Monday, April 19, 2010

ለዘብተኛነት/ሊበራሊዝም/፡የክርስትና ዘመናዊው ጠላት - ክፍል 2

ባለፈው ጽሑፍ የሊበራል ክርስትናን ምንነት እና ጠባያት ተመልክተናል፡፡ በዚህ ቀጣይ ጽሑፍ ደግሞ ያመጣውን መዘዝ እና መፍትሔውን እናያለን፡፡ መልካም ንባብ፡፡

ሊበራል ክርስትና ምን አመጣ?

ሰዎች እግዚአብሔርን እንዳይፈሩ አደረገ

ቀዳሚሃ ለጥበብ ፈሪሃ እግዚአብሔር የተባለው ተዘንግቶ ክርስቲያን ነን የሚሉ ሰዎች በእግዚአብሔር ላይ የሚያሾፉ ፊልሞችን እንዲሠሩ፣ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰይጣን እንኳን የማይለውን የዳቪንቺን ኮድን የመሰሉ አስተሳሰቦችን እንዲያራምዱ፣ በስቅለት ቅርጽ የፋሲካ ካንዲ እንዲሠሩ፣ ወዘተ አደረጋቸው፡፡ በየዘፈኖቻቸው ስመ እግዚአብሔርን እያነሡ እንዲቀልዱ አበረታታቸው፡፡ የጌታችን የስቅለት ሥዕል ከየቦታው እንዲነሣ ፣ አሠርቱ ትእዛዛት ከአሜሪካ ፍርድ ቤት በር እንዲነሣ አስደረጉ፡፡

ዛሬ ዛሬ ቅዱሳንን፣ ቤተ ክርስቲያንን እና የቤተ ክርስቲያን አካላትን እያነሡ መቀለድ እና ማቃለል በሀገራችን እየተለመደ ነው፡፡ ምሁራን፣ባለ ሥልጣናት፣ጋዜጠኞች እና ሌሎችም በይፋ በቤተ ክርስቲያን ነገሮች ላይ መቀለድ ልማድ አድርገውታል፡፡ የሚገርመው ነገር እነርሱም አይሰቀቁ፣እኛም ለምደነው እንስቃለን፤ አናዝንም፡፡ ለሌሎች አርአያ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁ አገልጋዮች፣የእምነት አባቶች እና ገዳማውያን ሳይቀሩ በሥነ ምግባር ብልሹነት እና በሙስና እስከ መዘፈቅ ደርሰዋል፡፡

ለአክራሪ እስልምና አጋለጠን

አክራሪ እስልምና እጅግ በጣም ወግ አጥባቂ እምነት ነው፡፡ ይህ እምነት ወደ ምዕራቡ ዓለም ሲዘምት በሊበራሊዝም የተቦረቦረ ኅብረተሰብ ነው ያገኘው፡፡ ይህ የራሱ ማንነት የሌለው እና ሁሉም ትክክል ነው ብሎ የሚያምን ኅብረተሰብ ደግሞ በፍጥነት እና በፍላጎት ለሚሠራው አክራሪ እስልምና የተመቸ ሁኔታ ፈጠረለት፡፡ ፓትሪክ ሱኬዶ የተባሉ «የእስልምና እና ክርስትና ጥናት ተቋም ዳይሬክተር» እንደ ተናገሩት 200 ከፍተኛ የአሜሪካ ኩባንያዎች የሸሪያ ሕግን አጣጥመው ይሠሩበታል፡፡ ሳዑዲ ዐረቢያም ለዋና ዋና የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የገንዘብ ርዳታ በመስጠት የትምህርት ሥርዓቱ ከተቻለ ለእስልምና አመቺ ካልተቻለም ለዘብተኛ እንዲሆን ታደርጋለች ብለዋል፡፡

እጅግ ታዋቂ የሆኑ አሜሪካውያን ክርስትናው አላረካቸው ብሎ እስልምናን ሊቀበሉ የቻሉት፣ መጀመርያውኑ ርግጠኛውን ክርስትና ባለማግኘታቸው ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ አንዳንድ የምዕራብ ዜጎች ከነ አልቃይዳ ጎን ተሰልፈው የገዛ ሀገራቸውን እና ወገናቸውን እስከማጥፋት የደረሱት ያሳደጋቸው ለዘብተኛ ክርስትና ሊያረካቸው ባለመቻሉ ነው፡፡

የሞራል መላሸቅን አስከተለ

ክፉ እና ደጉን ለይቶ የማያውቅ፣ ማንንም የማይፈራ፣ ለሱስ፣ ለመገዳደል፣ ለመጠጥ፣ ለሐሺሽ፣ ለዝሙት፣ ለጭፈራ፣ የተጋለጠ ለማኅበረሰባዊ እሴቶች ግድ የሌለው፣ ሀገሩን እና ወገኑን ለመርዳት የማያስብ፣ ከትምህርት ይልቅ መዝናናትን የሚመርጥ ትውልድ እንዲያፈሩ አደረገ፡፡ ዛሬ አሜሪካን ውስጥ ድራግ የማይቀምስ ወጣት የለም፡፡ በድንግልና መቆየት ነውር ሆኗል፡፡ ሌላው ቀርቶ አሜሪካውያን ለሂሳብ፣ ለፊዚክስ እና ለኢንጂነሪንግ ፍቅር የሌላቸው በሙዚቃ ግን የተለከፉ እንዲሆኑ ያደረጋቸው ይሄ ነው፡፡ ቅዱሳንን ንቀው ታላላቅ ሰዎችን የሚያመልኩ፣ የፈለግኩትን ባደርግ ምን አለበት? በሚል ስሜት ለወንጀል የሚዳረጉ እንዲሆኑ አደረጋቸው፡፡

ቅድመ ጋብቻ የግብረ ሥጋ ግንኙነት እንደ ኃጢአት ሳይሆን እንደ መብት በመታየቱ ዛሬ ወጣቶቻቸው እምብዛም አይጨነቁበትም፡፡ በአሜሪካ ውስጥ በተደረገ ጥናት ዕድሜያቸው 20 ዓመት ከሞላቸው ወጣቶች መካከል ቢያንስ 75% ቅድመ ጋብቻ የጾታ ግንኙነት ፈጽመዋል፡፡ በነገራችን ላይ የዛሬ 2 ዓመት በአዲስ አበባ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በተደረገ ጥናትም ከ50% በላይ ተማሪዎች 18 ዓመት ሳይሞላቸው ጾታዊ ግንኙነት ማድረጋቸውን አመልክቷል፡፡

ጋብቻ በተጋቢዎች መካከል የሚኖር ዘለዓለማዊ ቃል ኪዳን መሆኑ እየቀረ በተፈለገ ጊዜ ሊቀር የሚችል መሆኑ ስለተሰበከ ፍቺ በርክቷል፡፡ ጋብቻ በአንደ ወቅት የሚፈጸም ሥነ ሥርዓት እንጂ የቅድስና ምንጭ መሆኑ እየተረሳ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ሳይጋቡ በደባልነት መኖር እንደ ጋብቻ ኑሮ እየተቆጠረ መጥቷል፡፡

በአሜሪካ አብያተ ክርስቲያናቱ የጽንስ ማስወረድ ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች ተብለው እስከ መለየት ደርሰዋል፡፡

አገልግሎትን እንደ ሞያ ማየት

በሊበራሊዝም አስተሳሰብ መንፈሳዊ አገልግሎቶች እንደ አንደ ሞያ ብቻ ይታያሉ፡፡ ጵጵስና፣ ካህንነት፣ ዘማሪነት፣ወዘተ ሞያዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም የሃይማኖት ሥነ ምግባርን እና አርአያ ክህነትን አይጠይቁም፡፡ አገልግሎት እንደሞያ ከታየ ፈሪሃ እግዚአ ብሔር ጠፍቶ ድፍረት ቦታውን ይይዛል፡፡ የሚያስተምሩትን ራሳቸው የማይፈጽሙ፣ለክብር ፣ለዝና እና ለገንዘብ ብቻ ሲሉ የሚያገለግሉ፣ በመንፈሳዊነት ስም ኃጢአትን የሚፈጽሙ አገልጋዮች እየበዙ ይሄዳሉ፡፡ ባለፉት ዓመታት በአሜሪካ እና በአውስ ትራሊያ በካቶሊክ መነኮሳት ላይ የታየው የሞራል ዝቅጠት በሽታው የደረሰበትን ደረጃ ያመለክተናል፡፡

በሀገራችንም ቢሆን ዛሬ ዛሬ ምንኩስናን ለፍጹምነት መብቂያ መንገድ ሳይሆን የድብር አስተዳዳሪ ለመሆን፣ውጭ ሀገር ለመሄድ፣ የተሻለ ደመወዝ ለማግኘት የሚያስችል መንገድ አድርገው የሚቆጥሩት እየበዙ መጥተዋል፡፡ ሰባኪነት እና ዘማሪነትም ቢሆን ተሰጥኦ እና ትምህርት፣ሃይማኖት እና ምግባር የሚጠይቅ መሆኑ እየተዘነጋ ነው፡፡ እንዲያውም አንዳንዴ ቀላል እና ክፍት የሥራ ቦታም ይመስላል፡፡

የማይጾም፣ የማይጸልይ፣ የማያስቀድስ፣ ከምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን የራቀ፣ የሌለበትን ሕይወት የሚያስተምር እና የሚዘምር አገልጋይ እየመጣ ነው፡፡ እንደ ባለሞያ ለእንጀራው ሲል ብቻ የማያምንበትን የሚያስተምር አገልጋይ እየመጣ ነው፡፡ ሰዓታት መቆም፣መቀደስ፣መመንኮስ፣ኪዳን ማድረስ፣ ጠዋት ተገብቶ ማታ የሚወጣበት ሥራ እየሆነ መጥቷል፡፡

የቤተ ክርስቲያን መዋቅር የማያውቃቸው ምእመናንን እና ካህናትን አፈራ

ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደው የማያስቀድሱ፣ የንስሐ አባታቸውን አግኝተው የማያውቁ፣ በአዳራሽ እንጂ በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ለመሰብሰብ የማይፈልጉ፤ አንድም ቤተ ክርስቲያን የማያውቃቸው ካህናት፣ ገዳም የማያውቃቸው መነኮሳት እየበዙ መጥተዋል፡፡

ከዚህም ብሶ ከአጠቃላዩ የቤተ ክርስቲያን መዋቅር የተነጠሉ አብያተ ክርስቲያናት እና ጳጳሳት ቁጥራቸው እየጨመረ ነው፡፡ «እኔን ከመሰለኝ» የሚለውን የሊበራል አስተሳሰብ በመከተል በአንድ በኩል ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር እየተሰበሰቡ በሌላ በኩል ደግሞ የግላቸው ቤተ ክርስቲያን መሥርተው የሚንቀሳቀሱ ጳጳሳት ተፈጥረዋል፡፡

ትምህርት ቤቶች እና የጤና ተቋማት የግል እና የመንግሥት ተብለው እንደ ሚከፈሉት ሁሉ አገልጋዮችም የግል አገልጋዮች እና የቤተ ክህነት አገልጋዮች ተብለን እስከ መከፈል ደርሰናል፡፡

የሊበራሊዝም ግርፍ የሆኑ አንዳንዶች ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ሊያድን እንጂ ሃይማኖት ሊመሠርት አልመጣም የሚል ፍስፍና ያስፋፋሉ፡፡ ለመሆኑ ሃይማኖት ምንድን ነው? ሃይማኖት ማለትኮ በቀላሉ ሲተረጎም እግዚአብሔርን የማምለኪያ መንገድ ማለት ነው፡፡ ታድያ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን መንገድ አልዘረጋም? ሐዋርያው ይሁዳስ «ለቅዱሳን አንድ ጊዜ የተሰጠች ሃይማኖት» በማለት የገለጠው ምንድን ነው?/ይሁዳ 1÷3/ ቅዱስ ጳውሎስስ በኤፌሶን መልእክቱ «አንድ ሃይማኖት አለ» ያለው/ኤፌ 4÷5¼ ተሳስቷልን? ልጁ ቲቶን «ስለዚህም ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም እኔ አንተን እንዳዘዝሁህ» ቲቶ 1÷5 በማለት የገለጠው ክርስትና የራሱ አደረጃጀት ስላለው አይደለምን?

ምን ይደረግ ?

ሊበራል ክርስትና ዛሬ የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናትን እየተፈታተኑ ካሉት የዘመኑ ፈተናዎች አንዱ ነው፡፡ ይህ ፈተና በሁለት መልኩ ይገባል፡፡

የመጀመርያው አስተሳሰቡን በማራመድ ሆን ብሎ በሚደረግ ወረራ ነው፡፡ በሀገራችን ፕሮቴስታንቶች እና ተሐድሶዎች ሞክረውት የነበረው ይሄንን መንገድ ነበር፡፡ ዛሬም ቢሆን አንዳንድ ፖለቲከኞች፣ ፓስተሮች እና ተሐድሶዎች ይህንኑ አስተሳሰብ ያራምዱታል፡፡ የሁለት ሺ ዓመት መሠረትን በማጥፋት ቤተ ክርስቲያንን ያልተጣሩ አስተሳሰቦች መናኸርያ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ ባለፉት ሁለት ሺ ዓመታት ወንጌል የገባው ሕዝብ አልተፈጠረም፣ ክርስቲያኑ ክርስቶስን አያውቅም ነበር ብሎ ማሰብ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በቋንቋው ተርጉሞ እና ከዮዲት እና ግራኝ ጠብቆ ያቆየን ሕዝብ መጽሐፍ ቅዱስን አታውቅም ነበር ብሎ በድፍረት ማስተማር መሠረትን ለማናጋት እንጂ እውነቱ ጠፍቶ አይደለም፡፡ አንድ ምሁር እንዳለው ይህ «ክርስቲያንን መልሶ ክርስቲያን ማድረግ  re  christianization of the Christians » ማለት ነው፡፡

በተለይም አሜሪካ የዚህ ወረራ ዋነኛ ቦታ ሆናለች፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት፣ትውፊት እና ባሕል እያቃለሉ ማስተማር፣ወይንም ደግሞ በጭራሽ ርእሰ ጉዳይ አድርጎ አለማስተማር እና ማስረሳት አንዱ መንገድ ነው፡፡ ባለፉት ዘመናት ከ30 በላይ ገድላትን እና ድርሳናትን የሚሳደቡ ጽሑፎች በተሐድሶአውያን ታትመው በነጻ እየተሠራጩ ይገኛሉ፡፡  አክራሪ እስልምናን በተመለከተ ግን ትንፍሽ ብለው አያውቁም፡፡

ሁለተኛው ደግሞ አስተሳሰቡ ሳይታወቅ ይገባና ውስጥ ለውስጥ ይሸረሽራል፡፡ ከዚያም በሃይማኖት ለዘብተኛ ያደርጋል፡፡

ቅዱሳንን እና ክብራቸውን ማቃለል፣ ከቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ስሕተት ለመፈለግ መኳተን፣ የጸሎት መጻሕፍትን አለመጠቀም፣ በሰበብ በአስባቡ ከጾም መሸሽ፣ በየምክንያቱ ከቤተ ክርስቲያን መራቅ፣ ለንዋያተ ቅድሳት ያለን አክብሮት መቀነስ፣ ምን አለበት በሚል ምክንያት ነገሮችን በፈለግነው መንገድ ማድረግ፣ ጳጳሳትን፣ ካህናትን እና አገልጋዮችን መናቅ፣ እና በድፍረት መናገር፤ ቤተ ክርስቲያን ባልሄድም በልቤ መልካም ሰው ከሆንኩ ይበቃኛል እያሉ መጽናናት፣ በሃይማኖት ጉዳዮች ሳቅ እና ቀልድ ማብዛት፣ በሃይማኖት ማፈር፣ አንዲት እምነት ከሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ወጥቶ፣ ለሌሎቹ ያዘኑ በመምሰል፣ ሁሉም ልክ ነው የሚል አዝማሚያ መያዝ ከበሽታው ምልክቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

በሽታው ሌላም ምልክቶች አሉት፡፡ የሊበራል ክርስትና «እኔ እኔ» አስተሳሰብ ወደ መዝሙሩም፣ ወደ ትምህርቱም ይገባና ሁሉም በዚሁ ይቃኛል፡፡ እግዚአብሔርንም የኔ ማለት ይጀመራል፡፡ በትምህርታችን ውስጥ እኔ እንዲህ ሆኜ፣ ይህንን አድርጌ፣ እንዲህ ያለ ነገር ታይቶኝ፣ ወዘተ እያሉ ራስን ከፍ ከፍ ሊያደርጉ የሚችሉ ነገሮችን መጨማመር፣ በመዝሙሮቻችንም ራስን መስበክ ይመጣል፡፡ በምሥራቃውያን ትውፊት ሰው ስለ ራሱ ይናገር የነበረው ታናሽነቱን፣ ትኅትናውን ወይንም በደለኛነቱን ለመግለጥ ነበር፡፡ ሊበራሊዝም ዘልቆ ሲገባ ግን የራስን ታላቅነት እና ክብር መናገርም ይጀመራል፡፡

ሊበራሎች ኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሔር ነው ብለው አያምኑም፡፡ ከዚያ ይልቅ ለሰዎች ሕይወት «ሞዴል ነው» ይላሉ፡፡ ስለዚህም እንደ አንድ ፍቅረኛ፣ ጓደኛ፣ አርአያ ያዩታል እንጂ በአምላክነቱ አይቀበሉትም፡፡ በመሆኑም ናፈቀኝ፣ እወደዋለሁ፣ ጓዴ ነው፣ አብሮ አደጌ ወዘተ ብሎ መጥራት ያዘወትራሉ፡፡ ይህ አስተሳሰባቸው ገብቶብን እንደሆነም አላውቅም «ስትናፍቀን እንዘምራለን» የሚል መዝሙር በሰንበት ት/ቤቶች ሲዘመር የሰማሁ ይመስለኛል፡፡

ዛሬ ቤተ ክርስቲያናችን ከሁለት አቅጣጫ በሚመጣ ፈተና ተወጥራለች፡፡ ከምሥራቅ ወግ አጥባቂው እና በከፍተኛ ሁኔታ ኃይልን፣ ገንዘብን እና ነውጥን በሚጠቀመው አክራሪ እስልምና፣ ከምዕራብ በኩል ደግሞ ለሃይማኖት ግድየለሽ፣ በፈጣሪ በሚቀልደው እና ጠንካራ እና ጽኑዕ እምነትን ለመሸርሸር በተነሳው ሊበራል ክርስትና፡፡ አንዱ በኃይል ሌላው በፍልስፍና - ኦርቶዶክሳዊነትን ለማጥፋት ዘምተዋል፡፡

ይህንን ከሁለት ወገን የመጣ እና ሳንዱዊች ሊያደርገን የተዘጋጀ ፈተና «መንፈሳውያን ሃይማኖታውያን» በመሆን ብቻ ነው ድል የምንነሣው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን በመዋቅር የተበታተነች፤ በአሠራርዋ የተዳከመች ከሆነች፤ ልጆቿ በመንፈስ የዛሉ፣ በሃይማኖት ዕውቀት ያልበረቱ ከሆኑ ፈተናውን መቋቋም አይችሉም፡፡

«በክርስትና እና በሳይንስ መካከል ያለው ዐቢይ ልዩነት፣ በሳይንስ የቅርቡ በጣም የተሻለ ሲሆን፣በክርስትና ግን የጥንቱ በጣም የተሻለ መሆኑ ነው in science the latest is the best, but in Christianity the oldest is the best» በማለት ይስሐቅ አል ባራኪ የተባሉ ሶርያዊ ሊቅ እና ሳይንቲስት ተናግረዋል፡፡ ክርስቲያን የሆንነው እኛ አባቶቻችንን ለመምሰል እንጂ አባቶቻችን እኛን እንዲመስሉን አይደለም፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያንም የመጣነው እኛ በቤተ ክርስቲያንዊ ትምህርት እና ሕግ ልንመራ እንጂ ቤተ ክርስቲያን በኛ ትምህርት እና ሕግ ለመምራት አይደለም፡፡

በመሆኑም ትክክለኛውን ክርስትና ለመኖር እኛም ወደ ቤተ ክርስቲያን፣ ቤተ ክርስቲያንም ወደ እኛ መግባት አለባት፡፡ ኦርቶዶክሳዊ ክርስትና በሦስት መልኩ መገለጥ አለበት ትምህርታዊ፣ ሊተርጂያዊ፣ እና ትውፊታዊ፡፡ ትምህርታዊ ማለት መጽሐፍ ቅዱስን አባቶቻችን በተረዱበት መንገድ እና መሠረት መረዳት፣ መመስከር እና መኖር ማለት ነው፡፡  በክርስትና አዳዲስ ማብራርያዎች እንጂ አዳዲስ መሠረተ ሃሳቦች ሊኖሩ አይችሉም፡፡

ሊተርጂያዊ ማለት ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ሕይወት የሚገኙትን ጾም ፣ጸሎት፣ ቅዳሴ፣ የምሥጢራት ተሳትፎ፣ ዝማሬ፣ ወዘተ ገንዘብ ማድረግ እና የእነዚህ ፍሬዎች የሆኑትን የምግባር ፍሬዎች ማሳየት ማለት ነው፡፡ ትውፊታዊ ማለትም በቤተ ክርስቲያን ያገኘናቸውን የቀደሙ አበው የሕይወት መንገዶች፣ትሩፋቶች፣ጸጋዎች፣ ቅርሶች በመያዝ፣በመጠበቅ እና በመጠቀም መኖር ነው፡፡

ዋናን ከውኃ ውጭ መዋኘት እንደማይቻለው ሁሉ ክርስትናንም ከቤተ ክርስቲያን ውጭ መኖር አይቻልም፡፡ በመርከቧ ሲጓዙ ማዕበል በተነሣባቸው ጊዜ በዚያው መርከብ ውስጥ ሆነው አድነን ነበር ያሉት ሐዋርያት፡፡ እኛም በየምክንያቱ ከቤተ ክርስቲያን መውጣታችንን ትተን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመኖር ችግሮችን መጋደል እና መቋቋም ያስፈልጋል፡፡

በረከታቸው ይደርብንና ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ «ሸረሪት አትሁኑ» ይሉ ነበር፡፡ ሸረሪት ድር አድርታ የኖረችበት ቤት ሲቃጠል ውኃ አምጥታ ከማጥፋት ይልቅ ቤቱን ለቅቃ ሌላ ቦታ በመሄድ ድር ታደራለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን ፈተና በገጠማት ቁጥር እየሸሹ የራስን ኅሊናዊም ቁሳዊም ጎጆ መቀለስ ሸረሪትነት ነው፡፡

ሃይማኖት የትርፍ ጊዜ ሥራ መሆን የለበትም፡፡ መንፈሳዊነትም ባሕል እና ልማድ ብቻ ሆኖ ያለ ልቡና እንዲሁ የሚኖርበት መሆን የለበትም፡፡ በመሆኑም ቀጥ ብሎ ራስን መፈተሽ ያስፈልጋል፡፡ ዛሬ እንደዋዛ የምንናገራቸው እና የምናደርጋቸው ነገሮች ቤተ ክርስቲያንን ሸርሽረው ሸርሽረው በምእመናን ላይ የማይጠገን ቁስል ከመጣላቸው በፊት በቀደሙት አበው ትምህርት እና ኑሮ መነጽርነት መንገድን እና ልብንም መመርመሩ የተሻለ ነው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ከቡር
38 comments:

 1. +++

  እኔ ለቤተ ክርስቲያናችን የዘመኑ ዋና ፈተና የሆነባት « አገልግሎትን እንደ ሞያ ማየት» በሚለው ስር የተገለጸው ነው ብዬ አምናለሁ። በአገራችን ውስጥም የሚታይ ቢኖንም በተለይ በውጪው ዓለም ባለቺው ቤተክርስቲያናችን ውስጥ ብዙ አንገት የሚያስደፉ «አባቶች» ተበራክተዋል « ባዕዳን ሰዎችም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ገብተዋልና ነውር ፊታችንን ከድኖታል።» ኤር 51፣51 እንዲል ከማን እንደተማሩት የማይታወቅ ተረት ተረት የሚያበዙ ሆነውብናል። አገልግሎትን በአገልግሎትነቱ የሚያዩት የቀደሙትማ ያለምንም ፍርሃት «የሰጠኸኝን ሰጠሁህ» የሚሉ ነበሩ፤ አሁን አሁን ግን ያልተሰጣቸውን የሚስጡ «ካህናት» እየበዙ መጥተዋል። አገልግሎቱን እንደ ሞያ የሚያይ ካህን ደግሞ «ሞያዬ እንጀራ» ላለው መተዳደሪያው እግዚዖ! እግዚዖ!የሚያሰኙ ጉዳዮችን ሲፈጽሙ ምንም ስቅቅ አይላቸውም! ምዕመኑም «እገሌ ቢሄድ እገሌ ይመደብልናል» ማለት የማይችልበት ሁኔታ ላይ ስላለ «እግዜር ይፍታው» ብሎ ዝም ይላል።

  በጎ ቀል ያምጣ!

  ReplyDelete
 2. Dn. Daniel
  Qal heywote yasemalen
  "ክርስቲያን የሆንነው እኛ አባቶቻችንን ለመምሰል እንጂ አባቶቻችን እኛን እንዲመስሉን አይደለም፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያንም የመጣነው እኛ በቤተ ክርስቲያንዊ ትምህርት እና ሕግ ልንመራ እንጂ ቤተ ክርስቲያን በኛ ትምህርት እና ሕግ ለመምራት አይደለም፡፡"
  From Alexandria VA U.S.A.

  ReplyDelete
 3. ቃለ ህይወት ያሰማልን!
  እኛም ሰምተን የምናደንቅ ብቻ ሳይሆን ሰርተን የምንጠቀም እንድንሆን እግዚአብሔር ይርዳን፡፡
  ዳዊት

  ReplyDelete
 4. It is my first coment after I listen ur preaching & read the amazing written. Daniel, may GOD pless u. I always amaized how much u are vast and reached.
  Birhanu, Rochester NY.

  ReplyDelete
 5. In the name of the holy trinity one divinity amen!

  That is very true! Thanks to God for giving us this kind of brother or I can say father (".........lijochish abat honulish ") who can articulate "the truth", I think if all of us revise our "lezebtegna & liberal" life we can learn a lot from the above demonstrations. Let our merciful father help us to follow the best and oldest dogmas and kanons of our tewahido church!

  ReplyDelete
 6. ለተግሳጸ ዚአነ ዘተጽሕፈ
  ዘ ቦ እዝነ ሰሚዓ ለይስማዕ.
  ቃለ ሕይወት ያስማዓከ.

  ReplyDelete
 7. As one Father from Alexanderian church said it " We are not afraid of Persecuation from muslims. Even we love it. BUT THE BIG CHALLENGE FOR OUR CHURCH IS "ZEMENAWITNET... A LIFE OF FUN," . That is our challenge, he said.
  On top of the liberal ideology and Islamic fundamentalism, the big challenge for all orthodox world is the bomardment of us with all the media,Tv, internet, cellphone-iphone.All this take its own toll from our pure and faithfull mind.I heard from a friend of mine that watching or playing horror movie or game will diminish people's attitude about 'Hell'. So, we won't be scared of the ultimate judgment and makes us indifferent about final punishment.
  So, I say well said Dn, Daniel.
  May Medhanialem Save us.

  ReplyDelete
 8. Last week I said I will comment after reading your next deliberation. However, I am afraid I need more time for this one. I really appreciate the effort you put into this and the depth of the analysis plus the amazing concept synthesis skill; MAY GOD BLESS YOU ABUNDANTLY!!! I have to read it in sober mind at least three times, I guess. It is a problem we experience everyday and probably the biggest challenge of the time our mother church is facing. However, it is very very tough concept to be digested easily too! Honestly, I do not even know where I belong!!!! I will read it over, over, over and over!!! Congratulations on your wonderful work!

  ReplyDelete
 9. አባግንባር (ከሮማ)April 20, 2010 at 11:49 AM

  ውድ ወንድሜ ዲን. ዳንኤል፡

  ምንም ለማለት ቃላቶች ያጥሩኛል፡፡ ብቻ ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡ እንዳንተ አንብቦ ተረድቶ መጻሕፍትን አጣቅሶ ማስተማርና ማስገንዘብ ቢቻል ሁላችንም ወደ አንድ ሐሳብ ያቺ አንዲት እምነት ተብላ ወደ ተሰጠችን ቤት በተሰበሰብን ነበረ፡፡ የሆነው ሆኖ ግን እኔ በእኔ በኩል ክፍል አንድ ላይ የሰጠሁህን ጥቆማ ምላሽ ስላገኘሁ እግዚአብሔር ይስጥልን የአገልግሎት ዘመንህን ያርዝምልን እላለሁ፡፡ ሁላችንም አንባቢዎች መገንዘብ ያለብን ነገር ግን ዕውቀት እምነትን የሚያስረዳ እንጂ እምነትን የሚፈጥር መሆን የለበትም፡፡ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው ይላልና ቃሉ ፡፡ አሁን አሁንማ በጎቹም እንደ በግ አልታዘዝ ሲሉ እረኞቹም በትራቸውን ጥለው መንጋው እንደተበተነ እንዳይቀር ስጋት ቢያሳድርም “ህልም ፍራቻ ቁጭ ተብሎ አይታድርም”ና እስቲ ወደ መንጋው ባለቤት ወደ ክርስቶስ እንጩህ፡ እላለሁ፡፡ታናሽህ አባግንባር ነኝ

  ReplyDelete
 10. «በክርስትና እና በሳይንስ መካከል ያለው ዐቢይ ልዩነት፣ በሳይንስ የቅርቡ በጣም የተሻለ ሲሆን፣በክርስትና ግን የጥንቱ በጣም የተሻለ መሆኑ ነው in science the latest is the best, but in Christianity the oldest is the best»

  ReplyDelete
 11. አባግንባር (ከሮማ)April 20, 2010 at 1:05 PM

  ውድ ወንድሜ ዲን. ዳንኤል፡

  ምንም ለማለት ቃላቶች ያጥሩኛል፡፡ ብቻ ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡ እንዳንተ አንብቦ ተረድቶ መጻሕፍትን አጣቅሶ ማስተማርና ማስገንዘብ ቢቻል ሁላችንም ወደ አንድ ሐሳብ ያቺ አንዲት እምነት ተብላ ወደ ተሰጠችን ቤት በተሰበሰብን ነበረ፡፡ የሆነው ሆኖ ግን እኔ በእኔ በኩል ክፍል አንድ ላይ የሰጠሁህን ጥቆማ ምላሽ ስላገኘሁ እግዚአብሔር ይስጥልን የአገልግሎት ዘመንህን ያርዝምልን እላለሁ፡፡ ሁላችንም አንባቢዎች መገንዘብ ያለብን ነገር ግን ዕውቀት እምነትን የሚያስረዳ እንጂ እምነትን የሚፈጥር መሆን የለበትም፡፡ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው ይላልና ቃሉ ፡፡ አሁን አሁንማ በጎቹም እንደ በግ አልታዘዝ ሲሉ እረኞቹም በትራቸውን ጥለው መንጋው እንደተበተነ እንዳይቀር ስጋት ቢያሳድርም “ህልም ፍራቻ ቁጭ ተብሎ አይታድርም”ና እስቲ ወደ መንጋው ባለቤት ወደ ክርስቶስ እንጩህ፡ እላለሁ፡፡ታናሽህ አባግንባር ነኝ

  ReplyDelete
 12. i have no word to say this.. but may god bless u...!! u speak my mouth!

  ReplyDelete
 13. ዲያቆን ዳንኤል በእውነት ይህ በጣም ልብ የሚነካ እውነታ ነው፡፡ እኔም እስቲ የተሰማኝን ልበል፡፡

  1)ሰዎች እግዚአብሔርን እንዳይፈሩ አደረገ

  በአጉል ስልጣኔ የተነሳ እግዚአብሔርን እንዳይፈሩ የማድረግ ስነልቦናዊ ተጽዕኖ በአንድም በሌላም መንገድ እየተጫነብን ይገኛል፡፡ በትልቁ "westernization is modernization" የሚል በሽታም የተነሳ ብዙ 'የተማሩና የሰለጠኑ' ሰዎች ይኽንን ሊግቱን ይፈልጋሉ፤ በተለይ ውጭ ሀገር ትንሽ ቆይተው የመጡ ሰዎች፡፡ ዳንኤል እንዳለው እንደ ዳቪንቺን ኮድ አይነት መጽሐፍ፣ ፊልም፣ በየጊዜው በድፍርት ይወጣሉ፤ ሀገር ውስጥም በቀላሉ ይደርሳሉ፡፡ ይህ የዛሬ ልምምዶሽ ደግሞ ነገ ከነጭራሹ "There's probably no God" እንያሉ በመኪናቸው ሳይቀር እንደሚለጥፉ ደፋሮች ሊዳርግ ይችላል፡፡ (http://news.bbc.co.uk/2/hi/7681914.stm)

  2)ለአክራሪ እስልምና አጋለጠን

  "እጅግ ታዋቂ የሆኑ አሜሪካውያን ክርስትናው አላረካቸው ብሎ እስልምናን ሊቀበሉ የቻሉት፣ መጀመርያውኑ ርግጠኛውን ክርስትና ባለማግኘታቸው ነው፡፡" በጣም ትክክል!! በተለይ ብዙ ጥቁሮች የነጮቹን ‘የክርስትና’ ህይወትና አካሄድ እያዩ ወደ እስልምና እንዲለወጡ ምክንያት ሆኗቸዋል፤ ምክንያቱም የሚያራምዱት በአብዛኛው ከክርስትና ውጭ የሆነ ፍልስፍና ስለሆነ ነው፡፡

  3)የሞራል መላሸቅን አስከተለ

  ይኽ በሽታ በተለይ በእኛም ዋና ዋና ከተሞች አካባቢ እጅግ በሚያስደነግጥ መልኩ ተንሰራፍቷል፡፡ ነውር የሚባለው ቃል ምናልባት በዚሁ ከቀጠለ ለወደፊት ትርጉሙ ላየታወቅ ይችል ይሆናል፤ ብዙ ነገሮችን ከመላመድ የተነሳ ነውርነታቸው ተረስቷል፡፡ ለምሳሌ እስቲ አሁን ጫት መቃም፣ ሲጋራ ማጤስ፣ አዳር ሙሉ መጨፈር፣ ወዘተ ለብዙ ወጣቶች ነውር ነውን? ብዙስ አያከራክርም? በእኛ 2ሺህ ማብቂያ አካባቢ አንድ 'አርቲስት' አንድ የፎቶ ኢግዚብሽን ለማድረግ ጠይቆ ተከልክሎ ነበር፡፡ ብዙ ታዋቂ ኢንተርናሽናል ሚዲያዎችም "Ethiopia bans first nude photo exhibition, says it’s ‘pornography’" በማለት ለመኮነን ሞክረዋል፡፡ ለምሳሌ AFP ይኽንን በዘገበበት ማጠቃለያ ላይ እንደዚህ ብሏል፡፡ "Ethiopia is a largely conservative society, whose 81 million people are mostly Orthodox Christians and Muslims." ይኽ በእርግጥም Conservative መሆን ከሆነ ሁሌም ልንሆን ይገባናል!
  በነገራችን ላይ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙዎች ሀሳባቸውን ሰንዝረው ነበር፤ ከነዚያ መካከል የተወሰነውን እዚህ ለትምህርት እንዲሆን ልጥቀሰው፡፡
  " ማስታወቂያና ባህል ሚኒስቴር ዱሮ ገና በትኩረት ሊያዩዋቸው የሚገቡ አንዳንድ ነገሮች ነበሩ:: እነርሱም: -

  * በዘመናዊ ዘፈኖች ቀስ በቀስ እየተለመደ የመጣው ልቅ አለባበስ :
  * በድራማዎች ላይ በቃልና በንግግር ባይበረታታም በድርጊት ሳናውቀው አእምሮዋችን ውስጥ ጠልቆ የሚቀረው አንዳንድ መጥፎ ልማዶችን የማሞገስ ነገር - ለምሳሌ የ "ፓርቲ "፣ የስካር፣ የሱሰኝነት፣ "ይመችህ " "ይመችሽ " አይነት "ዘና የማለት " ስነ -ልቦና
  * በድራማዎች ላይ ሁል ጊዜ በተጋነነ ሁኔታ ባላገርን እንደሞኝ፣ አላዋቂ ፣ ያልተማረ፣ የማይገባው ፣ በምክንያት የማያምን፣ የሰው መብት የማያከብር፣ ጎጂ ባህል ብቻ እንጂ መልካም ባህል የሌለው ... አይነት አድርጎ መሳል
  * ከጋብቻ በፊት ወሲብና ጓደኝነት ምንም ማለት እንዳልሆነ ሰው አምኖ እንዲቀበለውና ቀስ በቀስም ተቃዋሚ እንዲጠፋ ማበረታታት፤ እንዲያውም ከጋብቻ በፊት ያለ ሀሳባዊ ፍቅርና ጓደኝነት የድራማ ሁሉ ማዳመቂያ ተደርጎ ሁል ጊዜ መሳሉ :
  * ወዘተ ...

  እነዚህ ሁሉ በወቅቱ "ይህ ነገር እንዴት ነው ?" ሊባልባቸው የሚገቡ ነገሮች ነበሩ :: በአይናችን : በጆሮዋችን ደጋግመን ስለሰማናቸውና ስላየናቸው ትክክልና ጥሩ ነገር አድርገን ተቀበልናቸውና አሁን ሊመጣ ስለተዘጋጀው ጋጠ ወጥነት ቀስ በቀስ መንገድ ከፈቱ :: የዛሬው ሙከራ ደግሞ ነገ ልጅ ወልዶ ወንዶች ሲሳሳሙ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለመመልከትና "ወይ ሲፋቀሩ ?!" እያልን በድንቁርናና በልቅነት የምናደንቅበትን ዘመን ያመጣው ይሆናል - በዚህ አካሄድ ከቀጠልን አይቀርም !

  ታድያ ምን እናድርግ ???

  መፍትሄው ሥነ -ሥርአት ብቻ ነው ! ስርአት እንዲኖረንና ሰዎች ስራት እንዲኖራቸው ያለሀፍረት በየፊናችን መናገር አለብን:: በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እንዲህ አይነት ነገሮችን በመብት ስም ከሚያመጡት ሌላውን የመጉዳት ተልዕኮ ማደናቀፍና ሌላውንም ማስጠንቀቅ አለብን !! የሚሰማ ይስማ ! ኃላፊነቱ ግን ከኛ ስንፍና የተነሳ መቅረት የለበትም!"

  4) አገልግሎትን እንደ ሞያ ማየት

  ይህ ደግሞ ከቅርብ ጊዜ የመጣ አዲስ ልክፍት ነው፡፡ ዛሬ ዛሬ ብዙዎች በመኮፈስ ለምን እንደሚያገለግሉ በደንብ የተረዱት አይመስልም፡፡ የሚገርመው እንደነዚህ አይነት አገልጋዮች እነሱ ካላገለገሉ ወይም ካልተጋበዙ ትምህርት የሚኖር፣ ቤተክርስቲያን የምትጠፋ ይመስላቸዋል፡፡ ይህ መንፈሳዊ አገልግሎትን እንደ ሞያ የማየት ጠባይ በተለይ በወጣቶቹ ላይ ጎልቶ ይታያል፡፡ ወደድንም ጠላንም "ቤተክርስቲያን ደማቸውን የሚያፈሱላት ሰማዕታት፣ ሌት ተቀን በብርሃን ሰይፍ እየተፈራረቁ በደጇ የሚማልሉላት መላእክት፣ የሚሟገቱላት ሊቃውንት፣ አሏት :: ይህ እያለን እንደሌለን የምንሆነውና ቤተክርስቲያንን የምናስደፍረው እኛ በአላዋቂነታችን ነው እንጂ ቤተክርስቲያን ዘላለማዊት፣: መንፈሳዊት ናት:: እኛ ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ቤተክርስቲያን ለእኛ ታስፈልገናለች ::"

  ...........

  በአጠቃላይ አባቶቻችን ያቆዩን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ጥንታዊት የቀናች፣ የጠራች፣ ስለሆነች ተካታዮቿን የምታኮራ እንጂ የምታሳፍር አይደለችም፡፡ ክርስትና የተጀመረው እነሱ ክርስቲያን ሆነናል ብለው ያመኑ ዕለት በሚመስላቸው በእነዚህ የሊበራል ክርስትና አቀንኝ ጉዶችና በነሱ ተላላኪ የእኛዎቹ ነጭ አምላኪዎች እንዳንታለል በቸርነቱ ይርዳን፡፡

  ReplyDelete
 14. Dn Daniel,
  Egzeabher Tsegawen yabizaleh.
  I think most of us are attracted by this world thing. I love waching moive & i have hard time reading even a chapter from the bible or any spritual book.I spent 5-6 hours on the internet reading non important staff.But now I thank God that at least we have such web site to spend some of our time & see ourselves.I know u are idetifying the problem we have but could u write a solution too. Thanks

  ReplyDelete
 15. ቃለ ሕይወት ያሰማልን.
  በስህተት መንገድ ያለን ሁሉ መልእክቱን ከስህተት መታረሚያ እድል እንጂ እንደ መጠቃት ሳንቆጥር ለመመለስ ይርዳን።
  ጌታቸው

  ReplyDelete
 16. +++

  Kalehiwot Yasemalin,

  Yabatochachin amilak Betekristianachinin yitebikilin Egnanim kezih tiwulid beshitawoch "zemanawinet", "Lezebtegnanet", "Menafiknet" ena "akrari isliminet" yisewuren"

  Likawintun tibeb yesete ytibeb minche Egzaebihaer ahunen lemitsfu enalemiastemiru abizito tibebun yistilin!

  Wosibihat LeEgzaebihaer!
  Wolewoladitu Dingel!
  Wolemeskul Kibure!

  ReplyDelete
 17. Kale Hiowten Yasemalen Get.Eth good observation!!!

  ReplyDelete
 18. Dear Ehuye Diakon,

  Kale Hiwot yasemalin.Dikamih hulu lefire yabkalih.

  G/Yohannes

  ReplyDelete
 19. Selam Dn Daniel,

  Kalhiwot yasemaln, Yihn tsuhufihin be Hamer lay Anabibew nebr, eziya endetsfkew. It is very important and timely written.

  Get Ethi, kalhiwet yasemaln... endzih hulum yalwen siwerwer melkm new

  melakm ken

  ReplyDelete
 20. Dear Daniel

  Huletunim kifloch anebebkuachew. Ene 32 amete new. ke 12 amete jemiro senbet timihirt bet adigalehu. balefut haya ametat wusit enkua lezebtegninet enedet kegize wede gize endetechanen mayet chiyalew. Huligize belibe yalewun neger betru agelalets tetsifo bemayete betam des bilognal. Egziabiher hulachinin yitebiken. Antenim beageligot yatsinalin, andebetihin ayilewutibin.

  Fikirte Sellasie

  ReplyDelete
 21. Dear Dn Daniel,
  It is a blessing to have someone like you in our church. I read all of your articles up to this point and I was impressed by the the dimension of its coverage. It touches almost all walks of life. Keep on dear brother and I can't wait for the other articles to come.

  May god bless you more and more...

  ReplyDelete
 22. Good one, Daniel!

  ራሳችንን እናድን:: ቤተክርስቲያናችንን እንታደጋት! በተለይ አዲስ የአሰባበክ እና የአዘማመር ዘዴ የሚባለው ዘዬ ይዞን ጥርግ እያል ነው::

  Blesses!

  ReplyDelete
 23. "ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደው የማያስቀድሱ፣ የንስሐ አባታቸውን አግኝተው የማያውቁ፣ በአዳራሽ እንጂ በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ለመሰብሰብ የማይፈልጉ፤" This is exactly me.
  "ወደ ቤተ ክርስቲያንም የመጣነው እኛ በቤተ ክርስቲያንዊ ትምህርት እና ሕግ ልንመራ እንጂ ቤተ ክርስቲያን በኛ ትምህርት እና ሕግ ለመምራት አይደለም፡፡

  በመሆኑም ትክክለኛውን ክርስትና ለመኖር እኛም ወደ ቤተ ክርስቲያን፣ ቤተ ክርስቲያንም ወደ እኛ መግባት አለባት፡፡"

  Diakon Eregim Edme keageliglot gara Yistih.

  ReplyDelete
 24. Hi Danei, i donot have words to express my idea. thank u alot, this is the bigest challenge that are facing our church as wel as the people of christanity but how can we access for all? May God bless u throught your life!!
  Desta

  ReplyDelete
 25. Kalehiwot Yasemalen Dn.

  ReplyDelete
 26. በ ስ መ ሥ ላ ሴ አ ን ድ አ ም ላ ክ አ ሜ ን
  ዲ. ዳ ን ኤ ል ፡ እ ኔ ፡ ም ን ም ፡ ለ ማ ለ ት ፡ ቃ ላ ት ፡ ያ ት ረ ኛ ል ፡ አ ሁ ን ፡ ጠ ቅ ላ ላ ፡ የ እ ኛ ን ፡ የ አ ገ ል ጋ ዮ ች ን ፡ ህ ይ ወ ት ፡ ቁ ል ጭ ፡አ ድ ር ገ ህ ፡ነ ዉ ። ያ ስ ቀ መ ጥ ከ ዉ ፡እ ኔ ፡ለ ራ ሴ ፡ እ ኔ ን ፡ የ ተ ና ገ ር ከ ኝ ፡ ነ ዉ ፡ የ መ ሰ ለ ኝ ፡ እ ን ደ ዉ ፡እ ን ደ ት ፡ብ ታ ስ ተ ዉ ፡ ነ ዉ ፡ ዛ ሬ ፡ሁ ሉ ም ፡የ ሚ ሠ ራ ዉ ፡ለ መ ኖ ር ፡ ነ ው ፡ እ ነ ጂ ፡ አ ን ደ አ ባ ቶ ቻ ች ን ፡ በ እ ም ነ ት ፡ አ ይ መ ስ ለ ኝ ም ፡ የ ኢ ት ዮ ጵ ያ ፡ ኦ ር ቶ ዶ ክ ስ ፡ ተ ዋ ሕ ዶ ፡ ቤ ተ ክ ር ስ ቲ ያ ን ፡ ዉ ስ ጥ ፡ ሊ ቨ ራ ሊ ዝ ም ፡ በ ደ ን ብ ፡ እ የ ተ ጠ ና ወ ተ ን ፡ ነ ዉ ፡ ያ ለ ዉ ፡ ከ ዚ ህ ም ፡ አ ን ዱ ፡ የ ራ ስ ን ፡ ማ ን ነ ት ፡ ታ ሪ ክ ፡ ሃ ይ ማ ኖ ት ፡ ማ ጣ ጣ ል ፡ ማ ና ና ቅ ፡ እ የ ተ ለ መ ደ ፡ መ ጥ ት ዋ ል ፡ ስ ለ ዚ ህ ፡ ኢ ት ዮ ጵ ያ ዉ ያ ን ፡ ወ ገ ኖ ቼ ፡ አ ጥ ብ ቀ ን ፡ እ ን ጸ ል ይ ፡ እ ግ ዚ ኦ ም ፡ እ ን በ ል ፡ እ ና ል ቅ ስ ፡ ሃ ይ ማ ኖ ት ፡ እ ን ደ ፡ አ ባ ቶ ቻ ች ን ፡ ሥ ል ጣ ኔ ፡ ደ ግ ሞ ፡ እ ን ደ ዘ መ ና ች ን ፡ እ ን ከ ተ ል ፡ እ ባ ካ ች ሁ ። ዳ ን ኤ ል ፡ እ ባ ክ ህ ፡ አ ሁ ን ም ፡ አ ሁ ን ም ፡ ደ ግ መ ህ ፡ ጻ ፍ ፡ ብ ዙ ዎ ቻ ች ን ፡ እ ን መ ከ ር በ ት አ ለ ን ። ለአ ን ተ ም ፡ ለ ዕ ዝ ራ ፣ ለ ሄ ኖ ክ ፣ ለ ቅ ዱ ስ ኤ ፍ ሬ ም ፣ ለ ቅ ዱ ስ ያ ሬ ድ ፣ ለ አ ባ ጊ ዮ ር ጊ ስ ፡ጥ በ ብ ና ፡ ዋ ስ ተ ዋ ል ፡ የ ሰ ጠ ፡ አ ም ላ ክ ፡ አ ሁ ን ም ፡ ጨ ም ሮ ፡ አ ብ ዝ ቶ ፡ ይ ግ ለ ጽ ል ህ ፡ ከ ፈ ተ ና ም ፡ ይ ጠ ብ ቅ ህ ፡ ፡ ለ ዉ ዳ ሴ ከ ን ቱ ብ የ አ ይ ደ ለ ም ።
  አ ባ ከ ቬ ጋ ስ

  ReplyDelete
 27. ዴርቶጋዳ

  ይህ ጉዳይ በጣም በጣም አሳሳቢ ነው፡፡ እንደው ቢቻል ሀገራዊ ወይም ወቅታዊ የሃይማኖት የመወያያ አጀንዳ ማድረግ ቢቻል ጥሩ ነው፡፡ አሁን አሁን ሕዝቡ ገዳማትን እና የገጠር ቤተክርስቲያንን ለመርዳት መነቃቃቱ ለውጥ አሳይቷል ፡፡ይህ የሆነው ደግሞ ጉዳዩን በሰፊው አንዲታሰብበት ማኅበረ ቅዱሳን እና ሌሎች አካላቶች ባደረጉት ቅስቀሳ ነው፡፡ ልክ እንደዚሁ ሁሉ ‹‹Liberalism, the current EOTC challenge›› በሚል ርዕስ በጣም በሰፊው ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም ከሊቅ እስከ ደቂቅ ከአለቃ እስከ ምንዝር ሳያውቀው የ‹‹ሊበራሊዝም›› ሰለባ እየሆንን ነው፡፡ክፋቱ ደግሞ እንደ ችግር መታወቅ አለመቻሉ እና አጀንዳ ተደርጎ እንዳይታይ ብዙ እንቅፋቶች መኖራቸው ነው፡፡
  ለእኔ አክራሪ እስልምና እና መናፍቃን ቤተክርስቲያን ላይ ከሚያደርሱት አደጋ ይልቅ ሊበራሊዝም የጭቃ ውስጥ እሾክ የሆነ አደጋ ነው፡፡ምክንያቱም ሳናውቀው በፈቃደኝነት ወደ መናፍቃኑና ወደ ሌሎች መንገድ ይወስደናል እና ነው፡፡
  ስለዚህ እኔ የተቻለኝን እጥራለሁ ፤እናንተስ ? ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ከእኔ የተሻለ ጉዳዩ እንደ ጉዳይ እንዲታይ የማድረግ ብቃት አለህ so ‹‹Let us make It a hot discussion issue››
  ከአባቶቻችን ቅዱሳን መንገድ ወደኋላ እንዳንል በክርስትናችን እንዳናቅማማ ያስፈልጋል፡፡

  ReplyDelete
 28. Thanks to GOD he never left us with out real Church servants(is it possible to say real shepherds? if it is possible use it please).
  GOD be with U -Daniel,Wright you are Now there are a number of priests & monks but not real keepers of believers(Christian mass).when I read your article I recall impressive speech of Megabe Hadiss Kesis Eshetu at the time when he preach in Mahidere S.Lideta Mariam Church (A.A) LAST MONTH," yebetekirstianachin yezemenu fetena kewuch sayhon kegna keagelgayoch new"

  ReplyDelete
 29. n the Name of Father,Son, and the Holy-sprite Amen!!!
  Dn. Daniel I can't to express what you wrote and the benefit of it;but, I want to say keep it up and we need your continuous perspective views.Thank you for your time with us may God bless you for a prosperous and Glorious life!!!

  ReplyDelete
 30. ራእግዚአብሔር ይስጥልኝ ራሴን ዞር ብ½ እንዳይ አድርጎኛል፡፡

  ReplyDelete
 31. kale hiwot yasemah
  daniel:-b careful.antem behzbu dgafna moral endatwdq tsely.beterefe berta HABIBU GIYORGISEN astawsew. may virgin marry be with u and ur spiritual work.

  yoseph from mekelle university
  endayesus gibi gubae

  ReplyDelete
 32. shimelis fantahunMay 2, 2010 at 2:44 PM

  በቅድሚያ ቃለህይወት ያሰማልን ወንድሜ ዳኒ፡፡ ቤተክርስቲያናችን እንዳነተ ያሉትን ሰዎች ስላፈራች በጣም ደስ ብሎኛል፡፡የምታነሳቸው ሃሳቦች ለኛ እጅግ ጠቃሚ ናቸው ፡፡
  እኔም አሁን አሁን ከሚያሳስቡኝ ነገሮች አንዱ ስብከቶቻችን ከቤተክርስትያናችን ቅጥር ግቢ ውጭ እየሆኑ መምጣታቸው ይሄም ለሊበራል ክርስትና በር ከፋች ናቸው ብዪ እገምታለሁ፡፡በመሆኑም ስብከቶቻችን የቤተክርስቲያናችንን ስርአት በጠበቀ መልኩ ቢሆን ወደፊት ለሚመጡት አደጋዎች እንድናለን ባይ ነኝ፡፡
  በመጨረሻም ውድ ዳኒ እባክህ በዚሁ ቀጥልበት፡፡ እግዚያብሄርም ካንተ ጋር ይሁን፡፡ድንግል ማርያም ትጠብቅህ፡፡

  ReplyDelete
 33. ቃሉ የታመነ ነው እንዲህ የሚለው።
  ከእርሱ ጋር ከሞትን፥
  ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንኖራለን፤
  ብንጸና፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን፤
  ብንክደው፥ እርሱ ደግሞ ይክደናል፤
  ባናምነው፥ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤
  ራሱን ሊክድ አይችልምና።
  ይህን አሳስባቸው፥ በቃልም እንዳይጣሉ በእግዚአብሔር ፊት ምከራቸው፥ ይህ ምንም የማይረባ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውና።

  ReplyDelete
 34. Daniel i'm a big fan of u. keep it up!
  but i wanna say some. in your article you mention 'akrari eslmna', but when i talk to my friend(Muslim) he said that their may be fundamental Muslims(akrari muslimoch)but not there is no fundamental Islam(akrari eslmna). how do you see this? post your comment on your face book page. thanks

  ReplyDelete
 35. "RECHRISTIANIZATION OF THE CHRISTIAN"

  ReplyDelete
 36. Dn.Daniel, I have nothing to say except, "qale htwet yasemaln, ftsamehn yasamrlh"

  ReplyDelete
 37. its really a good argument... But would be great if you are able to give us the reference or bibliography that you used to substantiate your arguments.

  God bless!

  ReplyDelete