Thursday, May 20, 2010

ልዩ መርሐ ግብር ከግንቦት 10 እስከ 12


አለቃ ተክሌ

አለቃ ተክሌ የታዋቂው ሊቅ የአለቃ ገብረ ሐና ልጅ ናቸው፡፡ ዝማሜው ከእርሳቸው የቀደመ ታሪክ ቢኖረውም ያሳወቁት እና ወንበር ዘርግተው ያስተማሩት እርሳቸው በመሆኑ «የተክሌ ዝማ» እየተባለ በስማቸው ይጠራል፡፡

የአለቃ ተክሌ እና የዝማሜው መገጣጠም ግን የሚከተለውን ይመስላል፡፡

በፍትሐ ነገሥት ዐዋቂነታቸው የዐፄ ቴዎድሮስ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩት አለቃ ገብረ ሐና በቀልደኛነታቸው ምክንያት ከዐፄ ቴዎድሮስ ጋር ሊስማሙ አልቻሉም ነበር፡፡

በኋላ ደግሞ ካህናት በዐፄ ቴዎድሮስ ላይ ባመፁ ጊዜ በአድማው ካሉበት ካህናት መካከል አንዱ ገብረ ሐና መሆናቸው ስለታወቀ ዐፄ ቴዎድሮስ በአለቃ ገብረ ሐና ላይ አምርረው ሊቀጧቸው ዛቱ፡፡ አለቃም ሸሽተው ጣና ሐይቅ ሬማ መድኃኔዓለም ገዳም ገቡ፡፡ በዚያም ባሕታዊ ጸዐዳ ገብረ ሥላሴ የተባሉ የአቋቋም ሊቅ አገኙ፡፡ ሁለቱም ተወያይተው በጎንደር አቋቋም ስልት የመቋሚያውን የአካል እንቅስቃሴ ጨምረው ዝማሜውን አዘጋጁት፡፡ አንዳንድ ሊቃውንት ለዝማሜው መነሻ ያደረጉት በጣና ዳር የበቀለውን ደንገል እየተባለ የሚጠራ ሸንበቆ መሰል ተክል እንቅስቃሴ ነው ይላሉ፡፡ ባሕታዊ ጸዐዳ «ከእንግዲህ እኔ ወደ ዓለም አልመለስም፤ አንተ ይህንን ስልት አስተምር» ብለው አለቃ ገብረ ሐናን አደራ አሏቸው፡፡

ይህንን በአፈ ታሪክ ሲነገር የነበረ ታሪክ ወደ ካቶሊክነት የተቀየረውና ከአንቶኒዮ ዲ አባዲ ጋር በዐፄ ቴዎድሮስ ዘመን ስለ ሆነው ሁሉ ደብዳቤ ይለዋወጥ የነበረው፣ የዋድላው ሰው ደብተራ አሰጋኸኝ ጥር ስድስት ቀን 1858 ዓ.ም ለአንቶኒዮ ዲ አባዲ በጻፈው ደብዳቤ እንዲህ በማለት ፍንጭ ይሰጥበታል፡፡ «አለቃ ገብረ ሐናን ንጉሥ መቱዋቸው በሽመል፡፡ ወደ ትግሬ ወደ ላስታ ተሰደዱ፡፡ እጅግ ተዋረዱ፡፡ እኔም በዋድላ አገኘኋቸው ወደ ቆራጣ ሄዱ፡፡» (Sven Rubenson ed.Acta Aethiopica: Tewodros and His Contemporaries, p 259)

አለቃ ይህንን ዝማሜ በጎንደር በኣታ ማስተማር ጀምረው ነበር ይባላል፡፡ ነገር ግን ጎንደሬ ሚባለውን መቋሚያ ስልት ከጥንት ጀምረው የሚያውቁት የጎንደር ሊቃውንት ለቀበሏቸው አልቻለም፡፡ በተለይ ይህ የአለቃ ገብረ ሐና አቋቋም ለተመስጦ እንጂ ለፕሮቶኮል ስለማይመች ከጎንደር ሊቃውንት ጋር ነጋ ጠባ ክርክር ሆነ፡፡ አለቃ ገብረ ሐናም ይህንን አቋቋም እንዳያስተምሩ ተከለከሉ፡፡ አለቃ ቢጨንቃቸው ቤታቸውን ዘግተው ለልጃቸው ለተክሌ አስተማሩት፡፡ ተክሌ በአቋቋሙ መካኑን ሲያውቁ ከእስልምና ወደ ክርስትና ተመልሰው የቤተ ክርስቲያንን ሊቃውንት በመብራት እየፈለጉ ወደሚሾሙት ወደ ወሎው ራስ ሚካኤል ሀገር ላኩት፡፡

አለቃ ገብረ ሐና ደርቡሽ ጎንደርን ሲወርር ልጃቸውን ወደ ወሎ ልከው እርሳቸው ዘጌ ገዳም ገቡ፡፡ በኋላም ዐፄ ምኒልክ ደርቡሽን ለመውጋት ወደ ፎገራ መምጣታቸወን ሲሰሙ ከተደበቁበት ወጥተው ንጉሡን ተከትለው ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ፡፡ ምኒልክም እንደገና የራጉኤል አለቃ አደረገው ሾሟቸው፡፡ ልጃቸው ተክሌ ወሎ ንጉሥ ሚካኤል ዘንድ እያሉ የተንታ ሚካኤል በዓል ሲከበር ከአባታቸው የተማሩትን ዝማሜ በተመስጦ አቀረቡት፡፡ ንጉሥ ሚካኤልም በዚህ ተደንቀው በዚያው በተንታ እንዲያገለግሉ አደረጉ፡፡ የተክሌ ዝማሜ በይፋ የተጀመረው ያኔ ነው ይባላል፡፡ በኋላ ራስ ጉግሣ /1792 -1818/ ዝናውን ሰምተው ንጉሥ ሚካኤልን በማስፈቀድ ወደ ደብረ ታቦር አምጥተው ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንን ሾሟቸው፡፡

አለቃ ተክሌም በደብረ ታቦር ኢየሱስ ተቀምጠው ትምህርቱን አስፋፉት፡፡ በምስክርም አለቃ ብሬን፣ አለቃ መኮንንን፣ አለቃ ዓለሙንና አለቃ ይትባረክን መርቀዋል፡፡ አለቃ ተክሌ ያረፉት ራስ ጉግሣ ወሌ በሌሉበት በመሆኑ ራስ ጉግሣ መርዶውን ሲሰሙ «ምን ተክሌ ሞተ ትሉኛላችሁ፤ የደብረ ታቦር ኢየሱስ ፈረሰ በሉኝ እንጂ፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ቢፈርስ አሁን ካለው በበለጠ አድርጌ ልሠራው እችላለሁ ተክሌን ግን ከወዴት አገኘዋለሁ?» በማለት ተናግረዋል ይባላል፡፡ አልቃሽም፡

«ተክሌ ገብረ ሐና ተቀበረ ጣቱ
መንክረ ክስተቱን የዘመመበቱ»
                               ብላ ገጥማለች፡፡

ታላቁ ራስ ጉግሣ ደብረ ታቦር ኢየሱስን በጣም ስለሚወዱ «ላቂያዬ» ብለው ይጠሩት ነበር ይባላል፡፡ የደብሩንም አገልጋዮች ብዛት ወደ 318 ከፍ እንዲል አድርገውት ነበር፡፡ በራስ ጉግሣ ወሌ ወደ 150 ዝቅ እንዲል ተደርጓል፡፡ የታላቁ ራስ ጉግሣ፣ የራስ ዓሊ፣የራስ ይማም፣የራስ ዶሪ፣ የራስ ማርዬ፣ የራስ እንግዳ፣ የንጉሥ ወልደ ጊዮርጊስ ባለቤት የወ/ሮ የሺ እመቤት ቀብር የተፈጸመው እዚህ ነው፡፡

በ15ኛው አለቃ ዘመን ዐፄ ኃይለ ሥላሴ የደብሩ አለቃ «መልአከ ታቦር» ተብሎ እንዲጠራ ፈቀዱ፡፡ የተክሌ አቋቋም ትምህርት ቤት በጥር አምስት ቀን 1993 ዓ.ም የአካባቢው ምእመናን፣ የሀገሩ ተወላጆችና በጎ አድራጊዎች ባደረጉት አስተዋጽዖ በአዲስ መልክ ተሠርቶ ተመርቋል፡፡

የክልሉ መንግሥት ለአለቃ ተክሌ አንዳች መታሰቢያ ማድረግ አለበት፡፡ በተለይም ብዙ በደከሙበት በደብረ ታቦር መንገድም ይሁን ትምህርት ቤት፣ አደባባይም ይሁን ድልድይ በስማቸው መሰየም ይገባዋል፡፡


18 comments:

 1. It is so nice. I am sure most of us don't know this great person. But concerned bodies should give emphasis for such peoples and give some memorial work in their name... D/n Daniel i hope you will tell us something about TENTA MICHEAL in other time. I know it is a great place with lots of spritual and cultural value around that area

  ReplyDelete
 2. Dear Daniel

  Thank you so much for sharing us that one enciant histrory of our church,

  But I have one comment for you

  "" «ተክሌ ገብረ ሐና ተቀበረ ጣቱ
  መንክረ ከሰተን የዘመመበቱ»

  ReplyDelete
 3. It is always nice to read such amaizing histry about our orthodox Fathers .please Can you write more about Aleka G/hana ??? because most of us only know about his joke but a few only what he has done for our church.i hope you will post it soon about him too.

  ReplyDelete
 4. "ምን ተክሌ ሞተ ትሉኛላችሁ፤ የደብረ ታቦር ኢየሱስ ፈረሰ በሉኝ እንጂ፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ቢፈርስ አሁን ካለው በበለጠ አድርጌ ልሠራው እችላለሁ ተክሌን ግን ከወዴት አገኘዋለሁ?» Dani, I think this is the one that we should think again and again. Currently; we are missing our icons "Yeabinet Memhiran". In my opinion, we should give attention for them in addition to build big Churches in Addis. Can you say something about this my brother.

  ReplyDelete
 5. አሁን በእውነት ይሄ ትውልድ ምን ሰራ?
  እንደዚህ በጣም ደስ የሚያሰኝ ሕይወትና ተጋድሎ ያሳለፉትን ቅዱሳን አባቶች ታሪክ ሲዘከር በጣም ደስ ከማለቱ አልፎ እምነትንም ያጠነክራል፡፡ ብቻ መማር ከቻሉ የዘመናችን መምህራን ነን ባዮችና ሳይገባቸው ባገኙት አጋጣሚ የአባትነት ማዕረግ የተሰጣቸው ነጋድያን የአባቶችን ሕይወት የሚያዩበት አጋጣሚ ቢኖር መልካም ይመስለኛል፡፡ ለምን መስመሩ ውስጥ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ፈልገው ይሁን ሳይፈልጉ ገብተውበታልና ምዕመናን በተኩላ እንዳይነጠቁ የአበቶችን ገድል ማወቅ ጠቃሚ ነው፡፡ ምንም ሳይኖራቸው ቡራ ከረዩ ማለት ዋጋ የለውም፡፡ የዘመኑም በሽታ ባዶ ሆነው ሳለ ሰማይና ምድር የሚጠባቸው ስም ብቻ ታርጋ ለጥፈው የሚዞሩ ብዙ ናቸው፡፡በብዛትም በጥራት የአባቶችን ገድል የሚዘክሩ ጽሁፎች እንድታስነብበን እግዚአብሔር ይረዳህ፡፡

  ReplyDelete
 6. It is very nice Dany. But it is too short.

  ReplyDelete
 7. Thank you Daniel for your wonderful story telling. I am always love your writings, they have a wonderful way of expresstions. Which makes a reader flow slowly...
  May God bless your work.

  ReplyDelete
 8. Actualy I know you physically and you thought me for a month 10 years ago and that is the only handful resource for me to stay in the church.Even now I am using your note what you gave us during that training so that is sososososo.........sweet! And now I was realy amezed when I read about Alequa Gebrehana so if youcould please give us more thing about him and our church relationship

  ReplyDelete
 9. Leoulseged W. from Addis Ababa.
  Me appriciation should go to your work. May God bless your work, Dani!. Thank you, for sharing us this great hitorical father. Keep on writing please, I am always ready to read your articls becuase they help me to know those forgoten fathers of our Orthodox Church.Thank you again!

  ReplyDelete
 10. Kale Hiwot Yasemalen Dn. Daniel
  you tought me today a new thing. i don't know that Aleka Geberehana have a Blessed Son.i only know the name Tekele Akuwakuwam.
  God Bless YOu ...
  and i hope you will tought us one day about Abune Aregawi. i know only very little by the way is He coming as a patriach of EOTC in the Good days of Ethiopia b/c he is not died?

  ReplyDelete
 11. i like the article but i have a question. who was first chronologically, ras Gugsa or Tewodrose? I think so there is chronological error on this article. i need your response about this.

  ReplyDelete
 12. I do hope you will make us to read more about the different styles of ZEMA and AQWAQWAM that our church had like TEKLIE, GONDERIE, QOUMIE, TEGULTIE, ACHABRIE and the like.

  I thank you.

  ReplyDelete
 13. በኋላ ራስ ጉግሣ /1792 -1818/ ዝናውን ሰምተው ንጉሥ ሚካኤልን በማስፈቀድ ወደ ደብረ ታቦር አምጥተው ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንን ሾሟቸው፡፡ አመታቱ ልክ ናቸው? አጼ ምኒሊክ እንደገና 1818...

  ReplyDelete
 14. አለቃ ተክሌን ወደ ደብረ ታቦር ያስመጡት በዘመነ መሳፍንት የነበሩት ራስ ጉግሳ አይደሉም፡፡ በኋላ ለበጌምድር ገዥ የሆኑትና ከዐፄ ኃይለ ሥላሴ ጦር ጋር ተዋግተው በ1922 ዓም ተዋግተው የሞቱት ራስ ጉግሣ ወሌ ናቸው፡፡ ለተፈጠረው መደናገር ይቅርታ፡፡

  ReplyDelete
 15. Yehiwotin kal yasemalin !

  ReplyDelete
 16. thank you dani.we expect more and more.God be with you

  ReplyDelete
 17. i have 1 question:
  "debtera" malet min malet new?
  is it sidib or ...
  what is its meaning

  ReplyDelete
 18. ዳንኤል በቅድሚያ ስለ አለቃ ገብረ ሃና ላቀረብከው ላመሰግን እወዳለሁ፡፡ ከዘህ በፊት አንድ አነስተኛ መጽሀፍ ነበር፡፡ በቅርቡ መጽሀፍ ሌላ ታትሞል፡፡ከዚህ በተጨማሪ አንድ እንግሊዛዊት የተወለዱበት አገር ጎንደር ድረስ ሄዳ ጥናት እነዳደረገች አውቃለሁ፤እና ስለ አለቃ ገብረ ሃና ያቀረብከው ነገር ቢሠፋ መልካም ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ብዙ አይታወቅ ብዬ ከማስባቸው ታሪኮች ውስጥ ስለ ዮዲት ጉዲት አንድ ጽሑፍ ብታቀርብል መልካም ነው፡፡

  ReplyDelete