ሰውም ሳይሰፍርባት አሜሪካ ታውቃ፣
ገና ጥንት ያኔ . . . . . . . . .
እንዲህ ሳትሠለጥን አውሮፓም ተራቅቃ፣
ገና ጥንት ያኔ . . . . . . . .
ዓለም፣ ከእንቅልፏ ሳትነቃ፣
እነ ሞዛርት እና እነ ቤት ሆቨን፣
የዜማን ምልክት ገና ሳይነግሩን፣
ያሬድ አንተ ነበርክ
የዜማን ቅማሬ የሠራህልን፣
. . . . . . . . . . . . . . . . . . . .
መንኮራኩር ሠርተው
ጨረቃ ላይ ወጥተው፣
አፈር ስላመጡ ዓለም ተደነቀ፣
ወሬው ተሟሟቀ፣
ከምዕራብ ተነሥቶ ከምሥራቅ ዘለቀ፣
ከሺ ዓመት በፊት ግን
ያሬድ የተባለ አንደ ሊቅ ነበረ፣
ጨረቃንም አልፎ ጠፈር ተሻገረ፣
ሐኖስን ሰንጥቆ ሰማያት ውስጥ ገብቶ፣
አስደናቂ ዜማ ከመላእክት ሰምቶ፣
አኩስም ላይ አዜመው
ከጽናጽል እና ከመቋሚያ አስማምቶ፣
ግና ምን ያደርጋል . . . . . . .
ከጨረቃ አፈር የሚበልጥ ነገር፣
ጨረቃም ላይ ካለው የሚበልጥ ምሥጢር፣
ያሬድ ይዞ መጥቶ፣
የሚናገር እና የሚያደንቅ ጠፍቶ፣
ዓለም አያውቀውም አልሰማውም ከቶ፣
ያሬድ ግን ቅዱስ ነው
ያሬድ ምሁር ሊቅ፣
ያሬድ መተርጉም ነው
ምሥጢር የሚያረቅቅ፣
ያሬድ ፈላስፋ ነው
ያሬድ ባለ ቅኔ፣
ያሬድ ባለ ዜማ
የዜማው መጣኔ፣
ያሬድ ሐጋጊ ነው
ሥርዓት የሠራ፣
ያሬድ መምህር ነው
ዕውቀትን ያበራ፣
ያሬድ ቀማሚ ነው
ብሉይ ከሐዲስ፣
ያሬድ ሰባኪ ነው
ነፍስ የሚመልስ፣
ያሬድ አመልካች ነው
ኖታን የፈጠረ፣
ያሬድ መናኒ ነው
በጸሎት የኖረ፣
እነ ቸርችል፣ ፑሽኪን እነ ካኒንግሃም
አደባባይ መንገድ ሲሰየምላቸው፣
ያሬድን ስላጡት አዘነ ልባቸው፣
ነቢይ በሀገሩ አይከብርም እንዲሉ፣
እኒህ ኢትዮጵያውያን እጅግ ይሞኛሉ፣
የእጃቸውን ንቀው ሌላ ያከብራሉ፣
ብለው አዘኑብን በፈጸምነው ግፍ፣
ያሬድን ረስተን ሌላውን ስናቅፍ፣
አይበቃም ወይ ታድያ የሞኝነት ኑሮ፣
መቅረት አለበት ወይ ታሪኩ ተቀብሮ፣
ይተረክ ታሪኩ ይነገር ዝናው፣
ይጠና ይመርመር ይታወቅ ሥራው፣
መወያያ ይሁን በየሚዲያው፣
መማማርያ ይሁን ትውልድ ያድንቀው፣
ያለበለዚያ ግን
ያለፉትን ንቀን ወደፊት ብንሄድ፣
እኛንም የሚንቅ ይመጣል ትውልድ፡፡
very nice poem.pls dn.daniel,write more about kiduse Yared
ReplyDeleteአልቦ ዘይመስላ ለጥበብ ዘይመስላ
ReplyDeleteጥበብ ትሔይስ እምብዙህ መዛግብት ይቤ ያሬድ ማኅሌታይ
+++
ReplyDeleteበስመ ሥላሴ ትቀጥ ከይሴ
እንደ እኔ የበለጠዉን አባቶቻችን የበለጠዉን አድርገውለታል እና እንደ ዓለማዉያን የተቀረጸ ሃዉልት እንዲኖረዉ አያስፈልግም::
ከዝዋይ
Be'ahun zemen linketelew yemigeba abat. Zefen mesel mezimur titen yebatachenen ye Kidus Yared feleg eniketel.
ReplyDeleteEgziabher yistilign
My Brother I have no word for you,Zare enesu baynorum ende ante yaluten tektewulenalena EGZEABHER yemesgen.
ReplyDeleteDeacon Dani, THANKS.
ReplyDeleteMAY GOD BE WITH YOU. I cannot wait to read the next.
I thank you for such a program!
ReplyDeleteWhat shall be our contribution in this event?
ይበል ይበል ይበል!!!
ReplyDeletehello
ReplyDeleteWhere will be the program?
ReplyDeleteAt the St Yared church, Addis Ababa?
ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ኢትዮጵያ አገራችንን ለአለም ካሳወቁ አንዱና ዋንኛው ስለሆነ በዓሉን ብሔራዊ በዓል እስከማድረግ መስራት ይጠበቅብናል፡፡
ReplyDeleteእግዚአብሔር የቅዱሳኑነን በረከተት አያሳጣን፡፡
አርያም
ReplyDeleteሀሌ ሉያ ለአብ ሀሌሉያ ለወልድ ሀሌሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ
ቀዳሚሀ ለጽዮን ሰማየ ሳረረ ወበ ዳግመ አርአዮ ለሙሴ በከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ
ቅዱስ ያሬድ በመጀመሪያ ያዜመው አርያም ዜማን እንደሆነ ይነገራል፡፡
በዜማ ብንሰማው ምንኛ ነፍሳችን ሐሴት ባደረገች፡፡
የዚህ ቅዱስ አባት፣ የዜማ ሊቅ ፣ባለቅኔ በረከቱ ይደርብን
http://www.mahiberekidusan.org/Default.aspx?tabid=89&ctl=Details&mid=371&ItemID=120
ReplyDeleteኦርቶዶክሳዊ መዝሙር የቱ ነው?
አምላከ ቅዱስ ያሬድ ጥበቡን ትእግስቱን ጽናቱን ያድልህ!!
ReplyDeleteዲያቆን ዳኒኤል ክብረት
መስራት ያለብንን ጠቀስ እያደረግን ብንወያይና እናም ለኛም ለበረከትና ለጽድቅ ለቅዱሳኖችም ክብር ይሆናይ፡፡ከዝዋይ የተፃፈው ግን በጣም ያሳዝናል፡፡እኛ ቅዱሳንን ብናከብር በሰማይ ከሚሰጣቸው ክብር ከምኑም አይደርስ ግን እላይ እንደገለጽኩት ለበረከት ለእውቀት ለጽድቅ ነው፡፡እናም ለቅዱሳኖቹ የሚገባቸው ክብር እንስጥ፡ካልሆነ.
Thanks dani! keep it up!
Egezire Yesetelen
ReplyDeleteEsme Albo Neger Zeyesano Le egziyabeher...Ye yared Bereketu Yedresen....
ReplyDeleteለተከበርከው ዳንኤል ክብረት
ReplyDeleteስለ ቅዱስ ያሬድ ያስነበብከን ግጥም በጣም ዸስ የሚል ነው፡፡ የህይወት ታሪኩንም የሚዳስስ ጽሁፍና ስታነብ ያገኘህውን እና ለኛ ት/ት ይሆናል የምትለውንም ስለ ያሬድ በደንብ ብታስነብበን በጣም ደስ ይለኛል ስንሰማቸው የነበርናችው ታሪኮች ቁንጽል ስለነበሩ፡፡
ለማንኛውም እንደተመራማሪነትህ ብዙ ታስነብበናለህ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
የቅዱሳን አምላክ ቅዱስ እግዚአብሔር ብርታቱን ይስጥህ፡፡
We have a number of churches named with different Saints but we have only two churches named with St. YARED- the one is here in Addis and the other is a monastery there in Ras Dashen. Yet we could have more than these...Think on this Fathers and you all the Laity. politely, the government could also boost the country's good image with St. Yared's works. But unfortunetly (intentionally or unintentionally), all authorities on the turism sector from the ministry of Turism down to Reginal offices of the country are occupied by muslim brother who may not bother or know the Saint. Rather they are striving to register about three heritages of Islam (though this is not bad, they should not also forget other heritages)to UNESCO.
ReplyDeleteDk.Daniel, yes you are right !
ReplyDeleteIn my point of view first of all lets scan our mind & make it free from virus and it will have a free space to save a drop of truth !
ዲ/ን ዳንኤል፣
ReplyDeleteመቸም አንተ የሚጠበቅብህን ሁሉ እያደረክ ነው። እግዚአብሔር ዕድሜህን ያስረዝምልን።
የቅዱስ ያሬድን ነገርማ እንዲያው ድንቅ! ድንቅ! ድንቅ! ከማለት በቀር ምን ቃላት ይገልጸዋል። ጊዜው ትንሽ ቆዬ አንድ አውሮፓ ከኖሩ እስራኤላውያን የሚወለድ በዜግነት ካናዳዊ ከሆነ የስራ ባልደረባ ጋር ስለ"ሙዚቃ" አንስተን ስንወያይ ስለቅዱስ ያሬድ ነገርኩት። አዳመጠኝና ተለያየን። ሌላ ጊዜ ስንገናኝ "ቅዱስ ያሬድ እንዳልከው ዜማውን ያገኘው ከሰማይ እንደሆነ አምኘበታለሁ" አለኝ። ሊቀልድ መስሎኝ አፍጥጨ አየሁት። እሱ ፊቱን ቅጭም እንዳደረገ ሄዶ ከኢንተርኔትና ከመጻሕፍት ስለቅዱስ ያሬድ ያገኘውን ሁሉ በአድናቆት እየተረከ በዚያ ጊዜ እንዲህ ሊያደርግ የሚችል ሰው ከሰማይ ካልሆነ ሊኖር አይችልም ብሎ እኔንም አስደንቆኛል።
ሌላ ጊዜ ደግሞ አንድ የአንትሮፖሎጂ ፕሮፌሰር የሆኑ ሰው ከነባለቤታቸው እቤት ጋብዘን ስንጨዋወት በትርፍ ጊዜአቸው ሙዚቃ እንደሚሰበስቡ አጫወቱኝና እኔ ምን አይነት ሙዚቃ እንደምሰማ ጠየቁኝ። ነገርኳቸው። የያሬድ ዜማዎች የጥንት ስብስብ እንዳላቸው ነገሩኝ። መስማት እንደምፈልግ ነገርኳቸው። ተዋስኳቸውና ሳዳምጥ በርግጥም ከተቀረጸ የቆዬ እውነተኛው የቤተክርስቲያን የያሬድ ዜማ ነው። ከየት እንዴት እንዳገኙት ስጠይቃቸው በንጉሥ ኃይለሥላሤ ዘመን ሱዳን አገር ለማስተማር በሄዱበት ጊዜ እንዳገኙትና እንደገዙት አጫወቱኝ። የዛን ቀን እኔ በራሴ አፍሬአለሁ።
ታዲያ ምን ለማለት ነው ቅዱስ ያሬድን እኛ ብናቃልለውም አለም ስለሱ እያወቀ ሲሄድ መነሳቱ መወሳቱ አይቀርም ለማለት ነው። ቢዘገይም ገና እኛ ከዓለም መቀላቀላችን ስለሆነ በነሱ ቋንቋ የተሰራ ብዙ ሥራ ባለመኖሩ የሚያውቁት ለጊዜው ውስን ስለሆነ ብቻ ነው የሚሆነው። መንግስትና በይበልጥ ደግሞ ቤተክርስቲያን ግን አንተም በጽሑፍህ እንደጠቀስከው አብይ የሆኑ መታሰቢያዎች ለቅዱስ ያሬድ ቢያዘጋጁለት የሚያስመሰግናቸው ከመሆኑም በላይ ለሃገር መኩሪያና ቅዱስ ያሬድ ለተተኪው ትውልድም በሕይወት ታሪኩ፣ በጽድቅ ሥራውና በታታሪነቱ አርአያነቱ ታላቅ ነው።
I don't what to say am really happy after reading all this pages. Kidus yared is our identity why we always talk about others? bezehu ketelubet 10q
ReplyDeleteAmlake Kidusan Yabertah Enesun Yatsena Egnanem Yatsenan
ReplyDeleteኦ ዳኒ ዘግይቼ ባነበውም ደስ ይላል አምላከ ቅዱስ ያሬድ ይባርክህ ዛሬ ይህው ቅዱስ ያሬድ 1500 የልደት በአሉን ለማክበር እየተዘጋጀን ነው "ያሬድ ግን ቅዱስ ነው"
ReplyDelete