Sunday, April 18, 2010

የመቅደላው ጌታ

ልዩ መርሐ ግብር
ዐፄ ቴዎድሮስ አስደናቂውን ገድል ከፈጸሙ 142 ዓመታት ሆኗቸው፡፡ ባለፈው ሚያዝያ 6 ቀን 2002 ዓም፡፡ መቅደላ ላይ ራሳቸውን የሠውት ሚያዝያ 6 ቀን 1860 ዓም ነው፡፡ ባለፈው ሳምንት መታሰቢያ ሊደረግላቸው ይገባ ነበር፡፡ ከአንዳንድ FM ሬድዮኖች በቀር ያስታወሳቸውም የለ፡፡ እስኪ በአዲስ ነገር አውጥቼው የነበረውን ጽሑፍ ለመታሰቢያነት መልሰን እንየው፡፡ መልካም ንባብ፡፡

እነሆ በዊንድዘር ቤተ መንግሥት እንገኛለን፡፡ ይህ ቤተ መንግሥት በዓለም ላይ በስፋቱ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት አገልግሎት ሰጭ ቤተ መንግሥት ነው፡፡ «ዊልያም ወራሪው» እየታባለ በሚጠራው የእንግሊዝ ንጉሥ/ 1066-1087/ የተገነባው ይህ ቤተ መንግሥት 10.5 ሄክታር ስፋት አለው፡፡ በውስጡ 951 ክፍሎች ሲኖሩት ከእነዚህም ውስጥ 225ቱ የመኝታ ክፍሎች ናቸው፡፡ ቤተ መንግሥቱ ለእንግሊዟ ንግሥት ኤልሳቤጥ በዓመት ሁለት ጊዜ /በሰሞነ ትንሣኤ እና በሰኔ ወር/ ለማረፊያነት ያገለግላል፡፡

ወደዚህ ቤተ መንግሥት የሄድኩት ልቅሶ ልደርስ ነው፡፡ በሃገራችን ባሕል አንድ ሰው በሞተበት ጊዜ ተገኝቶ ያልቀበረና ልቅሶ ያልደረሰ ሰው ዘግይቶ ሲመጣ ወደ መቃብር ሄዶ የሟችን መቃብር አይቶ እርሙን ያወጣል፡፡ እኔም ወደዚህ ቤተ መንግሥት የሄድኩት በቤተ መንግሥቱ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኘውን የልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስን መቃብር ለማየት ነበር፡፡

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ በጄኔራል ናፒየሪ አማካኝነት ከእናቱ ጋር ወደ እንግሊዝ ተጓዘ፡፡ መንገድ ላይ እናቱ ዐርፋ ብቸኛ የሆነው ዓለማየሁ የንግሥት ቪክቶርያ ክብካቤ ሳይለየው በእንግሊዝ የንጉሣውያን ቤተሰቦች ዘንድ አደገ፡፡ ነገር ግን እንደ ሀገሩ እንደ ሕዝቡ የሚሆንለት አላገኘም፡፡ በ18 ዓመት ዕድሜው ታምሞ ሞተ፡፡ በሀገሩ ቢሆን ኖሮ ሙሾ ወርዶለት፣ ፍትሐት ደርሶለት፣ የውሎ ልቅሶ ተዘጋጅቶለት፣ ግጥም እና ዜማው እየወረደ ነበር የሚቀበረው፡፡ ይህንን ክብር በባዕድ ሀገር ያግኘው ያግኘው አላወቅኩም፡፡

ትኬት ለመቁረጥ ወደ እንግዳ መቀበያው ስንገባ ረዥም ሰልፍ ነበር፡፡ እንዳይሰለቸን ስለ ቤተ መንግሥቱ የሚያብራራ የምናነበው ብሮሸር ሰጡን፡፡ የምንጎበኘው የዐፄ የፋሲልን ቤተ መንግሥት አይደለምና፡፡ መቼም እንግሊዞች ቱሪስትን በመሳብ፣ በመከባከብ እና በሥርዓቱ በማስጎብኘት የሚመሰገን ባሕል አላቸው፡፡ በዓመት ከ12 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ እንደሚያገኙበት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

እዚያ ቦታ ቆሜ የፋሲልን ቤተ መንግሥት የጎበኘሁበትን ጊዜ አሰብኩት፡፡ አልፎ አልፎ ከተጻፈው ነገር በቀር በሥዕል፣ በቅርጽ፣ በዓይነት፣ በጽሑፍ፣ በቪዲዮ ታሪኩን ለመግለጥ የተደረገ ጥረት አልነበረም፡፡ ሌላው ቀርቶ የቤተ መንግሥቱን ታሪክ አስጎብኝዎቹ ደስ እንዳላቸው ይተርኩታል እንጂ ከነካርታው የተዘጋጀ መጽሐፍ እንኳን አላገኘሁም ነበር፡፡ «እዚህ ቦታ ይተኙበት ነበር» ብሎ ከመግለጥ ባለፈ በዚያ ዘመን የነበረውን አልጋ አፈላልጎ ወይንም አስመስሎ ሠርቶ ለማሳየት አይሞከርም፡፡

ዊንድዘር ቤተ መንግሥትን ስትጎበኙ ግን ያን ጊዜ የነበረው ሳሎን፣አልጋ፣ ማዕድ ቤት ከነቁሳቁሱ ትጎበኙታላችሁ፤ ዶሮዎች እና በጎች እንዴት ይታረዱ እንደነበር በላስቲክ በተሠራ ቅርጽ ታዩታላችሁ፡፡ ይጠቀሙበት የነበረው መሣርያ፣ ቢላዋው፣ ሰሐኑ አልቀራቸውም፡፡ ታድያ እነ ዐፄ ፋሲል ቢያንስ ሞሰብ አልነበራቸውም፣ ይቀመጡበት የነበረውን ወንበር፣ ይጫወቱበት የነበረውን ገበጣ፣ ድስቱን እና መክተፊያውን፣ የዘመኑ ሰዎች ይጠቀሙበት የነበረውን መሣርያ፣ ልብሳቸውን እና ምንጣፋቸውን በየገዳማቱ ከሚገኙት ቅሪቶች ገልብጦ በመሥራት ማሳየት አቅቶን ነው?

በጥንታዊው የአሳሳል ዘይቤ የጥንቱን ሁኔታ ስለን በየግድግዳው ብናስቀምጠው፤ ፎቶ አንሥተን ለቱሪስቱ ብንሸጠው፣ ፖስት ካርድ ብናደርገው ሀገር ስለሚያሳድግ ከመጀመርያው መታሰብ የለበትምi

የሃያኛዋን ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ የሚያሳየው የአዲስ አበባው ቤተ መንግሥትስ ቢጎበኝ ምን ይለዋል? ነፍሳቸውን ይማርና የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የነበሩት ብርጋድዬር ጄኔራል ፍሬ ሰንበት ዓምዴ አያሌ ቅርሶችን አሰባስበዋል፡፡

የዊንድዘርን ቤተ መንግሥት በየክፍሎቹ እያየን፣ በኛም ስንፍና እየተናደድን ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ገባን፡፡ ከመግቢያው በር አጠገብ የቤተ መንግሥት አስጎብኝዎችን ልብስ የለበሱ በዕድሜ ጠና ያሉ ሰው አገኘን፡፡ ጠጋ አልንና «የዓለማየሁ ቴዎድሮስን መቃብር ለማየት ነበር» አልናቸው፡፡ «ኢትዮጵያውያን ናቸሁ?» ሲሉ ጠየቁን፡፡ እኛም በአዎንታ ራሳችንን ነቀነቅን፡፡ «ብዙ ጊዜ ነጮች እና ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ጥቁሮች ናቸው የሚጠይቁን» ሲሉ በመገረም ተናገሩ፡፡ ከዚያም እየመሩ ይዘውን ሄዱ፡፡ በበሩ ገብታችሁ ወደ ግራ ትታጠፉና ግድግዳውን ጨርሳችሁ ወደ ቀኝ ልትዞሩ ስትሉ ማዕዘኑ ላይ የዓለማየሁን መቃብር ታገኙታላችሁ፡፡

ከላይ የመፆር መስቀል፣ ዝቅ ብሎ ደግሞ የአንበሳ ሥዕል ይታያል፡፡ ከአንበሳው ሥር በእንግሊዝኛ Near this spot lies buried Alemayehu /ከዚህ ቦታ አጠገብ ዓለማየሁ ተቀብሯል/ ይልና መልሶ በአማርኛ «ዓለማየሁ ቴዎድሮስ» ይላል፡፡ ቀጥሎም The Son of Theodor king of Abyssinia, Born 23 April 1861 Died 14 Nov. 1879. This tablet is placed here to his memory by Queen Victoria. /የአቢሲኒያ ንጉሥ የቴዎድሮስ ልጅ፤ አፕሪል 23 1861 ተወለደ፣ ኖቬምበር 14 ቀን 1879 ዐረፈ፡፡ ይህ ጽሑፍ ለእርሱ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ በንግሥት ቪክቶርያ ተቀመጠለት/ ይላል፡፡ በመጨረሻም ልብን የሚነካ ጥቅስ ሠፍሯል I was stranger and ye took me in. ከጥቅሱ ሥርም የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕል ይገኛል፡፡

ዝም ብዬ ፈዝዤ አየው ነበር፡፡ በማያውቀው ሀገር፣ አባቱ እና እናቱ ሞተውበት፣ በልጅነት እድሜው እንዴት ይሆን ያሳለፈው? ምን ይሆን የተሰማው? እርሱ ትናንት ያለ ፍላጎቱ ወደ መጣባት ሀገር ዛሬ የርሱ ወገኖች በፍላጎታቸው በረሃ እና ባሕር እያቋረጡ እንደሚመጡ ያውቅ ይሆን?

እነዚህ ሁሉ በኅሊናዬ ሲያልፉ አስጎብኛችን «የእርሱ አባት ከጦርነቱ በፊት ራሳቸውን መግደላቸውን ዐውቃለሁ፣ የት ነው የተቀበሩት?» አሉና ጠየቁኝ፡፡ «መቅደላ በሚባል ተራራ ላይ ነው» አልኩና መለስኩላቸው፡፡ «ምናልባት እዚያ ቢሆን ኖሮ በሀገሩ ባሕል የተሻለ ክብር ያገኝ ይሆናል» አሉና አንድ አስደንጋጭ ጥያቄ አመጡብኝ «እንዴት ነው መቅደላ) መቼም መቃብሩን በሚገባ እንደ ያዛችሁት ተስፋ አደርጋለሁ፣ እዚህ ድረስ ዓለማየሁን ለማየት ከመጣችሁ እዚያ ያለውንማ በጣም ታከብሩታላችሁ ማለት ነው፡፡ እዚህ የሚመጡ አንዳንድ ጎብኝዎች ይጠይቁናል፤ እስኪ ስለ መቅደላ ንገሩኝ?»

ነገር መጣ፡፡

ምን ብዬ ልንገራቸው፡፡ መቅደላ የቱሪስት መዳረሻ አይደለም ልበላቸው? የልጃቸው መቃብር በባዕድ ሀገር ያገኘውን ክብር አባቱ በሀገሩ አላገኘውም ልበላቸው? መቅደላ ላይ ሙዝየም የለም፣ የሚጎበኝ ነገር የለንም፣ የአባቱም መቃብር እንደ እንግዳ መቃብር ያለ ነው ልበላቸው? ሴፓስቶፖል የመቅደላ አፈር ተሸከመው እንጂ በሥነ ሥርዓት አልተቀመጠም ልበላቸው? ዓለማየሁንስ መቃብሩን ሰው ይጎበኘዋል መቅደላ የአባቱ መቃብር ግን ተረስቷል ልበላቸው? በቴዎድሮስ መቃብር ላይ የተጻፈ ታሪክ፣ የተሠራ ሙዝየም፣ የተሰበሰበ ቅርስ የለም ልበላቸው? ጦርነት ካልመጣብን ቴዎድሮስ ትዝ አይለንም ልበላቸው? ራሳቸውን በጀግንነት መሠዋታቸውን እንጂ ሀገር ለማሳደግ፣ ቴክኖሎጂን ለመጠቀም፣ ራስን ለመቻል፣ ከጥገኛነት ለመውጣት፣ ሀገርን ለማደራጀት የሠሩት ሥራ ትዝ ብሎን አያውቅም ልበላቸው? ከልማታቸውመ ከጥፋቸውመ ገና ትምህርት አልወሰድንም ልበላቸው? አዲሱ ትውልድ ከእርሳቸው የወረሰው ቁንዳላቸውን ብቻ ነው ልበላቸው?

ቴዎድሮስ የተዋጉት ከእንግሊዞች ጋር ነው፡፡ የተዋጓቸው እንግሊዞች ልጃቸውን በሥርዓት ይዘው፣ ሲሞት በሥርዓት ቀበሩት፣ ንግሥት ቪክቶርያም መታሰቢያ አደረገችለት፤ ዐፄ ቴዎድሮስ የሞቱላት፣ የተዋጉላት፣ ኢትዮጵያ ግን ረስታቸዋለች ልበላቸው? መልሱን አልነገርኳቸውም፤ ዝም አልኳቸው፡፡

«በል ከዚህ እንደወጣህ ወደ ኩዊንስ ጌት እና ኬሲንግተን ጎዳን ሂድና ከንጉሣችሁ ጋር የተዋጋውን ሰው ታገኘዋለህ» አሉኝ፡፡ እንዳሉኝም ከኢንተርኔት ላይ አድራሻውን አውጥተን ወደዚያው በረርን፡፡

ቦታው ላይ ስንደርስ በፈረስ ላይ እንደሚጋልብ ሆኖ የታነፀ ሐውልት አገኘን፡፡ ከሐውልቱ ሥር የተጻፈውን ጽሑፍ ለማየት ዝቅ ስል በእንግሊዝኛ «ጄኔራል ናፒዬሪ፣ የመቅደላው ጌታ Lord of Magdala´ ይላል፡፡ ይህ መዓርግ የናፒየሪ የልጅ ልጆች ሁሉ የሚጠሩበት መዓርግ ሆኗል፡፡ ልቤ በኀዘን ተመታ፡፡ «የመቅደላው ጌታ» መቅደላ ላይ ተኝቷል፡፡ መቅደላን የመረጣት፣ ያከበራት እና ታሪክ የሠራባት የመቅደላው ጌታ እንደ ተራ ሰው መቅደላ ላይ ተኝቷል፡፡ እንግሊዞች ግን ሌላ የመቅደላ ጌታ ሰይመው እርሱንም አክብረው፤ ለልጅ ልጆቹም መጠርያውን ሰጥተው ሐውልቱን መሐል ለንደን ላይ አቁመውለታል፡፡ አዲስ አበባ ግን የመቅደላው ጌታ ሐውልቱ የላትም፡፡

31 comments:

 1. Thank you Dn Daniel for your wonderful observation! We never appreciated our own heros or history unless it is of political interest to current rulers! Our history is a tragedy of burying past history!!!! Thousand years later we are still committing the same crime!!! Three years ago I was talking to a Kenyan about our spiritual heritages and I was speechless when she asked me "how come you are who you are today despite all these?'!! I think I should have said that it is because we are suffering from a chronic disease called disrespecting where we come from and who contributed to that; not surprisingly we never knew where we are going!!!!

  ReplyDelete
 2. May God give you more wisdom so that we can see the unseen through you.
  Beta

  ReplyDelete
 3. አዬ ጉድ አሁን እኛ ታሪክ ጠባቂዎች ወይስ አጥፊዎች ነው የምንባል?
  ይህ ጽሁፍ በአጭሩ የሚገልጸን መሰለኝ።

  ወንድማችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን!

  ReplyDelete
 4. Dani, thank you very much. I think after this article published in Adis Neger, the Gov't start to build Monument for Atse Tewderos, the surprising thing is some group of people are ant-campaigning.

  Thanks

  ReplyDelete
 5. አባግንባር (ከሮማ)April 19, 2010 at 3:55 PM

  ውድ ዲን. ዳንኤል
  የተለመደው ሠላምታይ ይድረስህ እላለሁ፡፡ አፄ ተዎድሮስን አስመልክቶ አጭር ዝግጅት የዶቸ ቬሌ ራድዮ አዘጋጅቶ ነበረ፡፡ እናም
  ሚያዚያ 6፡ 1860 ዓ.ም. የማዕዶት ዕለት ለዓፄ ቴዎድሮስ እንደሚከተለው ሙሾ ወርዶላቸው እንደነበረ ገልጸው ለጆሮ በሚጥም ቅላጼ አቅርበውት ነበረ ፡፡ ምንም እንኳን ብዙ አንባቢ ቢያውቀውም ሙሉውን እንደሚከተለው አቅርቤልሃለሁ፡፡

  ሌላው ዳኒ ካልተሳሳትኩ መጨረሻ ላይ ለሰጠኸን ጥቆማ ግን የቴዎድሮስ ሐውልቱ ባይኖርም አደባባይ ተሰይሞለት መድፉም ተቀርፆ ፒያሳ ወደ ቸርችል ጎዳና ላያ መኖሩን መጥቀስም ጥሩ ነው፡፡

  እነሆ ሙሾ ……….
  አርባ ቀን ሁዳዴ ጡሞ ጡሞ ፋሲካ ሲደርስ
  በአፈር ገደፈ አሉ የሐበሻ ንጉሥ
  ዳር እስከ ዳር ይዞ የገዛው ንጉስ
  እንዲህ ስሱ ነው ወይ ጠመንጃ የሚጎርስ
  ጠላቶቹን ሁሉ አጭዶ እንደ ገብስ
  መቅደላ ተጣለ ራሱን በራስ
  በመቅደላ በኩል ጩኸት በረከተ
  የሴቱን አናውቅም ወንድ ኣንድ ሰው ሞተ
  አያችሁ ብያ ያንበሳውን ሞት
  በሰው እጅ መሞትን ነውር አድርጎት
  የትግሬንም ንጉስ ሲንቁ ሲንቁ
  የሸዋንም ንጉስ ሲንቁ ሲንቁ
  ወንድ አለራስዎ ገድለዉም አያውቁ
  አባትና እናቱ አለ አንድ አልወለዱ
  አባ ታጠቅ ካሳ ያው ወንዱ ያው ወንዱ
  መላው የጎጃም ሰው መላው የትግሬ ሰው ተይዞ በምጥ
  የእንግልዝ ሐኪሞች መጥተው ቢይዙት
  ተገላገለ አሉ ይህ ሁሉ ፍጥረት
  ገደልን እንዳይሉ ሞተው አገኙአቸው
  ማረክን እንዳይሉ ሰው የለ በእጃቸው
  ምነ አሉ እንግሊዞች ሲገቡ አገራቸው
  ለወሬ አይመቹም ተንኮለኞች ናቸው
  አምላክን መስሎ ቴዎድሮስ
  ንዑና ሁሩ ሲል ዋለ ሐሙስ
  ሰኞ መቅደላ ተጨነቀ
  ሰው መሆኑ ታወቀ

  ዳኒ ሌላ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ ሮም መሓል ከተማዋ (በአገሬው አጠራር TERMINI )ላይ የአፄ ዘርአይ ደረስን ገድል የሚተርክ ታሪክ ተፅፎበት የቆመ ሐውልት እስቲ የሱንና የአብዲሳ አጋን ከአበበ ቢቂላ ጋር አጣምረህ አስነብበን፡፡ የኔ ብዕር እንዳንተ የሰላች ስላልሆነች እንጂ የኢትዮጲያ ጀግኖች በሮም ብዬ (የዛሮዎቹን አየር ሐይልና ባህር ሐይል ) ያካተተ ጽሁፍ ባስነብብ ደስ ባለኝ ነበረ፡፡

  አባግንባር ነኝ ከሮማ

  ReplyDelete
 6. Once up on a time ,We lost our ways...
  We are cursed generations who throw our proud!so that we should pay for that....

  ReplyDelete
 7. thanks dani,
  tiwulidu yalayenewin nafaki honin engi !!!!

  ReplyDelete
 8. hi D/ Daniel ! nice memory, but no one may get up. u r always ringing z bell but hope fully u will get attention in its own time.i don't know what the so called "tourism bureau" is doing in all levels.
  we have nothing more to display than this. the history of emperror tewodros is is a mirror through which we can have an eye view about ethiopia's foreign contact during that time, which is z core of historical studies. any how be strong and keep it up one day may God awake ethiopians to preserve our heritage.

  may God be with u !!!

  ReplyDelete
 9. ቴዎድሮስ ለድሆችና ለአቅመ ቢሶች ተጨናቂ እንደነበሩ ቫልድሜዬር አንድ ልብ በሚነካ ምሳሌ ይነግረናል፡፡ ቴዎድሮስ በመንገድ ሲያልፉ አንድ ችግረኛ ባልቴት ወድቃ ቢያዩ ከፈረሳቸው ወርደው የለበሱትን ሸማ አንስተው ደረቡላት፡፡ ቫልድሜዬርን ያለውን ብር እንዲያበድራቸው ጠየቁትና የነበረውን አምስት ብር ተቀብለው ሰጧት፡፡ ለቫልድሜዬርም አምስት ብሩን አንድ መቶ አድርገው መለሱለት፡፡

  (ፕሮፌሰር መርዕድ ወልደ አረጋይ፤ የቴዎድሮስ ዓላማዎች ከየት እንደመነጩ፣ ጁን 1990)
  This was who Tewodros was!!!
  http://www.ethiopianreporter.com/index.php?option=com_content&view=article&id=1821:2010-04-14-08-27-31&catid=103:2009-11-13-13-46-23&Itemid=576
  This was Tewodros.

  ReplyDelete
 10. selam dani you are mahetot for tewhedo for ethiopia we allways apretiate you
  one day you and all of us we will pass but your work will stay for generation

  ReplyDelete
 11. I want to reveal my heart felt appreciation for your effort to show us the former Ethiopia in history mirror using the heritages as a eye wittiness.God may bless you,keep it up all your trials to aware more so as to awake us from deep sleep.If it is the good will of God we Ethiopians may stood on behalf of U to preserve our history and pass it to the next generation.10q

  ReplyDelete
 12. ዴርቶጋዳ /ያላቅማማው ንጉሥ/

  ሰው አማኙ ንጉሥ
  ‹‹በቴዎድሮስ እሻራለሁ፤እታሰራለሁ ወይም እገደላለሁ የማለት ፍርሃ ሊኖረው የማይችል ግራዝማች ዓለሜ ሊሾመውና ሊሸልመው አቅም ካልነበረው ከአመዴ በሽር ጋር ተላልኮ ወደሱ መኮብለሉን ሲሰሙ‹‹ ግራዝማች ዓለሜ የከዳኝ እንግዲህ ማንን አምናለሁ›› ብለው ተበሳጩ፤አዘኑ፡፡ለዚህም ነው በቴዎድሮስ ታሪክ ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ የኢትዮጵያ ታሪክ የገብርዬ የማይወላውል ታማኝነት ብርቅና ልብ የሚነካ ሆኖ የሚታየው፡፡ ረጅሙን የኢትዮጵያ ታሪክ ጠለቅ ብለን ብናስተውል የታማኝነት ጉድለት ለሰላምና እድገት ትልቅ እንቅፋት ሁኖ ይገኛል፡፡ የኃላፊነት ስሜታቸው ከፍ ያለ ብዙ ነገሥታት የሕዝቡን ችግር ለማቃለል ተነሳስተው ይረዱናል፤ያግዙናል ብለው የሾሙዋቸው ሰዎች እያደሙና እያሳደሙ፤እየሸፈቱና ስላስቸገሩዋቸው ዓላማዎቻቸው ከሽፈውባቸዋል፡፡›› Kasa And Kasa ገጽ 102

  ኢትዮጵያውያን ለነጻ አውጪ ንጉሣቸው ሞት ፀልየው ሌላ ነብይ ይጠብቃሉ
  የኢትዮጵያ ሕዝብ በበኩሉ የቴዎድሮስን ሞት በጣም ተመኘ፡፡ አንዱ ወታደር፤‹‹ፈጣሪውን ሲያማርር ንጉሡ በኋላ ደርሰው ቢሰሙት ለምን ፈጣሪህን ታማርረዋለህ ይህን ንጉሥ ግደልልኝ እንዳርፍ ብለህ ለምነው እጂ አሉት፡፡ እርሱም ሲመልስ ጃንሆይ አልሰማኝ አለ እንጂ እኔስ ሁልጊዜ ለመንሁት›› እንዳላቸው የሁሉም ሰው ጸሎት ይህ ሆነ፡፡ እንደፈለገውም በሚያዘያ 6 1868 ለተከፋባቸው ሕዝብ ራሱን አስወገደ፡፡ችግሩ ግን ተባባሰ እንጂ አብሮ አልተወገደለትም፤የችግሩ ምክንያት እሳቸው አልነበሩምና፡፡በቴዎድሮስ እቅዶች ተዳክመው የነበሩ ጦረኛ መሳፍንት በተዘናጋው ሕዝብ በመጠቀም አንሰራሩ፤ከድሮው በበለጠ ተጠናክረው ተነሱ፡፡ የቴዎድሮስ መነሳት አደናግጡዋቸው የነበሩት የውጭ ጠላቶች ይበልጥ ትምህርት ቀስመው በያቅጣጫው ብቅ ብቅ አሉ፡፡የኢትዮጵያ ሕዝብ ሌላ እውነተኛና ማይከሽፍበት ቴዎድሮስ የሚመጣበትን ቀን እንደገና መጠባበቅ ጀመረ፡፡›› Kasa And Kasa ገጽ 110
  በልብሱም ላይ ………………..
  ‹‹በወቅቱ የአይን ምስክር የነበረው አሜሪካዊ ሪፖርትር ህይወታቸው ስላለፈችው የመቅደላ ጀግና ሲያብራራ የተለየ ክብር ሳይደረግላቸው፤‹‹ጠባቂ ዘብ በአጠገባቸው ሳይቆም፤በቃሬዛ ላይ ለብዙ ሰዓት ያህል ከመሬት ተዘርረው፤ፀጉራቸው ተሸልቶ፤ልብሳቸው ተገፎና ተቀድዶ ከፊል እርቃነ ሥጋቸውን በማየቴ የቀድሞው ቴዎድሮስ መሆናቸው አጠራጠረኝ›› ይልና፤ ‹‹ራቅ ብዬ ስመለከት ብዙ ኦፊሰሮች በደም የተበከለውን የቴዎድሮስን ሸሚዝ ለኔ ይገባኛ በማለት ሲጓተቱና ሲጣሉ ተመልክቼ ነበር፡፡›› ብሎ ንግግሩን ይደመድማል›› Kasa and Kasa ገጽ 207

  ReplyDelete
 13. i read this history on addis negar and i was so amazed that time and when i saw it here i ask my self what kind of generations are we and i have no answer. this generation forget about his past history. D/Daniel i appreciate what you are doing currently i read all of your papers on addis negar

  ReplyDelete
 14. ውድ ዲ. ዳንኤል
  አባቶችን የሚያስታውስ ትውልድ እግዚአሔር ይፍጠር
  የአፄ ቴዎድሮስንም ነብስ ይማር
  ቃለ ህይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 15. ለተከበርከው ዳንኤል ክብረት
  ካንተ የአፄ ቴዎድሮስ ጽሁፍ ቦሃላ በክቡር ፕሬዘዳንቱ የበላይ ጠባቂ የሚመራ መቅደላን የሚያስተዋውቅና አከባቢው ጎብኚዎችን የሚጋብዝ ስራ እንዲሰራ ተመስረተዋል፡፡

  ይህ ነገር ግን የተከሰተው ካንተ ጥቆማ ቦኃላ ነው፡፡ በእርግጠኝነት ብዙዎች ለሃገር ጠቃሚ የሆኑ ጥቆማ አዘል መልዕክቶችህን እንደሚከታተኩት ያስታውቀል ሌሎች ብዙ የማስታውሳቸው አንተ ለሬድዮና ለቲቪ ቃለምልልስ ባደረክ ማግስት ብዙ ጥሩ ነገሮችን መረዳትና ባለስልጣናቱ ሳይቀሩ ሀገር በቀል ነገራዊ ነገሮች መለስ ብሎ ማየቱ መልካም እንደሆነ መስማት ችያለሁ የታየህን ነገሮች እንደትጽፍ የእግዚአብሔር ቸርነት ካንተ ጋር ይሁን በርታ፡፡

  ReplyDelete
 16. It is realy a great piece of work.keep up the good work.

  ReplyDelete
 17. I realy felt very bad after I read your article.when we will apreciate what we have? when we will stund up to keep our hairtage to pass it fro generetion? the things that are need to be improved if contunue as it is I don't what is next may be loss of identity tha is it! for sue it will..... may God give you more strength and wisdom!

  ReplyDelete
 18. i admired or spectacular your wonderful observation!!!!!
  definately it educates what the new generation would be do!!!!!!
  keep it up on!!!!
  እግዚአብሄር ይባርክህ!!!!!!!
  mamethioluv@gmail.com
  from አዲስ አባባ ዩኒቨርስቲ!!!!!!

  ReplyDelete
 19. Ah our mother,EOTC What is happening to you???

  ReplyDelete
 20. Dn Daniel,In this time You are Doing a great job by reminding this Generation his base and history he stands on.So that keep it on.

  ReplyDelete
 21. Hey guys... we all know it's against Christianity to kill oneself for any reason. Don't make him a hero for that. We should not leave aside our principles just because he was good to Christians. We should condemn him for killing himself and praise him for the good things he did. Let's not make a hero out of a man who killed himself against God's wish. Who gave him the right to kill himself first of all? Does God command us "to praise those who kill themselves?" Are our views based on Christianity or our whims and desires?

  ReplyDelete
 22. Dear Daniel, my friend and I really liked this article. Atse Tewodros was a great emperor and I do believe that he was a leader born ahead of his time. Evenif his views and actions towards implementing socio-economic developments for the then society seemed to have contributed to his untimely but graceful death, his legacy has continued to inspire generations. Look, we still have him as our role model...it's NEVER too late to continue to work on for Ethiopia and Ethiopians. Daniel ze Toronto

  ReplyDelete
 23. YOU are doing history. Berta
  thank you

  long live to you

  ReplyDelete
 24. Tewodros is not Hero, He was criminal No Ethiopian Scholar acknowledge him as Hero including Aleqa Gebrehana, Memhr Akalewold,Aleqa Zeneb, who were contemporary, He was criminal, his attempt to UNITE by force was not even supported,we can describe the battle which was the battle of a MAD MAN and strong kingdom to librate their citisens He may have strong commanders but no I dont see his virtue he was criminal - socilally and sinner in the church becouse he killed him self

  but Tsgaye Gebremedihen and the cruel
  Mengistu Haile mariam created him as Hero

  ReplyDelete
 25. hello dn.daniel it rally awesome , yalyenwen neger asyethenal berta.

  ReplyDelete
 26. I APRICIATE YOUR COMMENTS

  ReplyDelete
 27. One of the most magnificent Ethiopian leaders and founder of modern Ethiopia is Emperor Tewodros II.Tewodros’ dream of reigning over a united and strong Ethiopia and over Jerusalem (one of his motto was ‘husband of Ethiopia and fiancée of Jerusalem’

  ReplyDelete
 28. Daniel,I don't have enough words to express my appreciations,the only thing what i could say is MAY GOD BLESS ETHIOPIA,YOU AND YOUR ENTIRE LIFE.WUBE.

  ReplyDelete
 29. betam betam lib yemineka sehuf newe.

  ReplyDelete
 30. አዲሱ ትውልድ ከእርሳቸው የወረሰው ቁንዳላቸውን ብቻ ነው ልበላቸው? ANGET YASDEFAL !!!!

  ReplyDelete