Sunday, May 16, 2010

ሥጋ በል ዕጽዋት


ብዙዎቻችን ሥጋ በል እንስሳት መኖራቸውን እናውቃለንም ተምረናልም፡፡ እናም አይገርመንም፡፡ ሥጋ በል ዕጽዋት መኖራቸውን ግን ብዙ ጊዜ ሰምተንም ተምረንም ስለማናውቅ ከመገረም አልፎ «እንዴት ሊሆን ቻለ?» የሚል ጥያቄንም ይፈጥርብናል፡፡ ሥጋ በል እንስሳትስ በክርናቸው ደቁሰው፣ በጥርሳቸው ዘንጥለው ይበላሉ፡፡ ለመሆኑ እነዚህ ሥጋ በል ዕጽዋት እንዴት አድርገው ነው ሥጋ የሚበሉት? ደግሞስ በምን ሆዳቸው ይፈጩታል? እያለ ጥያቄው ይቀጥላል፡፡

ሥጋ በል ዕጽዋት አፈጣጠራቸው እንደ ዕጽዋት አኗኗራቸው እንደ አራዊት ነው፡፡ ነፍሳቱ የሚያውቋቸው በተክልነታቸው አብበው ሲለመልሙ ነው፡፡ በውስጣቸው ግን የአውሬነት ጠባይ ስላለ የዋኾቹ ነፍሳት አትክልት ናቸው ብለው ሲጠጓቸው ረዥም ቅጠላቸውን ጥቅልል ያደርጉና ነፍሳቱን እምሽክ አድርገው ይበሏቸዋል፡፡

ከእስስት እና ከእንሽላሊት ያመለጡ ነፍሳት እንኳን በእነዚህ ሥጋ በል ዕጽዋት በቀላሉ ይጠቃሉ፡፡ የንብ ጥበብ፣ የቢራቢሮ ውበት፣ የጢንዚዛ ጩኸት፣ የተርብ ኃይለኛነት፣ የትንኝ ተናዳፊነት፣ አይበግራቸውም፡፡

ለምን?
እነዚህ ሥጋ በል ዕጽዋት መልካቸውም፣ ቁመናቸውም፣ አኳሃናቸውም፣ እንደ ዕጽዋት ነው፡፡ የሚኖሩትም ከዕጽዋት ጋር ከዕጽዋት መካከል ነው፡፡ እንደ ዕጽዋት አበባ አላቸው፤ ቅጠል አላቸው፤ ግንድ አላቸው፤ ሥር አላቸው፤ ልምላሜ አላቸው፡፡ እንደ ዕጽዋት ከመሬት ተነሥተው ወደ ላይ ያድጋሉ፤ አፈር እና አየር ይወስዳሉ፤ በሁለመናቸው ዕጽዋትን ይመስላሉ፡፡

ነገር ግን የዋኾቹ ነፍሳት ሊያውቁት የማይችሉ አንድ ድብቅ ጠባይ አላቸው፡፡ እርሱም ለሌላ ያልተገለጠ የአውሬነት ጠባይ በውስጣቸው አለ፡፡ ይህንን ጠባይ እንኳንስ ነፍሳቱ ሰውም ያወቀው በቅርቡ ነው፡፡ በባህላዊው ዕውቀት ሥጋ የሚበላ አውሬ መኖሩን እንጂ ሥጋ የሚበላ ተክል መኖሩን የሚናገር ታሪክም፣ ተረትም፣ ወግም፣ አባባልም የለም፡፡

ይህ ጠባያቸው ነው እንግዲህ ሳይደክሙ አድፍጠው ግዳያቸውን በእጃቸው ላይ እንዲጥሉ ያደረጋቸው፡፡ የዱር አራዊት አንድ ጊዜ አውሬ መሆናቸው በሁሉም ዘንድ ስለታወቀ፤ በአራዊት እንበላለን ብለው የሚሰጉ እንስሳት ብዙዎች ናቸው፤ እያንዳንዱ እንስሳም ከእነርሱ የሚያመልጥበትን የየራሱን ጥበብ በዘመናት ብዛት አከማችቷል፡፡ ያደፍጣል፣ ያመልጣል፣ ይሸውዳል፣ ይመሳሰላል፣ ቀለሙን ይቀይራል፣ ጊዜ ይመርጣል፤ ይናደፋል፤ ይቧጭራል፤ ከባሰበትም በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ይጋደላል እንጂ በቀላሉ እጁን አይሰጥም፡፡

ይህንን የግዳዮቻቸውን ጠባይ ያወቁት አራዊትም ለመብላት የሚያስቧቸውን እንስሳት የሚያጠቁበት አያሌ ዘዴ ዘይደዋል፡፡ ኃይል፣ ጉልበት፣ ጥበብ ይጠቀማሉ፡፡ ጊዜ መርጠው አድብተው ያጠቃሉ፡፡ ግዳይ እንዲህ በቀላሉ አይጣልምና ብዙ ድካም እና ልፋት አለባቸው፡፡

ሥጋ በል ዕጽዋት ግን ይህ ሁሉ የለባቸውም፡፡ ጠባያቸውን አሳምረው፣ ዕጽዋትን መስለው፤ እስከ ጊዜው ድረስ አውሬነታቸውን በልምላሜያቸው እና በአበባቸው ሠውረው ጸጥ ይላሉ፡፡ ነፍሳቱ እንደ ለመዱት አበባ ለመቅሰም እና ቅጠልን ለመብላት፣ ለእረፍት እና ለመዝናናት ወደ እነርሱ ሲጠጉ ግን ተክልነታቸው ያበቃና አውሬነታቸው ብቅ ይላል፡፡ የገባ አይወጣም፡፡ የተያዘ አያመልጥም፡፡

አሁን አሁን ከሰዎች መካከል ማኅበረሰቡን እያስቸገሩ ያሉት ሥጋ በል ዕጽዋት ናቸው፡፡

እነዚህ ሥጋ በል ዕጽዋት በመልካቸው፣ በቁመናቸው፣ በንግግራቸው፣ በአስተሳሰባቸው፣ በአቀራረባቸው ፍጹም ትኁታን፣ ደጋጎች፣ ቅኖች፣ ታዛዦች፣ አስተዋዮች፣ ታማኞች፣ የተማሩ፣ የተመራመሩ ይመስላሉ፡፡ ውስጣቸው ግን ተቃራኒ ነው፡፡

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ አንድ እንግሊዛዊ ነበረ፡፡ እንግሊዝ ጀርመንን መምታት አለባት እያለ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይናገራል፡፡ የእንግሊዝ መንግሥት የሚወስደውን ማንኛውንም ርምጃ ይደግፋል፡፡ መቼም የእንግሊዝኛ ንግግሩ ለጉድ ነው፡፡ ከቃላት፣ ከሰዋስው፣ ከአባባል አንዳች አያዛንፍም፡፡ አገሬው የሚሳሳታቸውን የተለመዱ ስሕተቶች እርሱ ጨርሶ አይሳሳ ታቸውም፡፡ ስለ እንግሊዝ እና ስለ እንግሊዛዊነት የርሱን ያህል ሰባኪ እና ተቆርቋሪ አልነበረም፡፡ አንዳንዴ መንግሥት ያመናቸውን ስሕተቶች እንኳን እርሱ ስሕተት አይደሉም ብሎ ይከራከራል፡፡

ታድያ የእንግሊዝ የስለላ ድርጅት ተጠራጠረው፡፡ ተጠራጠረውና ክትትሉን በጥብቅ ቀጠለ፡፡ ከብዙ ምርመራ በኋላ ታድያ የጀርመን ሰላይ ሆኖ አገኘው፡፡ አለምክንያት እንደዚያ ለምለም ተክል አልሆነም፡፡ ውስጡ ሥጋ በል ቢሆን ነው፡፡

እየደጋገመ ወደድኩሽ ይለኛል
ማርያምን ይኼ ሰው ልቡ ይጠላኛል
ያለችው የገጠር ዘፋኝ ይህንን የእንግሊዝ ሥጋ በል ዕጽ ጉዳይ ቀድማ ሳትደርስበት የቀረች አይመስለኝም፡፡

ስለ ነጻነት ይሰብካሉ፣ ስለ ሴቶች መብት ይከራከራሉ፣ ስለ ትዳር ይቆረቆራሉ፣ ስለ ሕፃናት ይራራሉ፤ ሃይማኖትን ያጠብቃሉ፤ ምግባርን ያከርራሉ፤ ገንዘብን ይጠላሉ፤ ክብርን ይንቃሉ፤ ዝናን ይጠየፋሉ፤ ሥልጣንን ይርቃሉ፡፡ ይህንን ሁሉ የሚያደርጉት ግን አምነውበት፣ ወድደውት እና ውስጣቸው ከዚህ ተሠርቶ አይደለም፡፡ ጊዜ እስኪያገኙ ድረስ ብቻ ነው፡፡

«አንገት ደፊ፣ ሀገር አጥፊ» የሚለው አባባል ማኅበረሰባችን እነዚሀን ሥጋ በል ዕጽዋት በመጠኑም ቢሆን እንደ ደረሰባቸው ያመለክታል፡፡ ሁሉም አንገት የደፉ ሰዎች አገር ያጠፋሉ ማለት አይደለም፡፡ ነገር ግን ተክል መስለው ለስልሰው ውስጣቸው አውሬ የሆኑ ሰዎች አውሬ መሆናቸውን በግልጥ ካሳዩ ሰዎች ይበልጥ ይጎዳሉ ማለት ይመስለኛል፡፡

ፀጉሩን ቆጣጥሮ፣ ያረጀ እና የተቀዳደደ ልብስ ለብሶ፤ ፊቱ ኮስተር፤ ዓይኑ ደፍረስ፤ ጡንቻው ፈርጠም፣ ጣቱ ረዘም ያለ፤ ሎቲ አንጠልጥሎ ሠንሠለት ጠቅልሎ የሚመጣን ጎረምሳ ማን ያምነዋል? የቻለ ይሸሸዋል፤ ያልቻለ በዝምታ ያሳልፈዋል፤ ከባሰም ይተናኮለዋል፡፡ እርሱን የሚያምን፣ የሚቀበልና የሚያስተናግድ አይገኝም፡፡ አለባበሱን ሽክ አድርጎ፤ ፀጉሩን አሳምሮ፤ ልብሱን ቀያይሮ፤ ጫማውን ወልውሎ፤ የፊልም አክተር መስሎ ቢመጣ ግን «ኖር» ባዩ «ልተዋወቅህ» ባዩ ብዙ ነው፡፡ የሚጠራጠረው ቀርቶ «መጠርጠር» የሚለውን ቃል በእርሱ አጠገብ የሚያወራ አይገኝም፡፡

ግን «በቆብ ውስጥ ያለን ኃጢአትና በኮት ላይ ያለን ጽድቅ» ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ ይባላል፡፡ ይበልጥ መጠንቀቅም ገጽታው የሚያስፈራውን አይመስለኝም፡፡ እርሱማ ሁሉም ያፈጥጥበታል፡፡ ከባዱስ በለስላሳው የዕባብ ቆዳ ውስጥ ያለው መርዝ ነው፡፡

እስኪ አስተውሉ፡፡ በሀገራችን አያሌ ሕፃናት የተደፈሩት በጠላቶቻቸው እና በሚፈሩት ሰው፣ አይደለም፡፡ በጣም በሚወዷቸው፣ በሚቀርቧቸው፣ በሚያምኗቸው ሰዎች ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ለሕፃናቱ ከወላጆቻቸው በላይ ደግ እና ቅርብ ሆነው ነው ድርጊቱን የሚፈጽሙት፡፡ ድርጊቱን ፈጽመው ለመሠወር የሚያስችላቸውም ሥጋ በል ዕጽዋት በመሆናቸው ነው፡፡ ገጽታቸው፣ አለባበሳቸው፣ ንግግራቸው እና በማኅበረሰቡ የሚታወቁበት ጠባይ በውስጣቸው ከደበቁት ጠባይ በተቃራኒው እና እጅግ በደግነት የተሞላ ነው፡፡ እናም ይህንን አስነዋሪ ተግባር ይፈጽማሉ ብሎ ማንም አይጠረጥርም፡፡ አሁን ዕጽዋትን ሥጋ ይበላሉ ብሎ ማን ይጠረጥራል?

እንደ እባብ ብልህነትን ትተው እንደ ርግብ የዋሕ ብቻ ይሆኑ እኅቶቻችን ብዙ ጊዜ የሚደፈሩት በየሠፈራቸው በሚያስፈራሯቸው፣ በሚዝቱባቸው እና ይጎዱናል ብለው በሚያስቧቸው ጎረምሶች አይደለም፡፡ እንዲያውም እነዚህ ጎረምሶች ማኅበረሰቡ በክፉ ጠባያቸው ስለሚያውቃቸው ይጠነቀቃቸዋል፤ ሊያደርጉት ሲያስቡም ይነቃባቸዋል፡፡ ፖሊስም በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በዓይነ ቁራኛ ይጠብቃቸዋል፡፡

አደገኞቹስ ሥጋ በል ዕጽዋት ናቸው፡፡ ሰላምተኞች፤ ትኁቶች፤ ለእኅቶቻችን ተቆርቋሪዎች፤ ከአፋቸው የማር ወለላ ጠብ የሚል፤ ተናግረው አሳማኞች፤ አለባበሳቸው እና አካሄዳቸው በጨዋነት የተሞላ፤ ሲቀርቧቸው ክፉ ነገሮችን ሁሉ አውጋዦች፤ ኃጢአትን እና ወንጀልን እንኳን ሊፈጽሙ፣ ቃሉን ሰምተው የሚያውቁ የማይመስሉ እነዚህ ናቸው የእኅቶቻችን ጠላቶች፡፡

መቼም ደግን ነገር የሚጠላ የለም፡፡ ርግቦቹ እኅቶቻችን ለፍቅር የሚመች፤ ለኑሮ የሚደላ፤ ለትዳር የሚሆን ጨዋ የተማረ፤ እንኳንስ እኔን ሊያሰናክል ከመሰናከል የሚጠብቀኝ፤ ብረት መዝጊያ የሚሆን አገኘን ይሉና በቅጠሉ ሊያርፉ፤ ከአበባው ሊቀስሙ ጠጋ ይሏቸዋል፡፡ ያን ጊዜ ነው የዕጽዋቱ ሥጋ በልነት ብቅ የሚለው፡፡ «ሰው የሚጠላውን ኃጢአት ደጋግሞ ይሠራዋል» ይል ነበር ጋሽ ግርማ፡፡ በአፉ እየደጋገመ ያለ ቦታውና ያለ ጊዜው የሚያወግዝ ሰው፣ ያንን ነገር ይፈልገዋል ማለቱ ነው፡፡

እነዚያ የተጠቁ እኅቶች ለማን ይናገራሉ፡፡ እነዚህ ሥጋ በል ዕጽዋት የሚታወቁት በተክልነታቸው እንጂ በሥጋ በልነታቸው አይደለማ፡፡ ማን ያምናል፡፡ እርሷ ከምትናገረው ይልቅ እርሱ የሚናገረው ይታመናል፡፡ ይህ ተክል ሥጋ በልቷል ብትል ማን ያምናታል?

ከጋብቻ በኋላ የቤት አልጋ የውጭ ቀጋ፤ የቤት እሾክ የውጭ መልአክ፤ የቤት ንፉግ የውጭ ደግ የሆኑ የትዳር አጋሮችኮ ከጋብቻ በፊት እንደዚያ አልነበሩም፡፡ ወንዱም ስትጠሪኝ አቤት ስትልኪኝ ወዴት እላለሁ፤ ከልጅሽ በታች ከሠራተኛሽ በላይ ሆኜ እታዘዝሻለሁ ሲል ነበር፡፡ ሴቷም ብትሆን እንደ ምንጣፍ ተነጥፌ፤ እንደ እናት ተንሰፍስፌ፤ እንደ ጉዝጓዝ ተጎዝጉዤ፣ እንደ ሎሌ ታዝዤ ብላ ነበር የገባችው፡፡ ዛሬ ዛሬ አንዳንዶቹ ከትዳር በፊት የኖሩትንና በትዳር ውስጥ ያሉበትን ሁኔታ ሲያስተያዩት ፊልም ያዩ እንጂ የነበሩበት አይመስላቸውም፡፡

«ትዳር ምን እዳ ነው ትዳር ምን እዳ ነው» ተብሎ ሲዘፈን እንዴት እንዲህ ይባላል? ይሉ የነበሩት ሰዎች ዛሬ ዛሬ እነርሱ ራሳቸው ግጥም እየጨማመሩ መዝፈን ጀምረዋል፡፡ ሥጋ በል ዕጽዋት ገጥመዋቸው፡፡

በአንዳንድ አስነዋሪ ተግባራት ውስጥኮ በሁለት እጅ የማይነሱ ታላላቅ ሰዎች፣ ባለ ሥልጣናት፣ የሃይማኖት መምህራን፣ ታዋቂ ሰዎች ሲገኙ ፖሊስ እና ኅብረተሰብ የሚደነግጠው ዕጽዋት ሥጋ ይበላሉ ብሎ ስለማያሰብ ነው፡፡ በግብረ ሰዶማዊነት፤ በአደንዛዥ ዕጽ ንግድ፤ በሴተኛ አዳሪነት መስፋፋት፤ በሕፃናት ንግድ፤ በኮንትሮባንድ ሽያጭ፤ ጉቦ በመቀበል እና በማቀበል፤ በሕገ ወጥ መንገድ ሰዎችን ወደ ውጭ በመላክ ወንጀሎች ውስጥኮ ብዙ ሥጋ በል ዕጽዋት ይገኛሉ፡፡

ስፖርት እናሠራለን፤ ሙዚቃ አለማምደን ታዋቂ እናደርጋለን፤ ፊልም አሠርተን እናሸልማለን ብለው የዋሆችን እየቀረቡ የሚያታልሉትኮ ሥጋ በል ዕጽዋት ናቸው፡፡ ሲያዩት ቀጣሪ ነው፣ ሥራ አስኪያጅ ነው፣ የተከበረ ሰው ነው፡፡ ውስጡ ሥጋ በል ነው፡፡ ሲያዩት የፊልም ባለቤት፤ የፊልም ዳይሬክተር ነው ውስጡ የእኅቶቻችንን ሥጋ የሚበላ ሥጋ በል ዕጽ ነው፡፡ ሲያዩዋት እንደ እናት ርግብግብ፣ እንደ እኅት ቅሩብ ናት ነገር ግን ወንድሞቻችንን እና እኅቶቻችንን ለርካሽ ዓላማ የምታሰልፈው ሥጋ በል ዕጽ እርሷ ናት፡፡

ዛሬ ዛሬኮ የንግዱን ሚዛን ያዛቡትና ማጭበርበርን እና ሙስናን ባህል እንዲመስል ያደረጉት ብዙዎቻችን የምንጠራጠራቸው ዓይነት ነጋዴዎች አይደሉም፡፡ እነርሱማ መውጫ መግቢያቸው፣ መብያ መጠጫቸው የታወቀ ነው፡፡ የችግሩ ዋና ፈጣሪዎች «አያደርጉም፤ ደግሞ ምን ጎድሏቸው፤ ኧረ እነርሱ ይህንን አይሠሩም» እየተባለ የሚነገርላቸውና ሲያዩዋቸው እንደ ተክል አረንጓዴ፣ እንደ አበባ ውብ፣ ውስጣቸው ግን ሥጋ በል የሆኑት ናቸው፡፡

ቤተ እግዚአብሔርን የሚዳፈረው ምሥጢሩን የሚያውቀው ነው ይባላል፡፡ አንዳንድ ጊዜኮ የእምነት ሰዎች በሚባሉት ዘንድ የሚሠራውን ግፍ፣ በደል፣ ጭካኔ፣ ተንኮል፣ ኃጢአት ያህል በተራው ሕዝብ ሲሠራ አይታይም፡፡ ለቤተ መቅደስ ቅርብ ሆነው ከእግዚአብሔር የራቁ ሰዎች ሥጋ በል ዕጽዋት ናቸው፡፡ አለባበሳቸው፣ አዋዋላቸው፣ አነጋገራቸው፣ መዓርጋቸው፣ ሥልጣናቸው፣ እንደ አትክልት የለመለመ፣ አረንጓዴ፣ ሰላም እና ፍቅር የሞላበት፣ ፍትሕ እና ርትዕ የሰፈነበት ይመስላል፡፡ ወደ ውስጣቸው ሲገቡ፣ በጥላቸው ሥር ሲያርፉ፤ አበባቸውን ለመቅሰም ሲጠጉ ግን የሚያዩት ነገር እንደ ሎጥ ሚስት አድርቆ የሚያስቀር ነው፡፡

አሁን ችግሩ እነዚህን ሥጋ በል ዕጽዋት እንዴት እንለያቸው? የሚለው ነው፡፡ እኔ የዚህ ምሥጢር አልተገለጠልኝም፡፡ የተገለጠለት ካለ ግን ምናለ ቢገልጥልን፡፡
                  
                               ይህ ጽሑፍ ባለፈው ቅዳሜ በሮዝ መጽሔት ላይ ወጥቷል

33 comments:

 1. Actually I read it on "ROSE" magazine and amazed on it. As usual you are feeding us with important ideas and reflections. Those carnivore plants are catching animals by attracting them with their interesting leaves, flowers and pollen grains. The way you compare and contrast with such personalities is fantastic. As social critic is one of the systems to educate the society, I support you to continue in this way.

  Let God be with you Amen!

  ReplyDelete
 2. God bless you. Have you published the book of your compilations?

  ReplyDelete
 3. yes, it is in the printing house, it may be publish soon, according to the good will of electric corporation.

  ReplyDelete
 4. Haha, you're not only a social critic, but also a good humourist. By the way, didn't you find an equivalent Amharic word for 'BLOG'?

  ReplyDelete
 5. I did not found the appropriate amharic word for "blog', If some one welcome.

  ReplyDelete
 6. Another excellent piece as usual!!You never disappoint me in filling my insatiable appetite for a good writing.
  I would be using your comparison to suggest one solution for the problem of the " sega bel etsawat's" of the church.As botanists and biologists would have enlisted ,charterized, identified and named those plants the same should be done when those people are identifed in the church.I can see why that may not work from the very commandemnts of the Lord ('...Yemejemriawn dengay tal...". But to carry an incurable infection and voracious preditors within the church would be more crucial for the Church's very existence.
  Keakebrot gar.
  Mulugeta

  ReplyDelete
 7. tanks dani!! you are great man!"ethiopia endante aynet sew tefelgaleh". god bless you.

  ReplyDelete
 8. በዚህ ጽሑፍ ላይ የማልስማማበት ነገር አለኝ። ምክንያቱም ጽሑፉ ገና ለገና ይሆናል የሚል ስሜት በሰዎች መካከል እየፈጠረ ፍቀርን የሚያሳጣና ሁል ጊዜ ሰዎች በጥርጣሬ እንዲተያዩ የሚያደርግ ስለሆነ ነው።
  አንድ ሰው ይኽ ነው ሊባል የሚችለው የዚያ ባሕርይ መገለጫዎች ሲታዩበት ብቻ ነውና።በርግጥ በየጊዜውና በየቦታው እንደእስስት የሚገለባበጡ ሰዎች መኖራቸው የታወቀ ነው። ይህ ግን ሆነው ሲገኙ ብቻ ነው የሚታወቀው እንጅ ሊሆን ይችላል ብሎ ኩነኔ መግበት የሚያስፈልግ አይመስለኝም።
  ደግሞም አንድ ሰው በውስጡ የተደበቀውን ነገር ለመፈጸም ሲፈልግ ወትሮ የራሱ ያልሆኑትን ባሕርያት ቀድሞ ስለእርሱ ከምናውቀው በተለየ መልኩ ሲያደርግ ይስተዋላል እንጅ በደምሳሳው ሰውን ሁሉ ወደመጠራጠር የሚወስድ ድምዳሜ ላይ የሚያደርስ መሆን የለበትም። የዚህ ጽሑፍ መንፈስ ይህ ከሆነ አቀራረቡ በዚህ መልክ መሆን የለበትም።አንዳንድ ጊዜም ሰዎች ቀድሞ ከነበሩበት ጠባይ ተላቀው ወደ ተሻለው ምግባር ሲለወጡ የማንነታቸው መቀየር በጥርጣሬ እንዲታዩ ሊያደርጋቸው አይገባም።እኔ እነደማስበው የዚህ ጽሑፍ ይዘት በወንወጀል ምርመራ ማጣራት ሂደት ያለውን አካሔድ መምሰል ነው ያለበት።አንድ ሰው ወንጀለኛ የሚባለው ወንጀሉን መስራቱ በምርመራ ሲረጋገጥ ብቻ ነው። ጥፋተኝነቱን ማረጋገጥ ባይቻል ግን የሆነ ወንጀል ተፈጽሟልና ወንጀሉን ሊፈጽም የሚችለው ሰው ብቻ ስለሆነ ሰው ሁሉ በወንጀል ተጠርጣሪ ነው ሊባል እንደማይቻል። ይህ ሐተታ ግን አንዳንድ ሰዎች ምልክት በግልጽ እየታየባቸው በቃልም በስራም ከተመሰረተው ወይንም ከታወቀው የተለየ እየፈጸሙ ያ ማለት ይሔ ነው እንዲ ያልኩት እንዲህ ለማለት ነው እያሉ ለሚዘባርቁ አይደለም።

  ReplyDelete
 9. Dn በዝምታ

  in one part I do agree with yours ------------this days I do understand why our father become scarifies their live for truth ,

  and this kinds of society did not came with out scratch life is so diffeclut ,
  do u remmber abel, and kayel if u are honest u will be killed like Abel very soon , if u does not to be killed , u will be expert kayel (ሥጋ በል እንስሳት ) it is on your hand

  ReplyDelete
 10. Dn. Daniel may God give you his grace for you valuable lessons you are posting. In this world at this time we need to be more critical on our vision for life. It is in this kinds of articles that we can come to the light. Please, brother don't listen to both isle (Praise as well us insult from people). Be dead for these and do what you are give to do.
  About Amharic name of blog (another blog, Deje Selam has already suggested "ጡመራ"). Do you think it is acceptable? Comment on it.

  May God's blessing keeps us in his house.

  ReplyDelete
 11. +++

  Kalehiwot yasemalin! Dn. Daniel,

  I think we can say God only knows those who are real and those who are fake as Simon meseri!
  In secular life, God knows who the real people are as He chose David as King from his handsome brothers. So, the answer to your question how we can identify "those plants who eat meat" is by committing our way to God. ps.36:5!!!
  "The fear of the Lord is the beginning of knowledge" proverb 1:7

  May God help us!

  ReplyDelete
 12. I have nothing more to say than "AMAZING". although i have read almost all your articles On Addis Neger and on this blog, i still can't Waite to see your book and I hope you will add new articles too.
  May GOD be with you.

  ReplyDelete
 13. d/n daniel,
  bezu tsehufochen ewed neber. yezarew gen asferagn ... "sega bel etsewat" ehon yehon beye?

  ReplyDelete
 14. Dany,I really appreciate your contribution.May God give you the courage.

  ReplyDelete
 15. thank u dani
  we r human being this means we can't know by our limited knowledge but God show us one important thing i.e. LOVE(no limit) so we should exercise this love then God knows everything even what we thought in our heart again this means identify "siga beale" and others. can we know how much "siga beales" pass us till know? no it is not necessary to know that is not our responsibility. but it doesn't mean that we should be always full as bird but we should be wise as snake(but it has limit and we should not worry)as bible says.
  but leulchineme libona yistene
  selame

  ReplyDelete
 16. D/N Daniel

  It is correct, but i afraid people may be too much Suspicious. May God help us to identify those Carnivores plants!
  Keep on Contemplating.

  ReplyDelete
 17. Dear Dn Danny
  Thank you for the lesson ...We can not deny that it has become like a life style in the majority of our society to behave like "sigabel" till they get right time to attack...I can mention alot of examples of this phennomena, I even have personal experience...
  GOD MAY BLESS YOU.

  ReplyDelete
 18. Dear Dn. Daniel,

  Ahun ahun eyeferahu yalehut... anten kerbo ketichit mamlet ayichalim yimilewun neger newu! Esti anten yemiyasdesitu sewoch degimo tsafilign?

  Metifo mehonin feligo yemigebabet ale bileh taminaleh? Ene enja!? Yemigermewu mejemeriya leselamta sikerbuh enkuwan yemitasayewu yefit getsita lene yikebdegnal. Andande min endemiferalih tawukaleh yeAdinakiwoch mebzat endaytilih newu; ewunet "sileEne negeregn bileh bititeyikegn" anten kerbo mamaker betam kebad sewu neh-atsatsafih gin fitsum negn yemitil yasmesilehal.

  Silezih ewunetan metsaf tiru hono sale... endewu tiru neger fetsimo altefeterem ayinet atsatsaf gin kebed yemil yimeslegnal. Ketesasatiku arimegn.

  Kantew yemimar wondimih negn.

  ReplyDelete
 19. What a fantastic article !!!mindfull consideratinon and systematic explanation .
  It is great .God bless you brother.

  Semone K

  ReplyDelete
 20. ስጋ በል ዕጽዋት መኖራቸውን መስማት፤ ለመጠንቀቅ ይረዳ እንደሁ እንጂ ሰውን አትመኑ የማለት ያህል አይደለም፡፡ ‹‹የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡ በውስጣቸው ግን ነጣቂ ከሆኑ ተኩላዎች ተጠበቁ›› እንደሚለው አምላካዊ ቃል ያለ ነው፡፡ ከተክሎች መካከል ስጋ የሚበሉ አሉ ማለት ተክሎች ሁሉ ስጋ መብላት ጀመሩ ማለት አይደለም፡፡ ከሰዎች መካከል ስጋ በል ዕጽ ወደ መሆን የተሸጋገሩ ሰዎች ይህንን ጠባይ ያመጡት እንደ ተክሎቹ በተፈጥሮ አይደለም፤ ቀስ እያሉ ተምረውታል ወይም ተለማምደውታል፡፡ ማናችንም ብንሆን እንደነዚህ ዕጸዋት የመሆን ዕድል አለን፡፡ስለዚህም ይህንን ጽሑፍ ስናነብ ሌሎች ሰዎችን እያሰብን ሳይሆን ለኔ ብለን ቢሆን ፍሬ ይኖረዋል፡፡ ቢያንስ በሁለት መንገድ ሁላችንንም ይመለከተነናልና ራሳችንን ማየት ብንችል መልካም ነው ብዬ አስባለሁ፡-
  1. ማንም ሰው እንደነዚህ ስጋ በል ዕጸዋት ሆኖ አልተፈጠረም፡፡ ይህንን ጠባይ ያዳበረው ወይም የተማረው በሂደት ነው፡፡ አስተዳደግ ፤አኗኗርና የመሳሰሉት ነገሮች ለውጠውታል፡፡ እኛም ዛሬ እንዲህ የሆንን መስሎ ባይሰማን እንኳን፤ ካልተጠነቀቅን ነገ፤ ዛሬ አውሬ ብለን በጠራናቸው ሰዎች ቦታ ራሳችንን እንደማናገኘው ዋስትና መስጠት የሚችል የለምና ጠንቀቅ ማለቱ ይበጃል፡፡
  2. በመተማመንና በመጠንቀቅ መካከል ያለውን ልዩነት አንድነት በማስረዳት ጊዜ አላጠፋም፡፡ ታላላቆቹን መሪዎች፤ መምህራንና አገልጋዮች፤ መልካሞቹን ሰዎች (አንገት ደፍተው የሚኖሩትንም ቢሆን) እንደማንኛችንም ሰዎች መሆናቸውን አስበን ወደ አውሬነት ተለወጠው እኛንም ራሳቸውንም ከመጉዳታቸው በፊት መንገዱን በማጠር ብናግዛቸው መልካም ነው፡፡ ‹‹ታማኝ የምትለው ሰው ሁል ጊዜ ታማኝ እንዲሆን ከፈለግህ በርህን መቆለፍህን አትርሳ›› እንደሚባለው ማለት ነው፡፡
  በሌላ በኩል ደግሞ ጸሃፊው በስጋ በል እጸዋት የመሰላቸው ታላላቅ ሰዎች የሃይማኖት መሪዎችና በማህበረሰቡ የተወደዱ ሰዎች ብዙ ጊዜ ራሳቸውም የስጋ በል እጽ ወጥመድ የሚሻቸው ናቸው፡፡ ድንግልናው አስፈርሰዋለሁ፤ ቆቡን አስጥለዋለሁ ከማእረግ አዋርደዋለሁ ብለው በሰው ህይወት የሚወራረዱ፤ ልጅ መስለው ቀርበው አባቶቻቸውን፤ ተማሪ መስለው መምህራኖቻቸውን ለማሰናከል የሚተጉ ስጋ በል ዕጸዋት መኖራቸውም ይታወስ ዘንድ ይገባል እላለሁ፡፡
  በመጨረሻም እንዲህም አለ እንዴ ብለን መፍራት ሳይሆን መጠንቀቁ መልካም ነው፡፡ ጉዳዩ መነሳቱም ጥሩ ነው ቢያንስ ሰውረን ብለን ለመጸለይ ያነቃናል፡፡ ወትሮውንም ሰውን ማመን ቀብሮ አለች ቀበሮ እያልን ለምንተርት ግን በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ እንዳይሆንብን መልዕክቱን በጥሞና ተረድተነው ያለግብዝነት በፍቅር እንኑር፡፡ እንደ ርግብ የዋህ እንደ እባብ ልባም ብንሆን ከስጋት ነጻ መሆን እንችል ነበር፡፡ ችግሩ ወይ ርግብ ብቻ ነን ወይ እባብ!!
  ዳዊት፡፡

  ReplyDelete
 21. የሰው ሆዱ የወፍ ወንዱ አይደል የሚባለው ጽሁፉ ሁሉም ሰው ልክ እንደ "ሥጋ በል ዕጽዋት" ባይሆንም ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን የሰው ልጅ ባህርያት በጣም እየተለወጠ ያለበት ሁኔታ እንደተፈጠረ ሰንበትበት ብሎዋል፡፡ እንደውም አንድ አባባል ትዝ አለኝ ባልሳሳት "ምድር የተሸከመችን አታውቀወምና ሰው ነው ብለህ የተጠጋህው አውሬ ሆኖ እንዳይበላህ ተጠንቀቅ" የሚል አስተውሳለሁ ለማንኛውም ግዜው ጥንቃቄ የሚጠይቅና ማሰተዋል በጣም መኖር እንዳለበት ይሰማኛል፡፡እንደውም በአንድ ስብከትህ ኃጢያት ሲለመድ እንደ ጽድቅ ይቆጠራል ያልከው ትዝ ይለኛል፡፡
  ለኔ ከዘህ ምንባብ እንደተረዳሁት ከሆነ ሁሉም ሰው ሥጋ በል ዕጽዋት አይነት ባሕርይ ላይኖረው ይችላል ነገር ግን ወደፊት ማን ያውቃል? የሰው ልጅ ኃጢያትስ ቀንሰዋል? ወደ እግዚአብሔርስ ለመመለስ ምን ያህል ፍላጎት አለው? እና የመሳሰሉት ነገሮች መልስ እምብዛም እያገኙ ስላልሆነ ነገን በዛሬ መነጽር የሚያሳየን ጽሁፍ ነው፡፡
  ዲ.ን ዳንኤል ላንተ ቃለ ህይወት ያሰማህ ለሁላችንም ማስተዋልን ያድለን፡፡

  ReplyDelete
 22. ጌታነህ ሻMay 18, 2010 at 12:33 PM

  ሆሆ……. ይህም አለ ለካ!! ግን እግዚአብሔር ይጠብቀን እንጅ ስንቱን ተጠራጥረን ከስንቱ ተጠንቅቀን እንችላለን??

  ReplyDelete
 23. d/n daniel,
  bezu tsehufochen ewed neber. yezarew gen asferagn ... "sega bel etsewat" ehon yehon beye?
  በመጨረሻም እንዲህም አለ እንዴ ብለን መፍራት ሳይሆን መጠንቀቁ መልካም ነው፡፡ ጉዳዩ መነሳቱም ጥሩ ነው ቢያንስ ሰውረን ብለን ለመጸለይ ያነቃናል፡፡ ወትሮውንም ሰውን ማመን ቀብሮ አለች ቀበሮ እያልን ለምንተርት ግን በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ እንዳይሆንብን መልዕክቱን በጥሞና ተረድተነው ያለግብዝነት በፍቅር እንኑር፡፡ እንደ ርግብ የዋህ እንደ እባብ ልባም ብንሆን ከስጋት ነጻ መሆን እንችል ነበር፡፡ ችግሩ ወይ ርግብ ብቻ ነን ወይ እባብ!!

  ReplyDelete
 24. Danni,
  It is a very good story. I like the analogy and the deep-rooted wisdom you have been able to tell us. I know we can do away with one bad thing abd substitute with another one easly....Let us try...Egziyabeher Kale Hiwot Yasemeh...

  ReplyDelete
 25. WHEN I READ THIS ARTICLE I REMEMBER ONE TRUE STORY WRITTEN ON HAMER METSIHET . IT WAS ABOUT ONE BOY AND GIRL.INFLUENCED BY HER PEER AT SCHOOL, SHE FALL IN LOVE WITH HIM. SHE WAS SO MUCH IMPRESSED BY HIS ADVICE AND LIFE OBJECTIVES. HE TOLD HER MANY TIMES THAT THEY WILL NOT MAKE LOVE BEFORE THEY MARRIED. AND THEY PASSED SOLID THREE YEARS IN LOVE. HE USED TO INVITE AND ADVICE HER IN THE EVENINGS. BUT CONDITIONS CHANGED ON THE THIRD YEAR AND HE INVITES HER FOR DINNER. HOPING THAT NOTHING WILL OCCUR ON HER, SHE ACCEPTED THE INVITATION. MAKING HER TO DRINK SOMETHING THAT MAKES HER UNCONSCIOUS, HE BROUGHT HER TO BEDROOM AND RAPED HEM DESPITE HER BEGGING. SHE BECAME DESPERATE. FORTUNATELY, HER FAMILIES ARE PROUD OF HER AND SHE GETS AN OPPORTUNITY TO GO OUT OF THE COUNTRY THROUGH HER FAMILIES SUPPORT. BUT HER MEDICAL CERTIFICATE PROVED THAT SHE IS HIV POSITIVE.

  SHE PHONED HIM AND ASKED WHY HE DID SO. HE MOCKED ON HER CONDITION AND TOLD HER THAT HE IS HIV POSITIVE BEFORE MANY YEARS. HE DISRESPECTFULLY ADDED THAT THEY CAN LIVE TOGETHER IF SHE NEEDS...

  I WAS TEARING WHILE I READ THIS STORY. HOW CAN A PERSON CONCEAL HIS REAL AGENDA FOR SUCH EXTENDED YEARS? I WAS THINKING OF MANY OTHER NAIVE GIRLS AND BOYS TOO.

  IT WAS AFTER THIS TIME THAT I BECOME SO MUCH CONCERNED WITH DAVIDS PSALM WHICH SAYS
  KIFAT BELBACHEW EYALE KEBALINGERACHEW GAR SELAM KEMINAGERUT GAR ATITALEGN. MEZ 27.
  MAY GOD BE WITH US

  ReplyDelete
 26. ኧረ ሰዎች ምን ነካን የተጻፈውን ትተን ያልተጻፈ የምናነበው?
  I didn't see any where mentioned or showed that all people are "Segabel"...please people let us try to read what's only written, not what we only want to read!...ABOUT the one how mentioned Dn. Daneal’s personality...u get to know one thing..this is not Dn. Daniel writing...this is what how God teaches us! That is why all the ppl here thanks God!..if you don't think it's not God, but Dn. Danieal is writing this..u will be one and even the first, because u said u r close to him, how will stumble...please u better put ur eyes off Dn. Daniel and see God.."Our Lord and Savior Jesus Christ"- if you like EXAMPLE to follow...if you want God to teach you read what he is putting before you in one way or another...hope you don't want me to mention "Ye BELEAM AHIYA & YEBITANIYA DENGIYA" for u… I humbly think that we all are here taking our time not to appreciate a writer, but to learn from what is being written!
  May God help us to see what He only wants us to see and to understand what He only wants us to understand.
  Dn. Daniel, please keep God’s words coming to us. That is what matters the most to us!

  ReplyDelete
 27. Dani, do you have a plan to include an English vesion of your posts, so that your message can reach across more people? This is not undermining the use of amharic at all, but it is quite clear there is a good number of our brothers and sisters who canot read amharic fonts-may not be their fault.

  ReplyDelete
 28. Dear Deacon Daniel,
  I can not wait to see your next article. You are truly gifted. May God and his mother the Blessed Virgin Mary be with you all the time.

  ReplyDelete
 29. Dn Kale hiwot yasemalin.
  ene anduwa siga negn be Etsiwat ye tebelahu gin enza sigawoch bemin hatiyatachew yihon yemibelut? ye etsiwatu migib siga silhon bicha ways . . . ?

  ReplyDelete
 30. u r also an excellent social writer............

  ReplyDelete
 31. yes there are such kinds of Individuals. the only thing what we can do is prtecting ourselves through our spritual minstry nd worship. Dani plz .keep on reflecting your ideas.

  ReplyDelete
 32. please go on------!

  ReplyDelete