Saturday, June 19, 2010

ወንበሩ ነው እንዴ?

የአመለካከት ለውጥ በሰዎች ኅሊና ውስጥ ካልመጣ አሠራሮች እና መመሪያዎች ብቻቸውን ምን ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ፡፡ ጨለማን መተቸት ብርሃን፣ ክፉን መተቸት ደግነት፣ ኋላ ቀርነትን መተቸት ብቻውን ሥልጣኔ፣ ድንቁርናን መተቸት ብቻውን ዕውቀት አያመጣም፡፡ በሽታውን ተቃውመሃል ማለት መድኃኒቱን ይዘሃል ማለት ላይሆን ይችላል፡፡ ረሃብን ታወገዛለህ ማለት ጥጋብን ታመጣለህ ማለት ነው የሚለውን ዋስትና አያሰጥም፡፡ አንዳንዴ በተቃራኒውስ ሊሆን ቢችል?

ጥቂት የገረሙኝን ነገሮች እስቲ መጀመርያ ላካፍላችሁ፡፡ ተራ ሰው እያለ ጨዋ፣ ሰው አክባሪ፣ እንኳን የሰው ገንዘብ ሊወስድ የራሱን አበድሮ የማያስመልስ፣ በሀገሩ ኋላ መቅረት የሚቆጭ፣ በሞሳኞች የሚናደድ፣ በቢሮክራሲ የሚማረር የነበረ ሰው ዕድሉን አግኝቶ ቦታውን ሲይዘው፣ ሲጠላው የነበረውን ነገር ለምንድን ነው በባሰ ሁኔታ ሲፈጽመው የሚገኘው ?

ተራ አገልጋዮች እያሉ ትጉኃን፣ ብቁዐን፣ ቅኑዐን፣ መንፈሳውያን የነበሩ ሰዎች እንዴት ነው የሥልጣኑን ቦታ ሲይዙት፣ ደግነታቸው እና ቅንነታቸው፣ መንፈሳዊነታቸውና ታማኝነታቸው ሁሉ ጠፍቶባቸው «ሥልጣን በቀረባቸው ኖሮ» እስከመባል የሚደርሱት?

እዚህ ሀገር ቤት እያለ ዋነኛ የመንግሥት ፖሊሲ ደጋፊ እና ተከራካሪ የነበረ ሰው ወደ ውጭ ወጥቶ መኖር ሲጀምር ለመለወጥ አፍታ እንኳን ሳይወስድበት እንዴት ነው ሲደግፈው የነበረውን ሁሉ በጭፍን መቃወም የሚጀምረው? ጭንቅላት እንደ ኮምፒውተር ሶፍትዌሩን በደቂቃ ይቀይራል እንዴ፡፡ መለወጥስ ተፈጥሯዊ ሂደት የለውም?

በተቃራኒውም እዚያ ውጭ ሀገር እያለ መንግሥት ምንም ዓይነት የጽድቅ ሥራ ቢሠራ አልጥምህ ብሎት ሲቃወም የኖረ ሰው ሀገር ቤት ሲገባ በምን ዓይነት ሁኔታ ሀሳቡን ሊቀይር እንደቻለ ሳይታወቅ እንዴት ነው መንግሥት ተሳስቼያለሁ ያለበትን ነገር ሳይቀር «እንዴው ለትኅትና ነው የተናገረው እንጂ አልተሳሳተም» እያለ ጭፍን ደጋፊ ሊሆን የሚችለው?

አስቀድመው በተቋቋሙት ፓርቲዎች አለመተባበር፣ አለመሥራት፣ ግለኛነት፣ አለመጠናከር፣ የጠራ ፖሊሲ ማነስ ተናድዶ እና የተሻለ ነገር መሥራት አለብኝ ብሎ አዲስ ስም እና መተዳደርያ አውጥቶ አዲስ ፓርቲ ያደራጀ ሰው እንዴት ነው የተናደደባቸውን የሌሎች ፓርቲዎች ድክመቶች እና ስሕተቶችን በፎቶ ኮፒ የሚደግመው?

ምናልባት ከላይ ላነሣሁት ችግር መነሻው ወንበሩ ይሆንን?

ወንበሩ ግድግዳውን፣ ጣራውን፣ ጠረጲዛውን፣ መደርደርያውን ሁሉ ገንዘብ በገንዘብ አድርጎ ያሳያል እንዴ? ወንበሩ ዘመድ ዘመድ ቅጠር፣ ቢሮክራሲ አብዛ፣ ተሰብሰብ ተሰብሰብ፣ ያሰኛል እንዴ? ያለፈውን አሠራር ለማሻሻል ስንት ቢፒአር ያሠሩ ኃላፊዎች የበፊቶቹ ኃላፊዎች ከሠሩበት አሠራር በባሰ እንዲሠሩ የሚያደርጋቸው ወንበሩ ይሆን? የለውጥ ሐዋርያት ተብለው፣ የየመሥሪያ ቤቱን ቢፒአር አጥንተው፣ያለፈውን ተችተው እና አዲስ አሠራር ቀርጸው፣ለውጡን ያራምዳሉ ተብለው በቦታው ሲቀመጡ፣«የውኃ ውኃ ምናለኝ ቀሃ» የሚያሰኙን ከወንበሩ ይሆን?

ስብሰባ ላይ ስለ ሙስና፣ ስለ ብልሹ አሠራር፣ ስለ ሀገር ዕድገት፣ በምግብ ራስን ስለ መቻል፣ስለ ሰብአዊ መብት፣ስለ እኩልነት፣ስለ ፍትሕ፣ ተንትነው እና አሳምረው የሚናገሩ ሰዎችን ሳይ እና ስሰማ ሰዎቹ የሚያምኑበትን ነው የተናገሩት ወይስ ወንበሩ ነው ያናገራቸው? እላለሁ፡፡

የመጀመርያ ዲግሪያቸውንም ሆነ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የመመረቂያ ጽሑፍ ሲያዘጋጁ የተቹትን፣ ቢታረም እና ቢስተካከል ብለው ሃሳብ ያቀረቡበትን ነገር እነርሱ ቦታውን ሲይዙት ግን እንዲያ የሚባል ሃሳብ መኖሩን እስኪረሱት ድረስ በተቹት አሠራር መልሰው እንዲሠሩ የሚያደርጋቸው ወንበሩ ይሆን እንዴ?

ናይሮቢ ከተማ ውስጥ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ከድህነት ወለል በታች የሚኖርበት «ኪቢራ» የሚባል መንደር አለ፡፡ የሀገራችን ሰው «ካሉት በታች ከሞቱት በላይ» የሚለው የኑሮ ዓይነት በዓይነ ሥጋ የሚታየው እዚያ ነው፡፡ ከሚበሉበት የማይበሉበት ጊዜ የሚበልጥባቸው ድሆች በተጨናነቀ እና በቆሻሻ በተሞላ አካባቢ ይኖራሉ፡፡ የዛሬው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ከፍተኛ ድጋፍ ያገኙት በኪቢራ መንደር ነበር፤ ምርጫው ተጭበረበረ ባሉ ጊዜም አያሌ መሥዋዕትነት የከፈሉላቸው የኪቢራ ድሆች ናቸው፡፡ ኪቢራን ለማሻሻል፣ ቢያንስ መኖርያ፣መንገድ፣ ትምህርት ቤት እና የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ቃል ገብተው ነበርና፡፡

ምርጫው ከነግርግሩ አልፎ ራይላ ኦዲንጋም ቦታውን ያዙ፡፡ ኪቢራ ግን አሁንም ያንኑ የድህነት ጉዞዋን እንደ ቀጠለች ነው፡፡ የተነገረ እንጂ የተሠራ ነገር ለማየት አልታደለችም፡፡ እንዲያውም ኦዲንጋ ለቀጣዩ ምርጫ እየተዘጋጁ ነው፡፡ ኦዲንጋ ከመመረ ጣቸው በፊት «ኬንያውያን ፍትሕ እና ማኅበራዊ ዋስትና አጥተዋል» እያሉ ለመተቸት በምሳሌነት የሚያነሷት ኪቢራን ነበር፡፡ የኪቢራን የድህነት ጉዞ የኬንያን ኢፍትሐዊ አሠራር ማሳያ አድርገውት ነበር፡፡ በቦታው ላይ ሲቀመጡ ግን እርሳቸውም እንደ ቀድሞዎቹ ሆኑና አረፉት፡፡ እኔ ኪቢራን ከሁለት ሳምንት በፊት ስጎበኝ ያገኘኋቸው ኬንያዊ ሽማግሌ «ወንበሩ ነው፣ ችግሩ ከወንበሩ ነው፤ እኛ አሁን በወንበሩ ላይ ማን ይቀመጥ ማለታችንን ትተን ሰዎቻችን በምን ዓይነት ወንበር ላይ ይቀመጡ ብለን ማሰብ አለብን» ነበር ያሉኝ፡፡

አንድ ጊዜ እንስሳት ሁሉ በአንበሳ አገዛዝ ተማረሩ፡፡ በርሱ ያገዛዝ ዘመን በዙርያው ያለው ዛፉም ቅጠሉም፣ ሣሩም አፈሩም ሥጋ እየመሰለው ይህንን ቁረጥ ያንን ፍለጥ እያለ ሊጨርሳቸው ደርሶ ነበር፡፡ በዚህ ተማርረው እንስሳቱ ሁሉ ዐመጹና አንበሳን ከመንበሩ አወረዱት፡፡ ከዚያም ያለፈውን ስሕተት ሊደግም የማይችል ማን ነው? ብለው ተመካከሩ፡፡ በመጨረሻም በደግነቱ፣ በየዋሕነቱ በቅንነቱ ተማርከው፤ ሥጋ በል ባለመ ሆኑም ተደስተው በግ ንጉሥ እንዲሆናቸው መረጡት፡፡ እርሱም በደስታ ተቀበለው፡፡

የንግሥናውን በዓል አክብሮ በትረ መንግሥቱን ጨብጦ ወደ መንበረ መንግሥቱ ሄዶ ተቀመጠ፡፡ ወዲያውም አጠገቡ የቆመውን ጠባቂውን ጠራና «ያንን ሥጋ አምጣው» አለው፡፡ ጠባቂውም ግራ ገባውና «ጌታዬ እርስዎ ሥጋ የማይበሉ በግ ነዎት፣ ደግሞም በአካባቢው ቅጠል እንጂ ሥጋ የለምኮ» ብሎ መለሰለት፡፡ በጉም «ያ ሽንጥ እንዴት አይታይህም፤ ደግሞስ ሥጋ ካማረኝ መብላት መብቴ ነው፤ ንጉሥ አይደለሁም እንዴ» አለው፡፡

ግራ የገባው ጠባቂ ፈጠን ብሎ በአካባቢው ወደ ነበሩት ሽማግሌዎች ተጓዘና «ንጉሥ በግ» ያዘዘውን ነገራቸው፡፡ እነርሱም በተራቸው ግራ ተጋብተው ወደ ንጉሡ በግ መጡና «ጌታችን ምን ፈለጉ?» ብለው ጠየቁ፡፡ ንጉሥ በግም «እዚያ የተሰቀለውን ሽንጥ ሥጋ አምጡልኝ» አላቸው፡፡ ሽማግሌዎቹም «ጌታችን እርስዎ ከመቼ ጀምሮ ነው ሥጋ መብላት የጀመሩት፤ በግ እኮ ነዎት» አሉት በጉም «ዛሬ ብጀምርስ ማን ከልክሎኝ» አለና መለሰላቸው፡፡ «በግ እኮ ሣር በል ነው እየተባለ ነው የሚነገረው፣ በትምህርት ቤትም ልጆቻችን የሚማሩት እንደዚሁ ነው» አሉና ጠየቁት፡፡ «በሉ እንደዚያ ከሆነ የምታውቁት ዕውቀታችሁን አስተካክሉ፡፡ የመማርያ መጽሐፉንም አስተካክሉ» አለ ቆጣ ብሎ፡፡

ሽማግሌዎቹ ቢቸግራቸው «በአካባቢያችንኮ ቅጠል እንጂ ሥጋ የለም» አሉት በጉን፡፡ በጉም «ይሄው ይታየኛልኮ፤ በአስቸኳይ ሂዱና አምጡ» አላቸው፡፡ ሽማግሌዎቹም ተያዩና «አይ የለም ችግሩ ከበጉ ወይንም ከአንበሳው አይደለም፡፡ ከወንበሩ ነው፡፡ እዚህ ወንበር ላይ ሲቀመጡ ቅጠሉን ሥጋ አድርጎ ያሳያል ማለት ነው» ተባባሉ፡፡ ከዚያም በጉን አባረሩት፡፡ በሁኔታው ግራ የተጋባው አጋዝንም «እስኪ ይሄ ነገር ምን እንደሆነ ልሞክር» ብሎ መንበሩ ላይ ሄዶ ተቀመጠ፡፡ ሽማግሌዎቹም «ደግሞ አንተ ምን ታየህ?» ብለው ጠየቁት፡፡ አጋዝኑም ፊት ለፊቱ ወዳለው ዛፍ ዞሮ ምራቁን እየዋጠ «ያ ሥጋ እንዴት ያሳሳል» አለ ይባላል፡፡33 comments:

 1. beteley ethiopia yalat wenber leyet yalech nat man yihon yeserat yegnan wenber dn.
  hulum le hizb sayhon le wenberu yigagal.............................

  ReplyDelete
 2. አባግንባር (ከሮማ)June 20, 2010 at 3:07 AM

  በቅድሚያ ሠላምታዬ ይድረስህ ዳኒ

  ዛሬ ደፍሬ ወዳንተ ልጠቁም ነው ምን እንደሆነ ታውቃለህ ይኼ መጀመሪያ ላይ ያነሳኸው ነጥብ:

  “… ጨለማን መተቸት ብርሃን፣ ክፉን መተቸት ደግነት፣ ኋላ ቀርነትን መተቸት ሥልጣኔ፣ ድንቁርናን መተቸት ዕውቀት አያመጣም፡፡ በሽታውን ተቃውመሃል ማለት መድኃኒቱን ይዘሃል ማለት ላይሆን ይችላል፡፡”
  ከስራዎችህ ጋር የሚቃረኑ አይመስሉህም? ለምን መሰለህ ችግርን ማወቅ በራሱ የመፍትሄ ግማሽ አካል ነውና::መተቸት የምትችለው ደግሞ ችግሩ ስታውቅ ይመስለኛል::

  ሌላው ደግሞ እኔ ከምር ይህንን አንዳንዴ የምታነሳቸውን ነጥቦች እፈራልሃለሁ :: ያ አምና ታስሮ የተፈታው አንዱ ዘፋኝ ኢትዮጵያዊ ወንድማችንም እንዳንተው እውነት ተናጋሪ እንጂ እስከማውቀው ድረስ ፖለትከኛ አልነበረም እና አደራህን ጠንቀቅ እያልክ:: ብዙ ካንተ ጽሁፍና ስብከት እየተማረ ያለ ሕዝብ ስላለ ፆም እንዳታስድራቸው ከሚል ስሜት የመነጨ ነው የኔ አባባል:: እስቲ ሌሎቹ የሚሰጡንን አስተያየት ደግሞ አብረን እንስማ

  ReplyDelete
 3. አትፍረድ ይፈረድብካል ነው ነገሩ

  ReplyDelete
 4. great observation.
  dani,GOD BLESS YOU.let's looking for ourselves those readers of this blog.

  ReplyDelete
 5. Dani, I have asked the same question myself so many times but never had concrete answer. Funny enough if you still talk to them in private they will tell you exactly the same thing but when they are in office or behind a speaker the story is different. The most probable reason I can think of is the fear of loosing the position. Everybody vies for leadership position for the benefits associated with that certain position rather than the responsibility that comes with it. Hence, once you are there your primary objective becomes retaining the position as long as you can. In the process you associate yourself with existing ideology and administration staffs, who definitely want you repeat the same thing. This is mainly because exercising your belief requires breaking the current system and nobody is willing to face the risk of loosing the position. In the context of Ethiopia it is only one man that can change the leadership style of the country. Everybody else, if you want to stay in office you have to tune your dancing style to the ongoing music.

  ReplyDelete
 6. yigermal!!!
  Dink sitota ,girum eyta

  ReplyDelete
 7. Egziabher yitebikih Dn. Daniel. Yebizuhanun hasab new betewabe akerareb yakebeliken.

  ReplyDelete
 8. WENBERU ENDALIL ENIYA WNBER SAYASASACHEW NIGSINACHEWIN TILEW GEDAM YEGEBUT ABATOCHE TIZ ALUGN.ENA CHIGRU KE EZIH KEDEM ENDALKEW KE SOFT WARU NEW HARD WARU MIN AREGE.
  Getachew

  ReplyDelete
 9. Here is another problem. I couldn't get difference b/n real politica and religion. As my opinion D/daniel is in right path. This is the thing we need. Especially this generation. Why should he scared. One of the commenter is say daniel should be careful about what he is writing for. If he doesn't write true and real who is going to tell us? I think his pen and blank paper doesn't allowed to write conterfeit stuff. Thank you D/daniel. Good bless for all you have been doing.

  ReplyDelete
 10. grum new Dani. berta....I LAUGHED A LOT.

  Nairobi

  ReplyDelete
 11. Aba Ginbar: What the outhor said is identifying problem without comming up with a solution. He didn't say just idetifying problem. I don't think there is any kind of contradiction in there. I advice you to try to read and understand what is right infront of your eyes instead of bla, bla.

  ReplyDelete
 12. ለእኔ ዋናው ወንበሩ ሳይሆን
  1.ለወንበሩ ያለን አመለካከት ይመስለኛል(ወንበሩን ከማግኘታችን በፊት)
  2.የተደበቀ ማንነት ውስጣችን ነበር(ከምንናገረው ጀርባ)
  3.ወንበሩን ተያይዞ የሚመጡ ነገሮችን ሰዎች በቅንነት አለመተርጎም(ጥሩዎችን ጭምር)
  ሌላው ወንበሩ እንዴት ነው የተገኘው? ክምንድነው የተሰራው? በእኛ ልክ ነው ወይ? የሚሉት መታየት አለበት


  በጣም አመሰግናለው
  ጥሩ እይታ ነው፡፡

  ReplyDelete
 13. ይድነቃቸውJune 21, 2010 at 11:19 AM

  ዳኒ የወንበሩማ ነገር........
  እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡

  ReplyDelete
 14. eliask
  ሰዎች ወደ ስልጣን ሲመጡ ቃል የገቡትን ሁሉ ለመፈጠም ይቸገራሉ። በፊት ያልነበራቸው ጠባ ይም ሊያሳዩ ይችላሉ። ተራ ሰው መሆንና ባለስልጣን ሆኖ መኖር ለየቅል ነው። አካበቢያዊ ተጽእኖ ፤ የቢሮክራሲው አካሄድ፡ የበተዘመድ የግል ፍላጎት ጥ ያቄ ወዘተ… ብዙ ግፊት ይኖራል። ከዚህም በላይ ደግሞ አድናቂዎች ሲበዙ ፡መረን መልቀቅ ይጀመራል። ራስን ከበፊተኞች ጋር ማነጻጸርና ለራስ ከፍተኛ ማርክ መስጠት ይከተላል።ሌላው የድብቅ ባህሪ ችግር /ምናልባትም ዲ/ዳንኤል - ስጋ በል አትክልት በሚለው ጥሁፍ ላይ እንደገለጥከው ነው/። በስልጣን ላይ ሆነን ሁሉን ለመፈጠም የሚቻለን አይደለም ይሁን እንጂ አቅማችን የፈቀደውን በቀናነት ከፈጸምን ከዚህ በላይ ምንም አ ያስፈልገንም ። ምክኒያቱም የሁሉም ባለስልጣን ድምር የስራ ውጤት ያማረ ይሆናል ና ።

  ReplyDelete
 15. አባግንባር (ከሮማ) said

  " ሌላው ደግሞ እኔ ከምር ይህንን አንዳንዴ የምታነሳቸውን ነጥቦች እፈራልሃለሁ :: ያ አምና ታስሮ የተፈታው አንዱ ዘፋኝ ኢትዮጵያዊ ወንድማችንም እንዳንተው እውነት ተናጋሪ እንጂ እስከማውቀው ድረስ ፖለትከኛ አልነበረም እና አደራህን ጠንቀቅ እያልክ:: ብዙ ካንተ ጽሁፍና ስብከት እየተማረ ያለ ሕዝብ ስላለ ፆም እንዳታስድራቸው ከሚል ስሜት የመነጨ ነው የኔ አባባል::"

  I second this comment!

  I don't see a problem as it is now. But why do you have to give room for something that has high chances of entangling yourself in politics or at least a cause for conflict for "the wrong " reason.

  Are you " bored" of your spiritual service and longing something else? I know you are not bored but just to express my fear. With due respect,don't try to defend it by saying it is part of " my spiritual service" .

  No matter how appealing and how much audience it can produce and how much hot the discussion could be, such topics are better left for "other people" , NOT you in my view.

  I hope you would give it a second thought!

  We love you and don't want to lose you in a subtle way.

  May God bless

  ReplyDelete
 16. good job Dani! Berta.

  ReplyDelete
 17. "ወንበሩ ነው፣ ችግሩ ከወንበሩ ነው፤ እኛ አሁን በወንበሩ ላይ ማን ይቀመጥ ማለታችንን ትተን ሰዎቻችን በምን ዓይነት ወንበር ላይ ይቀመጡ ብለን ማሰብ አለብን» ነበር ያሉኝ"፡፡ I think that shimagle told you the exact reason for all Africans issue including our Ethiopians too.
  However, You are a very insightful person; Keep it up!

  But I have a question for you! What if, if you were on that "wenber"? How could you explain yourself? Can you pridict something now? kkk

  ReplyDelete
 18. there is one saying in our language that is "seshom yalbela seshare yekochewal" dane the problem is not wenberu rather our culture. any how GOD BLESS ETHIOPIA

  ReplyDelete
 19. ዲ/ን ዳንኤል፣

  በጣም ጥሩ ጽሑፍ ነው። እግዚአብሔር ረጅም ዕድሜ ይስጥልን።

  እንዳልከው ከወንበሩ ይሆን ችግሩ ብለህ ብታስብ አይፈረድም። ትክክል ነው። ወንበሩ (ማለት ስልጣን) በሰው ልጅ አስተሳሰብ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለማሳየት ይመስለኛል።

  ቅንና መልካም የሆኑ መሪዎች እንዲኖሩ ቅንና መልካም ሕዝብ መኖሩ የሚረዳ የመሆኑን ያህል (አንዳንዶች መልካም ሕብተረተሰብ ክፉ መሪዎች አያወጣም ብለው በሚለጥጡት መስማማት ቢያስቸግርም) መላው የሰው ልጅ ሁሉ እንዲህ አይነት ከስልጣን፣ ከገንዘብና ከመሳሰሉት ስጋዊ ነገሮች ጋር ያለው ግንኙነት ላይ ተመሳሳይ ደካማ ጎኖች ያሉበት መሆኑ የሚካድ አይደለም። መጠኑ ሊለያይ ቢችልም።
  ይህ ከሆነ ታዲያ አንዱ አገር ከሌላው እንዴት ተለየ ለሚለው መልሱ በተሻሉት አገሮች የመንግስት መዋቅር (መንግስት፣ ጦር ሰራዊት፣ ፖሊስ፣ ፍርድ ቤት፣ ደኅንነት፣ መገናኛ ብዙሓን ወዘተ) እርስ በራሱ አንዱ ሌላውን በቅርብ ክትትል እንዲቆጣጠረው ሆኖ የተደራጀ መሆኑ፣ እንዲህ እንዲደራጅ በአንድ ወቅት መስዋዕትነት የከፈሉ ዜጎችና መሪዎች ስለነበሩ ነው የሚል እምነት ነው ያለኝ። ዛሬ የሰለጠኑ የሚባሉትን አገሮች ታሪክ በአብዛኛው ያየህ እንደሆነ ቀደም ሲል መሪዎች በስልጣን ጥም የቅርብ ዘመዳሞች ሳይቀር በመርዝ የሚገዳደሉ፣ ሕዝብም በሕዝብ ላይ እየተነሳ እየተጨራረሰ ይኖር የነበረ ነው።

  ይሁን እንጅ በየሃገሩ ይህ እንዲቀየር የሚጥሩ ቅን ሰዎች በየዘመኑ ሳይኖሩ ቀርተው አይደለም። ስማቸው ሳይጠራ ያለፉትን “ተራ ሰዎች” ትተን በየሃገሩ የነበሩትን ታላላቅ ጸሐፍትና ፈላስፎች ማስታወሱ ይበቃል። በሃገራችንም በውጭም እንዲህ አይነት ሰዎች ጠፍተው አያውቁም። ግን በጨካኞቹ መሪዎች፣ በጋሻጃግሬዎቻቸውና አንዳንዴም በራሱ በተሳሳተው ሕዝብ ቀድመው መስዋዕት የሚሆኑት እነዚህ ሰዎች በመሆናቸው ለውጡ ሳይሳካ ኖሮ ኖሮ ከግፍ፣ ከነጻነት ዕጦት፣ ከመራራ ሕይወት፣ ከጉስቁልናና ከድኅነት ብዛት እንዲሁም ከነዚህ ቅን ሰዎች የጥበብ አያያዝ የተነሳ ሕዝቡ ለእነዚህ ቅን ሰዎች ጆሮ የሚሰጥበት፣ እስከሞት ድረስ ከፍ ያለ መስዋዕትነት እየከፈለ እነዚህን ሰዎች ተንከባክቦ ከፍ ያለ ቦታ ላይ የሚያስቀምጥበትና ምሩኝ የሚልበት ጊዜ የመጣበት ሁኔታ እንዳለ ነው - ጽዋው እየሞላ።
  እነዚህ ሰዎች ደግሞ ከመጀመሪያውም ሕይወት የፈተናቸው ይሆንና ባገኙት አጋጣሚ ለራስ ሳይሉ እርቅና ይቅርታን ገንዘብ በማድረግ የተነሱበትን አገር የመለወጥ ተግባር እንዲያከናውኑ እድል ያገኛሉ። የኔልሰን ማንዴላ ታሪክ እዚሁ አፍሪካ ውስጥ በእኛ ዕድሜ ሲፈጸም እማኝ ልንሆን የበቃንበት ነው። እነዚህ መሪዎች ነጻና ብቁ ባለሙያዎች ያሉበት የምርጫ አስፈጻሚ አካል መስርተው እውነተኛ የሕዝብ ተወካዮችን ያስመርጣሉ፣ በነዚህ ሕዝብ በመረጣቸው ተወካዮች ሕገ መንግስት ያጸድቃሉ፣ የመንግስትን ስልጣን ወሰን ያበጃሉ፣ ፍርድ ቤቶችን፣ ጦር ሰራዊቱን፣ ፖሊስንና ደኅንነቱን ገለልተኛና ነጻ ሆኖ ለሕዝብና ለሕገ መንግስቱ ብቻ ተገዢ በሆነበት መንገድ ያደራጃሉ፣ ነጻና ዲስፕሊን ያለው የሕዝብ መገናኛ እንዲስፋፋ ይፈቅዳሉ መንገዱን ያመቻቻሉ፣ ሕዝቡ ማንኛውንም አይነት መረጃ የማግኘት መብቱንና ድርጅቶችም ለሕዝብ ግልጽ እንዲሆኑ የሚያስገድዱ ሕጎችን ይደነግጋሉ ወዘተ።
  አንዴ ይህን ማድረግ የቻለ አገርና ሕዝብ አብዛኛውን ችግሩን ደህና ሰንብት አለ ማለት ነው። ከዚያ በኋላ ወደኋላ መመለስ እንዲህ በቀላሉ የሚታሰብም አይደለም።
  ስርዓት እንዲህ በተዋቀረበት አገር ግለኞችና አምባገነኖች ሕዝብም ሳያውቃቸው በየደረጃውም በተግባር ሳይፈተኑ ወደስልጣን እርከን የሚደርሱበት ዕድል የመነመነም ቢሆን እንዲያው ድንገት በስርዓቱ ትንሽ ክፍተት አግኝተው ለከፍተኛ ስልጣን ቢበቁ ወይም ለስልጣን ከበቁ በኋላ ቢለወጡ እንኳን ያሻቸውን ለማድረግ ከላይ የተጠቀሰው አወቃቀር የሚያፈናፍናቸው አይደለም። ሲሞከር ፓሊስም፣ ደኅንነቱም፣ ጦርሰራዊቱም፣ መገናኛ ብዙሐንም ዝም የሚሉ አይደለም። ሁሉም ተጠያቂነት አለበትና።

  እውነተኛ ዲሞክራሲን አብዛኛው የዓለም ሕብረተሰብ የተቀበለበት አንዱ ምክንያት ይህን የሰው ልጅ የባሕሪ ደካማነት በመገንዘብ ስርዓትን በዚያ ግንዛቤ መሰረት እርስ በርሱ አቆላልፎ እንዲጠባበቅ በማድረግ ማደራጅት የቻለ በመሆኑ ነው።
  እና ምን ለማለት ነው። የሰው ልጅ ደካማ ነው። ስለዚህ አገርን ማስተዳደር ያህል ታላቅ ነገር በየትኛውም የስልጣን እርከን ላይ ባሉ መሪዎች ላይ (ማንም ይሁን ማን) እምነት በመጣል የሚተው አይደለም - አንተ እንደጠቀስከው ለአንባሳ ለአጋዘን ለበግም ቢሆን። መሪዎች ስርዓት ያዋቅራሉ ከዚያም የስርዓቱ አካል ይሆናሉ እንጅ አገርን የሚያስተዳድረው ስርዓቱ ነው የሚሆነው። ስርዓቱን ሕገመንግስት ይመራዋል። ሕገመንግስቱን ሕዝብ ይጠብቀዋል። ስለዚህ ነው ግለሰብ መሪዎች ሕገመንግስቱን መረዳታቸውን በውድድራቸው ጊዜ ከማረጋገጥ ባለፈ መልካም እንዲሆኑ ሕዝብ የማይጠብቀውም የማያስገድዳቸውም። ስርዓቱ እስካለ የነሱ ጉዳይ “ጨው ለራስህ ብትል ጣፍጥ ….” ከማለት ያለፈ አይሆንም። ካጠፉ ይቀጣሉ፣ ሕዝቡ (በተወካዮቹ በኩል) እና የስርዓቱ አካላት ግን የግለሰብ መሪዎቹን ነገር ለፍርድ ቤቱ ይተውና ዋናው ትኩረታቸውን ግለሰብ መሪዎች ያን ጥፋት እንዲያጠፉ የፈቀደላቸውን ክፍተት በስርዓቱ ውስጥ በማጥናትና ያ እንዳይደገም በማስተካከሉ ላይ ያደርጋሉ። እንዲህ እያለ ስርዓቱ ከዛሬ ነገ ይበልጥ እየተሻሻለ ይሄዳል። ግለሰቦች ያልፋሉ። ስርዓቱ ይኖራል። ሕይወትም ይቀጥላል ማለት ነው። ይህ ባልሆነባቸው ቦታዎች ይህ እስኪሆን ምጥ አለ። እግዚአብሔር ግን ሁሉንም በጊዜው ያደርገዋል ለማለት ነው።
  እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

  ReplyDelete
 20. Zelafto DebretiguhanJune 22, 2010 at 12:01 PM

  Dn. Daniel Selam lante yihun,
  Thank u for your idea,

  I think the problem is not with the seat(Wenber) it is with our backward political system. I fully agree with Mulugeta's comment. If we have good democratic system we will not complain any person instead it will become a matter of choosing the best.
  Therefore, most African countries including us need to establish a practical democratic system rather than the current theorotical democracy.

  ReplyDelete
 21. be ewenetu gerum eyeta newe berta

  ReplyDelete
 22. Dani yeche wonberi yemanate betam tamiralch melikam yemidregbat tihune ahunem yeman wonberi nati abet anche wonber sintune tazbishwu.lemelikam sira yawulsh elalhu..

  ReplyDelete
 23. Dear d/n DANIEL

  I have no word to express this at all. but i can say let our creature God bless and save you!!

  ReplyDelete
 24. ውድ ወንደም ዲ/ ዳንኤል አመስግንሃለሁ ስለዚህ መልካም ዕይታ፤ ምንም እንኳን አንድ አንድ ግለሰቦች ዕይታህ ከመሰመር የወጣና ለአንተ ያሰቡ መስለው አንድ አንድ ሃሣብ ቢሰነዝሩም ውነታ ከመናገርና ሕዘብን ከማሰተማር ወደ ሗላ እንደማያደርግህ ተሰፋ አድርጋለሁ ። እንዳልከውም በተለይ እኛ ኢትዮጲያኖች ባሕላችን ራሱ ትልቁን ክፍል ይጫወታል ብዬ አሰባለሁ ሁላችንም የመጣነው በአንድ ሰው ከሚመራ ቤት ውሰጥ ነው ይህንንም ሣብራራ ብዙ ጊዜ ያደግንበት ቤተ ውሰጥ አባታችን ፈላጭ ቆራጭ ነው ሚስት ለባሏ ከልጅ ማሳደግና ምግብ ከመቀቀል እንግዳ ከመቀበል ሌላ መብት የላትም ልጆችም እንደዚሁ አባታቸው ያለውን ከማክበርና ከማድረግ ሌላ ምንም ምርጫ የላቸውም ሃሣባቸውን ለመግለጥ ወይም የማይስማሙበትን ለመቃወም ምንም መብት የላቸውም ለአንድ ቤት ግንባታ የሁሉም ተሳትፎ ቢጨመርበትም ቅሉ በወንበሩ ተቀምጦ የሚያዝ የሚወስነው አንድ ሰው ነው ያም አባት ብቻ ሲሆን ይህም በልጀች ሕሊና ጠልቆ መግባቱና ከዚህ ባሕል የሚወጡ ሰዎች ወደፊት ያንን ትልቅ ወንበር ሲይዙ የሚያሰታውሱት አስተዳደጋቸውን ይሆናል ይህም ወንድሜ ሙሉጌታ እንዳለሁ ባልሰለጠኑት ዓለማት ጎልቶ የሚከሰት እውነታ ነውና ውድ ወገኖች እርስ በእርስ መተቻቸታችንን ትተን የሚቀጥለውን ትውልድ ዲሞክራሲ በተግባር እናሰተምረው እናሳየው በተለይ ኢትዮጵያኖች አባቶች ምናልባት የኛ ልጆች ወንበሩ ላይ ሲቀመጡ ለስራ እንጂ ለራስ ጥቅም አለመሆኑን እንዲያውቁ በተለይም ወንበሩ በየጊዜው ተለዋዋጭ መሆኑን ተረድተው ተመቻችተው እንዳየቀመጡ ከአሁኑ ቢማሩ የወደፈት ተሰፋችን እንደሰለጠኑት አገሮች ሊሆን የችላል” መልካም ተመኝ መልካም እንደታገኝ” እንዲሉ የኔም ምኞት ይህ ነውና ሁላችንም በስራ ላይ ከዛሬ ጀምሮ አንድናውለው መልካም ልቦና ይሰጠን እላለሁ።
  መምህር ዳንኤል እውነትን ከማሰተማረና የማናየውን ከማሳየት አትቆጠብ የሃይማኖት አንዱ ክፍል እውነትን መሰበክ መዘከር ነውና አንደበትህንና ብዕርህን አምላክ የጠብቅልን እናመሰግናለን።

  ReplyDelete
 25. Egziabher Edimehin Yarzimilh
  Ybizu sewochin Hiwot
  atirfehal 10q somuch.

  ReplyDelete
 26. ውድ ዳንኤል
  ድንቅ ማስተዋል ነው:: ወንበሩም እንዳለ ሆኖ በወንበሩ ዙርያ የተኮለኮሉት ብርጩማዎችስ ትልቅ አስተዋጽኦ የላቸውም ብለህ ነው? እንደ እኔ ከሆነ የወንበሩ አጃቢዎች ይብሳሉ:: በዚያ ላይ ደግሞ ያ የኢትዮጵያችን አባባል አለ: "ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጭዋል" የሚሏትን አባባል ያማያውቅ ባለወንበርም ሆነ ባለ ብርጩማ ማግኘት በሀገራችን ከባድ ይመስለኛል:: አማርኛ አንችልም የሚሉት ሁሉ ይችን አቀላጥፈው ይሰሩባታል:: ጥያቄው መፍትሄው ምንድነው? የሚለው መሆን ያለበት ይመስለኛል:: እስቲ በዚህ ላይ አስተያየቶችን እንስማ/ እናንብ!
  አንተንና ሥራዎችህን አምላክ ይባርክልህ!
  ደመ መራራ - ስዊዘርላንድ

  ReplyDelete
 27. አንተ 'ወንበር'...እባክህ ተናገር

  አንተ የኛ ቤት ... ትልቅ 'ወንበር'
  እስኪ ተጠየቅ ... በል ተናገር
  * * *
  አንተን የነካህ ... በ...ሙ...ሉ
  ተቀያይሮና ... ተለዋውጦ አመሉ
  ጨክን ጨክን ... የሚለዉን
  ፍርድ አጓድል ... ያሰኘውን
  ንገረን እስኪ ... በሽታውን
  * * *
  በበፊቱ ወንበር ... መቆርቆር
  የኖረው ሁሉ ... ሲያማርር
  ቀን ሲወጣ ... እድል ሲያምር
  ሲፈናጠጥ ... ያንተን መንበር
  የቀየረውን ... በል ተናገር
  * * *
  ሞገስህ ነው? ድሎትህ?
  ሙቀትህ ነው? ቁመትህ?
  እባክህ አንተ 'ወንበር'
  ጨንቆናልና ተናገር።

  ReplyDelete
 28. Please dani, You have good views, please write allot.

  ReplyDelete
 29. Dir Dani, It is a good views,thank you! long live dani!

  ReplyDelete
 30. "kebero seyayut yamer seyezut yadenager" yemilew endale hono ene deom endih beye lechemer
  keberon seyayut yamer SELETENEW syezut AYADENAGER!!

  ReplyDelete