Sunday, May 23, 2010

100%


ሦስት ምሁራን ያቀረቡት ጥናት ተጠቃልሎ የታተመበትን ‹‹ያለ መቻቻል ፖለቲካ ሰማዕታት›› የተሰኘ መጽሐፍ ሳነብ ከ1969 - 1970 ዓ.ም የነበረውን የአገራችን ልዑላን እና ኀያላን ፍትጊያ በዐይነ ኅሊናዬ እየቃኘኹ ነበር፡፡ ከዚህ በፊት ካነበብኳቸው ዘመኑን ከተመለከቱ ጽሑፎች ጋር እያዛመድኩ አወጣሁ፤ አወረድኩ፡፡ ከዚያም ለምን እንደዚያ ‹‹ቀይ ሽብር›› እና ‹‹ነጭ ሽብር›› እየተባባልን መጨራረስ አስፈለገን? ያን ሁሉ ጭካኔ እና የእብድ ውሻ ሥራ ምን አመጣው? አብዮት ለማካኼድ የስንት ሰው ደም መፍሰስ አለበት? ውቃቤው እንዲረካ የስንት ሰው ?ሕይወት መቀጠፍ  አለበት? ከማይም እስከ ምሁር፣ ከሲቪል እስከ ወታደር እንዲያ ሲጨፋጨፍ አደብ የሚገዛ እንዴት ጠፋ?

እንደ እኔ እምነት የችግሩ አንዱ መነሻ ‹‹መቶ በመቶ የማሸነፍ አባዜ›› ይመስለኛል፡፡ ኢሕአፓም፣ መኢሶንም፣ ደርግም ሌላውም መቶ በመቶ አሸንፎ፣ ሌላውን አካል ደምስሶ በጠላቱ መቃብር ላይ የአብዮት ሐውልት ለመሥራት ነበር የሚያስበው፡፡ ሁሉም ለማሸነፍ እንጂ ለመሸነፍ አልተዘጋጀም ነበር፡፡ ሲያሸንፍ ደግሞ ያኛውን ወገን ከምድረ ገጽ ጠራርጎ አጥፍቶ ብቸኛ አሸናፊ ለመኾን ነበር የሚያስበው፡፡ ስለዚህም ሰውን መግደል፣ ማረድ፣ መጨፍጨፍ ዶሮ የማረድ ያህል እና ከዚያም በታች ቀልሎ ታየ፡፡

ሁሉንም ነገሮች መቶ በመቶ ማሸነፍ አይቻልም፡፡ የተወሰነ የመሸነፊያ መንገድ ማዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡ ብሸነፍስ ምንድን ነው የምኾነው፣ አሸናፊዬን በምን ዐይነት ሁኔታ ነው የማየው? ያሸነፈኝ ሁሉ ጠላቴ ነው ወይ? ሁለታችንስ አብረን ልናሸንፍ አንችልም ወይ? ወይም ደግሞ የአሸናፊነታችን መጠን ብቻ ሊለያይ አይችልም ወይ? ብሎ ማሰብም ያስፈልጋል፡፡

በምርጫ 97 የታየው አንዱ ችግር ይህ ይመስለኛል፡፡ ሁሉም ተቀናቃኝ አካላት መቶ በመቶ ወይም በዚያ ዘመን ቋንቋ ‹‹በዝረራ›› ለማሸነፍ ብቻ ነበር የተዘጋጁት፡፡ ገዥውም ፓርቲ ይኹን ተቃዋሚው መቶ በመቶ አሸንፈው አንዱ ሌላውን ድባቅ ለመምታት እንጂ አሸናፊነትን በተወሰነ እና መኾን በሚገባው መጠን ለመቀበል ዝግጁ አልነበሩም፡፡ አማራጫቸው ወይ ዜሮ አልያም መቶ ብቻ ነበር፡፡ በመካከል ምንም ነገር አልተገኘም፡፡ መቶውን ጠቅልሎ lመውሰድ እንጂ 99 ለማድረግ የተዘጋጀ እንኳን አልነበረም፡፡ ይህ ደግሞ ከአብዮቱ ዘመን ጀምሮ የለመድነው ጠባይ ኾኗል፡፡

ኔልሰን ማንዴላ ከተፈቱ በኋላ በተደረገው የመጀመሪያው የደቡብ አፍሪካ ምርጫ ፓርቲያቸው ብቻውን ሕገ መንግሥቱን ለማሻሻል የሚችልበትን የአሸናፊነት ድምፅ አላገኘም ነበር፡፡ ደቡብ አፍሪካን ከአፓርታይድ አገዛዝ ለማላቀቅ ግማሽ ምእት ዓመት ያህል የታገለው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ያን የአሸናፊነት አክሊል ያለመቀዳጀቱን በተመለከተ ማንዴላ ተጠይቀው ሲመለሱ፡- ‹‹መቶ በመቶ ማሸነፍ አልነበረብንም፡፡ ያ ቢኾን ኖሮ ማንንም ሳናማክር ሕገ መንግሥቱን እንዳሻን እናደርገው ነበር፡፡ አሁን ግን የግድ ከሌሎች ጋር መወያየት፣ መግባባት እና መተማመን ያስፈልገናል፡፡ ታዲያ ከሌሎች ጋር አብረን እንድ ንሠራ ከሚያደርገን ድል በላይ ምን ድል አለ?›› ነበር ያሉት፡፡

በእኛም ቤት እንዲህ የሚል ጠፍቶ ነው ያ ሁሉ ትርምስ የተፈጠረው፤ ብዙዎችም ያገኙትን ዕድል እንደ ዋዛ ያጡት፡፡

ይህ መቶ በመቶ ካላሸነፍኩ የሚያሰኝ አባዜ በአንዳንዶች የጓደኝነት እና የትዳር ሕይወት ውስጥም እናየዋለን፡፡ አብረው ኖረው፣ ተዋደናል ብለው፣ ስንት ታሪክ ሠርተው የነበሩ ባል እና ሚስት ወይም ጓደኛሞች በመካከላቸው ጠብ የተፈጠረ ዕለት ይኽው በሽታ ያገረሽባቸዋል፡፡ ሁለቱም መቶ በመቶ ማሸነፍ ስለሚፈልጉ ያኛውን ወገን ለመጉዳትም ኾነ አፈር ድሜ ለማስጋጥ የማይፈነቅሉት ድንጋይ አይኖርም፡፡ ሁለቱም ወገኖች ያኛው ወገን ተዋርዶ፣ አንገቱን ደፍቶ፣ ደኽይቶ፣ አጥቶ ነጥቶ፣ ተንከራትቶ፣ ወድቆ ካላዩት በስተቀር አይረኩም፡፡

በመካከል ሽማግሌ ገብቶ ለማስታረቅ ሲሞክር እንኳን ይቅርታ ካልጠየቀኝ/ ካልጠየቀችኝ የሚል እንጂ ይቅርታ ልጠይቅ የሚል ወገን ማግኘት ከባድ ነው፡፡ ያኛውን አካል እግር ሥር አንበርክኮ፣ ጫማ ሲስም እና ሲማፀን ማየት ያስደስታቸዋል፡፡ ‹‹የ'ታባቱ/ የ'ታባቷ ተንበርክኮ /ተንበርክካ ለመነኝ/ለመነችኝ›› ብሎ መፎከር ጀግንነት ነው፡፡ በተወሰነ መልኩ እንኳን ለመሸነፍ የተዘጋጀ ስለማይኖር ማስታረቁ ከባድ ይኾናል፡፡

ብዙ ጊዜ እንዲያውም ዕርቅ አስቸጋሪ የሚኾነው ሁለቱ ታራቂ ወገኖች መቶ በመቶ አሸንፈው መውጣት ስለሚፈልጉ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ'ኮ ከዕርቁ ስምምነት በኋላ ሁለቱም ወገኖች የሚተርኩትን ስንሰማ በቦክስ መድረክ አንዱ ሌላውን ዘርሮት ቀበቶ ውን ተሸልሞ የመጣ እንጂ ተደራድሮ፣ ተስማምቶ፣ ሰጥቶ እና ተቀብሎ፣ የተወሰነ ተሸንፎ፣ የተወሰነ አሸንፎ የተስማማ አይመስልም፡፡

የአገራችንን የንግድ ሂደት ስናየው ‹‹መቶ በመቶ የማሸነፍ›› ጠባይ የተጠናወተው ነው፡፡ ተደብቆ ወደ አምራች አገር ሄዶ፣ ተደብቆ ዕቃ አምጥቶ፣ ጉቦ ሰጥቶ ከጉምሩክ አውጥቶ፣ የእርሱ ዕቃ ብቻ ገበያ ላይ እንዲውል አድርጎ፤ ከዚህ ሁሉ በኋላ ደግሞ 100% አትርፎ ሲገኝ ነው የሚረካው፡፡ ሸማቹም ቢኾን ያለ ዋጋው ዋጋ ሰጥቶ ካልገዛ በቀር አይረካም፡፡ 30 በመቶ፣ 40 በመቶ፣ 50 በመቶ የሚባል ትርፍ ከትርፍ አይቆጠርም፡፡ ማጭበርበርን እና ደረጃውን ያልጠበቀ ዕቃ መሸጥን የሚያስከትለው ይህ ‹መቶ በመቶ ካላተረፍኩ› የሚያሰኝ አባዜ ነው፡፡

ተቋራጩም ቢኾን አውጥቶ አውርዶ፣ ደረጃ አሳንሶ፣ የዕቃ ጥራት ቀንሶ፣ ነካ ነካ አድርጎ ዛቅ ያለ ትርፍ ካላተረፈ የሠራ አይመስለውም፡፡ ትላንት የተመረቀ ሕንፃ ዛሬ ተሰንጥቆ፤ የምረቃው ዕለት ድልድዩ ሲጠገን፣ የርክክቡ ጊዜ መንገዱ ነቅቶ፣ አፉን ከፍቶ ኡኡ ሲል የምናየው ወይ ተቋራጩ መቶ በመቶ ለማትረፍ ሲል ከተገቢው ደረጃ በታች ሠርቶት ነው፤ አለበለዚያም ደግሞ አሠሪው መቶ በመቶ ለመብላት ሲል በዚህ መንገድ አሠርቶት ነው፡፡

አንድን አካል ፍጹም አድርጎ የማወደሱ አባዜ የመጣውም ከዚህ መቶ በመቶ ካላሸነፍ ከሚል ጠባይ ነው፡፡ ‹‹የእኛ የኾነው መልአክ ነው፡፡ ያኛው ደግሞ ሰይጣን ነው፡፡ በመካከል ምንም ነገር የለም፡፡ መልአኩን ስናወድስ ምንም ዐይነት እንከን አይታየንም ወይም ለማየት ፈቃደኛ አይደለንም፡፡ የማይሳሳት፣ ቅን አሳቢ፣ የልማት አርበኛ፣ ታጋሽ፣ ጀግና፣ ንጹሕ፣ ምንጊዜም በጎ ነገር ብቻ የሚሠራ አድርገን ነው የምንስለው፡፡ ይኽን እና ያንን ተሳስቷል ብለን ብንናገር ከ100% ስለሚቀንስብን ዐይኔን ግንባር ያድርገው ነው የምንለው፡፡ ያኛው ወገንም ቢኾን አንድ ቀን ተስቶ ስለ እርሱ ደካማ ጎን የተነገረ እንደ ኾነ tናጋሪውን እንደ ጠላት ነው የሚያየው፡፡

በተቃራኒው ደግሞ የሌላው ወገን ደግነት፣ ቅንነት፣ በጎነት፣ መልካም ሥራ፣ ንጽሕና የማይታየው አለ፡፡ እርሱ ስለ ተቃወመው እና ስለ ጠላው ብቻ ስንዴ ቢያመርት ‹‹እንክርዳድ ነው››፤ ጠላ ቢጠምቅ ‹‹አተላ ነው››፤ ጠጅ ቢጥል ‹‹አንቡላ ነው››፤ መን ገድ ቢሠራ ‹‹በዐፄ ኀይለ ሥላሴ ጊዜ የታሰበ ነው››፤ ት/ቤት ሲገነባ ‹‹ጥራት የለውም››፤ ከማለት ውጭ አንዷንም ቅንጣት በጎ ሥራ ለማየት ፈቃደኛ አይኾንም፡፡ «ከጠላት በጎ ነገር አይገኝም´ የሚለው አባዜ ስላለ መቶ በመቶ መጥላት እንጂ ‹98 በመቶ ለመጥላት› እንኳን ፈቃደኛ አይኾንም፡፡ ተቃራኒውን ጠላት አድርጎ ስለሚያየው የሚ ረካው መቶ በመቶ ሲጠፋ እንጂ በግማሽ ሲሻሻል ለማየት እንኳን በጄ አይልም፡፡

በአገራችን የፊልም ኢንዱስትሪ በማደግ ላይ ነው፡፡ ይህ ኢንዱስትሪ ከገጠሙት ፈተናዎች አንዱ ግን ‹‹መቶ በመቶ የማሸነፍ አባዜ›› ነው፡፡ የፊልሙ ባለቤት መቶ በመቶ ማትረፍ ስለሚፈልግ ብዙ ክፍያ የማይጠይቁ ባለሞያዎችን ለማሰባሰብ ይተጋል፤ ‹‹ገንዘብ የለኝም፤ ለሞያው ፍቅር ብዬ ነው›› እያለ በመለመን ያሠራል፡፡ አንዳንዶቹን በርዳታ፣ ሌሎቹን በአነስተኛ ክፍያ ያሠራል፡፡ እንዲህ እያደረገ ለወግ ለማዓርግ ከደረሰ በኋላ ፊልሙ ሲመረቅ የደረቀ አበባ ከመስጠት ያለፈ ባለውለታዎቹ ትዝ አይሉትም፡፡ ‹‹እነ እገሌ ረድተውኛል›› ለማለት እንኳን ይኮራል፡፡

በገንዘቡ ብቻ ሳይኾን በአሠራሩ ላይም ‹‹መቶ በመቶ የማሸነፍ አባዜ›› አለ፡፡ ባለቤ ቱም፣ ዳይሬክተሩም፣ ተዋናዩም እኔ ያልኩት ብቻ ይኹን ይላሉ፡፡ ማንም ለማንም የማርያም መንገድ እንኳን ለመስጠት ፈቃደኛ አይደለም፡፡ ሁሉንም ሊያግባባ/ ግን የተሻለ ውጤት ሊያስገኝ የሚችል መንገድ ከመፈለግ ይልቅ ሁሉም ለማሸነፍ ስለሚጥሩ እና በኋላ ፊልሙ ሲወጣ ‹‹እንደዚህ'ኮ ነበር፤ በኋላ'ኮ እኔ ነኝ እንደዚህ ያስደረግኹት›› ማለት ስለሚፈልጉ ፊልሙን ለመሥራት ከወሰደው ጊዜ በላይ የእነርሱ ገሃዳዊ እና ውስጣዊ ትግል ረጅም ጊዜን ይወስዳል፡፡

አሁን አሁን እየተለወጠ መጣ እንጂ'ኮ በመንግሥት ሚዲያ እና በግሉ ሚዲያ መካከል የነበረው ትግል «መቶ በመቶ ካላሸነፍኩ´ በሚለው አባዜ የተቃኘ ትግል ነበር፡፡ ለመንግሥት የብዙኀን መገናኛ የመንግሥት ስሕተት አይታየውም፤ ‹‹ቅዱስ መንግሥት›› ነውና፡፡ ለብዙዎቹ የግል ሚዲያዎች ደግሞ የመንግሥት ስሕተት እንጅ በጎ ጎኑ፣ መልካም ሥራው ፈጽሞ አይታያቸውም፤ ‹‹ርኩስ መንግሥት›› ነውና፡፡ ሁለቱም ‹‹መቶ በመቶ ማሸነፍ›› ስለሚፈልጉ ለመቀራረብ እና በተወሰነ መልኩ የጋራ ጠባይ ሊኖ ራቸው እንኳን አልቻለም፡፡ ድረ ገጾቻችንን እንኳን ስናይ ወይ ስለ ‹‹ቅዱስ መንግሥት›› አለበለዚያም ስለ ‹‹ርኩስ መንግሥት›› የሚተነትኑ እንጂ ለማጣጣም እና ሚዛናዊ ለመኾን የሚሞክሩ አይደለም፡፡ እንዲህ ያሉትን ገጸ ድሮች ለማግኘት ከባድ ነው፡፡

በቀን የሚሸነፍ ጨረቃ፣ በሌሊት የሚሸነፍ ፀሐይ በሌለበት ቦታ ጽንፈኝነት ሥር ይሰድዳል፡፡ ሰውዬው በአርባዎቹ መጨረሻ እና በኀምሳዎቹ መጀመሪያ ላይ ነበር አሉ፡፡ ታዲያ ጣለበትና ሁለት ሚስቶችን አገባ፡፡ አንዷ ወጣት ሌላዋ ባልቴት፡፡ ወጣትዋ ‹‹ባልሽ ሽማግሌ ነው›› መባል ስለማትፈልግ ወጣት ለማድረግ ቆርጣ ተነሣች፤ ባልቴ ቷም ‹‹ወጣት አግብታ ትመናቀራለች›› ላለመባል ባልዋን ሽማግሌ ለማድረግ ታጥቃ ተነሣች፡፡ ሁለቱም ሚስቶች ለዚህ ውሳኔያቸው የወሰዱት ርምጃ ወጣትዋ ሽበቱን መንቀል፣ ባልቴቷም ጥቁሩን ፀጉር መንቀል ነበር፡፡ ሁለቱም መቶ በመቶ ለማሸነፍ ስለ ፈለጉ የሚያግባባ መካከለኛ ነገር ለማግኘት እንኳን አልቻሉም፡፡ እናም አንዷም ነጩን ሌላውም ጥቁሩን ፀጉር ነቅለው ነቅለው በመጨረሻም መላጣ አደረጉት ይባላል፡፡ ቢያንስ ከጥቁሩም ተቀንሶ ከነጩም ተቀንሶ ሰውዬው ጎልማሳ የሚኾንበትን መንገድ እንኳን ቢያስቡ ምን ነበረበት ?!

ሁልጊዜም የሚገርመው ነገር ይህ ነው፡፡ በነጭ እና በጥቁር መካከል ግራጫ የሚባል ነገር የለንም፡፡ አማራጫችን ሁሉ ወይ ነጭ አለበለዚያም ጥቁር ብቻ ነው - ቀን ወይም ሌሊት፤ ቅዱስ ወይም ርኩስ፤ መልአክ ወይም ሰይጣን ብቻ ነው፡፡ ካለፈው ታሪ ካችን ለመማር እና በጎዎቹን ይዘን ስሕተቶችን አርመን ለመጓዝ ያልታደልነውም አዲስ የሚመጣ ሁሉ ያለፈውን መቶ በመቶ ካልቀየረ ወይም ካልተቃረነ በቀር የኖረ ስለማይ መስለው ነው፡፡ አዲስ አለቃ እንኳን በየመ/ቤቱ ሲመደብ ቢቻል ሌላ ቢሮ ቢቀመጥ፣ ካልተቻለም ወንበር እና ጠረጴዛውን ቀይሮ ቢቀመጥ የሚመርጠው መቶ በመቶ ለመለ የት እና ለማሸነፍ ነው፡፡ ደርግ የንጉሡን ውርስ ድራሹን አጠፋው፤ አሁን የመጣውም የደርግን ውርስ አጠፋ፤ ተቃዋሚ ኾነው ነገ መንግሥት መኾን የሚመኙትም የኢሕአዴግን ውርስ ካላጠፉ የነገሡ አይመስላቸውም፡፡ ተቻችሎ፣ ተወራርሶ፣ ተመቻምቾ (compromise) ለመጓዝ ፈቃደኝነቱ አይታይም፡፡

በሃይማኖቶች መካከልም ይኽው መቶ በመቶ የማሸነፍ አባዜ እየተንጸባረቀ ነው፡፡ የራሱን አጉልቶ የሌሎችን ተችቶ የሐሳብ ክርክር እና የአስተምህሮ ልዕልናን ከማሳየት ይልቅ የእርሱን መኖር ከሌሎች መጥፋት ጋር ያያይዘዋል፡፡ የእርሱ መኖር የሚረጋገ ጠው ሌሎች ሲጠፉ ብቻ ነው ብሎ ያምናል፡፡ ፈጣሪ ለምን ሰይጣንን ጨርሶ ማጥፋት እንዳልፈለገ እንኳን ለመመርመር ፈቃደኛ አይደለም፡፡ እንደ እኔ እምነት ግን ተቃራኒን መቶ በመቶ ማጥፋትን ከእርሱ እንዳንማር ፈልጎ ይመስለኛል፡፡

አንዱ ሌላውን ይተች፤ እርሱም ሲተች፣ ሲነቀፍ ይቀበል፤ ሌላውን ጨርሶ ለማጥፋት መነሣትን ግን ምን አመጣው? ነጥብ ለማስቆጠር ብቻ ሳይኾን ነጥብን ለመቀ በልም ፈቃደኛ መኾን ያስፈልጋል፡፡

ርኅራኄ የሚባለው ነገር መቶ በመቶ ካላሸነፍኩ የሚል አባዜ ባለበት ቦታ አይገኝም፡፡ ሰውን ከገደሉ በኋላ መቆራረጥ፣ ከመ/ቤት ካባረሩ በኋላ ሌላ ቦታ እንዳይቀጠር ነገር ዓለሙን (ማኅደሩን) ማበላሸት፣ ከፊቱ ለፊቱ ተመሳሳይ ሱቅ መክፈቱ ሳያንሰው ንግድ ፈቃዱን ለማስነጠቅ መኳተን፣ አንድን ሰው እስከ መጨረሻው መበቀል፣ ርኅራኄ ሲጠፋ የሚከሠቱ ናቸው፡፡

ድሮ ልጅ ኾኜ ያነበብኹት አንድ የተረት መጽሐፍ እንዲህ የሚል ታሪክ ነበረው፤ የበግ ሥጋ መንገድ ላይ ወድቆ ያገኙ ሁለት ቀበሮዎች ለእኔ ይገባል ለእኔ ይገባል እየተ ባባሉ መጣላት ጀመሩ፡፡ ሥጋውን ለመካፈልም ኾነ ሸጠው ገንዘቡን ለመካፈል ፈቃደኞች አልኾኑም፡፡ መንገድ አላፊዎች ሁሉ የተለያዩ አማራጭ የዕርቅ ሐሳቦች ቢያመጡላቸውም ሁለቱም ‹‹ሥጋው ሳይነካካ መቶ በመቶ ካላገኘን ሞተን እንገኛለን፡፡›› አሉ፡፡ ተናክሰው ተናክሰው ተዳከሙ እና ሁለቱም ወደቁ፡፡ በዚህ መካከል አንዲት ቡችላ በዚያ መንገድ ስታልፍ ሁለት ቀበሮዎች ቆስለው ወድቀው አንድ ሙዳ ሥጋ መካከላቸው ተጋድሞ ታያለች፡፡ ወዲያው ግራ ቀኙን ተመልክታ ሥጋውን አፈፍ አደረገችና በረረች፡፡

ይህን ትዕይንት የተመለከተ መንገደኛ፡-

ቀበሮ ሲጣላ፣
ተስማምቶ እንዳይበላ፣
መንትፋቸው ሄደች፣
ዘዴኛ ቡችላ፤

              ብሎ ገጠመ አሉ፡፡

ሥጋውን መቶ በመቶ እኔ ብቻ ነኝ የምበላው ማለት፣ ሥጋውን ለሁለቱም የማይበጅ ሦስተኛ አካል እንዲበላው አሳልፎ መስጠት ማለት ነው፡፡


37 comments:

 1. +++
  ጥሩ ነበር ግን የማይነኩ ተነኩ::
  እባክህ.............

  ከዲያስፖራ

  ReplyDelete
 2. ውድ ዳኒ ጥሩ መልዕክት በተገቢው ጊዜ አቅርበሐል ካሁን በፊት ይህን ጽሑፍ እንድታወጣው አስተያየት የጻፍኩ ቢሆንም እጅግ በተገቢው ወቅት ምላሽ ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ ጥሩ ትምህርት አዘል ነው ልቦና ከሰጠን እግዚአብሔር ይጠብቅህ

  ReplyDelete
 3. Yes this the great problem of our country. every time some individuals want onlt to be the winner for ever, they don't want any one to share from their side.For our surprise this problem is manifested even in small kids. HE or SHE didn't want to share his/her materials to play with others...what do we see from this? they saw from their elders and families. these kids are the leaders of the country for the future so how can they share power with others if they are not willing to share their playing ground for others today?

  ReplyDelete
 4. Dn. Daniel Egziabhere ahunim tigatun yichemirilih!zare hagerachin endatadig mikiniyat kehonut wust andu 100 be 100 mashenef yemil abaze texenawuton new, semi kale yih tsihuf tilik meliekit alewu.... , ebakachihu yetewededachihu Ethiopian kegna yalihone bahil newuna enaswegidew. Amlakachinim endih ayinetun neger alastemarenim.

  ReplyDelete
 5. That is interesting! This is important in changing the our mind set! you are playing your role in the social development of our country. I am proud of u!
  May God help u!

  ReplyDelete
 6. Wow wonderful i think we all have this issue.We have to leave with ፣ ተመቻምቾ (compromise).You now what Dn Daniel never heard of this amharic word.If it is not a miss spell i like the word "Temechtagnalech".I am learning a lot of new words.

  ReplyDelete
 7. ልቦና ይስጠን ከማለት በቀር ሌላ ምን ይባላል።

  ReplyDelete
 8. Danel,it is not bad, but please becarful befor you write this kind of article.

  DD.
  Seattle WA
  USA

  ReplyDelete
 9. It is so nice and timely!!!!!!!!! This is actually a sign of advancement and would come through exercise!! Let's try to exercise it..........

  ReplyDelete
 10. It is too much nice for me. God give his strength to do what we read

  ReplyDelete
 11. ምንም ነገር በጊዜው መወያያ ሲሆን ደስ ይላል፣

  ዲ.ዳንኤል በዚህ ወሳኝ ሰዓት እንዲህ አይነት ነገር በማንሳትህ በጣም እናመሰግናለን ግን ጥያቄ አለኝና ጥያቄዩን መልስልኝ ለመሆኑ ኢትዩጵያ መቼ ነው እንዲህ አይነት ታሪክ የጀመረቸው በአክሱም፣ በዛጉየ፣ በሰለሞዊና ስረወ መንግስት ወይን በቅርብ፡፡ ይህን ጥያቄ ለመጠየቅ ያስገደደኝ አንዳንድ የታሪክ መፀሀፎችን ሳነብ ከአንድ ቤተሰብ አንዱ ሲነግስ አንዱ ወደ ግሸን አንባ ይጋዝ ነበር፡፡ እና እባክህ መልስልስ መቼ ነው እኔ ብቻ ልብለጥ የሚለው ታሪካችን የጀመረው? ይህን ጥያቄ ያነሳሁት ምናልባት አነሳሱን ካወቅን አጣጣሉን ልንረዳ እንችላለን በሚል እሳቤ ነው፡፡

  ማኪ
  አዲስ አበባ

  ReplyDelete
 12. That is absolutely right! we should learn the win-win philosophy.......it all helps both in this fleshly world and in the coming kingdom Of God! May God bless you!

  ReplyDelete
 13. Thanks D/N Dani
  I want to reply to the one who commented first (Diaspora), please don't ascribe this disease to some group only. The lesson is for all of us.
  May God brighten up our heart !

  ReplyDelete
 14. Shall be entitled 200%!

  ReplyDelete
 15. this absolutely right!

  ReplyDelete
 16. We need and love you please be carful

  ReplyDelete
 17. Kale hiwot yasemah Dn. Daniel,
  It is big problem we have in our spritual and secular life. you gave us a great lesson if we are ready to learn!
  May God keeps you safe

  ReplyDelete
 18. ቃለ ህይወትን ያሰማልን፤ተስፋ መንግስተ ሰማያትን ያውርስልን

  ReplyDelete
 19. First of all I want to thank you that you've presentation was so great. We have a lot of issues which are yet to be dealt with. one of them is this one. The question is when are we going to realize that we are in this situation and get out of it? Any one who read this blog should be start to think where is he/she and get ready to change him/herself. God Bless you Dn Daniel

  ReplyDelete
 20. hmmm....
  I don't think the matter is as simple as lack of "win-win" mentality and I feel that some of the points are generalizations.
  I think the problem raised is one of the many problems we have. The history of poor nations is somehow akin to ours. Let me show you a scenario:
  You were poor----> You blame your poverty on someone else------>You do whatever necessary----->You get power------>Power feels good---->You begin to feel you DESERVE your power---->Someone comes challenging your power(Power= livelihood in our case)---->You remember your situation before power--->feeling of insecurity---->You do whatever necessary to eliminate that someone--->You continue till somebody you can't do away comes
  That's one reason I see as behind bloodsheds.

  ReplyDelete
 21. ዉድ ወንድማችን ዲ/ዳንኤል በተከታታይ እያወጣሃቸው ያሉት ጽሑፎች አስተማሪና ወቅታዊ ናቸው፡፡ እይታዎችህ ጥሩ ናቸው ሁሉንም ያሳትፋል፡፡ በተጨማሪ ግን መወያያ የሚሆኑ ርዕሶችንም እያነሳህ ሰው መፃፍ እንዲጀምር ብታደርግ የበለጠ ጥሩ ነው፡፡ 100% ሁሌ ማሸነፍ የሚፈልጉ መጨረሻ ላይ100% የመሸነፍ ዕድል ነው ያላቸው፡፡ ስለዚህ እባክህ አበክረህ ንገርልን፡፡ በተረፈ እግዚአብዜር ሥራህን ይባርክልህ፡፡
  ወለተ ሥላሴ

  ReplyDelete
 22. ይህን የመሰለ ትምህርት አዘል ጽሑፍ ስላካፈለከን እናመሰግናለን ፡፡

  ReplyDelete
 23. ዳንኤል እንዲህ ስትል አንድ ነገር አስታወስኸኝ

  አንተ እንዳልኸው የእኛ ማኅበረ ሰብ ከራሴ ጀምሮ ከምንጠላው ሰው ጋር ተደራድረን ከመስማማት ይልቅ
  ጠላችንን መበቀልና ከዛም : እንዴት እንደተበቀልነው እና ክፉ ሰው መሆናችንን, ተንኮላችንን,,እየዘረዘርን በኩራት ማውራት ከምንም በላይ ደስ ይለናል ::

  አንድ መላሽ እንዳለው
  ከዚህ ጠባይ የምንላቀቀው መቼ ይሆን ?

  እስኪ ሁላችንም ወደ ውስጣችን እንመልከት

  ReplyDelete
 24. Wendme Daniel

  It is great services at the right time. One question, when will u publish all this articles with some carton picture? I hope that will be great to address our socity. As you know from total population the internte user are less than 0.4%.

  Wendmih(uk)

  ReplyDelete
 25. the book will will distribute in the first week of june.

  ReplyDelete
 26. it is good Dani! Berta.

  ReplyDelete
 27. What a beauty Dn Daniel, may God bless you abundantly!!! I have been missing your 'tales' and really enjoyed reading today's issue. I must also say the timing was perfect. We suffer from deep rooted ideaological fanaticism and I think everything surrounding us was shaping us to think that way. We grew up in a society that branded criticism as 'yebalege' negegere! May God provide us the wisdom to see the beautiful color combination that lie between white and black!!!

  ReplyDelete
 28. ዲ/ን ዳንኤል
  ኢትዮጵያ ምጥ ይዟት
  መላ አጥታ ሲጨንቃት
  በዚህ ወሳኝ ሰዓት
  አለሁሽ የሚላት
  የሦስት ሺህ ዘመን ታሪክ አላት የተባለች አገራችን ዝናዋ ማፈሪያ ሆኖባት ስናይ የትውልድ ተወቃሽነታችን ዕለት ዕለት የሚያስጨንቅ ጉዳይ ነው፡፡ በተለይ ውስጧ ላለነው፡፡ ውጪ ያሉትማ
  እኛም አገር አለን የሚታይ በሩቁ እያሉ ትዝታቸውን ያንጎራጉራሉ፡፡ የሰውን አገር ስልጣኔ ዕድገት ልማት ወዘተ ሲያዩ፡፡ ከታሪክ ተወቃሽነት የምንድነው ምን ስናደርግ ይሆን እግዚአብሔር ማስተዋልና ጥበቡን ያድለን አሜን፡፡ አንተንም ያበርታህ
  ማኩሻ

  ReplyDelete
 29. "ቢያንስ ከጥቁሩም ተቀንሶ ከነጩም ተቀንሶ ሰውዬው ጎልማሳ የሚኾንበትን መንገድ እንኳን ቢያስቡ ምን ነበረበት ?!" This is what we miss....

  ReplyDelete
 30. it is a nice idea dani,but why don`t you write a book by compiling the ideas that you wrote in addis neger? I need your response

  ReplyDelete
 31. dani,ewedikalew beybelt gin wed poltica matekor tiru new tilalek?

  ReplyDelete
 32. i think its a free invte to give comment but what about the approval?

  ReplyDelete
 33. This is a good article. I think the povery and wide illiteracy in our nation have a great role in shaping our characters this way. look, even in our ages things are changing from bad to worse. and this, I think highly attributed to the worsening economic condition in the country.If you are not at peace with yourself, you will never be at peace with your neighbours or friends.
  thank you danny God bless you.

  ReplyDelete
 34. The issue is quite interesting,i dont know why peoples of ethiopia particularly ranked at the top want to win 100%only.if one won totaly no way to see his drawbacks even hard to accept failurity if happend once up on a time ratherthan accepting their defeat and reveiwing their performance,they declare war on others,want to wash their hand by the blood of others.pls lets stop thinking like that tomorrow is a bright day if we settle todays problem. GOD BLESS OUR COUNTRY AND HER PEOPLE!

  ReplyDelete
 35. i have no words to express.u have seen our problems & shown to us. 10q dn.daniel.

  ReplyDelete
 36. Dani,it is a nice message,i thank you ,kale hiwot yasemalin

  ReplyDelete