Friday, May 7, 2010

ትልቅ ሰው

እንዲሀም ሆነ

ስድስት ጓደኛሞች ነበሩ፡፡ ወጣቶች ወንዶች፡፡ ደግሞ የሚገርመው ሁሉም ቀጠን እና ረዘም ይላሉ፡፡ ከመካከላቸው አንዱ ሊያገባ ይነሣል፡፡ አምስቱ ጓደኞቹ ደግሞ ሚዜ ብቻ ሳይሆን ሽማግሌም ሊሆኑት ይነሣሉ፡፡ የሽምግልናውን ባሀል ጠይቀው፣ አጥንተው እና ተዘጋጅተው የልጅቱ ወላጆች በተቀጠሩበት ቀን ወደ ልጅቱ ቤተሰቦች ዘንድ ይሄዳሉ፡፡ «ግቡ ግቡ» ይባሉና ገቡ፡፡ «ተቀመጡ» ሲባሉ «አንቀመጥም ጉዳይ አለን» ይላሉ እንደ ባህሉ፡፡ ወላጆች እና ዘመዶችም ገላግለው ያስቀምጧቸዋል፡፡

እናትም ወደ ጓዳ፣ አባትም ወደ መኝታ ቤት ገቡ፡፡ የቀረው ቤተ ዘመድም የደራ ወሬ ጀመረ፡፡ ጥቂት ጊዜ ጠብቀው ትንሽ ከቤተ ዘመዱ ጋር የሚተዋወቀውን አንዱን ጓደኛቸውን ወደ ጓዳ ላኩት፡፡ እናቲቱን አገኛቸው፡፡ «እማማ ቁጭ በሉ ብላችሁን ጥላችሁን ጠፋችሁኮ» አለ በቀልድ «እስኪመጡ አንዳንድ ነገር ላድርግ ብዬ ነው» አሉት እናቲቱ፡፡ «የምትጠብቁት ሰው አለ እንዴ?» አለ ልጁ፡፡ «ምን ሽማግሌዎቹኮ ቀሩ፤ መጀመርያ የናንተን እንጨርስ መሰል» ይላሉ እናት፡፡

ልጁ ግራ ገባው፤ እንደ ማፈርም አለ፡፡ አሁን ምን ይባላል፡፡ ተመለሰና ለጓደኞቹ ነገራቸው፡፡ ተያዩ እና ተደነጋገጡ፡፡ ከዚያም እንደገና ሁለት ሆነው ወጡ፡፡ «እማማ እኛኮ ነን ሽማግሌዎቹ፤ ሌላ ማን ይጠበቃል?» አሉ እንደ ቀልድ አድርገው፡፡ «እናንተማ ሚዜ ናችሁ፣ ሌላ ሌላ ነገር አለን የምንነጋገረው፤ አሁን አትቸኩሉ ትንሽ ቆዩ» ይላሉ እናትም፡፡ ወጣቶቹ ምን ብለው ያስረዱ፡፡

ቢጨንቃቸው ቀልዱን ተውትና ትንሽ ኮስተር ብለው የመጡበትን ምክንያት አስረዷቸው፡፡ «እንግዲህ እኛ የወጣት ሽማግሌ አይተን አናውቅ፤ ምን ይደረግ ብላችሁ ነው፡፡ እንዲያውም አመጣጣችሁ ግራ ገብቶን ስለ ሠርጉ ልታወሩን መስሎን ነበርኮ፤ ለካ ሽማግሌዎቹ እናንተ ናችሁ ? እኛኮ «ትልልቅ ሰዎች» ነበር የምንጠብቀው» እያሉ ሳቁ፡ አባትዬውም «ትልልቅ ሰው ጠፋና እናንተ መጣችሁ» እያሉ እየተኮሳተሩም፣ እየሳቁም ወጡ፡፡ ሌሎቹም እንዲሁ፡፡

«የልጅ ሽማግሌ ከተገኘ እንግዲህ መልካም ነው» አሉና አጎትዬው ነገሩን አደላደሉት፡፡ አንድ ሁለት ቤተ ዘመዶችም ነገር የሚያስተካክል ወግ ጨማመሩ፡፡

እነዚህ «ሽማግሌዎች» ሁሉም መሐንዲሶች ናቸው፡፡ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ሠርተዋል፡፡ በትንሹ አሥር ዓመት በሥራ ዓለም አሳልፈዋል፡፡ የከተማዋን ታላላቅ ሕንፃዎች በማርቀቅ እና በመገንባት አስተዋጽዖ አድርገዋል፡፡ በየቢሮአቸው የሥራ ኃላፊዎች፣ የኩባንያ ባለቤቶች እና ብዙ ሠራተኞችን የሚያስተዳድሩ ናቸው፡፡ ነገር ግን «ትልቅ ሰው» ተብለው ሊቆጠሩ አልቻሉም፡፡ ለምን?

ደግሞም እንዲህ ሆኗል፡፡

አንዲት ትዳር ከመሠረተች ሰባት ዓመታትን ያስቆጠረች፣ የሁለት ልጆች እናት፣ ከአሥራ ሁለት ዓመታት በላይ በሥራ ያሳለፈች፣ የሁለተኛ ዲግሪዋን የያዘች ፤ በባንክ፣ በማስተማር እና መንግሥታዊ ባልሆነ ድርጀት የሠራች ሴት ለኤክስፐርትነት ቦታ ልትወዳደር ለቃለ መጠይቅ ከጠያቂዎቿ ፊት ተቀምጣለች፡፡ ለቦታው ደግሞ ከሚጠየቀው በላይ የትምህርት ደረጃ እና የሥራ ልምድ አቅርባለች፡፡ በግራ በቀኝ ያሉት ይፈትኗታል ያሉትን ጥያቄዎች እያነሡ ጠየቋት፡፡ መለሰችላቸው፡፡ ወደ ኋላ ወደ ታሪኳ፣ ወደ ፊት ወደ ምኞቷ እየሄዱ ጠየቁ፡፡ ተመለሰላቸው፡፡

በዚህ ጊዜ ከጠያቂዎቹ አንዱ እንዲህ አለ «ይህ ቦታ የትልልቅ ሰዎች ቦታ ነው፡፡ the great men position, specially grey haired men´ ታድያ ላንቺ አይከብድሽም?» አለ፡፡ እንግዲህ በእርሱ ኅሊና «ኤክስፐርት» ሲባል በእድሜ ጠና ያለ፣ ሽበት ጣል ጣል ያደረገበት፣ ኮት እና ሱሪ የለበሰ፣ ከረባት ያሠረ፣ መነጽር የሰካ ትከሻው ሰፊ ያውም ወንድ ነው የሚታየው ማለት ነው፡፡ ትልቅ ሰው ማለቱ ይኽ ነው፡፡

እነዚህ ታሪኮች አንድ ጥያቄ እንድናነሣ ያደርጉናል፡፡ «ትልቅ ሰው» ማነው? የሚል፡፡ በትምህርት፣ በሥራ ልምድ፣ በዕውቀት፣ በአስተሳሰብ ችሎታ፣ በብቃት «ትልቅ ሰው» መሆንና፤ በማኅበረሰቡ ዘንድ «ትልቅ ሰው» ተብሎ ተቀባይነት ማግኘት ይለያያሉ፡፡ ይኼ ልዩነት ደግሞ ዕድሜን፤ መልክን፣ የሰውነት ሁኔታን፣ አለባበስን፣ አንዳንድ ጊዜም ዘርን፣ ሥልጣንን፣ ወዘተ መሠረት ሊያደርግ ይችላል፡፡

አንደኛ፣ ሁለተኛ፣ ሦስተኛ እና አራተኛ ክፍል የተማራችሁባቸውን መጻሕፍት ስታስታውሱ በመማርያ መጻሕፍቱ ላይ ዶክተሩ፣ ሳይንቲስቱ፣ ዳኛው፣ ንጉሡ፣ አርበኛው፣ ነጋዴው፣ቄሱ፣ሼኹ፣ አባት፣ እናት፣መምህር፣ የተሳሉበትን ሥዕል እስኪ በዓይነ ኅሊናችሁ ቃኟቸው፡፡ ረዘም ብለው ትከሻቸው ደልደል ያለ፤ በዕድሜ ጠና ያሉ፤ ፀጉራቸው ወደ ውስጥ ገባ ገባ ያለ፤ ጉንጫቸው ትንሽ ሞላ ያለ፤ ዓይነት ሰዎች ናቸው፡፡ በቁመታቸው አጠር፣ በሰውነታቸው ቀጠን፣ ፀጉራቸው ሞላ፣ በእድሜያቸው ወጣት፣ ልጅ እግር ሰዎች የሚሳሉት ኳስ ሲጫወቱ፤ ዳቦ በወተት ሲበሉ፣ በትምህርት ቤት ውስጥ አትክልት ሲያጠጡ፣ ሐኪም ቤት ገብተው ሲታከሙ፣ የመኪና መንገድ ሲሻገሩ፣ ዛፍ ሲቆርጡ ወዘተ ነው፡፡

እንግዲህ የማኅበረሰባችን «የትልቅ ሰው አመለካከት» ከዚህ ይጀምራል ማለት ነው፡፡ አንድ ጓደኛዬ ከልጁ ጋር ትምህርት ቤት ሄዶ ዳይሬክተሯን ሲያነጋግራት አልተግባቡም፡፡ «ለነገሩ እኛ ወላጅ እንዲያመጣ ነው የነገርነው፤ ስለዚህ ከወላጆቹ ጋር እንነጋገራለን» ብላው እርፍ፡፡ ያንን ሲያዩት ልጅ የሚመስል ቀጭን እና ለግላጋ ወጣት ማን ከወላጅ ይቁጠረው፡፡ የልጁ ታላቅ ወንድም ነበር የመሰላት፡፡

ይህ አመለካከት በአንድ በኩል ሰዎችን በማንነታቸው ሳይሆን በውጫዊ ቁመናቸው ብቻ ቦታ እንድንሰጥ አድርጎናል በሌላ በኩል ደግሞ ተገቢ ሰዎች በተገቢ ቦታ እንዳይቀመጡ አግዶብናል፡፡

የክልሎች የአዳጊ ወጣቶች ሻምፒዮና ይባልና ውድድር ይደረጋል፡፡ ውድድሩ ለአዳጊ ወጣቶች ነው፡፡ ተተኪዎችን ለማፍራት ተብሎ፡፡ አወዳዳሪዎቹ ግን ያለ «ትልልቅ ሰዎች» በሌሎቹ አያምኑም፡፡ ስለዚህ እድሜ እያስቀነሱ «ትልልቆቹን» ተጫዋቾች በአዳጊዎቹ ምትክ ይዘዋቸው ይመጣሉ፡፡ በአዳጊዎቹ አይተማመኑም፡፡ በዚህ ምክንያት አዳጊዎቹም ጭንቀት ውስጥ ይገባሉ፤ በራሳቸው እንዳይተማመኑ ሆነው ተቀርፀዋልና፡፡ አገሪቱም ያለ ተተኪ ትቀራለች፡፡

በሩጫው ዓለምም ቢሆን በዚህ እና በዚያ ውድድር ተገኝቶ «ሚኒማ» ያላሟላ ለዓለም ዐቀፍ ውድድር አይቀርብም ይባላል፡፡ «ትልልቆቹ» በእነዚህ ገንዘብ አልባ በሆኑ የሀገር ውስጥ ውድድሮች ተገኝተው ላብ አይጨርሱም፡፡ ገና ለታዋቂነት ያልበቁ አዳዲስ ሯጮች በእነዚህ ቦታዎች ተገኝተው «ሚኒማ» ማሟላት ብቻ ሳይሆን ሌላ «ሚኒማ»ም ይፈጥራሉ፡፡ ዓለም አቀፍ ውድድሩ ሲመጣ ግን እነዚያ አዳዲስ ጀግኖች እንዲቀሩ ይደረጉና «ታላላቆቹ» ይላካሉ፡፡ ያለ «ታላላቆች» ውጤት ይመጣል ብሎ የሚጠብቅ የለምና፡፡

ሌላው ቀርቶ በሀገራችን የፖለቲካ ሂደት ውስጥ አንዱ ችግራችን ይኽ «ትልቅ ሰው» ለምንለው ነገር ያለን አመለካከት ነው፡፡ እስኪ አስተውሉ፡፡ በፖለቲካው መድረክ ከስድሳ ስድስት ጀምሮ ያሉት ተዋንያን ተመሳሳይ ናቸው፡፡ አዘውትረን ተመሳይ ፊት ነው የምናየው፡፡ ከአንዳንዶቹ በቀር ወጣት መሪ አናይም፡፡ እነዚያው ሰዎች ደግሞ ወይ በሀብት የገነኑ፣ በእድሜ የሸመገሉ፣ አንዳች የትምህርት ወይንም የውትድርና መዓርግ ያላቸው እንዲሆኑ እንፈልጋለን፡፡ ለብስለታቸው፤ ለዕውቀታቸው፣ ለአመራር ችሎታቸው እና ለጀግንነታቸው ከምንሰጠው ቦታ ይልቅ ለአካላዊ፣ እድሜያዋ እና መዓርጋዊ ሁኔታዎች የምንሰጠው ቦታ ይበልጣል፡፡ ስለዚህም ፊልሙ ሲቀያየር እንኳን እነዚያኑ ተዋንያን ብቻ ነው የምናየው፡፡

ቴሌቭዥናችሁን ከፍታችሁ የአክሲዮን ገበያውን እስኪ ተመልከቱ፡፡ «እንዲህ ያለ ኩባንያ ተመሠረተ፤ አክሲዮን እየሸጠ ነው፤ መሥራች ሁኑ» እየተባለ ይተዋወቃል፡፡ ሃሳቡን ያመነጩት፣ አስተባባሪዎች እና መሥራቾች በጠረጲዛ ዙርያ ተደርድረው ፈገግ እያሉ ይታያሉ፡፡ «ትልልቅ ሰዎች»፡፡ በእድሜ ጠና ያሉ፤ ትከሻቸው ለኮት የሚያመች፤ መነጽር ያደረጉ፣ ሰውነታቸው ሞላ ሞላ ያለ፣ ሲፈርሙ እጃቸው ወዝ የጠገበ «ትልልቅ ሰዎች»፡፡ መጀመርያ ነገር ወጣቶቹ ቢሰባሰቡ የሚያምናቸው የለም፤ ወጣቶቹ ቢቀላቀሉም የሚቀበል አይገኝም፡፡ ሀብትም ከ«ትልልቅ ሰዎች» ውጭ ይገኛል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ኧረ ምን ወጣቶቹን ብቻ ሴቶቹስ የአክሲዮን መሥራች እንዳይሆኑ ማን ነው ያገዳቸው? የግድ ለሴቶች ተብሎ ብቻ መቋቋም አለበት ?

አንድ በሚሊዮኖች የሚያንቀሳቅስ ኩባንያ ባለቤት የሆነ ጓደኛዬ ለአንድ ጉዳይ ማመልከቻውን ይዞ አንድ ቢሮ ይሄዳል፡፡ ጸሐፊዋ ደብዳቤውን ትቀበልና ካነበበችው በኋላ «ለዚህ ጉዳይ ራሳቸው የድርጅቱ ባለቤት ቢመጡ ነው የሚሻለው» ትለዋለች፡፡ እርሱ ቀልደኛ ነገር ነበርና እሺ ብሏት ይወጣና ተመልሶ ወዲያው ይመጣል፡፡ «ምነው የረሳኸው ነገር አለ» ትለዋለች፡፡ «ባለቤቱ ይምጡ ስለተባለ ነው» ይላታል፡፡ ግራ ገብቷት አየችው፡፡ «ታድያ ለምን አትነግራቸውም» አለች ጸሐፊዋ፡፡ «ሰምቼ ነው የመጣሁት» አላት፡፡ ይበልጥ ግራ ስትጋባ እየሳቀ «ባለቤቱኮ እኔ ነኝ» ብሎ አረዳት፡፡ ምን ታድርግ እርሷ «ትልቅ ሰው» ነዋ የጠበቀችው፡፡

ሌላው ቀርቶ አንዳንድ ማኅበረሰብ «ትልቅ ሰው» ለሚለው መዓርግ የሰጠው አለባበስ አለ፡፡ ጉዳይ ለማስፈጸም ወደ አንድ ቢሮ ስትሄዱ ኮት፣ ሱሪ እና ከረባት ሽክ አድርጋችሁ፣ የመኪና ቁልፍ እያሽከረከራችሁ፣ ሞባይል ጆሯችሁ ላይ ገጥማችሁ፣ መነጽራችሁን አናታችሁ ላይ ሰክታችሁ፣ ድምፃችሁን ጎርነን እያደረጋችሁ ካልሄዳችሁ፤ ያለበለዚያም የእድሜያችሁን ልክ የሰውነታችሁ ገጽታ ካላንፀባረቀባችሁ፤ ከ«ትልቅ ሰው» የሚቆጥራችሁ አታገኙም፡፡ ሴት ከሆናችሁም ሙሉ ቀሚስ፣ ወይንም ኮት እና ቀሚስ፣ ያለበለዚያም የአበሻ ቀሚስ ካላደረጋችሁ፤ «የኔ ልጅ» እያላችሁ ካልተናገራችሁ፣ ነጠላ ቢጤ ደረብ ካላደረጋችሁ፣ ስትሄዱ ዘገም ካላላችሁ ማን ከ«ትልቅ ሰው» ይቆጥራችኋል፡፡

አንዳንድ ሱቅ ገብታችሁ ወደድ ያለ ልብስ እና ጫማ ስትጠይቁኮ ቁመናችሁን እና አለባበሳችሁን፣ እድሜያችሁን እና ነገር ዓለማችሁን ተመልክተው «ይወደድብሃል/ይወደድብሻል» ይሏችኋልኮ፡፡ በእነርሱ ቤት እናንተ ያንን ዕቃ ለመግዛት የሚበቃ ገንዘብ ልትይዙ አትችሉም፡፡ የእነርሱን የ«ትልቅ ሰው» መመዘኛ አታሟሉማ፡፡ ቤት እና መኪና ስትገዙማ ሁኔታችሁን በማየት ብቻ ደላላ ናቸው ወይንም ሊያደክሙን ነው ብለው የሚገምቷችሁ ብዙ ናቸው፡፡ እናም አንዳንድ ጊዜ «የለም፣ አይሸጥም፣ ባለቤቶቹ የሉም፣ተሽጧል» ሲሏችሁ የ«ትልቅ ሰው» መመዘኛ ስለማታሟሉ ልትገዙት አትችሉም ማለታቸው መሆኑንም ተረዱ፡፡

የእድር ስብሰባ ላይኮ ዘመናዊውን ትውልድ ያጣነው መክፈል አቅቶት አይደለም፡፡ ነገር ግን እርሱን ቁም ነገረኛ ብሎ የሚቆጥረው ስለማይኖር፤ እድሩም የ«ትልልቅ ሰዎች» እድር ስለሆነ ነው፡፡ በየሠፈሩ ያሉ እድሮች በዚህ «የትልቅ ሰው» አሠራራቸው ከቀጠሉ ወራሽ ማግኘታቸውን እጠራጠራለሁ፡፡

እናም እስኪ «ትልቅ ሰው»ነትን ለዕውቀት፣ ለችሎታ፣ ለብቃት ሰጥተን ትርጉሙን እንቀይረው፡፡ ልጆቻችንንም በዚሁ መልኩ እንቅረፃቸው፡፡ እኛም «ሰው ፊትን ያያል» የሚባለውን ትተን ሊታዩ የማይችሉትን የምናይበትን መንገድ እንፈልግ፡፡ ያለበለዚያ the big man theory ሀገርንም ትውልድንም ይገድላል፡፡

42 comments:

 1. ግሩም አመለካከት ነው ዳንኤል። ብዙ ቁም ነገሮችን የያዘ የስነ ጥበብ ጭማቂ ማለት ይሄ ነው። ሌሎችንም ግሩም ዓይነት ጥበቦች እንጠብቃለን ።

  ReplyDelete
 2. Dani, it is a nice view. I was reading and laughing. You put real and practical situations.
  God bless you .

  ReplyDelete
 3. ይገርማር!!! እኔም እንዲሁ አጠር ቀጠን ያልኩ ሰው ነኝ። ለመስክ ስራ ወደ ቤንሻንጉል ጉምዝ-አሶሳ ለአንድ ወር ያህ በሄድኩበት ወቅት ተመሳሳይ ነገር ገጥሞኛል። አንድ ቤተሰቤ ቢጤ ነው "ትልቅ ሰው" ነው፤ ታዲያ አንድ ሌላ ቤተሰቤ የሚሆን ሰው ከአዲስ አበባ ይደውልና ስለኔ፣ስለ ስራዬ ደውሎ ይነግረዋል፤ በተጨማሪም እንዲተዋወቀኝ እና ከቤቱ ወስዶ እንዲያስተናግደኝ ያስጠነቅቀዋል "ትልቁ ሰውዬ" ስንተዋወቅ እንዳጫወተኝ። ታዲያ ሰውዬው ተጨንቆ ተጠቦ ይደውልልኛል እኔም ከዛው ከአሶሳ በስልክ ተዋወቅኩት። ከሳምንት በሃላ ቅዳሜ ቀን ጠዋት ነበር ስልክ ተደወለ ደዋዩ ሰውየው ነበረ፤ የይቅርታ መአት እየደረደረ እስካሁን ሳልጠይቅህ ምናምን ... ካለ በሃላ ሊወስደኝ እየመጣ እንደሆነ ገለፀልኝ። አንድ የመንግስት መስራቤት ውስጥ ስልጠና እየሰጠሁ ነበርና የምወጣበትን ሰዓት ነገርኩት። ታዲያ አስጥርቶኝ ወጥቼ ሲያገኝው ምን እንዳለ ታውቃላችሁ? "ውይ አንተማ ትንሽ ልጅ አይደለህ እንዴ ላንተ ነው ያ ሁሉ የተጨነቁት?" ብሎ እርፍ። ታዲያ ዳኒ እንደገለፀው ቁመናዬ "ትንሽ ሰው" አደረገኝ አይደል የሚባል?

  ዳኒ ወንድማችን እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋልና ጥበቡን ያብዛልህ።

  ReplyDelete
 4. the big man theory......«ሰው ፊትን ያያል».... «ይወደድብሃል/ይወደድብሻል».....really amazzing

  ReplyDelete
 5. yes, the big man theory kills generation as you clearly put.

  ReplyDelete
 6. Thanks Dani!
  I was enjoying reading Ur views as well as the constructive comments. But today I get access before the readers give U comment.
  Let me tell U one thing. I was competing for a par-time job. They Called me after going through my CV. I'm a first degree graduate in Law with great distinction. I've graduated last year. When I appear before them, they become reluctant to accept me because I'm not the BIG PERSON. I'm too young, short, & talked with them with calm voice.Because I wanna have a job, I get the job After BEGGING them & telling them who I'm. But now I've got Another course to teach in their center after they've got proof from my students.
  "THE BIG MAN THEORY" of ETHIOPIANS must be changed in a way that the measurement be THE MERIT OF THE PERSON IN QUESTION. DINGAYIM SHIBET ALEW!
  MAY GOD BE WITH U ALL THE TIME!

  ReplyDelete
 7. what an insight!

  ReplyDelete
 8. Excellent! I have faced similar situations while shopping shoes(dress) back home. It really irritates when somebody judges you with your physical appearance only. This scenario is apparent in the "modern world", Europe. It is really hard for them to accept a dark skin person with mercedes car...they prejudge and think "he stole it from some one". They have also less trust for dark skin professionals. I remember the first time I went to interview for work...the boss(who was a lady) asked me where I came from...and I told her that I am from Ethiopia. And she assure me I will be the president of Ethiopia when I return back home after getting educated in Europe. Betam girm new yalegne....benesu bet ethiopia yetemare sew yelatem.

  "It is harder to crack a prejudice than an atom."

  Albert Einstein

  ReplyDelete
 9. ይህም አለ ለካ!!! ህዝብ ሁሉ ይህንን ማየትና ማገናዘብ ይችል ዘንድ አምላክ ይርዳን!!!

  ReplyDelete
 10. በስመ አምላከ ኩሎ!!
  በጣም ትክክል እይታ ነው!
  እኔ የገጠመኝኝ ነገር ላጫውትህ፡፡የምህንድስና ባለ ሙያ ስሆን የማንም ፖለቲካ ፓርቲ አባል ሁኜ ባላውቅም በስራ ላይ ግን ቀልድ የለም ሌትና ቀን እሰራለሁኝ የባለቤቴ የማይረሳ ድጋፍና በዚህች ትንሽ ጥረቴ እግዚአቢሔር ባርኮልኝና አግዞኝ ግዴታዮን በመወጣቴ ምክንያት ከሶስት በላይ የጥሩ ስራ ሽልማቶች በ 28 ዓመቴ አግኝቻለሁኝ፡፡በዚህ የተነሳ ከብዙ ባለስልጣትም ሆኑ የተከበሩ ሰዎች ለመገናኘት እድሉ ገጠመኝ፡፡አንድ ቀን ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብየ እየሰራሁ እያለሁኝ እንግዶች መጡና ወደ ኦፊስ እንዲገቡ ጋበዝኳቸው፡፡ምን ልታዘዝ አልኳቸው እነሱም አቶ እገሌ እንፈልጋለን አሉኝ በጣም አክብረውና አድንቀው፡፡የተጠራው ስም የኔ ቢሆንም ግን እነዚህ ሰዎች የሚጠቡቅትን ያሰቡትን ሰው ባለማግኘታቸው አዝኜ እሺ ልጥራው አልኩኝና ውጭ ደረስ ብየ ተመለስኩኝ፡፡ እስከ ክግማሽ ሰዓት አቶ እገሌ የተባለውን ሊመጣ አልቻለም ፡፡እንደገና ጠየቁኝና አሁንም ውጭ ደርሼ መጣሁኝ፡፡20 ደቂቃ በላይ ሲጠብቁ መጠራጠር ይጀምራሉ፡፡ ከጥቂተ ደቂቃዎች በኋላ ይቅርታ አቶ እገሌ አንተ ነህ እንዴ ብለው ጠየቁኝ በደንብ እስክታስተውሉ ነው እንጂ እዎ ነኝ አልኳቸው፡በጣም ደነገጡና በጣም ይቅርታ አድርግልኝ አቶ እገሌ በአእምሮኣችን የሳልነው እድሜ የጠገበ፣ ረጅም ፣ወፍራም፣ የሚያሰፈራና፣ ወዘተ....በጣም አዝኜ ሰው በስራው እንጂ በሌላ ባይለካ መልካም ነው ብየ…….፡፡በስራ ጉዳይ በመምጣታቸው ምክንያት የሚፈልጉትን ስራ አቀላጥፌ ጨርሴ ስሰጣቸው አመስግነው በድጋሚ ይቅርታ ጠይቀውኝ ተለያየን፡፡ በአሁኑ ግዜ ጓዶኜቼ ሆነዋል፡እናም ሰው በወጣትነቱ አይታመንም ያለው ማን ነው!እንዲያውም ያልተበረዘ!ይገርምሃል በዚህ የሰባት ዓመት የስራ ግዜዮ በተለይ በኛ ሙያ ወጣቱ እያበላሹት ያሉትን በእድሜ የጠገቡ ወዘተ....ናቸው፡ሌላ ላንሳልህ የብዙ ነገር ጥናቶች እና ድዛይኖች በውጭ ባለዜጋ ካልተሰራ አንቀበልም የሚሉ ብዙ ሰዎች ገጥመውልኛል ይግርምሃል ብዙ እሳት የላሱ ባለሙያዎች እያሉን እነሱን የንሮ ጫና እንዳይከብዳቸው ለውጭ ዜጋ የሚከፈለውን ብር እየተከፈላቸው እንዴት አገራቸውንና ህዝባቸውን መቀየር አይችሉም፡በርግጠኝነት ይቀይርዋታል፡አንድ ትልቅ ሰው ያደረገውን ልንገርሀ ባላሀብት ነው የሎጅ ጥናትና ድዛይን ሊያሰራ ፈልጎ አንድ ያገር ውስጥ ባለሙያ ጋር ይገናኛል፡የክፍያ ጉዳይ ለሱ ምኑ አልነበረም፡የውጭ ዜጋ የሚሰራውነ በአገሬ ባለሙያ ላሰራው ብሎ ጠቀም ባለ ብር ተዋውለው ተስማሙ ይገርምሃል፡፡ ባለሃብቱ በመጀመርያ ያደረገው ምን አንደሆነ ልንገርህ በራሱ ወጪና አበል በኢትዮጽያ ያሉትን ሎጆችና የብሄር ሰቦችን ባህልና አኗኗርና የስነ ህንጻ ሙያ ባለሙያውን ማስጎብኝት ነበር፡እንዳለውም የተሳካ ስራ ተሰራ፡፡ስለዚህም ወጣቶቻችንና እንሰቶቻችን እንመናቸው፡፡let give them chance to change the live of ours!!@!...
  “ስብሃት ለእግዚአቢሔር አምላከ አበዊነ”

  ReplyDelete
 11. Yes, We failed to exploit dynamic people because we see thir physical appearance.
  May God help you to do more!

  ReplyDelete
 12. ዳኒ

  በህይወቴ የሰውን ልጀ ከታዘብኩባቸው ጉዳዮች አንዱን በማንሳትህ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ መታረምም አለበት፡፡

  ሰዎች ስብዕናህን፣ አመለካከትህን፣ ታማኝነትህ፣ ጨዋነትህን፣ ችሎታህን ... ወዘተ በዕድሜህ፣ በአለባበስህ፣ በመልክህ፣ በቁመትና ቅጥነት ውፍረትህ፣ በምትቀባው ሽቶና ቅባት፣ በዘር ሐረግህ/በመገኛህ፣ በገንዘብህ... ለክተው እንዲህ ነው በማለት የተሳሳተ ግንዛቤ ሲወስዱና ለአንተ ዝቅተኛ ግምት ሲሰጡ እስከ አሁን ባሳለፍካቸው የስራ ህይወቴ እና ማህበራዊ ግንኙነቴ ታዝቤአለሁ፡፡ እኔም ለራሴ እንዲህ ያለ ታላቅ ስህተት ውስጥ እንዳልገባ ተምሬአለሁ፡፡

  ወንድሞቸ እህቶቸ ሆይ ሰውን ውስጡን ጠልቀን ሳንመረምር በውጫዊ ማንነቱ ብቻ እንዲህ ነው ለማለት አንቸኩል፡፡

  ReplyDelete
 13. በጦርነት መጡ እንጂ እኮ አቶ መለስን በፊዚካላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ማን ያደርጋቸው ነበር በዚህ አይነት?

  ReplyDelete
 14. አባግንባር (ከሮማ) አባግንባር (ከሮማ)May 7, 2010 at 3:42 PM

  ሠላም ዳኒ፡
  ዛሬ ደግሞ የሁሉንም ቤት አንኳኳህ አይደል?
  እኔ ደግሞ እንዲህ ሆንኩልህ፤ እግዚአብሔር ይመስገንና እኔም የሆነ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ አስተምራለሁ፡፡ ለአንደኛ አመት (አዲስ ገቢ) ተማሪዎች አማካሪ ሆኜ ተመደብኩና የመመዝገቢያ ቅጻቸው ላይ እየፈረምኩኝ ነበረ፡፡ ሰልፉ በጣም ረጅም ከመሆኑ የተነሳ እና የተማሪው ጫና ስለበዛ እባካችሁ ትንሽ አየር እንዳገኝ ከፈት ከፈት አድርጉ ብዬ ወደ ውጪ ወጣ ስል አንዱ የተማሪ አባት “ይሄ አቶ እከሌ የሚባለው ምንድነው የሚሰራው ለመሆኑ” እያሉ የቁጣ መዓት ያወርዳሉ ከሠልፉ አጠገብ ሆነው፡፡ ልጃቸው ሰልፉ ውስጥ እንደሆነ ገባኝና ምንም ሳልናገር ፈገግ ብዬ መለስ ስል ተከትለውኝ ገቡና “ስማ አንተ” አሉኝ “አቤት” አልኩአቸው:: “ቆይ ማነው እዚህ የሚፈረመው ለእነዚህ ተማሪዎች? ልትጠራልን ትችላለህ አትችልም ንገረኝ!” አሉኝ:: አ…አ.. አይ ይህች ነገር ዱላ ማስከተሏ አይቀርም አልኩና በሆዴ “እባክዎትን ተማሪዎቹ ስለበዙ ነው እሳቸውም ይፈርማሉ ይረጋጉ አልኳቸው”፡፡ በጎን ግን ከፊት ለተሰለፉት እየፈረምኩላቸው ስለነበረ ያ የሚፈልጉት ሰውዬ እኔው ራሴ መሆኔን ሲረዱ ገልመጥ አረጉኝና እንደ መገረምም እንደመደንገጥም ሆነው ይወጣሉ፡፡ መጨረሻ ላይ እንደዚያ ሲቸኩሉ የነበሩት ትልቅ ኮት የለበሱ ሰውዬ ፊርማውን ጨርሼ እስክወጣ ጠብቀው የተናገሩኝ ነገር ነው ያሳቀኝ፤ “ምነው ልጄ ያለ ዕድሜህ ኮሌጅ በጥሰህ ጉድ አረከኝ እኮ፡ እንደው ትንሽ ከበድ የሚል ኮት ደርብ እንጂ ሰውም እንዳይሳሳት” ሲሉኝ ግርም እያለኝ በፈገግታ ተሰናበትኳቸው እልሃለሁ፡፡
  ብቻ ብዙ ሰው የየራሱ ገጠመኝ ስላለው እዚህኛው ጽሁፍህ ላይ ቢያቀርብ ብዙ ቁምነገርና አዝናኝ ነገር እናገኝበታለን ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ብች ይህች የቁመትና የኮት ነገር ብዙ ጎድታናለች፡፡

  ReplyDelete
 15. አ/ሚካኤልMay 7, 2010 at 3:51 PM

  ዲያቆን ዳንኤል
  እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህ ያብዛልን
  ዕድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን።እኛም አድናቂዎች ብቻ ሳንሆን ተጠቃሚዎች ያድርገን።
  እንዲህ ያለውን ለማን ይቻለዋል?
  በርታ ቀጥል

  ReplyDelete
 16. ይገርማል ባካችሁ!እገሌ ሲባል የጠበቅሁት በጣም "ትልቅ ሰዉ" ነበር፡፡

  ReplyDelete
 17. ዉድ ዳኒ እግዚአብሔር ይስጥልን! በእውነቱ ሁል ጊዜ የሚገርመኝን ጉዳይ እንዲህ ተብራርቶ ስመለከት በጣም ነው ደስ ያለኝ። በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ የሥራ ኃላፊነት ላይ ያሉ ወጣት ኢትዮጵያዊያን ትልቁ ችግር ይመስለኛል። እንደኔ እንደሚመስለኝ ሕብረተሰቡ ያልለመደው ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ የመስሪያ ቤት "demographic" ለውጥ እየተካሄደ ነው። በመጀመሪያዎቹ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው የተለያየ የሥራ ኃላፊነት ላይ የነበሩት አንጋፋዎቹ ጡረታቸውን አስከብረው ቦታውን ሲለቁ ኮሌጅ እየበጠሰ በከፍተኛ ቁጥር የሚመረቀው መሥሪያ ቤቶችን አጥለቀለቀ። ዩኒቨርሲቲው፤ ሆስፒታሉ፤ እንዲሁም ሌሎች የትላልቅ ሰዎች ቦታዎች ሱሪ ባልጠበበው ሸሚዝ ባላጠረው ተክለ ቁመናው ምንም ግርማ ሞገስ በሌለው ትኩስ ኃይል ተያዘ። ይህንን ፈጣን ለውጥ ህብረተሰቡ ቶሎ ሊገነዘበው አልቻለም። ምናልባት በሂደት ይቀየራል የሚል እምነት አለኝ። አሁን ያለው ትውልድ ለቀጣዩ ቦታ ሲለቅ ተመሳሳይ መደናገጥ ይፈጠራል ብዬ አልገምትም። እርግጥ አንድ አለማቀፋዊ እዉነታ አለ። በእድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች ሰከን ያሉ ናቸውና ከፍተኛ ውሳኔ በሚሰጡባቸው ቦታዎች ቢቀመጡ የሚወስዱት ውሳኔ እርጋታ የተሞላበት ስህተት የማይበዛው ይሆናል ተብሎ ይታመናል። ሆኖም ግን እኛ ወጣቶች አባቶቻችንንና እናቶቻችንን ልናስተምራቸው ይገባል። ለምን ሥራዬን ተመልክተው አያከብሩኝም ብለን ልንገርም አይገባም። ዋናው በጠንካራ እምነታችን ጎልያድን መጣል ነው። ክብሩ ኋላ የሚመጣ ይሆናል። በፊታቸው ስናልፍ ያላስታወሱን ሥራችንን ካዩ በኋላ ይገረማሉ። አመለካከታቸውንም ይቀይራሉ።

  ReplyDelete
 18. በስመ እግዚአ ኩሎ!
  ሰላመ እግዚአቢሔር በድጋሚ ይድረሳችሁ!
  ሌላም ተጨማሪ ታሪክ ልንገርህ!ቅድም እንደገለጽኩት ባለት ዳር እና የ33 ዓመት ጎልማሳ ነኝ፡፡ባለቤቴ ደግሞ የ23 ዓመት ወጣት ነች፡፡የሶስት ልጆች አባት ስሆን እላይ እንደገለጽኩት የምህንድስና ባለሙያ ነኘ፡፡ምን ገጠመኝ መሰለህ መቼስ በሙያችነ ታማኝ ሆሆ መስራት ማገልገል ችግሩ ሁሉም ያውቀዋል!እስከ መገደል ድረስ ያደርሳል!(እግዚአብሔር ጠበቀኝ ታሪኩ ሌላ ግዜ)እና እንደዚህ ያሉ ፈተናና የኢኮኖሚ ፈተና ሲገጥመኝ በጣም ተጨነኩኝ በጣም ስቃይ ሆነ፡፡በዚህ ሰዓት የምትሆነውን ይጨንቀሃል ያ ሁሉ የማትበገር ሰው አሁን አምነት እየት እንደሚደበቅ ግራ ይገባሃል፡፡ባዶነት ተሰማኝ፡፡መንፈሳዊ ጓዶኞቼ ምን እንደነካቸው መንፈሳዊ ድጋፋችው ከለከሉኝ፡፡በህይወቴ በጣም ፈታኝ የሆኑት ከ10 ዓመቴ ጀምሮ የገጠመኝ ሲሆን ይህ ግን በጣም ከበደኝ፡፡እናም ከስራ ወደ ቤተ ስገባ ሁለተኛዋ ልጄ ተኝታ ነበረ የ3 ተኩል ዓመት ህፃን ልጅ ነች፡፡ምሳ ልንበላ ከባለቤቴ ጋር ቁጭ ብለን እያለ በሃሳብ ጭንቀት ላይ ነበርኩ፡፡በቤታችን የእመቤታችን ስእል አለችን እናም ልጄ ከእንቅልፍ ብድግ ብላ ተነሳችና እመቤታችን ለምን ሁለት መስቀል ታደርጋለህ እለችህ አለችኝ፡፡በጣም ደነገጥኩና መቼ አለችሽ አልኳት እስዋም በጥያቄዮ ደንግጣ ብዙ ግዜ ስእልዋን ደጋግማ እያየች ያችን ነው ያለችን አለችኝ...አሁን፡፡ማመን አቃተኝ እመቤታችን በቤታችን ይህ ነገር አደረገችልኝ ብዮ በጣም ገረመኝ ፡፡ልጆቼ የእግዚአብሔር አደራዎች ናቸውና አደራ በሰጠኝ ልጆቹ መከረኝ እኔም አሀ.....ብዮ ተረጋጋሁና በእምነት እንደ ልጅነት ህይወቴ መቀጠል እንዳለብኝ ወሰንኩኝ ባለቤቴም ወሰነች፡፡አሁን ነገሮች ተስተካክለው ሰላም ንሮ እየኖርን ነው፡፡እናም ይህች ህፃን ልጄ የእግዚአብሔርና የእመቤታችን መልእክተኛ ሆና ከህይወታችን ከችግር እንድላቀቅ ምክንያት ሆነችኝ፡፡ እኛ ልጆቻችን ወንድሞቻችን እየደገፍን እያከበርን ከሆነ አይደለም ወጣቶችና እንስቶች ይቅርና ህፃናትም የድህነት የመከራ ህይወታችን ለማስተካከል መንገድ ወይም መነሻ ይሆኑናለ እና ማክበር ሃላፊነት መስጠት ይገባናል እላይ እንዳልኩት የኛን ህይወት ይቀይራሉና፡፡ በአካል አዲስ አበባ ብትመጣ ብዙ ገጠመኞች ላወራህ ነበር፡፡የምትፈልገኝ ከሆነ በ mesgina_live@live.com ተጠቀም፡፡
  ወስብሃት ለእግዚአብሔር አምላከ አበዊነ!

  ReplyDelete
 19. የልጅ ሽማግሌ ከተገኘ እንግዲህ መልካም ነው» አሉና አጎትዬው ነገሩን አደላደሉት፡፡Another excellent view on our society!!!We need to be more like the "uncle"
  mentioned above!!!Thx Dn. Daniel!!!

  ReplyDelete
 20. "Let us promote this blog in every direction if we care for this generation."

  ReplyDelete
 21. selam lante yihun d.Daniel that was one of ur excelent views thanks for that and God bless u.i want to say this i think this tradation comes from the bible as you know one of Solomon's son wanted an advice and he asked the elders they told him what he sould do in a right way but the yung ones advice him in a very wrong way and he lost everything including his life if i am not wrong though we took that tradation in a wrong way just to point out that every forgive me for my poor spelling

  ReplyDelete
 22. wow!!! excellent views Dani Berta.

  ReplyDelete
 23. እግዚአብሔር ይስጥልን ዲ/ን ዳንኤል

  ግን ግን ትልቅ ሰዉ ማነዉ? መልሱ "ዘመናዊ ት/ት የተማረ" እንደማትሉኝ አዉቃለሁ። የ"ትልቅ ሰዉ"ነት ፊቺ (definition) እንደየሰዉ የሚለያይ ይመስለኛል። ታዲያ እርስዎ ትልቅ ሰዉ የሚሉት ማንን ነዉ? እስቲ አንድ በሉኝ።

  አመሰግናለሁ።

  ReplyDelete
 24. Kalehiwot Ysemalen Dear Dani

  ReplyDelete
 25. that is excellent article.

  ReplyDelete
 26. ዲያቆን ዳንኤል


  ዳኒ መቼም አንተ ከማታውቀው ሰባዊ ፍጡር ስለአንተ ቢነገርህ አንተ እንዴት እና በምን መልኩ መስማት እንዳለብህ.፣.ከአምላክህ ተምራሃል…መቼም ባለንበት 21ኛው ክፍለ ዘመን..መንፈሳውዊ ስጋዊ ጥበብን ይዞ መገኝት ከአምላክ ካልተሰጠ በቀር ለማንም አይቻለውም ..ዳኒ አንተ መክሊት አለህ ፣መክሊትህ ለእኔ በአባቶችሽ ፋንታ ልጆችሽ ተተኩልሽ ተብሎ የተነገረለት ይመስለኛል
  እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክ፣በኑሮህ ኩሉ አይለይህ፣በመውጣህ እና በመግባትህ ካንተጋር ይሁን፣በቅዱስ መጽሀፍ እንዲል
  እኔ አድናቂህ ብቻ ሳልሆን እግዚአብሄር ባንተ ላይ በሚያደርገው ነገር ሁሉ ተጠቃሚ ነኝ።

  ማንጎ ከ ስዊትዘርላንድ

  ReplyDelete
 27. Dear Dani,

  Bundle of thanks! I have faced such kinds of problems on different times. Especially, I have presented scientific papers. The chairman mostly said I call up on Dr. X. In our country to present paper you must be Dr. This idea must be avoided.

  Mr. X
  (Holland)

  ReplyDelete
 28. exactly what has been going on in our society!! lets change our mind and stop classifying and undrmining people just by physical appearance

  ReplyDelete
 29. As usual nice observation Dn Daniel. Without revealing too much information I will share two negative and one positive experiences related to this issue. First, is a friend who demoted himself to be the secretary of the NGO established by him to have a gray hair man as a chairperson; very funny. No body was willing to talk to him about the idea, just because they thought the idea is too big for a young guy like him. Unfortunately the event happened in one of the countries institute supposedly have some of the elite brains. Another time I went to a house furniture shop with a friend who just came back from Europe to buy a bed. Unknowingly we run into a shop that sells very expensive stuff or to be sold to "old man" by unwritten law. A regular employee of the shop murmured the price and left us without expecting any reply. Mind you we were not both short but slim and young. My friend got angry and i burst into laugh. Indeed the price was too much but as a customer we were supposed to be attended equally. The positive experience involves acknowledgment by a brave well educated man (gray hair man) who publicly admitted that he did not dare to think what the young employees tried to do. Dani tselotehe dereso lemayete yabekane, Fetari Ethiopian yetadege!!!!

  ReplyDelete
 30. ለጽሁፉ እግዘር ይስጥልን።

  ነገር ግን ይቅርታ ይደረግልኝና በአንድ ነገር አልስማማም። አንድ ሰው ለተሾመበት ቦታ - ለተመደበበት ሃላፊነት የሚመጥን ውጫዊ ማንነት ሊፈጥር ይገባል። የፈለገ ልጅ ሆኖ ሚኒስትር ቢደረግ .. ገና ለገና ዋናው እውቀቱ ነው ተብሎ በቁምጣ ስራ ሊመጣ አይገባም። ወይም የአንድ ኩባንያ ሃላፊ ሆኖ ... በፒጃማ እነ ጋር መጥቶ ስራ አስኪያጅ ነኝ ቢለኝ መታወቂያውን ካላየሁ አላምነውም።

  ወጣቶች ለሃላፊነት ሊበቁ እንደሚችሉ ብንግባባም - ውጫዊ ማንነታቸውንም ግን ሊያስተካክሉ ይገባል። እነ ነጋዴ ሆኜ አሮጌ ሸሚዝ እና የተቀደደ ጫማ አድርጎ መጥቶ የ 500 ብር ልብስ ቢጠይቀኝ . ይበዛብሃል ይቅርብህ ልለው መብት ያለኝ ይመስለኛል። ገና ለገና ተምረናል ተብሎ አለባበስና አነጋገርን አለመጠብቅ ትክክል ነው ማለት አይደለም።

  ያለንበት አሜርካም ቢሆን ለሥራ ቃለመጠይቅ ስንጠራ .. አለባበሳችን እና ሁኔታችን በጣም ወሳኝ ነው። የፈለገ ዲግሪ ቢኖረኝ .. ሌላው ቀርቶ ታቱ አርገን ጆሯችን ላይ ሎቲ አንጠልጥለን ብንመጣ .... በዲግሪው ብቻ አይቀጥሩንም። እና የዳኒ ጽሁፍ ውጫዊ ማንነት ዋጋ የሌለው እንዳያስመስል እንጠንቀቅ።

  ReplyDelete
 31. እኔም ቁመቴ ረጅም ቢሆንም በጣም ቀጭን ነኝ ፊቴም የልጅ እግር ይመስላል:: እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ የከፍተኛ ት/ት አጠናቅቄ በአሜሪካን ሀገር እኖራለሁ:: ሰውነቴን በመመልከት የሚገመግመኝ ሰው ብዙ ነው ነገር ግን ከሀገሪ ከዚህ ይሻላል:: በአሜሪካን ሀገር ሰው የሚገመገመው በእውቀቱና በአስተሳሰቡ እንጅ በቁመናወ አይደለም:: የትኛው ይሻላል የሚለውን ዲ/ን ዳንኤል አስተያየት እንዲሰጥበት እተወዋለሁ:

  ReplyDelete
 32. D.n Daniel

  እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህ ያብዛልን
  ዕድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን።እኛም አድናቂዎች ብቻ ሳንሆን ተጠቃሚዎች ያድርገን።

  from Alexandria VA USA

  ReplyDelete
 33. I face the same story but I do not give attention for it. Thank you my dear brother Dn. Dani.

  ReplyDelete
 34. Dearest Dn Daniel thanks for your view. When I read this article I was really thinking if I told you my stories, although I never meet you in person. Being a 33 years old, MA, and mother of three, I have experienced the same stories, except that it is not only with Ethiopians. As you know most of our non Ethiopian African brothers and sisters, are relatively bigger than us. By chance, I worked with Zambians, Kenians, South Africans and Nigerians while I am a very small sized woman. Most friends tease me saying “Ehil wedajun ayitegam” .
  I faced the same challenge that the lady in your article faced from the interviewers , from the interview I had with Zambians. After, I joined the organization, my boss, who was one of the member of the panel in the interview told me that “I was tempted by your baby face”. Thanks for her being open any ways. Later on she started to call me “my girl” and I used to claim that I am a professional woman not a girl. By the way I always wear suit like professionals.
  Last year, I was pregnant for the third time, and another Nigerian colleague, who has the same position like me but her size is “damn big” (which she hates), she saw me after about three months. After a big hag and warmest greetings, she said “oh! you are having this for the third time?.... very good at least it helps you to look big”.
  Now I am working with South Africans and have one friend who is very close and knows my feelings. Both of us have the same position, but she wears ordinary clothes and looks big, whereas I always wear suits but still look “small”. She always sympathizes for huge cost to maintain my personality as "big" So, now I decided not to bother about my size. So long as I can do my work.So I pray and be greatful for “Egziabher Girma Mogesun Yisetegn zend setognalim”.

  Back home, especially those boutiques in Piasa who get tired of showing their staff rather prefer to say “lanchi ayihonishim”- that is luck of responsibility. Afterall most of them are not professional salespersons. They change prices as they wish and the price that one pays is different from the other – especially they increase on the “ferengees”. That is beyond this big man theory. It is “Cheating”. And as you know, in most of African countries that I have visited prices are fixed. Anybody can visit and either buy or plan to buy according to the pocket size- personality doesn't matter. I appreciate if those butiques could encourage this "fixed price approach".

  I know I am not good in narrating as you do. Thanks for allowing us discuss such important issues.

  T/D

  ReplyDelete
 35. Tebarekilign-Dani,this article forced me to write my friend's unforgettable occasion.He was& still is vice president of one of our universities,however, he has not fulfil the so called "tilik sew".At one fine morning he was at the office of the mayor with a mission of his institution."His excellency"-the mayor , said that " this is a big issue I should deal strongly with those who are at the high ranks of the university. So, go back &tell them".he(my friend) has internal strength & confidence but it was difficult to convince his mind initially.
  " we don't mark our age by the years we count,but by the scores we make our goods deeds".

  ReplyDelete
 36. thanks to GOD TO GIVE US SUCH KIND OF TIC...

  ReplyDelete
 37. ውድ ዲ. ዳንኤል፡
  ሠላም ላንቴ ይሁን፡
  ያነሳሄው ጉዳይ አንድ ገጠመኜን እንዳካፍል ግድ አለኝ፡፡ እነሆ፡፡
  ከጥቂት ዓመታት በፊት ገና ከዩኒቨርሲቲ ተመርቄ እንደወጣሁ በሌላ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በማስተማር ሥራ ተቀጠርኩ፡፡ በጣም ወጣት ነበርኩ፡፡ ቁመናዬም እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም፡፡ ለትርፍ ሰዓት ስራ ሌላ ተቋም ላስተምር ስሄድ እኔ የማስተምርበት ክፍል በሌሎች ተማሪዎችና በሌላ መምህር ተይዞ ጠበቀኝ፡፡ ዝም ብዬ ቆምኩኝ፡፡ ተማሪዎቼ ቀርበው አንኳኩ፡፡ መምህሩ ወጥተው ዙሪያውን አየት አደረጉና ተመልሰው ገቡ፡፡ ዕድሜአቸው ገፋ ያለ ነው፡፡ በጊዜው አጠናቅቀው ልወጡ መስሎን ብንጠብቅም ማስተማራቸውን ቀጠሉ፡፡ ተማሪዎቼ እንደገና ስያንኳኩ መምህሩ ውጥተው “መምህራችሁ እስኪመጣ ትንሽ ታገሱኝ” አሉ፡፡ ተማሪዎቼ “መጥተዋል” ስሏቸው “ዬት አለ?” ሲሉ የያዝኩትን ቾክ ሳሳያቸው “አንቴ ነህ? Excuse me! It is your physic” ብለው እየተጣደፉ ገብተው ተማሪዎቻቸውን አሰናብተው ቦርሳቸውን ይዘው ክፍሉን ለቀው ወጡልን፡፡ እስከ አሁን ሳስታውሰው በጣም ይገርመኛል፡፡ በኋላ ስንተዋወቅ የአንድ መሥሪያ ቤት ሠራተኞች ነን፡፡ ይሄው አሁን ለPhD አብረን እየተወዳደርን ነው፡፡
  እግዚአብሔር ካንቴ ጋር ይሁን፡፡ ጸጋውንም ያብዛልህ!

  ReplyDelete
 38. good point Dn. what do you think about people who think ladies always work secretarial works. am a lady with MSc working in a senior position but whenever a customer comes he/she asks me for my boss. and it takes me long to convince them that I can handle their case.

  ReplyDelete
 39. ሰዎች ብዙ ይላሉ፣ብዙ ማለት አልተከለከለምና። እንደዚህ አይነት እይታ ግን ከላይ የተሰጠ ነው።በዚህ ብዙውን እያስተማርክ ነው።
  እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህ ያብዛልን፡እኛም ተጠቃሚ ያድርገን!

  ReplyDelete
 40. ሔኖክ (San Diego)May 24, 2010 at 11:37 AM

  ይገርማል ዳኒ
  ይህን ሳነብ አንድ አስተማሪዬ የነገሩን ትዝ አለኝ
  ሴትዬዋ ልጃቸው ውጪ ሀገር ነው። ታድያ ይደውልና እናቱን አንድ ዶ/ር ጓደኛውን እንዲጋብዙለት ይጠይቃቸዋል። ታድያ ዶክተሩ ከሌላ ሰው ጋር ግብዣው ላይ ይገኛሉ። እነዚህን ሰዎች ሴትዮዋ እንዳገኙ ማንንም ሳይጠይቁ ወፈር ያሉትን ጥሩ ልብስ የለበሱትን ሰው ዶ/ር እያሉ ይጠሯቸዋል። ወደ እጅ መታጠብያው ሲመሯቸውም ዶ/ር ይቅደሙ ይሏቸዋል። የጨነቃቸው ሰውዬ ጠጋ ይሉና-እኔ አይደለሁም እሳቸው ናቸው ዶ/ሩ ይሏቸዋል።
  ሴትዮዋም በቁጭት "አይ ደርግ ማንን እንኳን ዶ/ር እንደሚያደርግ አያውቅም።" ብለው አረፉት::

  ReplyDelete
 41. min ebakih bezih zuriya yalideresebin yinoral ende? gin hasabu menesatu betam des yilal...keteketeriku huletenga ameten wedeyazikubet and yemenigisit University endititewawekeng kebeteseb akakababi yetelakech andit fresh temari yalechingen aliresawum...silik tesetuat sileneber dewulaling linigenang bete metach gena kasiteyayetua gemiro gira tegabita simen eyeterach betiritare degagima teyekeching ene mehonen binegiratim eyayech mamen akatat esua wusit yalechiw ye University memihirit yichi yemitayat aydelechim...keza behuala bezaw kerech lenegeru kerebat...yehone hono gin yih batekalay yegeneratinu chigir yimesilingal malete tinish memisel...by the way I like the cot'"It is harder to crack a prejudice than an atom."...
  thanks Dn.Daniel

  ReplyDelete