Friday, June 11, 2010

ዝምታ ወርቅ አይደለም

ሰውዬው ከሚስቱ ሌላ አንዲት ሴት ወደደና እፍ ክንፍ አለ፡፡ ልጁን እና ሚስቱን እየተወ ከዚህችኛይቱ ጋር ማምሸት፣ ብሎም ማደር ጀመረ፡፡ በመጨረሻም አንድ ቀን ወደ ሚስቱ መጣና ድንገተኛ የሆነ ጥያቄ አቀረበ፡፡ «እኔ እና አንቺ እንድንፋታ እፈልጋለሁ፤ ለምን ብለሽ ምክንያቱን አትጠይቂኝ፡፡ መፋታት ብቻ እፈልጋለሁ፡፡ ደግሞም ሌላ ቀን አይደለም፣ ነገ እንዲሆን እፈልጋለሁ» አላት፡፡ ሚስቱ በሁለት ነገሮች ተጨነቀች፡፡ በአንድ በኩል ምንም ነገር አትጠይቂኝ ብሏታል፡፡ በሁለተኛ ነገር ልጇ ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ፈተና ልትቀመጥ ጥቂት ቀናት ቀርቷታል፡፡

«ባልፈልገውም፣ ባልስማማበትም፤ ካልክ የግድ እቀበለዋለሁ፡፡ ነገር ግን በኛ ምክንያት ልጃችን መጎዳት የለባትምና የአንድ ወር ጊዜ ያህል እንታገሥ፡፡» አለችው፡፡ እርሱም አሰበና «ጥሩ አንድ ወር መታገሥ አያቅተኝም፤ ነገር ግን በዚህ አንድ ወር ውስጥ ሽማግሌ መላክ፣ ምክንያቱን መጠየቅ የለም፤ ስለ ፍቺው ማናችንም ምንም ነገር ማንሣት የለብንም፤ በዚህ ቃል ግቢ» አላት፡፡ እርሷም «እስማማለሁ፤ ግን አንተም የምነግርህን ለመፈጸም ከተስማማህ ነው፤ ታድያ በዚህ አንድ ወር ጠዋት ጠዋት ከዕንቅልፌ ስነሣ፣ ማታ ማታም ወደ አልጋዬ ስሄድ ያኔ የሠርጋችን ዕለት አቅፈህ እንደ ወሰድከኝ አድርገህ አቅፈህ ትወስደኛለህ» ስትል ጠየቀችው፡፡ ነገሩ ያልጠበቀው እና ያልተለመደ ዓይነት ቢሆንበትም፣ ቀላል እና ሊያደርገው የሚችል ስለሆነ እሽ ብሎ ቃል ገባላት፡፡

አንዱ ወር ተጀመረ፡፡

ጠዋት ጠዋት ከዕንቅልፏ ስትነሣ አቅፎ፣ ከፍ አድርጎ፣ ወደ በረንዳ ካደረሳት በኋላ ወደ ሥራው ይሄዳል፡፡ ማታ ማታም እንዲሁ አቅፎ ወደ አልጋዋ ይወስዳታል፡፡ ስለ ፍችው አይነጋገሩም፡፡ እየዋለ እያደረ ሲሄድ የሰውነቷ ጠረን፣ የምትለብሳቸው ልብሶቿ፣ የዓይኖቿ እና የፀጉሯ ሁኔታ፣ የገላዋ ልስላሴ እና የአካሏ ቅርጽ እየሳቡት መጡ፡፡ በየቀኑ እያቀፈ ሲያወጣት እና ሲያስገባት ሰውነቷ እየቀለለው፤ ለርሱም እርሷን አቅፎ መሸከሙ አንዳች እንግዳ የሆነ የደስታ ስሜት እየፈጠረለት መጣ፡፡

ከራሱም ጋር ሙግት ጀመረ፡፡ «ለምንድን ነው እንፋታ ያልኳት፤ አሁን የሚሰማኝን ስሜት ያህል ስሜት ከአዲሷ ወዳጄ ጋር ለምን አይሰማኝም? ለምንስ ነበር ይህንን ነገር እንዳደርገው ቃል ያስገባችኝ ? ይህን የመሰለውን ገላዋን፣ እንዲህ የሚማርከውን ጠረንዋን፣ እንዲህ የሚያስደስተውን ፈገግታዋን፣ እንዲህ የተዘናፈለውን ፀጉሯን፣ እንዲህ ልዩ የሆነውን አካሏን እንዴት እስከ ዛሬ አላስተዋልኩትም ?እርሷ ናት ከኔ ጋር የነበረችው ወይስ እኔም ከርሷ ጋር ነበርኩ?»

የወሩ መጨረሻ እየደረሰ መሆኑን ሲያውቅ ከእርሷ መለየቱ ጨነቀው፡፡ እንዲያውም ይህ ሁኔታ የፈጠረበትን እንግዳ ስሜት እየወደደው መጣ፡፡ ነግቶ እና መሽቶ እርሷን አቅፏት እስከሚወስዳት በጉጉት መጠበቅ ጀመረ፡፡ በሌላም በኩል ደግሞ በዚህ ድርጊቷ በውስጡ ያሳደረችበትን ስሜት እያሰበ ያደንቃትም ጀመር፡፡ ብልህነቷን፣ አስተዋይነቷን እና በቀላል ድርጊት ቀልቡን ልትገዛው መቻሏን ሲያስበው «ምን ዓይነት አስገራሚ ሴት ናት?» ይላል፡፡

ወሩ ሊያልቅ ሁለት ቀን ሲቀረው የመፋታቱን ሃሳብ በውስጡ መረመረው፡፡ ነገር ግን አላገኘውም፡፡ በዚህ ሁኔታ መፋታቱ ደግሞ ለሕይወቱ የማይፈታ ዕንቆቅልሽ እንደሚሆንበት እያሰበ ተጨነቀ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ አንድ ወር ውስጥ ፍችን በተመለከተ ላለመነጋገር ቃል ተግባብተዋልና እንዴት አድርጎ ይናገር፡፡ ዛሬም በደስታ ስሜት አቅፎ ከአልጋዋ እንደወሰዳት ሁሉ ማታ ወደ አልጋዋ መለሳት፤ ከበፊቱ እጅግ በጣም ቀለለችው፤ አሳዘነችውም፡፡

በወሩ መጨረሻ፡፡

ወደ አዲሲቱ ወዳጁ ዘንድ ሄደና «የፍችውን ሃሳብ ሠርዤዋለሁ፡፡ እኔና ባለቤቴ ፍቅር የሌለን መስሎኝ ነበር፡፡ እኛ ግን ለካስ ፍቅር አላጣንም፡፡ ያጣነው ሁለት ነገሮች ብቻ ነው፡፡ መነጋገር እና መቀራረብ፡፡ ለዚህ ያደረሰንም አለ መቀራረባችን እና አለመነጋገራችን ብቻ ነው፡፡ አሁን ግን መነጋገር ባንችል እንኳን መቀራረብ ግን ችለናል፡፡ ዛሬ ደግሞ መነጋገር እንችላለን፡፡ ስለዚህ ሌላ የሚሆንሽን ፈልጊ» አላት፡፡

ሴትዮዋ ተናደደችና በጥፊ መታችው፤ ከአጠገቧ የነበረውንም ውኃ ቸለሰችበት፤ «ይሄ ለብዙው ኃጢአቴ የተከፈለ ቅጣት ነው» እያለ ወጥቶ ሄደ፡፡ ከዚያም ወደ አበባ መሸጫ ሱቅ ውስጥ ገባ፡፡ ያኔ ሲጋቡ የገዛላትን ዓይነት አበባ ገዝቶ ወደ ቤቱ ከነፈ፡፡ «ጓደኛዬ ትዳር ማለት አግብተው የሚኖሩት ሳይሆን በየጊዜው የሚጋቡት ነው ያለው እውነቱን ነው፡፡ ትዳር እንደ አሥራ ሁለተኛ ክፍል ፈተና አንድ ጊዜ አልፈውት ሰርተፊኬቱን የሚሰቅሉት አይደለም ያለው እውነቱን ነው፡፡ ትዳር እና ተክል ክብካቤ ይፈልጋሉ፡፡ እንዲሁ ቢያድጉ ይደጉ ተብለው የሚተው ነገሮች አይደሉም፡፡

«ልክ እዚህ ሀገር ችግኝ የመኮትኮት፣ የማጠጣት፣ የመከባከብ እና የማሳደግ እንጂ የመትከል ችግር እንደሌለብን ሁሉ፤ እኛም ጋር የመጋባት ችግር የለም፡፡ ፍቅር ግን ማግባትን ብቻ ሳይሆን ማጠጣትን፣ መኮትኮትን፣ ማረምን፣ ከብት እንዳያበላሸው አጥር ማጠርን፣ በየጊዜው ማዳበርያ መጨመርን ጭምር ይፈልጋል፡፡ በርግጥ በዕድሉ የሚበቅል ዛፍ እንዳለው ሁሉ በእድሉ የሚኖር ትዳርም ይኖር ይሆናል፡፡ ይህ ግን ሕይወትን ለራስ ጥረት ሳይሆን ለአጋጣሚዎች ብቻ አሳልፎ መስጠት ነው» ያለው እውነቱን ነው፡፡ እኔ አልሰማሁትም እንጂ እርሱስ ተናግሮ ነበር፡፡»

መኪናውን አቆመና ወደ ግቢው ውስጥ ገባ፡፡ በረንዳ ላይ ትጠብቀው የነበረችው ባለቤቱ የለችም፡፡ በሩንም አንኳኳ፡፡ የሚከፍት ግን አልነበረም፡፡ ደግሞ ሲያንኳኳ ገርበብ ብሎ የተዘጋው በር በራሱ ጊዜ ተከፈተ፡፡ ባለቤቱ ግን በዚህች በወሩ ሠላሳኛ ቀን ሳሎንም የለችም፡፡ እየተገረመም፣ ግራ እየተጋባም ወደ መኝታ ቤቱ ዘለቀ፡፡ አልጋው ላይ ፈገግ እንዳለች ጋደም ብላለች፡፡ አበባውን እንደያዘ ጠጋ አለና በእጁ ጉንጯን ነካው፡፡ ቀዝቅዟል፡፡ በቁልምጫ ጠራት፡፡ መልስ ግን አልነበረም፡፡ ግራ ተጋብቶ ዓይንዋን ገለጥ አደረ ገው፡፡ ሊገለጥለት ግን አልቻለም፤ በርከክ አለና ሰውነቷን ደባበሰው፤ ቀዝቅዟል፡፡

«የመጨረሻው ቀን ነው፤ ይህችን ቀን ማየት አልፈልግም፤ ለልጄ ስል እስከዛሬ ታግሻለሁ፤ በቃኝ» የሚል ጽሑፍ ራስጌዋ ላይ አገኘ፡፡

እርሷ ፍችውን አትፈልገውም፤ ስለዚህም ሳትፋታ ሞተች፡፡ በርሱ ውስጥ የነበረውን የሃሳብ ለውጥ አላወቀችም፤ ምክንያቱም ላይነጋገሩ ቃል ተግባብተው ነበርና፡፡ እርሷ የዛሬዋን ቀን በስጋት እና በጭንቀት ነበር የጠበቀቻት፡፡ የመለያያቸው ቀን፤ የሕይወቷን ግማሽ የምታጣበት ቀን፡፡ የማትፈልገውን ነገር የምታደ ርግበት ቀን ናትና፡፡ እርሱ ግን የዛሬዋን ቀን በጉጉት ነበር የጠበቃት፡፡ የሚነጋገሩባት ቀን፤ ፍችውን እንደተወው የሚነግርባት ቀን፤ ፍቅሩን የሚነግርባት ቀን፤ ይቅርታ የሚጠይቅባት ቀን፤ ለፍቅሩ ሲል ትን ሽም ብትሆን ቅጣት ከፍሎ የመጣባት ቀን፤ በእርሱ እና በባለቤቱ መካከል የመነጋገር እና የመቀራረብ እንጂ፣ የመዋደድ እና ስሜት ለስሜት የመስማማት ችግር እንደሌለ መረዳቱን የሚገልጥባት ቀን ናትና፡፡ ግን ምን ያደርጋል፤ ሁለቱም ይህንን በየልባቸው ያውቁታል እንጂ አልተነጋገሩም፤ ሃሳባቸውንም በሌላ መንገድ አልተለዋወጡም፡፡ በዚህ የተነሣም በችግሩ መፍቻ ቀን ዋናው ቸግር ተፈጠረ፡፡

ሁለት የትዳር ነቀርሳዎች፡- አለመቀራረብ እና አለመነጋገር፡፡ አብረው አንድ አልጋ ላይ እያደሩ፤ አብረው እየበሉ፤ አብረው እየኖሩ የማይቀራረቡ ባል እና ሚስት አሉ፡፡ አንድ አልጋ ላይ የሚተኙት አንድ አልጋ ላይ መተኛት ስላለባቸው ብቻ ነው፡ ከመጋባታቸው በፊት የነበራቸው ጉጉት እና ናፍቆት አሁን የለም፡፡ ሳይተኙ እንቅልፍ ይወስዳቸዋል፡፡ አብረው ይበላሉ፤ በአንድ ማዕድ መሆኑ፣ አንድ ጠረጲዛ ላይ መሆኑ እንጂ ያኔ በፊት ለምሳ ሲገባበዙ የነበረው ናፍቆት እና ጉጉት የላቸውም፡፡ ዝም ብሎ መብላት ብቻ፡፡

እያንዳንዷን ቀን ልዩ፣ ደስታ የሚፈጠርባት እና ከትናንት የተለየች ለማድረግ አይጥሩም፡፡ ዛሬም እንደ ትናንቱ፣ ነገም እንደ ዛሬ ነው፡፡

በስንት ልመና በስንት ጥየቃ፣
በስንት ደጅ ጥናት በስንት ጥበቃ፣
እንግዲህ ምን ቀረሽ አገባሁሽ በቃ፣

እንደተባለው ይሆንባቸዋል፡፡ አገባኋት በቃ፤ አገባሁት በቃ፤ ከንግዲህ ምን ቀረ? ብለው ያስባሉ፡፡ ሰው ተፈጥሮ አላለቀም፡፡ በየጊዜው ነው የሚፈጠረው፡፡ ፈጣሪም ሰውን እንደ ተወለደ እንዲያልቅ አላደረገውም፡፡ በየቀኑ፣ በየሰዓቱ፣ በየደቂቃው ላስተዋለው ሰው እንግዳ ፍጥረት ነው፤ አዳዲስ ነገር ይታይበታል፡፡ ይህ ግን መቀራረብን ይጠይቃል፡፡ ባል እና ሚስት ከተቀራረቡ ሳይፋቱ በየቀኑ ይጋባሉ፤ ጋብቻቸው እየታደሰ ይሄዳል፡፡ የትና ንቷ ሚስት ከዛሬዋ ትለያለች፤ የዛሬው ባልም ከትናንቱ የተለየ ነው፡፡ ለውጥ፣ ዕድገት፣ ብስለት፣ አለ፡፡ መልክም ተለውጧል፡፡ ግን ቀርቦ የሚያየው ያስፈልገዋል፡፡

የዚያ ባል ችግሩ ሚስቱን አግብቷት እንጂ ቀርቧት አያውቅም ነበር፡፡ አብሯት ይኖራል እንጂ ከርሷ ጋር አይኖርም ነበር፤ ምድር በፀሐይ ዙርያ ስለምትዞር ይመሻል ይነጋል እንጂ በእነርሱ የተለየ የሕይወት ጉዞ ምክንያት አይመሽም አይነጋም፡፡ በማክሰኞ እና በረቡዕ መካከል ከስሙ በቀር በሕይወታቸው ውስጥ ልዩነት የለውም፡፡

ሌላው ችግር ደግሞ ያለ መነጋገር ነው፡፡ መነጋገር ማለት በሚያውቁት ቋንቋ ማውራት ማለት አይደለም፡፡ እርሱንማ ከብትም ሲገናኝ እምቧ እምቧ ይባባላል፡፡ ይህ ግን መነጋገር አይደለም፡፡ በየጊዜው፣ በየሰዓቱ፣ ሁለመናን መለዋወጥ ማለት ነው፡፡ ካልተነጋገሩበት የምሥራች፣ የተነጋገሩበት መርዶ ይሻላል፡፡ ካልተነጋ ገሩበት ፍቅር የተነጋገሩበት ጠብ ይበልጣል፡፡ ካልተነጋገሩበት ስጦታ የተነጋገሩበት ንጥቂያ ይሻላል፡፡

ባል እና ሚስቱ ባለመነጋገራቸው ችግሩን በሁለት አቅጣጫ ፈቱት፡፡ የሁለቱም ፍላጎት ችግሩን ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ መፍታት ነበር፡፡ የሁለቱም ፍላጎት ፍቺ የሚባለውን ነገር ላለማየት ነበር፡፡ የሁለቱም ፍላጎት ሠላሳኛዋን ቀን መገላገል ነበር፡፡ ነገር ግን ባለ መነጋገር ምክንያት በሁለት አቅጣጫ ሆነ፡፡ እርሷ ሞትን መረጠች፤ እርሱ ደግሞ ይቅርታን መረጠ፡፡ ችግሩ የመጣው በዚህ ጉዳይ ላለመነጋገር ሲወስኑ ነው፡፡ እርሷ በጉዳዩ ትጨነቃለች፤ ለምን ይሆን ከኔ መለየት የፈለገው? የሚለው ጥያቄ ያሳስባት ነበር፡፡ በሃሳብ ብዛትም እየከሳች ሄዳ ነበር፡፡ ለዚህም ነበር በየቀኑ ሲያቅፋት ትቀልለው የነበረው፡፡ እርሱ ግን መቅለሏን እንኳን ለመጠየቅ ፈራ፡፡ እርሱ ከራሱ ጋር እንጂ ከእርሷ ጋር አይነጋገርም ነበር፡፡

እናም አንዳንድ ጊዜ አስፈላጊ ቢሆንም እንኳ፤ በትዳር ውስጥ ግን ዝምታ ወርቅ አይደለም፡፡89 comments:

 1. Thank you God,since I`m the 1st person to comment!
  "ትዳር እንደ አሥራ ሁለተኛ ክፍል ፈተና አንድ ጊዜ አልፈውት ሰርተፊኬቱን የሚሰቅሉት አይደለም"

  Dani! ejjochih yibbareku.Le-egnam 'LIBB' yisten!!!

  ReplyDelete
 2. ዳኒ እባክህ ሰለ ትዳር ብዙ ጣፍ
  በመጵሀፍ የሚታተሙ መቸ ይሆን

  ReplyDelete
 3. thank you !i love your article ,they teach ,shape ,point the weak side and motivate me ! please keep it up!
  Endris Ali

  ReplyDelete
 4. አምደ ሚካኤልJune 11, 2010 at 9:48 AM

  ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል ተብሎ ተናጋሪ የሆኑ
  ዝም አይነቅዝም ሲባል ዝምተኛ የሆኑ ብዙዎች አሉ
  ዝምታ ጥሩ የሚሆነው በአግባቡ ሲሆን ነው

  በጣም ጥሩ አስተማሪ ጽሁፍ ነው።ግን ምን ያደረጋል ብዙ ኢትዮጵያውያን የሚያነቡት አይመስለኝም።እኛ ጽሁፉን የማምበብ አቅም/internet access/ ያለን ሰዎች ሌሎች አንዲያነቡ ብናደርግ መልካም ይመስለኛል። እኔ በበኩሌ ቢያንስ አራት ሰዎች በቋሚነት /print / አድርጌ ኮፒዩተር ላላችው soft copy እየሰጣለሁ አስነብባለሁ

  እናንተስ?

  ReplyDelete
 5. oh my god this is most ethiopian life.when i finish reading i cry as if that was my case b/c the finish line is very disappointing anyways i realy couldn,t explain well what my filling is .at all it is a heart breaking history.p/s do not repeat the above life history

  ReplyDelete
 6. amlak tiru tedare yesetne

  ReplyDelete
 7. Excellent!!!

  Egziabher Yisth Dn. Daniel. Lik liken Negerkegn.

  ReplyDelete
 8. It is a hot issue and really appreciate your view.

  ReplyDelete
 9. Oh Daniel , I don't have enough words how to express my feelings. You are very right. Its a problem that each and everyone of us are facing. Kale Hiwot Yasemalin.

  ReplyDelete
 10. ዳኒ እግዚአብሔር ይስጥልን። እንደው ልማድ ሆነብን እና ከመነጋገር ይልቅ ማኩረፍ መፍትሔ አድርገን እንወስዳለን። እንደው ዳኒ አንዴ ደግሞ በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያን ትዳር ምን ይመስላል የሚለውን እና የመፍትሔ ሃሳቦችን ብትጽፍልን መልካም ነው። ወንዶች በተለይ ከ ክፍለ ሃገር የመጡ ወንድሞች አሜሪካ እና አውሮፓ እየኖሩ ሚስቶቻቸው ላይ ጫና ይፈጥራሉ። ሃላፊነት አይጋሩም። ይህ ደግሞ በኋላ ሚስትየዋ ተማራ ወደፍቺ እንድትሄድ መንገድ ይከፍታል። በተለይ ከሰሜኑ የሃገራችን ክፍል። ከአዲስ አበባ እና አካባቢው የሚመጡ ደግሞ በተወሰነ መልኩ ሚስቶቻቸውን ያግዛሉ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ለትዳራቸው ታማኞች አይሆኑም። ይህንን አስተያየት ስሰጥ በአውሮፓም በአሜሪካም ተዘዋውሬ ካየሁት በመነሳት ነው። ይህንን ስል ግን ሚስቶቹ ፍጹማን ናቸው የሚል አቋም እንደሌለኝ የታወቅልኝ አመዛኙን ለማለት ፈልጌ ነው።

  እግዚአብሔር ይጠብቅህ

  ReplyDelete
 11. Deakon Endet keremik, Enanete Yealem Chew nachu Yetebalew endih endeante aynetun sira endinesera silhone Berta. Tsegawin Yabizalih.
  Wetatochunim and belachew. Ene sugardady aschegrewal ena.

  ReplyDelete
 12. Excellent Message; God bless you Deacon Daniel;

  ReplyDelete
 13. +++

  ጥሩ ሁኖ ሳለ ምስኪኗን ሳትገላት መጨረስ ትችል ነበር::

  በርታ ሌላም እንጠብቃለን እንደ .......
  ገብሬ
  ከዝዋይ

  ReplyDelete
 14. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
  ዳኒ በጣም ጥሩና አስተማሪ የሆነ ጽሁፍ ነዉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ በተለይ በሁለት ባለትዳሮች መካከል የሚታየዉ ችግር ይኸዉ ነዉ፡፡ላይላይዩን ይነጋገራሉ በአፋቸዉ ይፋቀራሉ በልባቸዉግን ሁለቱም የሁለት ሃገር ሰዎች ናቸዉ፡፡ በነብዩ ኢሣያስ አድሮ ሲናገር እግዚአብሔር እንዲህ ነበር ያለዉ"ይህ ህዝብ በአፉ ያመልከኛል በልቡ ግን ከእኔርቋል" በማለተ ህዝበእስራኤልን ሲወቅስ እናያለን፡፡የአሁኑ ትዉልድ ደግሞ ልክ "ብል ህልጅ እየበላ ይስቃል" እንደሚባለዉ አባባል ወንዱ ከጎኑ ይዞ ከማዶ ይመለከታል ሴቷም እንዲሁ አብሯት ያለዉን ወንድ አስቀምጣ ሌላዉን ወንድ ትመለከታለች፡፡ ብቻ እርሱ እግዚአብሔር ወደልቦናችን ሁላችንም ይመልሰን ፡፡
  ዳንኤል እግዚአብሔር ፀጋዉን ያብዛልህ
  በጣም መካሪና አስተማሪ ቁምነገሮችን ታስነብበናለህና ቀጥልብት፡፡

  ReplyDelete
 15. እግዚአብሔር ስራህን ይባርክ

  ReplyDelete
 16. ዳኒ እይታህ በጣም ይገርማል፡፡ በሚቀጥለው ደግሞ የምታየው ምን ይሆን???????? ለነገሩ መነጋገር በማንኛውም ግንኙነት ውስጥ በጣም አስፈላጊ ነው በተለይ ወላጀች ልጀቻቸው በግልጽን ስለእያንዳንዱ ነገር እንዲነጋገሩ አድርጎ በማሳደግ ወደ ፊት በትዳር ላይ በግልጽ የመነጋገር ችግር እንዳይፈጠር ይረዳል ብዬ አስባለው፡፡ እ/ር ይባርክህ

  ዳኒ ካላስቸገርኩ አንድ ጥያቄ እንድትመልስልኝ በእ/ር ስም እጠይቅሀለሁ፡፡ ይኸውም ምንድነው አንድ ሰው የሆነ ነገር አድርጐ ሲያስደስተኝ ምስጋናዬን የምገልጽበት ቃል እ/ር ይባርክህ በማለት ነው፡፡ አንድ ቀን እንዲህ ስል የሰማች አንድ መንገደኛ (ማለት አላውቃትም) ማንኛውም ሰው እ/ር ይባርክህ አይልም እንዲህ የሚሉት ካህናት ብቻ ናቸው እና እንዲህ እንዳትዬ አለችኝ፡፡ እኔ ግን መተው አልቻልኩም በጣም ስደሰት የምጠቀበት ቃል ነው እውነት ይህን ቃል ማለት የለብኝም ወይ እባክህ አርመኝ፡፡ ለጥያቄዬ መልስ እንደምትሰጠኝ ተስፋ አደርጋለሁ አንተን ለመጠየቅ የተነሳሁበት ምክንያት የምትጽፈው ነገር በጣም ደስ ስለሚለኝ እ/ር ይባርክህ ስለምልን ምናልባት ማለት የሌለብኝ ቃል እየተጠቀምኩ እንዳይሆን፡፡ ይመስለኛል ብሎጐ ከስህተት ማሪያ ነው፡፡

  ማኪ
  አአ

  ReplyDelete
 17. Dn. Daniel
  You knock so many doors. This is the great and basic issue which be distributed to all Ethiopians and others also. You know u told to my sister which is on the way to divorce. And your role is very great to change their decision for divorce I think after now they will meet again.
  God Bless you and Your family.

  ReplyDelete
 18. hi Dn. Daniel k. words fail to express my filling. keep it up.
  may God blessings be with you.

  ReplyDelete
 19. wey gud alu kemenager dejazemacchenet yekeral alu min dejazemachinet tedarem yekeral enji.seweren new enji min yebalal

  ReplyDelete
 20. ግሩም አገላለጥ:: አንድ መልስ እንድትሰጠኝ የምፈልገው ነገር ቢኖር ግን ሰውየው ከባለቤቱ የቀረበለትን መልካም የሆነ የአንድ ወር የእቀፈኝ መስፈርት ሳይስማማበት ቢቀር የሚፈጠረው ነገር ምን ይሆን:: በእኔ ህይወት እንደዚህ ዓይነት ነገር በየጊዜው እየገጠመኝ ሰላሜን ስለነሳኝ ነው ይህን ለማንሳት የተገደድኩት:: አመሰግናለሁ::

  ReplyDelete
 21. ይህን አስተያየት ለሰጠች/ው ሰው ማለት የምፈልገው ነገር አለ: "...እንደው ልማድ ሆነብን እና ከመነጋገር ይልቅ ማኩረፍ መፍትሔ አድርገን እንወስዳለን። እንደው ዳኒ አንዴ ደግሞ በውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያን ትዳር ምን ይመስላል የሚለውን እና የመፍትሔ ሃሳቦችን ብትጽፍልን መልካም ነው። ወንዶች በተለይ ከክፍለ ሃገር የመጡ ወንድሞች አሜሪካ እና አውሮፓ እየኖሩ ሚስቶቻቸው ላይ ጫና ይፈጥራሉ። ሃላፊነት አይጋሩም።..."
  እኔ ወንድ ነኝ: የምሆረው በአሜሪካን ሀገር ሲሆን የመጣውትም ከክፍለ ሃገር ነው:: መቸም ሚስት ካገባሁ በኋላ ባለቤቴን ሰርተሽ አብይኝ ብየ አላውቅም እንዴያውም የተቸገርኩት የአስተያየት ሰጭዋ ግልባጭ በኔ ደርሶ ነው:: ሁለት ስራ እሰራለሁ 72 ሰዓት: እማራለሁ: የቤታችን ግማሽ ስራ እሰራለሁ: ባለቤቴም እንዲሁ ትማራለች: በሳምንት 15 ሰዓት ትሰራለች:የቤታችን ግማሽ ስራ ትሰራለች:: ዘመዶቻችንም በምንረዳበት ጊዜ እኩል እናደርጋለን:: ባለቤቴን ይህን አወጣሽ: ይህን አደረግሽ ብየ አልናገራትም:: የሚገርመው ግን ስለምታደርገው ነገር አመሰግናለሁ: በርታ: ደከምክ:የቤቱን ስራ እኔ ልስራው ምክንያቱም አንተ ሁለት ስራ እየሰራህ ነው: ችግሮች ያልፋሉ ነገ የተሻለ ህይወት እንኖራለን ብላኝ እንኳ አታውቅም:: ዳንኤል እንደተናገረው ለማነጋገር ዘወትር እሞክራለሁ ነገር ግን ሲብስ እንጅ ሲሻል አላየሁም:: የቀረኝ ቢኖር እንደሰትዮዋ እራሴን ማጥፋት ነው:: ስልዚህ ጾታዊ ሀሳቦችን ስናነሳ ከአድልወ ነጻ በሆነ መልኩ መሆን አለበት ካልሆነ ግን የምንፈጥረው ትውልድ እንደ እኔ አይነት ትዳር ያለው/ደግሞ ተቃራኒውን ይሆናል ማለት ነው::

  ReplyDelete
 22. geltsenet betedare lay men yahel endemiyasefeleg yaseredal.
  dani kant bezu entebekalen

  ReplyDelete
 23. Dani kale hiwot yasemalin.
  tigist ena tsinatun eskemechereshaw yasadiribin.

  ReplyDelete
 24. It is really amazing!
  Fitsameachinin yasamirilin.

  ReplyDelete
 25. Thank God! God made me see my wickedness (through ur message) before I and my life perish !

  ReplyDelete
 26. thanks Dany, May God Bless you

  ReplyDelete
 27. You came with awesome topic.thanks.I had an answer at the right time for my owen questins. God bless you.

  ReplyDelete
 28. እግዚአብሔር በምህረቱ ይጠብቅህ አረጅም እድሜ ከረጅም አገልግሎተ ጋር ያድልህ። ዳኒ እኔም እንዳ አንዷ እህቴ እንደው በዚህ በባህር ማዶ ለሚኖሩ ወንድሞቻችን ምን ምከር ትመከርረናለህ። በተለይ የባል ዘመድ ሲመጣ እንደ አውሬ የሚያረጋቸው እሀቶች እነዲሁም ደግሞቸ የሚስት ዘመድ ሲመጣ ሰውነቱ የሚለዋወጠውን በሎች ምን ትመክረናለህ፣ አሁንም እግዚአብሐር አምላክ በአገልግሎትሀ ያጽናህ
  መልካሙን እመኛለሁ

  ReplyDelete
 29. Kale Hiwoten Yasemlen Dakon Daneil

  Betam Teru Temhert New Zeme Malet Agrnem Haymnotnem Eyatfaben New Tedaren Becha Sayhoen EGZIABHER Beblte Tsgawen Yabzale Bedme Betsgea Yetbklen Amen!

  ReplyDelete
 30. As always, very good,full of wisdom article.
  May God give you all the strength and wisdom to keep doing the good work.

  God bless,

  Ankiro USA

  ReplyDelete
 31. touchin,touchin,,,am so touched!!!!bicha anten yakoyilin!!!

  ReplyDelete
 32. Dear Dn. Daniel, thank you very much! it is a very nice message for all kinds of people including those who are preparing to be united in marrage. Tekerarbo menegageru lemetewaewku meseret new, bedenb kaltewaweku demo abro menor yikebdal mikniyatum dekama ena tenkara gonachinin eris be-eris meredat silemanichil, yemanakewin dekama gon bayen kutir hulem chigir wust eniwedkalen.

  tekerariben tenegagren tewawiken fitsum wuhidet yinoren zend amlak yirdan!

  ReplyDelete
 33. እግዚአብሔር ቃለ ሕይወትን ያሰማህ
  ትምህርት በልባችን ውስጥ ፍሬ እንዲያፈራ ይርዳህ
  በጣም ጥሩ መልክትና የሚያስለቅስም ጭምር ነው፡፡
  እኔ ግን ሁሌ አንድ ነገር ይገርመኛል ትዳር እያላቸው ወደ ሌላ ሴት (ወንድ) የሚሔዱ ጓዋደኛ(እጮኛ) እያላቸው ወደ ሌላ ሴት (ወንድ) የሚሔዱትን ለምንድነው የምንቀበላቸው ያቺን ትቶ/ታ ወደ እኛ እንደመጣ እኛንም ትቶ/ታ ወደ ሌላ እንደምትሄድ /እንደሚሄድ/ ብናስብ ምን አለበት፡፡ ደግሞ ዛሬ የሚወለዱት ልጆች ራሳቸው በእንደዚህ አይነት አስቀያሚ ህይወት ውስጥ ስለሚያልፉ አባታቸው ወይም እናታቸው የሰሩትን ታሪክ ይደግሙታል፡፡ ታዲያ መች ነው ወደ ተቀደሰው ትውልድ የምንደርሰው፡፡ ዲያቆን እባክህ በእጮኝነት ጊዜ የእጮኛውን ዕድሜ 7 ዓመት ተጫውቶበት 1 ዓመት ጊዜ ውስጥ ሌላ ስለሚያገቡ ወንዶችም አንድ በለን በእንደዚህ ዓይነት ህይወት ብዙዎች ከሞተው በላይ ካለው በታች እየኖሩ ነውና፡፡
  ልቡና ይስጠን

  ReplyDelete
 34. Dn. Dan, Egziabher yebelete tibebun geltsolih bizu enditastemiren yihun. Kale hiwot yasemalin, Amen!!!

  ReplyDelete
 35. እግዜአብሔር ይስጥልን ዲ.ዳንኤል አስተማሪ መልህክት ነው የቤተሰብ የአስተዳደግ ችግር እራሱ በግልጽ እንዳትነጋገር ተጽህኖ አለው

  ReplyDelete
 36. God, I was so concentrated and very hast to know what would happen at the end of the month and my guess was, his wife knows that she has made his( her husband) mind changed and he will ask an apology but she will not accept as he was supposed to be punished for what he did. but her death makes me fell terribly bad and some times the unexpected could happen so nobody needs this to happen and it is really a fantastic lesson.

  ReplyDelete
 37. Dn. Daniel i have no words to thank you, May the Almighty God bless your work. Amen

  ReplyDelete
 38. Kalehiwot yasemalein dn. Dan. Egziabher tibebun geltsilih kezihim belay enditastemirem yihun. anbabiwechim besira tergumen yante lifat wutet endiagen yadrgen. Regim edmie yistlin, amen!!!

  ReplyDelete
 39. እግዜአብሔር ይስጥልን ዲ.ዳንኤል አስተማሪ መልህክት ነው::እግዚአብሔር በምህረቱ ይጠብቅህ አረጅም እድሜ ከረጅም አገልግሎተ ጋር ያድልህ።

  ReplyDelete
 40. Dn. Dani Egiziabher ye agelegelot zemenehen yibarekew. betam timeheret seche meleheket new degemom yemeyaselekes.

  ReplyDelete
 41. Dn Daneil, I disappointed and cried, why you kill the wife? ooooooooooooooooo so sad
  Any way thanks

  ReplyDelete
 42. አንተ ግን አስትምር ገስጽም ጎስምም……በርታ ሁላችንም ያነበብን በማካፈል ትውልዳችንን እንጠብቅ እናድን
  ቃለ ህይወት ያስማልን።

  ReplyDelete
 43. I always enjoy reading comments on your blog but, I have never seen these kind of mixed responses before. You highlighted a very sensitive issue and hope you got more ideas from the ever mixed reactions. The story was touching and teaching! Thank you very much!

  ReplyDelete
 44. አባግንባር (ከሮማ)June 14, 2010 at 10:49 AM

  ለዲን. ዳንኤል፡
  አርዕስቱን ሳይ ምነው ዳንኤልም መፈላሰፍ ጀመረ እንዴ የአባቶቻችንን ብሂል የሚቃወመው አልኩኝ፡፡ ሙሉውን ሳነበው ግን ጥሩ መልዕክት እንዳለው ተረዳሁኝ፡፡ ትርጉም ያድናል የሚባለው ይህ ነው አልኩኝ እና እግዚአብሔር ይስጥህ፡፡

  ለአንባቢያን
  ዳንኤልም ይጽፋል እኛም እናነባለን እናነባለንም (እንባ) እንማርበታለን ራሳችንንም ከውስጡ እናነባለን፡፡ አንዳንድ ጠያቂዎች ያነሱት ሃሳብ ላይ አስተያየት ለመስጠት አሰብኩኝ፡፡ ከጽሑፉ የምንረዳው ተጨማሪ ነገር ከንግግሩም በላይ ተግባርም እንደሚያስፈልግ ነው፡፡ እኔ የትዳር ሕወት ውስጥ አይደለሁም የለሁት ነገር ግን የብዙ ባለትዳሮችን ህይወት የማዳመጥ ሁኔታዎች አጋጥመውኛል፡፡ የብዙ ሰው ችግር የአልሸነፍም ባይነት ስሜት ይመስለኛል፡፡ በክርስትና ውስጥም ሁልጊዜ መረሳት የሌለበት ነገር ቢኖር ከዝሙት በስተቀር ማንም መፋታት እንደማይችል ማስታወስ ይጠቅማል፡፡

  በውጪ ሃገር ያሉት ባለትዳሮች ያነሱት አንዳንድ ጥያቄ አለ፡፡ እኔ የሚታየኝ ትዳርና ገንዘብን ለይቶ ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው እላለሁ፡፡ አብዛኛውን ሰው ሳይ የግጭት መንስኤ የሚሆንባቸው አገር ቤት ያለን ቤተሰብ የመርዳት እና ያለመርዳት ጉዳይ ነው፡፡ እንዴ! እናንተ ከኖራችሁ እኮ ነው ያ ሁሉ ሊደረግ የሚችለው፡፡ እናንተ ሰላም ካጣችሁ ያንን እንረዳለን የምትሉአቸውን ዘመዶቻችሁን ሰላም እንደምትነሱ ከዛም በሻገር በሰው ልጅ እርዳታ እንኳን ሊቀረፍ የማይችል ችግር እንደምትፈጥሩባቸው ማስታወስ ያለባችሁ ይመስለኛል "እየየም ሲደላ ነው" ይባል የሌ፡፡ ከምንም በላይ የናንተ ሰላም መሆን ለወገኖቻቸሁ ትልቅ እርዳታ መሆኑን መዘንጋት የለባችሁም፡፡
  መጨረሻችንን ያሳምረው፡:
  አባግንባር

  ReplyDelete
 45. Deacon Now you start the best issue.We need to hear about the responsibility of the husband as the head of the house as christ deed.And the work of wife as the church.

  In your histroy I have a comment.On that critical date ,since his heart & attiude is changed, a work of God should be there. And also I belive he wouldn't leave the person with such a sorrow & the wife for sin.
  Besides the two issues you bring I think absence of understanding of marriage as well lack of knowlege on the prechears is the core problem.
  I think our church have a marvelos thought on the issue .

  God bless you & our country

  ReplyDelete
 46. what to say eheheheh--

  ReplyDelete
 47. i really suffer so much to get wife then God hear my prayer and gave me a wife u know that i mean a wife a real wife i guess so many people don't know the differece b/n being a women and being a wife being a man and being a husband what i suggest to everyone is to go to our church and get the lessen of marriege wich is the Holly mattermony one of the 7 sacrment of the church it is so helpfull but bear in mind that both partners need to do this not only one of the two.don't get married just n/c u fill like it.don't get married just b/c ur friend got married.don't get married just b/c ur familly wants u to do so. don't get married just b/c u fill u going to lose ur lover if u don't do so and some ather reasens that i did't state in here please please get married when u fully understand all about marriege most immportantlly when u know God's purpuse on marriege. lastly please remember thos in bad marriege when u stand for ur daylly prayer may God give us BEGO HILINA AND NITSUH LIBUNA. LIBE NITSUHA FITER LITE EGZIO. GOD BLESS D DANIEL AND ALL OUR PEOPLE

  ReplyDelete
 48. <greetings!!, new commer here,...I've seen some of your posts today!!,..really nice and educational!!, but if I may say here is my problem. Most of them are really long, and at times I feel like taking a break in the middle of the sentence!! So will it be possible to present your insights in fewer paragraphs than this? will it be ok to make them mre than one idea or as part1, 2,....and the like?
  Blessings!!

  ReplyDelete
 49. IGZI'ABHER YIBARKH KE MALET WICHI MIN YIBALAL.
  LE IGNA WETATOCHIM TIDARN YEMINFERAW YEZIHN AYNET CHIGR MEFTIHE IYETEFAN NEW KE PSCATRIST YILIK YE IGZI'ABHER SEWOCH GA BINHED BIZU MEFTIHE INDALE IGZI'ABHER BE DANI IYASAYEN NEW.
  YE IGZI'ABHER FIKADU YIHUNINA 1 KEN YALEHUBET AKABABI KEMETAH INEM DIBLIKLIK YALEWN HIWETE BAGARAH MENGED INDEMITASAYEGN AMINALEW FETRAI YACHIN KEN YAMTAT.
  AMLAKACHIN MECHERESHAHIN YASAMRLIH
  KE AYIN YAWTAH

  ReplyDelete
 50. Thank you....Please more and more.....
  wendwosen

  ReplyDelete
 51. joro yalew yesma!!!!!!!!!!!!!!!!


  thanx dani

  ReplyDelete
 52. ዳኒ እኔም ባልከው ነገር እስማማለሁ ግን ያላደግንበትን በውይይት የመፍታት ወይም የተሰማህን ደፍሮ የመናር ልምድ ከየት እናምጣ? አስተዳደጋችን ለዚ ችግር ትልቅ እስተዋጽኣ አለው እላለሁ አብዛኛውን ግዜ አባት ወይንም ባል ያለውን ነገር ከመቀበል ውጭ አይደለም ለመቃወም ለምን ብሎ ለመጠየቅ ድፍረት በሌለበት ቤተሰብ ያደገ ሰው እንዴት ነው ሁሉንም ነገር በንግግር መፍታት የሚችለው? ስለዚ እንዱ ለምን መባል አይፈልግም ሌላኛው ይሄንን ለመስበር ድፍረት ያጣል መጨረሻው እንዳነበብነው ይሆናል::

  ReplyDelete
 53. This is one of the astonishing stories I have read. Thanks a lot Daniel. You have raised the rock-bottom issue of marriage.

  May the grace of our Lord be with you in every aspect of your spiritual services.

  ReplyDelete
 54. In the Name of Father ,son and Holy sprite !!!Amen

  What a golden words you have !!! Alignment to God.
  May God bless the one who initiate me to read this script (T.A)

  ReplyDelete
 55. Thanks to God for giving us you to see ourselves. It is such a wonderful article. I hope many of us would once again look into ourselves(Our marriage).
  Joro yalew semtuwal!!
  Egiziabher eyitahin yasefaleh.Amen!!

  ReplyDelete
 56. Dn. Daniel bizuwin gize betimhirtoch neber yemawikih eziyam laye yemitesetachew meslewoch be amroye tekertsew kertewal.

  Yihe tarik betam newe yazazenegn be eneba newe yechereskut. Abet tidar minigna kebad neger new??????/

  Egziabher yabertah.

  ReplyDelete
 57. Kalehiwot Yasemalin! Egziabhair Tsegahin Yitebikilih!!!

  Ameha Giyorgis & Fikrte Mariam
  DC

  ReplyDelete
 58. thank u.egziabiher ageligilotihin yibarkleh.tiru timihirt agignchalehu.keep it up!!!

  ReplyDelete
 59. selam daniel your article was very interesting but you may say that i am expected a lot but we need a book from you conserning merraige becouse it is a great problem for our socity now a deys becouse most of us are "Woretgna" by the way can mahibere kidusan organize merrage councelelers?we expect if they can becouse your article is so nice but it is "Abayin Bechilfa"
  Nurilin

  ReplyDelete
 60. ewnetm yeniser ayn mechem yematayew neger yelem tinbim bihon

  ReplyDelete
 61. እግዚአብሔር ይስጥልን በጣም አስተማሪነው!!! በዚው ቀጥልበት

  ReplyDelete
 62. kaleywt yasmalen Dear Da, i am very intersting by this massage,i have a marrage so a good massage for me,i wish god save ur life

  ReplyDelete
 63. crucial issue that we all have to alleviate for getting a better and enjoyable life!!!
  keep it up

  ReplyDelete
 64. Good interpretation, nice job, I like the work but there should be siltation to it http://map4lostsouls.blogspot.com/2010/08/reuben-mathew-kurian-marriage-to-those.html.

  ReplyDelete
 65. Dani I want to appriciate your talent given by God,2nd please pray for ETH.ORTHODOX CHURCH please?///?/////////////

  Zelalem K.

  ReplyDelete
 66. You are so clever Di.Daniel. God bless you!

  ReplyDelete
 67. betam mekari new 10q anyway

  ReplyDelete
 68. you are so .....the mirte by GOOD..

  ReplyDelete
 69. It was so touching story as well as educational.
  Please let us share different real stories(both good and bad) and get lesson on different issues.And if we have questions if we can forward it and our fathers give us their comments.Like if we have a daily incident sharing media.

  God bless all who participated.I learn from all.

  ReplyDelete
 70. ካልተነጋገሩበት የምሥራች፣ የተነጋገሩበት መርዶ ይሻላል፡፡ ካልተነጋ ገሩበት ፍቅር የተነጋገሩበት ጠብ ይበልጣል፡፡ ካልተነጋገሩበት ስጦታ የተነጋገሩበት ንጥቂያ ይሻላል፡

  ReplyDelete
 71. grum new Dani!!!!!!!!!! Lela min elalehu. Egziher yistlign,

  ReplyDelete
 72. Thanks Dn.Daniel .Ewnet ena astemari message new. Ye sew lij kaltenegagere ena kalteweyaye minun sew hone?

  ReplyDelete
 73. Hello dear Daniel How are you;
  I think this is the right time to wake-up, You have to be vigilant about devils tricks.Don't let him play on you; he is making you stubborn.
  Remember GOD told you to be humble.We know that you have contribute a lot; but this is GOD's not yours.
  Knowledge with out humbleness is dangerous;it makes you think you are the best.
  Dear brother We want you continue you with your devotion & humbleness despite the challenges.
  May GOD be with you

  ReplyDelete
 74. Dicon Daniel kalehiwot yasemalin. it is very intersting and it will teach most of ours

  ReplyDelete
 75. Very interesting article. Keep it up. It teaches us a lot.

  ReplyDelete
 76. Just because some people are in a position of silence than discussion, how many of them put their life(marriage) & children in danger? How many of those who are close minded follow their foot steps? How many of their children prefer to go to street and become homeless? How many people become afraid of marriage after hearing such bad news? I think, the best remedial action against this is teaching.

  ReplyDelete
 77. betam des yemil meker azel temehrt new berta

  ReplyDelete
 78. በህይወቴ የማላውቀውን ትምህርት አሁን ተማርኩ አምላክ የተመሰገነ ይሁን፡፡

  ReplyDelete
 79. በህይወቴ የማላውቀውን ትምህርት አሁን ተማርኩ አምላክ የተመሰገነ ይሁን፡፡

  ReplyDelete
 80. this fantastic and good

  ReplyDelete
 81. Dn.Dany we always love you so much please keep it up.we are waiting your Next book.
  God Bless you!!!!!
  From Bahir DAr

  ReplyDelete
 82. Dear Dn.Daniel i always read your blog and i put a comment on it but you didn't approved(visible) one of them for the past 2 years does anything wrong with me???????????

  ReplyDelete
 83. ዳኒ ሰላም ላንተ ይሁን::
  እናቴ በዚህ ዘመን " ሰይጣን ጔዙን ጠቅልሎ የሰፈረው በትዳርና በቤተ ክርስትያን ውስጥ ነው" ትላለች:: በዚህ ምክንያት እኔም የአንተን ጽሑፍ ሳነበው በቅድሜያ አማትቤየ ነው:: ለምን ከተባልኩ?የዚህ አርእስት ሲነሳ መስቀል ያየ ሠይጣን ይመስል ከአገር ውስጥ እስከ ባህር ማዶ ያለነው ወገንህ ጸወታ ሳይለይ በሙሉ እንደምናለቃቅስብህ ስለታየኝ ነው::
  ብዙ ተብሎአል : ሆኖም እንደኔ ዓመለካከት ለዘንድሮ ትዳር ማደፍረሻው ሆነ ማፍረሻው ነው ብየ የማምነው መተማመን መጉደል ነው::ለዚህም የዳኔ የጽሑፍ ምክር አይጠቅምም ማለቴ ሳይሆን :ትልቁ ፈውስ ግን በየአለንበት አገር ሁነን በተገኘው አጋጣሜ ትልቁን ሰላም ሰጩን የሃይማኖት ትምህርት መከታተል ነው:: በሐይማኖት የቆመ ሰው ታጋሽ ነው ::አይሰርቅም :አይዋሽም :አይፈራም : ከነዚህ ከራቅን በግልባጩ ፍቅር :እምነት : ሰላም በውስጣችን ይሰፍናል:: ይህ የሃይማኖት ጽናት በተግባር ከተተገበረ ለራሳችንም ሆነ ለቤተሰባችን ብሎም ለህብረተሰባችን ጠናማ ዜጋ እንሆናለን::
  የድንግል ልጅ መንገዱን ይምራን:: አሜን

  ReplyDelete
 84. Nice Daniel.It is very impressive and teaching story.God bless you!!!

  ReplyDelete
 85. On the English version of the original story which is called "Until Death do us Apart", their son is a kid and he plays a great role by reminding (in fantasy) to his father in the morning saying "Dad, it's time to carry mom out". She loose weight due to cancer and died of it as her doctor already told her. She want to teach her husband and to give lesson for their son that his parents were perfect couple in love.
  Your translation is amazing and truly unique. However, I think it is better to quote (in my opinion) from where you got the premises of the moral story.
  Sorry, if I present it wrongly.
  Thank you very much and may God bless you. Keep on teaching us.
  I'm Addis.

  ReplyDelete
 86. እናቴ በዚህ ዘመን " ሰይጣን ጔዙን ጠቅልሎ የሰፈረው በትዳርና በቤተ ክርስትያን ውስጥ ነው" ትላ

  ReplyDelete