ከአራት ዓመት በላይ አብረን ስናገለግል ፀጉርዋን ተገልጦ አንድ ቀን አይቼው አላውቅም፡፡ ሁልጊዜ በሻሽ እና በነጠላ እንደ ተሸፈነ ነው፡፡ ቀሚሷ መሬት ወርዶ አፈር ይጠርግ ነበር፡፡ አንገቷ ቀና ብሎ የሚሄድ አይመስለኝም፡፡ አብረዋት በሚዘምሩት የመዝሙር ክፍል አባላት ጠባይ፣ ምግባር፣ አለባበስ ሁልጊዜ እንደ ተናደደች፡፡ እንደ ተቆጣች፡፡ እንደ ገሠጸች ትኖር ነበር፡፡ በተለይም ሱሪ የለበሰች ዘማሪት እርሷ ፊት ከታየች አለቀላት፡፡ የነነዌ ሰዎች በይቅርታ የታለፉትን እሳት ልታወርድባት ትደርስ ነበር፡፡ እንኳን ቀለማ ቀለም ቀርቶ ቅባት መቀባት በእርሷ ዘንድ ለገሃነም የሚያደርስ ኃጢአት ነው፡፡ ፀጉር መሠራትና ንጽሕናን መጠበቅማ አይታሰብም፡፡
ይህችን እኅት የማውቃት በአንድ ማኅበር አብረን ስናገለግል ስብሰባ እና የጋራ አገልግሎት እያገናኘን ነው፡፡ የእርሷን ተግሣጽ እና ቁጣ ፈርተው ብዙ እኅቶች የአገልግሎት ክፍሉን ለቅቀዋል፡፡ ሌሎች ደግሞ ለሽምግልና እኛ ጋር መጥተው በስንት ልመና መልሰናቸዋል፡፡ ሌሎቹም የመጣው ይምጣ ብለው ችለዋት አገልግለዋል፡፡
በመካከል ልጅቷ በድንገት ከአልግሎት ክፍሉ ጠፋች፡፡ እኛም ቤቷ ድረስ ሰው ልከን ነበር፡፡ ነገ ዛሬ እያለች አልተመለሰችም፡፡
አንድ ቀን ከቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በዓይነ ሥውራን ማኅበር በኩል ወደ የካቲት ሆስፒታል በሚወስደው የውስጥ ለውስጥ መንገድ በኩል ስጓዝ መልኳን የማውቃት የምትመስል አንዲት ልጅ አየሁ፡፡ አለባበሷ ለየት ያለ ነበር፡፡ የአጭር አጭር ሱሪ ለብሳለች፡፡ ከደረቷ በላይ ያለው አካሏ ልብስ የሚባል አልነበረውም፡፡ ከንፈሯ ቦግ ያለ ቀለም ተቀብቷል፡፡ የጥፍሯ ቀለምም ከሩቁ ይታያል፡፡ የጆሮዋ ጌጥ ባለ ሦስት አንገት አስደርጓታል፡፡
ዓይኔን ማመን አቃተው፡፡ ‹በሕልሜ ነው፣ በእውኔ፣ ወይስ በቴሌቭዥን› አለ ሰውዬው፡፡ ያች ዘማሪውን ሁሉ ሱሪ ለበሳችሁ ብላ ያባረረች፤ ቅባት ተቀባችሁ ብላ አትዘምሩም ያለች፤ ቀሚሳችሁ አጠረ ብላ ልብስ ያስቀየረች፡፡ ጥፍራችሁ ረዘመ፣ ፀጉራችሁ ተተኮሰ ስትል የነበረች ልጅ እንደዚህ ሆነች? ማረጋገጥ ፈለግኩና ከምሄድበት መኪና ወርጄ ከሰው ጋር ቆማ ወደምታወራበት ቦታ ተሻገርኩ፡፡ ሰላምም አልኳት፡፡ መቼም ባታየኝ በወደደች፡፡
ለመሆኑ መንፈሳዊነት ምንድን ነው፡፡ ረዥም ቀሚስ መልበስ ነው? ፀጉርን በአሮጌ ሻሽ መሸፈን ነው? ገላን ያለመታጠብ ነው? አንገትን መድፋት ብቻ ነው? ቀስ ብሎ መናገር ነው? ኋላ ቀርነት ነው? አይመስለኝም፡፡ ቴሌቭዥን አለማየት፣ኢሜይል አለመጠቀም ነው? ከጸሎት መጻሕፍት በቀር ሌላ ነገር አለማንበብ ነው?
መንፈሳዊነትኮ በመንፈስ ቅዱስ መመራት ነው፡፡ ራስን ማሸነፍ ነው፡፡ አእምሮን እና ልቡናን ቀና እና ሰላማዊ ማድረግ ነው፡፡ ለመሆኑ የውስጡ መንፈሳዊነት አይደለም እንዴ ወደላይ መገለጥ ያለበት፡፡ ስለ ሐዋርያት ስንናገርኮ የነፍሳቸው ቅድስና ለሥጋቸው፣ የሥጋቸው ቅድስና ለልብሳቸው፣ የልብሳቸው ቅድስና ደግሞ ለጥላቸው ተረፈ ነው የምንለው፡፡ መንፈሳዊነቱ ከውስጥ ወደ ውጭ እንጂ ከውጭ ወደ ውስጥ አልነበረም፡፡
አንዳንድ ጊዜ «መንፈሳዊነት» ከ «መንፈሳይነት» ጋር እየተመሳሰለ የምንቸገር ይመስለኛል፡፡ ዲያቆን ኤፍሬም እሸቴ ነው ይህችን ቃል ያመጣት፡፡ ከሁለት ቃላት «መንፈሳዊ» እና «መሳይ» ከሚሉ ቃላት ቆራርጦ «መንፈሳይ» የሚል ቃል ፈጠረ፡፡ ትርጉሙም «መንፈሳዊ መሳይ» ማለት ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች መንፈሳውያን ይመስላሉ እንጂ አይደሉም፡፡
አባ ኤፍሬም ሶርያዊ ባስልዮስን ለማየት በሄደ ጊዜ ስለ ክብረ ወንጌል ሲል ከላዩ የወርቅ ልብስ ለብሶ ፣ የወርቅ ወንበር ዘርግቶ፣ የወርቅ ጫማ ተጫምቶ በጉባኤው ላይ ባየው ጊዜ «ደገኛ መምህር የተባለው ባስልዮስ ይኼ ነውን?» ብሎ ነበር፡፡ በኋላ ግን ተአምራቱን አይቶ አድንቆታል፡፡ አንዳንድ ጊዜ የውጭ ገጽታ ውስጥን ሊገልጥም ላይገልጥም ይችላልና፡፡
ልክ ነው ክርስቲያናዊ አነጋገር፣ አለባበስ፣ አረማመድ፣ ገጽታ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ማለት መንፈሳዊነት ጅልነት፣ ከርፋፋነት፣ ኋላ ቀርነት ወይንም ደግሞ፣ ንጽሕናን አለመጠበቅ ማለት ግን አይደለም፡፡ በመንፈሳዊነታቸው የሚደነቁት የቤተ ክርስቲያን ከዋክብት እነ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ፣ባስልዮስ ዘቂሳርያ በዘመኑ በነበረው የግሪክ ፍልስፍና እና ዕውቀት የበለጸጉ ነገር ግን ዕውቀታቸውን እና ሥልጣኔያቸውን በወንጌል የቃኙ ነበሩ፡፡
ብዙዎቻችን ከውስጥ ለሚመነጩ ትእግሥትን፣ ደግነትን፣ ታዛዥነትን፣ ትኅትናን፣ አርቆ ማሰብን፣ ኀዘኔታን፣ ፍቅርን፣ ትጋትን ለመሰሉ ነገሮች ትኩረት አንሰጥም፡፡ ከዚያ ይልቅ ተዋንያን ሊያደርጉት የሚችሉትን የውጭ ገጽታን ብቻ በማየት መመዘን እንመርጣለን፡፡
እውነተኛው መንፈሳዊነት ግን ከመንፈሳይነት መለየት አለበት፡፡ መንፈሳይ ሰዎች የራሳቸው መለያ ባሕርያት አሏቸው፡፡
እነዚህ ሰዎች ከውስጣዊ መንፈሳዊነት ይልቅ ለውጫዊ ነገሮች ትልቅ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ውስጣዊ ማንነታቸውን ለመሸፈን ሲሉ ሕግ ከሚፈቅደው በላይ ለውጫዊ ገጽታ ይጨነቃሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ስለ የፀጉር አያያዝ የራስዋ ባህል አላት፡፡ እነርሱ ግን ፀጉር መታጠብን ኃጢአት ያደርጉታል፡፡ ክርስቲያኖች የሚለብሱት ልብስ ራሳቸውን የማያጋልጥ እንዲሆን ትመክራለች፡፡ እነርሱ ግን ልብስ ሁሉ መሬት ካልጠረገ ይላሉ፡፡ ያደፈ በመልበስ፣ የአእምሮ ችግር ያለባቸው ይመስል እጅግ ቀሰስ ብለው በመናገር፣ ሰው መሆናቸውን ረስተው ምንም ነገር እንደማይበሉ እና እንደማይጠጡ በማሳመን፣ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ በመልበስ፣ ሰንሰለት በመታጠቅ፣ ትልልቅ መቁጠርያ እጃቸው ላይ በመጠቅለል፡፡ ይበልጥ መንፈሳዊ ሆነው መታየት ይፈልጋሉ፡፡
ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው በዱርዬ እና በሴተኛ አዳሪዎች ዘንድ ያለውን ያህል ፈሪሃ እግዚአብሔር በአገልጋዮች ዘንድ የለም ይል ነበር፡፡ አንዳንዶች በአገልግሎት እየበረቱ ሲሄዱ ከመንፈሳዊነት ወደ መንፈሳይነት ስለሚለወጡ፡፡
ጋሽ ግርማ ከበደ ከሚያስተምረው ነገር የማልረሳው ቃል አለ፡፡ «ሰው የሚጠላውን ኃጢ አት ደጋግሞ ይሠራዋል» ይላል፡፡ ለምንድን ነው ደጋግሞ ይሠራዋል ያለው? እኔ እንደ ተረዳሁት መጀመርያውኑ ይህ ሰው ውስጡ ያላመነበትን እና ሊያደርገው የማይፈ ልገውን ነገር ነው ለማስመሰል ሲል እያወራ ያለው፡፡ ስለዚህም በውስጡ ያንን የጠላውን ነገር ላለማድረግ መንፈሳዊ ተጋድሎ ስለማያደርግ ደጋግሞ ሲሠራው ይገኛል፡፡
እንዲያውም አንዳንዶች መንፈሳያን ስለ አንድ ሰው መንፈሳዊነት ደጋግመው በጥላቻ ወይንም በንቀት፣ ወይንም ደግሞ በመመጻደቅ የሚያወሩ ከሆነ ያንጊዜ አንዳች ነገር ተረዱ፡፡ ሳያስቡት እየተናገሩ ያሉት ስለ ራሳቸው ነው፡፡ መንፈሳውያን ሰዎች ስለሌሎች ውድቀት ሲያነሡ ከርኅራኄ እና ከኀዘኔታ ጋር ነው፡፡ የደስታ ስሜት አይሰማቸውም፡፡ እንደ ጀብዱም አይቆጥሩትም፡፡ ለዚህም ነው በቅዳሴ አትናቴዎስ ሊቁ ስለ አዳምና ሔዋን አንሥቶ «እኛስ እናንተን ልንወቅሳችሁ አንችልም» በማለት የተናገረው፡፡
መንፈሳውያን ይነበባሉ፤መንፈሳያን ግን ይታያሉ፡፡ መንፈሳውያን ይቀመሳሉ፣ መንፈሳያን ግን ይላሳሉ፡፡ መንፈሳውያን ያዳምጣሉ፤ መንፈሳያን ግን ይለፈልፋሉ፡፡ መንፈሳውያን ያስተውላሉ፤ መንፈሳያን ግን ይቸኩላሉ፤ መንፈሳውያን ያጠግባሉ፣ መንፈሳያን ግን ያቁለጨልጫሉ፡፡ መንፈሳውያን ይመዝናሉ፤ መንፈሳያን ግን ያፍሳሉ፡፡ መንፈሳውያን ያርማሉ፤ መንፈሳያን ግን ይተቻሉ፡፡
መንፈሳውያን ጠላቶቻቸውን ወዳጆቻቸው ለማድረግ አንድ ሺ ዕድል ይሰጣሉ፤ መንፈሳያን ግን ወዳጆቻቸውን ጠላቶቻቸው ለማድረግ አንድ ሺ በር ይከፍታሉ፡፡ መንፈሳውያን ይጾማሉ፣ መንፈሳያን ይራባሉ፤ መንፈሳውያን ይጸልያሉ፣ መንፈሳያን ግን ይናገራሉ/ያነባሉ፡፡ መንፈሳውያን ሱባኤ ይይዛሉ፣ መንፈሳያን ግን ስለ ሱባኤያቸው ያወራሉ፡፡ መንፈሳውያን ይሰጣሉ፣ መንፈሳያን ግን ሲሰጡ ያሳያሉ፡፡ መንፈሳውያን ቃለ እግዚአብሔርን ያስተምራሉ፣ መንፈሳያን ግን በራሳቸው ቃላት ይጠበባሉ፤
መንፈሳውያን ወደ ውስጥ፣ መንፈሳያን ወደ ውጭ ያያሉ፡፡ መንፈሳውያን የነገን፣ መንፈሳያን የዛሬን ያያሉ፡፡ መንፈሳውያን ምክንያቱን፣ መንፈሳያን ድርጊቱን ያያሉ፡፡ መንፈሳውያን ራሳቸውን፣ መንፈሳያን ሌላውን ያያሉ፡፡
መንፈሳውያን ከመፍረዳቸው በፊት ይመክራሉ፤ መንፈሳያን ከፈረዱ በኋላ ይመክራሉ፡፡ መንፈሳውያን ዘጠኝ ጊዜ ለክተው አንድ ጊዜ ይሰፋሉ፣ መንፈሳያን ግን ዘጠኝ ጊዜ ሰፍተው አንድ ጊዜ ይለካሉ፡፡ መንፈሳውያን ከመናገራቸው በፊት ያስባሉ፣ መንፈሳያን ከተናገሩ በኋላ ያስባሉ፡፡ መንፈሳውያን ይወስናሉ፣ መንፈሳያን አስተያየት ያበዛሉ፡፡ መንፈሳውያን ሰው እንዳይሞት በችግሩ ጊዜ ይረዳሉ፣ መንፈሳያን ግን ሰው ሲሞት የልቅሶ ትርኢት ያሳያሉ፡፡ መንፈሳውያን ስለ ሌሎች በጎ መናገርን ያዘወትራሉ፣ መንፈሳያን ስለ ራሳቸው በጎ መናገርን ይፈልጋሉ፡፡ መንፈሳያን ነጭ እና ጥቁር ብቻ ያያሉ፣ መንፈሳውያን ግን ግራጫንም ጨምረው ይመለከታሉ፡፡
መንፈሳዊ ሰው አንድ ሰው ነው፡፡ መንፈሳይ ሰው ግን ሁለት ሰው ነው፡፡ ውጩ ሌላ ውስጡ ደግሞ ሌላ ነው፡፡ ገና ያልተሸነፈ፣ እንዲያውም እየገነገነ እና እየገነተረ የሚሄድ ክፉ ጠባይ አለባቸው፡፡ አይጋደሉትም፡፡ አይጸየፉትም፡፡ ሊያሸንፉት አይፈልጉም፡፡ አይቃወሙትም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እንደ ጥሩ ተዋናይ በአለባበስ፣ በአነጋገር፣ በአረማመድ፣ በመቅለስለስ፣ በመሸፋፈን እና ለሰው መስለው በመታየት ሊገልጡት የሚፈልጉት ሌላ ማንነት ደግሞ አላቸው፡፡ ይህ የውስጥ ማንነት አንድ ቀን ያሸንፍና እንደ ዴማስ ያስኮበልላቸዋል፡፡ ያን ጊዜ በሰው ይፈርዱ የነበሩትን ነገር ሁሉ አብዝተው ያደርጉታል፡፡ ወጣ ወጣ እና እንደ ሸንበቆ ተንከባለለ እንደ ሙቀጫ የተባለው ይደርስባቸዋል፡፡
አንዳንዴ መንፈሳይነት ሕይወት ሳይሆን በሽታ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ያውም የአእምሮ መዛባት/ mental disorder/፡፡ በሁለት ማንነቶች መካከል እየተምታቱ መኖር፡፡ መንፈሳዊ ሰው ኃጢአት ቢሠራ እንኳን ንስሐ ይገባበታል፡፡ ያርመዋል፡፡ ይጋደልበታል፡፡ ኃጢአቱን በመሸፈን እና በማስመሰል ሳይሆን በመጋደል እና በማስወገድ ያምናል፡፡ መንፈሳይ ሰው ግን ሌሎች እንዳያዩት እንጂ እግዚአብሔር እንዳያየው አይጨነቅም፡፡
አሁን እኛ እስኪ ራሳችንን እንየው
መንፈሳዊ ነን ወይስ መንፈሳይ?
This is really tuchy! Let God Help Us to be"Menfesawi"
ReplyDeleteጽሑፉን ማንበብ እንደ ጀመርኩ እኔም እንዳቅሜ የማውቃቸውን መንፈሳዮች ማሰብ ጀመርኩ፡፡ እየቀጠለ ሲመጣ የመንፈሳዊና መንፈሳይ ንጽጽሩ መሰጠኝ፡፡ ወደ ማለቂያው ይሄ ዲያቆን ለካንስ ስለ እኔ ነውና የሚናገር ያለ አስባለኝ፡፡ አወይ መንፈሳይነቴ! ቃለ ህይወት ያሰማለን መምህር፡፡
ReplyDeleteዳዊት
Dn,Dani.Qalehiwot Yasemalin
ReplyDeleteAbetu Amlake atitalegn,be mengesti asibegn/asiben
Weye gud
ReplyDeleteThanks Dani, really impressed me to look deep into my 'sprituality' O my God who am I? Stay blessed Dani
ReplyDeleteI am very touched too.
ReplyDeletebut it looks like i am very menfesai. I need to be menfesawi instead. I also think that i am commenting on this article because to look like menfesawi. GOD help me to be menfesawi.
መንፈሳይ አለመሆኔን በምን ላረጋግጥ...ተሸነፍኩኝ...ምነው ድያቆን ያን ያህል ባትገድለን ...ትልቅ ትምህርት ነው.ቃለ ህይወት ያሰማልን.
ReplyDeleteThank you for opening my eyes. There is really a distinction between the words. I sincerely believe you just gave us an eye glass to look closely at everyone around us. I will start from me, of course!!!
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን ዲ.ን ዳንኤል በትክክል ገልጸህ ስለሳልከኝ
ReplyDeleteእግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን አሜን
ተፈበ
kale hiwot yasemalin
ReplyDeleteDn. Danial
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማለን መምህር፡፡
God be with you and out Tewhedo church
Alexandria VA U.S.A.
May God bless you abundantly!!!! I can only say thank you!!! You made me realize who I am, but that is not enough. My external "someone" always blame my inside "somebody" for what went wrong in my spiritual life yet. I do now know when they are going to stop dragging me to different directions and act as one person. I told myself bizilion times to stop dwelling and start acting!!! But... I just hope that, that day will come before the two sides of me are separated forever!!!
ReplyDeleteForgive me God, I am one of መንፈሳይ. God Bless you Dani
ReplyDeleteእፁብ ድንቅ ጽሁፍ። ዎዪልኝ ለኔ ለመንፈሳዩ!
ReplyDeleteNow I have found my self to be 'MENFESAY'. Please God help me to be 'MENFESAWI' AMEN!
ReplyDeletethank u it help me to see myself.may `God help me to be menfesawi
ReplyDeleteበመሰረቱ ቅድስት ቤተክርስቲያናችን አለባበስን ጨምሮ የራሷ የሆነ አስተምህሮ እንዳላት ግልጽ ነው፡፡ ያንን የሚተገብሩትን ‘አካባጅ’ ልንላቸው አይገባም፡፡ ወደ መንፈሳዊ እና መንፈሳይ ጉዳይ ስንመጣ ግን እጅግ ትኩረት ሊደረግበት የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ ዳንኤል እንዳለው ትልቅ በሽታም ነው፤ አንዳንድ ጊዜ ሳስበው ይህ በሽታ የተጠናወተኝ ይመሰለኛል፡፡ መንፈሳዊ ነገር ስንሰራ ለማን እና ለምን እንደመንሰራው አንዳንዴ በትክክል የገባን አይመስለኝም፡፡ ብዙ ጊዜ ወደ ውጭ /ወደ ተመልካች/ እንመለከታለን፡፡
ReplyDelete“ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው በዱርዬ እና በሴተኛ አዳሪዎች ዘንድ ያለውን ያህል ፈሪሃ እግዚአብሔር በአገልጋዮች ዘንድ የለም ይል ነበር፡፡” ይህ የሚያስደነግጥ አልፎ አልፎ ግን የሚታይ እውነታ ነው፤ብዙ ጊዜ በመላመድና ከእኔ በላይ ላሳር በማለት እታች ወረደው የሚገኙ አገልጋዮች አይጠፉም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እንደነ አባ ሕርያቆስ ያሉ ትሁት አገልጋዮችም ምን አይነት ጸጋ እንዳገኙ እናውቃለን፡፡
በአጠቃላይ ይህ የፈሪሳውያን ጸባይ አንዳንዶቻችን ላይ ሰልጥኖ ሲያጠቃን ይታያል፡፡ አንድ ቦታ ያነበብኩትን እስቲ ቀንጨብ አድርጌ ልጻፈው፡፡ “ … ነገር ግን ከፈሪሳውያን የማይሻሉ ኦርቶዶክሳውያን አባቶችም (አገልጋዮች) አሉ :: ሳይጾሙ ጹሙ የሚሉ፣ ሳይሰግዱ ስገዱ የሚሉ፣ ሳይረዱ እርዱ የሚሉ .....ሞልተዋል :: የዛኑ ያህል ደግሞ እዩኝ እዩኝ የማይሉ ፣ ቤተክህነት በሚሰጣቸው ደሞዝ ጎዳና ተዳዳሪዎችን የሚያሳድጉ : ለሊት ስለወገናቸው ሲያለቅሱ ፣ መልአክ በህልማቸው ሲያናግሩ አይተው ቀን እንደተራ ሰው የሚንከራተቱ አባቶችም አሉ :: እነዚህን ግን ማንም አያውቃቸውም ምክንያቱም እዩኝ እዩኝ አይሉም :: እነዚህን ሁለት አይነት ሰዎች መለየት አንዳንዴ ቀላል ነው :: ሌላ ጊዜ ደግሞ ይከብዳል ::”
ለማንኛውም አንዳንዶቻችን ከተጠናወተን ከዚህ ከባድ በሽታ በቸርነቱ ይገላግለን፡፡ ዲያቆን ዳንኤል ወሳኝ የሆኑ ነጥቦችን በማንሳት መስተዋት ስለሆነከን እናመሰግናለን፤ እኛም በመስታዋቱ ተመልክተን ጉድፋችንን እንድናርም እንጂ መሰተዋት ሰባሪ እንዳንሆን ይርዳን፡፡
"Most truths are so naked that people feel sorry for them and cover them up, at least a little bit."
Let us try our best to avoid such errors rather than cover them up!
How can I be መንፈሳዊ ሰው?
ReplyDeleteቃለ ሕይወት ያሰማልን ዲ.ን ዳንኤል
ውድ ዲን. ዳንኤል
ReplyDeleteጽሑፍህን ሳነበው ራሴን ወደ ውስጥ አየሁት፡፡ ሌላው ቀርቶ ይህችን አስተያየት እንኩዋን ለመስጠት እኔነቴን እያሰብኩ ወደኋላ በምናብ ሄድኩ፡፡ ቃሉ አስተማሪ ነውና ቃለ-ሕይወት ያሰማልን እላለሁ፡፡
አይ ዳኒ! ቆይ እስቲ መንፈሳይነቴን እንዴት አወቅህ; በእውነት እኔነቴን ባንተ መስታውትነት አየሁት፤፤ እግዚአብሄር ለንስሀ ያብቃኝ!
ReplyDeleteአ
እጅግ ግሩም ምክር ነው! ቃለ ሕይወት ያሰማልን። መንፈሳይነት(ግብዝነት)ብዙ ክርስቲያኖች መንፈሳዊነትን በትክክል ካለመረዳት የተነሳ የሚመጣ ችግር ነው። በ1980ዎቹ የነበረው እጅግ ጠንካራ የባህታዊያን እንቅስቃሴ እንዱ ምክንያት እንደሆነ አምናለሁ። በጊዜው የተነሱ ባህታዊያን ነን ባዮች ምንም እንኳን ለብዙዎች ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ምክንያት ቢሆኑም ዳሩ ግን ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ክርስትናን ከገዳማዊ ሕይወት ለይተው እንዳይመለከቱ አድርገዋል። ይህ ደግሞ ብህትዉናን በከተማ ውስጥ ወደ መሞከር የሚያመራ ሆናል። ሕይወቱ ለተፈቀደላቸው በከተማ የጀመሩት ተጠናክሮ ወደ ፍጹም ገዳማዊ ሕይወት መርቷቸው በየገዳማቱ እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው መንፈሳዊ ፍሬ እንዲያፈሩ አድርጓቸዋል። ይህ ግን ለሁሉም አይደለም። ይህን ሳስብ ሁል ጊዜ ከአእምሮዬ የማይጠፋው በአጥቢያችን የነበረ አንድ ወንድም ነው። ይህ ወንድም በጾም ዕለት ፀሐይ ሳትጠልቅ አይመገብም ሁሌ የሚታየው ሲሰግድ ነው። በተጨማሪም በመኪና እንኳን በአንድ ቀን የማደረስባቸውን ገዳማትን(እስከ 450ኪ.ሜ.)ከአንድ ወር በላይ ጉዞ በእግሩ እየተጓዘ ይሳለም ነበር። ይህ ሁሉ ቀጣይነት ቢኖረው መልካም ነበር። ነገር ግን የሚያሳዝነው ከጥቂት ዓመታት በኋላ እንዲያ ይተጋ የነበረው ሰው ሕይወቱ ተመሰቃቅሎ ከካቲካላ ቤት የማይጠፋ ሆኗል። ለዚህ ሁሉ የዳረገው መንፈሳዊነትን በአግባቡ አለመረዳቱ ነው። መድኃኒታችን ጸሐፍት ፈሪሳዊያንን ይገስፅ የነበረው የወጪቱን ዉጭዉን አጥርተው ውስጡን ስለሚተውት ነበር(ሉቃ 11፡41)። ከልብ የመነጨ ፍቅር ትህትና የዋህነትና በጎነት ነው አምላካችንን የሚያስደስተው። ስለዚህም ወንድማችን እንደመከረን መንፈሳዊያን እንሁን።
ReplyDeleteDear Dn. Dani,
ReplyDeleteMay God keep you with abundant wisdom and talent of advising us in every way possible from every corner of our life.
Again I would say; God Bless You with long service age and wisdom.
ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዲ/ን ዳንኤል፡፡አምላክ አስተዋይ ልቦና ያድለን፡፡
ReplyDeleteDn Daniel,
ReplyDeleteI thanks God to preach us through you. I am Menfesi, but I believe one day I will be menfesaw, please pray for me. continou your hard work...
Kale-hiwot yasemalen Dn. Daniel! Mastewalun yadelen.Amen!
ReplyDelete"ጋሽ ግርማ ከበደ ከሚያስተምረው ነገር የማልረሳው ቃል አለ፡፡ «ሰው የሚጠላውን ኃጢ አት ደጋግሞ ይሠራዋል» ይላል፡፡ ለምንድን ነው ደጋግሞ ይሠራዋል ያለው? እኔ እንደ ተረዳሁት መጀመርያውኑ ይህ ሰው ውስጡ ያላመነበትን እና ሊያደርገው የማይፈ ልገውን ነገር ነው ለማስመሰል ሲል እያወራ ያለው፡፡ ስለዚህም በውስጡ ያንን የጠላውን ነገር ላለማድረግ መንፈሳዊ ተጋድሎ ስለማያደርግ ደጋግሞ ሲሠራው ይገኛል፡፡ " This is very important for me.
ReplyDeleteBless you Daniel
i am menfesi , i always pray to be menfesaw.
ReplyDeleteያች ልጅ ያንን አይነት መንፈሳይነት ከየት ያመጣችው ይመስልሃል? እኔ በበኩሌ እሱዋን ጥፋተኛ አላደርግም። ይህች ልጅ ከእምነትዋ አስቀድሞ ስርኣት ተሰብኮላታል። እድሜ ሳይማሩ አስተማሪ ለሆኑ ብዙም ያልበሰሉ መምህራን። ይህች በመጀመሪያ የክርስትና ዓላማ፣ የክርስቶስ ፍቅር አስቀድሞ ተሰብኮላት ቢሆን ኖሮ እንደዚያ ባልሆነች ነበር። ከውጭ የምታንጸባርቀው ነገር ከእምነትና የክርስቶስን ልዩ ፍቅር ከመረዳት ይሆን ነበር። የክርስቶስን ፍቅር ሰምተን በማመመን ያገኘነው የመንፈስ ቅዱስ የጸጋ ስጦታ ደግሞ ሰዎችን ሳይሆን እራሳችንን እንዳንመለከት ያደርገናል። ለመልእክቱ ቃለ ህይወት ያሰማልን።
ReplyDeleteEgna legna(lerasachin) keminasibew yilik ESU(God) legna yemiasbew yibelitalna Esu bemelekotu yitebiken, Amen.
ReplyDeleteGod bless you,Dn.
Gizat.
thanks Dani
ReplyDeleteአቤቱ ጌታዬ ሆይ አሁን መንፈሳይ ነኝና፡ ሰውን ሳይሆን አንትን ፈርቼ እንደዴማስ ሳልጠፋ መንፈሳዊ ሰው አድርገኝ ፡፡ ዲ/ን ዳኒ ቃለ ህይወትን የሰማልን ! የበለጠ እና በዙ ነገር እንጠብቃለን፡፡ቸር ያሰማህ!
ReplyDeleteመልካም እይታ ነው ለብዙዎቻችን መስታወት የሆነ ጽሑፍ ነው
ReplyDeleteሰባኪያንም መሰበክ አለባቸው ለእነርሱም ጽሑፍ/ስብከት ቢዘጋጅ መላካም ነው
I like it.kale hiwet yasmaln,egziabher bandm belelam ynageral.To day he told me .TANK YOU
ReplyDeleteቃለ ህይወት ያሰማለን!!!!
ReplyDeleteዴርቶጋዳ
ReplyDeleteአንዳንድ ጊዜ ለምን አስመሳይ ሆንኩ ወይም ‹‹ መንፈሳይ ›› ሆንኩ ብዬ አስብና መልሱን ‹‹እኔ ምን ላድርግ ታዲያ›› ብዬ እተወዋለሁ ምክንያቱም ህብረተሰባችን ያልሆንከውን ሆነህ እንድትንቀሳቀስ በጣም ተጽዕኖ ያደርግብሃል፡፡ እስቲ አስበው ከታላቅ ወንድምህ ጀምረህ ጉልበተኛ እናት እና አባትህን አስባቸው! እናትህ እንደትሆን የምትፈልገው ነገር አለ አባትህ እንድትሆን የሚፈልገው ነገር አለ! ታላቅ ወንድም እና የሰፈር ሰው ደግሞ የሚመኝልህ ነገር አለ! ከልጅነትህ ጀምሮ ደግሞ ስትመለከት ያደከው ነገር አለ! በሌላው ላይ ለማላከክ እየፈለኩኝ አይደለም ግን እነኝህ ለረጅም ጊዜ የቆዩ የስነልቦና ተጽዕኖዎች ሲያድጉብህ እና ስትላመዳቸው ራሳቸውን የቻሉ ማንነት ይሆናሉ፡፡ ይህ ደግሞ በሃይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ ብቻ አይደለም በሀገር ጉዳይ እራሱ በጣም በብዙ አስመሳይ እንድትሆን ያደርግሃል ፡፡ ስለዚህ መሰረታዊ የሆነ እና ተገቢውን የእድገት ደረጃ የጠበቀ ለውጥ ያስፈልጋል ባይ ነኝ ፡፡አሊያ ግን ልክ እንደ ሀገራችን የትምህርት ፖሊሲ አስራሁለት አመት ሙሉ ቅጥረኛ እንድትሆን ከተማርክ ወይም ‹‹ከተደረግክ›› በኋላ አሥራ ሦስተኛ ክፍል ላይ ስትደርስ ‹‹ሥራ ፈጣሪ ›› ሁን እንደተባለው ይሆናል፡፡
በነገራችን ላይ አስመሳይ ሃይማኖተኞችን ‹‹መንፈሳይ›› ካልካቸው አስመሳይ እና በሀገር የሚቀልዱ ሆዳም ‹‹ቦለጢቀኞችን›› ደግሞ ምን ትላቸዋለህ?
ለማንኛውም ሰው ክፉም ሆነ ደግ እራሱን ሆኖ የሆነውን ሆኖ /እራሱን/ መኖር እንዳለበት እና እንደሚጠቅመው ተገንዝብያለሁ፡፡
lhulachinem lib yisten new yemibalew betam tiru tsihif neber amesginalehu betam yemilewitegn yimesilegnal egziabher lhulachinem leb yisiten amen.
ReplyDeleteAyAL
ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ በቅርቡ በወጣ አንድ መጽሔት ላይ በሰጠው ቃለ ምልልስ የስብከት ዓላማ ሦስት ነው፤ ያላመነውን ማሳመን፤ ያመነውን ማጽናት፤ የጸናውን ማንጻት ብሎ ነበር፡፡ በዚህ አጭር ስብከት ዲያቆን ዳንኤል ለረዥም ዘመን በቤተክርስቲያን ትምህርት አምነን፤ በተማርነው ትምህርት ጸንተን እንኖራለን የምንለውን የሚያነጻ ትምህርት አስተምሮናልና ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡
ReplyDeleteWey Mekeraye? Endet yehon Yemekeyerew??????????
ReplyDeleteKale Hiwot Yasemalen
ራሴን አየሁት ቃኘሁትም . . .ሲበዛ መንፈሳይ ሆኖ አገኝሁት!
ReplyDelete~ሰ.ሚ~
ka tekite satate bafet ya menfaswent sera lesara wetawna laneme ya menfesawent sera serch mataw bey dest tesgmage.gine destaye bezume sayzelke yehinen tsihufe banababiku geza destaye hulu tefa wayew edela mech yehone ya menfeswent sera ya mesarw.
ReplyDelete"amelk hoy alemamenae erdaw endale" "ename menfasintaen erda beye amelkae endamerdage aseba ebakihe amelke manfsiye netane erdaw menfaswem lemhone abekge."
daniel kale hiwate yasemalen
"ጋሽ ግርማ ከበደ ከሚያስተምረው ነገር የማልረሳው ቃል አለ፡፡ «ሰው የሚጠላውን ኃጢ አት ደጋግሞ ይሠራዋል» ይላል፡፡ ለምንድን ነው ደጋግሞ ይሠራዋል ያለው? እኔ እንደ ተረዳሁት መጀመርያውኑ ይህ ሰው ውስጡ ያላመነበትን እና ሊያደርገው የማይፈ ልገውን ነገር ነው ለማስመሰል ሲል እያወራ ያለው፡፡ ስለዚህም በውስጡ ያንን የጠላውን ነገር ላለማድረግ መንፈሳዊ ተጋድሎ ስለማያደርግ ደጋግሞ ሲሠራው ይገኛል፡፡" This is very typical of me. Abetu Erdagne kezih endiwota.
ReplyDeleteThank you very much for your messag.But we can't complain that women b/c we get many reason for that, what she did at the end,allmost all of us we been like her.I want write in amharic many things but I can't write for the time being that is my probelm.Thanks, God belsse you!!!
ReplyDeleteThank u my dear
ReplyDeleteBetam Asetemary Newe Kale Hiwot Yasemalene
ReplyDeleteohhhhhhhhhhhhhhh First of oll thanks to GOD
ReplyDeleteb/c he give to us Very good brothers just like that D/n Dani'el Kibret.
Dani "Kale Hiywot Yasemalin, Mengiste semayat Yawarsilin, Tsega Menefes kidus Yalabsiln"
God give to you long life like that Matusalah
ኦ ፍቁርየ ዲ. ዳንኤል።በአማን አንተ መምህር ዘተዋህዶ.
ReplyDeleteአልብየ ቃላት ዘእንበለ እብል ቃለ ህይወት ያስምአከ.
ለዚአየ ዘተጽሕፈ ጦማር.
እግዚእየ ኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ 'መንፈሳይ'.
ርድአኒ እስመ እትወለጥ ሀበ መንፈሳዊ.
እሴብሀከ ዳግመ.
ባንተ ጽሁፍ ውስጥ ራሴን መንፈሳይ ሆኜ አየሁት ዳንኤል እግዚአብሔር ረጅም የአገልግሎት ዘመን ያድልህ እንዲዚህ አይነት ጽሁፎችህ አብዝተው ይቀጥሉ
ReplyDelete«ፊደል ይገድላል መንፈስ ግን ህይወትን ይሰጣል» ቃለ ህይወት ያሰማልን እግዚአብሔር ፍጻሜያችንን ያሳምርልን
ReplyDeleteKale hiwot yasemalen ....
ReplyDeleteI got myself.I knew myself as I am too hypocrat. Really you broke my heart through this life giver taught.How much I am 'asmesay'? This type of psychological taughts are impressive for this generetion like that of St. Peter, St.John the Golden mouth and megabi Hadis Eshetu.
ReplyDeleteKale hiwot yasemalin. Keep it up!
lekas menfesay negn!
ReplyDeleteደጀ ሰላም የመንፈሳውያን ብቻ ብትሆን ኖሮ ምፅአት በምልክት አይምጣም ነበር::
ReplyDeleteMekuanint Taye
minneapolis
thanks dear Dn.Daniel, may God bless you forever. you are gifted man, you have so many valuable things that u didn't shared us, i need to hear more from you and may God help us to live on God's way in all our life
ReplyDeleteእኔ
ReplyDeleteበጣም አመሰግንሀለዉ!
ዲ.ን.ዳንኤል ክብረት፣ በዚህ መንፈሳዊ ወይስ መንፈሳይ? በሚለዉ ጥያቄያዊ ፅሁፍ፣ እኔን መንፈሳዊ ሳይሆን መንፈሳይ ሆኜ አግኝቸዋለሁ፡፡ ቃለ ሕይወት ያሰማልን ዲ.ን ዳንኤል በትክክል ገልጸህ ስለሳልከኝ
እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን አሜን!
Oh I am so late to say nothing but Kalehiwot yasemalin I know Dn.Danel u can teach us more than this,u expressed what was/is happening.This is what we want "not around the Bush".
ReplyDeleteLong live!!Actually min yadergal edme endih kalserubet.Any way I got my home bertalin Dani!!
ቃለሕይወትን ያሰማልን ዲ.ዳንኤል መንፈሳዊ እንድንሆን አምላከ ቅዱሳን ይርዳን
ReplyDeleteዲ.ዳንኤል
ReplyDeleteመንፈሳይ አለመሆኔን ለማረጋገጥ ተቸገርኩ ድንቅ ጽሁፍ ነው፡፡
ቃለ ህይወት ያሰማልን
"አረንጓዴ ቢጫ ቀይ በመልበስ፣ ሰንሰለት በመታጠቅ፣ ትልልቅ መቁጠርያ እጃቸው ላይ በመጠቅለል"
ReplyDeleteከዚህ ቃል በስተቀር ተቀብዬዋለሁ ተሁት መምሰል እራስንም ከአስፈላጊው በላይ ዝቅ ማድረግም መሆኑ ሊታሰብበት ይገባል አስተያየት ሰጪዎች!
ቀለ ህይወት ያሰማልን
መንግስተ ሰማይ ያዋርስልን
እኛንም መንፈሳውያን እንድንሆን ቸሩ አባታችን ይርዳን
GOD BLESS U TEACHER!
ReplyDeleteMAY GOD HELP US ALL TO
LIVE LIKE MENFESAWI!
Tena Yistilin Dn. Daniel. am so happy to get ur articles at ur website. when addis Neger was..., i was so frustrated. it was especially cauz of missing ur articles. yet God show u the other way. that s why we should not refuse all the products of modern technology. Dear Dn, why don't u publish all ur articles on book. am sure, u ll be successful. Egziabher Aylewtih. Temesgen Tadele
ReplyDeletekale hiwot yasemaline ene kestafkew neger yetelye neger yelegnem.Menfesay
ReplyDeleteBelieve me I am reading 3 times.Really I am Menefesi.Dn.Daniel we are waiting many things from u especially in spiritual life. Let God be with you!!
ReplyDeletekemesber befit beteseberw memar yishal
ReplyDeleteDear Dani?
ReplyDeleteKale Hiwot yasemalen.
But the articles entitled "Liberalism/Lezebtegninet" and "Menfesawi weyis Menfesay" have been confused to me.(May be) either one or the other is not uptodate/wektawi issue?
Mistrun yigletleh/yigletlesh belegn.
ራስን የሚያሳይ የዕምነት መነፀር ነው፡፡
ReplyDeleteሁል ግዜ ግን የሚገርመኝ ነገር አለ ሁላችንም ከትንሽ እስከ ትልቅ ድረስ ያለነው ሰዎች ራሳችንን ከፍ ከፍ ማድረግና ስለራሳችን መንፈሳዊነት እና ትልቅነት መናገር እንጂ ወንድሜ ከእኔ ይበልጣል መስማት ካቆምን ሰነበትን ይሄ ሁሉ ግን መነፈሳዊ ህይወትን ለይቶ ካለማወቅ ይመስለኛል፡፡ ለጥበበኛ ሰው አንዲት ቃል ትበቃዋለች ነው የሚባለው አይደል በዕምነታችን በዚህም ትልቁ ችግር የአማኝ መጥፋት ሳይሆን ነገር ግን የሚያምኑትን ነገር አጽንቶ የመያዝ ችግር ግን በጣም ጎድቶናል፡፡
ዳኒ ይህንን ያንተን ድህረገጽ እና ሌሎችንም የቤ/ክ ድህረገጾች ሳስብ ለፍርድ ይመስለኛል፡፡
ላንተ ግን ቃለ ህይወት ያሰማህ እግዚአብሔር ይጠብቅህ፡፡
I found the manuscript very nice. It help me to check my life with God. May God help me to do my way with him
ReplyDeleteCould you please pray for me and for may family to go on the right way.
Thank you Dn Deniel
Lijalem said
ReplyDeleteበእርግጥም ንፅፅሩ መፈናፈኛ ከለከለኝ ወደ መንፈሳዊ ልሾልክ ስል መንፈሳይ መሆኔን ኅሊናዬ አጋፈጠኝ፡፡
ዳኒ ቃለ ህይወት ያሰማልን
ትልቅ ንገር ነው የተማርኩት መንፈሳዊ እና መንፈሳይ በውስጤ እየታገሉ ባሉበት ሰዐት ይህን የመሰለ ታላቅ መልክት በማንበቤ በጣም ነው ደስ ያለኝ: ለኔ ከአምላክ የተላከ መልክት ነው:: እግዝያብሄር ጸጋውን ያብዛልክ: ቃለ ህይወት ያሰማልን
ReplyDeleteckale heyewet yasemahe di-danel,betam yetechegereckubet ena ,rasen maweck betesanegn seat new ,yehenen tsehuf yanebebeckut ,gera yegebagn sew negn,maneneten yeminegeregn tsehuf selehon ,ahun gera ayegebagnem teru MENEFESAYE mehonene gebetognal ,dani betaam amesegenehalehu lecke new yasaweckegn,AMELACK TSEGAWEN YABEZALEHE
ReplyDeleteSelam le hulum.Dn.Dani qale hiwot yasemalgn.Dn.Dani who told you how i behaved? Ohh Dn. Dani specially this word touch my heart *ጋሽ ግርማ ከበደ ከሚያስተምረው ነገር የማልረሳው ቃል አለ፡፡ «ሰው የሚጠላውን ኃጢ አት ደጋግሞ ይሠራዋል» ይላል፡ This is real fact i had been praying for a long time not to complain about others.God bless you i learned a lot.
ReplyDeleteYour sis in Him
Ehete micheal
I am "menfesay" & i am sorry b/s the two things mixed up in my mind. I beg every body who reads this suggestion please pray for me. God may bless me with some body prayers.
ReplyDeleteበራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር። እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው። really good message to to evaluate who am i menfesawi or menfesay
ReplyDeleteI am not both. I am not menfesawi at all but I never try to look like one too/
ReplyDeleteየቅዱሳን አምላክ የተመሰገነ ይሁን በናንተላይ እያደረ የሚገስጸን ወደውጨ ስይሆን ወደውስጤ እንድመለከት ስላደረከኘ ጌታ ሆይ እባክሀን መንፈሳይ ሳይሆን መንፈሳዊ እንድሆን ቸርነትህ አይለየኝ አንተንም እማምላክ የተደበቀውን ተግለጽልህ ቃለሂወት ያሰማለን አሜን!
ReplyDeleteመንፈሳይ ነኝ
ReplyDelete«ሰው የሚጠላውን ኃጢ አት ደጋግሞ ይሠራዋል» መንፈሳዊ ሰው አንድ ሰው ነው፡፡ መንፈሳይ ሰው ግን ሁለት ሰው ነው፡፡ ውጩ ሌላ ውስጡ ደግሞ ሌላ ነው፡፡
ሁሉም የገለጽከው እኔ ነኝ ከመንፈሳይ መከራ ለመውጣት እየጣርኩ ነው በጸሎታችሁ አስቡኝ
Kalhiwot Yasemalen!
ReplyDeleteዲያቆን ጉዴን ዘረዘርከው መንፈሳይት ወየውልንኝ ለኔ!
ReplyDeleteNow I have found my self to be 'MENFESAY'. Please God help me to be 'MENFESAWI' AMEN!
ReplyDeleteመን
ReplyDelete