Thursday, May 13, 2010

ስማችሁ የለም


በሰማያዊው ዙፋን ዘንድ አንድ ውሳኔ ተላለፈ፡፡ «እነዚህ የኢትዮጵያ ሰዎች ሃይማኖተኞች ናቸው፡፡ ስለዚህም ዓለም ከማለፉ በፊት አስቀድመው ተጠርተው ዋጋቸውን ሊቀበሉ ይገባል» የሚል፡፡ አንድ ሊቀ መልአክ እልፍ አእላፍ መላእክትን አስከትሎ ከሰማይ ሲወርድ ታየ፡፡ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሰዎችንም ሁሉ ለሰማያዊ ፍርድ ሰበሰባቸው፡፡


ወዲያውኑ በመንግሥተ ሰማያት በር ላይ ሁለት ዓይነት ሰልፎች ታዩ፡፡ አንደኛው ሰልፍ ረዥም፤ ሌላኛው ሰልፍ ግን አጭር ነበር፡፡ ረዥሙ ሰልፍ ባለበት ቦታ ገበሬዎች፣ ወዛደሮች፣ የዕለት ሥራ ሠራተኞች፣ እናቶች፣ አባቶች፣ ሕፃናት፣ ሊስትሮዎች፣ የቤት ሠራተኞች፣ ሾፌሮች፣ መሐንዲሶች፣ ሐኪሞች፣ አስተማሪዎች፤ ማን ያልተሰለፈ አለ፡፡ ከጥቂቶቹ በቀር ብዙዎቹ መንግሥተ ሰማያት የመግቢያ ካርድ ማግኘት ቻሉ፡፡

ይህንን ሁኔታ ሲመለከቱ በአጭሩ ሰልፍ በኩል የተሰለፉት የልብ ልብ ተሰማቸው፡፡ መጀመርያውኑ ለብቻቸው ሰልፍ የሠሩት ከሕዝብ ጋር ላለመደባለቅ እና ላለመምታታት ብለው ነበር፡፡ እንዴት ሲያስተምሩት፣ ሲያስመልኩት፣ ሲያስሰግዱት፣ ሲያሳልሙት፣ ከኖሩት ሕዝብ ጋር አብረው ይሰለፋሉ? መጀመርያ ነገር እነርሱ ያስተማሩት ሕዝብ መንግሥተ ሰማያት ከገባ እነርሱ የማይገቡበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ሁለተኛ ደግሞ ወደፊትም ቢሆን በመንግሥተ ሰማያት ለየት ያለ የክብር ቦታ ሊጠብቃቸው ስለሚችል ለየት ብለው መሰለፋቸው ተገቢ ነው፡፡ ይህንን እያሰቡ እና እያወሩ እያለ አንድ መልአክ ወደ እነርሱ ሰልፍ መጣ፡፡

ተሰላፊዎቹ በኩራት ገልመጥ ገልመጥ አሉ፡፡ እንዲያውም «ከመካከላችን ማን ይሆን ቀድሞ የሚገባው» የሚለው ነገር ሊያጨቃጭቃቸው ነበር፡፡ አንዳንዶች በተከታዮቻቸው ብዛት፣ አንዳንዶች በነበራቸው መንፈሳዊ ሥልጣን፣ አንዳንዶች ባገኙት የካሴት እና የመጽሐፍ ገቢ፣ ሌሎችም በሕዝቡ ዘንድ በነበራቸው ተደናቂነት፣ የቀሩትም ደግሞ በንግግር እና በድምጽ ችሎታቸው እየተማመኑ እኔ እበልጣለሁ እኔ እቀድማለሁ ሲባባሉ መልአኩ «እናንተ እነማን ናችሁ?» የሚል ያልተጠበቀ ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡

ሁሉም መልአክነቱን ተጠራጠሩት፡፡ አገር ያከበራቸውን፣ሕዝብ ያረገደላቸውን፣እነርሱን ለማየት እና ለመንካት አዳሜ የተንጋጋላቸውን፣ በየፖስተሩ፣ በየካሴቱ፣ በየመጽሐፉ፣ በየመጽሔቱ «ታዋቂው» እየተባሉ ሲቀርቡ የኖሩትን፤ ሰይጣን ያወጣሉ፣ መንፈስ ይሞላሉ፣ ጠበል ያፈልቃሉ፣ እየተባሉ ሲያርዱ ሲያንቀጠቅጡ የኖሩትን፤ ሲዘምሩና ሲያስተምሩ ወፍ ያወርዳሉ የተባሉትን፤ ገንዘብ ከፍሎ መንፈሳዊ ቦታ ተሳልሞ ለመምጣት ሕዝብ ቢሮአቸውን ደጅ ሲጠናቸው የኖሩትን እነዚህን ጉምቱ ጉምቱ ሰዎች የማያውቅ መልአክ እንዴት ሊኖር ቻለ? ተጠራጠሩ፡፡

«ለምንድን ነው ለብቻ ሰልፍ የሠራችሁት? ለምን ከሕዝቡ ጋር አልተሰለፋችሁም?» መልአኩ ይበልጥ የሚገርም ጥያቄ አመጣ፡፡ ተሰላፊዎቹ እርስ በርሳቸው ተያዩ፡፡ ከመካከል አንድ በነገሩ የተበሳጨ ሰባኪ «እንዴት እንደዚህ ያለ ጥያቄ በዚህ በመንግሥተ ሰማያት በር ላይ እንጠየቃለን፤ እስካሁንም ተሰልፈን መቆየት አልነበረብንም፡፡ እኛን ለመሆኑ የማያውቅ አለ? ስንት ሕዝብ ያስከተልን ሰባክያን፤ ስንት ሕዝብ የፈወስን አጥማቂዎች፣ ስንት ሕዝብ ያስመለክን አስመላኪዎች፣ ስንቱን ያስረገድን ዘማሪዎች፤ ስንቱን የታደግን ፈዋሾች፣ ስንቱን የመራን የእምነት መሪዎች፤ ስንቱን በባዶ እግሩ ያስኬድን ባሕታውያን፤ ስንቱን ለገዳም ያበቃን መነኮሳት፤ ሕዝብ ተሰብስቦ የሾመን «ሐዋርያት»፤ እንዴት እነማን ናችሁ ተብለን እንጠየቃለን?» ሁሉም በጭብጨባ ደገፉት፡፡

መልአኩ «መልካም፤ የስም ዝርዝሩን ላምጣውና ስማችሁ እዚያ ውስጥ ካለ ትገባላችሁ» ብሎ አንድ ትልቅ ሰማያዊ መዝገብ ይዞ መጣ፡፡ «እኛ ካልተጻፍን እና የኛ ስም ከሌለ ታድያ የማን ስም በዚህ መዝገብ ውስጥ ሊኖር ነው፡፡ ይኼው እኛ የማናውቀው ሰው ሁሉ እየገባ አይደለም እንዴ?» አለ አንድ አስመላኪ በንዴት፡፡ «ልክ ነህ፤ እናንተ የማታውቁት፣ ፈጣሪ ግን የሚያውቀው፤ እናንተንም የማያውቅ ፈጣሪውን ግን የሚያውቅ ብዙ ሕዝብ አለ ወዳጄ» አለው መልአኩ መዝገቡን እየገለጠ፡፡

«የሁላችሁንም ስም ማስታወስ ስለምችል ሁላችሁም ስማችሁን ንገሩኝ» አላቸው፡፡ ከወዲህ ወዲያ እየተንጫጩ ስማቸውን ከነማዕረጋቸው ነገሩት፡፡ መልአኩ ከፊቱ ላይ የኀዘንም የመገረምም ገጽታ ይነበብበታል፡፡ ቀስ እያለ የስም ዝርዝሩን ያይና ገጹን ይገልጣል፤ ያይና ገጹን ይገልጣል፤ ያያል፣ ገጹን ደግሞ ይገልጣል፡፡ ብዙ ሺ ገጾችን ገለጠ፣ ገለጠ፣ገለጠ፤ ማንንም ግን አልጠራም፡፡ ከዚያ ይባስ ብሎ የመጨረሻውን የመዝገቡን ሽፋን ከቀኝ ወደ ግራ መልሶ ከደነው፡፡ «ምንም ማድረግ አይቻልም፤ የማናችሁም ስም መዝገቡ ላይ የለም» ብሎ መልአኩ በኀዘን ሲናገር «ምን?» የሚል የድንጋጤ ኅብረ ድምጽ ተሰማ፡፡ «የማናችሁም ስም ወደ መንግሥተ ሰማያት ከሚገቡት ሰዎች ዝርዝር ውስጥ የለም» አለ መልአኩ በድጋሜ፡፡

«ሊሆን አይችልም» «የተሳሳተ መዝገብ ይዘህ መጥተህ እንዳይሆን» «ወደ ሲዖል የሚገቡትን መዝገብ ይሆናል በስሕተት ያመጣህው» «እኛኮ አገልጋዮች ነን፤ የከበረ ስም እና ዝና ያለን፤ ስንኖርም፣ መድረክ ላይ ስንቀመጥም፣ ድሮም ልዩ ነን፤ የኛ መዝገብ ልዩ መሆን አለበት» «እስኪ ሌላ መልአክ ጥራ» ብቻ ሁሉም የመሰለውን በንዴት እና በድንጋጤ ይሰነዝር ጀመር፡፡ ሌሎች መላእክትም ሌሎች ዓይነት መዝገቦችን ይዘው መጥ ተው እያገላበጡ ፈለጉ፡፡ የነዚያ «የከበሩ አገልጋዮች» ስም ግን ሊገኝ አልቻለም፡፡

«እኛኮ የታወቅን ነን» አሉ አንድ አጥማቂ፡፡ «ሕዝብማ ያውቃችሁ ይሆናል መዝገብ ግን አያውቃችሁም» አላቸው መልአኩ፡፡ «እንዴት እኮ እንዴት? » አሉ በዋና ከተማዋ ታዋቂ የነበሩ ፓስተር፡፡ «ሊሆን አይችልም፤ ፈጽሞ ሊሆን አይችልም» አሉ አንድ ሼሕ፡፡ «የዚህን ምክንያት ማወቅ ትፈልጋላችሁ? » አለ አንዱ መልአክ፡፡ «አዎ» የሚል ኅብረ ድምጽ ተሰማ፡፡

«ምክንያቱኮ ቀላል ነው፡፡ ሌሎችን መንፈሳዊ እንዲሆኑ ታስተምሩ ነበር እንጂ እናንተ መንፈሳውያን አልነበራችሁም፡፡ እናንተ ድራማ ስትሠሩ ነውኮ የኖራችሁት፡፡ መድረክ ላይ ወጥታችሁ መንፈሳዊ ድራማ ትሠሩ ነበር፡፡ ልብሳችሁ፣ንግግራችሁ፣የእጅ አጣጣላ ችሁ፣ ጸሎታችሁ፣ የተዋናይ ነበርኮ፡፡ የማትሆኑትን ነበር ስታስተምሩ የነበራችሁት፡፡

ለመሆኑ ለሕዝቡ የምታስተምሩትና እናንተ የምትመሩበት የሃይማኖት መጽሐፍ አንድ ነው?  ወይስ ይለያያል?  እናንተ የምድር ቤታችሁን በብዙ ሺ ብሮች እየገነባችሁ ሰዎች ግን ቤታቸውን ረስተው የሰማዩን ቤት ብቻ እንዲያስቡ ታስተምሩ ነበር፤ ሕዝቡን ስጡ ስጡ እያላችሁ እናንተ ግን አምጡ አምጡ ትላላችሁ፡፡ ሕዝቡን በባዶ እግሩ እያስኬዳ ችሁ እናንተ የሚሊዮኖች መኪና ትነዱ ነበር፤ ሕዝቡን እያስጾማችሁ፣ እናንተ ግን ጮማ ትቆርጡ ነበር፤ ታስተምሩት የነበረውኮ ያጠናችሁትን ቃለ ተውኔት እንጂ የምታምኑ በትን እና የምትኖሩትን አይደለም፡፡ እናንተኮ ግብር የማትከፍሉ ነጋድያን ነበራችሁ፡፡ እናንተ ከገዳም ወደ ከተማ ትገባላችሁ፤ ሰውን ግን ከከተማ ወደ ገዳም ትወስዳላችሁ፡፡

እርስ በርሳችሁ እንደ ውሻ እየተናከሳችሁ ለማስተማር እና ለመዘመር ሲሆን፣ ለማስመ ለክና ለማሰገድ ሲሆን፣ የአዞ እንባ እያነባችሁ መድረክ ላይ ትወጣላችሁ፡፡ እርስ በርሳ ችሁ ከበርሊን ግንብ የጠነከረ የመለያያ ግንብ እየገነባችሁ ሕዝቡን ግን አንድ ሁኑ፣ ተስ ማሙ፣ ታቻቻሉ እያላችሁ ታስተምራላችሁ፡፡ ለመሆኑ ይህ ሁሉ ፓስተር፣ሰባኪ፣ ዘማሪ፣ መነኩሴ፣ባሕታዊ፣ ዑላማ፣አሰጋጅ፣አስመላኪ፣ የእምነት አባት፣እያላት ነው ኢትዮጵያ እንዲህ ስሟ በድህነት እና በጦርነት የሚነሣው?  ሙስና እና የዘመድ አሠራር፣ ጠባብ ነት እና ዘረኛነት፣ስግብግብነት እና ማጭበርበር፤ ክፋት እና ምቀኛነት የበዛው ይኼ ሁሉ አገልጋይ እያላት ነው?  ለመሆኑ እናንተ ባትኖሩ ኖሮ ይህች ሀገር ከዚህስ የከፋስ ምን ትሆን ነበር?

ለመሆኑ ተከፋፍላችሁ፣ተከፋፍላችሁ፣ተከፋፍላችሁ መጨረሻችሁ ምንድን ነው?  ለመሆኑ አንድ ባትሆኑ እንኳን ለመግባባት፤ ለመገነዛዘብ፤ ቢያንስ ላለመጠላላት፤ ቢያንስ በጠላትነት ላለመተያየት፤ ላለመወጋገዝ፤ ላለመነቃቀፍ አስባችሁበት ታውቃላችሁ? የሀገራ ችሁ ፖለቲከኞች እንኳን የሥነ ምግባር ደንብ ይኑረን ሲሉ እናንተ ለመሆኑ የሥነ ምግባር ደንብ አላችሁ?  ሻማ ሲበራ ዋናው ጨለማ ከሻማው ሥር ነው የሚገኘው፡፡ ሌላውን ታበራና ሻማዋ ለራሷ ጨለማ ትሆናለች፡፡ እናንተስ? በየቤተ እምነታችሁ ያለውን ችግር መቼ ፈታችሁ ነው ሕዝብ እናስተምራለን የምትሉት?  ለናንተ ሁልጊዜ ጠላታችሁ ሌላ እምነት የሚከተለው ብቻ ነው?  ለራሳችሁ ግን ከራሳችሁ በላይ ጠላት የለውም፡፡ ሕዝቡኮ አንዳችሁ ሌላውን ስትተቹ፤ አንዳችሁ በሌላው ስትሳለቁ፤ አንዳችሁ በሌላው ላይ ነጥብ ስታስቆጥሩ፤ አንዳችሁ የሌላውን ኃጢአት ስትዘረዝሩ መስማት ሰልችቶት ነበር፡፡

«ታድያ እኛ ያስተማርነው ሕዝብ እንዴት ጸደቀ? » የሚል አንድ ድምጽ ተሰማ፡፡

«ሕዝቡማ ምን ያድርግ በምትናገሩት እናንተ አልተጠቀማችሁም እንጂ ሕዝቡማ ተጠቀ መበት፡፡ ሕዝቡማ በሁለት መንገድ ተጠቀመ፡፡ እናንተን እያየ «እንደነዚህ ከመሆን አድነን» በማለቱ ተጠቀመ፤ የምትሉትን እየመዘነ በማድረጉም ተጠቀመ፡፡ እንደ እናንተ ቢሆን ኖሮማ ማን ይተርፍ ነበር፤ አጫርሳችሁት ነበርኮ፡፡ የዚህ ሕዝብ ጉብዝናው ይሄ አይደል እንዴ፤ ሙዙን ልጦ መብላቱ፡፡ ሲገዛው ከነልጣጩ ነው፤ ሲበላው ግን ልጦ ነው፡፡ የእናንተንም ትምህርት የሰማው መላጥ ያለበትን ልጦ እየጣለ ነው፡፡

እናንተ ለዚህች ሀገር መድኃኒት ነበራችሁ፡፡ ነገር ግን ጊዜው እንዳለፈበት መድኃኒት በሽታዎቿ ሆናችሁ፡፡ የሚከተል እንጂ የሚድን፤ የሚያደንቅ እንጂ የሚለወጥ፤ የሚያወቅ እንጂ የሚሠራ፣ የሚመስል እንጂ የሚሆን መች አፈራችሁ?  ሕዝቡን የናንተ ተከታይ አድርጋችሁት ቀራችሁ፡፡ ያንን ጠባያችሁን ይዛችሁ እዚህ ከገባችሁ ደግሞ የገባውን ታስወጡታላቸሁ ተብሎ ይፈራል፡፡

የሚያለቅሱ ድምጾች እየበረከቱ መጡ፤ አንገታቸውን ያቀረቀሩት ብዙዎች ናቸው፡፡ አንዳንዶቹን ፀፀቱ ያንገበግባቸው ነበር፡፡ ሌሎቹም ራሳቸውን ጠሉት፡፡

«አሁን ምንድን ነው የሚሻለን» አሉ አንድ ፓስተር፡፡

«የዚህን መልስ እኔ መስጠት አልችልም፤ ፈጣሪዬን ጠይቄ መምጣት አለብኝ» አለና መልአኩ ትቷቸው ሄደ፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ ሲመለስ እንዲህ የሚል መልስ ይዞ ነበር፡፡

«አንድ እድል ይሰጣችሁ፡፡ ትስተካከሉ እንደሆነ አንድ እድል ይሰጣችሁ፡፡ ሕዝቡን ተውትና ራሳችሁን አስተካክሉት፤ ያኔ ሕዝቡ በራሱ ጊዜ ይስተካከላል»

ድንገት ሁሉም መሬት ላይ ተገኙ፡፡ እነሆ አሁን በየቤተ እምነቱ ያሉት በዚህ መንገድ የተመለሱት ናቸው፡፡63 comments:

 1. ግሩም አመለካከት ነው ዳንኤል። ብዙ ቁም ነገሮችን የያዘ የስነ ጥበብ ጭማቂ ማለት ይሄ ነው። ሌሎችንም ግሩም ዓይነት ጥበቦች እንጠብቃለን ።

  ReplyDelete
 2. You were aganist liberalism. Doesn't this look like a liberal piece of advise. I think it was fantastic if it was only orthodox centered. Or the idea shouldn't start from 'Genet Mengistesemayat'.

  ReplyDelete
 3. EGZIABEHER FESTAMEHEN YASAMEREW.

  ReplyDelete
 4. memihiran bebezu kutire dinkurena
  awakiyoche ..... alemastewal
  habte .......siset

  yelidyan leb yekefete yegnanim yekifetiline!
  lela min malet yichalal?

  ReplyDelete
 5. ሕዝቡን ተውትና ራሳችሁን አስተካክሉት፤ ያኔ ሕዝቡ በራሱ ጊዜ ይስተካከላል.....

  leneseha edme lemiset Amlakachin mesgana yehun.
  Abetu alemun hulu aterfen nefsachinin gin endanata redeAteh ayeleyen.

  Dani ejig astemari tsihuf new.
  Egziabher yehulachininim sim be semayawiwe mezgeb yetsafilin.
  Amen.
  Kale hiwot yasemalin.

  ReplyDelete
 6. ሰላም ዲያቆን ዳንኤል፣ይህ በትክክል ራእይ ነው እንጂ ልብወለድ አይደለም፤ማስተዋል የለንም እንጂ ብናስተዉል በእውነት የሚያጋጥመንን ነው የጻፍከው;እግዚአብሔር ዓይነ ልቦናችንን ያብራልን;፤ላንተም ጨምሮ ጨማምሮ ሰማያዊውን ምሥጢር ይግለጽልህ፣አሜን፤
  አባ ነኝ

  ReplyDelete
 7. ቃለሕይወት ያለማልን የአገልግሎት ዘመንህን ያርዝምልን

  «ምክንያቱኮ ቀላል ነው፡፡ ሌሎችን መንፈሳዊ እንዲሆኑ ታስተምሩ ነበር እንጂ እናንተ መንፈሳውያን አልነበራችሁም፡፡ እናንተ ድራማ ስትሠሩ ነውኮ የኖራችሁት፡፡ መድረክ ላይ ወጥታችሁ መንፈሳዊ ድራማ ትሠሩ ነበር፡፡ ልብሳችሁ፣ንግግራችሁ፣የእጅ አጣጣላ ችሁ፣ ጸሎታችሁ፣ የተዋናይ ነበርኮ፡፡ የማትሆኑትን ነበር ስታስተምሩ የነበራችሁት፡፡
  ታስተምሩት የነበረውኮ ያጠናችሁትን ቃለ ተውኔት እንጂ የምታምኑ በትን እና የምትኖሩትን አይደለም፡፡
  ………..
  ለራሳችሁ ግን ከራሳችሁ በላይ ጠላት የለውም>>

  እኔም እንደዛው ነኝ

  ReplyDelete
 8. Egziabher ke Enzih wegen yishefinen...

  Amen

  Thank you Dn Daniel

  ReplyDelete
 9. Wey Dn Daniel,
  That is faculat true that we have the same issue. Admachochos binhon...
  Sisebek kenfer metiten betachin Sinhed gin Ende Yale Sebaki Sebeke Enje Endet Tesebekhu Bilen mechi Enawukina....
  Yigermal.
  Bertana Tsafiln....Lik likachinin Yane Enawukewalen.

  ReplyDelete
 10. “እነሆ አሁን በየቤተ እምነቱ ያሉት በዚህ መንገድ የተመለሱ ናቸው፡፡” አንድ እድል የሚጠብቃቸው ከተጠቀሙበት ሊተርፉበት ካልተጠቀሙበት ሊጠፉበት ነው፡፡ እንዲያውም እግዚአብሔር ቸር፣ ደግና ርሐሩሕ በመሆኑ ነው እድሉንም ያገኙት፡፡ የመንቃት ግዜ አሁን ነው! የእስከዛሬው ይብቃ! የደወሉን ድምጽ ሰምታችሁ ተመለሱ! ተመለሱ! ተመለሱ!
  ቃለ ሕይወትን ያሰማልን! እኛንም ማስተዋሉን ሰጥቶ የምግባር ሰዎች ያድርገን!

  ReplyDelete
 11. KaleHiwot Yasemalen Dn. Daniel

  ReplyDelete
 12. ድንቅ ጽሁፍ ነው። የሚያሳዝነው ነገር... ሁሉም ተመልሶ ከትፋቱ ላይ መገኘቱ ፡ ፈጣሪ ለሁላችን ማስተዋሉን ያድለን።

  ReplyDelete
 13. Thank You Dn Daniel. It was an excellent and timely article .Some "preachers" has created more damage to our church than any other enemy can do.I hope this article will help them to see toward themselves.
  joro yalew sew yemelakun kal yisma. edilu and gize bicha new !!!

  ReplyDelete
 14. +++

  በጣም የሚያሳዝን እውነታ ነው! ያለ ምስክርነት የሚወጠን ትምህርት ድሮውንም የዕውቀት ድርደራ እንጂ ስብከት አይሆንም። ከሁሉ የሚናፍቀኝ ዛሬ ያሉትም ሆነ ድሮ የነበሩት ድሮ ድሮ ትምክርታቸውን ሲጀምሩ የሚመሰክሩት ምስክርነት ነበር፦ >>> በአብ ስም አምኜ አብን ወላዲ ብዬ፣ በወልድ ስም አምኜ ወልድን ተወላዲ ብዬ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምኜ መንፈስ ቅዱስን ሰራጺ ብዬ ምንም እንኩዋን...... <<< በዚህ የዕምነት መሠረትነት የተወጠነ ትምህርት ዘሪውም አዝመራውም የተባረከ ያደርግ ነበር። ምን ያደርጋል አሁን ይህ የ «ፋራ» ሆነና ተረሳና ይልቁንም ፉከራ አይሉት መመሪያ «ሰረገላዎቹ እሳት በሆኑ በክርስቶስ ስም እንደምን ዋላችሁ?» «ከደመናት በላይ በሚመላለስ በክርስቶስ ሰላም ይብዛላችሁ» «ማንም በዚህ ስፍራ የሚነጋገር አይኑር» ወዘተ ወዘተ የሚሉ መምህራን በዙ፣ በስመ ሥላሴ የማይጀምሩ በራሪ ወረቀቶች የተለመዱ ሆኑ።

  አቤቱ እንደ ቸርነትህ እንጂ እንደበደላችን አይሁን!

  ReplyDelete
 15. I believe our preachers will learn a lesson or two from this article.The last sentence ሕዝቡን ተውትና ራሳችሁን አስተካክሉት፤ ያኔ ሕዝቡ በራሱ ጊዜ ይስተካከላል» sends a powerful message if there is ear to listen.
  keep it up brother,and God bless.

  ReplyDelete
 16. dani thank u for ur advice
  "JORO YALEW MESMATUNE YISMA" i don't want to add or comment bcs it is 100% correct but please others let as ask questions for our self i.e
  are we tring to USE from the preach?
  are we tring to SELECT from the thing they tell to us?
  are we tring to EXERCISE what they tell to us?...
  if so it is OK but i don't think. so the message have two direction for "MEMIRANE" and "MIMANANE". let us check our self.
  again thank u dani

  ReplyDelete
 17. You have no idea how i loved this article when i first read it On Addis Neger. Thanks for sharing it again and GOD bless you

  ReplyDelete
 18. አቤቱ በመንግስትህ አስበኝ፡፡

  ላንተ ግን ቃለ ህይወት ያሰማህ፡፡

  ReplyDelete
 19. ማዶ ለማዶ
  በዚህ ዘመን ያለው የቤተክርስቲያን በተለይም ደግሞ የወንጌልና የዝማሬ አገልግሎት ለብዙ ትችቶች የተጋለጠ ነው፡፡ በርግጥም እንዲተች ግድ የሚሉ በተርካታ ነገሮች የሚስተዋልበት መሆኑ የሚካድ አይደለም፡፡ ይሁን እንጅ እየተሰጠ ያለው አገልግሎት የማይጠቅምና ከዜሮ በታች የሆነ ፍሬ አልባ አድርጎ መመልከት ደግሞ የሚታይ እውነትን ለማዬት አለመፍለግ ካልሆነም ማዬት አለመቻል ብቻ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ በዚህ ጉዳይ ስንወያይ አንድ ወንድም እንዲህ ሲል ሰምቻለሁ “ወደ ዓይናችን የምናስጠጋት ትንሽ ጠጠር ትልቁን ተራራ ትጋርዳለች”፡፡ በዛሬው አገልግሎት ውስጥ እንደ ተራራ የገዘፉ መልካም የአገልግሎቱ ውጤቶች ቢኖሩም ዐይኖቻች ሥር ያሰጠጋናቸው ጠጠር የሚያክሉ በአገልግሎቱ ውስጥ የሚታዩ ችግሮች እንዳናዬው ጋርደውናል፡፡ ስለዙህ አገልግሎቱን በዜሮ የተባዛ እንደሆነ እናምናለን፡፡ በዚያ አገልግሎት ንስሐ የገቡ፣ የቆረቡ ከኑፋቄ የተመለሱ እንዳሉ ብናውቅም እንኳ መንግስተ ሰማያት እንደማይገቡ ግን እርግጠኞች ነን፡፡
  በጎውን ጎን በጉልህ አድንቆ መጥፎውን ለማረም በሚያስችል መልኩ አሰተያየት መሰስጠትና አስተያየቱን ለጆሮ ግቡ በሆነ መልኩ ማቅረብ በጭራሽ የታደልነው ነገር አይመስልም፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‘ ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጅ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ’ኤፌ.4፡29 ማለቱ ለአድማጮቻችን እንድንጠነቀቅ የሚያስታውስ ነው፡፡ ክርስቲያን የሚናገረው የሚሰሙትን ለማነጽ በማሰብ እንጂ ለማፍረስ ወዶ አይደለም፡፡ ከመናገራችን በፊት የምንናገረው ነገር የሚነገረውን ሰው ጆሮ በማይጎረብጠው መልኩ እንዴት ልንነግረው እንደምንችል ብዙ መጨነቅ አለብን፡፡ ንግግርን ‘መናፍቅ’ ወይም ሌላ ስም ሰጥቶ መጀመር ግን ለማፍረስ እንጂ ለማነጽ አይመስልም፤ ለመናፍቅም ቢሆን እሰኪመለስ ድረስ ምጥ ይያዙለታል እንጅ አይዘልፉትም፡፡ ‘ልጆቼ ሆይ! ክርስቶስ በእናንተ እስኪሳል ድረስ ዳግመኛ ስለናንተ ምጥ የዞኛል’ገላ.4፡19 እንዳለ ሐዋርው፤ ፈጥነው ወደ ልዩ ወንጌል ለሔዱት ልጆቹ፡፡ ተመልሰው በትክክለኛው መንገድ ሲሔዱ ከማየት ይልቅ ከምድረ ገጽ መጥፋታቸውን የሚመኝ በሚመስል መልኩ መናገር ወይም መጻፍ እስከ ምጽዐት እንኳ ቢደጋገም አንዳች ጠብ አያደርግም፡፡2ጢሞ2፡25
  በዚህ ሳያበቃ በአገልግሎቱ ውስጥ ምንም መልካም ነገር የሌለ በመሰለን ቁጠር ‘ልክ አይደለም’ ያልነውን መንገድ ለማስቆም ያቅማችንን ያክል እንሮጣለን፤ የማስቆም አቅም ሲጠፋ ደግሞ ዛሬ እንደሚታየው ባገኘናቸው አጋጣሚዎች ሁሉ በመተቸት እንዲጠላ ለማድረግ የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን፡፡ ከሁሉ የሚከፋው ደግሞ እንዲህ ባደረግ ቁጥር ቤተክርስቲያንን ከጥፋት የጠበቅንና እግዚአብሐርን በፍጹም ቅንነት እያገለገልን እነደሆነ እርግጠኞች መሆናችን ነው፤ እንደዚህ ዓይነቱ እርግጠኝነት ደግሞ ከኛ በተቃራኒ ላሉት ክፍሎች ግትርነትና እኔ ብቻ ልክ ነኝ እንደማለት ሆኖ ስለሚታይ ለውይይትና ተቀራርቦ ለመሥራት እንቅፋት ሆኖአል፤ ይህ አካሔድ እስካሁንም ድረስ በወጣትነታቸው ዘመን ለእነዷ ቅድስት ቤተክርስቲያን በሚደክሙት መካከል የልዩነት ጎራ ከመፍጠር ያለፈ የተጨበጠ ለውጥ ሲያመጣ አልታየም፡፡
  ብዙዎች ትችቶቻቸውን ትክክለኛነት ለማሳየት በማሰብ በቃለ እግዚአብሔር ይደጋግፉታል፤.....http://www.facebook.com/note.php?created&&suggest&note_id=121833727845326

  ReplyDelete
 20. Dear Dn Daniel Kibret
  I was laughing and feeling sad while reading your view. Dear preachers, you better not to preachers than to lose the heaven of the Kingdom.
  God bless You!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 21. This is all!!!!!!

  ReplyDelete
 22. "ማዶ ለማዶ"በሚል ርዕስ አስተያይት ለሰጠኽው/ሽው ልጅ::
  በመጀመሪያ አስተያየት አሰጣጥህ ደስ ይላል::ስክን ያለና ጨዋ ነው::ማለት የፈለከውን ነጥብ በደንብ ተናግሯል-አስተያየትህ::ግን ያንተ አስተያየት የሚለውን ነገር "ስማችሁ የለም" የሚለው ጽሑፍ ተቃርኖ አይቆምም::እኔ እንደ ገባኝ የሚለው ያስተማራችሁትን ትምህርት አለኖራችሁብትም ነው::"የተከበራችሁት ሰዎች " ለስልጣን :ለገንዘብ :ለዝና:ለክክብር...ወዘተ ሐይማኖትን ተገን በማድረግ ስትራኮቱ ሥራችሁን አፈረሳችሁት ነው መልክቱ::መንግስተ ሰማያት ለተማሪዎቻችሁ("ተክታዮቻችሁ") ብቻ ሳትሆን ለእናንተም ጭምር ናትና እንደ ምትናገሩት (እንደ ምትሰብኩት) ቃል ኑሩ:":ትልልቅ ሰዎች" በፍቅርና በምግባር ብትኖሩ ሕዝብ እናንተ አካባቢ በሚፈጠረው መገፋፋት ሳይደናበር በሰላም ይኖራል :: በዚህ መገፋፋታችሁ መሃከል እንኳ በምትወረውሩት የህይወት ቃል እየተጠቀመ ነው:: እንደ ዝህ
  "... «ታድያ እኛ ያስተማርነው ሕዝብ እንዴት ጸደቀ? » የሚል አንድ ድምጽ ተሰማ፡፡

  «ሕዝቡማ ምን ያድርግ በምትናገሩት እናንተ አልተጠቀማችሁም እንጂ ሕዝቡማ ተጠቀ መበት፡፡ ሕዝቡማ በሁለት መንገድ ተጠቀመ፡፡ እናንተን እያየ «እንደነዚህ ከመሆን አድነን» በማለቱ ተጠቀመ፤ የምትሉትን እየመዘነ በማድረጉም ተጠቀመ፡፡ እንደ እናንተ ቢሆን ኖሮማ ማን ይተርፍ ነበር፤ አጫርሳችሁት ነበርኮ፡፡ የዚህ ሕዝብ ጉብዝናው ይሄ አይደል እንዴ፤ ሙዙን ልጦ መብላቱ፡፡ ሲገዛው ከነልጣጩ ነው፤ ሲበላው ግን ልጦ ነው፡፡ የእናንተንም ትምህርት የሰማው መላጥ ያለበትን ልጦ እየጣለ ነው፡፡
  ..."

  አስተያየት የሰጠኽው/ሽው ልጅ ስክን ያለ አስተያየት አሰጣጥህን ወድጄዋልሁ::
  ዲ. ዳንኤል በርታ!
  እግዚአብሔር ክሁላችንም ጋር ይሁን::

  ReplyDelete
 23. This seems the practical translation of your article about our preachers, their knowledge and talent.

  Their effort is useless because was not based on true faith!

  Their effort is not fruitful because was not based on spirituality!

  Their effort is worldly because was not rooted with the holy spirit!

  And finally their name itself erased from the heavenly book because they are absent.

  How about our name?

  ReplyDelete
 24. እስከዛሬ በዚህ ብሎግ በጻፍካቸው ጽሁፎችህ እጅግ ተደስቼያለሁ፡፡ በዚህኛው ጽሑፍም ማዕከላዊ ሃሳብ እስማማለሁ፡፡ ነገር ግን ለፖለቲካዊ ትክክለኛነት ስትል ትንሽ ከመስመር የወጣህ ስለመሰለኝ ይህቺን አሳብ ለመሰንዘር ወደድሁ፡፡
  ፖለቲካዊ ትክክለኛነት ከእውነት የተለየ ነው፡፡ እስላሞቹ ጀሃነብ ትገባላችሁ ይሉናል፡፡ መናፍቃኑ ጌታን ስላልተቀበላችሁ አትድኑም ይሉናል፡፡ አንተ ደግሞ ፓስተሩ ያስመለከውም፤ ሼሁ ያሰገደውም መንግስተ ሰማያት ገባ ትለናለህ፡፡ እንዴት ነው ነገሩ የNew generation movement እምነት አራማጅ ሆንክ እንዴ? ወይስ ሊበራሊዝም አንትንም ሳታውቀው ወሰደህ? የጻፍከው ጽሑፍ politically correct ሊሆን ይችል ይሆናል፤ ለተዋህዶና ስለዕምነታቸው ከመናፍቃንና ከአህዛብ ጋር ሲታገሉ ለኖሩ አበው ግን ጽርፈት ነው፡፡ ኢየሱስ አማላጅ ነው ያሉት መናፍቃንና ከነቢይ ያነሰ ነቢይ ነው(ሎቱ ስብሐት) ያሉት መሐመዳውያን እንዴት ወደ መንግስተ ሰማያት እንደገቡ ብትነግረን ጥሩ ነው፡፡ ይህ ጽሁፍ በአዲስ ነገር ጋዜጣ ላይ ወጥቶ ሳነበው ዳንኤል ለፓርላማ ሊወዳደር አሰበ እንዴ ብዬ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ የኦርቶዶክሳዊ መምህር ክህሎት ይሆን እንዴ? ብዬ አሰብኩ፡፡ እባካችሁ ግራ አታጋቡን አታዝሉን፡፡
  ይህንን አስተያየት ፊት ለፊት ባትለጥፈው ግድ የለኝም፡፡ በሆነ መንገድ ግን ብትመልስልኝ ደስ ይለኛል፡፡
  አድማሱ

  ReplyDelete
  Replies
  1. እስማማለሁ አድማሱ

   Delete
  2. በአድማሱ ሃሳብ እስማማለሁ

   Delete
  3. endih meleketu kekebedeh ema tadiya lemen huletegna edel tesetetoachew temelesu beleh aleteyekem? mekeneyatum siol megebat neberebachewa. daneal gen berasu gize lela alem adereso melesachew. endiyawem yemayemesel neger ehen neber meteyek. neger gen yedaneal hasab kegeletsem belay new. ewenetegnoch abatoch moletewal menekat yalebachew degemo ene ekele sayel neketoachew abezagnaw teredetotal. tadiya men gera agabah?

   Delete
 25. Dear Daniel K

  I like so much your way of presenting things.

  keep it up!!

  ReplyDelete
 26. ሰባኪው ስለ ሰባኪው ሕይወት እንጂ ስለአገልግሎቱ የሰበከ አልመሰለኝም!። አትፍራ አይዞህ!። ሰባኪው መልዐኩ አልመሰለኝም!።

  ReplyDelete
 27. this is excellent job!!!!!!!!BETA Dani

  ReplyDelete
 28. እኛን አላዋቂዎችን ለማስተማር ሁልጊዜ ከአውደ ምሕረት ላይ ለመገኘት የምትተጉ የዛሬ ሰባክያነ ወንጌል ሆይ ፤ በጥንቃቄ ተሰካክተው በሚያስገመግም ድምጽ ከአንደበታችሁ ከሚወጡ ቃላት ይልቅ ህይወታችሁ የበለጠ ያስተምረናልና ራሳችሁን በየለቱ መመርመሩን አትዘንጉ።

  ReplyDelete
 29. This is for brother Admasu.I like your comment in the direction you have seen the article.But according to my perception there are two things to consider:

  1. The blog is not entirely dedicated to religious matters and orthodoxy. It also reflects views on culture, politics,tradition etc as described in the logo.
  2.The article is a poetic description of a number of things. I don't believe that you don't know about "wax and Gold"; that is why you agree with the central idea of the article.

  Therefore I didn't understand the way you mix up things. The "Gold" meaning of the article never say the muslims and protestants posses the heaven and truly will never be unless through the sacraments of Baptism, penance and the holy Eucharist.

  By the way what do you mean by "politically correct"?

  ReplyDelete
 30. The person who commented under the title 'mado le mado'needs to be under the radar for his comment is a poison wraped with honey.He/she wants to buy time inorder to carry out the clandestine project of spreading heretic teachings in our church.Why does he/she ask for patience for those who are not willing to correct the wrong teachings? What you say is always there,but for those who deliberately want to destroy the teachings of Tewhedo,there should not be patience.NOBODY WAS KICKED OUT OF OUR CHURCH BEFORE HE WAS GIVEN ENOUGH TIME TO CORRECT HIMSELF.Aba yonas/belete/,Zewudu,and accomplices were all changed to be heretics,insulted the church,and joined the group that paid them.Nobody else was persecuted before he was repeatedly told to correct himself.If there is somebody you know lets know.But there is nobody unless he is a confirmed heretic.And those heretics have their own place.Why do we need to give them position in our church?To poison others?
  Patience,patience....the tactic of the day's undercover hertics.

  ReplyDelete
 31. ውድ ዲያቆን ዳንኤል
  ……ያን ጊዜም ቀርበው በስምህ………አላደረግንም ይሉኛል፡፡ እኔ ግን ከቶ አላወቅኩኃችሁም ነበር እላቸዋለው፡፡ ከሚለው የመጽሐፉ ቃል ጋር ስለሚስማማ ትክክል ነው እላለሁ፡፡ ነገር ግን ስለፖለቲከዊ ትክክለኛነት እንደተናገረው ወንድም ሳይሆን የክርስቶስን ስም የሚጠሩትን ሁሉ የሚመለከት ነው፡፡ መች ኢየሱስ አማላጅ ነው/አይደለም በማለት መዳን-የዘላለም ህይወት መውረስ አለና!

  በረከተ እግዚአብሔር ያግኝህ!

  ReplyDelete
 32. ተስፋብርሃንMay 16, 2010 at 12:32 AM

  ውድ ወንድሜ ዲ/ን ዳንኤል እዚህ ላይ ባነሳሃቸው ብዙ ሃሳቦችህ እስማማለሁ በእኛ ቤተክርስቲያን ባሉ ሰዎች ብቻ ብትወሰን ኖሮ በጣም ጥሩ ያስተምራል ልብ ያለው ቢኖር ግን ከሌሎች የእምነት ድርጅቶች ጋር መቀልቀልህ ጥሩ አይደለም መምህራኑስ እሺ አንድ ዓይነት ግብር ስላልቸው ወደ ገነት/ጽድቅ ቦታ/ መግባት አልቻሉም እንበል ታዲያ ምእመናኑ ዳኑ ስንልስ እስላሞቹና ፕሮቴስታንቶቹ ዳኑ አያሰኝም? እንደዚያ ከሆነ ደግሞ ኦርቶዶክሳዊ እምነትና ስራዓት ላይ ችግር ይፈጥራል እስላሙ ፕሮቴስታንቱ የፈለገውን እያደረገ የሚድን ከሆነ እኔም እንደፈለግሁ ልሁን እንዲል ለኦርቶዶክሳዊ ምእመን ምክንያት ይሆነዋል "በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ" እንዲሉ አበው ዘመናዊነትና ንዝህላልነት የያዘውን ሰዋችንን እንዳናጣው እሰጋለሁ ሰምና ወርቅ ነው ብሎ ወንድም ደረጄ ለማቅረብ የሞከረውም አያስማማኝም የእግዚአብሔርን ታቦት ከጣኦት ጋር ማወዳደር ይሆናልና /ፕሮቴስታንቱና እስላሙ ምእመን ከኦርቶዶክሳዊው ምእመን ጋር አብሮ መሰለፍ የለበትም/

  "... «ታድያ እኛ ያስተማርነው ሕዝብ እንዴት ጸደቀ? » የሚል አንድ ድምጽ ተሰማ፡፡ ይህ ድምጽ የየትኛው እምነት መምህር እንደሆነ ግልጽ አይደለም ቢሆንም ሌሎቹንም ወክሎ ነውና የተናገረው የሌሎቹም እምነት ተከታይ ሕዝብ ድኗል ያሰኛል ከተሰጥው መልስ

  «ሕዝቡማ ምን ያድርግ በምትናገሩት እናንተ አልተጠቀማችሁም እንጂ ሕዝቡማ ተጠቀ መበት፡፡ ሕዝቡማ በሁለት መንገድ ተጠቀመ፡፡ እናንተን እያየ «እንደነዚህ ከመሆን አድነን» በማለቱ ተጠቀመ፤ የምትሉትን እየመዘነ በማድረጉም ተጠቀመ፡፡ እንደ እናንተ ቢሆን ኖሮማ ማን ይተርፍ ነበር፤ አጫርሳችሁት ነበርኮ፡፡ የዚህ ሕዝብ ጉብዝናው ይሄ አይደል እንዴ፤ ሙዙን ልጦ መብላቱ፡፡ ሲገዛው ከነልጣጩ ነው፤ ሲበላው ግን ልጦ ነው፡፡ የእናንተንም ትምህርት የሰማው መላጥ ያለበትን ልጦ እየጣለ ነው፡፡

  ሕዝቡ ባለበት ቤተ እምነት መምህራኑ የሚሰጡትን ትምህርት በጎበጎውን እየወሰደ እንደዳነ ነው እኔ የምረዳውና ወደፊት ባይደባለቅ ጥሩ ነው እላለሁ

  በተረፈ የተነሳው ነጥብ ጊዜውን የዋጀ በተለይ አባቶቻችን እነ ቅዱስ ተ/ሃማኖት እና ሌሎችም ቅዱሳን በቆሙበት አውደ ምሕረት አሁን ለቆምነው ውስጠ ዘ ሰባኪያን ለንስሃ እንድንበቃ እግዚአብሔር የጥሪ ቃሉን እያሰማን ነው ስለዚህ ይህንን አውቀን ወደ ልባችን እንድንመለስና ንስሃ እንድንገባ ቸሩ መድኃኔ ዓለም ማስተዋሉንና ጥበብን ይስጠን አሜን

  ተስፋብርሃን

  ሁላችንም አሁን ላለው የቤተክርስቲያን ችግር ባንድም ሆነ በሌላ ተጠያቂዎች ስለሆንን እግዚአብሔር የአባቶቻችንን ፍቅርና እንባ እንዲሁም ትጋሃ ጸሎት እንዲሰጠን እንጸልይ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ድፍረትህ ያሳዝናል። መንግስተ ሰማያት የሚገባ ኦርቶዶክስ ብቻ ነው?? በጣም ጠባብ አይምሮ!!! ፈጣሪን ሳይሆን ፍጡርን የምታመልኩ፣ በቅዱሳን ስም መተትና አስማትን በየ ደብሩ የምትለማመዱ የሰይጣን ማህበርተኞች፣ ጥላ ወጊ ደብተራዎች። ህዝቡን አይኑን ያሳወራችሁ እውሮች፣ በባዶ ታሪክ፣ በተረት የተፈጠረ ጸሎት የምትደግሙ! ወዮላችሁ!!! ሌሎች እንዳይገቡ በር የዘጋችሁ እውሮች ንስሐ ግቡ። ወዮላችሁ የእውነትን መንገድ ለወጋችሁ የምታጣምሙ ጸረ ክርስቶስ ንስሐ ግቡ ጊዜው ሳያልፍ!!!!!!!

   Delete
 33. ቃለ ህይወት ያሰማልን! እመብርሀን ትርዳህ!! ረጅም እድሜ ጸጋና በረከት አምላካችን ይስጥህ፡፡ አንደበትህ በኃይማኖት የወደቁትን የሚለውጥ ይሁን፡፡

  ወይንሸት

  ReplyDelete
 34. ትምህርት ሰጪ ነው ሰባኪዎቻችን ካነበቡት፡፡

  ReplyDelete
 35. ዲ/ን ዳንኤል፣

  በቃላት መግለጽ ከሚቻለው በላይ በጣም ጥሩ ጽሑፍ ነው። እግዚአብሔር ያቆይልን።

  ጽሑፍህን ሳነብ በአይነ ኅሊናዬ ያን የመጨረሻውን የሕይወት መጽሐፍ የሚገለጥበትን ቀን እያሰብኩ የእኔስ ዕጣ ምን ይሆን እያልኩ ነበር። የተዋጣለት ጽሑፍ ስለመሆኑ ከዚህ የበለጠ ማስረጃ የለም።

  በዚህ ጽሑፍ ጊዜ አግኝቸ የተሰጡትንም አስተያየቶች ባብዛኛው አንብቤአለሁ። "ማዶ ለማዶ" እና አድማሱ የተባሉ አስተያየት ሰጭዎች የሰነዘሯቸውን ሃሳቦች እንደገና ማውጠንጠኑ ጉዳት ያለው አልመሰለኝም። ቅን ሃሳቦች ያዘሉ ይመስለኛል።

  የአንተን የአቀራረብ ዘይቤ በቅርብ የሚያውቅህ ለመረዳት አይከብደውም ብዬ አስባለሁ። ቤተክርስቲያናችንም ሆነ አገራችን በዚህ ትውልድ ያለፉበትንና እያለፉበት ያለውን በቅርብ ሲከታተልና ያቅሙን ብዙ ሲደክምና የተለያዩ መንገዶችንም በመጠቀም ሁኔታዎችን ሊያስተካክል ሲማስን ለኖረና አሳዛኙን ውጤት በውስጥም በውጭም በቅርበት ላዬ ሰው አሁን ባለንበት ሁኔታ የሚያቆላምጥ ቋንቋ ለማውጣት ትልቅ ፈተና እንደሚሆንበት አይጠረጠርም። ግን ምናልባት እንደተባለው ድካሙ ሁሉ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑ ነውና ለሁሉም በማይጎረብጥ መንገድ ይህንኑ ተመሳሳይ መልዕክት ማስተላለፍ ከተቻለ ደግሞ እሰየው የሚያሰኝ ነው። እና በዚህ መንገድ እንድታየው ነው። ይህ የ"ማዶ ለማዶ"ን አስተያየት የሚመለከተው ነው።

  አድማሱ የሰጡት አስተያየትም በተመሳሳይ ጠቃሚ ነው። ከአጻጻፍ አኳያ ይህ የአንተ ጽሑፍ የትኛው መደብ ውስጥ እንደሚወድቅ ከአንተና መሰል የመስኩ ባለሙያዎች በተጨማሪ ከአንባቢውም ውስጥ ገምቶ አጠቃላይ የጽሑፉን ጭብጥ የሚረዳ እንዳለ ሁሉ ንባቡን ብቻ የማየት ነገር ሊኖርም እንደሚችል መገመት አያስቸግርም። እነዚያ ሰዎች "ምነው ዱባና ቅልን ቀላቀላቸው" ካሉ ጽሑፍህን እነሱንም ከመሰናከል ለማዳን የሚቻልበት ማድረግ ከተቻለ ምናለ ለማለት ነው።

  ከተቻለ የምለው በተለይ አሁን ካለንበት ውስብስብ ሁኔታ በቴክኒክ ረገድ ለብዕረኞች ይልቁንም በአንድ በኩል ስለቤተክርስቲያናቸው ገበና በሌላ በኩል ስለሚፈጸመው አሳዛኝ ነገር ለሚጨነቁ ክርስቲያን ጸሐፍት እንዴት ጽሑፋቸውን እንደሚያዘጋጁ ፈጽሞ የማይቻል ባይሆንም በእኔ በኩል ከባድ እንደሚሆን ስለምገምት ነው። እስካሁን ከሰራኸው አንተ ይህን በተዋጣለት መንገድ ልታደርገው እንደምትችል ያለኝ እምነት ታላቅ ነው።

  በመጨረሻም ለአንተ አስተያየት ለመስጠት የምችል ሆኜ አይደለም። እንደ እኔ በተግባር ለማይሳተፍ ሰው "ማረም" እንደሚቀናው የምታውቀው ነው። ያው በጽሑፉ እንደጠቀስካቸው ሰዎች ማለት ነው። አንተ እስካሁንም ካደረከው በላይ አድርገህ ለማየት ያለኝ ታላቅ ጉጉት አላስችል ስላለኝ ብቻ ነው ለማለት ነው።

  እግዚአብሔር ይጠብቅልን!

  ReplyDelete
 36. Dear DC Daniel

  It is an interesting insight in to the reality in our church. I see a challenge ahead of you. There will be many who will not be happy with your views. They may also take different measures against you. I beg you to keep on writing, no matter what. I pray to God to give you all the strength for the same.

  ReplyDelete
 37. ወንድማችን ዲያቆን ዳንኤል እግዚአብሔር አምላክ እረጅም እድሜ ይስጥ!

  ReplyDelete
 38. It is Yalemie T.
  Oh, still I remember the document which written in 'Hamer' before 10 years ago named 'Sebakew' similar to this article for all responsible bodies.

  Please everyone read it.

  ‘Amlakachen Mechershachinin yasamerlen’

  Daniel Egiziabher Yistelen

  ReplyDelete
 39. May God bless your life,we need more peppl
  like you. you are awesome.

  Getachew

  ReplyDelete
 40. Thank u Dn. Daniel may God bless u,this will initiate us for spiritual works But for those who contradict u're idea I think they didn't understand u're message, they have to know that (sewochne mesab yemichalew befikire bicha new degmome bihone Yeprotestant weyeneme yelela eminet teketayoch mengiste semayat gebu teblo begeletse altetsafeme Yihim Tibebe Yetemolabete Yeatsatsafe zeybe new.

  ReplyDelete
 41. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

  ReplyDelete
 42. ዲ/ን ዳንኤል,ሰላም ላንተ ይሁን!!
  የሚያውቅ ሲናገር ደስ ይላል... በአጭሩ መስመር የተሰለፉት ምንኛ ትህትና እንደጎደላቸው እና በእግዚአብሄር ፊት ማንም ቢሆን ማን ለራሱ ዋጋ መስጠት እንደማይችል:ራሱን ከፍ የሚያደርግ መዝገብ ላይ እንዳይጻፍ ተምሬበታለሁ;;
  የቆመ የመሰለው ሁሉ እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ...
  ለነገሩ በረጅሙ መስመር እኛ ባናያቸው እንጅ ብዙ ``ለኔ አይገባኝም ብለው በ ትህትና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው የእግዚአብሄርን ቸርነት የሚጠባበቁ የቤተ ክርስትያናችን እንቁ ሊቃውንት አይጠፉም የኛ አሰላለፍ በ አጭሩ መስመር ሆኖ እንጅ::
  ``እግዚአብሄር በአንድም በ ሌላምመንገድ ይናገራል:: ሰው ግን አያስተውልም::`` እዮብ 33:14
  አስተዋይ ልቦና ይስጠን!!!

  ReplyDelete
 43. ... መንፈሳውያን አልነበራችሁም፡፡ ድራማ ስትሠሩ ነውኮ የኖራችሁት፡፡ መድረክ ላይ ወጥታችሁ ልብሳችሁ፣ንግግራችሁ፣የእጅ አጣጣላ ችሁ፣ ጸሎታችሁ፣ የተዋናይ ነበርኮ፡፡ የማትሆኑትን ነበር ስታስተምሩ የነበራችሁት፡፡ተውኔት እንጂ የምታምኑ በትን እና የምትኖሩትን አይደለም፡፡...God bless u
  አስተዋይ ልቦና ይስጠን

  ReplyDelete
 44. «አንድ እድል ይሰጣችሁ፡፡ ትስተካከሉ እንደሆነ አንድ እድል ይሰጣችሁ፡፡ ሕዝቡን ተውትና ራሳችሁን አስተካክሉት፤ ያኔ ሕዝቡ በራሱ ጊዜ ይስተካከላል»

  ReplyDelete
 45. ዳንኤል ክብረት እኔ ሀጢያተኛ ነኝ፣ የእኔ ምርቃት ከፈጣሪ ዘንድ ዋጋ ካላት እግዚአብሄር በሞገስ ይጠብቅህ፣ ውለታህን አምላክ ይክፈለው።

  ReplyDelete
 46. "ሕዝቡን ተውትና ራሳችሁን አስተካክሉት፤ ያኔ ሕዝቡ በራሱ ጊዜ ይስተካከላል" ደስ የሚል ቃል!!!

  ReplyDelete
 47. እራሴን እንድመለከት ስለረዳኸኝ አመሰግናለሁ
  ዳኒ እግዚአብሔር አምላክ ይስጥልኝ
  `እግዚአብሄር በአንድም በ ሌላምመንገድ ይናገራል:: ሰው ግን አያስተውልም::`` እዮብ 33:14
  አስተዋይ ልቦና ይስጠን!!!

  ReplyDelete
 48. The theme of the story is from the late pope shenouda book" the release of the spirit" from the section " it happened that night" . Nice translation,.

  ReplyDelete
 49. ዲ/ዳንኤል በትክክል ነው የገለፅከው እጅግ በጣም ደስ የሚል ትምህርት ሰጪ ፅህፍ ነው እድሜና ጤና ይስጥልን

  ReplyDelete
 50. igezabhere thigawen chemero chemero yabezalhe ..

  ReplyDelete
 51. igezabhere thigawen chemero chemero yabezalhe dani.

  ReplyDelete
 52. Weye aba serqe erson Belo Aba Danin Lemetechet Yekerena hasabe Lemesenzer b Errr mejemeriya Aqmon Yefeteshu yachin Gooooode endalawetabote yemayehon Neger Ayekbateru

  ReplyDelete
 53. ለመወደድ ነው?

  ReplyDelete
 54. ቤተክርስቲያንን የመተትና አስማት ያልከዉ አንተ ዉሻ ልክስክስ ለቃቃሚ ለራስህ ንሰሃ ግባ ገሃነብ ግባና!

  ReplyDelete
 55. የሚያሳዝሳው ያንተም ሥራ ከድራማ የሚቆጠር መሆኑ ነው። በዚህም ራስህን ባጭሩ ሰልፍ ታገኘዋለህ።ክርስትና የኪነትና የጽሑፍ ጥበብ ውጤት ቢሆን ኑሮ፤ ዘፋኝ ሁለ ይጸድቅ ነበር። እናት ቤተክርስቲያንን የሚጠብቅ በደሙ የመሰረታት ሙሽራዋ ክርስቶስ ብቻ እንጁ ድርጅት ወይም ግለሰብ አለመሆኑን አለማወቅህ ለዚህ ስህተት እንደዳረገህ ግልጽ ነው። በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ድዋይን ሚፈውሱ ሁሉ ላንተ ጠንቋዮች አስማተኞች ሱሆኑ ብድርጅት ስውር ክህነት እስከ ጵጵስና በመድረስ የሲኖዶስን መንበር መውረስ
  እንደ አንድ ትግል ይዘው ያሉት ቅሩባንህ ግን ስማቸው ተጽፏል።
  ክርስትና እንደፓለቲካ የስልጣን እሽቅድምድምና ሽሚያ እንዲኖረው ማሰብ ክርስትና አይደለም። በሲኖዶስ ላይ ድብቅ ተሃድሶ መመኘትም በተሾሙት ምትክ መንጋ ጠባቂ መሆንም
  እጅግ ክፋትን ያሳያል። ብዙ መተተት አጋንንት መጎተት በቤተ ክርስቲያን ከቆሎ ትምህርት ጋር ተምረው እላይ የደረሱ ብዙ አሉ እስቲ ስለሚፈውሱት ሳይሆን ስለሚያሳምሙት ድፍረህ ስበክ።ስማቸው አልተጻፈም ብለህ ብዙ ካህናትን እውነትን በፍሬአቸው ያሳዩትን ሁሉ አትዘርዝር ምእመኑን አባቶችን እንዳያከብር እንቅፋት አትሁን። አንተንና መሰሎችህ የቤተ ክርስቲያን ፍቅር ቅናት ምን እንደሆነ በራሱ በክርስቶስ ጅራፍ
  ተገርፋችሁ እንድትፈወሱ በደካማው አንደበቴ እጸልያለው።
  ቤተክርስቲያን ያለባት ተኩላዎች በሁለት ይመደባሉ።
  1.ተሃድሶ ይገባታል
  2. መታደስ አይገባትም
  የመጀመሪያው የውጭ ሲሆን አላማው ምእመኑን መምታት ነው
  ሁለተኛው የውስጥ ሲሆን አላማው ካህናትንና ፈዋሴዎችን መምታት ነው። ይማይገለጥ የተከደነ የለም። ይገለጣል።

  ReplyDelete