Friday, April 9, 2010

ባሕር ዛፍአሜሪካ፣ ሜሪ ላንድ ግዛት፣ ሲልቨር ስፕሪንግ ከተማ ውስጥ፣ ስታር ባክስ የተሰኘ አንድ ቡና መሸጫ ቤት ተቀምጠን ሰው እንጠብቃለን፡፡ ዕድሜያቸው ከዓርባዎቹ በላይ የሆኑ ሁለት ኢትዮጵያውያን ከኛ አጠገብ ከሚገኘው ጠረጲዛ ዙርያ ተቀምጠው የሞቀ ክርክር ይዘዋል፡፡ ክርክሩ ሲጀመር አልደረስንም፡፡ ከንግግራቸው ግን የክርክሩ መነሻ ጉዳይ ይታወቃል፡፡

በተለይም አንደኛው ሰውዬ በአካባቢው ሰው መኖሩን እስኪረሳው ድረስ እጁን እያወና ጨፈና እየጮኸ «የለም የለም በዛ፤ ዲቪ፣ አሳይለም፣ ስኮላርሺፕ ምናምን እያሉ ማንንም እየሰበሰቡ ኑሮውን አበላሹት፣ ስንት ነገር ነው የቀረው፡፡ ድሮኮ አበሻ ብርቅ ነበረ፤ ዛሬማ እንደ ጠጠር ረክሶ፡፡ ያለነውን በሚገባ ሳይይዙ መጨመር ምን ዋጋ አለው» ይላል፡፡

ጓደኛው ደግሞ «አሜሪካ የእኩል ዕድል ሀገር ናት፡፡ እድሉ ይሰጥሃል፤ አጠቃቀሙ የራስህ ነው፡፡ በመብዛት በማነስ አይደለም፡፡» እያለ ቻይናዎችን እና ላቲኖችን እየጠቀሰ ይከራከረዋል፡፡ ያኛው ግን እየደጋገመ «በጭራሽ በጭራሽ ስደተኛ አበሻ በዝቷል» እያለ እጁን ያወናጭፋል፡፡

እኔ በኋላ መገረም ጀመርኩ «ይኼ ሰው እንኳንም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አልሆነ፡፡ እርሱ ራሱ በሰው ሀገር መጥቶ እየኖረ ሌላውን መምጣት የለበትም፣ መብዛት የለበትም እያለ እንዴት ነው የሚከራከረው?»ብዬ ማሰብ ጀመርኩ፡፡ «የሰው ኃይሏን ለምታጣው ኢትዮጵያ ተቆርቁሮ ነው እንዳልል የሚያንገበግበው ሰው ከሀገሩ መውጣቱ ሳይሆን እርሱ በሚኖርበት ሀገር መብዛቱ ነው፡፡ ለስደተኛው አዝኖ ነው እንዳልል ተንቀባርረን እንዳንኖር አበሻ እንደ ጠጠር በዝቶ እድሉ ሁሉ ተበላሸ ነው የሚለው፡፡ ታድያ የዚህ ሰው ችግሩ ምንድንነው?»

መልሱን የሰጠኝ አንድ ወዳጄ ነው፡፡ ባሕር ዛፍነት ነው ችግሩ አለኝ፡፡

መነሻው አውስትራልያ ሆኖ እስያን፣ አፍሪካን፣ አውሮፓን፣ ሰሜን አሜሪካን እና ደቡብ አሜሪካን ያጥለቀለቀው ባሕር ዛፍ የድኾችን ጉሮሮ በመዝጋት እና የማገዶን ፍጆታ በመቻል ረገድ ትልቅ አስተዋጽዖ ቢኖረውም ጠባዩ ግን አስቸጋሪ ነው፡፡

ባሕር ዛፍ ብዙ ውኃ ይፈልጋል፡፡ ከተተከለበት አካባቢ ይነሣና በዙርያው ያለውን ውኃ ሥሩ እስከደረሰበት ድረስ ሙጥጥ አድርጎ ነው የሚሰበስበው፡፡ ሌሎቹ ዛፎች በአካባቢው ቢኖሩም ባይኖሩም እርሱ ግን ለራሱ ብቻ የሚሆን ውኃ ወደ ታች እና ወደ ጎን ሥሮቹን እየላከ መሰብሰብ ብቻ ነው፡፡ በዚህ የተነሣ ሌሎቹ ዛፎች ያላቸው አማራጭ ሁለት ነው፡፡ ነቅሎ ሌላ ቦታ የሚተክላቸው ካገኙ አካባቢውን መልቀቅ ያለ በለዚያም መድረቅ፡፡

አንዳንዱ ሰው ጠባዩ እንደ ባሕር ዛፍ ነው፡፡ ሥልጣንንም፣ገንዘብንም፣ ትምህርትንም፣ ዕድልንም፣ ሀብትንም የሚችልበት ቦታ ድረስ ሥሩን እየሰደደ ብቻውን መሰብሰብና ብቻውን ማደግ ይወዳል፡፡ ስለ ሀገር፣ ስለ ትውልድ፣ ስለ ወገን፣ ስለ ሌላ የሰው ዘር ግድ የለውም፡፡ ብቻ የሚገኘውን ነገር ሁሉ እርሱ ራሱ ብቻ አግኝቶ ማደግ ነው ሃሳቡ፡፡

እነርሱ ውጭ ሀገር ሄደው በርዳታ በተገኘ ገንዘብ ተምረው፣የቤት ዕቃ እና መኪና ገዝተው፣ በመጠኑም ቢሆን ገንዘብ ሰብስበው የሚመጡ ሰዎች አሉ፡፡ የሄዱበትን መንገድ፣ ያገኙትን ጥቅም ያውቁታል፡፡ ያ መንገድ ሌሎች ብዙ ወገኖቻቸውን ሊጠቅም እነርሱ የበሉትን ዓይነት እንጀራ እንዲያገኙ ሊያደርግ እንደሚችል ያውቃሉ፡፡

ወደ ሀገራቸው ተመልሰው የሥልጣኑን ቦታ ሲይዙት ግን የባሕር ዛፍን ጠባይ ይዘው ቁጭ ይላሉ፡፡ የሚረዱት የውጭ መንግሥታት መረረን ሳይሉ፡፡ የሚልከው የኢትዮጵያ መንግሥት አትላኩ ሳይል፡፡ የሚቀበሉት የውጭ ዩኒቨርሲቲዎች ሞላን ሳይሉ የሀገራችን ባሕር ዛፎች ግን ዕድሉን ብቻቸውን ተጠቅመው ለሌላው በሩን ዘግተው ቁጭ ይላሉ፡፡ ሥራቸው እንደ ባሕር ዛፍ ብዙ ነውና በቢሮክራሲ እና በቀጠሮ ብዛት፣ አልፎ አልፎም ደግሞ ለሰው ከባድ የሆኑ መመርያዎችን በማውጣት ዕድሉን ሁሉ ይዘጉታል፡፡

«በኛ ጊዜ ማስተርስና ፒኤች ዲ በስንት መከራ ነበር የሚገኘው፡፡ ሰው ተመርጦ ነበር የሚሄደው፡፡ ዛሬማ ማንንም እየላኩ አበላሹት፡ ክብሩን አሳጡት» ይላሉ፡፡ እንዲህ የሚሉት ግን ለማዕረጉ ክብር ተጨንቀውለት ሳይሆን የባሕር ዛፍ ጠባያቸው ሁሉን እኔ ብቻ ስለሚያሰኛቸው ነው፡፡

በምዕራቡ ዓለም ያሉ ድርጅቶች ሰውን በማስታወቂያ ከመቅጠር ይልቅ እዚያው ድርጅት የሚሠራ ሰው በሚያቀርበው በጎ አስተያየት /ሪኮመንዴሽን/ መቅጠር ይወዳሉ፡፡ ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ሰይጣን ብለው ነው መሰል፡፡ ታድያ በዚህ መንገድ ሕንዶች፣ ቻይናዎችን እና ላቲኖችን ያህል የተጠቀመበት የለም፡፡

በአሜሪካ ምድር ስዘዋወር የምሰማው የኛ ታሪክ ግን ለየት ያለ ነው፡፡ በአንድ ድርጅት አንድ አበሻ ከተቀጠረ ማንንም ሪኮመንድ ማድረግ አይፈልግም፡፡ ከአፍሪካ ተወስዶ የእንስሳት ማቆያ ውስጥ እንደ ተቀመጠ ቺፓንዚ ብቻውን እየተጎበኘ ቢኖር ደስ ይለዋል፡፡ ቀጣሪዎቹ እና የሥራ ባልደረቦቹ ሌላ የርሱን ወገን ባለማየታቸው «ይህ አበሻ የሚባል ዘር እየጠፋ ያለ ዘር ነው እንዴ» እስኪሉ ድረስ ቢገረሙም፤ ቢሞት ሌላ ወገኑ እዚያ እንዲመጣ አይፈልግም፡፡

መሬት ለሁሉ ትበቃለች፡፡ የአማዞንን እና የኮንጎን ጫካዎች በአንድ አካባቢ አስተናግዳ የምትኖር ናት፡፡ መሬት፡፡ ባሕር ዛፍ ግን ሁሉንም ውኃ አሟጥጦ ካልጠጣ አይደሰትም፡፡ ይህም ሰው እንዲህ ነው፡፡ የድርጅቱ ሀብት ከርሱ ሌላ ሺዎችን ሊያስተናግድ ቢችልም ሥሩን ሰድዶ ብቻውን ካላሟጠጠ የኖረ አይመስለውም፡፡

በአንዳንድ መሥሪያ ቤቶችኮ በየስብሰባው፤ በየዐውደ ጥናቱ፤ገንዘብ ሊያስገኝ በሚችል ጉዞ፤ በውጭ ሀገር ተልዕኮ ተመሳሳይ ዓይነት ሰዎች ነው የምናየው፡፡ ሌላ ባለሞያ፤ ሌላ የተማረ፣ ሌላ ዐቅም ያለው ሰው የሌለ ይመስል ለሂሳብም ጉዳይ፣ ለኤች አይ ቪ/ ኤድስም ጉዳይ፣ ለአካባቢ ጥበቃም ጉዳይ፣ ለሴቶችም ጉዳይ፣ ለሕፃናትም ጉዳይ፣ ለመዝገብ አያያዝም ጉዳይ፣ ለድርጅቱ ጥበቃም ጉዳይ እነዚያው ተመሳይ ሰዎች ናቸው የሚሄዱት፡፡

እነዚህ ሰዎች ሁለገብ የሆነ ዕውቀት እንዲኖራቸው ተፈልጎ፣ ወይንም በመሥሪያ ቤቱ የሚላክ ሰው ጠፍቶ፣ ያለበለዚያም ሞያው የሚመለከተው ሰው አልሄድም ብሎ አይደለም፡፡ እንደ ባሕር ዛፍ ሥርን ዘርግቶ ሁሉን የመሰብሰብ አባዜ ነው እንጂ፡፡ ባሕር ዛፍ የአካባውን ውኃ ሁሉ መልጭ አድርጎ እንደሚጠቀማት ሁሉ እነዚህም በመሥሪያ ቤቱ የተገኘን ዕድል ሁሉ ብቻቸውን ሙልጭ አድርገው ነው የሚጠቀሙት፡፡

በሀገራችንኮ ሌሎች ነጋዴዎች ሊደርሱባቸው የማይችሉ ጥቂት ሰዎች ብቻ የሚጠቀሙባቸው ስንት የንግድ መንገዶች አሉ፡፡ እነዚህ ዕድለኛ ነጋዴዎች ሥራቸውን በሚገባ ይሰድዱና በአካባቢያቸው ላለው ለሌላው ነጋዴ ሳያዝኑ ውኃውን ሁሉ ሙልጭ አድርገው ወደ ራሳቸው ይሰበስቡታል፡፡ እነርሱ ያድጋሉ ሌላው ይቀጭጫል፡፡ ያንጊዜ ሌላው ነጋዴ ያለው አማራጭ ሁለት ነው፡፡ ዐቅም ካለው ወደ ሌላ ሥራ ወይንም ቦታ ይሄዳል፡፡ ዐቅም ከሌለው ግን ሥራውን በኪሳራ ይዘጋል፡፡

ባሕር ዛፍ የአካባቢውን ውኃ ሙልጭ አድርጎ ለራሱ ብቻ በመውሰድ ሌላ ዓይነት ዛፍ እንዳይበቅል ማድረጉ ብቻ አይደለም፡፡ በአካባቢው ሌላ ዛፍ የሚበቅልም ከሆነ ያው እንደ እርሱ ዓይነት ባሕር ዛፍ መሆን አለበት፡፡ እንደ እርሱ የሚሻማ፡፡ ለሌላ ግድ የሌለው፡፡ ሥሩን የቻለውን ያህል ሰድዶ ውኃውን የሚሰበስብ ሌላ ተመሳይ ባሕር ዛፍ፡፡ ባሕር ዛፎች ለአካባቢያችው አያዝኑለትም፡፡ የአካባው ሥነ ምዕዳር ቢበላሽም፡፡ መሬቱን በማድረቅ ወንዞች እንዲነጥፉ ቢደረግም፡፡ ሌሎች ዛፎች በመድረቃቸው ምክንያት የአካባቢው የአየር ሁኔታ ቢዛባም ለባሕር ዛፎች ምንም አይሰማቸውም፡፡ ብቻ እነርሱ ያግኙ፤ እነርሱ ይደጉ፡፡

የባሕር ዛፍ ጠባይ ያላቸውም ሰዎች እንደዚሁ ናቸው፡፡ እነርሱ በሚገኙበት ቦታ ሊገኝ የሚችለው እንደ እነርሱ ባሕር ዛፍ የሆነ ብቻ ነው፡፡ ሲበሉ የሚበላ፤ ሲሰርቁ የሚሰርቅ፤ ሕግ ሲጥሱ የሚጥስ፤ ሲጨክኑ የሚጨክን፤ ሀገር ሲጎዱ አብሮ አገር የሚጎዳ የነርሱው ቢጤ፡፡ ስለ ሀገር ጥቅም፡፡ ስለ ትውልድ አያስቡም፡፡ ብቻ እነርሱ ይጠቀሙ፡፡

አሜሪካ ውስጥ ፓርኪንግን በመሳሰሉ በአንዳንድ ሥራዎች የሚቀጠሩ ሰዎች የስርቆት ሥርዓት ይዘረጋሉ፡፡ እዚያ ቦታ ላይ የማይሰርቅ ሰው መቀመጥ አይችልም፡፡ ሌሎችን ያጋልጣላ፡፡ እነዚያ ሥራቸውን ሰድደው የሰው ገንዘብ መሰብሰብ የለመዱ ባሕር ዛፎች ከእነርሱ ውጭ ሌላ ዓይነት ዛፍ እንዲመጣ ስለማይፈልጉ ነገር ዓለሙን ሁሉ ዘጋግተው ሰውዬው አካባቢውን ጥሎ እንዲሄድ ያለበለዚያም እንደ እነርሱ ባሕር ዛፍ እንዲሆን ያደርጉታል፡፡

ባሕር ዛፍ ከተስማማም ከሌላ ባሕር ዛፍ ጋር ነው፡፡ ባሕር ዛፍ የሆኑ ሰዎችም ከተስማሙም በዘር እና በትውልድ ቦታ ከሚመስላቸው ጋር ብቻ ነው፡፡ «የወንዛቸውን» ሰው ካልሰበሰቡ በቀር ሌላ ዐይነት ዛፍ አይታያቸውም፡፡ ሌላው ቀርቶ «ከትናንት ወዲያ»/አዲስ አበባ/ እና «ሠለስትና»/ጎጃም/፣ከትናንት በስቲያ/ጎንደር/ የሚሉ ሦስት ዓይነት ዛፎችን እንኳን ለማስተናገድ ፈቃደኞች ያልሆኑ ባሕር ዛፎች አሉ፡፡

ለዚህም ነው አንዳንድ ቤተ ክርስቲያን፣ አንዳንድ መሥሪያ ቤት፣ አንዳንድ ደርጅት፣ አንዳንድ አካባቢ፣ አንዳንድ የሥራ መስክ ውስጥ ተመሳሳይ የዘር ሐረግ ወይንም የትውልድ ቦታ ወይንም ቀየ ያላቸውን ሰዎች ብቻ የምናየው፡፡ በባሕር ዛፍነት ጠባይ ምክንያት፡፡

68 comments:

 1. ወይ ዳ. ዳንኤል....
  ባሕር ዛፍ አልክ... ትክክል ነህ ኢትዮጵያዊ ባሕር ዛፍ ነው... ሌላው ደግሞ ሐረግ.... ተያይዞ የሚያድግ

  ReplyDelete
 2. This is Really True!!! Let Us not to Be "Baherzaf" Especialy here in North America!!

  ReplyDelete
 3. I have read all and found it so fantastic; by the way this message should reach so many others; otherwise, it will be of no more use as the problem is vivid and needs to get attention. Dani please try dispatching this information on other national as well as international medias.

  may God bless you!

  ReplyDelete
 4. ዴርቶጋዳ
  መርካቶ ውስጥ የሚሰራ አንድቴክኒሻን ወዳጄ ሁልጊዜ መርካቶ ውስጥ ዕቁብ ሰብስበው ስለሚጠፉ፤አግባብ ባልሆነ መንገድ የሚከብሩ እና እንኳን የደሃ ሰራተኛቸውን ደሞዝ መክፈል ቀርቶ የተበደሩትን እንኳን የሚክዱ ‹‹እከሌ›› ከሚባል አካባቢ የሚመጡ ነጋዴዎችን በተመለከተ እየተገረመ እና እየተበሳጨ የነገረኝን አልረሳውም ፡፡ ‹‹እነኝህ ሰዎች እንዴት ነው ከሌላ አካባቢ የመጣውን ሰው ብቻ የሚጎዱት እርስ በእራሳቸውስ ተንኮል አይሰራሩም ወይ ? ›› ብዬ ስጠይቀው እነርሱማ ይህ አመላቸው ስለታወቀ ገና ከሀገራቸው ሲወጡ እርስ በእርስ እንዳይጨራረሱ የሀገሩ ሽማግሌ ሰብስቦ ያስምላቸዋል፡፡ ያን መሃላ ስለሚፈሩም የ ‹‹ወንዛቸውን›› ሰው አንዲት እንኳን ተንኮል አይሰሩትም አሉ፡፡ይህ ባህርይ ከቻይናዎች እና ከህንድ ሰዎች ጋር ይመሳሰል ይሆን ?
  እኔ የሚገርመኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ክርስትያን ነኝ ወይም ሙስሊም ነኝ ብሎ መስኪድ ስለሄደ እና በተክርስቲያን ስለሳመ ብቻ ሃይማኖተኛ መባሉ ነው፡፡ አሁን እንደው ከምቀኝነት የበለጠ ምን ኃጢአት አለ ?
  በበኩሌ ኢትዮጵያዊ ጽድቅ ሲሰራ ወደር እንደሌለው ሁሉ ተንኮል ሲሰራም ተፎካካሪ አይገኝለትም፡፡እንደው ምናልባት እንደነዚያ የ ‹‹እከሌ›› አካባቢ ሰዎች ውጭ ሀገር የሚሄዱ ሰዎችን እንደ የእምነታቸው የሚያማምል እና ቃል የሚያስገባ ፤መፈክሩ ‹‹የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ቢጠፋ›› የሚለው ኢትዮጵያዊ ብሂል የሆነ ‹‹የኢትዮጵያውያን በጎ ምግባር ቃል ኪዳን መግቢያ ድርጅት›› እናቋቋም ይሆን ?

  ReplyDelete
 5. እውነት ነው፡፡ አምላክ ባህር ዛፍ ከመሆን ይጠብቀን፡፡ አሜን፡፡

  ReplyDelete
 6. hahaha... It is a very nice expression Dani. wey ye bahirzaf neger....

  ReplyDelete
 7. Very true!!! Unfortunately the world is made by and for greedy trees not for nice trees like Zigeba!!! Perhaps Zigba is paying the ultimate price of being nice to others!!!

  ReplyDelete
 8. አባግንባር (ከሮማ)April 9, 2010 at 11:24 AM

  ወይ ባህር ዛፍ!
  አዎ ባህር ዛፎች በዝተው ሌሎች ዛፎች መጎዳታቸው አሁንም መላ የሚሻ ጉዳይ ነው፡፡ ግን የሚገርመው ይሄ የአየር ለውጥ (climate Change) የሚባለው ጉዳይ ባህር ዛፉን ከማንኛውም የአትክልት አይነት ሳይለይ እኩል ሊዳኝ መምጣቱ ደግሞ ሌላው አስገራሚ ነገር ነዉ፡፡
  አንድ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ እስራኤሎች የውሃ እጥረት ሲያጋጥማቸው የእንጥፍጣፊ መስኖን ተፈላሰፉ፤ እናም የማንጎ ዛፍ ይተክሉና ትንሽ ውሃ በዚያች እንጥፍጣፊ ይሰጡታል፡፡ ሳይወድ በግድ ሥሩን መስደድ ይተውና ውሃዋ ባለችበት ቦታ ቢቻ ተወስኖ ልክ ወቅቱን ጠብቆ የሚፈልጉትን ያህል ፍሬ ይሰጣቸዋል፡፡ የባህር ዛፍ ጠባይ ግን እንዳልከውም ለየት ያለ ነው፡፡ ከላይ ቢሰጡትም ሰርጎ መግባቱ አይቀረ ነገር ነው፡፡ ምናለ ግን ለባህር ዛፍ የግመልን ፀባይ ቢሰጠው፤ በትንሽ ውሃ ብዙ አግልግሎት ለረጅም ቀን የሚሰጥ፡፡
  ውድ ዳንኤል አንዳንዴ ምን እንደማስብ ታውቃለህ፤ የሌሎቹን ዛፎች ሥራቸውን አይቶ ይሆን ባህር ዛፍን ያበረታባቸው እላለሁ፡፡ ለምን መሰለህ ከባድ መሪ አንድም ሊምርህ አንድም ሊያስተምርህ ይመጣል ብዬ ነው፡፡ ብቻ እንደ አየር ለውጡ ሁሉንም ከላይ የሚዳኝ መኖሩ አንድ ተስፋ ነው፡፡ እንደ እስራኤላዊያን ማጉረምረም አሁንም ትርፉ ባህር ዛፍን ማባዛት ነውና፡፡
  አባግንባር (ከሮማ)

  ReplyDelete
 9. wedaje dane,
  selam lanteyihun.
  Really,Really,we are starting to know alot of things from you.go on!
  [Dereje Tizazu]

  ReplyDelete
 10. Wooow GOD Bless you Men , you have a very different view of life.

  ReplyDelete
 11. ተረርበቢነኖሰስApril 9, 2010 at 12:58 PM

  አይ ዳኒ

  ባህር ብቻ የሚገልጸን አይመስለኝም ባህር ዛፍ ሲደመር አውሬነት ጭምር እንጅ

  አክባሪህ ተርቢኖስ ነኝ

  ReplyDelete
 12. አክባሪህ ተርቢኖስApril 9, 2010 at 1:12 PM

  ወይ ዳኒ
  ባህር ዛፍ አልክ፤ ባህር ዛፍ ብቻ አይገልጸንም፤ ይልቁን ባህር ዛፍ ሲደመር አውሬነት እንጅ፤፤፤

  አክባሪህ ተርቢኖስ ነኝ

  ReplyDelete
 13. woy gud beabeshanete eko endafir yemiyadergu sint gudoch alu meselachihu, bahirzafoch ena aremoch

  ReplyDelete
 14. Dani andade sab enem beharzaf salhon alkerm, le ene kemola behal bich new lelew yemsab

  ReplyDelete
 15. Thanks Danie, that is a very good analogy. Habesah is like Bahir Zaf. I also like the Dertogada idea of "የኢትዮጵያውያን በጎ ምግባር ቃል ኪዳን መግቢያ ድርጅት", that may help.

  ReplyDelete
 16. very intresting and so true, bahir zafe kemhone hulachinenem yetbken. Thank you Dani for all the hard work u do, may God bless u more and more

  ReplyDelete
 17. Dani, i always read your articles and they are very interesting. Ye mitadu sigeremegn degmo ye bahrezafu yemidenk new sint ethiopiawian alen be baed hager le wogen kemaseb yilek ende bahirzaf yehonen.

  Esti lehulachenim mastewalun yadelen. endihum bahrezaf kemehon yadenen.

  Egziabher sirahen yibarkeleh, betesebehen yitebekeleh

  ReplyDelete
 18. Great analogy. By the way, another thing that puzzled me about Abesha (including myself)is we agree with such observations when we read or discuss. I never hear a single person opposing such characterizations or suggested solutions. But why we can't implement it? Dani, would you relect on this, please.

  ReplyDelete
 19. Thanks Dani, I got a good lesson from this article just to avoid bad habit of mine which may resemble this, thanks again. Stay blessed

  ReplyDelete
 20. this the exact expression for we ethiopian. i have faced so many times such problems. even a teacher is not volunter to write recommendation for his student.two years before i have facilitated all things for my friend to go europe for his Msc but in next year he was not volunteer to recommend me for the same university. please we should think as ethiopians. in earlier times our fathers was so much worried for their brotheres but now we are the most harsh generation with lots of problems. that is why our growth is down so deep like bahir zaf...

  ReplyDelete
 21. የተከበርክ ዲ.ዳኒኤል የጻፍካቸው ጽሑፍ ለብዙዎቻችን ያስተምራል ብየ አምናለሁ፡፡ ያነሳኸው ነጥብ በሜሪ ላንድ ግዛት የተወሰነ ሳይሆን በደቡብም፣ በሰሜኑም፣ በምሥራቁም በምዕራቡም የአሜሪካ ግዛቶች ያለ ነው፡፡ ከገጠመኞቼ በመነሳት እኔ የምሰራበት የነበረው ቦታ ፋብሪካ ውስጥ ነው፡፡ እያንዳነዱ ዲፓርትመንት የራሱ የሆነ ሀላፊ አለው፡፡ ከኔ ጋረ ጨምሮ 4 ኢትዮጵያውያን በዚሁ ቦታ እንሰራለን፡፡ መጀመሪያ ስቀጠር ከወንድሞች የተጠየኩት ጥያቄ ቢኖር በማን በኩል መጣሽ የሚል ነው፡፡ በራሴ አመልክቸ እንደሆነ ነገርኳቸው፡፡ ይህ ጥያቄ ለምን እንደጠየቁኝ የገባኝም በኋላ ነው፡፡ ለካስ ከሦስቱ በስተቀር ሌላ አበሻ እንዲገባ አይፈልጉም ነበር፡፡ ይህም የተረዳሁት በነሱ ዲፓርትመንት የሚሰሩት አንድላይ ሦስቱም ብቻ ናቸው ረዳትም የላቸው ይህም የሆነው ሰው መጨመርን ስላልፈለጉ ነው፡፡ እግዚአብሔር ፈቅዶም እኔ ባለሁበት ዲፓርትመንት የሀላፊነቱን ቦታ ተረክቤ መስራት ስጀምርም በዓመት አንድ ግዜ ብዙ ገቢ በሚገኝበት ወቅት ጊዜያዊ ሰራተኞችን እንቀጥራለን፡፡ እናም ታታሪ የሆኑት ሰራተኞችን በቋሚነት እናስቀራለን፡፡ እናም በዚህ ወቅት የሌሎች አገር ዜጎችን ጨምሮ 15 ኢትዮጵያውያን በኔ ዲፓርትመንት እንዲሰሩ ሆነ፡፡ የስራው መገባደጃ ሲደርስ የተወሰኑትን ኢትዮጵያውያን ለማስቀረት ሀሳቡ ነበረኝ እና ስማቸውን ለሃላፊዎቼ አስረከብኳቸው በቋሚነት እንዲሰሩ ፈቃደኞች መሆናቸውን ተነገረኝ፡፡ ይህ የሆነው አርብ ከስራ ስወጣ ነው፡፡ ሰኞ ስራ ልክ እንደገባሁ አንዱ አበሻ መጣና ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ አበሻ መቅጠር እንደሌለብኝ ብዙ ምክንያቶች እየደረደረ ይነግረኝ ጀመር፡፡ አስጨረስኩትና የኔ ሀሳብ ከሱ እንደሚለይ ዘርዝሬ ለማሳየት ሞከርኩ፡፡ እንዳልተቀበልኩት ሲረዳ ሀላፊዎቼን ለማነጋገር ሄደ፡፡ እንደው ምን እዳላቸው አላውቅም ሀሳባቸውን አስቀይሮ እንኳን ልጆቹ ሊቀጠሩ ቀርቶ እኔ እንክዋን ተደማጭነት አጣሁ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በሌሎች ዲፓርትመንት እራሳቸው የሚያመጥዋቸውን ሲያስቀጥሩ እኔ ግን ከዚያ መስሪያቤት ለቅቄ እስክወጣ ድረስ ተቀባይነት ሳላገኝ ቀረሁ፡፡ የሰውልጅ ክፋት ምን ሊጠቅመው ባላውቅም፣ የሌላ ሰው እንጀራ ለሱ የሚያገኘው ይመስል ክፉ ሲያልምና ሲሰራ ይኖራል፡፡ እኔም ከዚያ ጊዜ ወዲህ አበሻ ያለበት ቦታ ለመቀጠር አልደፍርም፡፡ ሁሉም አንድ ነው ባልልም ውጭ ሀገር በመቆየት ብዛት ኢትዮጵያዊነቱን እየሳተ ያለ ኢትዮጵያዊ ብዙ ነውና፡፡

  ዲ.ዳኒኤል ሌላም ብዙ እንደምትለን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ያገልግሎት ዘመንህን ያርዝምልህ፡፡ አገልግሎትህን ይባርክልህ፡፡

  አስመረት ዮሐንስ

  ReplyDelete
 22. Dear Dn. Daniel
  This kind of behavior is mainly apparent among the Ethiopian academicians. I have this experience to get a recommendation letter (leave alone the content) from my boss and university professors. You will find many Asian students in Europe and American universities, not many Africans. The main reason is not luck of talent or intelligence, it is luck of information. We don’t want to share information among each other, have no interest to guide the new comers, our professors think we are not qualified enough to pursuit high level education ( don’t forget that we are their students) . The bottom line is we are like ‘ bahir zafs’.
  Thank you Dn. Daniel.
  Cher yakoyen

  ReplyDelete
 23. Very observant, Thanks for sharing

  ReplyDelete
 24. ኢትዮጵያዊ

  Something U do not Understand About ኢትዮጵያዊ

  1
  2 can not work together
  3

  ReplyDelete
 25. so true thank you i learned a lot God bles

  ReplyDelete
 26. "ከአፍሪካ ተወስዶ የእንስሳት ማቆያ ውስጥ እንደ ተቀመጠ ቺፓንዚ ብቻውን እየተጎበኘ ቢኖር ደስ ይለዋል፡፡ " I like this saying.

  ReplyDelete
 27. “habesha yegeza sewunetu leloch sewochin yemixeqm meslo ketayew gundan lay yiqemexal::”

  ReplyDelete
 28. I also liked the analogy. I am surprised, however, that every body commenting here is externalizing the subject from himself. We should start thinking "I am the baherzaf".

  ReplyDelete
 29. you can say more,but show some solutions too
  God bless you

  ReplyDelete
 30. Dani, berta esti?! Endih bekelalu yemayderk ena yemaygenefil bi'er yalachew endante yalu sewoch zarem yemenorachew guday ek'o be'Iwnet yemiakora neger new.Yiheninns man ayebet lefetari?!

  Ye Tinsa'e bekur yehone Getachin bemechereshaw seat yekibr Tinsa'en yasnesan!

  ReplyDelete
 31. God Bless you more Dani.

  ReplyDelete
 32. i like such ideas!brave start from u as a social critique. i wish the youth learn a lot from this and be a generation of action not stories!! thank u so much.

  muluken

  ReplyDelete
 33. ጥሩ አስተውሎት ነው ዲ/ን ዳንኤል… ‘እኔ ከሞትሁ ሰርዶ አይብቀል’ አይነት አስተሳሰብ በሃገራቸን፡ በተለይም ‘ሰለጠንሁ’ ባለው ማህበረሰብ መሃል የተስፋፋ ነው። ምናልባት ይህ ባህል የመነጨው ለዘመናት እየዳከርንበት ካለነው የድህነት አረንቛ ብቸኛው ማምለጫ ‘በለጦና ተበላልጦ መገኘት’ ነው ብሎ ከማሰብ ሊሆነ ይችላል። ምስኪኑ ድሃና መሃይም ደግሞ ‘የተማረ’ እና ‘ያለፈለት’ ሲያይ ከመጠን ያለፈና ተገቢ ያልሆነ ክብር ይቸራል። ይሄኔ፡ ‘ምሁሩ’፡ ‘ባልስልጣኑ’፡ ‘ባለሃብቱ’ ሁሉ ከርሱ በላይ ላሳር ይመስለዋል። እሱን መሳይ ሲመጣም ክብሩን ሊቀማው፤ ህልውናውን ሊያዛባው በጠላት እንደተላከ እንጂ፤ ከርሱ ጋር አብሮ ወገን የሚጠቅም፡ ሃገር የሚገነባ፡ ታሪክ የሚለውጥ መስሎ አይታየውም።
  እውንትም ይህ የባህር ዛፍንትና ‘እኔ ከሞትኩ..’ ያለችው አህያ ጠባይ ከመንግስት እስከ ቤተ-ሰብ አንቀው የያዙን ችግሮቻችን አንዱ መሰረት ነው።
  ምናልባትም እያንዳንዳችን ይህን መጥፎ ባህርይ በአቅማችን በተግባር ለማስወገድ ብንጥር (ከራሳችን እየጀመርን) የምንመኝው ለውጥ አንድ ቀን ይታይ ይሆናል…

  ReplyDelete
 34. That is true...there's quite a few of those. Interesting.

  ReplyDelete
 35. ኦህህህህህህ አይ ዳኒ
  ሰማይ ብራና ወንዞች ቀለም ሁነዉ ቢጻፍ የማያልቅ ርእስ ጀመርክ

  ReplyDelete
 36. Fikert Canada
  Thanks Daniel for pointing out one of our ugliest behaviour (which is being “Baherzaf”) that will not go away as if it is in our blood. I always hear from Ethiopian expressing the other nation being helpful to each other but when it comes to us, it is pitiful to see us being “baherzaf”.
  Thanks again, lebyalew lebyaderg new message.

  ReplyDelete
 37. WOW dani this is the right way of teching people special yang. we are with you
  BERTA God Helps u! !

  ReplyDelete
 38. Bewnetu Assaye ( From Addis Abeba)
  Dear Dani: This is realy nice obsevation. A friend of mine who is living in America has recenly told me the same story.It is true,that is what is happenning.We have to change ourself please.I hope your comment will give them a lesson to adjust themselves.Keep-up Dere!!!

  ReplyDelete
 39. Egziabiher sirahinna hasabihn yibarklih wud wondmie. You taught me alot.

  Berta

  ReplyDelete
 40. of course it is right. but i need the solution also on te same feature.

  ReplyDelete
 41. ዲ.ዳኒኤል ሌላም እንደምትለን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ያገልግሎት ዘመንህን ያርዝምልህ፡፡ አገልግሎትህን ይባርክልህ፡፡

  ReplyDelete
 42. fist of all thanxs Dany
  let me tell you what happen in virginia, some ethiopian lady came to our campany to have an aplication and my best freind was findin the application to give to her but there was one ethiopian lady with us and said BAKIH ENDATSETAT we dont't need HABESHA any more we are enough
  so isn't she a bahirazaf? she a the tolest bahirzaf

  ReplyDelete
 43. Hi Dani, this is really ur life, it teaches us alot, if we understand and used it!

  Thank u!!

  ReplyDelete
 44. Wey good yehenin tekiklegna anegager balhubet ager selmayew sanbew eko germegn Dn. Dani tsegaun yabzalh.

  ReplyDelete
 45. ጥሩ ነገር ነው ዳንኤል ያነሳኸው። በመስጠት (መልካም በማድረግ) መቀበል (ከእግዚአብሔር) እንዳለ ማስተዋል ያልቻሉ የሳሱ ብዙ የኢትዮጵያ ሰዎች አሉ።

  ReplyDelete
 46. ዳኒ አሪፍ ነገር ብልሃል ነገር ግን ያልገባኝ አንድ ነገር አለ እርሱም ባህርዛፍ ስለባህርዛፍ መናገር ይችላል ወይ? የቤቱ ሞሶሶ ማን ሆነና ነው? መሶሶው አሜሪካ ስለሆነ የሃገርቤቱን ግድግዳና ጣራ ደግፎ የያዘው አለበለዚያማ ነገሩ ሁሉ የተበላሸ ይሆናል። ስለዚህ ሃበሻ(ባህርዛፍ) ስለሃበሻ(ስለባህርዛፍ) ማውራቱ መጻፉና መተረኩ ለቀባሪ ማርዳት ይሆናል!!

  ReplyDelete
 47. Danny, I missed your articles; it is like you're Lost and Found for me today after Addis Neger.

  ReplyDelete
 48. Diakon Daniel what a noble idea u have?
  Gobez! Egziabher sew ayasatan belachihu tseliyu.
  Dani Zemen lefisiha Gizie lnesiha amlak yadilih.

  ReplyDelete
 49. እውነት አልክ ዲ/ን ዳንኤል፡፡እርስ በርሳችን የምንተሳሰብ ያድርገን፡፡

  ReplyDelete
 50. Everyone pls let's start looking and correcting ourselfes. Am sure all of us has got one character that make us similar to Bahrzaf. It is good to share waht we have, But first let us unplannt the one that is inside us and then we all can grow together and correct others. Please let us start helping each other and sharing what we have just liek our fore fathers use to. ...1 ...2 ...3 pls lets start now...then we can make a difference!!!!!!!!!! Thanks Dani.
  May God bless u.

  ReplyDelete
 51. ahunim beneger hulu mastewalin tibebin yadilh. leberket hun.

  ReplyDelete
 52. እንደሚታወቀው ባህር ዛፍ የመጣው ከባህር ማዶ ሲሆን ይህ 'የባህር ዛፍ ጸባይ'ም ሀገር በቀል ነው ብዬ አላስብም፡፡ ስለዚህ በአሁኑ ሰዓት ሀገር በቀል ዛፎችን በብዛት ለመትከልና የባህር ማዶ ዛፎችን ለመተካት እንደሚታሰበው ሁሉ እውነተኛውን ሀገር በቀል ኢትዮጵያዊ ማንነት ለመመለስ እያንዳንዳችን የበኩላችንን መወጣት አለብን ብዬ አስባለሁ፡፡ ባህር ዛፍን ለብዙ ጊዜ በማሳደጋችን የእኛ ነው የሚለውን ድርቅና ግን መቀበል ይከብዳል፡፡ በተለይ በአሁኑ ዘመን ብዙ 'ባህር ዛፎችን' በስልጣኔ ስም እያስገባን እንገኛለን፡፡
  እኔ እያደኩኝ ሌላው ለምን እንደኔ ይሆናል ማለት ግን የሚገርም የባህር ዛፍ ጸባይ ነው! ለነገሩ እውነቱ ይወራ ከተባለ "There are many things that we would throw away if we were not afraid that others might pick them up."

  ReplyDelete
 53. This is very smart experssion keeption D dany

  ReplyDelete
 54. dn. dani that article was so educational

  ReplyDelete
 55. ነጮች (አሜሪካዉያን) እኛን ኢትዮጵያውያንን ጥቁር ባህርዛፍ እያሉ መጥራት ጀምረዋል ከባህር ማዶ ከአፍሪካ የመጡ የተቃጠሉ ባህርዛፎች የማይጸድቁ ፍሬ የማያፈሩ ስሮቻቸው ከአፈር በላይ ቅርንጫፎቻቸው ከአፈር ዉስጥ ሲሉን ይገርማል ስራቸውን እንዳንጠቀምበት ጎመን ሆኑ ቅጠላቸውን እንዳንጠቀምበት ካሮት ሆኑ እየተባልን ባለበት ዘመን እራሳችን ባህርዛፎች ነን ብለን ስንመሰክር የእነርሱን አባባል እውነት መሆኑን ተናገርን!!!!! ለበተክርስቲያን አባቶች ልቦናውን ይስጥልን አሜን

  ReplyDelete
 56. ስንቱን እንላለን እንጂ በደጀ ሰላም የአባቱ ስም ዳቢሎሰ የሆነ ስንት መአት አለ መስልህ፡፤
  Mekuanint Taye

  ReplyDelete
 57. መንፈሳይ ሰው፤ በደጀ ስላም ውስጥ የሚኖር የዳቢሎሰ የክብር መጋረጃ ነው።
  mekuanint taye

  ReplyDelete
 58. Dani It is good lesson I like it ....

  ReplyDelete
 59. ሰወች በአንተላይ እንዲያደርጉብህ የማትፈልገውን አንተ በሌሎች ላይ አታድርግ የሚለው አባባል የሚሰራው ለባሀር ዛፎች ነው ማለት ነው?!?!

  ReplyDelete
 60. Dear Daniel

  I really appreciate the article and hope that a lot could learn from it. However, i don't agree with some of the issues raised in it. I guess you are blaming 'Bahir Zaf' because it doesn't allow other plants to grow around. Are u saying this is wrong? come on! so what do u expect it to do ... let the others grow and die? ... that is its nature and that is how it can survive. If other plants need to grow around it, they need to win the battle.That is it! u mentioned that some business people don't show for the new entrants their know how bla bla. this is really ridiculous. why do they need to show that? does anybody like a competitor if it is possible not to have one? I guess no one

  In general you are blaming people cus they are acting according to their nature. please think of human behavior and try to answer why they are doing it like the 'Bahir Zaf".

  ReplyDelete
 61. Hello Diakon Daniel,
  I have never seen such kind of person who strive to create a better future like you.
  please keep it up,Only GOD pay your salary.
  GOD BLESS YOU & YOUR WORK.

  ReplyDelete
 62. I had missed this article of yours. You are great writter. Keep it up,

  ReplyDelete
 63. አንዳንዱ ሰው ጠባዩ እንደ ባሕር ዛፍ ነው፡፡

  ReplyDelete
 64. very nice writing it's so true. well said!!

  ReplyDelete