Monday, June 21, 2010

ሦስተኛው ወር


እነሆ የፊታችን ሰኔ 15 ቀን 2002 ዓም ይህንን ጡመራ የጀመርኩበት ሦስተኛ ወር ይሆናል፡፡ በእነዚህ ሦስት ወራት ውስጥ 44 ጽሑፎች ተለቅቀዋል፡፡ በአጠቃላይም በ67 ሀገሮች የሚገኙ አማርኛ አንባቢዎች ተመልክተውታል፡፡ እስካሁን ባለው ሂደት የኢትዮጵያ አንባቢዎች ቅድሚያውን የሚያገኙ ሲሆን የአሜሪካ አንባቢዎች ሁለተኛውን ይይዛሉ፡፡ ካናዳውችም ከጀርመን ቀጥለው አራተኞች ናቸው፡፡

ከአውሮፓ ጀርመን፣ እንግሊዝ፣ ፊንላንድ፣ ጣልያን፣ ኖርዌይ፣ ሆላንድ፣ ቤልጅየም፣ ግሪክ እና ቱርክ በተከታታይ ያለውን ቁጥር ይዘዋል፡፡ ከአፍሪካ በናይጄርያ፣ በኬንያ፣ ሱዳን፣ ኡጋንዳ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቦትስዋና፣ ብሩንዲ፣አንጎላ እና ኤርትራ ብዙ አንባብያንን አበርክተዋል፡፡

ከእስያ አህጉር የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ፣ ሕንድ፣ ታይዋን፣ ማሌዥያ፣ ከፍተኛ አንባብያን የሚገኙባቸው ሲሆኑ ከላቲን አሜሪካ ደግሞ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ እና ኢኩአዶር ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ከኦሺኒያ ሀገሮችም አውስትራልያ እና ኒውዚላንድ ከፍተኛ ቁጥር አስመዝግበዋል፡፡

በተለይ ግን በሳኡዲ ዓረቢያ፣ በባሕሬይን፣ ኩዌት፣ የመን፣ ኳታር፣ ሶርያ፣ ሊቢያ፣ ፓኪስታን እና ኤርትራ ከሚገኙ ወገኖቼ ጋር ለመገናኘት በመቻሌ እንደ ትልቅ ዕድል እቆጥረዋለሁ፡፡ በደቡብ ኮርያ፣ ጃፓን፣ ጀርሲ፣ ሪዩኒየን፣ አይስ ላንድ፣ ያሉ ወገኖችም ከተሳትፎ ጋር ታላቅ አስተዋጽዖ አድርገዋል፡፡

ለዚህ በሦስት ወራት ለተገኘው ውጤት ተጠቃሾች አሉ፡፡ በዚህ መልኩ አገልግሎት መጀመር እንዳለበት ከጉትጎታ ጋራ ብርቱ ጥረት ያደረገችውን ባለቤቴን ጽላት ጌታቸውን፣ ሃሳቡን ወደ ተግባር የለወጠውን ኤፍሬም እሸቴን፤ ተግባሩን በሞያው ያሳለጠውን የአሜሪካውን ወንድሜ ስለሺን እኔም አመስግኛለሁ እናንተም አመስ ግኗቸው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በራሳቸው ጊዜ በኢሜይል፣ በፖስታ፣ በስልክ፣ በልዩ ልዩ መንገዶች በማስተዋወቅ፣ በማበረታታት፣ ኢንተርኔት ለሌላቸው በወረቀት አትመው በመስጠት የሠሩትን ሁሉ ማመስገን ይገባል፡፡ በተለይም የአቡዳቢ ወገኖች ላደረጉት ሁሉ እግዚአብሔር ዋጋቸውን ይክፈላቸው፡፡ በአሜሪካ ኦሐዮ የሚገኘው ወንድሜ ቀሲስ ያሬድ ገብረ መድኅን የመሣርያዎች እገዛ እንዲገኝ በማድረግ ታላቅ ሥራ ሠርተዋል፡፡

በየጽሑፎቹ ሃሳብ ለሰጣችሁ፣ ላነበባችሁ፣ ላበረታታችሁ ሁሉ ዋጋ ከፋይ አምላክ ዋጋ ይክፈላችሁ፡፡ በተለይም አንዳንድ ጉዳዩ ያልገባቸው ሰዎች በእስልምና ላይ የተከፈተ ብሎግ ነው ብለው ባስወሩ ጊዜ በእውነት ስለ እውነት እና ስለ ሀገር ብላችሁ ለተከራከራችሁ ሙስሊም ወንድሞቼ ፈጣሪ የእውነትን ዋጋ ይክፈላችሁ፡፡

አንዳንድ ወንድሞቼ በመሳደብም ሆነ በመራገም፣ ሞራሌ በቀላሉ የሚነካ መስሏቸውም ስም የሚያጠፉ ጽሑፎችን በመላክ የተባበሩኝን ሁሉ እግዚአብሔር ልብ ይስጣቸው እላለሁ፡፡

ይህ ጡመራ የተጀመረው ሀገርን በሚቻለው ለማገልገል በሚፈልግ ቀና ልብ ነው፡፡ ቅር አይበላችሁና በየቀኑ ቢያንስ ሁለት ሰዓታትን እሰጠዋለሁ፤ በየወሩ ደግሞ ቢያንስ 1000 ብር ለኢንተርኔት ክፍያ አወጣበታለሁ፡፡ ነገር ግን ለሀገሬ የምችለውን በማድረጌ እረካለሁ፡፡ ለመጽሐፈ ስንክሳር፣ በያንዳንዱ ቀን ለሚነበበው ቅዱስ፣ ባለ አምስት ሐረግ አርኬ የጻፈለት ሊቁ አርከ ሥሉስ፣ ሲያጠናቅቅ እንዳለው «ሀብታሞች ከተረፋቸው ካቀረቡት ይልቅ የመበለቷን ስጦታ የተቀበልክ ሆይ» እያልኩ እጽናናለሁ፡፡

አሁን አንድ ሃሳብ ልሰንዝር፡፡ እስኪ እናንተ አንባብያን ምን ትላላችሁ? ምን ይጨመር? ምን ይሻሻል? ምን ትመክራላችሁ? እስኪ ሕዝብን የሚጠቅም ቃል እንዳላችሁ ተናገሩ?92 comments:

 1. Egziabher hoy, ehen kena neger yamenechu linochin hulu ebakih bark.

  Dn. Dan, may God bless you abundantly!!! For now I do not have ideas to suggest, I just want to say "Egziabher bebizu lay yihumih!!!" I may write ideas some time latter.

  Tselat, thank you for what you have done and keep helping him more.
  yours sister in Him,

  Cape Town.

  ReplyDelete
 2. i would say keep going...
  and it would be very nice if you leave your bank account or paypal account etc...to help this web site.

  berta berta

  ReplyDelete
 3. ዲ.ን ዳንኤል የመጀመሪያው ሀሳብ ሰጪ ልሆን እችላለሁ የሶስት ወር አጠቃላይ ግምገማው እጅግ በጣም አስደስቶኛል። እንደ እኔ አይነት ሰው ሙሉ ጊዜውን ሰጥቶ ቢሰራው የማይሳካለትን የሀገርን ሰዎች ለመጥቀም የተወሰነ ጊዜ ብቻ ሰጥተህ እንዲህ ፍሬ ማፍራትህ የአምላክህ ታላቅ ስጦታ እንደሆነ ያሳያል።

  ወደ አስተያየቱ ለልግባና እኔ የምለው ይሄ ብሎግ ይህን ሁሉ ሰው የሚጠቅም ከሆነ ለምን በምስጋናህ የጠቀስካቸውን ሰዎች ውድ ባለቤትህን ጨምሮ እራሱን የቻለ የሚያስተባብር ኮሚቴ ተዋቅሮ አገልግሎቱ በሰፋ መንገድ አይቀጥልም?። ለምሳሌ ኢትዮጵያ አንድ የባንክ አካውንት ቢኖርና የቻልነውን ያህል ከበረከቱ ብንሳተፍ?በየሀገራችን እንደምናውቀው ምን ያህል የሰዓት ውድነት ይገባናል። ታዲያ ለምን 'ብር ቢያብር አንበሳ ያስር' የሚለውን አንጠቀምበትም ምክንያቱም መጽሐፍ ለመግዛት ብዙ ብር እናወጣለን ይህንን በነጻ ስናገኘው ከየት መጣ ብለን ልናስብ ይገባናልና።

  ወንድሜ ዲ. ዳንኤል አምላከ እስራኤል በፀጋ ላይ ፀጋ አብዛልህ የበለጠ ጥበቡን አብዝቶልህ እኛም የምንጠቀምበት ያድርገን። የተጀመረው ተስፋፍቶ እኛም አውቀን ለሌላው አርአያ እንድንሆን አምላካችን ይርዳን።

  ReplyDelete
 4. ዉድ ዲ/ን ዳንኤል፤

  "ሶስተኛዉ ወር" በሚል ርዕስ የጻፍከዉን ጽሑፍ እኔና ባለቤቴ ማንበብ ስንጀምር ተሳቀን ነበር፤ የመጨረሻዉን ዓረፍተ-ነገር እስክናነብ ድረስ። ፍቅር ያስያዘንን ይህንን ብሎግ ለማቆም ያሰብክ መስሎን የልብ ትርታችን ጨምሮ ነበር፤ ግን አይደለም...እፎይ!

  ላሁኑ አንተንና ከጎንህ የቆሙትን ሁሉ እግዚአብሔር ይስጥልን ለማለት ፈለግን፤ እንደ አስተያየት ግን ጽሑፎችህን በመጽሐፍ መልክ የምታሳትምበት ሁኔታ ቢኖርና ለትዉልድ ማስተላለፍ ቢቻል መልካም ይመስለናል (ለነገሩ ይህን ስራ የጀመርክ ይመስለናል፤ ቀጥልበት)። አሁን ለተጠየቀዉ ጉዳይ ሀሳብ ከመጣልን እንመለሳለን።

  ወንድምህና እህትህ ከብርታኒያ

  ReplyDelete
 5. ተክለ እስጢፋኖስJune 22, 2010 at 12:08 AM

  ወንድማችን መካሪያችን ዳንኤል፣ በመጀመሪያ ቀና ብዪ መመረቅ ባይሆንብኝ በእወነት ውዳሴ ሳይሆን እግዚአብሔር አምላክ በበረከቱ በረድኤቱ ይከተልህ፣ ስራህን ሁሉ የተቃና የሰመረ ያድርግልህ፣ ካንተ ጋር በእወነት ሊመሰገኑ የሚገባቸው ወንድሞች እና እህቶችም የመጀመሪያውን ቦታ የምትይዘው ባለቤትህ በእውነት ልትመሰገን ይገባታል “ከብዙ ጠንካራ፣ ብልህ ወንዶች፣ በስተጀርባ በጣም ብልህ አነስቶች እንዳሉ” ያንተ ባለቤት ምስክር ነች እና ምስጋናችን ይድረስሽ።
  እኔ መቼም እስካሁን ድረስ ያመለጡኝ የለም ብል ማጋነን አይሆንብኝም ገሚሱን እራሴ እየሰበሰብኳቸው ነው፣ ገሚሱንም ደግሞ ለወዳጆች በጦማር፣ እንዲሁም በማተም እናዳርሳለን ትምህርቱ ለሁላችንም ስለሆነ። ከዚህ በተጨማሪ እንደው ቢኖር ብዪ የምመኘው እስከ አሁን ቀደሙ “ቅዱስ ያሬድ ማነው” “አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ” “አለቃ ገብረሃና ታሪክ ናቸው እውነት?” በመሳሰሉት ዙሪያ መረጃዎች ካሉህ፣ ይኖሩሃል ብዪ አምናለሁ ብዙ ቅዱሳን አባቶች አሉን ትውልዱ ሊያውቃቸው የሚገባ እኛ ከነሱ ምን እንማራለን በስንት ተጋድሎ ይህችን ሃዋሪያዊት ቤ/ክርስቲያን እዚህ ያደረሱልን አባቶቻችን ገድላቸው ምን ይላል? ምንስ አስተዋጽኦ አበረከቱ በሚል ዙሪያ ስለ ተለያዩ አባቶቻችን ታሪክና ገድላቸውን የሚተርክ ክፍል ቢኖር ለምሳሌ “አፄ ዘርአ ያእቆብ” “አቡን ጴጥሮስ” አንዲሁም በዙ አበው ቅዱሳን አባቶች ነፍሳቸውን ይማርና እንደነ አቡነ መልከጼዲቅ ዛሬ በህይወተ ስጋ የተለዩን አባቶች ተጋድሎዎቻቸውን የሚገልጥ ጽሁፍ ቢኖር፣ ብዙ ወገኖቻችንን ያስተምራል ብዪ አምናለው።
  ሌላው በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች የሚገኙ የተለያዩ አድባራትን፣ ገዳማትን አሰራር እንዲሁም ምስረታ ለምሳሌ “ይማኅረነ ክርስቶስ የተሰወረ ስልጣኔያችን” በሚል ያቀረብከው ጽሁፍ በእውነት ከሆነ ብዙ ነገሮችን እንድናገናዝብ እረድቶናል ብዪ አምናለሁ። አሁንም በበለጠ ወገኖቻችን ሊያውቁት የሚገቡ ታሪኮቻችን ተሸፍነው ቀርተዋል፣ ይገለጡ እና በትውልድ ሲዘከሩ እንዲኖሩ ሊረዳ ይችላል ብዪ አምናለሁ።
  በተረፈ በእውነት የቅዱሳን አምላክ ሥራህን ሁሉ ይባርክ፣ በበለጠ ደግሞ አሁንም በስራህ ብዙ ነፍሳትን የምታድንበትን ሃይል ብርታቱን አምላከ ቅዱሳን ያድልህ። ቤተሰብህን ሁሉ እግዚአብሔር ይጠብቅ እላለሁ።
  ከሰሜን አሜሪካ
  ተክለ እስጢፋኖስ

  ReplyDelete
 6. ዲ.ዳንኤል ይህን ጡመራ ከጀመርክ እንዳልከው 3 ወር ሊሞላክ ነው በቀን 2 ሰዕት በወር 100 ብር እያወጣክ ማለት ይህን መስዋት እየከፈልክ ሕዝብን እያስተማርክ እንዳለክ ይታወቃል ለዚህም ፈጣሪ ዋጋህን ይክፈልክ ። እንዲህ ብታደርግ የምልክ ነገር እንኩዋን የለም በዚሁ እንድትበረታ አምላከ ቅዱሳን ካንተ ጋር ይሁን ።

  ReplyDelete
 7. dani bekidmeya hulunim ameseglalhu beteley balebtihin lelaw ante haimanotawe ena hagerawe gidetahin eyetewetah new anas? min enagizih 50 lome le and sew shekim new le50 sew gin getu new en bemin bekul lagizih

  ReplyDelete
 8. Yes,I have something to say if i may reach your views: I knew you have a power to convince your fellows.I knew you are also a great compassionate live-wire,and insightful person.For real; No Joke! So,How about if you focus more on social and marriage issues! As you knew,social and marriage issues, these days, are almost negligible; meaningless! Is that possible to add a "counseling-like" service on your blog?

  However,As a reader, I can say,You contributed a very dedicated and sacred job for those who could not reach you in person! Great man!

  Keep it up!

  Golgule!

  ReplyDelete
 9. ዳኒ በቅድሚያ እግዚአብሄር ያክብርህ ይህ ስለእውነት ከሆነ ለሃገርም ሆነ ለእምነት በጣም ጠቃሚ ነው በመሆኑም በርታ ቀጥል እነላለን የብዙዎቻቸን አስተሳሰብ በእጅጉ ተለውጧል እግዚአብሄር ከነ ቤተሰበህ ይጠብቀህ ዋጋህን በሰማያዊው ማዕረግ ይክፈልህ

  ReplyDelete
 10. +++
  wondime Dani,Seleewnet berta yeewnet amlk enji sew minliredah?

  ReplyDelete
 11. Dearest Dn Daniel Kibret...brother in Christ
  I would like to thank God first for His kind willingness to initiate you for the good work you have been contributing so far. I have once pointed out if you could make footnotes on some of the Amharic words and their meanings.Some words in the articles are bit old and uncommon, some are commonly used but never been recognized about their actual meaning...The language is also one of the treasures that needs our attention.
  We will rise up and strengthen ourselves to accomplish prophecy word..... "....And they shall rebuild the old ruins, they shall raise up the former desolations, and they shall repair the ruined cities, the desolations of many generations" Isaiah 61:4.
  Ethiopiawe wendemeh ke bahir mado!

  Blesses!

  ReplyDelete
 12. Agnatiwos the gaschaJune 22, 2010 at 2:27 AM

  Dn. Daniel, You are doing a great job. I am always eager to read your blog. Keep it up.What I would like to suggest here is that we, readers, should contribute at least $1.00 per month for this constractive idea. This will incourage the bloger to feed us his precious knowledge.

  ReplyDelete
 13. God Bless you and your family. In my opinion it is a fantastic job. I beleive Christ will give more wisdom each day. Keep it up.

  You brother in Christ
  Calgary,Canada

  ReplyDelete
 14. ወንድሜ ዲ/ን ዳንኤል!
  እግዚአብሔር ሥራህን ይባርክልህ! እኔ በበኩሌ ብዙ ትምህርት አግኝቼበታለሁ፡፡ ለወደፊቱም አለፍ አለፍ እያልክ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መሠረተ ኃይማኖት፣ በሀገራችን ስለነበሩ ብዙም ስላልተነገረላቸው ቅዱሳን አባቶች እና እናቶች ገድላት ... ወዘተ አጠር አጠር ባለ መልኩ ብታሳውቀን መልካም ምኞቴ ነው፡፡
  ጌጥህን (ባለቤትህን) እግዜር ይባርካት!
  አምሐ ገብርኤል ከጀርመን

  ReplyDelete
 15. It is a great start and am sure with the grace of God u will continue to provide ur insightful message of unity and love.This uniting voice is really what we need at this time in our history......keep it up brother!and if it is not much to ask including book reviews or critiquing on the blog will be grat asset especailly for the young generation like myself who are trying to be on the right side of history!

  ReplyDelete
 16. Dear Dn Daniel,
  It`s great work. May God give you all the power and strength to continue your work and spread the word of God. Thank you brother.
  Komche from Australia

  ReplyDelete
 17. Dear Dani,

  The knowlege i get with in these three months are more than the knowlege i had fot the last three years or more. Thank you very much , God bless you, your family and everyone who help you to this.

  Keep it up !!!!!!!

  ReplyDelete
 18. 1 = በጣም እወድህአለው የኔ ሃሳብ በማኀበራዊ ጐዳይና በትዳር ዙርያ ብትጥፍ
  2 = ያለነን ጥያቄ ብትመልስልን እንደ ሚስጥሬን ላካፍላቹህ አይነት
  3 = ያገር ቤት ቤተ ክርስትያን ለመርዳት (ፕሮጀክት) የምንረዳበት ነገር ቢፈጠር ማለቴ ሌላ አማራጭ ይኋናል ብየ ነው
  4 = ሌላው ከፖለቲካው ቢቀነስ እኔጃ ፈራሁ

  ReplyDelete
 19. Dear Danid,

  I would just say Keep it up! May God bless you and those who helped you ( mainly your wife)in your service at this blog!
  Just a comment on the content of your blog: I don't know who said it before but for sure it was commented- it would be good to write also on the strong part of Ethiopians, cultural/social life or any other asset to be encouraged;please,also try your best to publish your articles on local magazines and newspapers intensively ( that way you'll address so many readers).

  MAY GOD BE WITH YOU!

  Wendimih HG(Mekelle)

  ReplyDelete
 20. First of all I would like to say thank you God. you gave us our brother Dec.Daniel to teach us what we sould have to know.Please God keep them safe our brother and sister who have done such a great job no body has done ever especialy when they are stil in the third world but that didn`t kept them to do the right things .please Let us help them financialy so they can do more.And finaly I would like to say thank you all who have been involved in this great job keep it up, may God bless you all.
  Never give up!


  G MN,usa

  ReplyDelete
 21. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን!!
  የተከበርክ ወንድሜ ዲያቆን ዳንኤል
  ልቦናን አነሳስቶ የሚያስጀምር ፍጻሜንም የሚያሳምር ኃያል አምላክ እግዚአብሔር ራስህን፣ ቤተሰብህን በቅድሚያ ይጠብቅልህ!
  አንተ የቤተክርስቲያን በተለይም የዚህ ዘመን ወጣቶች የመልካም ሥራ አይከን ነህ፣ ውዳሴ ከንቱ ይሆንብሃል ብዬ አልፈራም ምክንያቱም የቤክርስቲያንን ነገር ጠንቅቀህ የተረዳህ ለብዙዎችም ምሳሌና አርአያ ነህነና፡፡
  በእድሜ ብዙ አትበልጠኝም በሥራና በፍሬ ግን የምንገናኝም አይመስለኝም በእጅጉ ልቀሃል፡፡ ዲያቆን በዓለም መኖርን ከመንፈሳዊነት ጋር አጣምሮ በሁለት ወገን እንደተሳለ ሰይፍ ሆኖ መኖር ካንተ ሌላ ምን ማስረጃ ይኖር ይሆን
  በብዙ ወንድምና እህቶቻችን ብዙ የሚያውቁ፣ ብዙ የተማሩ የተመራመሩ፣ ብዙ ህይወት ልምድ ያላቸው ለሌሎች ማካፈልና ማስተማር ሲችሉ ዕውቀታቸው የጋን መብራት የሚሆን ሞልተዋል፡፡
  በዕውነቱ ብሎግ መክፈት በጣም ቀላል ነው፡፡ ለሃገርና ለወገን አስቦ ጥቂት ሃብትንና ጥቂት ጊዜን ከሠጡ ደግሞ ብዙ መትረፍ ይቻላል፡፡ ስለዚህ እነዚህ ወገኖች ያላቸውን እንዲያወጡ ብትመክር ብታስመክር፣ ብታበረታታ፡፡
  እኔ በስብከቶችህ ለረጅም ጊዜ ባወቅህም፣ በአዲስ ነገር ጋዜጣ የረጅም ጊዜ ተከታታይህ ብሆንም አሁን ደግሞ የብሎግህ ቋሚ ደንበኛ ነኝ፡፡ የሚገርመው የአንተን ትምህርቶች፣ ጽሑፎች ሳነብ ኢትዮጵያዊነት በብዙ ጠልቆ ይሰማኛል፡፡
  ትውልዱ የጎደለው ማንነቱን አለማወቁ ነው፡፡ ስለሆነም ስለራሱ በብዛት ሊነገረው ይገባል፡፡ ስለኢትዮጵያዊነት እሴቶች ያልተነገሩ በብዛት በብዛት መነገር ያለባቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡
  ትኩረትህ በዚህ ላይ ቢሆን የበለጠ ፍሬ ታገኛለህ ብዬ አምናለሁ፡፡
  በተረፈ ያስጀመረህ አምላክ ፍጻሜህን ያሳምርልህ፡፡
  ወስብሃት ለእግዚአብሔር
  ወለወላዲቱ ድንግል
  ወለመስቀሉ ክቡር

  ReplyDelete
 22. Dear Dn Daniel i donot have much to say except thanks for everything so far. u have no idea how u make a change on our life.may God make you even more strong. am longing to read your blog every other minutes.....counting days trust me.
  and we r with u on our prayer.
  let u thank your wife on behalf of us, she is helping us alot than she do for u.God bless u more.

  ReplyDelete
 23. dani berta egziabher kante gar yihun

  ReplyDelete
 24. Zelafto DebretiguhanJune 22, 2010 at 10:44 AM

  Dn. Daniel, Amlak yitebikeh,
  Your views are interesting and educating us. And I would like to thank ur wife and friends for their support. I think u need support from readers in any possible way(financially and technichally). So would u please make things easy for support.

  Kale hiwot yasemalin,

  ReplyDelete
 25. ውድ ዲ/ ዳንኤል፡-
  በአዲስ ነገር ጋዜጣ ላይ ታወጣቸው የነበሩትን ሳቢ ፁሁፎችን የጋዜጣው ህትመት በቆመ ጊዜ ካሳሰበኝ ጉዳዮች መካከል ያንተን ፁሁፍ ጭምር ማጣቴ ነበር፡፡ ሆኖም በዚህ በኩል በመምጣትህ የተወሰኑ አንባቢያን ልናገኝህ ችለናል፡፡ ፁሁፎችን ለማንበብ የሚጋብዙና የማህበረሰባችንን አኗኗር በግልጽ የሚያንጸባርቁ ናቸው፡፡ እይታህም በጣም የሚደንቅ ነው፡፡ በእነዚህ ሶስት ወራት ውስጥ ብቻ እንኳን ምን ያህል ጠቃሚ ሃሳቦች እንዳገኘሁና እይታዬ ምን ያክል እንደሰፋ መመስከር እችላለሁ፡፡ እንዲሁም እኔ ያገኘሁትን ጥቅም ቤተሰቦቼና ጓደኞቼ እንዲያገኙት የተቻለኝን እያደረኩ ነው፡፡
  በሌላ በኩል አንዳንድ አንባቢያን የሚሰጡትን አመክንዮአዊ ያልሆነ አስተያየቶች አልፎ አልፎ እኔም ተመልክቼአቸዋለሁ፡፡ በእርግጥ በተወሰነ መልኩ እነዚህ አስተያየቶች መኖራቸውን አትጥላው፡፡ ምክንያቱም የበለጠ ጠንክረህ እንድትሰራ የሚያደርጉህ በመሆናቸው ነው፡፡ አንተም በፁሁፍህ እንደጠቀስከው ሞራልህ በቀላሉ የሚነካ አለመሆኑን በያዝከው መንገድ በርትተህ በመጓዝ ማረጋገጥ ይኖርብሃል፡፡
  እስካሁን ካስተዋልካቸው ጉድለቶች መካከል አንዱና መሻሻል አለበት የምለው አንዳንዴ የምታወጣቸውን ፁሁፎች ቀድመህ ታስተዋውቅና ባላከው ቀን የማይወጣበት ጊዜ አለ፡፡ አስተዋውቀኸንም ጭራሹኑም ያላወጣኻቸውም አሉ (ለምሳሌ ዲጂታል ሌቦች)፡፡ ለምን መሰለህ ባልከው ቀን ፁሆፎችን ለማንበብ እንጠብቅና ሳይወጡ ስለሚቀሩ ጉጉታችንን ስለሚቀንሱት ነው፡፡ ምን አልባት እነዚህ ጥቃቅን ስህተቶች በመሆናቸው በቀላሉ ልታስተካክላቸው የምትችል ይመስለኛል፡፡
  ሌላው አንባቢው ምን አልባት በገንዘብ ያግዝህ ዘንድ አንድ ወንድም እንዳለው የባንክ አካውንቱን ነገር ልታስብበት ትችላለህ፡፡
  በተረፈ ለስራህ መቃናት የረዱህን ሰዎች አመስግኑልኝ ባልከው መሰረት ላቅ ያለውን ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡ ለአንተም የበለጠ ምስጋና ይገባሃል፡፡ እግዚአብሄር ይርዳህ፡፡

  ReplyDelete
 26. ጆሮ ያለው ይስማ! ቃለ ህይወት ያሰማልን ዳኒጆሮ ያለው ይስማ! ቃለ ህይወት ያሰማልን ዳኒ

  ReplyDelete
 27. ዲ.ዳንኤል በእኛ በኩል በጣም የደከምንበት ነገር ቢኖር ይህ online ነው በር ከፋች በመሆንህ እግዚአብሔር ይስጥህ። ለምንድነው ቤ/ክኖች በዚህ መንገድ የማይጠቀሙት። ፌስ ቡክ የመሳሰሉትን፡፡ መልሱን እንድትሰጠኝ እባክህ፡፡ ከሁዋላ ከመከተል መቅደም ሳይሻል አይቀርምና። በተረፈ እመ አምላክ ታበርታህ።

  ReplyDelete
 28. ውድ ወንድማችን ዳኔ እግዚአብሔር አምላክ ውለታችሁን ይክፈላችሁ ውለታ ከፋይ ክርስቶስ ስለሆነ፡፡ እኛ ለማመስገን ቃላት ያጥረናል፡፡ ያለህን ጊዜ፣ገንዘብ፣እውቀት ወ.ዘ.ተ በመጠቀም የዜግነትህን እየተወጣህ ስለሆነ አንተን የሠጠን እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ እኛ በአንድ መሥሪያቤት የምንሠራ ሠራተኞች የኪዳነምህረት ማህበር አለን፡፡ ባንተ ሀሣብ ተነሳሽነት ‘ፊደል እያለው የማያነብ ማነው?’ መልሱ ኢትዮÉያዊ እንዳይሆን በየወሩ አንድ መፅሐፍ ገዝተን ለማንበብ ስለተስማማን አሁን ሁለተኛ መፀሀፋችንን ገዝተናል፡፡ ብዙ መፅሐፍ ብትጽፍ በጣም ደስ ይለናል ያንተ መፃፎች ሁሉም አስተማሪዎች ናቸው፡፡ ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና የሚለው መፅሐፍ በአንቀፀ ብፁሃን ብሥራተ ገብርኤል ሰንበት ት/ቤት በኪነ-ጥበብ ፕሮግራም በዋሽንት ተቀነባብሮ በትረካ መልክ ቀርቧል፡፡ በእውነቱ የብዙዎቻችንን ስሜት የገዛ ነው፡፡ እግዚአብሔር በአንድም በሌላም ይናገራልና ወንጌልን፣ ሥርዓትን፣የመሳሰሉትን ነገሮች ለማስፋፋት የአቅማችንን እናድርግ የዜግነታችንን እንወጣ፡፡ በመጨረሻ በወጣቶች ህይወት፣ በጋብቻ፣ በአለባበስ በመሳሰሉት ነገሮች ብትፀፍ ደስ ይለናል ብዙ ወጣቶች ማንነታችንን ትተን በምዕራብዊያን ተፅኖ ስለተዋጥን ዜጐችህን ብታድነን እንዲሆም ምሳሌ የሚሆኑ የቅዱሳንን ታሪክ ለምሳሌ የነ ቅድስት አርሴማን፣የነ ቅድስት መሪናን እነ ብዙ ቅዱሳን የህይወት መስታወት የሚሆኑ ስላሉን ስለነሱም ማወቅ ያለብንን ብታሳውቀን ጥሩ ነው ብዮ አስባለሁ፡፡ የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ለሁላችሁም ፀጋውን ያብዛላችሁ የአገልግሎት ዘመናችሁን ይባርክ የእመቤታችን፣የመላዕክት፣የቅዱሳን፣የፃድቃን አማላጅነታቸውና ጥበቃቸው አይለይን፡፡ አሜን!!!

  ReplyDelete
 29. +++
  Well done.
  May God be with you all the time, Amen.
  GKidan, Austria

  ReplyDelete
 30. አልያሰ ከ/ማርያም
  እኔ በስራ ምክኒያት በጅቡቲ ነው የምኖረው ። የአነተን ጽሁፍ የተወሰንን ባልጀራሞች እናነበዋለን ።አስፈላጊም ሲሆን በጽሁፉ ላይ ውይይት እናደርጋለን።የምታነሳቸው የመወያ ያ ሀሳቦች አንዳነዶቹን የምናውቃቸው ቢሆንም የአንተ አቀራረብ ግን ያማረና ፍሰት ስላለው ደጋግሜ ማንበብን ባህሌ አድርጌዋለሁ። እንደኔ ሀሳብ ቢሆን ፡ ይህ ብሎግ እንዲቀ ጥል ከተፈለገ ከምንም በላይ የመንቀሳቀሻ በጀት ያሰፈልገዋል። የወግ ጽሁፍ በተለያዩ አባላት የሚቀርቡበት ሁኔታ ቢኖር የተሻላ ይሆናል።ይህ ድህረ ገጽ ተባብሮ ማስተማርን የምናይበት መድረክ እንዲሆን እመኛለሁ። ያሰብነውን እንድንፈጽም እግዚአብሄር ይርዳን።

  ReplyDelete
 31. Dear Daniel,

  I am sure you have still unreserved views for our country. You need financial resources to make them practical.

  My suggestion for this constraint is to compile all what you have done as a book and let's buy it. Then, you can get the power to exercise for ward to thirst us.

  God bless you.

  Sisay.

  ReplyDelete
 32. Dear Daniel,

  Compile these works and let's buy them and contribute financial power so that we can harvest more of your views in the future.

  We have to support your country wide gift.

  God bless you to stay safe and long, Amen.

  Sisay

  ReplyDelete
 33. ዘውዱ ክራርJune 22, 2010 at 3:25 PM

  የኔ አስተያየት

  ስለሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን አንተንም ያነሳሳ ያበረታታ ፣ ላንተም እድሜ ይስጥልን፡፡ በምሰራበት ቢሮ የሙሉቀን ኮኔክሽን ስላለኝ ሁሉንም በሚገባ ልከታተል ችያለሁ የእርሱ ስጦተ ነው እግዚአብሔር ይመስገን ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የዚህ እድልም ሆነ አቅም ለሌላቸው ከቻልኩ አባዝቼ ካልቻልኩ እንዲያባዙ በመስጠት ከዚህ ውጪ ጠቅማቸዋል ይቀበሉታል ላልኳቸው በአካል ሄዶ በማንበብ ብዙ ሰው ያንተ ዳታ የማያቃቸው ተከታታዮች አብዝቻለሁ ፡፡ አሁን ደግሞ ሁሉንም ባነድ በማስጠረዝ በተለይ ወጣቶች በሚበዙበት እንደ ጸጉር ቤት መስሪያ ቤቶች እየተዋሱ ለማንበብ አዘጋችቼዋለሁ ፡፡ ይህንን ሁሉ የማደርጋው እኔ በጣም ስለተጠቀምኩበት በመሆኑ ነው ፡፡ ወደፊት ብዙ እንደምንማማር ተስፋ አለኝ አንተን ያበርታህ እንጂ ለስርጭቱ የበኩሌን ለመወጣት ያለኝን ታዛዥነት እየገለጽኩ፡፡

  ለወደፊቱ ስራህ ይታከል የምለው
  1. የኢትዮጵያን ጥንታዊ ታረክ በተመለከተ ብዙ የተሸፈኑ ያልተገለጡ አልያም መጽሐፎቹ በመጥፋታቸው ምክንያት የማናቃቸው ብዙ ነገሮች ስላሉ የታሪክ ዳሰሳው ቢያካትታቸው ፣
  2. ቀደም ባሉት ጊዜያት የኢትዮጵያ ለቃውንት በየጊዜው ለተነሱ መናፍቃን የሰጡአቸው መልሶች ልዩ ልዩ ጽሑፎቻቸው ለዚህ ትውልድ ቅርብ ስላይደሉ በዚህም ላይ ሥራ ቢሰራ ፣
  3. ከዚህ በፊት እሱባለው በለጠ በተባለ ጸሐፊ ተዘጋጅቶ የቀረበ ፕሮቴስታነታዊ ጀሀድ በኢትዮጵያዊነት ላይ ስፋፋም የሚል መጽሐፍ ብዙ ቁም ነገሮችን የያዘ ስለሚመስለኝ ምን አልባት አገራዊ ፋይዳ ካለው ፍተሻ ቢደረግበት ብዙ ያልተሰራጨ ስለመሰለን ነው ፣

  ReplyDelete
 34. ዲ/ን ዳንኤል ሰናይ የሆነ ጅምር ነው።ስለ ሃገር እና ማህበራዊ ጉዳዮች የምትፅፋቸው ጉዳዮች ሁሉንም ያማከሉ ናቸው።የብዙዎች አመላካከት እየተለወጠ ነውና በዚሁ ቀጥል። ድንግል ታበርታህ። ሃሳቡን ከማመንጨት ጀምሮ አስፈላጊውን ሁሉ በማቅረብ ለተራዱህ እግዚአብሔር የሚበልጠውን ዋጋ ይስጣቸው።ጉትጎታችሁ ለከንቱ አይደለምና ደስ ይበላችሁ። ፀጋው ያላቸዉ ሌሎች እህቶችና ውንድሞች እንዲህ ባለ የጡመራ አገልግሎት እንዲያገለግሉ ቢበረታቱ። በየቀኑ ቤትህን እንጎበኛለን።

  ሰናይ ዘቤልጅየም።

  ReplyDelete
 35. ይድነቃቸውJune 22, 2010 at 4:49 PM

  በመጀመሪያ ለአንተና ለባለቤትህ እንዲሁም አንተን ለረዱ ሁሉ እግዚአብሔር ውለታችሁን ይክፈል፡፡

  ዳኒ የአንተን ጽሁፍ በማንበብና ለቤተሰቤም በማስነበብ ብዙ ትምህርትን ገብይተንበታል፡፡ አንተ ግን የሰራኸው ሥራ ቀላል አይደለም እና እባክህን እኛ አንባቢዎችህ በአቅማችን አንተን የምንረዳበት መንገድ ቢመቻች በበኩሌ ደስተኛ ነኝ፡፡

  እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ፡፡

  ReplyDelete
 36. well done . thanks W/ro Tsilat may God bless your family .
  Comment :
  1. as some one mentioned earlier pls write on issues like Marriage (befor and after )
  esp. what to be done befor Marriage acc. to Church teachings.

  2. Concerning your preaching why don't you come to Hawassa incorporating with MK ? that will be Great .i hope you understand what i mean.

  thanks Dn. Daniel
  we look forward to hear your voice .

  ReplyDelete
 37. +++
  Dani,--
  Ke 67 Hagerat Tera Engeba. Le Eredarw Sewoche Lerasachen.

  ReplyDelete
 38. Dn Daniel & Tsilat,

  Egziabher abzito Yibakachihu, Ke hultu 'Gormsoch' gar. I donot want wast my time by saying it good, thank you bila bila. Just you born to do this , so do it. Comments:
  1. Eskahun yewtu tsuhufoch gudelten bemasyat yemiyastmru nachew, yiketlu, gn beka hulgize wekesa selcheng libelh, est andaande tiru negarchinnm tsaf... ande ande mok yibeln...des yibeln
  2. Yihen eyserha endale hono yaa Bizu nefsoch yemdinubt yewengel azmara fetsomo endynak, yane entalalen
  3. Give chance for others to submit some article for to publish it, even it may minimize ur load....
  4. I will join you in other work may be after 3 years , we will do more, not in the social aspect... I will tell u when the time come...

  Egziabher betsebhin yibark....


  The future man(uk)

  ReplyDelete
 39. Hi, Dani I'm a regular visitor of your blog, it worths me too much, especially when I was too far from the cities for field work. I know you are doing something good today for the better tomorrow. I understand you and your ideas are really a treasure for evry body with an open mind and heart, I understand the problem you have encountered may be more than you have expressed. However don't give up, may God help you.

  ReplyDelete
 40. Dani,

  be enezeh 3 werate weste bezu kemeneger azel tsufochih endinimar, erasachinen endinimeremer, aderegonale ena bezuhu ketel.

  Mejemrer hulum yejemeral, mefetsem gin le tikitoch new ena egziabher amelak eske fitsame dires yetebekeh, yaberetah. Endihum wede balebetehen tselaten endezehu.

  egziabher lejochehen yibarekachew, le antem tsegawen yadeleh

  Berta Berta

  ReplyDelete
 41. ዉድ ዲ/ን ዳንኤል፤

  ሰላም በድጋሚ። የዚህን ብሎግ መቀጠል አለመቀጠል ጉዳይ በኛ በአንባቢያንም ሆነ ባንተ ዘንድ ለዉይይት ስላልቀረበ (ስለማይቀርብ) ምን ይጨመር ወዳልከዉ ላምራ። ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች ያሉት በተለይ የፋይናንስ አቅም ማጎልበትን በተመለከተ እኔም የምጋራዉ ሲሆን (በተለይ ጽሁፎችህን በመጻህፍት መልክ በማባዛት ብንገዛዉ) የኔ ተጨማሪ አስተያየቶች የሚከተሉት ናቸዉ (አዳዲስ ሐሳቦች አይደሉም፤ ግን ትኩረት ቢሰጣቸዉ ለማለት እንጂ)፡-

  1. በተለይ ወጣቱ ትዉልድ ራዕይ እንዲኖረዉ የሚያስተምር፤ ራሱን፣ ቤተሰቡን፣ ሀገሩን፣ ሃይማኖቱን፣ ባህሉን ወዘተ እንዲያከብር የሚያስተምሩ፤ ስራ ወዳድ እንዲሆን የሚያነሳሱ ጽሑፎችን ብታስነብበን፤

  2. አንተ ከኢትዮጵያ ዉጭ ብዙ ሀገሮችን እንደመጎብኘትህ መጠን በነዚህ ሀገሮች የሚኖሩትን ኢትዮጲያዉያንና ትዉልደ-ኢትዮጵያዉያን የመንፈሳዊና ማህበራዊ ኑሮ ሁኔታ በራስህ እይታ ወይም ከእዉነተኛ ታሪክ በመነሳት ብታቀርብልን ደስ ይለኛል፤ ይህ በተለይ ሀገርቤት ላሉትና ወደ ዉጭ አገር ለመሄድ ለሚመኙ ወገኖቻችን (የመጥፎም ሆነ የጥሩ) የልምድ ልዉዉጥና ትምህርት ይሆናል ብዬ አስባለሁ።

  3. በአገር ቤትም ይሁን በዉጭ አገር የሚኖሩና መንፈሳዊ ህይወታቸዉ አስተማሪ የሆኑ ሰዎችን (በተለይ በጋብቻ ህይወታቸዉ፣ በልጆች አስተዳደግ ወዘተ) በቃለ-መጠይቅ ወይም በስነ-ጽሑፍ መልክ ብታቀርብልን ደስ ይለኛል።

  በተረፈ የቅዱሳን አምላክ ከነቤተሰብህ በዕድሜ በጤና ይጠብቅልን።

  ወንድምህ በብሪታኒያ

  ReplyDelete
 42. በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡ በቅድሚያ የባለቤትክንም ሆነ የአንተን ልብ ያነሳሳ አምላክ ስሙ የተመሰገነ ይሁን ላበረታቱህ እና ከጎንህ ላልተለዩት ለሁላችሁም እግዚአብሔር እድሜና ጤና ያድላችሁ አሜን፡፡ብዙ አስተምረኸናል አሁንም በርታ ተበራታ ከዚህ የበለጠ ለመስራት እግዚአብሔር ሞገስ ይሁንህ የልብህን መሻት ሁሉ አምላክ ያሳካልህ እኛ አቡዳቢ ደብረ ሰላሞች በጣም እንወድሃለን እናከብርሀለን ኑርልን መልካም ሴት የባልዋ ዘውድ ናት እና ባለቤትህም በህይወታችን ትልቅ ትምህርት ሰታናለችና እግዚአብሔር እድሜ ከጤና ጋር ያድልልን በርቱልን፡፡ ሌላው እንደ ሀሳብ የምሰጠው እኛም ከበረከቱ እንድንሳተፍ የቻልነውን እንድንሰጥ የሂሳብ ቁጥር ቢኖራችሁ መልካም ነው እላለሁ ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሃምሳ ሰው ግን ጌጡ ነውና ብቻህን እንዳትጎዳ ለማለት ነው እግዚአብሔር ይጠብቅህ ለእኛም አንብበን የምንለወጥበት አዕምሮ አምላክ ያድለን አሜን

  ReplyDelete
 43. dane be stronge we are withe you

  ReplyDelete
 44. Dear Dn. Daniel
  I would like to thank you for all you done to my
  knowledge in Orthodox Tewahido through your books and preachs. From this blog i am learning everyday something to become a beter humanbeing and to see my self in a real mirror as an Orthodox Christian and an Ethiopian. Everybody involved to happen this get a Blessing from our GOD and his Holy Mother Kidst Dingel Mariam.I would like to thank your wife for everything she done and will do to support you in any way. If it is possible i love to contribute something (financially )to help you to continue writing on this blog.Last but not least I am very proud to be an Ethiopian with brothers like you.
  God Bless you and your beloved ones .
  Your sister from Holland

  ReplyDelete
 45. +++
  ሰላም እግዚአብሔር ከቤተሰብህና አንተን ከተራዱጋር ይሁን::
  ለቀጣይ
  1= በማኀበራዊ ጐዳይና በትዳር ዙርያ ብትቀጥል
  2 = ለአገልግሎት ስለሚኖረን ትጋት
  3 = ስለራስን መግዛት፡ መቻቻል፡ መተሳሰብን፡ ፍቅርን (ክርስቲያናዊ ህይወት)
  4= ጥንታዊ ጽሑፎችን
  5= የቅዱሳንን ተጋድሎ
  6= ገዳማትና አድባራት
  7= ስለልጆች መንፈሳዊ አስተዳደግ
  8= አልፎ አልፎ ከፖለቲካው ጋር የሚገናኙትን ቢቀነስ እኔጃ ፈራሁ

  ከዝዋይ

  ReplyDelete
 46. Dear brother Daniel,
  Thank you very much for your contribution in nation building. I would like to see some contribution on the hidden treasure of EOTC mostly available in Geez and in remote areas. I believe you have done detailed research in this regard and you have the basis to write on these issues. These include its knowledge in astronomy vs. the modern astronomy,its knowledge in traditional medicine vs. modern medicine including the Chinese and Asians, the view of its philosophers such as Zerayakob, etc. It will help all Ethiopians to know our ancestors unique capacity and may also initiate graduate students at home and abroad to continue further study based on what you ave learned so far.
  God bless

  ReplyDelete
 47. Dear Dani

  I agree with the person who said KEPOLTICAW BEKENES

  Abu Dhabi

  ReplyDelete
 48. አስተያየቴን ትላንት ነበር የሰጠውት ዛሬ ሳየው የለም(connection problem).ቢሆንም በአጭሩ
  3 ወሩ "አጭር ግን ረጅም"(i take it from AN)
  ለአንባብያን፡ አሰተያየታችን መገምገሙን ውደዱት በጣም በጣም በጣም ይጠቅመናልና

  ለዳኒ፡ ከላይ እነደገለፅከው አኛ ከተለያየ ቦታ፣የተለያየ የእውቀት ዸረጃ፣የተለያየ አላማ፣የተለያየ...ስለዚ መጥፎ ነገር ውስጥ ራሱ ጥሩ ነገር አይጠፋምና አሁን ካለክ በላይ ታጋሽ ሁንና....."ለምጣዱ ሲባል..." አይደል?
  በተቀረው በርታ።

  ReplyDelete
 49. የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን
  በቅድሚያ ይህን ሀሳብ ያመነጨው የባለቤትህ አይምሮ የተመሰገነ ይሁን! በርታ፣ ጠንክር እያሉ በቃል ብቻ አይደል በተግባርም ካንተ ጎን ለቆሙት ሁሉ እግዚአብሔር እስከፍሜው ድርስ በበጎ ምግባር ያፅናቸው!
  ይህን ጡመራ ከጀመርከው አሁን 3 ወር ነው ይህን ጨምር የምለው ነገር የለኝም በውስጤ ያለውን ነገር ሁሉ በጊዜው እንደምታስነብበኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
  አንዱ አስተያየት ሰጪ ‹‹ለምሳሌ ኢትዮጵያ አንድ የባንክ አካውንት ቢኖርና የቻልነውን ያህል ከበረከቱ ብንሳተፍ?›› እንዳለው ሀገር ውስጥም ያለነው እንዴት አንተን ማገዝ እንዳለብን በገንዘብ ብቻም አይደለም በማቴርያልም፣ በጉልበትም ቢሆን እንደ አቅማችን ማድረግ የሚገባንን ብትለን ደስ ይለኛል፡፡

  ፍፃሜህን እግዚአብሔር ያሳምርልህ በክፉ ከሚያይህ ጠላት ዲያቢሎስ ይጠብቅህ!

  ReplyDelete
 50. +++
  ውድ ዳኒ ሦስት ወር ሙሉ ከተሰጠህ ሳትሰስት፣ እውቀትህን፣ግዜህንና ንዋይህን ሳትቆጥብ ላቀረብካቸው ጽሑፎችህ እግዚአብሔር ይስጥልን። ለምናነባቸውና ለሚመለከተንም ልብ ይስጠን።

  እኔ ጽሑፎችህን ከሁለት ወገን ነው የማደንቃቸው፦ሥነ ጥበባዊ ውበታቸው እና ቁም ነገረኛነታቸው። የአርከ ሥሉስን ነገር ስታነሣ አንድ ነገር ትዝ አለኝ። ብሎግህ የተጀመረ ሰሞን ሞራሌ መጣና 'ዳኒ በሚጽፋቸው እያንዳንዱ ርዕስ አንድ አንድ ግጥም እጽፋለሁ' አልኩና ጀመርኩልህ ግን ከሦስት በላይ መጻፍ አልቻልኩም... ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው አይደል የሚባለው። ተሰጥኦ ያላቸው ሌሎች ቢያደርጉት እና ወደፊት ስታሳትማቸው ቢካተቱ የአርከ ሥሉስን ዋጋ አያጡበትም። ምን ይመስልሃል?

  አንዳንዴ ለዚህች ሀገር የተወሰኑ ሰዎች ብቻ የሚሮጡ ይመስለኛል።ብዙዎቻችን ግን አሯሯጭ /pace maker/ ወይም ተመልካች ነን። አብረን እንድንሮጥ ምን ቢደረግ ይሻላል ትላለህ?

  ReplyDelete
 51. Dane, Thanks allthings good Bereta for Family Egezabeher Yetebekelhi.
  Urs.

  ReplyDelete
 52. ዳኒ እግዚአብሔር ጸጋዉን ጨምሮ ይስጥህ ፡፡ ብዙ ቁምነገሮችን አስጨብጠህናል አሁንም ብዙ ማወቅ እንፈልጋለን በርታልን ፡፡

  ReplyDelete
 53. Selam Dani,

  -Your 3 months works are very fantanstic.
  -The most important and crucial point is its continuty with out much stressing you both in time and financially too.
  -What suppose to be done,I think, is that you need to organize the web site properly.That is

  1.you could give access for advertisment,
  2.Invite some Ethiopian or else writers,scintists,etc to contribute their works on your web site.This will upgrade more the site.You may add a statment for these other people works as*this work may not reflect Daniel's view* or other favourable word.

  In such a way by your administrating the website, new ideas may come arise for a number of problems that our socity is facing.

  Who knows in feuter you may have access to have TV chanal,Radio station,...etc who knows? YE MENGISTU LEMA GITIM LAY TIZ YALEGNIN HAREG LICHEMIR ENA LISENABET.-*MAN YAWKAL YE MESKEL WEFI ENA MESKEREM KETERO ENDALACHEW....HULETUM BE MESKEREM WER BIK MALETACHEW*
  There for who knows in such your briliant begning you may have TV chanal,in feuter.The precious thing is an idea that every or most people is agreed.The other thing is very simple.Moreover our Almighty God is with those of all who have positive mind.
  YIKOYEN
  Getachewb22

  ReplyDelete
 54. Your initiative is absolutely appreciable and your articles of extremely high standard.

  I don't want to sound as if I can foresee things better than you do, but I am against your involvement in issues of politics.

  I wish you could withdraw from any topic with political sentiment to focus and consolidate the other areas we usually know you of.

  Today we may admire your works but the very same people would start rejecting you the days you start making " mistake" with politics.

  Well, criticism and objections are inevitable even if you strive for excellence as you are doing, but it would be very disappointing and unfortunate for you if people start rejecting you becuase of your involvement in politics whether directly or indirectly.

  I am so much indebted to your work and may God bless you now and forever.

  KEEP GOING!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!


  Andu negn.

  ReplyDelete
 55. I appreciate all of your work, i have the acess to read almost all your writting (the blogs as well as your books) which were very nice. I do not want to say much about you... your simply exceptional so please keep it up. But i want from you if you add the following in your future blogs:
  1. The good side of our society
  2. More things about sprituality since moral values might not sufficient by it self to solve our deep routed problem (my opinion)

  ReplyDelete
 56. Dear Dn Daniel
  I would say Thanks to God and to you too.
  Those articles are realy important for the renaissance of Ethiopia.I don't want to take over your crown which God has arranged for you by praising you too much.
  I don't have words to appriciate the issues you raised and the way you presented them.
  Yet, there are lots of things to you have to write in the future.We can contribute the issues you can write on. We prey for those helping you in all aspects.
  Keep it up!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 57. በመጀመሪያ እግዚአብሔር ልብህን አነሳስቶ ይህን ስራ እንድትሰራና በዚህም ስራ ውስጥ እኛ አንባቢ አንተ አቅራቢ ሆነን ለ3 ወራት እንድንቆይ ያደረገ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፡፡

  እኔ በብሎጉ ላይ ያለኝ አስተያየት እስከ ዛሬ ያቀረብካቸው ጽሁፎች በሙሉ በጣም አስተማሪና ጠቃሚ በተለይ ለኢትዩጵያ ወደ ተግባር ቢለወጥ የሚበጅ ጹሁፍ ነው እላለሁ፡፡ በጹሁፎችህ ላይ ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ነገር ይበዛል ይህ ደግሞ የሀገርን ታሪክ ለመቀየር እስከሆነ ድረስ ግድ ነው፡፡ እኔ ለአንተ የምሰጠው ምክር በብሎጉ የግልህን ፖለቲካዊ አመለካከት እንዳታንፀባርቅ እንድትጠነቀቅ ብቻ ነው እንጂ ፖለቲካዊ ነገር መጻፍህ ጥሩ ነው፡፡ ምክንያቱም የኢትዩጵያ ፖለቲካ ጥሩ ቢሆን በጥሩ መልኩ የሚጠቅማት መጥፎም ቢሆን በመጥፎ መልኩ የሚጐዳትን ከማንኛውም ተቋም በላይ ቤተክርስቲያናችንን ስለሆነ የአለምን የፖለቲካ ሁኔታ የተገነዘቡ ልጆቿ በፖለቲካ ውስጥ እንቅስቃሴ ቢያደርጉ (ለሀገር የሚጠቅም የፖለቲካ እስትራተጂ ሀሳብ የሚያቀርቡ ቢሆኑ) ለቤተክርስቲያናችን ይጠቅማታል ብዬ አምናለሁ፡፡


  በተጨማሪ ብሎጉ የጥያቄና መልስ ውድድር ቢያዘጋጅ ጥያቄው ማንኛውም አይነት ሊሆን ይችላል ማለት የኃይማኖት፣ የታሪክ … ሰውን ወደ ንባብ የሚገፍ ወይም በብሎጉ ላይ ካቀረብካቸው ጹሁፍች ውስጥ ሊሆን ይችላል እና እንዲሁም ተሳታፊም ጥያቄ የሚያቀርብበት እዚህ ጋር ተሳታፊ ብዙ አይነት ጥያቄ ሊያቀርብ ስለሚችል በብሎጉ መቅረብ የሚገባቸው የጥያቄ አይነት ተወስኖ በዛ መልክ እንዲቀርብ ቢቀረግ መልካም ነው እያልኩ በመጨረሻ የባንክ አካውንት ከፍተህ ሁላችንም የአቅማችንን ብናደርግ ምክንያቱም 50 ሎሚ ለ50 ሰው ጌጥ ለአንድ ሰው ሸክም ስለሆነ በጋራ እየተጠቀምን አንተ ብቻ እዳ ከፋይ መሆን ስለሌለብህ አካውንት ብትከፍት እኔ በራሴ በየወሩ የቻልኩት ላደርግ በእግዚአብሔር ስም ቃል እገባለሁ እርግጠኛ ነኝ ሁሉም በዚህ እንደሚስማሙ፡፡ እግዚአብሔር እይታህን ከዚህ ይበልጥ ያስፋልህ

  ማኪ
  አ.አ

  ReplyDelete
 58. በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!
  ሰላም ወንደማችን እና መካሪያችን ዲ/ዳንኤል ክብረት በቅድሚያ እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን መካሪ ወንድም ስለሰጠን።
  ፅሑፎችህን አንብበናቸዋል በጣም መካሪ እና ገንቢ ናቸው በዚሁ ቀጥል ብሎጉ እንዲቀጥል በሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ከጎንህ ነን።
  እግዚአብሔር ቤተስቦችህንና አገልግሎትህን ይባርክ።

  ታናናሽ ወንድሞችህና እህቶችህ
  ከምድረ ጣልያን

  ReplyDelete
 59. my comment is i sow most people want you to open a bank account to support you fainansioly which i think is a bad idea you know why?
  1. thos people who hate what u doing will say he got the blog for money
  2.thos people who work for money will do the same and when accountebilty comes they will use you as a reference
  3.money is the most eveil object as it's mentioned in the bible you might go out of your way in that case but that dose't mean i don't want u to get that support no no don't get me rong offcourse u do what am saying is u need extra carfull when you do it. KINDU from johannsburg

  ReplyDelete
 60. ወንድሜ ዲ/ን ዳንኤል በመጀምሪያ ባንተ ላይ አድሮ እያስተማርን ላለ ልኡል እግዚእብሄር ክብር ምስጋና ይግባው! ቀጥሎ እንተን በሃሳብም ሆነ በማንኛውም ነገር ከጎንህ ሆነው ለረዱህ በተልይም ለውድ ለባለቤትህ ትልቅ ምስጋና እናቀርባለን:: ላንተም የፀጋ ሁሉ ባለቤት ፀጋውን ያብዛልህ የድካምህንም ፍሬ ይቀበል:: ይህ እገልግሎት ቀላል አይደለም አስካሁን በፃፍካቸው ጽሁፎች ምን ያህል እራሳችንን እንድናይ እና እንድንለወጥ እንዳደረገን ልነግርህ አልችልም ስለቤተክርስቲያንናችን ጻድቅ እባቶችም ታሪክ እና ህይወት እንድናውቅ እረድተኽናል አሁንም መድሀኒአለም በአገልግሎት ያፀናህ አኛንም አስተዋይ ልቦና ይስጠን::
  እህትህ ከሰሜን አሜሪካ

  ReplyDelete
 61. please! open bank acaount for this web sit. from USA

  ReplyDelete
 62. Dear Dn. Daniel

  thank you very much for your heart to assess your effort on the blog, this by itself is a lesson for us to be purposeful on everything we do including our services. With in the past three months, I and my friends learned a lot especially all the burning issues that you have raised helped us to see ourselves and see where the problem of our country & church lies. And we realized that each and everything we do including the information we pass to our brothers and sisters have a big impact on our country & church situation. All the issues have great messages which help us to see serving beyond a confined place & time. I suggest if there is a way that this blog can be viewed by more and more people through out the world, as some of my brothers & sisters mentioned in many other comments, for those who don't have internet access, if there is a way to reach out to them, it will impact so many. There are issues that you should raise concerning ethnicity, parent-child relationship, internet usage, identity, confusions on the border b/n culture & faith, responsibility, devotion, the digital generation & the future ......etc

  Let the lord of wisdom help you to reach out as many people as needed for transforming our country!

  your sister in him

  ReplyDelete
 63. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን።
  ዲያቆን ዳንኤል በመጀመሪያ እግዚአብሔር አምላክ አገልግሎትህን ይባርክልህ በዚህ ሦስት ወር ዉስጥ ቡሎግዋ በጣም ብዙ ትምህርት ሠጥታለች አሁንም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በመስጠት ላይ ትገኛለች እንደኔ ከሆነ በጣም ለሁሉም ሕብረተሰብ በጣም ጠቃሚና ራሳችንን ዘዎር ብለን እንድናይ ያደረገንን ብዙ ትምህርት አግኝተንበታል በጣም እናመሰግንህ አለን እናከብርህ አለን።
  ዲ.ዳንኤል አሁን ደግሞ ቡሎግዋ በምን ዙሪያ ብታተኩር እነደሚሻል አስተያየት እንድንሰጥህ ጠይቀኻል እነደኔ ከሆነ ምንም እነኳን ገና ብዙ የሚዳሰስ ዘርፈ ብዙ ጉዳይ ቢኖርም አሁን አጥብቀህ እንድትመክርና እነድታተኩርበት የምፈልገዉ ወቅታዊ ጉዳይ ነዉ ብየ የማስበዉ ነገር ቢኖር በተለይም በዉጭዉ ዓለም ትልቅ ፈተና እየሆነ ስለመጣዉ እየፈረሰ ስላለዉ የእግዚአብሔር ሕግ የሀገር ዋልታ የቤተብ ምሰሶ ስለሆነዉ ሰዉ እንደዋዛ እያየዉ ሰለመጣዉ ሰለ ቅዱስ ጋብቻ/ትዳር /ምንነት ሁሉም ወንዴ ላጤና ሴተ ላጤ ሁኖ ሳያልቅ አሁኑኑ ሳይቃጠል በቅጠል እነዲሉ አበዉ ዳኒ በተለመደዉ የተባ ብዕርህ እባክህ አንድ በለን ተእዳርና አላማዉን እባክህ በደንብ በተከታታይ አስተምረን ምከረን።
  አምላከ ቅዱሳን አገልግሎትህን ይባርክልህ ቤተሰብህንም ይጠብቅልህ እድሜ ጤና በረከት ያድልሕ አሜን።
  አባ ገ.ኪ.ከቤጋስ

  ReplyDelete
 64. dn.dani, first of all i would like to thanks for your dedicate work.
  keep it up! GOD bless you.

  ReplyDelete
 65. አምደ ሚካኤልJune 24, 2010 at 10:57 AM

  አምደ ሚካኤል

  "አንዳንድ ወንድሞቼ በመሳደብም ሆነ በመራገም፣ ሞራሌ በቀላሉ የሚነካ መስሏቸውም ስም የሚያጠፉ ጽሑፎችን በመላክ የተባበሩኝን ሁሉ እግዚአብሔር ልብ ይስጣቸው እላለሁ፡፡"

  እኔ በበኩሌ እንዲህ ብታደርግ እንዲህ አድርግ የሚል አስተያየት የለኝም
  ሳይነግሩህ የህብረተሰቡን ሃሳብ ተረድተህ የምተጥፍ ስለሆነ
  በርታ ቀጥል
  ከጎንህ ለቆሙ ሁሉ እግዚአብሔር መልካም የድካማቸው ዋጋ ይስጥልን
  አንተንም ብዙ እድትመክረን እግዚአብሔር ዕድሜ ከጤና ጋር ሰጥቶ ያቆይልን

  ReplyDelete
 66. ዳኒ እስካሁን ለቤ/ክ ሆነ ለሀገርህ እያደረክ ላለከው ነገር ሁሉን ማድረግ የሚችል ልዑል እግዚአብሔር ማንም ሊቀማዕ የማይችለውን በረከት ይስጥህ።
  ከዚህ ሌላ ግን ሁለት ነገር ማለት እፈልጋለሁ፡-
  ፩. ሁሉም የዚህ መልካም ስራ ተሳታፊ የሚሆንበትን መንገድ መቀየስ ያስፈልጋል። ለመጀመር ያህል ብዙ ወንድሞችና እህቶች እንደጠቀሱት ስራውን በፋይናንስ እና በዕውቀት የምናግዝበት መንገድ ቢመቻች።
  ፪. የአንድ ወንድሜ አስትያየት እንደመነሻ አድርጌ ሃሳብ መስጠት እፈልጋለሁ። ይህውም"4 = ሌላው ከፖለቲካው ቢቀነስ እኔጃ ፈራሁ " ይህ የብዙ ሰዎች አመለካከት ይመስለኛል። ግን ፍፁም ስህተት የሆነ አመለካከት። ያለውን እውነታ እንደውንትነቱ ማስቀመጥ ውይም ማስትላለፍ የሁላችንም ግዴታ ይመስለኛል። ይሄ ፖለቲካ ነው፣ እነገሌን ይነካል እና የመሳሰሉትን ስያሜዎችን በመስጠት መቆም በነበረብን ቦታ ላይ ባለመቆማችን ተጎጂዎች እየሆን ነው። ቤ/ክ እንደምሳሌ ብናነሳ በእንደዚህ አይነት አስተሳሰባችን ምክንያት የአጥበያ ተሳትፏችን ባለመወጣትና ከሰበካ ጉባኤ እራሳችንን በማግለል ቤተክርስቲያናችንን ሌሎች የግል ጥቅማቸውንና ተልዕኮቸውን እንዲያሰኩ በር ከፋች መሆናችን ለዘህ ማሳያ ነው። በሌላውም ቢሆን እንደዘሁ ነው። ስለዚህ ስለ እውነት በኩሽናውስጥ በመንሾካሾክ (በሀሜት) ሳይሆን በአደባባይ እንቁም
  ልዑል እግዚአብሔር ጥበቡንና ማስተዋሉን ያድለን አሚን
  ወስብሃት ለእግዚአብሔር
  ወለወላዲቱ ድንግል
  ወለመስቀሉ ክቡር
  ወ/አማኑኤል

  ReplyDelete
 67. Hi Dn. Daniel I have been your fan from the day you start writing on addis neger and I really enjoyed it. When I saw your blog I was very happy, let me list the things that I like from your writing
  1. History : I like the fact that you write about historical facts which is the base for any community. History will make you to know about your past and enables you to have a clear view of your future because you will know your identity.
  2. Social: this is the part where you are really good at. You just make me to picture life in a simple way
  3. Religion: still on this one what you write are more related to historical aspect of religion and I love this because most of the time we don’t get that information easily. Churches usually preach about the Holly Bible and the rules and regulation that must be followed in the religion so your view will helps us to strengthen about the religion.
  So what I would say is, your potential is beyond writing articles
  Try to make a community in different sectors from different parts of the world to help their country. Let’s say we have a computer science community then this group should take the responsibility of developing free software may be for very important organizations in Ethiopia like hospitals , Kebeles,…. And make their job easier. You have said on “ወንበሩ ነው እንዴ? Article የአመለካከት ለውጥ በሰዎች ኅሊና ውስጥ ካልመጣ አሠራሮች እና መመሪያዎች ብቻቸውን ምን ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ ጨለማን መተቸት ብርሃን፣ ክፉን መተቸት ደግነት፣ ኋላ ቀርነትን መተቸት ብቻውን ሥልጣኔ፣ ድንቁርናን መተቸት ብቻውን ዕውቀት አያመጣም፡፡ በሽታውን ተቃውመሃል ማለት መድኃኒቱን ይዘሃል ማለት ላይሆን ይችላል፡፡ ረሃብን ታወገዛለህ ማለት ጥጋብን ታመጣለህ ማለት ነው የሚለውን ዋስትና አያሰጥም፡
  So what I am trying to say is let’s make your articles to take peoples into actions. Pointing out problems only cannot be the solutions. I know it is a very hard thing but we can do it with unity.
  All in all you are very very good writer with amazing views and Thank you for sharing it with us
  May GOD be with you through all your life.

  ReplyDelete
 68. dear d/n Daniel

  This work is very interesitng. I have read the reviews of this three months articles. I am exremely greatifull for this. I can say you have contributed a lot for your country and this work must be continued to the future deeply and consitentily.I would like to tanck all the peaple who have helped you through this article preparation and continuation.
  Let almighty God give you stength and bless you.

  ReplyDelete
 69. hi dani gongradulations you are doing something for yor people,i know you face different chalanges during all your ways but i have full confidence that you will withstand it alwayes becouse you are following your heart and your heart is filled by the good sprit keep it up dani we ethiopians need you

  ReplyDelete
 70. Selam dn.daniel what a blessed time it was!!
  Let me add an idea:
  As u told as 'liberal kirstna'is one of the challenges of the eotc,that is right if so it is better to teach us dogma and kenona(MIstirate bete krstian) of the church with histories and social critiques.

  Yemstir balebet ablto mistirun yigletlih!!
  we are ready to advertise the web,we did,doing....
  Belekso yemizeru bedesta yachidalu endil zare bitgodam nege firewun tayalehna des yibelih.

  ReplyDelete
 71. Selam Dn Daniel,

  I am coming again for the comment. Most the people raised about contribution for the bloge. In my view late us leave it for the time being. Our God have blessed your home by many things, you know well that. You can sell your books for us, but please do not take any cash for now. Time will come to do that. Tsilat will cover 1000 birr, you are giving 2 hours per day for us. Just it is my view,

  Egziabher yistilnn

  ReplyDelete
 72. ሀብተ ሥላሴJune 24, 2010 at 6:03 PM

  Dear Daniel,
  I really appreciate your commitment for the nations building.Next plz incorporate more and more deep spritual articles.
  May GOD bless u.

  ReplyDelete
 73. Selam Dn. Daniel;
  It is a good practice to reflect back what you did in the first 90 days. Hope you will continue in the same spirit.
  About the blog itself, I did not come across your opinion about what your readers write. I feel that some of them require further discussion or your inputs.
  The second one is about the number of readers of this blog. We know that they are from 67 countries. What is their number?
  Thank you

  ReplyDelete
 74. ዲ/ን ዳንኤል፤

  በመጀመሪያ እየሰራህ ያለኸው ሥራ ታላቅ መሆኑን ለመግለጽ እፈልጋለሁ። ተነባቢነቱና ውጤቱ በጣም እየሰፋ እንደሚሄድ አያጠራጥርም። አምላከ ቅዱሳን እሱ ሁሉንም ድካምህን የሚያውቅ ዋጋህን ይክፈልህ። ጸጋውን ያብዛልህ። ሁሉንም እንዲህ ባለው መድረክ መግለጽ አይቻልም። እግዚአብሔር በዚያ ማሕበር ልጆች ብዙ ተጠቅሟል አሁንም ብዙ እየተጠቀመ ነው። ገና ብዙ ብዙ ሰርተህ የምታሳየን እንዳለ አልጠራጠርም። ይህን በዚሁ ላብቃ። እንድትበረታ አደራ ለማለት ብቻ ነው። ይህ በጠቅላላ የባለቤቴም አስተያየት ነው።

  ይህ ብሎግ ተጀምሮ ጽሑፎችህን እንዲህ በቀላሉ ለማግኘት እንድንችል ለረዱ ለባለቤትህ ለሌላው የወንጌል መምሕሬ ለዲ/ን ኤፍሬም እሸቴና ለጠቀስካቸው ለሌሎችም የእኔና የባለቤቴ ምስጋናችን ይድረሳቸው። እግዚአብሔር ዋጋቸውን ይክፈላቸው።

  በጽሑፍህ ላይ ይህንን ብሎግ ስትጀምር ስለነበረው ሁኔታና በስራ ላይም እየደረሱህ ስለነበሩት አንዳንድ ደካማ ጽሑፎች አንስተሃል። በአብዛኛው ካለማወቅ የሚመነጭና ሌላ አላማ ያላቸው ሰዎች እያሳሳቷቸው ሊሆን ብቻ ነው የሚችለው የሚል እምነት ነው ያለኝ። እና አንተም እኛም እንጸልይላቸዋለን። ሥራውን በሚመለከት ግን “እድል ፈንታ አትስጡ” እያልክ ያስተማርከን አንተ መሰልከኝ። ይህንም በዚሁ ልዝጋው።

  ለጽሑፎችህ አንድም እንከን ማውጣት አይቻልም። በዚሁ ይቀጥል ከማለት ሌላ የምለው ብዙ የለኝም። ምናልባት ከጠቀመ አንድ ያለኝ ሃሳብ ምንድን ነው የብሎግ ፎርማት እንደተጠበቀ ሆኖ (በየጊዜው አዳዲስ ጽሑፍ የመታየቱ ነገር) አሁን ጽሑፍ በምታወጣበት ፍጥነት (3 ወር ባልሞላ ጊዜ 45 ጽሑፍ) ልቀጥል ካልክ ብዙ ጊዜህን የሚሻማ ሊሆን ስለሚችል በሳምንት ወይም በአስር ቀን ከአንድ ጽሑፍ በላይ ይበዛብህ እንደሆነ ለማለት ነው። አንባቢው በየቀኑ ጽሑፍህን ቢያገኝ የሚጠላ ያለ አይመስለኝም። ግን ዘላቂ እንዲሆን በአንተ በኩል ያለው ጫና በመጠኑ የሚቀንስበት መንገድ ቢታሰብበት ጥሩ ይመስለኛል።

  ይህን ካልኩ በኋላ እኔና ባለቤቴ በግላችን ብዙም ባይባል ለአንድ ወር የኢንተርኔት ወጭህን የሚሸፍን አንድ ሽህ ብር እንዲደርስህ ፈልገን ነበር። መልካም ፈቃድህ ከሆነ የስልክ ቁጥርህን በኢሜል አድራሻዬ ብትጠቁመኝ በረከቱ ለእኛም ይደርሰናል።
  እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

  ReplyDelete
 75. ዳኒ አስተያየቶቹን ሁሉ አነበብኩ በተጨማሪ ለሚወጡ ጽሑፎች ብዙ ስለተባለ እኔ ምንም ባልል ግድ የለም። ብሎጉን በገንዘብ መደገፍ ግን በጣም የምስማማበት ጉዳይ ነው። እንዴት ለሚለው አሁንም አስቴያየቶች ቀርበዋል። ለምሳሌ የባንክ አካውንት መክፈት፣ ጥሩ ነገር ሆኖ ሳለ አንድ ወንድም እንዳለው ሌላ ነገር ይዞ የሚመጣ ከሆነ መጽሐፍትህን ብሎጉ ላይ የሚወጡትን እጨመርክ እንዲሁም እስከዛሬ የታተሙትን ላልገዙ ሰዎች ማዳረስ ምንችልበትን መንገድ ካለ ተጨምሮ ቢታሰብብት።ከሁሉም በላይ ግን አንተ ከኛ አስቴያየት ተነስተህ ጥሩ ዘዴ እንደምትጠቁመን አልጠራጠርም።

  ሰላመ እግዚአብሔር አይለይህ

  ወንድምህ ከአሜሪካ ምድር

  ReplyDelete
 76. Dear Dn. Daniel,

  I have no words to express my appreciation about your articles. I am benefited a lot form them. Please keep it up. God bless you and your family!

  From Wageningen University
  ( The Netherlands)

  ReplyDelete
 77. ምን ብዬ ላምሰግንህ አንት ብርቅዬ የብዕር ሰው በመጀመሪያ ከዚህ በፊትም ደጋግሜ እንደገለጥኩት አንተ ግሩም አሰተማሪ ነህ ሁልጊዜ እወነታን ስትናገር ፈጥኖ ልባቸው የሚነካ ሰዎች እንዳሉ መገንዘብ አለብህ ይህም ሰዎች ራሳቸውን እንዲያዩ ያደርጋቸዋል የሕብረተሰብን ችግር መቅረፍ የሚቻለው ሁልጊዜ በሀይል መሆኑን አስቀርቶ አንድ አንዴም በብዕር መሆኑን ያረጋግጣል ለዚህም ዋነኛው ተዋናይ አንተና መሰሎች ናቸው ይህ ነው ብይ ልነግር አልችልም የተሰማኝን ደሰታ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንተርኔት ሳገኝ ሰለዚህም እኔም ብዙዎቹ እንዳሉት እባክህ በምን መንገድ ይህ መልካም ትምህርት ሊሰፋፋ እንደሚችልና እኛም እንዴት እንደምንረዳ አሳውቀን ተጠቃሚ ብቻ ሳንሆን ጠቀሚም መሆን መቻል አለብን ብዬ አምናለሁ
  በዚህ አጋጣሚ ይህንን ሃሣብ ከአንተ ጋር ሆነው ላበረታቱህ ለውድ ባለቤትህና በሰራ ላይ ለማዋል ያለተቆጠበ ጥረት ላደረጉልህ ግለሰቦች በሙሉ ምሰጋናዬ ይድረስቸው።

  ReplyDelete
 78. Thank you Danni, I really appreciate your work. Tebarek.

  ReplyDelete
 79. Dear Dani,

  I am one of the guys who are really addicted to your blog and consistently refer to it. I just write you my comments whenever I had a question or whenever I had something to say but I usually gave you my thanks and appreciation in my heart. I had a lot to say now but I think most of my ideas are already explained in the above comments by others and I hope you will keep them into account. all I can say now is replies to some of the comments posted by some people which I am against.

  1. Politics: well, firstly the mission of the blog is "regarding Ethiopia's culture, politics, religion and tradition.". and so far you were just in the same page with your mission consistently and that is what makes this blog great. consistent in your schedule, consistent in your topics and consistent in everything. all I can see from this is you are doing this just to make a difference and the result is coming. when you write about politics I don't see you writing blindedly. it is just for the betterment of the country as a whole and as a citizen that is the best thing to do from your part. I don't mean that everybody is cheering you when you write on politics. there might be people out there who needs to attack you for no good reason with out analyzing but God may open their heart if they understand what you meant in those topics as your aim is not to attack them but to let them understand in a different dimension for the sake of the country and its people. bottom line, form my side it would be good if you pursue writing on politics as well with great care but above all, just follow your heart.

  2. Money. I just read some people are willing to contribute money for funding this blog. well I am with them. but I read some guy commenting as this is not a good idea for fear that money is evil and may cause some problems. let's be clear with some thing. so far you have been alone feeding us with all this knowledge. now I don't think that it will be a problem for those who are willing to contribute including me for making this blog a great blog where people can learn and change for a good reason. The fact is everybody do not have the same idea and some people may see the bottle half empty instead of half full. contributing money will help the blog to proceed in a bigger scale and as mentioned by other comments there are a lot of ways to get the fund. I really can't advice you as I am the kind of guy who needs advice but my view is for the sake of this blog's continuity finance is very necessary and that is the least we can do as readers and beneficiaries of this blog to explain our appreciation. if there are people out there who take this as a negative idea, no one is forcing them and they have the right not to contribute while still visiting the site and that is still okay.

  ReplyDelete
 80. Thanks and long live to you! I was out of connection and a little bit backdated but thanks to the archives I have seen everything.

  Congratulations for the third month anniversary of this blog. I hope and pray to go for the next three years, decades, centuries and ….who knows!

  I am also happy to see readers from Ethiopia took the first place.

  I would like to thank those people you mention for their great contributions for the reality of this big job. You are even lucky to have such supportive, cooperative and industrious life partner. So thanks dear Tsilat (the Tablet or the Ark).

  I have seen all the comments and I hope you will summarize it and a constructive manner.

  Bye the way I was eager to see the photos of Aleka Gebrehana and where is it?

  ReplyDelete
 81. Dear brother,thank you. May God encounter your efforts and May He blesses you with His gifts.

  Saying this,as per my view your writing focuses more on psychological thought and ideology (I mean religious). In addition, u shall add some dogmatic religious thoughts of Fathers and Bible.Besides,by cooperating with brothers/if possible/ you ought to give answers to readers.Moreover, my last comment is to readers: dear brothers and sisters, your comments shall be free from emotions,biases, and should be constructive.

  ReplyDelete
 82. በመጀመሪያ ላመሰግን እፈልጋለው::የምታነሳቸው አሳቦች የምትጽፋቸው ፁሑፎች አስተማሪ ናቸው ስለዚህ ቀጥልበት:: ሌላው እንድታካትት የምፈልግገው

  1.ዘመናዊነት ወይም የተሻላ ሰው መሆን በልብስ ነው ወይስ?
  2.ማንነታችንን ገንዘብ ይለውጠዋል ወይስ?

  ReplyDelete
 83. Congratulatin!you did good.
  God bless you.

  DD
  Seattle WA
  U.S.A

  ReplyDelete
 84. ክቡር
  ዲያቆን ዳንኤል ክብረት

  እስኪ ምናልባት ጠቃሚ ሆኖ ቢገኝ
  ትንሽ ምክር ቢጤ ጣል ላድርግ

  እኔ አሁን ልነግርህ ያሰብሁት ምስጋና አይደለም :
  ምክር ነው

  1ኛ , በኢትዮጵያ አገራችን በአሁኑ ሰአት ያለው ሁኔታ በግልጽና በነጻነት ለመጻፍ ለሚፈልጉ ወገኖች : መስዋዕት የሚያስከፍል ነው ሲባል ስለምሰማ : ወደ ፖለቲካ ነክ ነገሮች ጠልቀህ ባትገባ ጥሩ ነው እላለሁ

  2. የጽሑፎችህ ይዘታቸው : አንዳንድ ጊዜ በጣም መረር . ጎምዘዝ ስለሚሉ :: በተቻለ መጠን : እያዋዛ የሚያስተምር የሥነ ጽሑፍ ውበት እየተጠቀምህ : በማኅበራዊ ጉዳዮች , በሃይማኖታዊ ትምሕርቶችና በሌሎችም ትምሕርት ሰጭ ጽሑፎች ብትቀጥል : ጥረትህ ሁሉ
  ከመወደድ
  ከመናፈቅ
  ከማዝናናትና ዕውቀት ከማስጨበጥ ጋር
  እገዚአብሔር በሰጠህ ፀጋ ብዙ ሰዎችን ልታስተምርና ልትመክር ትችላለህ ::

  3. ሃይማኖት ነክ ጽሑፎችን ስትከትብ : አባቶችን የሚደፍርና የሚገስጽ ጽሑፍ ባታዘውትር : ከቻልህ እንደዚህ ዓይነቱን አካሄድ መቼም ብትተወው እመክርሀለሁ ::

  አባቶች ምንም በአባትነት ደረጃ ላይ ቢቀመጡ ;
  . ሰዎች ናቸውና ሊሳሳቱ ይችላሉ :
  . ትንሹ ስህተትም በነሱ ዘንድ ሲሆን በጣም ገዝፎ ይታያል :
  . አንዳንዴም ; አንዳንድ ጠማማ ሰዎች በግል ጥላቻ ተነሳስተው (ዘሪሁን የሚባል ሰው በአቡነ ሳሙኤል ላይ እንደጻፈው ) የሚቀራረብ ቃላት እያገጣጠሙ ስም ሊጠፉ ይችላሉ ::

  ምንም ይሁን ምን : አባትቶችን በአደባባይ ላይ እያወጡ መሳደቡ መርገም እንጅ በረከት አይሆንም ::
  ለቤተ ክርስቲያናችንም ውርደትና ሀፍረት እንጅ : ክብር ሊሆን አይችልም ::


  ካም (ከነዓን ), አባቱ ኖኅ የወይን ጠጅ ጠጥቶ በመስከሩ ምክንያት : ራሱን ስቶ : ራቁቱን ወድቆ ባገኘው ጊዜ : ይህ ድርጊት : ለካም ስህተት ሆኖ ታይቶት ነበር .... ::

  ነገር ግን የአባቱን ገመና ለሌላ በማውራቱ ምክንያት : በዚህ ድርጊቱ : ተረገመበት እንጅ አልተመሰገነበትም ::

  ይህን ድረ ገጽ የሚያነቡትም የእኛ ቤተ ክርስቲያን አባላት ብቻ ላይሆኑ ስለሚችሉ ::
  ላላፊ ላግዳሚው አባቶችን ማሳጣቱ አይጠቅምም ::
  ለማንም ቢሆን : መራራ ነገርና : ሌላውን በመንቀፍ ላይ የመሰረተ መልእክት ማስተላለፍ : ሰውን ወደ አውሬነት ስለሚለውጥ እንዲህ ዓይነቱ የአጻጻፍ ዘዴ ተወት በማድረግ : ወደ ምርምር , ትንተና , አመስጥሮ , የሥነ ልቡና የሥነ ተፈጥሮ , የእግዚአብሔርን ከሀሌ ኩሉነትና መፍቀሬ ኩሉነት ወዘተ ............ ብትጽፍ እንዴት ደስ ባለኝ

  ከፈጣሪ የተሰጠህ ፀጋ : በማንናውም ረገድ ብትጽፍ : ይቻልሃልና :
  አደራ ብዕርህን ለበጎ (ለፍቅረ ቢጽ , ለመክሥተ ምሥጢራት , ለአርትዖ , ለአለብዎ , ለአመስጥሮ , ለምክርና ለዕዝናት ,....... አውለው ::

  ማሳሰቢያ
  ይህን ከላይ የላክሁልህ መልእክት : ጠቃሚ መስሎ ከታየህ በድረ ገጹ ላይ አውጣው : ለሌላ አስተማሪነቱ ካልታየህ ግን ; ለራስህ አስቀረው :
  ቢወጣም ደስ ይለኛል :
  ባለመውጣቱም ቅር አይለኝም ::

  ዋናው ነገር : ጽሑፉ አንተ ዘንድ መድረሱ ነው ::

  አድናቂ ወንድምህ

  ReplyDelete
 85. ዳኒ በርታ እስኪ እስከጊዜው ድረስ እንጅ አሁን ባለው የመጣፍ መብት ምክኒያት… ከመታገዱ በፊት እስኪ በእግዚአብሔር ስለ ዴር ሱልጣን በሰፊው ጣፍልን እባክህ አንጀቴን ሁልጊዜ የሚበላው ስለሆነ ነውና፡፡ ድንግል አትለይህ

  ReplyDelete
 86. May the Mercy of our God the Almighty and the prayer of our beloved lady St. Mary be with you and all yours (specially your wife, your life).

  Dani, I read your Articles with a great imperssion, the wisdom of our Lord be with you and keep it on. Then, I want to post One idea; in our sunday school,Addis Ababa, I am serving as head of education department. So, I am trying my best to organize the first big electrinic library beside the book library we have; me and my brothers and sisters are on move.

  Among the collections that we need to have in our list your sermons, articles and researches are on the top of the page. So, would you please help us to collect them. (i.e. your more than 1000 sermons that you mentioned during your interview with dejeselam blog and othe sources that you have). please, please, please, please, ..........................

  I hope you will communicate me and I promise that I will show you building the bigest electronic library we ever had;

  Next is my e-mail address; looking for your response soon.
  wessagnubeti@yahoo.com

  ReplyDelete
 87. May God bless you and make your vision real.

  ReplyDelete
 88. Anti- Agura zeleleJuly 2, 2010 at 8:37 AM

  I feel it is a nice start but not to be proud or fel quite special. You need to strengthen your efffort much more to adress other peoples and ideas! I feel that you better keep on feeding us. Pl otherwise don't feel anything special.... If so, You may also join the path of "AguraZelel sebakins".

  ReplyDelete
 89. I am happy to read your articles. i do not agree with poeple who say that reduce the poletical issues. As far as i understand u are not supporting one group over the other. what i am seeing is showing how weaker things can be improved for overall welbeing and development of our country. please do continue writing. Benatih hulem tsaf. As someone said it is also good to open a bank account. 50 lomi land sew shekim new le 50 sew gin get new. if we contribute a little bit of money, it will be a great thing for the sustainability.

  beyezemenu astemari, mekari, tekuami yemayasatan leul Egziabher yikiber yimesgen. bechernetu antenim Yitebikilin.

  ReplyDelete
 90. DEAR DANI ...I AND MY FRIEND WANT TO THANK U FOR EVRYTHING THAT U DOING NOW.... WE ARE happy to read your articles..GOD BLESS U AND ETHIOPIA
  BIRUK TEKLU ..ADDIS ABEBA

  ReplyDelete
 91. my name is Genene
  u are the bast to me.plies go the same way i am read every thing written by this WEB cite.some of them printed and give to "seninbet timhirt bate" and read to the member.but i have one question to u.that is "how can develop my reading habit?" plies respond to me."kiya1433@yahoo.com"
  GOD BLESS U!10Q

  ReplyDelete