleteIts true Dani, I heard this issue a year ago and God protect us
ReplyDelete" የጳጳሱ ቅርብ, በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነግሣ የምትኖር"
KaleHiwot Yasemalen Dn. Daniel
ReplyDelete+++
ReplyDeleteአሜን።
ቃለ-ህይወት ያሰማልን።
ወንድምህ ከብሪታኒያ
Short and straight to the point!!!
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን!
እግዚአብሔር ፀጋህን ይጠብቅልህ
Ameha Giyorgis
DC/VA
ዲ ዳንኤል
ReplyDeleteለተከበረው ጤንነትህ እንደምን ከርመሃል ?
""የጳጳሱ ሚስት...." ያልኸው ነገር : ቀልቤን ሳበው::
መጽሐፍ ቅዱሱ ላይም (ቦታውን በትክክል ባላስታውሰውም) ""ኤጲስ ቆጶስ, ቄስ, ዲያቆን አንዲት ሚስት ትኑራቸው"" ይላል :
ታዲያ ለምንድነው ? ከሦስተኛው መክዘ መጨረሻ በኋላ ጳጳሳት ሚስት እንዳያገቡ የተከለከሉት ?
ምክንያቱስ ምን ነበር ?
እስኪ ባክህ በዚህ ጉዳይ : ሰፋ አድርገህ አቋድሰን ::
ይህ ነገር መፈታት ከቻለ እኮ
ሳያስቡት የገቡበት ብዙ መነኩሴዎችም..... ሚስት ይኖራቸውና በክህነታቸው ይቀጥላሉ
ባለትዳሮች የሆኑ ቄሳውስትም : ከነትዳራቸው ወደ ሲኖዶስ አባልነት ሊሸጋገሩ ይችላሉ
ማለት ነው ::
እረ እባክህ
ከምታውቀው : አንድ ነገር በለን
Amen!!!!
ReplyDeleteአሜን እግዚአብኤር አምላካችን ቅ/ቤ/ክርስትያንን ይጠብቅልን
ReplyDeleteየተማርከት፡
1.ሁላችንም በተሰጠን እድሜ ተጠቅመን ንስሐ ገብተን ክቡር ስጋውን ቅዱስ ደሙን ተቀብለን መቆየት እንደሚገባን፣
2.የቤተ ክርስትያንን ችግር ለመፍታት ህለት ህልት በጸሎት እንዲሁም በተሰጠን ፀጋ የአቅማችንን መሞከር እንዳለብን
በመጨረሻም እርሱ ለእያንዳንዱ እንደ የሥራው ያስረክበዋል ስለዚ እከሌ ነው እከሌ አይደለም እያልን ለምንድነው አጥያት የምንሰራው? መናገር ያለበት ይናገራል እኛ ደግሞ በፀሎት፡፡
አንበርታ
It is surprise for me when i read the article.I have heard the controversy last year.But i have passed it as if it is a common rummoour.But now i have to challenge with ugly truth.Mastewalin Leabatochachin Yistilin.
ReplyDeleteኤልዛቤል ማናት?እኔ እሆንን? ለቤተ-ክርስቲያን የቁልቁሊት እድገት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱ ቢኖሩም እኔስ ምግባረ-ኤልዛቤልን አልተላበስኩም? ለንስሀ የተፋጠነ ልቡና ይስጠን። ዲ.ን ዳኒ ቃለ-ህይወት ያሰማልን።
ReplyDeleteፈጣሪ መምህራንን ያብዛ። ዛርም ሁላችንን ከዚህ አይነት ሕይወት ያድነን።
ReplyDeleteዳ/ን ዳንኤል መቸም የተባረክ ልጅ ነህ እግዚአብሔር የመረጠህ እኔ የምመኝልህ በዚች በፀዳች ሃይማኖትህ እግዚአብሔር እስከጠራህ ድረስ እንድትኖር ነው እኔ በቀን አንድ ጊዜ የአንደትን ድረ-ገፅ ሳላየው አልውልም ጌታ አንደበትህን እንደባረከው የምድራዊ ህይወትህም የተባረከ እንዲሆን እመኝልሃለሁና በተጨማሪም እንደዚሁ የተገኘውን የመንፈስ ምግብ እያቃመስከን ህይወታችን እንድትቀጥል አድርግ አደራ
ReplyDeleteአስካለ ማርያም ከአዲስ አበባ
God gives u more wisdem
ReplyDeleteAmen!
ReplyDeleteለሁሉም በርታ ድንግል አትለይህ
Thank GOD we now have ONE person who speaks TRURTH.Tell us, tell them, tell all the truth. Our GOD is GOD of truth,justice,peace and love.
ReplyDeleteMay our benvolent LORD bless you,your family and your work.
Thanks Dn Daniel
ReplyDeleteWe saw the present Elizabeth /Ejegayehu the great/ in this insight
please Dani approve the previous comment.
ReplyDeleteይሄ ይከፋል
ReplyDeleteኤልዛቤል የሚለው ጽሑፍ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ጣኦት አምላኪዎች ጨካኞች ነፍሰ ገዳዮች ዋና መገለጫቸው ነው ፣ አሁን ያሉት ኤልዛቤሎች ግን እውነተኛ መገለጫቸው ጠንቋዮች መናፍቃን ጥቅመኞች /ገንዘብ እየተቀበሉ ወይም የተለየ ጥቅም እየጠየቁ ወደ ቤተክርስቲያን ባለስልጣናት መናፍቃንን ሳይቀር የሚያቀርቡ/ የሚያስገቡ የሚያሾሙ የሚያሽሩ /መሆናቸውን በግልጽ እያየን ነው ፡፡
ዛሬ የታዘብኩትን ልንገራችሁ
• ትላንት አባቶችን በግልጽ የቤተክርስቲያን ሀብት የሆነውን ለግላችው ለክብራቸው እያዋሉ ቤ/ክንን አሰደቡ ስጋውን ሆኑ ለበአለ ሲመታቸው ይህን ያህል ገነዘብ ባከነ እግዚአብሔር ተረስቶ ምስጋናና ቅነው ለቅዱስነታቸው ተሰተ እያሉ ሲነቅፉ የነበሩት እነ አቶ በጋሻው ዛሬ የፓትሪያርኩን በአለ ሲመት ለማክበር ጉባኤ ዘርግተው የክብር እስፖነሰር ሆነው ብቅ አሉ - እነዚህ መናፍን እና ጥቅም ፈላጊ የዘመኑ ኤልዘቤሎች ውስጥ የሚመደቡ ናቸው
• ትላንት በአቃቂ መድኃኔዓለም ቤ/ክ እየሰራ በነበረው በአጥማቂነት ስም ጥንቆላ ይሰራ የነበረውን ጌታቸው ዶኒን በግልጽ ሲቃወም ሲከስ የነበረው ቀሲስ ሰሎሞን ሙሉጌታ ምን ትቅም ያገናኛቸው ይመስላችኋል የፓትሪያርኩ በአለ ሲመትን ምክንያት በማድረግ ይዘጋጃል ስለተባለው ጉባኤ/ሐምሌ 3 እና 4/ ሁለቱ በአንድነት በአንድ ኮሚቴ አዘጋጅ ሆነው ብቅ ያሉት - ጠቅመኞች ቤተክርስቲንን አሳልፈው ለጥቅማቸው የሚሰጡ እና ለመንጋው ፍጹም የማይራሩ ኤልዛቤሎች /አሁን እነዚህን ምን እንበላቸው /
• በየሀገረ ስብከቱ ህዝቡን ይመራሉ ተብለው የተቀመጡ ሹማምንት ከግለሰብ ጋር በመመሳጠር ሹመቱን ለግል ጥቅማቸው መጠቀማቸው ሳያንስ የተከበረውን የቤ/ክ አውደ ምሕረት የወንበዴ የቀማኛ መፈንጫ ማድረጋቸው ምእመኑን ግራማጋባታቸው ከምን እንመድባቸው ይሆን;
የተከበራቸው አንባቢያን ከላይ ስማቸውን በግለጽ የገለጽኳቸው አስመሳ አገልጋዮች ቤተ ክህነት ተጠግተው ዓላማቸውን ሰውረው ብዙ ጠፋት እያጠፉ ስለሆነ እናንተ ተጠንቅቃችሁ ለሌላውም እንድትተርፉ ብየ ነው ስማቸውን የገለጽኩት ፡፡
Hi dani I think the known elzabel at this time is the ex-wife of artist mohamed ,wow fantastic idea.
ReplyDeleteSamson the debub!!!!!!!!!+
"በነገራችን ላይ እስከ ሦስተኛው መክዘ መጨረሻ ድረስ ጳጳሳት ሚስት ያገቡ ነበር፡፡"
ReplyDeleteበአረተኛው መክዘ የነበረው ጎርጎርዩስ ዘእንዚናዙ አባት ኤጲስ ቆጶስ ነበር፡፡ የተወሰነው በስድስተኛው መክዝ ነው ይባላል እንዴት ነው ብታብራራልኝ ከተቻለ
አመሰግናለው
አስተውለህ አንብብ ከእንደዚህ አይነት ኤልዛቤሎች ለመጠበቅ ጳጳሳት ያላገቡ ቢሆን ይመረጣል/ የበቃውን እስኪያስቱ ድረስ ይላል ቃሉ
Deleteአስተውለህ አንብብ ከእንደዚህ አይነት ኤልዛቤሎች ለመጠበቅ ጳጳሳት ያላገቡ ቢሆን ይመረጣል/ የበቃውን እስኪያስቱ ድረስ ይላል ቃሉ
Deleteከእንደዚች አይነት ኤልዛቤል ሚስቶች ለመጠበቅ
DeleteBizu edme yaleh aymeselegn. ebakeh "ይሄ ይከፋል" aynetun asteyayet atawutaw...lebeletew setel... bemetesefew sehuf memar enefelegalen. ebakeh...ebakeh...
ReplyDeletereally wenderful saying !
ReplyDeleteThis story remembered me one event that happened in our church before 2 years(Abunu office). One day some elders of the church was very much eager to discuss some very important issue with the Aba Paulos. They waited for one full day to get him. It was only promise from his secretary "you will see him after an hour". Finally, they decided to communicate one lady as a mediater(Elizabel- most of you may know her real name). It was a surprise that within 30 minutes they have succeded to meet him.
ReplyDeleteAll doors are open for her; all evils are going down there with her lead; all promotion and demotion comes through her....-For me she is Elizabel.
KT-USA
አሜን።
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን!
እግዚአብሔር ፀጋህን ይጠብቅልህ
Hailmeskel
Mozambique-maputo
I am both very pleased & hearty sorrowed.
ReplyDeleted/n Daniel may god bless u & safeguard unto the last.I have thing to say i.e telling the truth and informing to every responsible body is not sin.so we all should be frank for the things w/c are valid up to surrender.
amen
ReplyDeleteጳጳስ ሚስት አገባ ማለት የሐዋርያው ጳውሎስ ቃል እስከ ፫፻ ክ/ዘመን ተረስቶ ነበር ማለት ነው............አርድእትም ሚስቶች ነበርዋቸው ማለት እንደሆነስ አስበሀዋል ለመሆኑ ከየትኛው መዝገብ ነው ያመጣሀው ከኦሬንታል አብያተ ቤተክርስትያናት ውጪ ያመጣሀው ከሆነ ነገ ደሞ ክህደታቸውን እንደ ክህደት ሳይሆን ከመካዳቸው በፊት በነበራቸው ታሪክ ብቻ ተነስተህ የኛውና እውነተኛ ቃል እያመሰልክ እንዳታመጣብን እሰጋለሁ በተጨማሪ ካሰብከው እኮየሐዋርያት ደቀ መዛሙርትም በዚሁ ተግባር እየጨመርሃቸው መሆኑን አስበሃል ይህ ደሞ ፈጽሞ ሊታመን የማይችል ነው ምክንያቱም የመጀመርያወቹ ጳጳሳት መላሕይወታቸው ሐዋርያት መስለው ነበር የሚያሳልፉት ነበር እንካን ሚስት አግብቶ ትዳር መምራት ለመንፈሳዊ አገልግሎት እንኳን ባአግባቡ እንዳይፈጽሙ የዓላውያን ነገሥታት ጫና ምን ያህል የጸና እንደ ነበረ እናውቃለን..........ምናልባች ሐዋርያት ልጆች አዋቸውና እነሱም ሚስቶች ነበርዋችው ብለህ ያመጣሀው ነገር ከሆነ ደሞ እርግጥ ሚስቶች ነበርዋቸው ነገር ግን ክርስቲያን ከመሆናቸው በፊት ነው ክርስትያን ከሆኑ በኋላ ግን በጥምቀት እንደ ሕጻናት ሰለአደረጋቸው ወደሚስቶቻቸው ሳይመለሱ ሐዋርያት አድርገፖ ሾሟቸዋል ይህ የሆነበት አንድ ሰው ከጥምቀት በፊት የነበረው ሕይወት ከተጠመቀ በኋላ እንደ ሕጸን ስለሚሆን አይቆጠርለትም ትዳርም ቢሆን አይፈታም ያለው ኦሪት ሳታልፍ በኦሪት ሕግ የተፈጸመ ትዳር ኦሪት ካለፈች በኋላ ደሞ በሕገ ወንጌል የተፈጸመ ትደር ሲሆን ብቻ ነው ከዚህ ውጭ ያልው ሕገ እግዚአብሔር ያልጠበቀ በመሆኑ ቢጸናም ባይጸናም ትዳር ወይ ጋብቻ/ሕጋዊ ማለትነው/ሊባል አይችልም በዚህ መሠረት ሐዋርያት ሆኑ አርድእተ ሌሎእም አንድ አነድ ጳጳሳት የነበሩ አባቶች ልጆች አልዋቸው ሲባል ቅድመ ክርስትና በነበራቸው ሕይወት ወይ ትዳር /በስርዓታቸው የተፈጸመ ትዳር ማለቴ ነው እንጂ ሕጋዊ ትዳር እያልኩ አይደለም/ያፈርዋቸው ለጆች ናቸው ከክርስትና በኋላ ግን በተለይ ከኤጲስ ቆጶስነት ሹመት በላይ የተሾሙ ንስሐ ለዘማዊ ድንግል እንደምታደርግ በተመሳሳይ መልኩ ጥምቀተ ክርስትና ደናግል ኣድርጋአው የተሾሙ ናቸው እንጂ ከተሾሙ በኋላም ሚስት ነበርዋቸው ማት ለሰሚም አይመች እንዶውም በትግርኛ ክበልዕዋያ ዝበሉ ኣባ ጉንባሕ ዛግራ ይብልዋ እንደሚባለው ያስመስለዋል ለአገልግሎት እንዲመች የተተወ ነው ቢባ ደሞ ለምን ካህናትስ በትዳር ምክንያትየሚጎድለወ አገልግሎት እነዲኘፈን እንዲህ አይባሉመ
ReplyDelete