Monday, April 12, 2010

ለዘብተኛነት/ሊበራሊዝም/፡የክርስትና ዘመናዊው ጠላትግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን ዕወቅ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፣

የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፡፡ 2ኛጢሞ. 3÷5

ለዘብተኛነት/ሊበራሊዝም/ በ18ኛው መክዘ መጨረሻ እና በ19ኛው መክዘ መጀመርያ ብቅ ያለ አስተሳሰብ ነው፡፡ ይህ አስተሳሰብ በፖለቲካው መስክ ግራ ዘመም አስተሳሰብ በመባል ይታወቃል፡፡ በደምሳሳው ልቅ በሆነ መብት እና ነጻነት የሚያምን፤ ነባር ባሕሎችን፣ ልምዶችን እና እምነቶችን በየጊዜው በመናድ ሰዎች ራሳቸውን አማልክት አድርገው እንዲያስቡ የሚያበረታታ አመለካከት ወይም ርእዮተ ዓለም ነው፡፡

ዛሬ በፖለቲካው መስክ ያለው ለዘብተኛነት ርእሰ ጉዳያችን አይደለም፡፡ የምንወያየው ስለ ለዘብተኛ/ሊበራል/ ክርስትና ነው፡፡

ሊበራል ክርስትና የግራ ዘመምን አስተሳሰብ በመያዝ በዚያው በ18ኛው መክዘ መጨረሻ እና በ19ኛው መክዘ መጀመርያ ብቅ ያለ አስተምህሮ ነው፡፡ ይህ አስተምሮ ፕሮቴስታንቲዝምን ሳይቀር አክራሪ /conservative/ ነው ብሎ የሚያምን እና በሃይማኖት ለሰው ልጅ ልቅ የሆነ መብት እና ነጻነት ሊሰጠው ይገባል በሚል የተነሣ ነው፡፡ በአሜሪካ እና በአውሮፓ አብዛኞቹ ፕሮቴስታንቶች እና ፓስተሮቻቸው በዚህ አመለካከት የሚመሩ ናቸው፡፡

ይህ አመለካከት የፕሮቴስታንቱን ዓለም ሃይማኖት አልባ ማድረጉ ሳያንሰው የካቶሊካውያንን እና የምሥራቅ እና የኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናትን በር በማንኳኳት ላይ ይገኛል፡፡ በመገናኛ ብዙኃን እና በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያው በየጊዜው ስለሚለፈፍ፣ ታላላቅ የሚባሉ ፖለቲከኞች እና የተከበሩ ሰዎች በየአጋጣሚው ስለሚያነሡት የሊበራል ክርስትና አስተሳሰብ እንደ ተስቦ በየሰው እየሠረፀ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ሊበራል ክርስትናን እንዲህ እና እንዲያ ነው ብሎ ከመበየን መገለጫዎቹን ማቅረቡ ይበልጥ ግልጽ ያደርገዋል፡፡

የሊበራል ክርስትና አመለካከት ዋና ዋና መገለጫዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል አይደለም ይላሉ

ሊበራል ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ወቅት የነበሩ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ምን እንደሚያምኑ የገለጡበት መጽሐፍ እንጂ የእግዚአብሔር ቃል አይደለም ብለው ያምናሉ፡፡ በመሆኑም ሊተች፣ ሊስተካከል፣ ሊታረም እና ሊቀየር የሚችል ጽሑፍ ነው ይላሉ፡፡ በዚህ አስተሳሰባቸው ምክንያትም ዛሬ ዛሬ ብዙዎቹ የፕሮቴስታንት አስተማሪዎች በትምህርታቸው ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ማለት አልነበረበትም እያሉ ይተቻሉ፡፡ ወይም አንድ ሰው እንዳለው they want to re-write the bible፡፡ ሃይማኖታቸውም የግድ መጽሐፋዊ መሆን እንደሌለበት እና መጽሐፍ ቅዱስ የሃሳብ መነሻ ብቻ መሆን እንደሚችል ያስተምራሉ፡፡ በመሆኑም በየጊዜው አዳዲስ እና የተሻሻሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጅዎች እንዲታተሙ ያበረታታሉ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ወጥ ትርጓሜ አያስፈልገውም ይላሉ

ሊበራሎች መጽሐፍ ቅዱስን ማንም ሰው እንደተመቸው እና እንደገባው መተርጎም ይችላል፡፡ አንድ ወጥ የሆነ እና «ትክክል ነው» ተብሎ ሊመሰከርለት የሚችል ትርጓሜ የለም ይላሉ፡፡ ይህም በሃይማኖት እና በአስተሳሰብ የተለያዩ ሚሊዮን ዓይነት የክርስትና ክፍልፋዮች እንዲፈጠሩ አድርጓል፡፡ ዶግማ እና ቀኖና የሚባል ነገር ስለሌላቸው ስለሚያመልኩት አምላክ እንኳንስ ሁሉም፣ በአንድ ጉባኤ የተገኙት እንኳን ተመሳሳይ እምነት የላቸውም፡፡ በማናቸውም ትምህርታቸውም ቢሆን የቀደሙ አበውን ትምህርት፣ ትርጓሜ እና ሐተታ አያካትቱም፡፡ ምናልባት መጽሐፍ ቅዱስን ይጠቅሱ ካልሆነ በቀር፡፡ የቅዱሳንን ሕይወትም አስረጂ አድርገው አይቆጥሩትም፡፡

በሃይማኖት ጉዞ ውስጥ አንድ ሊቋረጥ የማይገባው አንድነት «አሐተኔ» አለ፡፡ ይኸውም በአንድ ዘመን በሚኖሩ ክርስቲያኖች መካከል፣በአንድ ዘመን በሚኖሩ ወይንም በነበሩ ክርስቲያኖች እና ከእነርሱ በፊት በነበሩ ክርስቲያኖች መካከል፣እንዲሁም በአንድ ዘመን በሚኖሩ ወይንም በነበሩ ክርስቲያኖች እና ከእነርሱ በኋላ በሚመጡ ክርስቲያኖች መካከል የሃይማኖት አንድነት መኖሩ ነው፡፡ እኛ ከቀደሙ ክርስቲያኖች እና ወደፊት ከሚመጡ ክርስቲያኖች ጋር የሃይማኖት አንድነት ከሌለን «አንዲት ሃይማኖት፣ አንዲት ቤተ ክርስቲያን» ብለን መጥራት አንችልም፡፡

ሊበራሊዝም መጽሐፍ ቅዱስን እያንዳንዱ ሰው በራሱ መንገድ እንደፈለገ እንዲተረጉመው በመፍቀዱ የተነሣ በአንድ ዘመን በሚኖሩ ክርስቲያኖች መካከል የሃይማኖት አንድነት የለም፡፡ በአንድ ዘመን በሚኖሩ ክርስቲያኖች እና ከእነርሱ በፊት በነበሩ፣በኋላም በሚመጡ መካከል ያለውም አንድነት ፈርሷል፡፡

ትክክለኛም ሆነ የተሳሳተ ሃይማኖት የለም ይላሉ

ሊበራሎች «አንድ ሰው ትክክል ነው ብሎ እስካመነበት ድረስ ማንኛውም እምነት ትክክል ነው» ብለው ያስተምራሉ፡፡ ከኤፌሶን ምዕራፍ ሁለት «አንዲት እምነት» ከሚለው ትምህርት በተቃራኒ «የተሳሳተ ሃይማኖት የለም፤ ሁሉም ሃይማኖት እኩል እና ትክክል ነው፡፡ ልዩነቱ የሰዎች አስተሳሰብ ነው» ብለው ያስተምራሉ፡፡ በመሆኑም ልዩ ልዩ አመለካከት ያላቸው አማኞች በአንድ ጊዜ፣ በአንድ ቦታ ፣በጋራ ማምለክ ይችላሉ ብለው ያስባሉ፡፡

ይህ አስተሳሰባቸውም ሰዎች የራሳቸውን ፍልስፍና እንደ ሃይማኖት ትምህርት እየቆጠሩ በየጊዜው እንዲበታተኑ አድርጓቸዋል፡፡ ወደ ትክክለኛዋ መንገድ ከመመለስ ይልቅ ሁላችንም ትክክል ነን በሚል ፍልስፍና በስሕተቱ ጎዳና እንዲበረቱበት ረድቷቸዋል፡፡

የሚያስፈልገው ማኅበራዊ ወንጌል ብቻ ነው ይላሉ

የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ለማኅበራዊ ኑሮ፣ ለፍትሕ፣ ለዴሞክራሲ፣ ለሰብአዊ መብት እና ለእኩልነት መዳበር ከሚሰጠው ጥቅም አንጻር እንጂ በመሠረተ እምነት/ዶግማ/ ላይ ማተኮሩን ይቃወማሉ፡፡ ለስብከቱ ማራኪነት፣ አስደሳችነት እና ሳቢነት እንጂ ለትምህርቱ ትክክለኛነት አይጨነቁም፡፡ የነገረ ሃይማኖት ጉዳዮችን ማንሣት ሊለያየን ስለሚችል «ከዚህም ከዚያም ያልሆነ አቀራረብ» /neutral approach/ መጠቀም ያስፈልጋል ባዮች ናቸው፡፡ ትምህርታቸው መንፈሳዊ ሳይሆን ሥነ ልቦናዊ፣ ለማዳን ሳይሆን ለማስደሰት፣ እውነቱን ለመመስከር ሳይሆን ሰው እውነት የመሰለውን እንዲመርጥ ለማድረግ የታሰበ ነው፡፡ የዶግማ እና የቀኖና ትምህርት አይሰጡም፡፡

ዛሬ ዛሬ ይህ በሽታ እኛም ውስጥ ገብቶ ነው መሰለኝ ሰባክያን የተባልን ሰዎች ከዶግማ ትምህርት እየወጣን በስብከት ላይ ብቻ ወደማተኮር እየቃጣን ነው፡፡ በትምህርታችን ውስጥ እንኳን መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርትን በተገቢው መንገድ አናቀርብም፡፡ ምእመናንም ይህንኑ ለምደው መሠረታዊ ትምህርት ሲሰጥ እንደ ባከነ ጊዜ ይቆጥሩታል፡፡ በትምህርት አሰጣጣችንም ውስጥ የአበው ትምህርት፣ ትርጓሜ እና ሐተታ እየተረሳ፣ የቅዱሳንም ሕይወት በአስረጅነት መጠቀሱ እየቀረ ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያን አልባ ክርስትናን ያስፋፋሉ

ሊበራል ክርስቲያኖች ቤተ ክርስቲያን ለድኅነት የግድ አስፈላጊ አይደለችም፡፡ ያለ ቤተ ክርስቲያን ክርስቲያን መሆን ይቻላል፤ ብለው ያምናሉ፡፡ አንድ ሰው ካመነ ክርስቲያን ለመሆን በቂው ነው፡፡ ስለዚህም ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄዶ መጠመቅ፣ መቁ ረብ፣ መማር፣ መዘመር ወዘተ የግድ አያስፈልገውም ብለው ያስተምራሉ፡፡ ፕሮቴስታንቲዝም ሲጀመር «ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ከተራ ቤት እኩል ነው» ብሎ ተነሣ፣ ቀጥሎ ደግሞ ሊበራሎቹ «ያም ቢሆን አያስፈልግም» ብለው ደመደሙት፡፡ ውሻ በቀደደው አይደል ድሮስ ጅብ የሚገባው፡፡

በዚህ የተነሣም ብዙ ፕሮቴስታንቶች ወደ ቤተ ክርስቲያን አይሄዱም፣ አይሳተፉምም፡፡ ለምሳሌ በእንግሊዝ ሀገር 10% የሚሆኑ ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው ቤተ ክርስቲያን እሑድ እሑድ የሚሄዱ፡፡ በስካንዴኒቪያን ሀገሮች ደግሞ ከ2 እስከ 3% ብቻ ይሄዳል፡፡ በአሜሪካ 60% ክርስቲያኖች ቤተ ክርስቲያን አይሄዱም፡፡ ከሚሄዱት ከ40% ብዙዎቹ ማኅበራዊ ጥቅማ ጥቅም ለማግኘት የሚሄዱ ናቸው፡፡ እንዲያውም በአሁኑ ዘመን ደግሞ «የኮምፒውተር ቤተ ክርስቲያን» online church የሚባል እየተከፈተ ነው፡፡ ስለዚህም በዳታ ቤዙ ላይ የኃጢአት ዝርዝር አለ፤ የሠሩትን ኃጢአት ከዳታ ቤዙ ውስጥ ገብተው ክሊክ ሲያደርጉ ቅጣቱን ይነግርዎታል፡፡

መዋቅር አልባ እምነትን ያስፋፋሉ

ሊበራሊዝም ማንኛውም ክርስቲያን በፈቀደው መንገድ እንዲያምን ስለሚያስተምር ማናቸውንም ዓይነት የሃይማኖት መዋቅሮች አይቀበልም፡፡ ሃይማኖታዊ መዋቅሮች ይኑሩ ከተባለም በዲሞክራሲያዊ መንገድ በሚመረጡ የቦርድ አባላት የሚመሩ እና ለብዙኃኑ ድምጽ ተገዥ የሆኑ መሆን አለባቸው ይላል፡፡ በዚህም የተነሣ የክህነትንም ሆነ የአስተዳደር እርከኖችን አይቀበልም፡፡ ጳጳሳት በካህናት ላይ፣ ካህናት በምእመናን ላይ ያላቸውን ሃይማኖታዊ ሥልጣን፣ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖታዊ እና አስተዳደራዊ ጉዳይ በመወሰን ረገድ ቅዱስ ሲኖዶስ ያለውን ሥልጣን አይቀበልም፡፡

በአሜሪካን ሀገር በ1960 እኤአ መሥመራውያን አብያተ ክርስቲያናት /main line protestants/ ከጠቅላላ ክርስቲያኑ 40% ይሸፍኑ ነበር፡፡ በ40 ዓመታት ውስጥ ግን በሊበራሎች ተነጥቀው ዛሬ 12% ብቻ ናቸው፡፡

ኑፋቄ የሚባል ነገር የለም ይላሉ

ሊበራሎች «የሁሉም ሰው ሃይማኖታዊ አመለካከት ትክክል ነው» ብለው ስለሚያምኑ ኑፋቄ የሚባል ነገር የለም ይላሉ፡፡ እንዲያውም ጥንት የተወገዙ መናፍቃን መብታቸው ተነክቷል ብለውም ያስባሉ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ጉባኤያት የተለዩ የግኖስቲኮች መጻሕፍትን እንደ ገና ወደ ቤተ ክርስቲያን ለማስገባትም ይጥራሉ፡፡ መናፍቃንን በተመለከተ ምናልባት በዚያ ጊዜ የነበሩ አባቶች ተሳስተው ከሆነ ነገሩን እንደ ገና ማየት አለብን የሚል አመለካከት አላቸው፡፡ የበርናባስ ወንጌል፣ የይሁዳ ወንጌል፣ የማርያም መግደላዊት ወንጌል ወዘተ የተባሉና በግኖስቲኮች የተጻፉ የክህደት መጻሕፍት ዛሬ ዛሬ እንደ አዲስ ግኝት በመቸብቸብ ላይ ናቸው፡፡

መናፍቃንን መናፍቃን ማለተ ሰውን ማራቅ ነው፡፡ ስለ መናፍቃን ማውራት መለያየትን ማባባስ ነው፡፡ ስለ ራሳችን ብቻ እንናገር እንጂ ስለሌሎች አናንሣ፡፡ የሚሉት አመለካከቶች የልዩነቱን ድንበር አፍርሰው ክርስቲያኖች ስንዴውን እና እንክርዳዱን መለየት እንዳይችሉ የሚያደርጉ ናቸው፡፡

ለአዳዲስ አስተሳሰቦች ክፍት በር ይከፍታሉ

ሊበራሎች ለአዳዲስ አስተሳሰቦች በራችን ክፍት መሆን አለበት፣ አንድ ነገር አሳማኝ እስከሆነ ድረስ ልንቀበለው ይገባል ይላሉ፡፡ ዋናው ነገራቸው በቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርት መሠረት ሳይሆን ምን ያህል ሕዝቡ ይቀበለዋል? በሚለው መሠረት ነው፡፡ በዚህ የተነሣም የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን፣ የሴቶችን ክህነት፣ የእንስሳትን አባልነት ወዘተ በመቀበል ላይ ናቸው፡፡ የሊበራሎች አንዱ መሠረታዊ አስተሳሰብ ዘመኑን በቅዱሳት መጻሕፍት መዋጀት ሳይሆን ቅዱሳት መጻሕፍትን ለዘመኑ ማመቻቸት ነው፡፡ በዚህ የተነሣ ቤተ ክርስቲያን በቅዱሳት መጻሕፍት ቃል እና በአባቶች ትምህርት ሳይመረመሩ አዳዲስ አስተሳሰቦች እንዲሁ የሚገቡባት ቤት መሆን አለባት ይላሉ፡፡

ግዴለሽነትን ያስፋፋሉ

ሊበራሎች ለጾም፣ ለጸሎት፣ ለሥነ ምግባር እና ለባሕል ግዴለሾች ናቸው፡፡ ሥርዓታዊ እምነት አይመቻቸውም፡፡ አንድ ሰው ክርስቲያን ለመሆን ከማመን እና ከማወቅ በላይ አያስፈልገውም ስለሚሉ ሌላ ዓይነት ሥርዓተ አምልኮን እንዲፈጽም አይገደድም፡፡ ጋብቻን ማክበር፣ ከሱስ ነጻ መሆን፣ ንጽሕናን መጠበቅ፣ ድንግልናን ማክበር፣ ወዘተ የሰው በጎ ፈቃድ እንጂ የሃይማኖት ትምህርት ናቸው ብለው አይወስዷቸውም፡፡ ስለዚህም አማኞች ትክክለኛ ኑሮ እና የተሳሳተ ኑሮ፣ሥነ ምግባራዊ እና ኢሥነ ምግባራዊ የሚባለውን ለይተው እንዲያውቁ እና እንዲኖሩ አይነገራቸውም፡፡

ሊበራል ክርስትና ምን አመጣ?
               ይቀጥላል

54 comments:

 1. አከሊሉ በየነApril 13, 2010 at 12:28 AM

  ዳኒ እጅግ ግሩም መልእክት ያለው ወቅታዊ እውነታዎቸን የያዘ በተለይም በውጭው ዓለም ለምንኖር እጅግ ጠቃሚ የሆነ መረጃን ለማስጨበጥ የሚያስችል ከመሆኑም በላይ በዘመናዊነት ሰበብ በክርስትና ህይወታችን የሚገጥሙንን ፈተናዎችን አስተውለን እንድንጎዝ የሚያደርግ ደንቅ ጅምር ነው
  እግዚአብሔር አምላከእ ጸጋህን ያብዛልህ አሜን

  አክሊሉ በየነ

  ReplyDelete
 2. When i try to read more it is not amharic it is just some kind of diff sings please try to fix.

  ReplyDelete
 3. i can read now thanks

  ReplyDelete
 4. May God bless you dear Dn Dani, Yes, we can see so many liberal preachers and followers in our church today. Please let's follow the words of God in the Holy Bible and lead our needs to His words rather than trying to make the words of the Holy Bible to follow our needs.

  May God richly bless us all.

  Dani, please be strong, never give up. God's grace, wisdom and blessing and the intercession of our Lady Virgin Saint Mary and the protection of all Saint be with you.
  TFB

  ReplyDelete
 5. Thanks D/N Daniel I totally agree with you, everything you talked about is what we are observing in our daily life. “LIBE YALEW YASTWEL"

  ReplyDelete
 6. Today I will keep my comments for next time, I can not wait to read the next part!!!

  ReplyDelete
 7. I faced problem when i tried to open this article. It gives u some other language script when u click upon the title. But i was able to open it after several trials now.What is the problem? Are u guys using different kind of font? If so would u please post the link to download the new font. If it is any other problem ,please try to fix the error .

  ReplyDelete
 8. Thanks Dani, its really what is expected from the foreseeing teachers.It really makes me to critically observe all activities around our sprituallity. I hope it helps all who have open heart to rectify all which might be 'errors'. Stay blessed.

  ReplyDelete
 9. ጽዮን ግርማApril 13, 2010 at 8:01 AM

  ዳንኤለል እንዲህ ያሉ ጹሁፎችን ማስነበብ መጀመርህ ሊበረታታ ይገባዋል፡፡በዚህ ጹሁፍ ላይ ቀጣዩ ክፍል ከተጠናቀቀ በኋላ የምሰጠወው አስተያየት ይኖረኛል፡፡

  ReplyDelete
 10. ዲያቆን ዳንኤል ዘመኑን እንዴት አስተውለኸዋል ?
  አምላክ ለዘብተኛ እንዳንሆን ይርዳን:፡ አሜን

  ReplyDelete
 11. ዲ/ን ዳንኤል አገልግሎትህን እግዚአብሔር ይባርከው፡፡ ያልከው ነገር ሁሉ በጣም ትክክል ለመሆኑ የሊብራልን አስተሳሰብ ውጤት ዛሬ በገሀድ እያንው ነው፡፡ በዚህ አስተሳሰብ የተነሳ በተለይ ምዕራባውያን የሃይማኖት ለዛው ጠፍቷቸው ብዙዎች ሃይማኖት የለለሽ /አለማውያን/ ሆነው ቀርተዋል፡፡ ዘሬስ ቢሆን በኛው ቅድስቲቱ ሀገር ኢትዮጵያ እና ጥንታዊት፤ ሐዋርያዊት እንዲሁም እውነተኛ በሆነችው ቤተክርስቲያናችን መጀመሩ እንዳልቀረ እሰጋለለሁ፡፡ከዚህ የበለጠ ብዙ መረጃ እንደምታደርሰን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም ከአንተ ጋር ትሁን!
  ደረሰ ታደሰ ሚያዝያ 05,2002 ዓ.ም

  ReplyDelete
 12. Hi Daniel I also encountering the same problem like Hiwot to read the text please let me know how to solve it. I always had to copy and paste it on Microsoft Windo to see the proper Amharic text.

  ReplyDelete
 13. አባግንባር (ከሮማ)April 13, 2010 at 10:44 AM

  ውድ ዲን. ዳንኤል

  ካለ ህይወት ያሰማልን እያልኩ ቀጣዩን በጉጉት እጠባበቃለሁ::
  እንደ ጥቆማ ግን “ሊበራሊዚም ምን አመጣ?” የሚለውን ቀጣዩን ጽሑፍህን ስታስነብበን በውጪው ዓለምና በሀገር ውስጥ ምን አይነት ገጽታ እንዳለው ብታሳየን አስተማሪነቱ የጎላ ይሆናል እላለሁ አመሰግናለሁ ::
  እዚአብሔር መጨረሻችንን ያሳምረው::

  ReplyDelete
 14. ቃለ ሕይወት ያሰማልን!እረድኤተ እግዚአብሔር አይለይህ።የሚቀጥለውን ክፍል በጉጉት እጠብቃለሁ።

  ReplyDelete
 15. Dani, keep it up the good work. just one comment. i would be very glad if you could also have English version of your blog. Amharic is good for us but I got your articles very toughtful and english speakers could also benefit alot reading your blog.

  ReplyDelete
 16. oh!Dani you raise a very important issue I really appreciate your idea!!
  GEMEDA

  ReplyDelete
 17. My beloved brother,I can't tell u how much I appreciate the agendas & z way u present those agendas.Do you believe if I tell u that I've listened ur cd "dimtse tewahido" more than 30 times & that I'm continuing to do so.And now I'm highly pleased for u started ur own blog.Please keep it up & let the almighty be with u.

  ReplyDelete
 18. Dertogada
  Oh that is good and decisive issue for the Ethiopian Orthodox Church followers. Because the current problem of the church is some how related with this, so we expect explanations about the side effect of liberalism on current EOTC service.

  ReplyDelete
 19. Many thanks Dn Daniel. Yes, that is a reality! Our church and its 'Mi'imenan' are at a high risk of this 'evil' liberalism. But, who else noticed this fact? ዉሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነዉ ይላል ያገሬ ሰዉ። We are knowingly or unknowingly being influenced and victimised. If this trend continues, it is a matter of time that we are going to lose all things we own -- our identity, our christianity, ...!

  May the Almighty God keep us all from this evil formula! Let's keep our identity! Let's search only the good knowledge from the Western, not Christianity! Let's not pretend, but be OURSELVES! We may change our Nationality, but not our Identity! Let's widely open our eyes and see what is going on in this world... and identify the goods from the bads.

  HG

  ReplyDelete
 20. It is just a collection of numbers which is displayed on the blog. Please rectify it if possible.

  ReplyDelete
 21. dear my readers,some of you encountered a problem to read the article. at the right side of the blog there is an amharic software to install, or you can get it on my face book, daniel kibret/facebook.

  ReplyDelete
 22. I realize zat it was the problem of the PC which I use i can read it now... thanks

  ReplyDelete
 23. Thank you Dn. Danny
  I wonder if it is for this reason that we say "Min alebet"
  whats wrong if I eat muslims' food, if i make love befor marriage, ...we say the main thing is the cleanliness of our heart...
  GOD may bless you

  ReplyDelete
 24. ከሊበራልነት ይታደገን::

  ReplyDelete
 25. ቃለ ሕይወት ያሰማልን

  ReplyDelete
 26. yetnayet

  revaling z truth is saving lots of peoples thinking,the yuouth have been poluted in liberalism.I beg u 2 write a book make it avaliable to all.GOD BLESS U DANI.

  ReplyDelete
 27. To Yonas Alemayehu and for all interested!
  I found the comment to present the article in English and other languages is really very interesting. How ever this assignment wont be let only on Dani's shoulder, why not me? you? and other who can have a capacity? I know H.H.Pope Shenoda's book are originally written in Arabic, others will translat it to English. Lets' follow their path. Dani what do say about?

  ReplyDelete
 28. dear Red,
  I appreciate your idea. If some one who has time and capacity to translate these articles for any foriegn language, welcome.
  Daniel k

  ReplyDelete
 29. Very interesting. True! Religion becomes only knowledge and agreement. The core point of religion as identity of humans is being forgotten. May God save this generation and mostly our church!

  Daniel Bless you!

  ReplyDelete
 30. May God endow you long life! I agree with the drawbacks of Religious Liberalism.

  ReplyDelete
 31. Hi all my lovely brothers and sisters of orthodox tewahido religion followers ,our comment must be free from supporting groups or individuality/personality/.This is not our aim and it will not take us any longer. RATHER WE HAVE TO PRAY TO THEM AND ACCEPT THEIR SPRITUAL TEACH FOR THOSE WHO FORWARDS THE TEACH OF OUR MOTHER ORTHODOX TEWAHIDO CHURCH.

  ReplyDelete
 32. Thank you again Dn. Daniel. Your research findings are always valuable and practical. Keep it up. May God keep helping you to use your potential for the better. Good job!

  ReplyDelete
 33. ዳኒ
  እግዚአብሔር አምላክ ጸጋወን በረከቱን ያድልህ በእወነት ይጠብቅህ ክክፍ ኣሳቢዎች ሁል ይጠብቅህ የቤተ ክርስቲያናችን እንቁ ነህ በል አልተሳሳትኩም
  የሚቀጥለውን ክፍል ለማየት ጓዋጉቻለሁ።
  እግዚአብሔር የስጠልን

  ReplyDelete
 34. dn daniel, thank you...could u imagin how many devils are shoked with this blog & also how many angeles are happy... this is spiritual war you need praying... let the praying of all saints be with you...amen
  Edmonton

  ReplyDelete
 35. kale hiwot yasemalen !!!!

  ReplyDelete
 36. yonas-II
  Dear Daniel -(just give the chance---
  I would like to thank all the contribution for our religions/ethical/social development. But
  Some time you must ignore the emotion feeling (not logical) that is not consider the entire situation
  (Just give the chance for us to take the conclusion)
  In the future, I will expect for your study must include all the consternate and opportunity

  ReplyDelete
 37. Dear Dn.Dani, this is the truth these days!
  GOd bless You!

  ReplyDelete
 38. Thank you for sharing such wonderful contribution!
  I can't wait to read the next part..

  God Bless you Brother!

  Nahom.D

  ReplyDelete
 39. Thank you Dn. Daniel. One way to tackle the influence of liberalism is keeping our identity. As Christians we need to keep our Christian traditions intact and avoid adopting other cultures without considering the impact. That is what we did not really understand and usually confuse it with civilization. Civilization is not adopting what others follow without questioning. We can keep our tradition and become civilized. For instance, as Christians what is the meaning of celebrating 'Santa' instead of the real Christmas (birth of Christ)? Why we celebrate European new year if we believe our Calendar is biblical? Why we follow those preachers who want to imitate how western pastors preach? Why do our priests like to wear suites than their traditional uniforms? That is where things need to begin if we meant to reverse the already started path to the hollow of the snake.

  ReplyDelete
 40. kale hiwot yasemalin, dani. these days, i can feel that i am influenced by some of my friends who have a few of these thoughts

  ReplyDelete
 41. Elias k/m
  I do not agree partially with the previous writer idea (anonymous April14.2010 9.48pm) . Our preachers are humans like us they need tom improve their skill with existing knowledge. What is wrong if they wear suits or jackets when they are off duty ? or if they use mobile phone for their daily activities ? why you need them to look shaggy? why you wear suite and neck tie ?is it your traditional cloth?

  ReplyDelete
 42. This is a very interesting topic that I have looked for recently. It is time that every one of us should wake up from the deep sleep as a lot is planned for us in the name of freedom and modernization. I hope we might have heard the movement to create a new world order (NWO) by those groups who want to rule the world according to their tune.
  Anyway please continue the next part & I never wait to read it.

  ReplyDelete
 43. ሰላም ለከ ዳኒ በጣም ጥሩ ትምሕርት ሰጭ ጽሑፍ ነው በርታ እግዚአብሔር ከክፉ ይጠብቅህ ሰይፈ ገብርኤል ነኝ

  ReplyDelete
 44. ሰላም ለከ ዲ.ዳንኤል በመጀመሪያ ዳኒ የሚሉህን እርማት እንዲያደርጉ አሳስባለሁ አንተን ስለማይገልጽህ ጽሑፉ በጣም አስተማሪ ነው በዚሁ ቀጥል በርታ ምዕመናንም ከማድነቅ ባለፈ በጸሎት እንድናስበው አደራ እላለሁ፡፡ ሰይፈ ገብርኤል ነኝ

  ReplyDelete
 45. dear Dn Daniel k
  The ieads are very inhtersting and intersting continue in such away.

  ReplyDelete
 46. Kale hiywot yasemalen!
  ... But the prophecy will be fullfiled , i do not think the world get recoverd ! but Ethiopian orthodox tewahido childeren keep your promise .... keep your forfathers blessing !

  ReplyDelete
 47. Kale hiywot yasemalen!
  This issue is the warning signal for for our church,because nowadays majority our preachers focus on style of preaching than teaching real Christianity and they also emphasize on enjoining than criticizing for fault done by different individual at the different ministry of the church. So every body has to realize the fact raised by daniel kibret.

  ReplyDelete
 48. Likemekuas ZelalemApril 25, 2010 at 9:36 PM

  ዳኒ! እውነት ነው፡
  ዕለት ዕለት ምናየው ነው፡
  እኔ የምለው እነመምሩ፡
  እረኝነታቸው ከወጣ ከፍቅሩ፡
  ሥርዓት አስተምረው እየተገበሩ በእምነት ካልኖሩ፡
  አመልኴሹን ትቶ መናኙ ይሄዳል ሳይገባው ሚስጥሩ፡
  ሊቀመኴስ ዘላለም

  ReplyDelete
 49. What do you feel about consciousness? Cause this days teachers like Echart Tolle telling the world. “We are a drop of water in the ocean”. Meaning we can consider our selves like gods” Please say something about these…

  ReplyDelete
 50. May Alimightly God be with you ,you are one of the precious child of EOTC.

  GOD BLESS YOU

  ReplyDelete
 51. pls try to write about monastries in Cairo Dani

  ReplyDelete
 52. የኢትዮጵያ የዘመናት ታሪክ የመውደቅና የመነሳት ነው፡፡
  አሁንም ከወደቀችበት ተነስታ ራስ ትሆናለች፡እናት ኢትዮጵያ ምእራባውያኖች እንደፈሯት
  አይቀሩም፡በሃይል ያልሆነላቸውን የዘመናት ቂምና ቁጭት በሆዳም ባንዳዎች ቢያጠቋትም በመጨረሻ ድሉ የእርሷና የጀግኖች እውነተኛ ልጆቿ ነው፡፡
  ድሮም የአረቦች፡የጣሊያን፡አሁንም የአሜሪካ ባንዶች ሲያፍሩና ሲዋረዱ ኖረዋል ይኖራሉም፡፡
  እናት ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

  ReplyDelete