Wednesday, May 26, 2010

ሀገር እንወዳለን


ሰውዬው የውጭ ሀገር ዜጋ ቢሆኑም ዐሥር ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ አስተምረዋል፡፡ ሚስተር ዣክ ይባላሉ፡፡ ሻሂ እየጠጡ ኢትዮጵያዊውን ጓደኛቸውን እየጠበቁ ነው፡፡ ሁለት ጊዜ ፉት እንዳሉት ጓደኛቸው ከች አለ፡፡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የተጠለፈበት ቆብ አድርጓል፡፡ በለመዱት የኢትዮጵያውያን ባህል መሠረት ከመቀመጫቸው ተነሥተው ተቀበሉት፡፡ ወንበር ስቦ እንደ ተቀመጠ ያጠለቀውን ቆብ ጠረጲዛው ላይ አኖረው፡፡ ሚስተር ዣክ የተቀመጠውን በኢትዮጵያ ባንዴራ የተጠለፈ ቆብ አየት አደረጉና «እናንተ ኢትዮጵያውያን ለምንድን ነው በባንዴራችሁ ማጌጥ የምትወዱት?» አሉና ኢትዮጵያዊውን እንግዳቸውን ጠየቁት፡፡

«እኛ ኢትዮጵያውያን ሀገራችንን እንወዳለን፡፡ በሀገራችን ለመጣ ርኅራኄ የለንም፡ ይህ የሀገር ፍቅር በደማችን ውስጥ አራተኛ ሴል ሆኖ ተቀምጧል፡፡ ለዚህ ነው» አላቸው፡፡

«ቆይ ግን ሀገራችንን እንወዳለን ስትሉ ምን ማለታችሁ ነው? ለመሆኑ ምኑን ነው የምትወዱት? ለእናንተ ሀገር ማለትስ ምን ማለት ነው? ወንዙ እና ተራራው ነው? ሜዳው እና ጫካው ነው? ምኑ ነው ሀገር?»

ኢትዮጵያዊው ትኩር ብሎ እያያቸው «ሁለመናው ነው፡፡ ሰው፣ እንስሳው፣ ሜዳው፣ ተራራው፣ ጫካው፣ ወንዙ፣ ሁሉም» አለና መለሰላቸው፡፡

«እኔ ግን አይመስለኝም» አሉት ሚስተር ዣክ፡፡

«እንዴት?» ተገርሞ ጠየቃቸው፡፡

«እናንተ ለሀገራችሁ የድመት ፍቅር ይመስለኛል ያላችሁ»

«የድመት ፍቅር ምን ዓይነት ነው» እንግዳው ተገርሞ እንደገና ጠየቀ፡፡

«ቤት ያከራዩኝ ሰውዬ ምን እንዳሉኝ ታውቃለህ፡፡ ድመት ልጆቿን የምትበላው ስለምትወዳቸው ነው፡፡ ፍቅሯን የምትገልጠው ልጆቿን በመብላት እና ለዘላለም ሆዷ ውስጥ በማድረግ ነው አሉኝ»

«እና»

«እናማ እናንተም ለሀገራችሁ ያላችሁን ፍቅር የምትገልጡት ሀገራችሁን በመብላት ይመስለኛል»

«ያንን ያህል እንደርሳለን ብለው ነው» አንገቱን ወዘወዘ እንግዳው፡፡

«ኧረ እንዲያውም ሳይብስ አይቀርም፡፡ አሁን ለምሳሌ እናንተ ኢትዮጵያውያን በቅኝ ገዥዎች ባለመገዛታችሁ ስትኮሩበት አያለሁ፡፡ ልክ ነው ለጀግኖች አባቶቻችሁ ምስጋና ይግባቸውና ለዚህ የታሪክ ዕድል አብቅተዋችኋል፡፡ የሦስት ሺ ዘመን የነጻነት ታሪክ አለን እያላችሁ በኛ በአፍሪካውያን ላይ ትኮሩብናላችሁ እንጂ በሦስት ሺ ዘመን ምን ሊሠራበት እንደሚችል አላሳያችሁንም፡፡ ነጻነትን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል አሳያችሁን እንጂ በነጻነት እንዴት መጠቀም እንደሚቻል አርአያ ልትሆኑን አልቻ ላችሁም፡፡ እርስ በርስ ስትዋጉ፣ አንዳችሁ የሠራችሁትን ሌላችሁ ስታጠፉ፣ መቶ ዓመት የለፋቸሁበትን በአንድ ቀን ደምስሳችሁ እንደገና ስትጀምሩ ነው የኖራችሁት፡፡ እስቲ ተመልከቱት የሦስት ሺ ዘመን ታሪክ አለን ነውኮ የምትሉት፡፡ ታድያ ሦስት ሺ ዘመን ተጉዛችሁ እዚህ መድረስ ብቻ ነው የቻላችሁት? አቆጣጠራችሁ ግን በምንድን ነው? አንድ ዓመትስ በእናንተ ዘንድ ስንት ቀን ነው?

«ለመሆኑ ሀገራችሁን ስለምትወዱ ነው እርስ በርስ ስትዋጉ የኖራችሁት? ሀገራችሁን ስለምትወዱ ነው የቀደመውን እያፈረሳችሁ እንደ አዲስ የምትጀምሩት? ወንዙን ሰው ሲነካባችሁ ዘራፍ ብላችሁ ትነሣላችሁ፤ እናንተ ግን ወንዙን አትጠቀሙበትም፡፡ መሬቱን ሰው ሊቆርስ ሲመጣ አራስ ነብር ሆናችሁ ትነሣላችሁ፤ እናንተ ግን መሬቱን አታለ ሙትም፡፡ ቅርሳችሁን ሰው ሊዘርፍ ሲመጣ የቻለ ይዘምታል ያልቻለ ያቅራራል፤ እናን ተም ግን ቅርሱን አትጠብቁትም፡፡ አሁን ይሄ ምቀኝነት ነው ወይስ ሀገር መውደድ ነው?»

ኢትዮጵያዊው እንግዳ ያልጠበቀው ነገር ስለመጣበት ትክዝ እንደማለት አለና «በርግጥ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ አንዳንድ ዋልጌዎች የሚሠሩት ሥራ ግን መላውን ሕዝብ መወከል የለበትም» አላቸው፡፡

«ልክ ነህ» አሉ ሚስተር ዣክ «ልክ ነህ ጥቂቶች ሁሉንም አይወክሉም፡፡ የማየው ነገር ግን ይህንን አባባልህን እንዳልቀበለው ያስገድደኛል፡፡ ተመልከት ቅቤው ውስጥ ሙዝ እየጨመረ የሚሸጠውኮ የራሳችሁ ሰው ነው፡፡ ለውጭ ሀገር አይደለም የሚሸጠው ለገዛ ጎረቤቱ ነው፡፡ ሂድ እስኪ በየሱቁ ስንት ጊዜው ያለፈበት የታሸገ ምግብ ይሸጣልኮ፡፡ ገዥው የሌላ ሀገር ሰው አይደለም፡፡ የራሳችሁ ወገን ነው፡፡ ያደረ ኬክ፣ ያደረ ምግብ፣ የተበላሸ ሥጋ የምትሸጡትኮ ለጠላት ሀገር አይደለም ለራሳችሁ ሰው ነው፡፡ አሁን እነዚህ ሰዎች ሀገራችንን እንወድዳለን ብለው ግሥላ ሲሆኑ ባይ ይገርመኛል፡፡ ወገናቸውን እየገደሉ ምኑን ነው የሚወድዱት እላለሁ፡፡ አሥር ብር የገዛችሁትን ዕቃ አንዳች እሴት ሳትጨምሩበት በገዛ ወገናችሁ ላይ መቶ ብር አትርፋችሁ ያለ ርኅራኄ እየሸጣችሁ ሀገራችሁን ትወድዳላችሁ ማለት ነው?»

«መሬቱን ብቻ ነው እንዴ ሀገር የሚሉት? በአንድ መንደር ውስጥ የሚገኝ መሸታ ቤት መንደርተኛውን እየበጠበጠ ስላስቸገረ የቀበሌ ጥበቃዎች መጡና ድምጽ ቀንሱ አሏቸው፡፡ እነርሱም እሺ አሉና የሚገርም ዘፈን ከፈቱ አሉ፡፡»

«ምን የሚል?»

«እኛም አንተኛ ሰውም አናስተኛ የሚል»

«ሆሆይ! ይህቺን አገር አገላብጠው ነውኮ የሚያውቋት» አለ እንግዳው ተደንቆ፡፡

«ሂድና ሠራተኛውን እየው፡፡ ሌላ ትርፍ ሀገር ያለው፣ በቅኝ ገዥዎች ተገድዶ የሚሠራ ነውኮ የሚመስለው፡፡ አንዳንዱ ዘግይቶ ይገባል፣ አንዲት ነገር ሳይሠራ ለሻሂ ይወጣል፤ እጁን ወደ ኋላ አጣምሮ እየተዝናና ቢሮ ይመለሳል፣ አንዲት ነገር ሳይሠራ ለምሳ ይወጣል፡፡ አንድ ነገር ከጠየቅከው «ነገ፣ ነገ» ነው የሚለው፡፡ ነገ መቼ እንደሆነ አይታወቅም፡፡ ግንባታዎቻችሁ ለጠላት ሀገር የሚሠሩ እንጂ እንወድዳታለን ለምትሏት ሀገር የሚሠሩ አይመስሉም፡፡ የሚጀመሩበትን እንጂ ግንባታው የሚያልቅበትን ጊዜ ማንም አያውቅም፡፡ ተሠርቶ ሳይመረቅ ይፈራርሳል፡፡ ከሚሠራበት ገንዘብ የሚበላው ይበልጣል፡፡ ሠራተኛው ምድጃ ከብቦም ተረት ያወራል፣ አካፋ ተደግፎም ሥራ ላይ ተረት ያወራል፡፡

«ለመሆኑ እነዚያ የዚህ ሁሉ ግንባታ ሠሪዎቹ፣ አሠሪዎቹ፣ ተቆጣጣሪዎቹ አሁን አንተ እንደ ምትለኝ ሀገራቸውን ይወዳሉ ማለት ነው? የትኛዋን ሀገር ነው የሚወድዱት? ወይስ እኛ የማናውቃት ሌላ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር አለቻችሁ? ቻይናዎቹ ያሉትን ሰምተሃል?»

«ምን አሉ?»

«መንገድ ሲሠሩ፣ እነርሱ ቀን ቀን የሠሩትን እና የሰበሰቡትን የአካባቢው ሰው ሌሊት ሌሊት አፍርሶ እና አግዞ እየወሰደ አስቸገራቸው፡፡ በኋላ እንደ እኔው ሀገራችሁን ትወዳላችሁ ሲባል ሰምተው ስለነበር «ቆይ እነዚህ ኢትዮጵያውያን ሌላ ሀገር አላቸው እንዴ? ከሀገራቸው ሰርቀው የት ነው የሚወስዱት?» አሉ ይባላል»

«አሁን አሁንኮ ትውልዱ ጉዳዩን እያስተዋለ እየተለወጠ ነው፡፡ ምናልባት ቀድሞ እንዲህ ያለ ነገር ሊኖር ይችላል» አለ ኢትዮጵያዊው እንግዳ፡፡

«የለም የለም እንዲያውም ብሷል፡፡ አዲሱ ትውልድ የምትለው የሚገኘውኮ እኔ በማስተምርበት ኮሌጅ ነው፡፡ አየሁትኮ፡፡ ቤተ መጻሕፍት ገብቶ በድኻ ሀገር በጀት የታተመ መጽሐፍ የሚሰርቅ፣ የሚቀዳድድ፣ እላዩ ላይ ትርኪ ምርኪ ነገር የሚጽፍ ይህ ነው ሀገር ወዳዱ ትውልድ? ከእርሱ ቀጥሎ እዚህ ትምህርት ቤት የሚማረው የራሱ ወንድም እና እኅት መሆኑን እንኳን የሚረሳው ነው ሀገር ወዳዱ? ከዕውቀት ክርክር ይልቅ በጎጠኛነት ተቧድኖ መደባደብ የሚቀናው ነው ሀገር ወዳዱ ትውልድ? ነገሩ ምን ያድርግ የሚያስተምሩትም ቢሆኑኮ የሀገራቸውን ሰው የሚያስተምሩ፣ እንወዳታለን ለሚሏት ሀገር ትውልድ ሊያፈሩ የሚያስተምሩ አይመስሉም፡፡ የዛሬ ሃያ ዓመት ባዘጋጁት ማስታወሻ እያስተማሩት፣ ከቤተ መጻሕፍት አውጥተው ቢሮአቸው የደበቁትን መጽሐፍ ማጣቀሻ እየሰጡ ጥናት እያዘዙት ምን ያድርግ፡፡ በገጠሩ ሴት ልጅ በልጅነቷ ተጫውታ ሳትጨርስ ትዳርና በልጅነቷ ትወልዳለች፡፡ እርሷም ልጅ፣ የወለደችውም ልጅ ይሆንባትና አብረው እየተጫወቱ ያድጋሉ፡፡ አሁንም ኮሌጃችሁን እንደዚያው አደረጋችሁትኮ፡፡

«አሁን በየሕክምና ቦታው የሚሠራው የድሮው ትውልድ ነው ልትለኝ ነው? ለመሆኑ እርሱ ሀገር ወዳድ ነው? ጊዜ ባለፈበት መድኃኒት ወገኑን የሚያክመው፣ በመንግሥት በጀት የተገዛ መድኃኒት አውጥቶ የሚሸጠው፣ ገንዘብ ለመሰብሰብ ብቻ የሌለ ምርመራ እያዘዘ ድኻው ተማርሮ ከሕክምና ይልቅ ወደ ዳማ ከሴ እንዲጓዝ ያደረገው ሀገሩን ስለሚወድድ ነው?

«እስቲ የመኪና ምርመራ እንዴት እንደሚደረግ ተመልከት፡፡ መኪናው ሳይታይ በስልክ እኮ ነው የሚመረመረው፡፡ ለመሆኑ መርማሪው ሰውዬ ይሄ መኪና እርሱን፣ ቤተሰቡን፣ ዘመዶቹን እንደማይገጭ ርግጠኛ ነው? ሀገሩን ስለሚወድ ነው ሕዝብ እንዲያልቅ ፈቅዶ የተበላሸ መኪና ጤነኛ ነው ብሎ የሚፈርመው?

«በአንድ ወቅት አዲስ አበባ መንገዶቿን ሰየመች ተብሎ በየቦታው ተለጠፈ፡፡ ሦስት ወር አልሞላውም ሲወድቅ እና ሲጠፋ፡፡ ማን ዘረፈው? ሀገር ወዳዱ፡፡ ተካዮቹስ ቢሆኑ ለምን ዘወር ብለው አላዩትም? ሀገር ወዳድ ስለሆኑ፡፡

«እኔ ሀገር የመውደድን ጉዳይ አሁን እርስዎ ባሰቡበት መንገድ አስቤው አላውቅም፡፡ ብቻ እኛ የሀገራችን ጉዳይ ሲነሣ ደመ ቁጡዎች፣ አትንኩን ባዮች እና ኮስታሮች መሆናችንን አውቃለሁ፡፡» አለ ኢትዮጵያዊው እንግዳ፡፡

«ልክ ነህ ይህንንማ ዓለም በሙሉ ይመሰክርላችኋልኮ፡፡ ይህች ሀገርኮ ዝም ብላ እንዲሁ በነጻነት አልኖረችም፡፡ አንዳች ልዩ ነገርማ አላችሁኮ፡፡ ሀገራቸውን ባይወድዱ ኖሮ አባቶቻችሁ ደማቸውን ባልገበሩ ነበር፡፡ አጥንታቸውን ከስክሰው ድንበር ባላጠሩ ነበር፡፡ ዘመናዊ መሣርያ የታጠቁትን በባህላዊ መሣርያ ባላሸነፉ ነበር፡፡ ግን ሀገር መውደድ ይሄ ብቻ ነወይ) ሌላ አይንካን እኛ ግን እንደፈለግን እንጫረስ፣ ሌላ አይዝረፈን እኛ ግን እንዘራረፍ፣ ሌላ አይጨቁነን እኛ ግን እንጨቋቆን፣ ቅኝ ገዥ መጥቶ ቀንበር የሆነ ሕግ አያውጣብን እኛ ግን እርስ በርሳችን ቀንበር እንጫጫን፣ ጠላት ወርሮ መብታችንን አይንካ፣ እኛ ግን መብታችንን እርስ በርስ እንገፋፈፍ ነው የምትሉት) ይሄኮ ነው ያልገባኝ ነገር፡፡ ሀገር ማለትኮ መልክዐ ምድሩ ብቻ አይደለም፤ ይሄ ባለጉዳይ ሆኖ ቢሮህ የመጣው፣ታምሞ ሊታከም አንተጋ የመጣው፣ሊማር አንተ ጋ የመጣው፣ሊገዛ ሱቅህ ጋ የቆመው፣ በሞያህ እያገለገልከው ያለኸው፣በመኪናህ ላይ የተሳፈረው፣ እርሱኮ ነው ሀገር» አሉ ሚስተር ዣክ፡፡

«እንዴ ሚስተር ዣክ በዐሥረኛው ዓመት ሀገራችን መረረዎት መሰለኝ፡፡ እርስዎም እንደኛው ደመ ቁጡ ሊሆኑ ነው ማለት ነው፤ባለፈው ታምመው ተኝተው እያለ የኢትዮጵያዊ ደም ነበር እንዴ የተደረገልዎ» አለ ኢትዮጵያዊው ነገሩን ወደ ቀልድ ወስዶ ሀሳብ ለማስቀየር፡፡

«አየህ ይህች ሀገር ይበልጥ ስታውቃት ይበልጥ የምታሳዝን፣ ይበልጥ የምታስቆጭ፣ ይበልጥ የምታንገበግብ ናት፡፡ ቆይ ግን ይህንን ሁሉ የምታደርጉት ሀገራችሁን ስለምትወዱ ከሆነ ሀገራችሁን ባትወድዱ ኖሮስ ከዚህ የከፋ ምን ታደርጉ ነበር?አንድ እዚህ ሀገር የሰማሁት ቀልድ ነገር አለ፡፡ አንድ ባል ሚስቱን ይደበድባታል፡፡ እርሷም ቤቷን ትታ ትወጣለች፡፡ በኋላ ሽማግሌ ገብቶ ታረቁ ይላቸዋል፡፡ ባልም እኔኮ ስለምወዳት ነው የመታኋት፣ የፍቅር ነው ይላል፡፡ ሚስቲቱም ስትወደኝ ከሆነ እንዲህ የምትመታኝ ስትጠላኝ ምን ልታደርግ ነው? አለችው አሉ፡፡ አሁንም እናንተ በሀገራችሁ ላይ ራሳችሁ ይህንን ሁሉ ግፍ የምትፈጽሙት ሀገር ወዳድ ስለሆናችሁ ከሆነ ብትጠሏት ኖሮ ምን ልታደርጉ ነበር?
60 comments:

 1. It is a nice observation. It is what we are doing day and night. So, it gives us a good lesson.

  ReplyDelete
 2. Interesting ! kale hiwot yasemalin

  ReplyDelete
 3. መልካም እይታ ነዉ! ቃለ ህይወት ያሰማልን!

  ReplyDelete
 4. dani,hager malet min malet endehone,ye hager fikir min endehone bedenib yemigelte article bemehonu betam menager kemichilew belay yemigermina bizu sew liyanebew yemigeba new elalew.

  ReplyDelete
 5. wow, so perfect!

  ReplyDelete
 6. D/Daniel, You R a great writer! what U R writing is always right! pls let the whole Ethiopia to hear your voice! God bless,

  ReplyDelete
 7. የሚገርም ትዝብት ነው! ግን እውነት የሆነ

  እግዚአብሔርን የሚፈራ እኮ በወገኑ ላይ እንዲህ እንዲህ አያደርግም!
  ልብ ይስጠን!

  ReplyDelete
 8. አባግንባር (ከሮማ)May 26, 2010 at 4:43 PM

  ውድ ዲን. ዳንኤል ሠላምታዬ እንደተለመደው ይድረስህ፤

  የእትዬለሌ ማጣቀሻ ዎችን ማቅረብ ቢቻልም፤ ባለፈው አንተ ያቀርብከው የባህርዛፍም ነገር ትዝ አለኝ፡፡ ባህርዛፍ መሆንን እየናፈቅኩኝ እንዴት ስለሃገር መውደድ ላውራህ? ብቻ ምሳሌዎቹ ባንተ ይብቁንና እስቲ እንመለስ እንሥራ እላለሁ፡፡ እንዲያው ሌላው ቀርቶ ያንተን ጽሁፍ እንኳን አንብቦ አስተያየት የሚፅፍልህ 20-30 የሚሆነው ሰው የራሱን ድርሻ ቢወጣ ቀላል አይደለም፡፡
  ጥሩ ፅሁፍ ነው በርታ ግን መፍትሔውንም እየጠቆምክ ታዲያ?!

  አባግንባር
  ከሮማ

  ReplyDelete
 9. ጥሩ ማስተዋል ነው ዲ.ን ዳንኤል! እግዚአብሔር የአገልግሎትህን ዘመን ያብዛልህ!

  ReplyDelete
 10. ዲ/ን ዳንእል
  መቼም በምንም መልኩ ከተጠያቂነት የምድን
  አይመስለኘም.አሁንማ በሀይማኖት መመዘኛነት
  ሳየው/በሐገርወዳድነትም ፤ሳየው ከምን ወገን እንደሆንኩኝ
  ግራይገባኛል . ዳኒ መቺም በምንም መልኩ ከህሊና ተጠያቂነት
  ነጻ እንደማልሆን ተረድቻለሁኝ.

  ReplyDelete
 11. i want to do something for my country before i die if God willing soon i will do something posetive that is for sure just pray for me.
  By the way is any one out there who is profsionally willing to help me? here is what i want to do i want to biuld a scool in Debre stige Mariam church that futures class rooms ; accomedation for the teachers and students :income genratter that can fund the scool so that it can run by it self for the future if any one is willing to help ur welcome but i don't need money only proffesional help may God bless our country it's people and our church.thanks D Daniel for ur insight if someone respond for this i will email my addres to Dani

  ReplyDelete
 12. +++

  ዲ/ን ዳንኤል ግእዚአብሔር አንተን እና ቤተሰብህን ይጠብቅህ::አሜን

  በጣም አስተማሪ የሆነ ስነ_ጽሑፍ ነዉ::
  አሁን ያለዉ በምላሱ እየደለለ "እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል" የሚል ትዉልድ ነዉ::
  ግእዚአብሔር የዉነት ልቦና ይስጠን::

  በርታ >>>>>>>>>>>>> እንጠብቃለን::

  ከዝዋይ

  ReplyDelete
 13. this is nice specially 4 ..........

  ReplyDelete
 14. እግዚአብሔር ብዙ እውቀት ይግለጥልህ::ለረጅም ጊዜ ሳስበው የነበረውን ነው ያተትከው::እንዲያውም የኔ ምኞቴ የነበረው በልብ ወለድና በድራማ መልክ እንዲቀርብ ነበር ምክንያቱም ብዙ ኦዴንስ ማዳረስ ስለሚቻል::

  ReplyDelete
 15. Dk Daniel Egzare yebarekh edeman ende Matosal yarzemlh kemalt wech menem malt alchem Kal hiwot yasemaln mengest semayat yawerseln sol

  ReplyDelete
 16. THANK YOU

  EGNA YALIRARANILATIN HAGER LELA ENDIRARALAT YEMINTEBIQ EBIDOCH NEN ENJI HAGER WEDADIS AYIDELENIM.

  ReplyDelete
 17. +++

  በሚስተር ዣክ ፋንታ ታሪኩን የሚናገሩትና የሚተቹት አንድ ሸበቶ የዕድሜ ባለጸጋ ኢትዮጵያዊ ቢሆኑ ኖሮ ይህንን ጽሁፍ ለግድግዳ ፖስተርነት ባተምኩት ነበር። ከኢትዮጵያዊ ውጪ ፈረንጂም ሆነ ሌላ አፍሪካዊ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን ዝቅ አድርጎ ሲያይ፣ ሲተች፣ሲመክር ስመለከት ወይንም ሳነብ በጣም ያመኛል። የጎልማሳነት ዘመኔን እኩሌታውን ከፈረንጂና ከጎረቤቶቻችን ጋር ስለኖርኩና ስለመዘንኩዋቸው ለእኔ በየትኛው መስክ ቢሆን ፈረንጅ ልቆ ሲታይና መካሪ ሲሆን ያመኛል። የፈለገውን ያክል ትክክል ቢሆንም እንኩዋን ያገሬ ሽማግሌ ይምከረኝ፣ ይተቸኝ እንጂ ፈረንጂ ወይንም ሌላ ሲተቸኝ ያመኛል ። የባለፈውንም «ፊደል እያለው የማያነብ ማነው?» የሚለውን ጽሁፍክን በጣም ስለወደድኩት ለአንድ ወዳጄ ልልከው ብዬ ሳለ በጣም በካባዱ ከፈረንጅ ጋር የተወዳደርንበትና ያነስንበት ሆኖ ስላዬሁት መልሼ ተውኩት፤ ከወርቃማው የስነ ጽሁፍ ዘመናችን ጋር ብቻ እያነጻጻረ የሚተች ቢሆን ኖሮ አሁንም በደስታ ለባልጀሮቼ ሁሉ በላክሁት ነበር። አንባባቢ መሆን ትልቅ ሃብት ቢሆንም በማንበብ ምክንያት ሰው ለሕይወቱና ለስብዕናው ያተረፈላት ነገር ዋናው መለኪያ መሆን ያለበት ይመስለኛል። ምንም እንኩዋን የተለያዩ የሕይወት ገጽታዎችን የምትዳስስበት ዌብ ሎግ እንደሆነ ባምንም አንኩዋር ግንዛቤው «ቴክ ሆም ሜሴጅ » ከክርስትና ሕይወት እሴቶች መውጣት የለበትም ብዬ አምናለሁ። ለመላ የኢትዩጵያ ሕዝብ ዲ ዳንኤል አንድ ዕውቅ ሃያሲ ሊሆን ይችላል፤ ለእኔ ግን ዲ ዳንኤል ማለት የሕይወቴን ዙሪያ ገባውን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያናዊ በሆነ መልኩ እንድዳስሰው የሚያመላክተኝ ታላቅ ወንድሜ ነውና እንደዚያ እንደሆነ እንዲቀጥል እወዳለሁ። ከአለፈው ኢትዮጵያዊ ትውልድ ጋር ስንወዳደር በብዙ ነገሮች ኢትዮጵያችን አዝናብናለችና ትችቱም ከአባቶቻችን ጋር እየተነጻጸረ ብቻ ቢሆን በቂ ይመስለኛል።

  ReplyDelete
 18. Thank you

  Egna yaliraranilatin hager leloch endirarulat yemintebiq ebidoch nen enji hager wedad ayidelenim.

  ReplyDelete
 19. it is good idea! GOD bless you.

  ReplyDelete
 20. You really got an eagle eye. nice work. bless you.

  ReplyDelete
 21. It is not with saying, "Honey," "Honey," that sweetness will come into the mouth.

  እግዚአብሔር ይስጥልኝ.

  ReplyDelete
 22. That was a wonderful observation. Weak up HABESHA !!!

  ReplyDelete
 23. thanks Dany, it makes me to check my self, do I love my country? of course I do. I should rectify my mistekes do whats right. thanks again Stay blessed

  ReplyDelete
 24. Dn Daniel, thank you very much!!! But I think the root cause for the majority of the problems mentioned here is dissatisfaction of being who we are!! First of all we need to accept and appreciate our human nature with all its pitfalls, and in real world nobody on this planet likes anything more than himself. Yes there are many humanity champions but that is relative for me!!! If I am not happy with who I am, If I feel that I practically contributed nothing to who I am today, If I do not see any reward for being patriotic, If promotion is based on with who you align with or your relationship with the boss anything unprofessional, If I did not feel what ever built or manufactured or sold or... benefits me as a person... why should I be expected to be the good Samaritan?? I accept that the trend needs to be changed at some point if we have to bring Ethiopia where we all wish to be and generation sacrifice is necessary but when I see the people who are preaching about being patriotic are trying to take advantage of that why should I sacrifice myself? The issue regarding defending our country in the past and even in our recent history clearly demonstrates how much the issue of patriotism is manipulated in benefit of our leaders (except some few real patriotic leaders). In short the issue surrounding being patriotic should begins when you feel belongingness to your country, when you feel your scarification or honesty will ultimately contribute to the overall change not to certain group or … and when you see good leadership to build a country that will make you proud. Otherwise in a country where being a citizen is viewed as a curse we should not expect anything!! To be honest if you ask an American or European what citizenship he would have chosen if he is given the opportunity today he will say American or European. With all honesty if you ask me the same question I will never ever say Ethiopian. I am an Ethiopian because I did not choose to be an Ethiopian; the truth is as simple as that. I might be viewed as somebody…. but the fact of the matter is I should not be expected to choose a citizenship for which I am not proud of!!! If you ask me who should do it? My simple answer is I do not know because I can’t see it happening! I am ready to accept any harsh criticism to this end but due to unforeseen circumstances plus am coward I have changed my usual name.

  ReplyDelete
 25. ይገርማል ዳኒ እስከዛሬ አገሬን የምወድ ይመሰለኝ ነበር ለካስ እንኳንስ አገሬን እረሴንም ይሁን ቤተሰቦቼንም አልወድም

  ReplyDelete
 26. It is interesting topic.There is a generation gap in our country.Because our fathers (grand fathers)used to put country first but our generation( our fathers and us, I mean current generation)puts personal interest first so it takes time to be like our founding fathers.My God bless our country and give us good heart as well.

  ReplyDelete
 27. እውነት ኢትዩጵያችን እንወድሻለን?

  ሀገርንና ወገንን የሚወድ ትውልድ እንዲፈራ ቤተሰብ፣ ት/ቤት እና እናት ቤተክርስቲያን ባለ እዳ ናቸው? ዳኒ በጣም የሚገርም ጹሁፍ ነው ያወጣኸው በእውነት ግን ሀገራችንን የምንወደው በምን አይነት መልኩ ነው? ቆሻሻ ከቤታችን ጠርገን መንገድ ላይ እንጥላለ፣ መንገድ ተሰርቶ ሲያልቅ መብራት ኃይል ወይም ቴሌ ቆፍረው አበላሽተው ይሄዳሉ፣ በየገዳመቱና በየአድባራቱ ያሉ ቅርሶች ተሰርቀው ለፈረንድ የሚሸጡት በእኛው በሀገር ወዳዶቹ ነው በጣም የሚገርም ነው እውነት ኢትዩጵያችን እንዴት ነው የምንወድሽ? ፍቅራችን አይገርምም፣ አብርሀና አጽብሃ ክርስትናንን በመስበክ ወደዱሽ፣ ያሬድ ድንቅ ዜማ በመስጠት ወደደሽ፣ ካሌብ ድንበር ተሻግሮ ስምሽን በደም ጻፈልሽ፣ ላሊበላ ድንጋዩን ወርቅ አድርጐ ስምሽን በአለም ድንቅ መዝገብ ውስጥ አሰፈረልሽ፣ በአደዋ በማይጨረው ልጆችሽ ድንበርሽ ታፍሮ እንዲኖር ሞቱልሽ አፋዊ ያልሆነ ታሪክ ሰርተው አለፉልሽ… ታዲያ እንዲህ ያለ ፍቅርን ከየት ወሰድነው?

  የኢትዩጵያ ቤተክርስቲያን ልጆች ምድራዊ ርስታችን ኢትዩጵያ ናት፡፡ ኢትዩጵያ ከሌለች በአንገታችን ላይ ማህተም አድርገን የክርስቶስን ስም እየጠራን የሚቀበለን ጐረቤት ሀገር የለም ጐረቤቶቻችን እኮ ሱማሌ፣ ኤርትራ፣ ግብጽ፣ጅቡቲ ናቸው እውነት ይቀበሉናል? ስለዚህ ኢትዩጵያችንን መውደዱ ባለብን መልኩ መውደድ አለብን፡፡ የቀደሙት አባቶች ለሀገራቸው ፍቅራቸውን እንዲገልጹ በተጠየቁበት መንገድ ፍቅራቸውን ገልጸዋል፡፡ እኛ ለሀገራችን ያለንን ፍቅር እንድንገልጽ የምንጠየቀው እንደነሱ ደም በመለገስ አይደልም ለእድገቷ፣ ለሰላሟ፣ ለፍቅሯል ፣ ለአንድነቷ፣ ታሪኳን በመጠበቅ እንድንታመን ነው…. በእውነት ግሩም ድንቅ ጹሁፍ ነው ብዙ ሰው ሊያነበው በሚችል መልኩ ብታወጣው መልካም ነው

  የኢትዩጵያ አምላክ እ/ር ይጠብቅህ

  ማኪ/አ.አ

  ReplyDelete
 28. Mekuanint

  I support your Idea SendkAlama
  the problem is not only for Ethiopians. It is for all human nature. Look from the begining" What Kayen did on Abel. And look again Yakob and Esaw.,, Do you see this is for all human kind. Please don't underestimate ourselves.
  God Bless Ethiopia.

  ReplyDelete
 29. thank you for your constractive essay.It is a good observation. keep itup !,please.

  ReplyDelete
 30. DANI THANKS FOR THESE WRITING SO WHAT WE DO

  ReplyDelete
 31. በስመ እግዚአ ኩሎ!
  በጣም የሚገርም ነው
  ክፍል አንድ
  እንደያውም ሚስተር ዣክ ቤት ስላላሰሩ ወይም የህንፃ ሱፐር ቫይዘር ስላልሆኑ እንጂ ጉድ እኮነው በኮንስተራክሽን ያለው፡፡ሃገራቸውን በጣም በጣም ከማይወዱት ቅድምያ ማሃንዲሶች ነን፡፡እግዚአብሔር ይጠብቀን እንጂ መሬት መንቀጥቀጥ ቢመጣ እኮ ሀይቲማ ሰላም ነው ኢትዮጽያችን እኮ ገድለናታል ኮንሳልታንቶች ብር ከሚያወጡ ይልቅ የህንፃ ድዛይኑ በ ሁለት ሺ ብር እውቀቱም ሞራሉም በሌው ሰው ያሰሩታለ ብዙ ህንፃዎች እኮ የህንፃ ኮድ ህግ ሟሟላት ቀርቶ ጭራስኑ የምህንድስናው ጥበብ ብጥጋቸው የለፈም አይመስልም በየትኛው የህንፃ ኮድ እየተሰሩ እንደሆነ አምላክ ይወቀው ፡፡ አንድ ጨረታ ሲወጣ ምን ያህል ፐርሰንት ይደርሰኛል ብለው ፕላን የሚያወጡ ብዙ ሱፐርቫይዘሮች አምላክ ይቁጠራቸው፡፡ታማኝ ሁኖ የሚሰራ ኮንትራክተር ወይም ጉቦ ካልሰጠ ስራውን እንዲቋረጥ ይደረጋል ህገ እግዚቢሔር የሚያስቀድሙ ወንድሞች ከስራም የሚባረሩም አሉ፡፡ከሳምንት በፊት አንድ የታወቀ ማሃንዲስና ኮትራክተር ያለኝኝ ብነግራችሁ ያስደነግጣል፡፡የድህረ ምረቃ ጥናትህ በምን መስራት ፈለክ ይለኛል እኔም ያበራታታኛል ብዮ በመሬት መንቀጥቀጥና በህንፃ ያላችው ተዛማጅነትና ጉዳት ጥናት ነው ስለው እባክህ ህንፃው መፍረስ ስለማይቀር የህንፃው ስራ ምን ይሁን ምን ብርህን በባንክ ማስቀመጥ ይሻላል አለኝ አስቡት በመንግስትም በህዝብ ታምኖ ጨረታ ወስዶ እየሰራ ያለ ሰው ነው በሚሊዮኖች የሚቆጠር የኢትዮጽያ ህዝብ አልቆ እርሱ ግን ተቀምጦ ሊበላ፡፡ኢትዮጽያ ያላደገችው ትልቁና ዋነኛው ፈተና መሃንዲስ ነው ምክንያቱም ኮንስትራክሽኖች ሲሰሩ ብቻ ሳይሆን ሲጠገኑም ሲፈርሱም ብዚ ቢሊዮን ብር ይወጣል ይህም ጥራታቸው በስርቆት ስለሚበላሽ እስቲ እናስተውል የባለቤቱ መሃንዲስ በሚሊዮኖች ይሰርቃል ኮንትራክተሩ ይሰርቃል ሱፐርቫይዘሩ ይሰርቃል ታች ያሉትን ሰራተኞች ይሰርቃሉ ምን ቀረ ታድያ ህንፃው ከ77 ዓ/ም ከነበረው ድርቅ የባሰ አግኝቶታል ማለት ነው አምላክ ይጠብቀን ከማለት ውጭ ሌላ ምን ይባላል በጣም የሚገርመው አስተማርያችን ያለንን ላቅርብ የጀርመን ኮድ ካረቀቀት አንዱ ነው እኔ የሚገርመኝ አለ እኔ ድዛይን የማደርጋችው ኮሎኖች/አምዶች/በጣም ወፍራሞች ናቸው በሌሎች የተሰሩት ግን ጭራሮ ናቸው አለንና ቁጭ ለምን ስንለው ምንም አይነት የምህንድስና ስራ በውስጣቸው ስለሌለ ነው ሶፍት ዌር ግን ገብተው ወጥተዋል አለን ፡፡
  ክፍል ሁለት ይመልከቱ

  ReplyDelete
 32. ክፍል ሁለት
  ሌላም እንውሰድ በአንድ ከተማ የጋጠመኝኝ ላጫውታችሁ ከንቲባው አገር ወዳድ ነኝ ከሚሉ ሰዎች ነው አንድ ቀን ለከተማው ፕሮጀክት በመቅረጽ ድዛይኑና ሌሎች ዶቹሜንቶች ከጀርመን መንግስት ለኢትዮጽያ መንግስት ከሰጠው እርዳታ ወደ 20 ሚልዮን ብር እርዳታ አገኘሁኝ ወደ 7 ሚሊዮን ብር በሙሉ ተጠቀምኩበት ነገር ግን 13 ሚሊዮኑ ገና በመምጣት ላይ ሳለ እኔ ይህ እርዳታ ለማስፈፀም አዲስ አበባ ላይ መከራዮን እየበላሁ (በ70 ብር አበል የታክሲ አይጨምርም ሌሎች ወጪዎች አሉ)እያለሁ ተሳክቶልኝ ወደ መስሪያቤት ስመለስ ወድያውኑ በጣም የታወቁ ሽማግሌዎችና አባቶች ወደ ቢሮየ መጡ እንፈልግሃለን አሉኝ ደነገጥኩ ምንድን ፈለጋችሁ አልኳቸው እነሱም ለምንድ ነው ስራ እለቃለሁኝ የምትለው አሉኝ :: ወይ አምላኬ! እኔ አዲስ አበባ ፕሮጄክት ለማስፈፀም ነበርኩኝ እንጂ እንዲህ ያለ ሀሳብ የለኝም አልኳቸው:: እውነትም አልነበረኝም በሁኔታም በጣም ደንግጫለሁኝ::እንተ ትልቅ ሰው አይደለህም እንዴ እንዴት ትዋሻለህ አሉኝ እኔም በሁኔታው ገርሞኝ ግን ማን ነው እንዲህ ያለው አልኳቸው እነሱም ከንቲባው ከፕሮጀክቱ 1% ካልተሰጠኝ አልሰራም አለኝ አለን አሉኝ በእውነት በፍፁም ውሸት ነበር ሃሳቡም አላቀረብኩም አላልኩምም የሆኖ ሁኖ ስራው እቀጥላለሁኝ አልኳቸው እነሱም በሰጥሁዋችው መልስ አመስግነው ሄዱ፡፡ስራው መቀጠል ጀመርኩ እንደገና ከሳምንት በኋላ አባቶቹ መጡ ደግሞ ምን ተፈጠረ ብዮ ጠየቅክዎቸው ወረዱቡኝ ቃልህን ታጥፋለህ እንዴት እንዲህ ታደርገናለህ ባለፈው እቀጥላለሁኝ ብለሀን አልነበረም ወይ አሉኝ እኔም እና ምን ተፈጠረ ስላቸው እኛ ከሄድን በኋላ ለከንቲባው ቢለምንህ እምቢ አልከው አሉኝ በእውነት ውሸት ጭራሽኑ በዚህ ሳምንት አልተገናኘንም አልኳቸው በጣም አዘኑብኝ በዚህ እድሜ ውሸት ምን ያደርግልሃል አሉኝ የሚገርመው በቤተክርስቲያን የሚያውቁኝ ካህናትም ነበሩ ግራ ገባቸው እንዴት ከንቲባው ይዋሻል ብለው ይጠርጥሩት! ግራ ገባኝ ሶስተኛ ድግሞ እኔ በስራ ተወጥሬያለሁኝ እቅዴ 100 ሚሊዮን ብር በ4 ዓመት ለማስመጣትና በተግባር ለማዋል ደፋ ቀና እያልኩኝ ነበረ “ለዛውም በንፅህና” ወደከንቲባው ቢሮ ተጠራሁኝ አሁንም ሽማግሌዎቹ ተሰብስበዋል ይህ ነገር ዛሬ ጉዱ መውጣት አለበት አልኩኝ ያ ደፋር ከንቲባው የውሸት ፊት ለፊትም እንዲህ አልከኝ አልኝ ሽማግሌዎቹ በቃ አመኑት እኔም የአለም ውሸታም ተባልኩኝ በጣምም ተናደዱ እኔም ውሸት መሁንን እያወቁኝ ዝም ዝምምምም አልኩኝ እኔ ውሸትህን ነው ብል ማን ያምነኛል ካል አምላክ በቀር!ግን አሰብኩና አሃሃሃ ገባኝ እቅዱ በጣም ገባኝ ለካ ያ የእርዳታው ብር አስጎምጅቶት(እንደ እርጉዝ አምሮት አምርሮት ነው) ነው እንዲህ የሚያደርገኝ በትግርኛ አንድ ምሳሌ አለ ”ኪድ አይትበሎ ከም ዝኸድ ግበሮ” ይህም ማለት ሂድ አትበለው እዲሄድ ግን አድርገው ማለት መሆኑን ገባኝ ይገርማችኋል የከተማዋ በጀት 4 እጥፍ ሁኖላት ብዙ ስራ አጦች ስራ አግኝተው እግዚቢሔር አመስግነው ነጋዴዎች መንቀሳቀስ ጀምረው ነበር በጣም ደስ የሚል የ ኢኮኖሚ እቅስቃሴ ተፈጥሮ ነበር ግን ምንይደረግ ከንቲባውና ጓደኞች ያ ብር ፈለጉት! በቃ ፈለጉት! እንደ አንባሳ ቁምጥምጥ እድርገው ሊጨርሱት! ወይ አምላከ ኩሉ ስንት ነገር ነው ያለው!!! እኔም እያዘንኩኝ ስራ ለቀኩኝ እቅዴ መና ሁኖ ሊቀር መሆኑን ገባኝ ግን ውሸታም ሆንኩኝ ላገሬ ሌት ተቀን በመልፋቴ ውሸታም አስባለኝ ወይኔ!! እኔ በሌሌሁበት በቢሮ ሰራተኞች ወደ ውጭ የደወሉትን፣ እኔ ፊልድ በወጣሁበት፣ እኔ ያልደወልኩ መሆኔን በማስረጃ ቢረጋገጥም መክፈል አለብህ ተብዮ ከዚህ በተጨማሪ አንዳንድ ፕሮጀክቱ ለማስፈፀም ያወጣሁዋቸውን ወጪዋች በሽልማት የተሰጠኝኝ መሬት ሽጬ እዳዮን ከፍዮ ምንም ብር ሳይኖረኝ አንድ ጥሩ ሰው ለትራስፖርት ሰጥቶኝ ምስቴንና ልጄን ይዤ ወደ ሌላ ስራ ፍለጋ…….. ሄድኩኝ፡፡የሚገርማችሁ ይህ ነገር እስከላይ የመንግስት አካላት ቢደርስም ማንም ስለእውነታ ሳይጠይቀኝ እኔ ጥፋተኛ ተደረኩኝ አምላክ ይፍታው ብዮ ዝም ዝምምምም አልኩኝ የምንበላው ስላጣን የተሸለምኩትን ወርቅ ሽጬ ስራ እስካገኝ ድረስ በላነው ለካ ሽልማቱ ለዚህ ግዜ ነበር ይገርማል! ይገርማል እንጂ! ግን አምላክ ይመስገን አልተወኝም አሁንም እደዛ ደስ የሚሉ ፈተናዋች ዘመዶቼ ሁነው አብረን እየኖርን ነው፡፡እናም በመንግስትና በግል የምንሰራ ሰዎች ከውጫችን አገር ወዳዶች ከውስጥ ግን ተናጣቂ ተኩላዎች እየሆንን ሌሎችን እውነተኛ አገር ወዳዶች ስቃያቸው እያስበላናቸው ያለነው ከመጥፎና አፀያፊ ስራችን ብንቆጠብ ወንድማችን መክሮናል እናም በእውነት ሃገራችንን እንውደድ:: መቼስ አማርኛዮ በጣም ደስስስስስስስስስስስ ይላል አይደል ቋንቋው በደምብ አለመቻሌ ስለሆነ ሁላችሁም ሀሳቤን ብቻ ከተረዳችሁልን ይበቃኛል::
  ዳኒ በርታ
  አምላክም ይርዳህ
  ወስብሃት ለእግዚአ ኩሎ

  ReplyDelete
 33. pa..pa..pa..relly nice GOD bless you and your family.

  ReplyDelete
 34. ዲ/ን ዳንኤል እግእዚአብሔር አንተን እና ቤተሰብህን ይጠብቅህ::አሜን

  በጣም አስተማሪ የሆነ ስነ_ጽሑፍ ነዉ::
  እግእዚአብሔር የዉነት ልቦና ይስጠን::

  ReplyDelete
 35. for the one who want to build a school please find my adress from dani I aleady send it to him.I can help you Professionally.

  ReplyDelete
 36. የሀገር ወዳድነት መለኪያዬ የተሳሳተ እንደነበር የተረዳሁበት ቆንጆ ትምህርት፡፡
  እግዚአብሔር ሆይ ደካማነታችንን እርዳው!!!

  ReplyDelete
 37. tiru melikit new
  egiziabiher dikamih besew lib wist fire endiyafera yadirgilih
  legnam libona yisiten

  ReplyDelete
 38. Yam, I like "Your biblical proverb: Egziabher hoy dekamanetachenen erdawu!"
  thanks.

  ReplyDelete
 39. በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

  ትክክለኛ እይታ ነው ቃለ ህይዎት ያሰማልን

  ዳኒ እይታዎችህ ግልጽ የሆኑ እውነታዎች ስለሆኑ በዚሁ ቀጥልበት አምላክ በጉዞህ ሁሉ ስኬትን ይስጥህ

  ReplyDelete
 40. Hello,

  For the guy who said needs professional help to build schools, what kinds of professional helps do you need?

  ReplyDelete
 41. thank u teklehaymanot i will contact u soon

  ReplyDelete
 42. REALLY INTERESTING.... IT WOULD HAVE BEEN NICE IF THIS ARTICLE MAKES IT TO OUR COUNTRY AND RELIGION LEADERS TABLES...

  ReplyDelete
 43. ወንድም ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥልኝ

  እራሱን የቻለ ብዙ ሊያነጋገር የሚችል ጥሩ መንደርደሪያ ሃሳብ ነው። ሆኖም ፣ አንድ ኢትዮጵያዊ በሰንደቅ አላማው ለመኩራት እና ለመዋብ ፣ የግድ ሚር ዣክ በደረደሩት ሃሳብ ብቻ የተገለጸ የሃገር ወዳድነት መገለጫ መስፈርቶችን ሊያሟላ ግድ አይልም።

  ለምሳሌ ሚር ዣክ የደረደሯቸው አይነት፦ የአገር ፍቅር መገለጫ ሳይሆን ጥላቻ ፣ አገርን የሚያለሙ ሳይሆን የሚያወድሙ ክንውኖች ፣ በኢትዮጵያውያን ብቻ የሚፈጸሙ ሳይሆኑ ፣ በሰለጠኑት አለማት የሚኖሩ ዜጎችም የሚያደርጉት ነው። በየትኛውም ህብረተሰብ ውስጥ ፣ አገርን ወደ አዘቅጥ የሚመራ ተግባር ፈጻሚ ዜጋ ሞልቷል። ያንኑም ያህል ለአገር ተቆርቋሪ እና አገርን በሃላፊነት የሚያገለግል ዜጋ በሁሉም አገራት ውስጥ አለ። ጥሩውም ሆነ መጥፎ ባህርያት የሁሉም ዜጎች ባህርያት ናቸው። በአገራት ላይ መጥፎው ም ሆነ ጥሩው ነገር ጎልቶ የሚስተዋልበት ዋነኛ ምክንያቱ ግን ፣ የአገራቱ አስተዳድራዊ መዋቅር ነው። አዎን! የየትኛውም አገር ሁለንተና የሚወሰነው እና አገራዊ ቅርጹ የሚገመገመው በአስተዳደሩ ነው። “መንግስት የሚመራው ህዝብ ውጤት ነው” የሚለው የ እንቁላሏና የዶሮዋ ታሪክን ለእኛዋ አገር የማልቀበልበትን ምክንያት እግዚያብሄር በፈቀደ ጊዜ አብራራለሁ።

  ከፍያለው ካናዳ

  ReplyDelete
 44. +++

  Dn Daniel,Where are today's observations????
  "የተከበራችሁ አንባብያን

  ይህ ብሎግ በሚከተሉት ፕሮግራሞች መሠረት ጽሑፎችን ይለቅቃል

  ዓርብ
  ወጎች "
  Be strong with the help of God.
  Ke Ziwaye

  ReplyDelete
 45. thank you D/N Dani very observant as always. May god bless you & your familly.

  ReplyDelete
 46. መልእክቱ አስተማሪ ነው ግን የምንማረው መቼ ነው፡፡ እስኪ ያነበብነው ለላለላነበብነው እያስተላለፍን እንማማርበት፡፡ ያነበብነውም ለመለወጥ እንሞክር፡፡ ለዘዚህም እግዚአብሔር ይርዳን፡፡
  ዳኒ በርታ፡፡

  ReplyDelete
 47. It is true we Ethiopians have our own problems. It could be economic, social,.................However I don't think we are the only people in the world with such problems and difficulties. We have our own good and bad side like any other people in the world. If there are some jelous people in a Ethiopia we can't generalize all Ethiopians are jeleous, the same to all other weaknesses mentioned in the blog.

  Yes some Ethiopians are disrtuctive but there are other Ethiopians who are constructive..... So the best thing could be not to exaggerate our weaknesses but to capitalize on our strength!!!! Better for us to learn how our ancestors did what they did to create that famous Ethiopia!! Let us concentrate on that.

  ReplyDelete
 48. i need any kind of professional help that relates to a scool biulding from a to z

  ReplyDelete
 49. Kale Hiwoten Yasmlen Tgawen Yabzle Yegltle Dakon Daneil
  Gien Ye Grmeg Kelay Betstew Astyayit Fernjeu Absa Bihoen ale Frenj Yhen Siel Yamgeal Ale
  Gien Fernjuem Eko Yheneneu Neber Yalew
  Memkeat Beasbe Memkeat Bechea Honen1

  ReplyDelete
 50. ሃቅ ነው!!!!! Alem said.

  ReplyDelete
 51. Eleni ke-SyracuseJune 2, 2010 at 3:32 AM

  amazing truth!!!

  It will be very helpful if there is a way to distribute this truth for people through out the country. It helps us to see ourselves whether we really love our country, church, family & friends

  Let God help us avoid the pretentious love we have and give us genuine love!

  ReplyDelete
 52. እ/ር ኢትዬጵያን ይባርካት

  ReplyDelete
 53. ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር ይስጥልኝ በጣም አስተማሪ የሆነ ጽሑፍ ነዉ::

  ReplyDelete
 54. አቶ ከፍያለው ከካነናዳ እንዳሉት በእርግጥ ይህ አይነቱ ባህሪይ የሁሉም አገር ዜጎች ሊሆን ይችላል ግን ደግሞ እኛን ከሁሉም አጉልቶ እንድንነሳ የሚያደርገን በኛ ሃገር ያሉት አገርን ያለመጥቀም ስራ የሚያከናውኑት መብዛታቸው ከሀሃገር ገንቢው ይልቅ አጥፊው መብዛቱና ያመለካከት ችግር መኖሩ ያመለካከት ችግር ስል ሃገርን ከመንግስት ለይቶ አለማየት መንግስታት በተለያየ ጊዜ ይለዋወጣሉ ሃገራችን ግን ቀሪ ሃብታችን የሁላችን የጋራ ናት ስለዚህ በአንድ መንግስት/መሪ ላይ ተቃውሞ ሲኖረን ሃገራችንን በመጉዳት ስራ ባለመስራት፣ የተሰሩትን በማፍረስ መግለጽ የለብንም

  ReplyDelete
 55. this is for the one who is willing to help me professionaly {Teklehayimanot} D Daniel sayed he did't get any address can you please try to email him again i hope u will respond to this

  ReplyDelete
 56. yabrham yayesak yayakob amelake yaserawet gat egzabhare yehenen yatakadas hasabe banta laye hono selasaseben enamasegnawalen antenem yebarkehe zande ensalyalen.

  ReplyDelete
 57. Really Golden pen u have.

  ReplyDelete
 58. እስቲ ለተግባራዊነቱ እንድንነሳሳ ስለመፍትሄው ጀባ እንበል፡-
  በኔ በኩል የአንድ የደርግ ዘመን ተውኔት ጥቅስ መግቢያየዬ ይኹነኝና የህሊና ነጻነት መልካም ሥራ ነው በሚለው መርህ ለራሳችን፣ ለወገን፣ ለሀገር፣ ለዓለም ሁሉ በጎውን እናስብ! እናድርግ!
  የመንግስት ተቋማት፣ የመንግስት ደጋፊም ሆኑ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች፣ ዕድሮች፣ የተለያዩ ሕዝባዊ ተቋማት፣ ፎረሞች...ወዘተ ስለመልካም ስነምግባር እናስተምር!በተግበባርም አርአያ በመሆን ለማሳየት እንጣር! ለኛ ካለኛ ማንም የለንም፡፡ እግዚአብሔር ለሁላችንም አስተዋይ ልቡና ይስጠን!
  ዳኒ አሁንም ለወገንህ ብርሀን ለመሆን የፍቅር አምላክ እውቀቱን ይግለጽልህ!

  ReplyDelete
 59. "ዝንቱ ውእቱ ወልድሃ ለቤተክርስቲያን" እግዚአብሄር ይባርክህ

  ReplyDelete
 60. aune gna yelbe derese

  ReplyDelete