Saturday, May 29, 2010

ፕሮፌሰር ሳቤክ

አንድ መምህር ስለ source credibility ለተማሪዎቻቸው የሚከተለውን ገጠመኝ ተናገሩ፡፡ አንድ ጊዜ ከጓደኞቻችን ጋር ተሰብስበን በአንድ ጉዳይ ላይ ስንነጋገር ነበር፡፡ እኔም አንድን ሃሳብ አነሣሁና ሙግት ጀመርን፡፡ ያንን ሃሳቤን ለማስረዳት ያቀረብኳ ቸውን ማስረጃዎች እና መከራከርያዎች ወዳጆቼ ሊቀበሉኝ አልቻሉም፡፡ በኋላም አንድ ሃሳብ መጣልኝ፡፡ የኔውን ሃሳብ እንደገና አሣመርኩና «ባይገርማችሁ ፕሮፌሰር ሳቤክ የተባሉ የታወቀ የእንዲህ ያለ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ምሁር እንዲህ እና እንዲያ ብለዋል» እያልኩ ማስረዳት ጀመርኩ፡፡ ያን ጊዜ ሁሉም በአድናቆት ያዳምጡኝ፤ ራሳቸውንም ይነቀንቁ ጀመር፡፡ እኔም በፕሮፌሰር ሳቤክ ስም ሃሳቤን ሁሉ አስረድቼ ተቀባይነትም አግኝቼ ቤቴ ገባሁ፡፡

የሚገርማችሁ ግን ፕሮፌሰር ሳቤክ ማለት ፕሮፌሰር ሳ/SA/ ቤክ /BEK/ ማለት «ሳሙኤል በቀለ» ማለቴ ነበር፡፡ ነገር ግን የውጭ ሃገር ምሁር ስም አስመስዬ ስለተናገርኩት ተቀባይነት አገኘሁ፡፡ ያንኑ ሃሳብ ግን እኔ ራሴ አንሥቼ ስከራከርበት ማንም ሊቀበለው ፈቃደኛ አልነበረም፡፡

እንጀራ እንዴት ተቦክቶ እንዴት ይጋገራል? ጥጥ እንዴት ተለቅሞ፣ እንዴት ተባዝቶ፣ እንዴት ተፈትሎ፣ እንዴትስ ይሸመናል? በሬ እንዴት ይጠመዳል፣ እንዴትስ ይታረሳል? ቡና እንዴት ተቆልቶ፣ እንዴትስ ተወግጦ፣ እንዴትስ ይፈላል? ሽሮ እንዴት ወጥ ይሆናል? ለሚሉት ሃሳቦች ሁሉ የግድ የውጭ ሀገር መጽሐፍ እና የውጭ ሀገር ምሁራን፣ የውጭ ሀገር ድርጅቶች እና የውጭ ሀገር ጥናት መጥቀስ ፣በዚያም ላይ ተነሥቶ መከራከር የዐዋቂነት ማሳያ የሆነበት ክፉ ልማድ አለን፡፡

ይህ ልማድ ዛሬ የተፈጠረ ብቻ ሳይሆን ሥር የሰደደ መሠረት ያለው ይመስለኛል፡፡ በእምነት ታሪካችን ውስጥ እንኳን ኢትዮጵያውያን የደከሙባቸውን እና የዕውቀት እና የትጋት ውጤቶቻቸው የሆኑትን ጥበቦች እና ድርሰቶች፣ ቅርሶች እና ሀብቶች በኅብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖራቸው እና ከበሬታን እንዲያገኙ ሲባል ከኢየሩሳሌም የመጡ፣ ከግብጽ የተገኙ፣ ከመካ የወጡ እያልን የፕሮፌሰር ሳቤክን ማዕረግ ስንለግሳቸው ኖረናል፡፡

ብራና ዳምጠው፣ ቀለም በጥብጠው፣ ብርዕ ቀርፀው ታላላቅ ሥራ የሠሩ ቀደምቶቻችንም ኢትዮጵያዊ ስማቸውን ከገለጡ፣ «ነቢይ በሀገሩ አይከበርም» የተባለው ይደርስብናል ብለው በመፍራት የውጭ ሀገር መሠረት ያለው የብዕር ስም እንዲጠቀሙ ተገድደዋል፡፡ በኋላም በዚሁ የስም መኩሼነት የተነሣ የደከሙበት ሥራ የእነዚያ የውጭ ሀገር ሰዎች ሥራ እየተደረገ ተቆጥሮባቸዋል፡፡

ሌላው ቀርቶ ይህንን ጠባያችንን ጠንቅቀው ያወቁት የውጭ ሀገር ሰዎች እንኳን የሀገርን ስም የሚያስጠሩ እና የሐበሻን ታሪክ ከፍ አድርገው የሚዘክሩ ነገሮችን በዚያው በተለመደው ልማድ መሠረት ለውጭ ሀገር ሰዎች እየሰጡ እንዲጽፉ እና የስም ዝርፊያ እንዲያካሂዱ አድርገናቸዋል፡፡ የላሊበላ የሥነ ሕንፃ ጥበብ በአውሮፓውያን የተገነባ ነው እየተባለ ለብዙ ዘመናት የተነገረው፤ ኢትዮጵያዊው ፈላስፋ ዘርዐ ያዕቆብና ደቀ መዝሙሩ ወልደ ሕይወት ኢትዮጵያውያን አይደሉም የተባሉት በዚሁ ልማድ መሠረት ነው፡፡

የፕሮፌሰር ሳቤክ ጉዳይ የእምነት ሰዎችን ብቻ ሳይሆን ፖለቲከኞቻችንንም የለከፈ በሽታ ነው፡፡ በስድሳቹ አጋማሽ እና መጨረሻ ለሀገሪቱ እናስባለን ብለው የተነሡት አብዮታውያን ምሁራን የሀገሪቱን ነባራዊ ችግር አጥንተው፤ የሀገሪቱን ነባር ፍልስፍናዎች እና መንገዶች ፈትሸው፤ ለኢትዮጵያዊው ችግር ኢትዮጵያዊ መፍትሔ ከማፈላለግ ይልቅ ማርክስ እና ሌኒን ለዚህች ሀገር ከእነርሱ በላይ ያስቡ ይመስል፣ የኢትዮጵያን ዕጣ ፈንታ ከማርክሲዝም ሌኒኒዝም ውስጥ ማፈላለግ ነበር የያዙት፡፡

ነገራቸው ሁሉ ሕዝቡ ምን ይላል? እኔ ራሴስ ምን አስባለሁ? ለሀገሬ የሚበጀው ሀገራዊ መንገድስ የቱ ነው? ከማለት ይልቅ ማርክስ እንዲህ ብሏል፣ ሌኒን እንዲህ ብሏል እያሉ እነ ማርክስ እንኳን የማያውቁትን ትርጓሜ እየሰጡ ነበር ሲተላለቁ የነበሩት፡፡ «የተሻለው ሀገራዊ ሃሳብ እና መፍትሔ የኔ ነው» ከሚለው ይልቅ የተሻልኩት ማርክሲስት፣ ሌኒኒስት እኔ ነኝ ነበር ክርክሩ፡፡

ከጎጃም እና ጎንደር ይልቅ ሩሲያን እና ዩክሬንን፣ ከወለጋ እና ጋምቤላ ይልቅ ሀንጋሪን እና ቼኮዝሎቫኪያን፣ ከሐዲስ ዓለማየሁ ይልቅ ማክሲም ጎርኪን፣ ከጸጋዬ ገብረ መድኅን ይልቅ ፑሽኪንን፣ ከወንፈል እና ደቦ ይልቅ ወልባ እና ማልባን፣ ያጠኑት የዚህች ሀገር ልጆች ነበሩ መግባባት ያቃታቸው፡፡ ለሁሉም ነገር መነሻዎቻቸው እና መከራከርያዎቻቸው ፕሮፌሰር ቴቤክ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹም የራሳቸውን ሃሳብ ማቅረብ መሸነፍ እና መናቅን ስለሚያስከትልባቸው ቢቻል ለማርክስ እና ሌኒን፣ ባይቻልም ለማዖ እና ለቼ ጉቬራ፣ ያም ካልተሳካ ለፊደል ካስትሮ እየሰጡ ያቀርቡ የነበሩት ይኼው ልክፍት አስገድዷቸው ነው፡፡

የሀገሪቱ ባለ ሥልጣናት እና መሪዎች ለሀገራቸው ጋዜጠኞች ተናግረው፣ ነገ የእነርሱ ቃለ መጠይቅ ሲጠቀስ ትውልደ ኢትዮጵዩውያኑ አዲስ ዘመን እና የኢትዮጵያ ሬዲዮ፣ አዲስ አድማስ እና አዲስ ነገር፣ ሪፖርተር እና በሬሳ ተብሎ ከሚነገር ይልቅ ፋይናንሻል ታይምስ እና ኒውዮርክ ታይምስ፣ ቢቢሲ እና አልጄዚራ፣ ተብለው ፕሮፌሰር ሳቤክ ቢጠቀሱላቸው የሚመርጡ ይመስለኛል፡፡ ለዚህም ነው የራሳችንን ጉዳይ በእንግሊዝኛ እና በዐረብኛ ተጽፎ፣ መልሰን በአማርኛ እንድንሰማውና እንድናነበው የሚደረገው፡፡

«የኛ ሙሽራ ኩሪባቸው
በእንግሊዝ አናግሪያቸው» እየተባለ ይዘፈን የነበረው የሠርግ ዘፈን እዚህም ይሠራል ማለት ነው፡፡

የውጭ ሀገር ዲፕሎማቶችን እና የውጭ ሀገር ታላቅ ድርጅቶችን ሠራተኞች እና ኃላፊዎች ለማሳመን እና ስለሀገሪቱ በእነርሱ አፍ እንዲነገር፣ ብሎም «የእገሌ ሀገር ባለ ሥልጣን የሀገሪቱን ዕድገት አደነቁ፤ እገሌ የተባሉት የዚህ መሰሉ ዓለም ዐቀፍ ድርጅት ልዑክ ኢትዮጵያ በአስደናቂ ዕድገት ላይ ናት አሉ» እየተባለ ዜና እንዲሠራ የሚደረገው የፕሮፌሰር ሳቤክ ልክፍት ስለያዘን ካልሆነ በቀር ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? ከኢትዮጵያውያን የኑሮ ሁኔታ፣ ከሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ፣ በሀገሪቱ ላይ ከሚታዩት ተጨባጭ ለውጦች፣ በሕዝቡ ላይ ከሚታየው ገጽታ፣ ራሱ ተጠቃሚው ከሚናገረው ይልቅ ለምን የእነዚህ ሰዎች ምስክርነት አስፈለገ?
አንዳንድ ጊዜኮ ክርክራችን በራሱ አስገራሚ ነው፡፡ ኢትዮጵያ አድጋለች ወይስ አላደገችም፤ በኢኮኖሚያችን ላይ ለውጥ መጥቷል ወይስ አልመጣም፣ የኑሮ ዋጋ ተወድዷል ወይስ ረክሷል፣ እያሉ ለመከራከር የዓለም ባንክ እና ዓለም ዐቀፉ የገንዘብ ድርጅት እንጂ እኛ ራሳችንን ከቁም ነገር አንቆጠርም፡፡ እነርሱ አድጋችኋል ካሉን ሕዝቡ የፈለገውን ቢል ችግር የለውም፤ አላደጋችሁም ካሉንም ሕዝቡ የፈለገውን ያህል ቢያድግ አንቀበለውም፡፡ የግድ ፕሮፌሰር ሳቤክ መመስከር አለባቸው፡፡

ብለነው ብለነው የተውነውን ነገር
ባሏ ትናንት ሰምቶ ታንቆ ሊሞት ነበር

እንደተባለው ሕዝቡ እና የሀገር ውስጥ ሚዲያው ሲያቦካው እና ሲጋግረው ለኖረው ነገር ማብራርያ ወይንም መልስ የሚሰጠው በውጭ ሀገር የሚኖሩት፣ የሚታተሙት፣ የሚሠሩት፣ የተደራጁት ፕሮፌሰር ሳቤክ አንድ ነገር ከተናገሩ ነው፡፡ አንዳንድጊዜማ ፕሮፌሰሩ ያሉት ሳይነገረን መልሱን እንሰማዋለን፡፡ ይህም ሕዝቡ በአማርኛ ከሚናገረው ይልቅ ፕሮፌሰር ቴቤክ በእንግሊዝኛ የሚናገሩት ይበልጥ ያስደነግጣል ማለት ነው፡፡

በምርጫ ጊዜ ከሚታዩት ገጽታዎቻችን አንዱ ይሄ ልክፍት ነዉ፡፡ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ ነው አይደለም? ተጭበርብሯል ወይስ አልተጭበረበረም? ደረጃውን የጠበቀ ነው ወይስ የወረደ? ለሚሉት መከራከርያዎች እገሌ ወይንም እገሊት የተባሉ ታዛቢ፣ እገሌ የተባለ የውጭ ሀገር ሰው፣ እነ እገሌ የተባሉ የውጭ ሀገር ዲፕሎማቶች፣ ወይንም ደግሞ የእገሌ ሀገር መንግሥት ምን አለ? ነዉ ክርክሩ፡፡ ሕዝቡ ያለውን ማንም ሊሰማው ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ በምርጫው መሳካት ተጠቃሚው፤ በመጭበርበሩም ተጎጅው ሕዝቡ ነው፡፡ ከእርሱ በላይ ሊሰማ የሚገባው አልነበረም፡፡ ግን «የሐምሌ ውኃ ጥሩ ነው የሚጠጣው የለም፣ የድኃ ምክር መልካም ነው የሚሰማው የለም» የተባለው ነው የተፈጸመው፡፡

ሕጎቻችን እና ሥርዓቶቻችን ሲረቀቁ እንኳን እንደ ትልቅ ነገር የሚነሣው «ከኢትዮጵያውያን ባህል እና ወግ፣ በኢትዮጵያ ካሉ ብሔረሰቦች ነባር ልምዶች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ምሁራን ይህ እና ያ ሃሳብ ተገኝቷል» የሚለው ሳይሆን «የእገሌ ሀገር ልምድ ተቀስሟል፤ በእነ እገሌ ሀገር እንዲህ እና እንዲያ ይደረጋል» የሚለው ጉዳይ ነው፡፡ በነጥቡ ላይ ክርክር ሲነሣም እንደ ማስረጃ የሚቀርበው የዚያ ሀገር አሠራር እና ሕግ፣ ልምድ እና ባህል ነው፡፡

«መልክ ከፈጣሪ፣ ሞያ ከጎረቤት» ይባላልና መልካም መልካሙን መቅሰም የሚያስፈልግም የማይጠላም ነው፡፡ ነገር ግን ዋናው መመዘኛው ፕሮፌሰር ሳቤክ ምን አሉ? የሚለው ሳይሆን ለኢትዮጵያ ምን ይበጃታል?የሚለው መሆን አለበት፡፡

በዚያ ሀገር የሚበላው ሁሉ በኛ ሀገር አይበላም፣ በዚያ ሀገር ነውር የሆነው ሁሉ በኛም ነውር አይሆንም፣ በዚያ ሀገር የሚፈቀደው ሁሉ በኛ ሀገር አይፈቀድም፣ የዚያ ሀገር የኑሮ ፍልስፍና ከሀገራችን ሊለይ ይችላል፤ የነርሱ ደረጃ ከደረጃችን፣ ፍላጎታቸውም ከፍላጎታችን የሚለይበት ነገር ይኖረዋል፡፡ ደግሞም የዚያ ሀገር ሰዎች ያንን ሕግ እና አሠራር ሲቀርጹ ለሀገራቸው እንዲጠቅም ብለው እንጂ ለኛ አርአያ ምሳሌ ለመሆን ብለው አይደለም፡፡ ስለዚህም ወሳኙ ጫማውን በእግር ልክ ማስተካከሉ እንጂ እግርን በጫማ ልክ መቁረጡ አይደለም፡፡ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን እስካልበጀ ድረስ አሜሪካ የሠለጠነችበት፣ ቻይና የተመነደገችበት፣ ጀርመን የተመነጠቀችበት ቢሆንም እንኳን ሊቀር፣ ሊሻሻል እና ሊቀየር ይችላል፡፡

22 comments:

 1. this seems to be an attempt to attack abiye, your former colleague.

  ReplyDelete
 2. Kalehiwot yasemalen dani.Berta!

  ReplyDelete
 3. Kale hiwot Yasemalen Dn. Daniel

  ReplyDelete
 4. Wonderfull! dani.

  DD
  Seattle WA
  U.S.A

  ReplyDelete
 5. What a wounderful reading it is.God is telling as in one way or another if we are ready to listen.Most of us are having this kind of problems insted of learnning our culture and histry first admirring Europe and eastren countries.I belive this is a great advise for us.Keep itup Good blees you and your family as well.
  G from mn,USA

  ReplyDelete
 6. I read it somewhere but it is timely. There is something that loss our confidence and ability to believe in our works.We hesitate in everything that it is our own work. Our fore fathers hide their names in fear of unnecessary worldly blessing but open a hole for thieves like we have seen on our manuscripts.They gave their copyright to angels, martyrs and the like./ we know that everything is with the help of God but.../. We have no detail information on who did what like other countries.The present generation is equipped with our inability and will not even believe in his own works.

  ReplyDelete
 7. Dear Dn Daniel I salute you once again! That was sensational, just brilliant!!! Recently you are picking hot topics and I liked your observations so far but I loved this one. We live in a society that considers failure to explain ourselves in Amharic as modernization, very funny!!! What worries me more though is some of our strategic development plans (the ones I am familliar with) are based exactly on the same ideology. The government, institutes, individuals... all are try to justify their wrong turns by quoting America, Europe or China or in short 'Prof Sabek'. It is, however, ETV that suffers the most from this chronic disease. I have one disagreement though! I am not sure if I can buy what 'Ethiopians' say about election (if Ethiopians voice about it was what was televised in the rally the day after, r u kidding me?). I said this not because I do not trust my fellow Ethiopians when it comes to election but because I do not think we have the proper channel to air our real political feelings!!! Anyway, it was a an excellent observation and I can not wait what you are going to say next week.

  ReplyDelete
 8. What a prolific writer you are! May God bless you and your works!

  ReplyDelete
 9. Nice view and good observation. We have left a lot of things to correct, such like this. We expect similar posts on other areas of our weakness.

  ReplyDelete
 10. This article demonstrates the contrast between truth of this world and its standards versus truth of the Truth and its measurements. To me, the former one is filled with contradictions and is relative, even negating its own standards while the latter is absolute. So, the entire problem in an analysis of such events like in the writer’s article emanates in our attempt to find truth of the Truth in this world of politicians who are the major actors in the dominant social scenario. A simple less professional survey of what some of these actors said, wrote, and advocate at a particular period of time will proof how inconsistent they can be in their basic principles and standards. So, according to their standards every kind of falsity, corruption, irrationality, theft, and what have you can be acceptable to them in as far as it is politically rational and appealing. This is not unique to Ethiopia as many would think. All nations though the degree of visibility of such acts to the public varies, I think, experience it. So, why search truth in a world whose body and soul is built from vain truth, irrational rationality, and lots of oxymoron deeds??? Yes, I admit one has every right to do so but all in vain!!! Selame egziabhere ayleyen

  ReplyDelete
 11. I couldn't understand the first comment!

  ReplyDelete
 12. greate i dont have any word to discribe wonderfull

  ReplyDelete
 13. ዳንኤል እውነቴን ነው የምልህ
  በጣም ደፋር ነህ ::

  እስኪ : በደፋሩ/ሀቀኛው አንደበትህና በተባው ብዕርህ :
  ብዙ ነገሮችን : እንድትነግረን
  አምላክ ይጠብቅህ

  ReplyDelete
 14. @anonymous who said this topic is meant to attack Abiy!!! Let us not limit the freedom of the writer by individualizing topics. I do not mind if that is what you feel but I do not understand the motive of you dragging the rest of us into your nightmares!! Once again let us not politicize or personalize what ever is written on this blog as i consider that a strategy to deflect us from the real essence of wonderful topics like this. Even if the intent of Dn Daniel was what you stated you are helping him to use the site to attack individuals by mentioning names. Hence let us not publicize our own insecurity or help the site administrator to use the blog for wrong reasons if indeed he has that intention which I strongly disagree without forgetting the human nature of Dn Daniel.

  ReplyDelete
 15. betam des yilegnal bewuste yalewun neger leloch tsifewut sayew. sewoch hulu endiyanebut yih dire gets min yahil tewawukuwal?

  ReplyDelete
 16. Dn Daniel u are extracting and enabling us to visualize things that are sticked to us like harming parasaites that must be rejected.Its nice topic and i agree with the idea u wrote.carry on....please dani.
  Egziabhere yitebikih

  ReplyDelete
 17. ዳኒ ውኃ በጣም ጠምቶህ ስትጠጣ የተሰማህ የደስታ ወይም የእርካታ ስሜትህን ታስታውሳለህ ሕያው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው ውስጤ ልክ እንደዛ ነው የረካው፡፡ በአንተ የውኃ ጥማትና እርካታ እኔን እንድትረዳኝ ያረኩህ ምን ያህል ውስጤን እንዳስደሰትከው ጥሜን እንዳረካኸው እንድትረዳልኝ ብዩ ነው፡፡ ለራሴ በጣም ነው የገረመኝ ውስጤ እንደዚህ አይነት እውነት ለካ በጣም ተጠምቶ ነበር! ከዚህ በፊት ስለ ቅዱስ ያሬድ ያወጣኸው ላይ የአባ ጊዩርጊስ ዘጋስጫን መፀሀፊ ሚስጥርን ሳነብ የተሰማኝ ስሜት ገልጨ ነበር ልክ መፀሀፋን አንብቤ እንደጨረስኩ ከውስጤ የወጣው ቃል ምነው ይሄ አባት ግብጻዊ በሆነ ኖሮ ገና ድሮ እናውቀው ነበር ብዬ ነበር፡፡ ይሄም ጹሁፍህ ይሄን ስሜትን ነው የገለፀው በእውነት ቃለ ሕይወት ያሰማህ

  ኢትዩጵያ የራሷን ጉዳይ በራሷ እንድትፈታ በልሀ ልበልሀ አይነት የዳኝነት ስርዓታችን ችግራችንን እንዲፈቱ ቢደረግ፣ እኛ ለራሳችንን ሐሳብና እውቀት አድናቂ ብንሆን፣ እኛም እንደሌላው አእምሮአችንን ስራ ብለን ብንፈቅድለት የሚሰራ ጭንቅላት እንዳለን ብናውቅና ብንጠቀምበት መልካም ነው፡፡ በነገራችን ላይ በቀኝ ግዛት ሳንገዛ እንዲህ የነጭ አባዜ የያዘን በቀኝ ብንገዛማ ኖሮ???????????????????????????????????

  ማኪ
  አ.አ

  ReplyDelete
 18. I like it. God be with U.

  ReplyDelete
 19. Eleni ke-SyracuseJune 2, 2010 at 2:59 AM

  Amlak yabertahe! Dn. Daniel, this is really true, it is because our minds and actions are indirectly colonized by the foreign culture, and if our eyes keep on looking those references we will mess up our life soon b/c the people we want them to be refereed are currently going through a lot of scary life styles which take us back to the time of "Sedome ena Gemora"

  Let our everlasting father help us to focus on referring to our forefather's fruit of faith!

  ReplyDelete
 20. Very good point!!!...yemisema binor

  ReplyDelete
 21. Selam Dani,

  Menew tefah semonun beselam new?

  ReplyDelete