Friday, June 4, 2010

ሰበር ዜና


   አያሌ ኢትዮጵያውያንን የጨረሰው ነፍሰ ገዳይ እስካሁን አልተያዘም

አያሌ ኢትዮጵያውያንን ሳያውቁት በማታልለ፣ ዐውቀውትም ለመኖር ሲሉ በማስገደድ የገደለውና አሁንም ነፍስ እያጠፋ ያለውን ገዳይ እስካሁን ለመያዝ እንዳልቻለ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ይህ ነፍሰ ገዳይ ራሱን በተለያዩ ስሞች በየጊዜው የሚቀያይር ሲሆን በተለይም «አሉ» «ተባለ» «ይላሉ» «ይባላል» የሚሉትን ስሞች ይበልጥ እንደሚጠቀምባቸው ታውቋል፡፡

ነፍሰ ገዳዩ ኅብረተሰቡን የሚያጠቃበት ልዩ ልዩ መንገዶች እንዳሉት ፖሊስ አስገንዝቧል፡፡ ያልተረጋገጠውን ነገር ምንጩ ከየት እንደሆነ ባልታወቀ መንገድ «እንዲህ ሊሆን ነው አሉ» በማት ያስወራል፡፡ ተቀባዩም ያንኑ ያልተረጋገጠ ወሬ ተቀብሎ «ኧረ እንዲህ እየተባለ ነው» ይላል፡፡ ከአንዱ ወደ ሌላው የመተላለፊያ መንገዶቹ አሉ፣ ተባለ፣ ይባላል፣ እየተባለ ነው የሚሉት ስሞቹ ናቸው፡፡

ነገሮችን በተጠየቃዊ መንገድ የመመርመር፣ አንድን ሃሳብ ከመቀበል እና ለውሳኔ ከመድረስ በፊት ከሌሎች ነገሮች ጋር የማገናዘብ፤ ማስረጃ የመፈለግ እና አውሎ አሳድሮ የማረጋገጥ ልማድ ባለመኖሩ ይህ ነፍሰ ገዳይ በአንድ ጊዜ ብዙ ሰዎችን እንዲጨርስ ዕድል ሰጥቶታል፡፡

«እንዲህ ያለው ዕቃ ሊጠፋ ነው አሉ፤ እንዲህ ያለ ነገር ሊመጣ ነው አሉ፤ እንዲህ ያለ ፋብሪካ ሊቆም ነው አሉ» የሚለውን ወሬ በመቀበል እና አንዳንድ ጊዜም ከነፍሰ ገዳዩ ጋር ተባብሮ በመሥራት አንዳንድ ኅሊና ቢስ ነጋዴዎች ዋጋ በመጨመር እንደሚጠቀሙ ተረጋግጧል፡፡

ሕዝቡም ከትክክለኛ ምንጭ ሳያረጋግጥ «አሉ» ተብሎ የተወራውን እንዳለ በመቀበል በአንዳንድ ወቅቶች ከዐቅሙ በላይ ሲሸምት ይገኛል፡፡ ለምሳሌ በምርጫው ሰሞን «ግርግር ይፈጠራል አሉ» «በግርግሩ ምክንያትም እህል ላይገኝ ይችላል አሉ» እየተባለ በመወራቱ ለወር የሚበቃ ነገር ገዝቶ የማያውቀው ቤተሰብ ሁሉ የሦስት ወር ቀለብ መሸመቱ ታውቋል፡፡

ይህ ክፉ ነፍሰ ገዳይ «እንዲህ ያለ በሽታ በከተማዋ ውስጥ ገብቷል አሉ፤ እንዲህ ያሉት ዐዋቂ ካልሆኑ በቀር አያድኑትም አሉ፤ እንዲህ እና እንዲያ ያለ ቅጠል፣ሥር፣ ድግምት ፍቱን ነው አሉ፤ በቀኝ ወይንም በግራ ጎን መነሣት ጥሩ ነው አሉ፤» እያለ አያሌዎችን በማታለል እና የአጭበርባሪዎችን ኪስ በመሙላት ኅብረተሰቡን እየጨረሰ ነው፡፡

በተለይም በምዕራቡ ዓለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተደራጀ እና የታመነ የመረጃ ምንጭ እምብዛም ስለሌላቸው ማታ ከምሽቱ 3 ሰዓት /9pm/ በኋላ ነጻ በሚሆኑት ስልኮች አማካኝነት ይህንን «አሉ» የተባለ ነፍሰ ገዳይ ሲያዛምቱ እንደሚያመሹ ታውቋል፡፡ በዚህም የተነሣ ስማቸው የጠፋ፣ ሞራላቸው የተነካ፣ ክብራቸው የተደረፈረ፣ ትዳራቸው የተናጋ፣ ቤተ ክርስቲያናቸው የተበጠበጠ፣ ማኅበራቸው የፈረሰ፣ ክህነታቸው ጥያቄ ውስጥ የገባ፣ ብዙ መሆናቸው ይነገራል፡፡

ይህ ነፍሰ ገዳይ ከዚህም አልፎ «መዓት ሊመጣ ነው አሉ፤ ዓለም ልታልፍ ነው አሉ፤ እንዲህ ያሉ የበቁ ሰው እንዲህ ያለውን ራእይ እያባዛችሁ በትኑ ብለዋል አሉ፤ የደረሳችሁን መልእክት ካልበተናችሁ በምትኩ ትዳራችሁ ይበተናል አሉ፣ ንግዳችሁ ይበታተናል አሉ፤» እያለ በማስወራት ሽብር እንደሚነዛና የዋሐንን በጭንቀት እንደሚገድል ተረጋግጧል፡፡

በአንዳንድ ድርጅቶች እና መሥሪያ ቤቶች ደግሞ «እንደዚህ ያለ ምደባ ሊመጣ ነው አሉ፤ ሠራተኛ ሊቀነስ ነው አሉ፤ ዝውውር ሊጀመር ነው አሉ፤ መሥሪያ ቤቱ ሊታጠፍ ነው አሉ፤ ድርጅቱ ከሥሮ ሊበተን ነው አሉ፤ እገሌ የተባለው ሠራተኛ ለአለቃው ጆሮ ጠቢ ነው አሉ፤ እገሌ ቀራቢ ነው አሉ፡፡» እያስባለ ሠራተኛውን ሁሉ በሃሳብ እና በጭንቀት፣ በጥበት እና በሰላም ማጣት እየረሸነ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል፡፡

በትምህርት ቤቶች አካባቢም «እገሊት ለመምህሩ ቅርብ ናት አሉ፣ እነ እገሌ ፈተናውን አግኝተውታል አሉ፤ እነ እገሌ «ሀንዳውቱን» ደብቀውታል አሉ፤ ፈተናው በጣም ከባድ ነው አሉ፤ መምህሩ «ኤ» አይሰጡም አሉ፤ ይህንን ያህል ተማሪ መባረር አለበት ተብሎ ተወስኗል አሉ፤» በሚሉ የማሳሳቻ ስልቶች እንደሚንቀሳቀስ ተደርሶበታል፡፡ በተለይም በፈተና እና በውጤት ወቅት ብዙ ተማሪዎችን እንደሚገድል ተገልጧል፡፡

ወደ ውጭ ሀገር ለመጓዝ ልባቸው ያቆበቆበውንም «እንዲህ ያለ ሀገር በቀላሉ ጥገኝነት እየተሰጠ ነው አሉ፤ እንዲህ ያለች መርከብ ስደተኞችን ጭና ወደ አውስትራልያ ልትሄድ ነው አሉ፤ እዚህ ሀገር እስከዚህ ዓመት ለገቡ ሰዎች ዜግነት ሊሰጥ ነው አሉ፡፡ እንዲህ እና እንዲያ ያለ ኬዝ እዚህ ቦታ እያበላ ነው አሉ፤ እገሌ እና እገሊት እንዲህ እና እንዲያ በማድረጋቸው በአንድ ቀን አሜሪካ ገቡ አሉ፤» እያለ ከሀገራቸው አስወጥቶ በየበረሃው በማንከራተት መግደሉን ፖሊስ ደርሶበታል፡፡

ሌላው ቀርቶ ኅብረተሰቡን ሊያስተምሩ ይችላሉ የተባሉትን መንፈሳውያን አባቶችን እንኳን ከመግደል እንደማይመለስ ተገልጧል፡፡ አሁን ጵጵስና ሊሰጥ ነው አሉ፡፡ እገሌ እና እገሌ ሊሾሙ ነው አሉ፡፡ እንዲህ እና እንዲያ የተባለ ዕርቅ ሊጀመር ነው አሉ፤ እገሌ የተባለው ሰው ቀራቢ በመሆኑ ሹመት ያሰጣል አሉ፡፡» በማለት ሰው እየጨረሰ እና እያጫረሰ ነው፡፡ ብዙዎቹም «እዚህ ቦታ በዚህ እና በዚያ መንገድ ሹመት ይሰጣል አሉ» የሚለውን ሰምተው የጸኑበትን ገዳም እና በኣት ለቀቀው በመምጣት በአዲስ አበባ ከተማ በችግር ላይ መውደቃቸውን ገልጠዋል፡፡

በመሆኑም ይህንን «አሉ» የተባለ አደገኛ ነፍሰ ገዳይ ኅብረተሰቡ ነቅቶ እንዲከታተለው፤ የነፍሰ ገዳዩ ሰለባ ከመሆን ራሱን እንዲጠብቅ፣ ባገኘውም ጊዜ እጅ ከፍንጅ ይዞ ለፖሊስ እንዲያስረክበው ፖሊስ አደራ ብሏል፡፡45 comments:

 1. what a nice message for us!

  ReplyDelete
 2. Dear D/n Daniel,

  yemiweduten yitelutal? Yemitelutinis yewedutal inde? aligebagnim. anten betam iwedihalehu. yemititsifachewn degimo etelachewalehu, sis biliten nekitewibignal. gin and ken inesunim ewedachewina mirt Etiopiawi tadergegn yihonal. esun tesfa adergalehu. gin betam ewedihalehu.

  ReplyDelete
 3. አሉ፡ ሊገኘ ነዉ አሉ!

  ReplyDelete
 4. አንድ ጓደኛዬ በጣም ቤተክርስቲያን ይከታተላል በተለይ ባህታውያንን ምርጫው ሊደርስ አካባቢ ይህ ልጅ ምን ይለኛል ቴዎድሮስ የሚባል የተነገረለት ንጉስ በአሁኑ ምርጫ ስልጣን ይይዛል፣ ኢሀዲግም ግንቦት ወርን አይጨርስም ይወድቃል ይህ ኢንፎርሜሽን ለሁሉም ማለት ለመንግስት ባለስልጣናት፣ ለሰባኪያን፣ ለመዘምራ ተልኳል በገዳም ያሉ አባቶችም በግንቦት ወር በኢትዩጵያ ውስጥ ብዙ ደም መፋሰስ ይሆናል ብለዋል በማለት በጣም የሚያስፈራ ነገር ነግሮኝ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት እቤት በምርጫው ምክንያት ችግር ሊኖስ ስለሚችል ብንኖር የምንበላው ምግብ በዛ ብሎ እንዲዘጋጅ በአሉ ምክንያት ነገሬያቸዋለሁ ነበር፡፡ እ/ር ይመስገን እሱ በሚያውቀው እስከ አሁን ሰላም ይመስለኛል፡፡ አሉ ካጠቃቸው ሰዎች አንዷ ነኝ፡፡ ዳኒ እ/ር ይባርክህ እንዲህ ልክ ልካችንን ንገረንና አስተካክለን አደባብሶ መፃፍ/ማስተማር ቢቀር ጥሩ፡፡

  ማኪ
  አ.አ

  ReplyDelete
 5. my prediction is good."Arfegen"!!! Dani!Pleas write the solution.

  ReplyDelete
 6. ዘእግዚእነJune 4, 2010 at 4:30 PM

  ዳንኤል ሐሳቡ ጥሩ ነው ሆኖም መረጃ በትክክል ማግኘት በማይችል ህብረተሰው ውስጥ አሉን ማጥፋነት አይቻልም። በሰለጠኑት ሐገራት መረጃው ትክክል መሆኑንና አለመሆኑን ከብዙ መገናኛ ብዙሐን በሚገኘው ፍሰት ማወቅ ይቻላል። በሐገራችን ግን መረጃዎች በልማዳዊ መንገድ ስለሚሄዱ የሚተላለፉት ከሰዎች ወደ ሰዎች ነው። መረጃን ከሰዎች የተቀበለ ሰው ለሌሎች ለማውራት ተባለ ፤አሉ ይባላል ብሎ ነው የሚናገረው።

  በህይወት ላይ ለውጥ ለሚያመጣ ጉዳይ ላይ ግን አሉ በሚባል ነገር ከመጠለፍ ይልቅ ማስተዋልና ማረጋገጥን ባህላችን ልናደርግ ይገባል። ያም ቢሆን ትክክለኛ መረጃ አግኝቶ ማረጋገጥ በሐገራችን አንጻር ከባድ ነው።

  ለዚህ ነው መረጃ ሐይል ነው የሚባለው። ትክክለኛ መረጃ ለህብረተሰባችን እንዲደርስ በያለንበት መጣር አለብን።

  ReplyDelete
 7. «አሉ» «ተባለ» «ይላሉ» «ይባላል» ብለው አሉ አይገርምም?

  ReplyDelete
 8. የሚገርመው ግን የተባለው ነብሰ ገዳይ ከጊዜ ወደ ጊዜ አድማሱን እያሰፋ እንጅ አልቀነሰም፡፡ እግዚአብሔር ሆይ ኃይልህን ስጠን!!!
  ለወንድማችንም የጥበብን ጽዋ ደጋግሞ ይስጥልን!
  Yam

  ReplyDelete
 9. Dani what you wrote was too smart to thought us those who killed more than millions times, oh am sorry my Father ADAM & Hewan(EVE) were THE FIRST to be killed by evil.

  ReplyDelete
 10. +++

  ጎበዝ ምን ይሻለናል? ሲወርድሲዋረድ እየሰፋ መጣ::ለፖሊስ እንዴት ተብሎ.....ማን ነዉ ራሱን .....
  ይህንን «አሉ» የተባለ አደገኛ ነፍሰ ገዳይ ኅብረተሰቡ አሁኑኑ በአንድነት:በፍቅር: በሰላምና በትግስት ማጥፋት አለብን::

  ግን ዲ/ን ዳንኤል የመጣዉ ከየት ነዉ????

  ከዝዋይ

  ReplyDelete
 11. የብዙ ኢትዩጵያኖቸ ገዳይ እሰካሁንም ያልተያዘው ከሚቀያይራቸው ስሞች አንዱ አለማወቅ፤ ሰባል ሌላው ደግሞ ራሰ ወዳድነት፤ እኔ አውቃለሁ፤ የኔ ዘር ይበለጣል ፤እኔ ያልኩት በቻ ትክክል ነው ሌላው እኔ ከሞትኩ ሰረዶ አየብቅል አይነቱ ነገሮች ናቸው በውስጣቸን ተሰግስገው በየአንዳንድችን አይምሮ ውስጥ ጠልቅው ዓይነ ልቦናችንን እንዲታውር አድረገው ፊታችን ላይ ያለውን እንዳናይና ወገናችንን በጅምላ ከመሞት እንኳን ለማዳን እንዳንችል ያደረጉን ገዳዮች እነኝሁ ስማቸውን ከላይ የጠቀሰኩት ናቸው ብዬ ዕደመድማለሁ።

  ReplyDelete
 12. አይ ዳኒ ደግሞ ዛሬ የፐፖለሊሰስ መማሰስተታወቀቂየያ አመጠጣሀህ!!

  እግዚአብሔር በአንድም በሌላም ያስተምራል የይሀህወው አየነወው

  በአገራችን ከተደረገ ጥናት በመነሳት የሰውን ነብስ በመጨረስ
  1ኛ. ኤችአይቪ ኤድስ
  2ኛ. ወባ
  3ኛ. የመኪና አደጋ
  4ኛ. የይህው ያንተው ፀሁፍ መሆኑ የሚቀር አይመስለኝም

  1-3 ምንጭ ኤፍ ኤም 98.10 እሮብ 11.00 ሰአት የሚቀርበው የመኪና እርዳታ
  ለ 4 ደገግመሞ http://www.danielkibret.com/2010/06/blog-post_04.html#more

  ቀቃለ ሀህየይወተት የያሰመማለልነን

  ReplyDelete
 13. kkkkkkk Betam beyasekim kumnegeru gin yelake newu andebetehen EGZIABHER yebarkewu yene wud wendem.EMEBERHAN titebekeh.

  ReplyDelete
 14. Amazing article this is what I expect from you.
  Dany, God bless you everything is good let you continue like this.

  DD
  Seattle WA
  U.S.A

  ReplyDelete
 15. እሴብሐከ ለዘመሐርከኒ
  ምክር ሰናይት ለዘየአቅባ

  ReplyDelete
 16. ዲ/ን ዳንኤል
  በጣም አመሰግናለሁ፡ ግሩም ዕይታ ነዉ። ይህ በሽታነቱ ሳይታወቅበት የኖረ ገዳይ ነዉ፡ ለአንድ በሽታ መድሃኒት ከማፈላለግ በፊት ህብረተሰቡ በሽታነቱን መገንዘብ ያስፈልጋል። በእኛ ህብረተሰብ ግን ይህ ስር የሰደደ በሽታ ከመሆኑ አንጻር በቀላሉ እጅ የማይሰጥ ነፍሰ-ገዳይ ነዉ።

  እስቲ ከራሳችን እንጀምር። አለ የተባለ ሃይላችንን አሰባስበን "አሉ" የተባለዉን ነፍሰ-ገዳይ በቁጥጥራችን ስር እናዉል። በተለይ የዉጭዉን ዓለም ያየን ሰዎች እንደምንማረዉ ማንም በሌላዉ ህይወትና ኑሮ ዉስጥ ገብቶ የማዉራትን አባዜ እናቁምና ሰለሚመለከተንና ስለምናዉቀዉ ነገር ብቻ ለሌላዉ እናቀብል። ደግሞ እንዲህ አሉ? እንዳትሉ። ሰላም ቆዩ፤ ወንድማችንን ያበርታልን።

  ReplyDelete
 17. ለየት ያለ ጥያቄ (ከጹሁፉ ርዕስ ወጣ ያለ።
  ጤና ይስጥልኝ ወንድሜ ዳንኤል። እስኪ እባክህ ስለ ታላቁ መንፈሳዊ አባት እና አርበኛ ስለ ብፁዕ አቡነ ሚካኤል የምታውቀውን በለን። እኔ እንደሰማሁትና እንዳነበብኩት እኝህ ታላቅ አባት እንደ ጻድቁ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በፍሽስት ዘመን በግፍ እንደተገደሉ ነው። ነገር ግን የብፁዕ አቡነ ሚካኤል ገድልና ባለውለታ እንብዛም እንደ ጻድቁ አቡነ ጴጥሮስ ጎልቶ አልወጣም። እኔ ስለ አባታችን ከሰማው ጅምሮ ለምን ታሪካችው እንዳልገነነ ለዚህ መልስ ይሰጡኛል ያልኳቸውን ብጠይቅ ነፍሴን የሚያርካ መልስ አላገኘውም። እስኪ ወንድሜ አንተ አንድ በለኝ። እስከአሁን መጣጥፍህ ለብዙ ጥያቄዎቼ መልስ ሆነውኛልና።
  በቅድሚያ ስለሁሉም እግዚአብሔር ይስጥልኝ። ችር ይግጠመን።
  ወንድምህ

  ReplyDelete
 18. Egyptian Convert Endures Life at a Standstill – on the Run

  http://www.coptsunited.com/Details.php?I=183&A=1432


  By CDN May 30, 2010

  ReplyDelete
 19. WOY TEBALAE ALU!? TEBALE.... TEBALE ALU....

  NEW YALEW ZEFAGNU!?...MIN MALETU NEBER?

  ReplyDelete
 20. GOD BLESS U MEMIHIR DANIEL,CANADA HAS EXPETING U TO HEAR YOUR MOUTH TEACHING,WE THANKS GOD FOR HIS GIFT (bread of life)through his servant daniel. we all should pray for this dor of service, pray pray pray

  ReplyDelete
 21. dani you are absolutely right. this is a virus. let's fight it together.
  abiy Nbi

  ReplyDelete
 22. If we have inormation based on evedence,those things will kill them selves not to kill others.

  ReplyDelete
 23. ሰላም ጤና ይስጥልኝ በድጋሚ፤

  እስቲ ሁላችንም ይህንን "አሉ"/"ተባለ"/"ይባላል" የተባለዉን ሽፍታ ለማጥፋት የሚያስፈልጉትን መፍትሔዎች እንጠቁም፡ ለመጀመር ያህል፦

  1. አንዱና ዋነኛዉ መንገድ ነፍሰ-ገዳዩ የሚዉልበትንና የምያድርበትን ቦታ ማጥራት ነዉ። ገዳዩ ሁለትና ከዚያ በላይ ሰዎች በተሰበሰቡበት አከባቢ እንደምያንዣብብ ጥናቶች ይጠቁማሉ። ከነዚህም የመሰባሰቢያ አጋጣሚዎች (በተለይ በገጠራማዉ የሀገራችን ክፍሎች) አንዱ ቡና ተጠራርቶ ሲጠጣ ነዉ። ጠላና ጠጅ ቤቶችም ከቡና ያላነሰ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ። ገዳዩ እነዚህን ስብሰባዎች እንደአጋጣሚ በመጠቀምና የቡናና የመጠጥ ንጥረ-ነገሮችን እንደመሳሪያ በመጠቀም ጥቃቱን ይፈጽማል። ስለዚህ ህብረተሰቡ ከእነዚህ ዓይነት ቦታዎች መራቅ ወይም በቦታዉ መገኘት የግድ አስፈላጊ ከሆነም ገዳዩ በአከባቢዉ አለመኖሩን ማረጋገጥ አለበት።

  2. ሌላዉና ከላይ ከተጠቀሰዉ መፍትሔ ጋር የሚገናኘዉ የገዳዩን መዘዋወሪያ መንገዶች መዝጋት ነዉ። ይህም ከስራ ፈትነት ጋር ይገናኛል። ህብረተሰቡ በየመንገዱና በየመንደሩ እየቆሙ ስራ ከሚያስፈቱ የገዳዩ 'ተሸካሚዎች' መራቅ አለበት፡ ከተቻለም 'ተሸካሚዎቹን' መስተማር አለበት። ህዝባችን በወሬና አሉባልታ የሚያጠፋዉን ያህል ጊዜ ለስራ ቢያዉል ራሱንም ሀገሩንም አንድ እርምጃ ወደፊት ያራምድ ነበር። ከዚህ አንጻር ይህ ገዳይ የሰዉ ብቻ ሳይሆን የሀገርም ገዳይ መሆኑ አያጠያይቅም። ስለዚህ ...ጎበዝ...ገዳዩን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ረዥም ጊዜ የሚፈልግ ቢሆንም እኛ ግን ዛሬዉኑ ታጥቀን እንነሳ። ይሉኝታን ትተን ገዳዩን ከማስተናገድ እንቆጠብ፡ ሁሉም ከተባበረ መኖሪያ አያገኝምና፡ ያኔ ነዉ ራሱ እጁን ለፖሊስ የሚሰጠዉ።

  እስቲ እናንተም ከመፍትሄዉ አንድ በሉን።
  ወንድማችሁ ከለንደን

  ReplyDelete
 24. ልክ ብለሀል ወንድማችን ሌላው ቀርቶ እኛ በምእራቡ አለም የምንኖር እንኩዋን የሰማነውን ማጣራት ስንችል አሉን አምነን ተባለ እያሉ ማውራት ይቀለናል:: የምእራቡ አለም ስንት በጎ ባህላችንን ሲያስጥለን ይኽንን አልተውንም:: ከነሱስ ደግሞ ምን እለ መልካሙን ብንማር? የማይሆነንን ከኛ ባህል እና እምነት ጋር የማይሄደውን ሙጭኝ ብለናል:: ግን ምን ነክቶን ነው?

  ReplyDelete
 25. + + +
  Thank you very much! Dn. Daniel, these is the top dangerous problem in our country especially in our church, this killer is effective in killing so many, and it is the one who is responsible for splitting our church & unity. Let God forgive us! for killing many people with it with out having a tangible evidence, is there any solution that we can do in order to control it? although we are late, we can still save the life of so many others if we can contribute at least by cutting the tools from disseminating the killer & by avoiding of being its tool ourselves.

  If we can use it wisely, we can also make it useful in such a way that we can learn about the history of our country, church, forefathers based on evidences but the problem is this killer only kills in a destructive way that its killing issues are selected for dividing & over-analyzing

  Let God give us strength to just speak constructive ideas!

  ReplyDelete
 26. Dear Dn Daniel, first of all I really liked the build up towards this interesting topic. Much has been said how big the problem is and I would like to highlight some of the causes. Note: this is not a complete list neither is the correct reason; but it is my personal view. First lack of credible information source (as one of my brother/sister already mentioned) has forced everybody to live in a guessing world and helped the liars to disseminate their ill-forecasted information. We all now about the media status in the country and I do not want to discuss about that on this blog. However, what always frustrate me is that our church and church leaders are part of the problem. A church that owns more than fifty percent of the countries population does not have single credible media to communicate with its followers. Are you kidding me? I even sometime think that our church leaders have media-phobia. We are always told in different congregation to disseminate information’s and what is more frustrating is everybody accepted that it is the duty of the church followers to disseminate the info. I am not saying that it should not be our obligation as Christians’ but I do not understand why we totally rely on "tell every body what you heard principle" in 21 century. Why do not we utilize technologies to disseminate the message of God and message of the church instead of asking everybody who attended a particular congregation to disseminate certain info. And we ask them to do it 'IN GODS name' and every body thinks that they are fulfilling the request of the church to disseminate something the way he understood it then the likely result is distorted info. I believe this has contributed in the making of a society that heavily relies on 'alu'. enetene guba’e laye endihe tebale tebeleo yijemerena... I do not exactly remember where but in one particular training the instructor gave us a practical example of how information can be distorted by telling the first whispering something to the first guy in line and instructed him to do so to the man next to him. The information the man at the end of the line got was the exact opposite of what the instructor whispered to the first man. One might argue that the media regulation of the country has hindered the church from having its own medium of communication by citing MK's effort and others unsuccessful efforts. However, I do no think it has been seriously considered and deemed as necessary at highest level. We have seen other religions' exploiting external sources to reach out their followers and us who did not have alternative option. In simple example, how many of churches have notice board and how many of them properly utilized it if there is one? Funny enough notice boards of many churches are owned by Sunday Schools as if the church has endorsed all adults are illiterate. Yet it is our church who started modern school in the country. The other big problem is .... (next part)

  ReplyDelete
 27. (continued from prvious one)...
  The other big problem is our reading habit. How many of us read notice boards unless we are searching for jobs? You post some announcement and you always hear people complaining that they have not seen one. We tend to rely on what we hear. I remember a guy who was firmly arguing that what he heard is the opposite of what is posted and when I asked him why he did not read the post he told me that because he trusted the guy who told him the wrong one. In summary two main reasons that created fertile ground for 'alu' are lack of credible information source and our reliance on our ears rather than our eyes. Let us not blame anybody for that. For me it starts from each one of us and I still expect more from our church to play a leading role in this one. As we claim the pride of making the majority of Ethiopia history let us also accept the blame. The church should play lead role in democratic society development by democratizing itself and one way for that is having a credible information source. I will discuss other issues in appropriate time as Dn Daniels incredible eyes bring up more issues. Do not get me wrong; I am one of the proud guy regarding the contribution of our mother church to Ethiopia but I also do feel that we failed in some aspects which we should start discussing about it and improve on. It does not mean that there is no attempt but I feel it is not enough. Dn Daniel has already taken a big step in the right direction and others we should follow. Thank you Dn Daniel for creating the forum and covering such kinds of important issues.

  ReplyDelete
 28. በጣም ይገርማል!!
  ለካ ሰው ሳያውቀው እራሱን ይገላል? ይህ እኮ ሁሉም የሚያናፍሰው ወሬ ነው።
  በቃ ሁሉም ለሚያወራው ነገር ትኩረት ሊሰጥ ይገባል። ላንተም ጸጋው ያብዛልህ!!

  ReplyDelete
 29. ብዙ ጊዜ አምድህን እከታታላለሁ ባገኜሁት አጋጣሚ ሁሉ፡፡ሃሳቦችህ በጣም ይስማሙኛል፡፡የዛሬው ደግሞ ወቅታዊ ነው እኔም ከራሴ እጀምራለሁ-ብችል አሉን ላለመዳመጥ አሊያ አሉ ተባለ ሳይሆን አይቀርም ምናልባት እንትና እንደተነገረው…ከሚሉ የነፍሰ ገዳዩ ዘመዶች ጋር ሚሄዱ ቃላትን አልናገርም፡፡ሁላችንም ቢያንስ አሉ ከኛ ሲደርስ ብናቆመው መጠኑን እና ጉዳቱን መቀነስ እንችላለን፡፡ እግዚአብሔር እስከመጨረሻው ያጥናህ

  ReplyDelete
 30. danie u r wonder

  ReplyDelete
 31. አምደ ሚካኤልJune 7, 2010 at 8:16 AM

  ሳያረጋግጡ ወሬ ምንሳይሉ ጎፈሬ
  እንደሚባለው ነው
  ክፉ ወሬ በሚል እስተምረኸን የለ?
  ዛሬ ደግሞ በክታብህ ደገምኸን
  እግዚአብሔር ዕድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን

  ReplyDelete
 32. ልቦና ይስጠን አምላካችን
  ችግራችን እኮ ምን አልባት ነገሩ ከተፈፀመ እንዳልነው ከሆነ እኔ ብዬ አልነበር ብለን ለማውራት ነው ራሳችንን እንደ አዋቂ ወይም መገለጥ እንዳለው ሰው ከፍ ለማድረግ “አሉ” “ተባለ” የሚሉትን እንዳንሰማ ልክ እንደዛ ዕንቁራሪት “ክፉ ወሬ” ስብከትህ ላይ እንዳለው ጆሮዎቻችን ባይሰሙ እናሸንፋለን ብዬ አስባለሁ፡፡

  መልካም አስበሃልና ላንተና ለቤተሰቦችህ መልካም ሁሉ ይሁንላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 33. Besides appreciation pls write about your experiences shortly

  ReplyDelete
 34. for the socity who nevr come acrros genune information services "alu" is the reliable sourse! other nations at least they have variety of info sourses from which they can verifie the trouth from "Alu". I dont think it's fair to criticize the society bay this regard. thanks dany.

  ReplyDelete
 35. alubalta(alu), hammet and smetawinet are the major killer diseases in Ethiopia.

  ReplyDelete
 36. ዲ/ን ዳንኤል፤

  ጥሩ ትዝብትና ምልከታ ነው።

  በተቻለ እያንዳንዱ ሰው አጣርቶ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሳይደርስበት እርሱም በደረሰው መረጃ ባይጨነቅ ለሌላውም ባያሰራጨው ለማለት ነው።

  ነገር ግን አንድ ነገር ልንገርህ። ኢትዮጵያ መረጃው ጠባብ ነው፣ የተረጋጋ ሕይወትና የኢኮኖሚ ዋስትና የለም። ብዙ ሌላ ሌላም ውስብስብ ጉዳዮች አሉ ለዚህ ነገር ሰለባ እንዲሆን ህዝቡን የሚያመቻቹ። እንዲያው የተለየ ሕዝብ ሊሆን ፈልጎ አይደለም።

  በውጭው አለምም ታብሎይድ/tabloid የሚባሉ ይህንን መሰል መረጃ ብቻ በማሰራጨት ቀላል የማይባል ገንዘብ የሚሰበስቡ ህትመቶች አሉ። ይህ ሁሉ የመረጃ ፍሰትና የንቃት ደረጃ ባለበት ለምን ገበያ አጥተው አልጠፉም ለሚለው ሁለት ዋና መልሶች ያሉ ይመስለኛል።

  አንዱ በጣም የሚገርመው ነገር ሁልጊዜም አንድን አብይ የሚባል መረጃ ማንም ባላሰበው ጊዜ ቀድመው የሚደርሱበት እስካሁንም እነዚሁ የተናቁ የመረጃ ምንጮች መሆናቸው ነው። እነሱ ቀድመው ሳይዘግቡበት ዜና የሆነ ነገር ስለመኖሩ እስከሚያጠራጥር ድረስ ሊባል ይችላል። ከሚጽፉት ብዙው ገለባ ቢሆንም እነሱ ቀድመው ያልደረሱበት መረጃ በዋናዎቹ የዜና ማሰራጫዎች በአብዛኛው አይሰማም። አገር ቤትም ልብ ብለህ ከተከታተልክ ሁሉም የሚናፈሰው አየር ላይ የሚቀር አይመስለኝም።

  ሌላው ምክንያት በውጭውም አለም እንደምናስበው ሁሉም ድርጅቶችና መንግስትም ራሱ ሙሉ ለሙሉ ግልጽ የማይሆኑባቸውና ዋና ዋናዎቹ የዜና ማሰራጫ ድርጅቶች (Mainstream Media) ስማቸውን ለመጠበቅ ሲሉ በሚከተሉት የውስጥ የስነምግባር መመሪያ የተነሳ በሚያደርጉት ጥንቃቄ ሳይታወቁ የሚዘገዩ ነገሮች ይኖራሉ። በአሜሪካ ብቻ ብዙ እንዲህ አይነት ክስተቶች አጋጥመዋል። ጠቅላላ ቅሌት / scandal የሚባሉት ነገሮች ምክንያታቸው ይሄው ነው። ተደብቀው በኋላ የተደረሰባቸው መሆናቸው ነው። ስለዚህ አሁንም ይኖራሉ የሚል ጥርጣሬ በሕዝቡ ዘንድ መኖሩ አይቀርም። ይህ ምን እንድሚያስከትል መገመት አያስቸግርም።

  ከብዙ ብዙ ነገሮች ማካከል የጆን ኤፍ ኬኔዲ ግድያ ጉዳይና የዩፎዎች (UFOs) መኖር አለመኖር እንደጥሩ ምሳሌ ሊሆኑ ይችላሉ። መንግስትና ሕዝብ በዚህ ጉዳይ እንዳልተማመኑ ነው የሚኖሩት። በቅርብ ወጥተው የነበሩ ጥናቶች እንዳሳዩት ዛሬ ድረስ ሁለት ሦስተኛው የአሜሪካ ሕዝብ መንግስት ያቀረበውን ሁሉ መረጃ ትቶ ጆን ኤፍ ኬኔዲ በልዩ ሴራ (Conspiracy) ነው የተገደለው የሚል እምነት ነው ያለው። በዚህም ምክንያት አንድ ትንሽ ዜና በተለይ አሟሟቱን በሚመለከት ስለጆን ኤፍ ኬኔዲ ብታወጣ በሰዓታት ውስጥ ዜናው እንደሰደድ እሳት ይዛመታል።

  በዩፎዎች ጉዳይ NASA እና ጥቂት የማይባሉ አንዳንዶች በመስኩ የሰለጠኑት ሰዎች ሳይቀር እንዲሁ እስከዛሬም አይተማመኑም።

  በእንግሊዝ የልዕልት ዳያና ጉዳይ በፍርድ ቤት ሁሉም ካለቀ በኋላ እንዲሁ ነው። ሌሎችም የተለያዩ ብዙ ነገሮች አሉ።

  አንዳንዴ እንዲያውም "ወደቀ ተሰበረ" በፈጣኑ ቴክኖሎጂ እየታገዘ በሰለጠነው አለም ሳይብስ አይቀርም የሚያስብልም አይነት ነው።

  እና ምን ለማለት ነው የሰውን አእምሮ የሚያጠኑ ጠበብት እንደሚሉት ሰው ሲፈጠር አብረውት የተፈጠሩ ምናልባትም ለደህንነቱ አስፈላጊ ከሆነው ግዙፍ አእምሮው ጋር የማይነጠሉ ነገሮች ሳይኖሩ አይቀርም የሚል ነው። ይህ አንተ የጥቀስከው ባሕሪአችን አንዱ ሳይሆን አይቀርም። የስነ-ሕይወት ሳይንስም ይህንን የመሰሉ የሰው ባሕሪያት ለሰው ከህልውናው ጋር የሚተሳሰሩበት ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ ምክንያቶች አሉ የሚል ነገር አለው።

  ይህ ምንም ሚዛን ላይደፋ ይችላል ለአብዛኞቻችን። ግን ሁሉም ቦታ ያለ ችግር መሆኑን ስታየውና ይልቁንም የኑሮ ዋስትናና መረጋጋት በሌለበት ደግሞ ችግሩ የጎላ ቢመስል ልዩ ሆነን ሳይሆን ከሰው ልጅ ተፈጥሮ ጋር ያለ ነገር መሆኑን ብትጠራጠር ተገቢ ይመስላል።

  እና ምን ለማለት ነው የሰው ልጅ ታላቅ ኃይል ስላለው በእግዚአብሔር ጸጋ ራሱን ለመግዛት ሲችልና ሁሉን በመንፈስ መመልከት ሲጀምር የዚህን ዓለም ነገር ሊንቅ ካልበቃ እንደምናስበው ይህን ነገር ከሰው አእምሮ ማስቀረት ቀላል አይመስልም። ይህ ጸጋ ያላቸው ስንቶች ናቸው? እግዚአብሔር ብቻ ያውቃል ሊያውም አሁን በዚህ ያለቀ በሚመስል ጊዜ። ለምን ይህ ሆነ? በሚል ምክንያት የሌለው መስሎ እንዳይሰማን እንጅ ምክሩ እጅግ መልካም ነው። ከጻሕፍት የሚጠበቅ ነው - ጉድፋችንን መንቀስ - ሰሚ ጭራሽ የሚጠፋበት ጊዜ ስለማይኖር።

  እድሜ ይስጥልን!

  ReplyDelete
 37. ዲ/ን ዳንኤል እንደምን አለህ የእግዚአብሔር ፀጋና በረከት ይብዛልህ
  እስኪ ሁሉን የሚችለው እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ሁሉ ማስተዋልን ይስጠን አሜን!!! በርታ በዚሁ ቀጥል ቶሎ ይቆማል ብለህ ተስፋ እንዳታቆርጥ ባይሆን ለተተኪው ትውልድ ጥሩ ሀውልት እያቆምክ ነውና በርታ እግዜአብሔር ይርዳህ

  እህትህ ከአዲስ አበባ

  ReplyDelete
 38. it is really a verry good view,thanks dani.God bless u

  ReplyDelete
 39. ቃለህይወት ያሰማልን!!

  ReplyDelete
 40. በጣም ትልቅ ቁም ነገር ነው!!!!

  ች2
  ከባህር ዳር

  ReplyDelete
 41. ጤፍ ሊወደድ ነው አሉ ….. ደሞዝ ሊቀነስ ነው አሉ ……… መለስ ሊወርድ ነው አሉ…… ቴዲ አፍሮ ዲጋሚ ሊታሰር ነው አሉ………. ወይ ይህ በሽታ መች ይለቀኝ ይለቀን ይሆን


  እግዚአብሄር ኢትዮጲያን ይባርክ

  ReplyDelete
 42. የሚገርም እይታ ነው

  ReplyDelete
 43. wow endih endenka erdan ke geta gare Egziabher yetbkh wendmi

  ReplyDelete