Monday, May 31, 2010

አለቃ ገብረ ሐና ተረት ናቸው እውነት

የአባታቸውን ስም አንዳንዶቹ ደስታ ተገኝ ነው ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ ገብረ ማርያም ነው ይላሉ፡፡ ምናልባት ግን አንዱ የዓለም ሌላው የክርስትና ስማቸው ሊሆን ይችላል፡፡ የእናታቸው ስም ደግሞ መልካሜ ለማ መሆኑን የእንጦጦ ራጉኤል 125ኛ ዓመት መታሰቢያ መጽሔት ይገልጣል፡፡ ታኅሣሥ 10 ቀን 1978 ዓም የታተመው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ግን የእናታቸውን ስም ሣህሊቱ ተክሌ ይለዋል፡፡ የተወለዱት በደቡብ ጎንደር ዞን፣ ፎገራ ወረዳ፣ ናበጋ ጊዮርጊስ በተባለው ቦታ በ1814 ዓ.ም በኀዳር ወር ውስጥ ነው፡፡

Saturday, May 29, 2010

ፕሮፌሰር ሳቤክ

አንድ መምህር ስለ source credibility ለተማሪዎቻቸው የሚከተለውን ገጠመኝ ተናገሩ፡፡ አንድ ጊዜ ከጓደኞቻችን ጋር ተሰብስበን በአንድ ጉዳይ ላይ ስንነጋገር ነበር፡፡ እኔም አንድን ሃሳብ አነሣሁና ሙግት ጀመርን፡፡ ያንን ሃሳቤን ለማስረዳት ያቀረብኳ ቸውን ማስረጃዎች እና መከራከርያዎች ወዳጆቼ ሊቀበሉኝ አልቻሉም፡፡ በኋላም አንድ ሃሳብ መጣልኝ፡፡ የኔውን ሃሳብ እንደገና አሣመርኩና «ባይገርማችሁ ፕሮፌሰር ሳቤክ የተባሉ የታወቀ የእንዲህ ያለ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ምሁር እንዲህ እና እንዲያ ብለዋል» እያልኩ ማስረዳት ጀመርኩ፡፡ ያን ጊዜ ሁሉም በአድናቆት ያዳምጡኝ፤ ራሳቸውንም ይነቀንቁ ጀመር፡፡ እኔም በፕሮፌሰር ሳቤክ ስም ሃሳቤን ሁሉ አስረድቼ ተቀባይነትም አግኝቼ ቤቴ ገባሁ፡፡

የሚገርማችሁ ግን ፕሮፌሰር ሳቤክ ማለት ፕሮፌሰር ሳ/SA/ ቤክ /BEK/ ማለት «ሳሙኤል በቀለ» ማለቴ ነበር፡፡ ነገር ግን የውጭ ሃገር ምሁር ስም አስመስዬ ስለተናገርኩት ተቀባይነት አገኘሁ፡፡ ያንኑ ሃሳብ ግን እኔ ራሴ አንሥቼ ስከራከርበት ማንም ሊቀበለው ፈቃደኛ አልነበረም፡፡

Wednesday, May 26, 2010

ሀገር እንወዳለን


ሰውዬው የውጭ ሀገር ዜጋ ቢሆኑም ዐሥር ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ አስተምረዋል፡፡ ሚስተር ዣክ ይባላሉ፡፡ ሻሂ እየጠጡ ኢትዮጵያዊውን ጓደኛቸውን እየጠበቁ ነው፡፡ ሁለት ጊዜ ፉት እንዳሉት ጓደኛቸው ከች አለ፡፡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የተጠለፈበት ቆብ አድርጓል፡፡ በለመዱት የኢትዮጵያውያን ባህል መሠረት ከመቀመጫቸው ተነሥተው ተቀበሉት፡፡ ወንበር ስቦ እንደ ተቀመጠ ያጠለቀውን ቆብ ጠረጲዛው ላይ አኖረው፡፡ ሚስተር ዣክ የተቀመጠውን በኢትዮጵያ ባንዴራ የተጠለፈ ቆብ አየት አደረጉና «እናንተ ኢትዮጵያውያን ለምንድን ነው በባንዴራችሁ ማጌጥ የምትወዱት?» አሉና ኢትዮጵያዊውን እንግዳቸውን ጠየቁት፡፡

«እኛ ኢትዮጵያውያን ሀገራችንን እንወዳለን፡፡ በሀገራችን ለመጣ ርኅራኄ የለንም፡ ይህ የሀገር ፍቅር በደማችን ውስጥ አራተኛ ሴል ሆኖ ተቀምጧል፡፡ ለዚህ ነው» አላቸው፡፡

Sunday, May 23, 2010

100%


ሦስት ምሁራን ያቀረቡት ጥናት ተጠቃልሎ የታተመበትን ‹‹ያለ መቻቻል ፖለቲካ ሰማዕታት›› የተሰኘ መጽሐፍ ሳነብ ከ1969 - 1970 ዓ.ም የነበረውን የአገራችን ልዑላን እና ኀያላን ፍትጊያ በዐይነ ኅሊናዬ እየቃኘኹ ነበር፡፡ ከዚህ በፊት ካነበብኳቸው ዘመኑን ከተመለከቱ ጽሑፎች ጋር እያዛመድኩ አወጣሁ፤ አወረድኩ፡፡ ከዚያም ለምን እንደዚያ ‹‹ቀይ ሽብር›› እና ‹‹ነጭ ሽብር›› እየተባባልን መጨራረስ አስፈለገን? ያን ሁሉ ጭካኔ እና የእብድ ውሻ ሥራ ምን አመጣው? አብዮት ለማካኼድ የስንት ሰው ደም መፍሰስ አለበት? ውቃቤው እንዲረካ የስንት ሰው ?ሕይወት መቀጠፍ  አለበት? ከማይም እስከ ምሁር፣ ከሲቪል እስከ ወታደር እንዲያ ሲጨፋጨፍ አደብ የሚገዛ እንዴት ጠፋ?

Thursday, May 20, 2010

ልዩ መርሐ ግብር ከግንቦት 10 እስከ 12


አለቃ ተክሌ

አለቃ ተክሌ የታዋቂው ሊቅ የአለቃ ገብረ ሐና ልጅ ናቸው፡፡ ዝማሜው ከእርሳቸው የቀደመ ታሪክ ቢኖረውም ያሳወቁት እና ወንበር ዘርግተው ያስተማሩት እርሳቸው በመሆኑ «የተክሌ ዝማ» እየተባለ በስማቸው ይጠራል፡፡

የአለቃ ተክሌ እና የዝማሜው መገጣጠም ግን የሚከተለውን ይመስላል፡፡

ልዩ መርሐ ግብር ከግንቦት 10 እስከ 12

አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ

ከቅዱስ ያሬድ ቀጥሎ ታላቅ ቦታ የያዘ ኢትዮጵያዊ ሊቅ፡፡ ዐፄ ዳዊት ደግሞ «ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ» ብለውታል፡፡ አባቱ ሕዝበ ጽዮን እናቱ አምኃ ጽዮን ይባላሉ፡፡ እንደ ድርሳነ ዑራኤል አባቱ በመጀመርያ የትግራይ በኋላ ደግሞ የሰግላ «ጋሥጫ» ገዥ ነበረ፡፡ እንደ ገድሉ ደግሞ ጠቢብና የመጻሕፍት ዐዋቂ፤ የእግዚአብሔር ወዳጅና በቤተ መንግሥት በነበረችው ድንኳን «ሥዕል ቤት» ከሚያገለግሉ ካህናት ወገን ነበር፡፡ የመካከለኛውን ዘመን ታሪክ የመረመርን እንደሆነ ሁለቱም ምንጮች ስለ አንድ ጉዳይ የተለያዩ መረጃዎች የሚሰጡ ሳይሆኑ አይቀርም፡፡

ለምሳሌ በንጉሥ ላሊበላ ዘመን የአራቱ የኢትዮጵያ ግዛቶች አስተዳዳሪዎች የታላላቅ አድባራት ገዥዎች ነበሩ፡፡ ከዚህም በላይ የአንዳንድ ገዳማት አበምኔቶችና በቤተ መንግሥት የሚያገለግሉ ካህናት አንድ አንድ አውራጃ ወይም ወረዳ ይሾሙ ነበር፡፡ በመሆኑም የአባ ጊዮርጊስ አባት ክህነትን ከገዥነት የደረበ ሳይሆን አይቀርም፡፡ የአባ ጊዮርጊስን እናት ገድሉ «ወእሙኒ እም ስዩማነ ወለቃ» ይላታል፡፡ ይህም በወለቃ /የዛሬው ደቡብ ወሎ፣ ቦረና / ከነበሩ መኳንንት ወገን መሆኗን ያመለክታል፡፡

Tuesday, May 18, 2010

ልዩ መርሐ ግብር ከግንቦት 10 እስከ 12ቅዱስ ያሬድ ማነው?


 የቅዳስ ያሬድ አባቱ አብድዩ /ይስሐቅ/ እናቱ ክርስቲና /ታውክልያ/  ይባላሉ /በሌላም በኩል አባቱ እንበረም እናቱ ትውልያ ይባላሉ የሚል ታሪክም አለ፡፡/ የትውልድ ሥፍራው አከሱም ነው፡፡ የተወለደው በ505 ዓ.ም/  ሚያዝያ 5 ቀን የሚል አለ/ ሲሆን በተወለደ በ7 ዓመቱ ወላጅ አባቱ ስለሞተ እናቱ የአክሱም ጽዮን መምህር ለነበረው ለአጎቱ ለጌዴዎን እያስተማረ እንዲያሳድገው ሰጠችው፡፡ ከአባ ጌዴዎንም ዘንድ እየተማረ ለ25 ዓመት ተቀመጠ፡፡

ሆኖም ቃለ እግዚአብሔር የመቀበል ችሎታው ደካማ ስለሆነ በጣም ያዝን ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ከትምህርት ድክመቱ የተነሣ አጎቱ በጨንገር ቢገርፈው በዚህ ተበሳጭቶ ትምህርቱን ትቶ ሄደ፡፡ በመንገድም ሲጓዝ ውሎ በቀትር ደክሞት ከዛፍ ሥር ዐረፈ፡፡ በዚያ ጊዜ አንድ ትል ከዛፉ ላይ ያለውን ፍሬ ለመብላት ስድስት ጊዜ በመውደቅና በመነሣት ዛፉ ላይ ለመውጣት ሞክሮ በሰባተኛው ሰተት ብሎ ወጥቶ ሲበላ ተመለከተ፡፡ እርሱም በፈጸመው የብስጭት ተግባር በመጸጸት ተመልሶና አጎቱን ይቅርታ ጠይቆ ትምህርቱን ቀጠለ፡፡ አጎቱም ተደስቶ ዓይነ ልቡናውን ያበራለት ዘንድ እያለቀሰ ፈጣሪውን ለመነለት፡፡ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶ ለቅዱስ ያሬድ ዕውቀትን ገልጾለት መጻሕፍተ ብሉያትንና ሐዲሳትን ዐወቀ፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይህን በተመለከተ

ልዩ መርሐ ግብር ከግንቦት 10 እስከ 12

                                 ያሬድ ክብር አነሰው
                   ገና ጥንት ያኔ . . . . . . .
                  ሰውም ሳይሰፍርባት አሜሪካ ታውቃ፣
                  ገና ጥንት ያኔ . . . . . . . . .
                  እንዲህ ሳትሠለጥን አውሮፓም ተራቅቃ፣
                ገና ጥንት ያኔ . . . . . . . .
                  ዓለም፣ ከእንቅልፏ ሳትነቃ፣

               እነ ሞዛርት እና እነ ቤት ሆቨን፣
               የዜማን ምልክት ገና ሳይነግሩን፣
               ያሬድ አንተ ነበርክ
                   የዜማን ቅማሬ የሠራህልን፣

Sunday, May 16, 2010

ሥጋ በል ዕጽዋት


ብዙዎቻችን ሥጋ በል እንስሳት መኖራቸውን እናውቃለንም ተምረናልም፡፡ እናም አይገርመንም፡፡ ሥጋ በል ዕጽዋት መኖራቸውን ግን ብዙ ጊዜ ሰምተንም ተምረንም ስለማናውቅ ከመገረም አልፎ «እንዴት ሊሆን ቻለ?» የሚል ጥያቄንም ይፈጥርብናል፡፡ ሥጋ በል እንስሳትስ በክርናቸው ደቁሰው፣ በጥርሳቸው ዘንጥለው ይበላሉ፡፡ ለመሆኑ እነዚህ ሥጋ በል ዕጽዋት እንዴት አድርገው ነው ሥጋ የሚበሉት? ደግሞስ በምን ሆዳቸው ይፈጩታል? እያለ ጥያቄው ይቀጥላል፡፡

ሥጋ በል ዕጽዋት አፈጣጠራቸው እንደ ዕጽዋት አኗኗራቸው እንደ አራዊት ነው፡፡ ነፍሳቱ የሚያውቋቸው በተክልነታቸው አብበው ሲለመልሙ ነው፡፡ በውስጣቸው ግን የአውሬነት ጠባይ ስላለ የዋኾቹ ነፍሳት አትክልት ናቸው ብለው ሲጠጓቸው ረዥም ቅጠላቸውን ጥቅልል ያደርጉና ነፍሳቱን እምሽክ አድርገው ይበሏቸዋል፡፡

ከእስስት እና ከእንሽላሊት ያመለጡ ነፍሳት እንኳን በእነዚህ ሥጋ በል ዕጽዋት በቀላሉ ይጠቃሉ፡፡ የንብ ጥበብ፣ የቢራቢሮ ውበት፣ የጢንዚዛ ጩኸት፣ የተርብ ኃይለኛነት፣ የትንኝ ተናዳፊነት፣ አይበግራቸውም፡፡

ለምን?
እነዚህ ሥጋ በል ዕጽዋት መልካቸውም፣ ቁመናቸውም፣ አኳሃናቸውም፣ እንደ ዕጽዋት ነው፡፡ የሚኖሩትም ከዕጽዋት ጋር ከዕጽዋት መካከል ነው፡፡ እንደ ዕጽዋት አበባ አላቸው፤ ቅጠል አላቸው፤ ግንድ አላቸው፤ ሥር አላቸው፤ ልምላሜ አላቸው፡፡ እንደ ዕጽዋት ከመሬት ተነሥተው ወደ ላይ ያድጋሉ፤ አፈር እና አየር ይወስዳሉ፤ በሁለመናቸው ዕጽዋትን ይመስላሉ፡፡

ነገር ግን የዋኾቹ ነፍሳት ሊያውቁት የማይችሉ አንድ ድብቅ ጠባይ አላቸው፡፡ እርሱም ለሌላ ያልተገለጠ የአውሬነት ጠባይ በውስጣቸው አለ፡፡ ይህንን ጠባይ እንኳንስ ነፍሳቱ ሰውም ያወቀው በቅርቡ ነው፡፡ በባህላዊው ዕውቀት ሥጋ የሚበላ አውሬ መኖሩን እንጂ ሥጋ የሚበላ ተክል መኖሩን የሚናገር ታሪክም፣ ተረትም፣ ወግም፣ አባባልም የለም፡፡

ይህ ጠባያቸው ነው እንግዲህ ሳይደክሙ አድፍጠው ግዳያቸውን በእጃቸው ላይ እንዲጥሉ ያደረጋቸው፡፡ የዱር አራዊት አንድ ጊዜ አውሬ መሆናቸው በሁሉም ዘንድ ስለታወቀ፤ በአራዊት እንበላለን ብለው የሚሰጉ እንስሳት ብዙዎች ናቸው፤ እያንዳንዱ እንስሳም ከእነርሱ የሚያመልጥበትን የየራሱን ጥበብ በዘመናት ብዛት አከማችቷል፡፡ ያደፍጣል፣ ያመልጣል፣ ይሸውዳል፣ ይመሳሰላል፣ ቀለሙን ይቀይራል፣ ጊዜ ይመርጣል፤ ይናደፋል፤ ይቧጭራል፤ ከባሰበትም በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ይጋደላል እንጂ በቀላሉ እጁን አይሰጥም፡፡

ይህንን የግዳዮቻቸውን ጠባይ ያወቁት አራዊትም ለመብላት የሚያስቧቸውን እንስሳት የሚያጠቁበት አያሌ ዘዴ ዘይደዋል፡፡ ኃይል፣ ጉልበት፣ ጥበብ ይጠቀማሉ፡፡ ጊዜ መርጠው አድብተው ያጠቃሉ፡፡ ግዳይ እንዲህ በቀላሉ አይጣልምና ብዙ ድካም እና ልፋት አለባቸው፡፡

ሥጋ በል ዕጽዋት ግን ይህ ሁሉ የለባቸውም፡፡ ጠባያቸውን አሳምረው፣ ዕጽዋትን መስለው፤ እስከ ጊዜው ድረስ አውሬነታቸውን በልምላሜያቸው እና በአበባቸው ሠውረው ጸጥ ይላሉ፡፡ ነፍሳቱ እንደ ለመዱት አበባ ለመቅሰም እና ቅጠልን ለመብላት፣ ለእረፍት እና ለመዝናናት ወደ እነርሱ ሲጠጉ ግን ተክልነታቸው ያበቃና አውሬነታቸው ብቅ ይላል፡፡ የገባ አይወጣም፡፡ የተያዘ አያመልጥም፡፡

አሁን አሁን ከሰዎች መካከል ማኅበረሰቡን እያስቸገሩ ያሉት ሥጋ በል ዕጽዋት ናቸው፡፡

Thursday, May 13, 2010

ስማችሁ የለም


በሰማያዊው ዙፋን ዘንድ አንድ ውሳኔ ተላለፈ፡፡ «እነዚህ የኢትዮጵያ ሰዎች ሃይማኖተኞች ናቸው፡፡ ስለዚህም ዓለም ከማለፉ በፊት አስቀድመው ተጠርተው ዋጋቸውን ሊቀበሉ ይገባል» የሚል፡፡ አንድ ሊቀ መልአክ እልፍ አእላፍ መላእክትን አስከትሎ ከሰማይ ሲወርድ ታየ፡፡ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሰዎችንም ሁሉ ለሰማያዊ ፍርድ ሰበሰባቸው፡፡


ወዲያውኑ በመንግሥተ ሰማያት በር ላይ ሁለት ዓይነት ሰልፎች ታዩ፡፡ አንደኛው ሰልፍ ረዥም፤ ሌላኛው ሰልፍ ግን አጭር ነበር፡፡ ረዥሙ ሰልፍ ባለበት ቦታ ገበሬዎች፣ ወዛደሮች፣ የዕለት ሥራ ሠራተኞች፣ እናቶች፣ አባቶች፣ ሕፃናት፣ ሊስትሮዎች፣ የቤት ሠራተኞች፣ ሾፌሮች፣ መሐንዲሶች፣ ሐኪሞች፣ አስተማሪዎች፤ ማን ያልተሰለፈ አለ፡፡ ከጥቂቶቹ በቀር ብዙዎቹ መንግሥተ ሰማያት የመግቢያ ካርድ ማግኘት ቻሉ፡፡

Monday, May 10, 2010

ኦርቶዶክሳዊ መምህር፣ ዕውቀቱ እና ክሂሎቱ ክፍል 2

ባለፈው ጊዜ አንድ መምህር ከየት ከየት ትምህርት ሊያገኝ እንደሚችል መመልከት ጀምረን ነበር፡፡ ከቅዱሳት መጻሕፍት ስለሚገኝ ዕውቀት በመጠኑ አይተናል፡፡ ዛሬ ደግሞ ሌሎችን እናያለን፡፡                                                                           

የቤተ ክርስቲያን ትውፊት፡
ሁሉም ነገር በመጽሐፍ አልተጻፈም፤ በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ በጸሎቱ፣ በማኅሌቱ፣ በቅዳሴው፣ወዘተ የምናገኛቸው ትምህርቶች እና ሥርዓቶች ለቤተ ክርስቲያን ርቱዐዊ ጉዞ አስፈላጊ ናቸው፡፡


የቤተ ክርስቲያን ጉባኤያት ውሳኔዎች
በየዘመናቱ የተነሡ መናፍቃንን፣ በየጊዜው የተፈጠሩ ችግሮችን፣ በየሁኔታው የገጠሙ ፈተናዎችን ለመፍታት በጉባኤያት ተሰብስበው አበው የደነገጓቸው ድንጋጌዎች ቤተ ክርስቲያን ከማዕበል ወጥታ ወደ ጸጥታ ወደብ እንድታመራ ያደረጉ፤ የቤተ ክርስቲያንንም አንድነት ያጸኑ ዋልታዎች ናቸው፡፡

በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሁለት ዓይነት ጉባኤያት ተደርገዋል፡፡                           

ዓለም ዐቀፍ ጉባኤያት፡ እነዚህ ጉባኤያት በወቅቱ የነበሩ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የተሳተፉባቸው፣ የቤተ ክርስቲያንንም ጉዞ የመወሰን ሥልጣን ያላቸው ጉባኤያት ናቸው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን በ325 ዓም የተደረገውን ጉባኤ ኒቂያ፣ በ381 ዓም የተደረገውን ጉባኤ ቁስጥንጥንያ እና በ431 የተደረገውን ጉባኤ ኤፌሶን ትቀበላለች፡፡ ለሌሎቹ ግን ርቱዓን ናቸው ብላ ዕውቅና አትሰጥም፡፡

አካባቢያዊ ጉባኤያት እነዚህ ጉባኤያት በአንድ አካባቢ የተነሡ ችግሮችን ለመፍታት በአካባቢው የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት የሠሯቸው ጉባኤያት ናቸው፡፡ የእስክንድርያ፣ የጋንግራ፣ የዕንቆራ፣ የካርታጎ ወዘተ እየተባሉ የሚጠሩ ጉባኤያት ናቸው፡፡ በሀገራችንም በ14ኛው መክዘ የተደረገውን የደብረ ምጥማቅ ጉባኤ መጥቀስ ይቻላል፡፡ አንድ የቤተ ክርስቲያን መምህር በእነዚህ በሁለቱ ዓይነት ጉባኤያት የተወሰኑ ውሳኔዎችን ማወቅ አለበት፡፡

ተጨማሪ ዕውቀቶች

Friday, May 7, 2010

ትልቅ ሰው

እንዲሀም ሆነ

ስድስት ጓደኛሞች ነበሩ፡፡ ወጣቶች ወንዶች፡፡ ደግሞ የሚገርመው ሁሉም ቀጠን እና ረዘም ይላሉ፡፡ ከመካከላቸው አንዱ ሊያገባ ይነሣል፡፡ አምስቱ ጓደኞቹ ደግሞ ሚዜ ብቻ ሳይሆን ሽማግሌም ሊሆኑት ይነሣሉ፡፡ የሽምግልናውን ባሀል ጠይቀው፣ አጥንተው እና ተዘጋጅተው የልጅቱ ወላጆች በተቀጠሩበት ቀን ወደ ልጅቱ ቤተሰቦች ዘንድ ይሄዳሉ፡፡ «ግቡ ግቡ» ይባሉና ገቡ፡፡ «ተቀመጡ» ሲባሉ «አንቀመጥም ጉዳይ አለን» ይላሉ እንደ ባህሉ፡፡ ወላጆች እና ዘመዶችም ገላግለው ያስቀምጧቸዋል፡፡

እናትም ወደ ጓዳ፣ አባትም ወደ መኝታ ቤት ገቡ፡፡ የቀረው ቤተ ዘመድም የደራ ወሬ ጀመረ፡፡ ጥቂት ጊዜ ጠብቀው ትንሽ ከቤተ ዘመዱ ጋር የሚተዋወቀውን አንዱን ጓደኛቸውን ወደ ጓዳ ላኩት፡፡ እናቲቱን አገኛቸው፡፡ «እማማ ቁጭ በሉ ብላችሁን ጥላችሁን ጠፋችሁኮ» አለ በቀልድ «እስኪመጡ አንዳንድ ነገር ላድርግ ብዬ ነው» አሉት እናቲቱ፡፡ «የምትጠብቁት ሰው አለ እንዴ?» አለ ልጁ፡፡ «ምን ሽማግሌዎቹኮ ቀሩ፤ መጀመርያ የናንተን እንጨርስ መሰል» ይላሉ እናት፡፡

Tuesday, May 4, 2010

ኦርቶዶክሳዊ መምህር፣ ዕውቀቱ እና ክሂሎቱ

ማስተማር ምንድን ነው?

ጌታችን ሐዋርያትን ሲልካቸው የሰጣቸው የመጨረሻው መመርያ ለመምህራን ሁሉ መሠረት ነው፡፡ በኢየሩሳሌም፣ በይሁዳ፣ በሰማርያ፣ እስከ ዓለም ዳርቻ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ» /የሐዋ 1÷8/ ይህ ቃል የአንድ ሐዋርያ ተግባር ፍጻሜ እንደሌለው ያስረዳናል፡፡ ሊቃውንቱ ይህንን መመርያ በሁለት መንገድ ተርጉመውታል፡፡ (Arch bishop Anthonios Marqos, The Theology of mission and missionary.)

1/ ከቅርብ እስከ ሩቅ፡- የአንድ ሐዋርያ ተግባር አጠገቡ ካለው ማኅበረሰብ ጀምሮ አይቶት እና ሰምቶት እስከማያውቀው ሕዝብ ሊደርስ እንደሚችል

2/ ከቀላል ወደ ከባድ፡- ለአገልግሎቱ ቀላል ከሆነው አንሥቶ ውስብስብ እና አስቸጋሪ ወደሆነው አገልግሎት፤ መሥዋዕትነት ከማይጠይቀው አገልግሎት መሥዋዕትነት እስከ ሚጠይቀው አገልግሎት እንደሚደርስ ያስረዳል፡፡

በዚህ ተግባሩ የሚፈጽማቸው አገልግሎቶች በሁለት ዋና ዋና ተልዕኮዎች እና በአምስት ዝርዝር ተልዕኮዎች ይጠቃለላሉ፡፡

ስለ ንባብ የአንባብያን አስተያየቶች

አንባቢ ትውልድ እንዲኖረን ኅጻናት ላይ ብዙ መስራት ይጠበቅብናል 

ዲ/ን ዳንኤል፣

እጅግ በጣም ጥሩ ጽሑፍ ነው። እግዚአብሔር ያቆይልን።

መፍትሔው ብዙ ሊሆን ቢችልም አንዱና ምናልባትም ከዋናዎቹ አንዱ የሚከተለው ይመስለኛል። የሚያነብ ትውልድ እንዲኖረን በመጀመሪያ የሚያነቡ ኅጻናት እንዲኖሩ ያስፈልጋል።

ማንኛውንም በጎ ልምድ ማንበብን ጨምሮ በአጭር ጊዜ የሚዳብር አይደለም። ይልቁንም በእድሜ ከጠነከሩ በኋላ ለመለወጥ ጥረት ቢደረግም በውስጥ ስላልዳበረ ለውጡ ዘላቂ አይሆንም። ፈደልንም ሆነ የማስተማር ስርዓቱን ወደሰጡን የሃገራችን ሊቃውንት ብንመለከት ከዚያ ትልቅ ቁምነገር እንማራለን። አንተ እንደጠቀስከው በተወሰኑ ዘመናት የማንበብንና የመጻፍን ነገር የሚያዳክሙ ክስተቶች ቢፈጠሩም ለመማር ከቻለው በጣም ጥቂት የማሕበረሰብ ክፍል ውስጥ የነበሩትን ብዙ የማይባሉ መጻሕፍት እያስደጎሰና እየጠረዘ ተንከባክቦ በመያዝ እያነበበ ለማወቅ ይጥር የነበረና አውቆም የተራቀቀ ትውልድ የነበረን መሆኑ አይካድም። ይልቁንም በቤተክርስቲያን። ያ የሆነው በሃገራችን ሊቃውንት በተሰራው ስርዓት መሠረት ትምሕርት የሚጀመረውና ልጆች ከማንበብ ጋራ የሚተዋወቁት (ዳዊት በመድገም ወዘተ) ገና በኅጻነነታቸው ወራት ስለነበረ ነው።