Monday, June 14, 2010

የዓለም ዋንጫ በኢትዮጵያ

አሥራ ዘጠነኛው የዓለም ዋንጫ በአፍሪካ ምድር በመካሄድ ላይ ነው፡፡ ሀገራቸውን የወከሉ ቡድኖች ዋንጫ ለመሳም ይፋለማሉ፡፡ እኔ ግን «የኳስ ብቻ ነው እንዴ ዋንጫ ያለው? የሀገርስ ዋንጫ የለውም እንዴ?» ብዬ እጠይቃለሁ፡፡ «ሀገር እንደ ቡድን ለዋንጫ አይጫወትም ወይ» እያልኩ አሰላስላለሁ፡፡ እናም ኅሊናዬ «ይጫወታል እንጂ» አለና የሚከተለውን ወግ አወጋኝ፡፡

ባታውቀው ይሆናል እንጂ ሀገርማ እንደ ቡድን ለዋንጫ ይጫወታል፡፡ ይሄው ኢትዮጵያ እንኳን ስንት ጊዜ ለዋንጫ ተጫውታለችኮ፡፡ ታድያ እንደ እግር ኳሱ አይደለም፡፡ በዚህኛው ግጥሚያ ዋንጫ የበላችበትም፣ ያጣችበትም ጊዜ አለ፡፡ በርግጥ በታሪክ መዝጋቢዎች ዘንድ አንድ ልዩነት ተከስቷል፡፡ አንዳንዶች ዋንጫ ካጣችበት ይልቅ የበላችበት ጊዜ ይበልጣል ሲሉ፤ ሌሎች ደግሞ ዋንጫ ካገኘችበት ይልቅ ያጣችበት ጊዜ ይበልጣል ይላሉ፡፡

በታሪክ ሊቃውንቱ ዘንድ ያለው ልዩነት በኳስ ጠቢባኑም ዘንድ ተፈጥሯል፡፡ ጠቢባኑ «በእግር ኳስ ማጥቃት መከላከል ነው፤ መከላከል ግን ማጥቃት አይደለም» በሚለው ላይ ተስማምተዋል፡፡ «ለመሆኑ ኢትዮጵያ እንደ ቡድን የምትጫወትበት የጨዋታ ፍልስፍና በማጥቃት ላይ ነው ወይስ በመከላከል ላይ ነው የተመሠረተው?» በሚለው ላይ ነው ዋናው ልዩነታቸው፡፡ አንዳንዶቹ በመጀመርያዎቹ የሥልጣኔ ዘመናት በማጥቃት ላይ የተመሠረተ ጨዋታ ስንጫወት እንደ ነበር፤ በዚህም ምክንያት በሥልጣኔ ለመግፋት፣ በዓለም ላይ ኃያል ሀገር ሆኖ ለመቆጠር፣ የዓለምን ንግድ ከሚቆጣጠሩት ኃያላን አንዱ ለመሆን መቻላችንን ያትቱና ከተወሰኑ ዘመናት በኋላ ግን በመከላከል ላይ የተመሠረተ ጨዋታ መጫወት መጀመራችንን ይገልጣሉ፡፡ በዚህም ምክንያት አሸንፈናቸው የነበሩት ማይምነት፣ ረሃብ፣ ኋላ ቀርነት፣ ድህነትና ሌሎችም ቡድኖች ሲያሸንፉን መኖራቸውን ያስረዳሉ፡፡

ሀገሪቱ በእግር ኳሱ ለአፍሪካ ፋና ወጊ፣ለካፍ መሠረት ጣይ፣ ለመጀመርያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫዎች የአንበሳውን ደርሻ ወሳጅ እንዳልነበረች፣ ጭራሽ ወደ ኋላ ሄዳ እግር ኳስ በሀገሪቱ ያለ እስከማይመስል ድረስ ከአፍሪካ ዋንጫ ከራቅን ዘመናት መቆጠሩን በምሳሌነት የሚያነሡ ተንታኞች አሉ፡፡ ይህ ሂደት በብሔራዊ ቡድኑ ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱም እንደ ሀገር ጥንት አጥቅታ በመጫወት ስመ ገናና ሆና የሥልጣኔን ዋንጫ እንዳልወሰደች ሁሉ፤ ወደ ኋላ ግን «ሥልጣኔ» የሚለው ቃል በመዝገበ ቃላታችን ውስጥ ያለ እስከማይመስል ድረስ ከውድድር ውጭ ሆነን መኖራችንን በቁጭት ያነሡታል፡፡

ደግሞ አንዳንዶቹ በዚህ አይስማሙም፡፡

እነዚህ የኳስ ተንታኞች ነገራቸውን በማስረዘም «የጣልያን፣ የብራዚል፣ የእንግሊዝ፣ የስፔን፣ የግብጽ፣ እግር ኳስ» እየተባለ የሚጠራ በየሀገሩ የበቀለ፣ በቅሎም ሀገራዊ መሠረት ይዞ ያደገ እግር ኳስ አላቸው፡፡ የአንዱ ፍልስፍና፣ ጠባይ፣ ስልት ከሌላው ይለያል፤ ግን ለመሆኑ የኢትየጵያ እግር ኳስ የሚባል አለ?» በማለት ይጠይቃሉ፡፡ ታድያ አንዳንዶቹ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን መልስ ቢጤም ለመስጠት ሞክረዋል፡፡

«የኢትዮጵያ ሀገራዊ እግር ኳስ አንዱ ችግሩ ይኼ ነው» ይላሉ፡፡ አንዴ በእንግሊዝ፣ አንዴ በፈረንሳይ፣ አንዴ በአሜሪካ፣ አንዴ በሶቪየት ኅብረት፣ አንዴ በኩባ፣ አንዴ በቻይና የፍልስፍናና የርእዮተ ዓለም እግር ኳስ ስንሠለጥን ኖርን፡፡ ስለዚህም ኢትዮጵያዊ መሠረት ያለው፣ ከትውልዱ ጋር ተስማምቶ የመጣ፣ ለውጤት ልንበቃበት የምንችል ኢትየጵያዊ እግር ኳስ አጣን» ሲሉ ያመሠጥሩታል፡፡

ይህ ሁሉ ቢሆንም ግን ሀገር ቡድን ሆና ስትጫወት ጨዋታው እንዴት ምርጥ መሰላችሁ ይላሉ ተንታኞቹ፡፡ ሕግ አለ፡፡ ሜዳ አለ፡፡ ዳኛ አለ፡፡ አጥቂ አለ፡፡ ተከላካይ አለ፡፡ አማካይ አለ፤ ግብ ጠባቂ አለ፤ አሠልጣኝ አለ፤ ተጠባባቂ ተጨዋች አለ፡፡ ምን የሌለ አለ፡፡

መቼም የእግር ኳስ ሕግጋት በዓለም ላይ ግልጽ ከሚባሉት መካከል ናቸው፡፡ ደግሞ የሚገርመው የእግር ኳስ ሕግጋት ለሁሉም እኩል የሚሠሩ መሆናቸው ነው፡፡ ታዋቂ ብትሆን ባትሆን፣ ኮከብ ብትሆን ባትሆን፤ ውድ ብትሆን ባትሆን፤ የዳኛው ሀገር ሰው ብትሆን ባትሆን ልዩነት የለውም፡፡ እስከ ተጫወትክ ድረስ፡፡ ታድያ ሀገር ስትጫወት እንደ እግር ኳስ ሕግጋት ግልጽ እና ለሁሉም በእኩልነት የሚሠራ ሕግ ያስፈልጋታል፡፡ በእግር ኳስ የቤት እና የእንጀራ ልጅ እንደ ሌለው ሁሉ ሀገር ከድኅነት፣ ከኋላ ቀርነት፣ ከረሃብ፣ ጋር ተጫውታ ዋንጫ ለመውሰድ በምታደርገው ግጥሚያም የቤት እና የእንጀራ ልጅ የማይለይበት ሕግ ያስፈልጋታል የሚሉ የኳስ ባለሞያዎች ሃሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡

አንዱ ያልታደለ ተጫዋች ቀይ ካርድ ያገኘበትን ጥፋት ሌላው እድለኛ ተጫዋች በቢጫ የሚታለፍ ከሆነ፤ አንዱ ምስኪን ባላደረገው ነገር ቢጫ እያየ፤ ተደጋጋሚ ጥፋት የሚያጠፋው ተጫዋች የዳኛ ዓይን እንኳን ሳይገረምመው የሚታለፍ ከሆነ ቡድኑ ይጎዳል፡፡ እንኳን ዋንጫ ማምጣት በስዕለት እንኳን ማጣርያውን አያልፍም የሚሉም አሉ፡፡

እግር ኳስ ሕግ ብቻ ሳይሆን ሕጉን በሜዳ ውስጥ በብቃት የሚተገብሩ ዳኞችም ያስፈልጉታል፡፡ ከተጫዋቾቹ ወገንተኛነት የጸዱ፣ ለኅሊናቸው እና ለሕግ ብቻ ተገዥ የሆኑ፣ ሕጉን በማስፈጸም ብቃት ያላቸው፣ ለሚወስኑት ውሳኔ በቂ ምክንያት እና በራስ መተማመን ያላቸው፤ ይህንን ብወስን እንዲህ እሆናለሁ ብለው የማይፈሩ፣ እውነቱን ፈርደው ከመሸበት የሚያድሩ፣ ብቁ ዳኞችን ያገኘ ጨዋታ ባለሞያ ሴት እንደያዘችው ወጥ አርኪ መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡

መቼም ዳኛ ያጣን ጨዋታ እንደማየት እድሜ አሳጣሪ ነገር የለም፡፡ ስንቱን ድንቅ ጨዋታ ብቃት እና ቆራጥነት የሌላቸው ዳኞች አበላሽተውታል፡፡ አንዱን ቡድን በቀይ ሲያሸበርቁት ሌላኛውን ሞት የሚያስፈርድ ጥፋት እንኳን ቢያጠፋ በፈገግታ የሚያልፉ፤ ለአንዱ ፍጹም ቅጣት ምት ያለ አግባብ ሲሰጡ የአንዱን ቡድን አግባብ ያለው ቅጣት ምት የሚከለክሉ፤ ገንዘብ ተቀብለው ፍርድ የሚያዳሉ፣ ቡድን የሚበድሉ፤ በወገንተኛነት ፍርደ ገምድል ውሳኔ የሚሰጡ ስንት ዓይነት ዳኞችን በእግር ኳስ ታሪክ አይተናል፡፡

አሁን ያ ቲየሪ ኦነሪ በእጁ እያባበለ ያገባትን ግብ ዳኛው ባለማየቱ አየርላንዶች እንዴት ነው አንጀታቸው ያረረው፡፡ የማያይ ዳኛ ችግሩ ይኼ ነው፡፡ አንዳንዱ በእግሩ አግብቶ ያልተቆጠረለትን ሌላው በእጁ አግብቶ ይቆጠርለታል፡፡ በተለይ ሀገር እንደ ቡድን ስትጫወት በእጃቸው የሚያገቡ ተጫዋቾች እንዳይበዙ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ይኼው ሁላችንም ይህችን ታሪካዊት ሀገር «ብልጽግና» በሚባለው የፊፋ የደረጃ ሰንጠረዥ ቢቻል እንደ አሜሪካ እና ቻይና ከመጀመርያዎቹ ተርታ ማሰለፍ፤ ካልቻልን ደግሞ የነብራዚልን እና የነ ሕንድን ያክል መካከለኛው ደረጃ ላይ ማድረስ አለብን ብለን ልምምድ ከጀመርን ቆየት ብለናል፡፡

ታድያ እንዲህ በሚሆንበት ጊዜ ምርጥ፣ ብቁ፣ የሀገር ነገር የሚበላቸው፣ ባንዴራ ለተባለው እና በአንጓዴ ቢጫ እና ቀይ ቀለማት ላሸበረቀው ማልያቸው ፍቅር ያላቸው፤ ለማሸነፍ እልክ የተሞሉ፤ የቴክኒክ እና የታክቲክ ክሂሎት የተላበሱ ተጨዋቾችን መምረጥ ያስፈልጋል፡፡ የተጨዋቾቹ አመራረጥ ብቃት፣ ችሎታ እና ዕውቀትን መሠረት ያደረገ እንጂ በዝምድና፣ በወገንተኛነት እና በጥቅማ ጥቅም እንዳይሆን የእግር ኳስ አምላክ አደራ ብሏል፡፡

በአንዳንድ የእግር ኳስ ቡድኖች እንደሚታየው መመረጥ ያለባቸው ተጨዋቾች ይቀሩና እንኳን ለዓለም ዋንጫ ለሠፈር ግጥሚያ የማይሆኑ ተጨዋቾች ይመረጣሉ፡፡ ደጋፊ፣ ተመልካች፣ ሚዲያ፣ ባለሞያ እሪ ቢልም አሠልጣኞቹ «የመጣው ቢመጣ ምን ጦር ቢደረደር» ብለው በወሰኑት ብቻ ይጸናሉ፡፡ ታድያ በኋላ ውጤት የጠፋ እንደሆነ መከራ ነው፡፡

አገርም ስትጫወት ታድያ እንዲህ ያለውን አሠራር ካላረምን አለቀልን፡፡ ተጨዋቾች መመረጥ ያለባቸው በችሎታቸው ብቻ መሆን አለበት፡፡ የዚህ ወይንም የዚያ ፖለቲካ አባል መሆን እና አለመሆን፤ ይህንን ወይንም ያንን አመለካከት መቀበል እና አለመቀበል፤ ሰሜን ወይንም ደቡብ መወለድ፣ ቅርበት እና ርቀት አይደሉም ወሳኞቹ፡፡ ችሎታ፣ ፍላጎት፣ የሀገር ፍቅር፣ ቁርጠኛነት፣ታማኝነት፣ሥነ ምግባር፣ ለሕግ ተገዥነት፣ እነዚህ ናቸው ዋነኞቹ፡፡ ያለበለዚያ ግን ሀገራችን እንኳንስ የብልጽግናን ዋንጫ ልታመጣ፣ እንኳንስ ማጣርያውን ልታልፍ፣ ከጎረቤት ሀገሮች ተወዳድራ ለሴካፋን ዋንጫ ማጣርያ መቅረቧም ያጠራጥራል፡፡

እግር ኳስ የቡድን ጨዋታ ነው፡፡ አጥቂ፣ ተከላካይ፣ አማካይ፣ ግብ ጠባቂ፣ ሌላውም ሌላውም ተቀናጅቶ ለአንድ ውጤት ሊጫወት ያስፈልጋል፡፡ በርግጥ የኳስን ማርሽ የሚቀይሩ፤ በግላዊ ችሎታቸው ለቡድን ውጤት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱ ተጨዋቾች በየዘመናቱ ይኖራሉ፡፡ እንደነ ፔሌ፣ ማራዶና፣ ጋሪንቻ፣ ቤከን ባወር፣ አቢዲ ፔሌ፣ ሮማርዮ፣ ሮናልዲኒዮ፣ ካካ፣ ሜሲ፤ ኧረ ስንቶቹ፡፡ በሀገር ቡድንምኮ እንዲህ ያሉት ሞልተዋል፡፡ በፖለቲካ፣ በዲፕሎማሲ፣ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በጦር አመራር፣ በግብርና፣ በፍልስፍና፣ በንግድ፣ በስፖርት፣ የታሪክን ማርሽ የሚቀይሩ ምርጥ ተጫዋቾች አሉ፡፡

ታድያ እነዚህ ተጨዋቾች ዓይን ያለው አሠልጣኝ ይፈልጋሉ፡፡ ካሉበት በመብራት ፈልጎ፤ ተደራድሮ፣ አባብሎም ቢሆን፣ ያለ የሌለ ገንዘቡንም ቢሆን ከስክሶ ወደ ቡድኑ የሚያመጣቸው፡፡ ያደላቸውማ የራሳቸውን ብቻ ሳይሆን የሰውንም ሀገር ተጫዋች ለዕውቀቱ እና ችሎታው ሲሉ በገንዘብ ገዝተው ያጫውታሉ፡፡ በሀገር ውስጥ ሲገኝማ ክብር ነው፡፡ ይኼው ብራዚሎች ለፔሌ፣ አርጀንቲናዎች ለማራዶና፣ ጀርመኖች ለቤከን ፓዎር፣ ፈረንሳዮች ለኦነሪ፣ እንግሊዞች ለቤካም፣ ጋናዎች ለአቢዲ ፔሌ፣ አይቮሪኮስቶች ለድሮግባ ያላቸው ፍቅር እና አክብሮት ከመሰማት አልፎ የሚታይ እኮ ነው፡፡

ታድያ እኛም ለእነዚህ በግል ችሎታቸው የታሪክን እና የጨዋታን ማርሽ ለሚቀይሩ ተጫዋቾች ልዩ ክብር ሊኖረን ይገባል፡፡ በእግር ኳስ ቡድናችንም ውስጥ በተገቢው እና በሚገባቸው ቦታ ብናሰልፋቸው ለብልጽግና ዋንጫ የምናደርገውን ጥረት እንዲመነደግ ያደርጉታል፡፡

ምንም እንኳን በግላቸው ተአምር የሚሠሩ ተጫዋቾች ቢኖሩም ብቻቸውን ግን ምንም ሊሠሩ አይችሉም፡፡ እግር ኳስ የቡድን ጨዋታ ነውና፡፡ አገር የብልጽግና ዋንጫ እንድታገኝ የሚደረገው ሰላማዊ ፍልሚያም የቡድን ጨዋታ መሆኑ እሙር ነው፡፡ ይህ የዋንጫ ፍልሚያ ምርጥ አሠልጣኝ ያስፈልጉታል፡፡ እንዲያውም አንዳንድ ሀገሮች ለዓለም ዋንጫ ያሰለፉትን ቡድን በውጭ ሀገር ሰው እስከ ማሠልጠን ይደርሳሉ፡፡ ሰውዬው ከዜግነቱ በላይ ዕውቀቱ ይፈለጋልና፡፡

ሀገርም ድኅነትን እና ኋላ ቀርነትን አሸንፋ የብልጽግና ዋንጫ ማግኘት ትችል ዘንድ ምርጥ አሠልጣኝ ያስፈልጋታል፡፡ ትዕግሥትን ከዕውቀት፣ ልበ ሰፊነትን ከችሎታ፣ አባታዊነትን ከብቃት አዛምዶ ገንዘብ ያደረገ አሠልጣኝ፡፡ ለወገኑ፣ ለሀገሩ ልጅ፣ ለአብሮ አደጉ፣ ያመነውን ለሚያምን፣ በሚሄድበት ለሚሄድ፣ የሚወድደውን ለሚወድ የማያዳላ፡፡ ተጨዋች የመምረጫ መመዘኛው ችሎታ እና ብቃት የሆነ አሠልጣኝ ያገኘች ሀገር ዋንጫ ባትስም እንኳን ማጣርያውን አልፋ ቢያንስ ግማሽ ፍጻሜ መግባቷ አያጠራጥርም፡፡

ደግሞ እሳት የላሱ አጥቂዎችን ማሰለፍ እንዳንረሳ፡፡ ጉልበት ከታክቲክ የያዙ፤ እልክ ከሞራል የተላበሱ አጥቂዎች በመብራት መፈለግ አለባቸው፡፡ ታድያ እነዚህ አጥቂዎች የሥነ ልቡና መረጋጋት እና የልቡና መሰብሰብ ያሻቸዋል፡፡ አታዩትም አንዳንዱን ጎል ሥር ደርሶ መረጋጋት ሲያቅተውና «አሞራው በሰማይ ሲያይሽ ዋለ» እያለ በእግሩ ሲዘፍን፡፡

በተለይም ደግሞ የማጥቃት ብቃት ያላቸው ፖለቲከኞች፣ ሳይንቲስቶች፣ ምሁራን፣ ገበሬዎች፣ ነጋዴዎች፣ ጋዜጠኞች፣ አርቲስቶች፣ ስፖርተኞች፣ የዲፕሎማሲ ባለሞያዎች፣ በቡድኑ ውስጥ መካተታቸውን አሠልጣኞች እና ረዳት አሠልጣኞች ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ እነዚህ ናቸው በድኅነት እና በኋላ ቀርነት ላይ እንደ ዶሮ ወጥ የሚጣፍጡ፣ እንደ ብርንዶ የሚያስጎመጁ ግቦች ማስቆጠር የሚችሉት፡፡

ምን አጥቂ ብቻ፤ ተከላካይ የሌለው የእግር ኳስ ቡድን የጎል ናዳ ነው የሚወርድበት፡፡ ጨዋታውንም እግር ኳስ መሆኑ ቀርቶ ቅርጫት ኳስ ያደርገዋል፡፡ ከተቃራኒ ቡድኖች ከድኅነት፣ ከኋላ ቀርነት፣ ከጭቆና፣ ከአምባገነንነት፣ የሚመቱ አደገኛ አደገኛ ጎሎች እንዳይገቡብን ከተፈለገ እንደ ጣልያን ካቴና ዘግተው የሚይዙ የፖሊስ፣ የፍትሕ፣ የሲቪል ማኅበራት፣ የፋይናንስ ሥርዓት፣ የኦዲት፣ የጤና፣ የመንፈሳዊ ተቋማት፣ የፀረ ሙስና፣ ተከላካዮች በደንብ ሠልጥነው መሰለፍ አለባቸው፡፡

በርግጥ አንዳንድ ጊዜ በመከላከል ላይ የተሠማሩ ተጫዋቾች ግብ እንዳይቆጠር በሚያደርጉት ግብግብ ሕግ እስከ መተላለፍ እና ከቢጫ አልፈው ለቀይ ካርድ እስከመዳረግ ይደርሳሉ፡፡ ብዙ ጊዜም የቢጫ እና የቀይ ካርድ ሰለባዎች የሚሆኑት ተከላካዮች ናቸው፡፡ እናም በሀገር ቡድን ውስጥም ያሉ ተከላካዮች ሕግን ያለ ሕግ እናስከብራለን ብለው፣ ሕግ በመተላለፍ እግር እየሰበሩ፣ ተቃራኒን እየጎተቱ፣ እየገፉና እየጣሉ ለቢጫ እና ቀይ ካርድ እንዳይዳረጉ ሥልጠናው ላይ አሠልጣኞች፤ ጨዋታውም ላይ ዳኞች ትኩረት ሊሰጡ ይገባል፡፡

የአማካዩን ነገርስ እንዴት እንረሳዋለን፡፡ ከበረኛው እየተቀበለ፤ ከተከላካዩ እየወሰደ፤ ለአጥቂው እያቀበለ፤ ግቡ እንዲቆጠር ወሳኙ ተጨዋች አማካዩ እኮ ነው፡፡ እኔ ብቻ ላግባ ሳይል፣ ለአጥቂዎች ምርጥ ምርጥ ዕድሎችን እየፈጠረ፣ ግብ የሚሆን ኳስ እያመቻቸ የሚያቀርበው ያ ጀግና አማካይ ባይኖር የምን የጨዋታ ውበት፣ የምን የዋንጫ ሽልማት፡፡ እግር ኳስስ መች በቴሌቭዥን ይታይ ነበር፡፡

ለሀገርምኮ አማካዩ የውጤቷ መሠረት ነው፡፡ በየመንግሥት መሥሪያ ቤቱ ያሉት አማካይ ተጫዋቾች እኔ ብቻ ላግባ ሳይሉ፣ ለአጥቂ ሳይንቲስቶች፣ ምሁራን፣ ገበሬዎች፣ ባለ ሀብቶች፣ አርቲስቶች፣ አትሌቶች ነጋዴዎች ኳስ የሚያቀብሉ ታታሪ፣ ጥበበኛ፣ የቡድን ሥራን ዋጋ የሚያውቁ አማካዮች እንዲሆኑ ነው ይህ ሁሉ ልፋት፡፡ አማካይ ሲቪል አገልጋዮች ኳሱን በጊዜ ለአጥቂዎቹ ማቀበላቸውን ትተው እዚያው መሐል ሜዳ ላይ በቢሮክራሲ ሲያንከባልሉት ከዋሉ፤ ሰዓቱም ያልቃል፣ውጤቱም ይጠፋል፡፡

ምን ምርጥ ምርጥ አጥቂ ብናሰልፍ የቢሮክራሲው አማካይ ካልተስተካከለ የአጥቂዎቹን አንጀት እየላጠ፣ ተስፋቸውን እያስቆረጠ፣ ሞራላቸውን እየገደለ፤ የሥራ ተነሣሽነ ታቸውን እየከሰከሰ ሀገሪቱን ውጤት አልባ ማድረጉ የታለመም፣ የተፈታም ነው፡፡ ይሄው በየሀገሩ ገንዘቡን፣ዕውቀቱን እና ልቡን ይዞ ለሀገሩ ቡድን ሊሰለፍ የተነሣውን አልሚ ሁሉ ተስፋ አስቆርጠው ከሀገር ያስወጡት እነዚህ መሐል ሜዳ ላይ ኳስ ማንከባለል የሚወድዱ ቢሮክራት አማካዮች አይደሉ እንዴ፡፡ ይድነቃቸው ይሙት፡፡

እንደ አሞራ የሚንሳፈፉ፣ እንደ ካንጋሮ የሚዘሉ፣ እንደ ዓሣ አንበሪ ኳስ የሚቀልቡ በረኞችንም ካሉበት ተፈልገው የቡድን ተሰላፊ መሆን ይገባቸዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፍጹም ቅጣት ምት እና የመለያ ምት የመጣ እንደሆነ ብቻቸውን ነውና የሚጋፈጡት፡፡ ኢትየጵያ እንዲህ በነጻነት ኮርታ እንድትኖር ያደረጓት በምንም መልኩ ግባቸውን የማያስደፍሩ ቆራጥ እና ጀግና አርበኛ በረኞች ስለነበሯት ነው፡፡

ዛሬም ታድያ ለአጥቂውም፣ ለተከላካዩም ለአማካዩም የማያዳሉ፤ ገለልተኛ ሆነው ግባቸውን የሚጠብቁ በረኞች ከሌሉን የዋንጫውን ነገር እንርሳው፡፡ የመከላከያ ሠራዊታችን ይኼው በየድንበሩ ዘብ ቆሞ በሀገሪቱ ላይ አደገኛ ቡድኖች ግብ እንዳያስቆጥሩ እየጠበቀ አይደል እንዴ፡፡

መቼም ሀገራቸው አሠልጥና፣ ስንት እና ስንት ገንዘብ አፍስሳ፣ ውለታዬን ይከፍላሉ ብላ በእግር ኳስ ቡድን ውስጥ ስታሰልፋቸው ከተቃራኒ ቡድን ገንዘብ እየተቀበሉ ውጤት አሳልፈው የሚሰጡ ተጫዋቾች መኖራቸውን ሰምታችኋል፡፡ እነዚህ ማልያው የሀገራቸው፣ ልባቸው የገንዘባቸው የሆኑ ተጫዋቾች በሁለት መንገድ ቡድናቸውን ጎድተውታል፡፡ በአንድ በኩል የቡድኑን የቴክኒክ እና የታክቲክ፣ ብሎም የአሰላለፍ ምሥጢር ለተቃራኒ ቡድን በማሾለክ፤ በሌላ በኩል ደግሞ በሀገራቸው ቡድን ውስጥ ተሰልፈው ለተቃራኒው ቡድን በመጫወት ሀገር ይጎዳሉ፡፡ የሀገሬ ሰው «ባንዶች» የሚላቸው እነዚህን ነው፡፡

ጠላትማ ምንጊዜም ጠላት ነው
አስቀድሞ መምታት ባንዳ ባንዳውን ነው

ተብሎ የተዘፈነው ስለነእርሱ መሆኑን መቼም የኳስ ደጋፊዎች አትረሱትም፡፡

ደግሞም ሌላም የሚሰማ ነገር አለ፡፡ አንዳንድ የአፍሪካ እና የላቲን አሜሪካ ተጨዋቾች ለተሸጡበት ቡድን የሚጫወቱትን ያህል ለሀገራቸው ቡድን አይጫወቱም እየተባሉ ይታማሉ፡፡ ምክንያቱስ? ሲባል እግራቸውን አጥተው እድሜያቸውን ላለማሳጠር ነው እያሉ የሚተነትኑ ባለሞያዎች አሉ፡፡ በሀገራችን ቡድን ውስጥስ ይኖሩ ይሆን እንዴ፡፡ ከሀገራቸው ወጥተው በባዕድ ሀገር ደም ተፍተው፣ ዕውቀት ሠውተው፣ ጊዜ ከስክሰው እያገለገሉ፤ በየሚሠሩበት ሀገር ባለ ሀብት፣ ሳይንቲስት፣ ምሁር፣ ባለሞያ ሆነው እየሠሩ ለሀገራቸው ተሰልፈው መጫወት ግን የማይፈልጉ ይኖሩ ይሆን እንዴ፡፡

ርግጥ ነው አንድ የሰማሁት ነገር አለ፡፡ አንዳንድ ጥበበኛ እና በሳል ተጫዋቾች፣ አሠልጣኞች በሀገራቸው ክለብ እና ቡድን አላሰልፋቸው ሲሉ ሳይወዱ በግድ ለባዕድ ሀገር ይጫወታሉ ይባላል፡፡ በእነዚህ ላይ ለመፍረድ ይከብዳል፡፡ ታድያ ኢትዮጵያ ከድኅነት፣ ኋላ ቀርነት፣ ኢ ፍትሐዊነት፣ አምባገነንነት ጋር ለምታደርጋቸው ግጥሚያዎች መሰለፍ ሲችሉ የሚያሰልፋቸው ያጡ፤ በዚህም ምክንያት ሀገራቸውን ጥለው ለባዕድ ሀገር ሳይወዱ የተሰለፉ ተጫዋቾች ካሉ አሠልጣኞች እንደገና ጉዳዩን ማየት ሳያስፈልጋቸው አይቀርም፡፡

አንዳንድ ተጫዋቾች ደግሞ ለቡድን ተመርጦ ነገር ግን ዘወትር «ቤንች» ላይ መቀመጥ ይሰለቻል ብለውኛል፡፡ እውነታቸውን ነው፡፡ አልተመረጥንም እንዳይሉ ተመርጠው፤ ነገር ግን አንዳንዶች እንደ መስቀል ወፍ አልፎ አልፎ ብቻ ሲጫወቱ፣ አንዳንዶች ደግሞ ከናካቴው አንድም ቀን ኳስ ነክተው የማያውቁ ተጠባባቂዎች አሉ፡፡ አሁን እነዚህ የሚያጫውተን አጣን ብለው ለሌላ ቡድን ቢሰለፉ ይታዘንላቸዋል እንጂ ይታዘንባቸዋል?

ሞት ይርሳኝና የተመልካቹን ነገር ረሳሁት፡፡ መቼም ጨዋ እና የተማረ ተመልካች ማግኘት ምርጥ አጥቂ የማግኘት ያህል ነው ይባላል፡፡ ሙሉ ጨዋታ እያበረታታ፣ ተስፋ ሳይቆርጥ እየደገፈ፡፡ ውጤት ሲጠፋም ለቀጣዩ ግጥሚያ እየተዘጋጀ፤ ውጤት ሲገኝም እየረካ፤ በገንዘቡ እና በዕውቀቱ እየተሳተፈ፤ በሞራል እና በጭብጨባ መንፈስ የሚያድስን ተመልካች ያህል ጸጋ የት ይገኛል? ሲሠሩ እያመሰገነ፣ ሲያጠፉ በምክንያት እየተቸ፤ ጎበዞችን እየሸለመ፣ ያለ ብቃታቸው የተሠለፉትን እያረመ የሚጓዝ ተመልካች ለማግኘት ለየትኛው ታቦት እንሳል ይሆን፡፡

የኢትዮጵያ ቡድን የብልጽግናን ዋንጫ እንዲያመጣ ከተፈለገ እንዲህ ያለ ተመልካች ያስፈልጋል፡፡ የሚያማ፣ የሚሳደብ፣ የሚወራወር፣ ወገን ለይቶ የሚደባደብ፤ ወይንም ጨርሶ «እኔ የለሁበትም» ብሎ እጁን አጣጥፎ የሚቀመጥ ተመልካች ሳይሆን የሚያበ ረታታ፣ የሚሸልም፣ ለምርጥ ተጫዋቾች ዕውቅና የሚሰጥ፣ ሀገሩ የብልጽግና ዋንጫ እንድታመጣ የሚደረገውን ግጥሚያ በገንዘቡም፣ በዕውቀቱም ባለው ሁሉ ነገር የሚደግፍ ተመልካች ከሌለ ዮፍታሔ ንጉሤ «ነገራችን ሁሉ የእንቧይ ካብ፣ የእንቧይ ካብ» እንዳሉት ይሆናል፡፡

አንድ የመጨረሻ ነገር እናንሣ፤ ጨዋታው ሊጀመር ስለሆነ፤ የቡድኖቹ ብሔራዊ መዝሙር እየተዘመረ ነው፡፡ በዘመናዊው እግር ኳስ የሚዲያው ሚና ወሳኝ መሆኑን መቼም ታውቃላችሁ፡፡ ገለልተኛ የሆነ፣ በዕውቀት ላይ የተመሠረተ፤ ክፉ እና ደጉን ሊያሳይ የሚችል፤ ከስሜታዊነት የጸዳ ሚዲያ ያስፈልገናል፡፡ የሆነውን ነገር በርግጡ የሚነግረን ሚዲያ፡፡ እየተጠቃ ያለውን ቡድን እያጠቃ ነው፣ እያሸነፈ ያለውን ቡድን ጎል እየገባበት ነው፤ ጥፋት እየሠራ ያለውን ተጫዋች እንከን የለበትም፤ ጥፋት የተሠራበትን ቡድን ጥፋተኛ ነው እያለ ጨዋታ የሚያበላሽ ሚዲያ ካለ እግር ኳስ ምኑን እግር ኳስ ይሆናል፡፡

አሁን ጨዋታው ተጀምሯል፡፡ የኢትየጵያ ቡድን ወደፊት መታ፤ ለጥቂት፣ ለጥቂት፣ አያያያያ፡፡53 comments:

 1. Betam Dink tsihuf new! Joro Yalew yisma. Gin meche new be'akal dimtsihin yeminisemaw?

  ReplyDelete
 2. Gudegna nehi Dani!!!.Berta!

  ReplyDelete
 3. hmariamm123@yahoo.comJune 15, 2010 at 12:15 AM

  Interesting . However, Dany when do you play "Ethiopian football" so that......
  By the way, the Ethiopian football team should be retired because many of the players have already played about 20 years and currently they want to play additional 5 years. Especially the team leader who is characterized to play and score the goal alone shoud be replaced by youngsters. The coach is almost unable to walk by himself.....hahahahhah
  I wish successful team to Ethiopia

  ReplyDelete
 4. Konjo tinitane new Dani.
  Participatory Developmental analysis yilutal frenjoch.

  ReplyDelete
 5. ወይ ዳንኤል፤
  መቼስ ምን ይባላል...ምን አለበት አምላክ ለሁላችንም እንዲህ ዓይነት እይታን ብገለጽልን...እስቲ የተፃፈውንም ይግልጥልን። የኢትዮጵያ አምላክ ይጠብቅህ፤ በርታ።

  እኔዉ ከለንደን

  ReplyDelete
 6. dani thats great

  ReplyDelete
 7. Girum tibeb new! kale-egziabeherun beketita tekebilen metegber biyakiten amlakachin simetachin beteshenefebet bemigeban neger (kuankua) zarem eyastemaren new (lik medhane-alem bezihech medir simelales endastemarew). Be-agerawiw ye-alem wancha chewata, beminim tesfa sanikort beteselefnibet bota derejawin yetebeke chwata lemechawet enitir zend ye-kidusan amlak yirdan!

  ReplyDelete
 8. it was good ...but we need our poleticians ear

  ReplyDelete
 9. ዳንኤል እግዚአብሔር ይባርክህ፡፡

  እኛም እኮ በተሰማራንበት ሙያ ሁሉ በቅንነት እና በታማኝነት ብናገለግል ኖሮ የት በደረስን፡፡ እግዚአብሔር ለህዝቡ አንድነትንና ፍቅርን ይስጥ፡፡

  አመሰግናለሁ፡፡

  ReplyDelete
 10. Dn. Daniel, Tiru hasab new.Lehageru Yemikorekor weyim hagerawi fikir ena raiy yalew tiwilid yasifeligal. Yane lebiltsiginaw wancha astemamagn buddin yinorenal. E/r yirdan.
  kemisgana gaar,

  ReplyDelete
 11. እንዲ በቀላሉ ጫወታ ይጀመራል እንዴ? ከላይ ያልካቸው ነገሮች እስቲስተካከሉ ራሱ...ሁሁሁሁ ባዶ ተስፋ እንዳይሆን አሰጋለው፡፡እኔ በግሌ ዋንጫ ኖረም አልኖረም መጫወቴን አላቆምም ምክንያቱም ሥራዬ ነው። ለማጣሪያውም ራሱ...ይሁና

  ReplyDelete
 12. marvelous that is what i can say. if we have a man of wisdom at this time u r the one & as far as i'm concerned the only

  ReplyDelete
 13. አምደ ሚካኤልJune 15, 2010 at 11:22 AM

  ገና አሁን ነው የንስሩ ትርጉም የገባኝ
  አርቆ ማየት ማለት ይህ አይደል?
  የተለመደው ጠሎቴ ዕድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን
  አንዳንዶች ዕድሜ ምን ያደርጋል ማቱሳላ ይሄን
  ያህል ዘመን ሲኖር ምንም አልሰራም ይላሉ
  ታዲያ አንዱ ህጋዊ ሰባኪ ምን አለ
  ቢያንስ ምንም አልሰራም ከምንል
  ምን ያህል እናቱና አባቱ ቢያከብር ነው ዕድሜው የረዘመው ብሎ ማሰብ ሲቻል አሉ

  ReplyDelete
 14. YEMIGERM VISION LEKA CHEAWATAW LEMEJEMER BIZU NEGER MESTEKAKEL ALEBET INEKO YE ASELTAGNU [YE MERIW] TACTIC BICHA YIMESLEGN NEBER.
  ANTEN YESETEN AMLAK YETEMESEGEBE YHUN

  ReplyDelete
 15. It is good observation. But it needs national conses/agreement. God bless us.
  I thank u my dear bro., dani
  Yam

  ReplyDelete
 16. MAY THE ALMIGHTY GOD KEEP YOU FROM EVIL EYES!

  ReplyDelete
 17. ዳኞች እና አሰለጣኞች አባካችሁ ለተጫዋቾቹ እና ለተመልካቹ ፍትሀዊ እድል እንስጥ! ስራችንን በብቃት እንወጣ!
  ዲ/ን ዳኒ አምላክ ይጠብቅህ! ጥሩ ጎል አግቢ ሆነሀል! ዘላቂነት የሚኖረው ግን ሁሉም ተጫዋች በአግባቡ መሳተፍ ሲችል ነው፡፡

  ReplyDelete
 18. wow great thought and view!!

  let God look after you!

  ReplyDelete
 19. +++
  Dani Edme Yestilign.

  ReplyDelete
 20. +++
  Dani Berta Entebekehalen Ahunem.

  ReplyDelete
 21. እግዚአብሔር ልብን ይስጠን!

  ReplyDelete
 22. thanks dani,
  i don't words to express

  ReplyDelete
 23. Dear Dn Daniel:
  Wow! It is a great article, again. May God give you all the strength to keep on doing the good work. What more can I say ?
  God bless,

  Ankiro from USA

  ReplyDelete
 24. Let us prayer to be hereo

  ReplyDelete
 25. በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

  ወቅታዊ አስተምህሮ ነው በጣም እናመሰግናለን ምን ዋጋ አለው ሰሚ የለ በጣም የምናሳዝን ህዝቦች እኮ ነን የሁሉ ነገር ጀማሪዎች ነን ነገር ግን የሁሉ መጨረሻ ነን ለምን ይሆን? ,,,,አምላክ ሆይ እባክህ አንተ በቃ በለን ,,,,

  ReplyDelete
 26. gezahegn
  wow it great idae. the one who can hear it makes all things perfect.

  ReplyDelete
 27. ዳኒ በጣም የሚገርም ጹሁፍ ነው ምኑን ከምን እንዳገናኘኸው? የጻፍከው ነገር 2 አይን ከሚያየው ነገር በልጧል፡፡ ለነገሩ አሁን ያለው የኢትዩጵያ ችግር እኔ ሲመስለኝ ሁሉም ዳኛ መሆን ነው የሚፈልገው ማለት ተጫዋች፣ ተመልካች ወይም አራጋቢ መሆን አይፈልገም ለዚህ ይመስለኛ የማንደማመጠው እ/ር መደማመጡን ይሰጠን እናመሰግናለን፡፡

  ማኪ
  አ.አ

  ReplyDelete
 28. ዳኒ ተባረክ!!!

  ReplyDelete
 29. Dear Dn.Daniel
  V.Goooooooooooooood job keep up the good work
  My God bless you and our tewhedo church.

  Thank you
  from Alexnadria VA USA

  ReplyDelete
 30. Dear Dn Daniel:

  I have no word to express the lesson I get form this article. Thank you very much. I believe that it wouldn't be to long to see the prosperious Ethiopia if every body understand this and interprate it in works. Let our creature God save and blease Ethiopia.

  ReplyDelete
 31. ምነው በሩጫ አንደኛ ስንሆን
  እንዲህ መሆናችን ቢሉ
  በግር ኳስ እኵ የቡድን ስለሆነ በህብረት መስራት አንችልም
  የየብቻ ስንሮጥማ አንደኛ ነን ዳኒ
  ክእኔ

  ReplyDelete
 32. ዳኒ እምላክ ይባርክህ...ጥሩ ትንታኔ ነው:: እንብቤ ስጨርስ ..የጨዋታው ነጋሪ ..የጋዜጠኞቹ ድርሳ ታወስኝና እንዴት ስለነሱ ምንም እላልም እልኩ...ለካ እንተው እራስህ የነሱ ወኪል ነሀ...በሃገር ጨዋታም.. የጨዋታውን ሂድት ሳያጋንን..ሳያብርድ እንዳል.. ለ እድማጩ በሚገባና በሚሰብ መልኩ የሚያስደምጡ ..ታምኝ ወሬ ነጋሪዎችም የሚያስፍልጎት እይምስልህም ዳኒ...ትንታኔሀ በታም ተምችቶኛል...ጸጋው ይብዛልህ...

  ReplyDelete
 33. tnx daniel...........1 tnx lemalet 27 dekika zim alhu. Hulachin beteselefinibet hulu tiru techewachoch enihun......"YES WE CAN"

  ReplyDelete
 34. Nice article. Keep providing us such a great vision. Amlak kante gar yihun.

  ReplyDelete
 35. What a phenomenal discourse!!!

  That is absolutely inspiring to me.

  Please continue exercising great caution to not mess with politics as it can ruin your spiritual service.

  May God help you endure to the end.

  ReplyDelete
 36. መልካም ብለሃል ዲ/ን ዳንኤል
  እንዲያው:የተመልካቹን:ነገር:ለማጠቃለያ:አመጣኅው:እንጂ:ዋናዉ:የጐደለን:ይኅው:
  ነበር::ተመሳሳይ:ማልያ:ለብሰን:እኩል:ማጨበጨቡ:እና:ባንድ:ዜማ:ሞራል:መስጠቱ:ይቅር:እና:እንዲያው:በቅጡ:ሰላምታ:መለዋወጡ:የት:አለና?
  ለብሔራዊ:ቡድን:ማሰቡ:እና መሰባሰቡ:ቀርቶ:ሁሉም:ለትናንሸ:ክለባት:ሁሌም:
  ሙጥኝ:ማለቱ:ከክለብ:ጨዋታ:ያለፈ:እርምጃ:አያስኬድም::ጠባብነትን:ተላብሰን:እንደ:ሌሎቹ:ሃገራት:መሆንን:መመኘቱ:ቀቢጸ:ተስፋነት:ይሆናል::

  መዋደዱ:ይቅደም!!!

  ReplyDelete
 37. +++
  ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥልኝ::

  ተጫዋቾቹ በለሉበት ዳኞች ብቻ ወይም ተጫዋቾቹ በለሉበት አሰለጣኞች ብቻ ወይም ሜዳ በለለበት ተመልካቾች እንሁን ስለምንል ይመስለኛል :: እስቲ ቆም ብለን እናስብ:: ድርሻችን አዉቀን ድርሻችን እንወጣ::

  በርታ

  ከዝዋይ

  ReplyDelete
 38. It is great idea and expression that shows every one is responsible what was doing and what is going on?

  Keep it
  tinikishu
  Israel

  ReplyDelete
 39. Egziabher yestelen Deacon Daniel!!!Amazing!!!

  ReplyDelete
 40. Much has been said. Hope the day Ethiopians play for Ethiopia will come soon. Great job!!!

  ReplyDelete
 41. Dani

  it is very interesting and good. Could u p/s publish it on any public newspaper most people can read it.

  ReplyDelete
 42. Dani:
  Now, I got my old friend with modern idea.

  God bless you.

  ReplyDelete
 43. አንት ይምታንብ ስው ለእውቀት ነው ወይስ በሌላ መድረክ ይህንኑ ቃል ለምናግር ነው የምታነበው፡ ወይስ እግዚአብሔርን ራሴን ለውጬ ሌሎችንም ለመለወጥ እውነተኛ ሰው አድርገኝ እያልክ ነው የምታነበው....እስቲ ለወንድማችን እረዳት እንድንሆን ለመለወጥ እንሞክር። ወንድሜ ዳናኤል አንተስ በርተተሃል ያበረታህም ማን እንደሆነ ተረድቼለውኝ በርታ.....

  ReplyDelete
 44. ውድ ወንድማችን ዲ/ ዳንኤል ቸሩ እግዚአብሔር እንዲሁ ደግ ደጉን አትረፍርፎ ይስጥህ:: የጦማሩን መኖር ካወቅኩ ገና 24 ሰዓት አልሞላውም:: የቱን አንብቤ የቱን እንደምተው ግራ ስለገባኝ ከኮምፒውተሩ ጋር ከተፋጠጥን ሰዓታት ተቆጠሩ:: ለበጎ ነውና አልጠላሁትም:: ወቅታዊ ብቻ ሳይሆን ድንቅ መማማርያ ጽሑፍ ነው:: አንድ በኩሌ የሚሰማ ቢገኝ አይደለም!ይለኝና ሌላው ደግሞ የሰማው ሰምቶ ከዚያ መካከል ደግሞ መተግበር የሚችል ከመቶ 2 እንኳን ቢገኝ ጽሑፉ አላማውን መቷል ማለት ይቻላል ይለኛልና በርታልን::
  ደመ መራራ - ከስዊዘርላንድ

  ReplyDelete
 45. I dont want to thank you.But not go to pristage but it itself comes to you!

  ReplyDelete
 46. ዲ/ን ዳንኤል እግዚአብሔር
  ይባርክህ !!!!!!!!!
  ይጠብቅህም !!!!!!!!!
  በምትጽፋቸው ጽሑፎች አጅግ መልካምና አስተማሪዎች ናቸው
  በዚሁ ቀጥል በርታ ደግሞ ለብዙዎች መማሪያና ምሳሌ መሆን
  በመቻልህ ደስ ሊልህ ይገባል!!!!!
  ወንድሜ አንዲት ነገር ላስቸግርህ?????
  • በዘመናችን ስላሉ መዝሙሮች?
  • በአጠቃላይ በሰ/ት/ቤቶች ስለሚዘመሩ መዝሙሮች?
  • ይበልጡን ስለ አማርኛ መዝሙሮች? ያለውን ጠቅላላ ሃሳብና
  • ስለ ያሬዳዊ ዜማ?
  • በተጨማሪም የአማርኛ መዝሙሮች ከያሬዳዊው የዜማ ስልት
  ጋር ያለህን የመረጃ ምንጭ ተጠቅመህ
  የምክር እና የዕውቀት ድጋፍህን ብትለግሰን ፡፡

  ReplyDelete
 47. እግዚኣብሄር ይባርክህ! ጥሩ እይታ ነዉ(ዘግይቼ ባነበዉም)::
  እንዳልከዉ ሁሉም የጨዋታዉ አካል የሆኑት ሚናቸዉ በይናቅም
  የአሰልጣኙ ሚና ላቅ ያለ ነዉ ባይ ነኝ:: ጎበዝ አሰልጣኝ ጎበዝ አጥቂ መፍጠር የችላል
  (ቴሪ ኦነሪን ለዚህ ደረጃ ያበቁት አርሰን ቬንገር ናቸዉ)፡፡ አስተዋይ አሰልጣኝ ምርጥ ተጨዋቾችን
  መፈለግ ይችላል፤ በአነስተኛ ገንዘብ ታላቅ ቡድን ይገነባል፡፡ ለብዙ ዘመናት በኦልትራፎርድ
  የቆዩት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን በአለም 75ሚሊዮን በላይ የክለቡ ደጋፊዎች ዛሬም ድረስ ይወደዳሉ፡፡
  ምንም ጎበዝ ዳኛ፤ ልዩ ክህሎት ያላቸዉ ተከላካዮች፡ አማካኝ፡ አጥቂ ቢኖሩም ያለ ጥሩ አሰልጣኝ ሲሳካ አልታየም ፡፡አሰልጣኝ(Boss)!

  ReplyDelete
 48. በግል ችሎታቸው ከሚደነቁት ተጫዋቾች ውስጥ፣ አንተ አንዱ መሰልከኝ!
  እግዚአብሄር ብርታቱን ይስጥህ።

  ReplyDelete