Wednesday, March 31, 2010

ጲላጦስሚያዝያ 14 ቀን 2000 ዓ.ም በኢትዮùያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET 603 ከዱባይ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ላይ ነበርኩ፡፡ ሻርጅያ በተባለው ከተማ አንድ ኢትዮ ጵያዊ የጠየቀኝን ጥያቄ አወጣለሁ፣ አወርዳለሁ፡፡ ወቅቱ በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ዘንድ ‹ሰሙነ ሕማማት› የሚባለው ነው፡፡ ሚያዝያ 17 ቀን ስቅለት ከሁለት ቀናት በኋላ ደግሞ የትንሣኤ በዓል ይከበራል፡፡

ያ ኢትዮጵያዊ ወዳጄ፡- ‹‹መስፍኑ ጲላጦስ ክርስቶስን ለምን አሳልፎ ሰጠው?›› የሚል ጥያቄ ነበር ያነሣልኝ፡፡ ለጊዜው ይኾናል ያልኹትን ማብራሪያ ሰጠኹት፡፡ በኋላ ግን እኔው ራሴ በነገሩ ማሰላሰሌን ቀጠልኹ፡፡

ጴንጤናዊው ጲላጦስ ክርስቶስ በተሰቀለበት ጊዜ (በ34 ዓ.ም) በኢየሩሳሌም የሮምን ንጉሥ በመወከል የይሁዳ መስፍን ነበር፡፡ ክርስቶስ በፊቱ ተከስሶ የቀረበውም ከዚህ ሥልጣኑ የተነሣ ነበር፡፡ በዘመኑ ይደረግ እንደ ነበረው ተከሳሹን አስቀርቦ ጠየቀ፡፡ እር ሱን ያስረዳሉ የተባሉ የከሣሽ ምስክሮችንም ጠየቀ፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስን ‹‹ወንጀለኛ›› ሊያስደርግ የሚችል ምንም ነገር ዐጣ፡፡ ሚስቱም በሕልሟ ያየችውን ነገር በመግለጥ በርቱዕ መንገድ ብቻ ፍርድ እንዲሰጥ ነገረችው፡፡

እነዚህ ሁሉ ተደማምረው መስፍኑ ጲላጦስ ክርስቶስን፡- ‹‹ለሞት የሚያበቃው ቀርቶ የሚያሳስረው ጥፋት አላገኘሁበትም›› ሲል ደመደመ፡፡ አይሁድ ይህን ሲሰሙ ‹‹ይህን ካደረግኽ የቄሣር ወዳጅ አይደለህም›› የሚል ፖለቲካዊ ተቃውሞ በከረረ ሁኔታ መሰንዘር ጀመሩ፡፡ ጲላጦስ ነገሩን ለማብረድ በማሰብ ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስን ገርፌ ልስቀልላችሁ›› የሚል አማራጭ ሐሳብ አቀረበ፡፡ ከሳሾቹ አይሁድ ግን ‹‹ሞቶ ካላየነው አንተ የቄሣር ወዳጅ አይደለህም›› ብለው ነገሩን አጠነከሩት፡፡ በመጨረሻም መስፍኑ ጲላጦስ ተሸነፈ እና ይሙት በቃ ፈረደ፡፡

የተከሰሰው እና በፍርድ አደባባይ የቆመው ክርስቶስ ምንም ጥፋት እንዳላጠፋ ዳኛው ዐውቋል፡፡ ማወቅ ብቻም ሳይኾን በአንደበቱ መስክሯል፡፡ ሕጉም ንጹሕ የኾነ ሰው ከተከሰሰበት ነገር ነጻ እንዲኾን እና እንዲሰናበት ያዝዛል፡፡ ታዲያ ጲላጦስ ይህን ሁሉ እያወቀ ለምን የተዛባ ፍርድ ፈረደ?

አንድን ነገር ማወቅ፣ በጉዳዩም ማመን እና ላመኑበት እውነት እስከ መጨረሻው በጽንዐት መቆም የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡ ጲላጦስ የዕውቀት ችግር አልነበረበትም፡፡ በዘ መኑ በነበረው የፍርድ አሰጣጥ ሥነ ሥርዐት መሠረት የከሳሾቹን ምስክሮችም ኾነ ተከሳሹን በፊቱ አቁሞ ጠይቋል፡፡ በዚህም ክርስቶስ ምንም ወንጀል የሌለበት መኾኑን ዐውቋል፡፡ ነጻ መኾን እንዳለበትም አምኗል፡፡ ይህን ዕውቀቱን እና እምነቱን በተግባር እንዳያውል ግን አንድ ነገር ከለከለው - የሚያጣው ጥቅም፡፡

ክርስቶስ የተከሰሰበት አንዱ ወንጀል ‹‹ራሱን ከቄሣር ጋር በማስተካከል ‹ንጉሥ ነኝ› ይላል›› የሚለው ነው፡፡ በመኾኑም ክርስቶስን ነጻ ቢለቀው ‹‹ከቄሣር ሌላ ንጉሥ አለ ብሎ ያምናል›› ተብሎ ሊወነጀል፣ በኋላም ሥልጣኑን ሊያጣ ነው፡፡ ጲላጣስ እውነ ትን ተቀብሎ፣ ለእውነት መሥዋዕትነት ከፍሎ ሥልጣኑን ከሚያጣ እውነትን ሠውቶ በሥልጣን መቆየትን መረጠ፡፡ ያመነው ነገር፣ የተናገረው ነገር እና የፈረደው ፍርድ ተለያየ፡፡

አንዳንድ ሰዎች የሚናገሩት፣ የሚያምኑበት፣ በየመድረኩ የሚደሰኩሩት፣ አጠናን ብለው የሚተነትኑት፣ ከልብ ጓደኞቻቸው ጋር ሲያወጉ የሚዘረዝሩት፣ ‹‹ቢኾን መልካም ነው›› የሚሉት እና በቦታው ላይ ኾነው የሚፈጽሙት የሚለያየው ለእውነት መቆም የሚያስከፍለው ዋጋ ስላለ ነው፡፡

አንድ ዳኛ የሚተቸው፣ የሚተነትነው፣ በኅሊናው የሚያምንበት እና በልቡ የሚያመላልሰው ከሚሰጠው ፍርድ ጋር ከተጋጨ፣ አንድ ባለሥልጣን እውነት ነው ብሎ የተቀበለው እና ትክክል ነው ብሎ የወሰነው ከተለያየ፣ አንድ ባለሞያ የጥናቱ ውጤት እና እርሱ ለአለቃው ያቀረበው ውጤት ከተቃረነ እንዳያጡት የሚፈሩት ጥቅም አለ ማለት ነው፡፡

በስብሰባ ተቀምጠው አለቆቻቸውን ወይም የሚመጣውን መከራ ፈርተው አንዳች ነገር የሚወስኑ ነገር ግን በልቡናቸው የተቀበሉት እውነት ከወሰኑት ጋር የሚጋጭባቸው ሰዎች ይህን በሽታ የሚያሥታግሱት ‹‹ምን ይደረግ ብለህ ነው፤ በግድ፣ ሳናም ንበት፣ አስፈራርተው፣ ሐሳባችንን ሳይቀበሉ ቀርተው . . .የማይኾን ነገር ወሰኑ›› እያሉ ለሚቀርባቸው ሰው በማውራት ነው፡፡ የውስጡን ግጭት በወሬ ነው የሚያስተነፍሱት፡፡

ከወዳጆቻቸው ጋር ሲቀመጡ የተቹትን፣ የነቀፉትን እና የተቃወሙትን ነገር በቦታው ሲኾኑ ግን ‹‹የጠሉት ይወርሳል. . . ›› የተባለው ደርሶባቸው እነርሱ የባሱ ኾነው ይገኛሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በሚያምኑት ነገር እና በሚሰጡት መግለጫ መካከል ቅራኔ ሲያጋጥማቸው በረዥም ዐረፍተ ነገሮች፣ ኧ. . .ኧ. . .ኧ በሚል የሚታክት የነገር ጉተታ ወይም ደግሞ ‹‹አበረታች ነው፤ አስደናቂ ነው፤ ልዩ ነው፤ ብሩህ ነው›› በሚሉ የማይለኩ ነገሮች ሊያሥታግሱት ይሞክራሉ፡፡

ሁለት እና ሁለት አራት መኾኑን እያወቁ፣ ጠረጴዛቸው ላይ በሚገኘው ወረቀት ይኽንኑ ሳያስቡት እየሞነጫጨሩ፣ 2 እና 2 ‹‹አምስት ነው›› ብለው ለማሳመን ሲሉ የማርስ እና የጁፒተርን ልምድ የሚጠቅሱት ኅሊናቸው እና ንግግራቸው ሲጋጭባቸው ነው፡፡

‹‹የእንጀራ ጉዳይ ነው፤ ልጆቼን ላሳድግ ብዬ ነው፤ ‹ከሰው ጋር ሲኖሩ ሞኝ ኾኖ አህያ ሲጭኑ ሦስት ኾኖ› ስለሚባል ነው፤ ክፉ ቀንን እና ቅዝምዝምን ጎንበስ ብሎ ማሳ ለፍ ስለሚገባ ነው፤ ብቻዬን ለውጥ ላመጣ ስለማልችል ነው . . .›› የሚባሉት ማብራ ሪያዎች ሁሉ ከነመሰሎቻቸው የዚሁ ጲላጦሳዊ ችግር መገለጫዎች ናቸው፡፡

ሰው በመኖር ብቻ ሳይኾን በመሞትም ያሸንፋል፡፡ ሰዎችን ከእንስሳት ከሚለዩ አቸው ነገሮች አንዱ ሰዎች በሞት ሊገታ የማይችል አሸናፊነት ሊኖራቸው ስለሚችል ነው፡፡ እነ ማርቲን ሉተር ኪንግ፣ እነ ማኅተመ ጋንዲ፣ እነ አብዲሳ አጋ ተገድለዋል፤ ነገር ግን አሸንፈዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ለሰማዕትነት እንዲበቁ ያደረጋቸው የሚሠሩት ሥራ ከሚያምኑበት ነገር ጋር እንዲቃረን ባለመፍቀዳቸው ነው፡፡

የተማረው እና የሚያምንበት ሌላ ኾኖ ጥቅም ብቻ በሚያስገኝለት ክሊኒክ የሚሠራ፣ ጥቅም ብቻ ባለበት ትምህርት ቤት የሚያስተምር፣ ጥቅም ብቻ ባለበት የፋይናንስ ሥራ ላይ የተሠማራ፣ ጥቅም ብቻ በሚገኝበት የጋዜጠኝነት መስክ የሚኳትን ስንቱ ነው !! ውሎ አበል፣ የተሻለ ክፍያ፣ የውጭ ዕድል፣ ሥልጣን፣ የወንበር አበል፣ መኪና፣ የሪሴፕሽን ግብዣ፣ ያማረ ቢሮ እና የተደላደለ ቤት ይቀርብኛል ብሎ የማያምንበትን የሚሠራ ስንቱ !!

ጲላጦስ ውሳኔውን ወስኖ ክርስቶስ ከተሰቀለ በኋላ በሠራው ሥራ መጸጸት ጀመረ፡፡ የውስጡ እምነት እየገፋ፣ ኅሊናውንም ዕረፍት እየነሳው መጣ፡፡ ያ ሰዓት ግን ምንም ሊያደርግ የማይችልበት ሰዓት ነበር፡፡ የእርሱ ፍርድ ተፈጻሚ ኾኖ ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሏል፡፡ በታሪክ እንደሚነገረው ጲላጦስ እስከ ዕድሜው ፍጻሜ በዚያ በሠራው ሥራ እንደ ተጸጸተ፣ ኅሊናውም ሰላም ሳያገኝ ነው የኖረው፡፡

ነገር ካለቀ በኋላ ከመጸጸት እና የኅሊና ሰላም ከማጣት ከሚያምኑት እውነት ጋር መቆም እጅግ የተመረጠ ነው፡፡ ጦርነቱ ሲያበቃ፣ ፖለቲካው ሲቀየር፣ አስቸጋሪው ዘመን ሲያልፍ፣ የችግሩ ጊዜ ሲጠናቀቅ ‹‹እንዲህ ብዬ ነበር፣ እንዲህ ማድረግ አልነበረብኝም፤ ያደረግኹት ተገድጄ ነው፤ ተጽዕኖ ነበረብኝ፤ ለታሪክ ምስክርነት ለመትረፍ ብዬ ነው፤በሠራሁት ሥራ አዝናለሁ፤ ተሰምቶኛል፤ ወዘተ ወዘተ›› ለችግሩ መፍትሔ አይሆኑም፡፡

የሞተው አይነሣም፤ የደኽየው ሀብት አያገኝም፤ የተነጠቀው አይመለስም፣ ትዳሩን የፈታው አያገባም፤ ያለቀ ዕድሜ አይተካም፤ ያመለጠ ዕድል አይገኝም፡፡ እናም ውስጣዊ ሰላም ይጠፋል፤ ጸጸት እንደ እግር እሳት ይበላል፡፡

በስታድዬሙ ዙሪያ ተሰብስቦ መተቸት፣ ሐሳብ መስጠት፣ ‹‹ለምን አልገባም›› ብሎ መውቀስ፣ ጎል ሲገባም መጨፈር፣ አሠልጣኝ እና ተጨዋችን መሳደብ እጅግ በጣም ቀላል ነው፡፡ ከዐሥራ አንዱ ተጨዋቾች እንደ አንዱ ኾኖ ውጤት የሚያመጣ ጨዋታ መጫወት ግን ከባድ ነው፡፡

የጨዋታ ጊዜው ሲጠናቀቅ ‹‹ይህ ቢደረግ እንዲህ ይኾን ነበር፤ ያ እንዲህ ቢያደረግ ይገባ ነበር፤ እገሌ ይህን l!ሠራ አይገባም ነበር፤›› እየተባለ ይተነተናል፡፡ እንዲህ ያለው ነገር ለወደፊቱ ጠቃሚ ልምድ ይገኝበት ይኾናል፡፡ ያን ጨዋታ ግን አይቀይረውም፤ የገባው ገብቷል፤ የተሳተው ተስቷልና፡፡

እናም ነገር ካለቀ በኋላ እንዲህ የኾነው እንዲያ ስላልኾነ ነው ከማለት በወቅቱ ማድረግ ያለብንን ነገር ማድረግ ነው፡፡ ‹‹አገራችን በባዕድ መያዝ የለባትም›› ብለው ያመኑበትን እምነት በተግባር ለመግለጥ በዐድዋ ዘመቻ መሥዋዕትነት የከፈሉት ጀግኖ ቻችን ኢትዮጵያን በነጻነት ለማቆየት ችለዋል፡፡ ነገር ግን ‹‹ከጣሊያን የምናገኘው ጥቅም ይበልጥብናል›› ብለው ባይዘምቱ ኖሮ ታሪክ በተቀየረ ነበር፡፡ ታዲያ ዛሬ እነዚያ ዘማቾች ያልዘመቱበትን ምክንያት ቢያስረዱን እንኳን የዐድዋን ድል ሊተካው አይችልም፡፡ በክፉ ቀን በጦርነት ሜዳ የተወለዱት ጀግኖች አባቶቻችን ግን መሥዋዕት ኾነው በሞታቸው ወራሪን አሸነፉ፡፡

ከስብሰባ ሲመጡ፣ ነገር ሲያልቅ፣ ጨዋታው ሲያበቃ፣ መከራው ገሸሽ ሲል ሺሕ ጊዜ ከማውራት ‹‹ጀግና የሚወለደው በጦር ሜዳ ነው›› ብሎ እዚያው ላይ ላመኑበት መሟገት ነው ሞያ ማለት፡፡

ስለ የሌሊት ወፍ ‹አፈጣጠር› የሰማሁትን እዚህ ላይ ባነሣው መልካም ነው፡፡ በጥንት ጊዜ የሌሊት ወፍ የሚባል ነገር አልነበረም አሉ፡፡ አንድ ጊዜ ግን ወፎች ተሰብስበው የሚወዳድቀውን ጥራጥሬ አይጦች እየበሉ ጦማችንን ስላሳደሩን አይጦችን የሚከ ታተል፣ መልኩ አይጥ የሚመስል የወፍ ዘበኛ እንቅጠር  ብለው ማስታወቂያ አወጡ፡፡ በዚህ ጊዜ ጉድጓድ ውስጥ መኖር የመረራት አይጥ ክንፍ አሰፍታ ‹‹ወፍ ነኝ›› ብላ ቀረበች፡፡ ምንም እንኳን ዘመዶቿ ‹‹አይጦች ጥራጥሬ መብላት የለባቸውም›› የሚሉትን ብትቃወምም ለመኖር ስትል ግን ለዘበኝነቱ ተስማማች፡፡ ጥርሷን አይተው እንዳያባርሯትም በድንጋይ ሰብራ አረገፈችው፡፡ ለብዙ ዘመን በዘበኝነቱ ጸንታ የገዛ ዘመዶቿ የሆኑትን ወፎች ስታስበረግግ ኖረች፡፡ እየቆየች ግን ጥርሷ እያደገ፣ ፀጉርዋም እየታወቀ ሄደ፡፡ ለመደበቅ ብትሞክርም አልቻለችም፡፡ ወደ ድሮው ኑሮዋ እንዳትመለስ አይጥነቱን ረስታዋለች፡፡ ያደረገችው ነገር እየጸጸታት ስለ መጣ ከሁሉም ለመራቅ ስትል በሌሊት ብቻ መንቀሳቀስ ጀመረች ይባላል፡፡ የሌሊት ወፍ አይጥም ወፍም ኾና የኖረችው በዚህ ጠባይዋ ነው ይባላል፡፡

ትናንት የሠሩት ነገር  ‹ጥርሱ እየበቀለ፣ ፀጉሩም ብቅ እያለ› እያስቸገራቸው ስን ቶች ወገኖቼ መከራ እያዩ ነው፡፡ ውስጣቸው አይጥ ኾኖ ላያቸው ወፍ እየኾነ፡፡ እንደ አይጥ እያሰቡ፣ እንደ ወፍ ሊሠሩ እየሞከሩ፣ መጨረሻቸው በጸጸት ጨለማ ውስጥ መሰወር ይኾናል፡፡

የእስክንድርን ታሪክ የጻፈው የግብጹ ንጉሥ በጥሊሞስ እንዲህ ይተርክልናል፡፡ በአንድ ትንሽ ጦርነት የእስክንድር ጦር ብዙ ጉዳት ደርሶበት አሸነፈ፡፡ የዚህ ጦርነት ጉዳት ያንገበገበው አንድ ወታደር ‹‹የአመራር ድክመት ባይኖር ኖሮ ይህን ጦርነት ለማ ሸነፍ ይህን ሁሉ መሥዋዕትነት መክፈል አያስፈልግም ነበር›› ብሎ በመተቸቱ ተከስሶ እስክንድር ዘንድ ቀረበ፡፡ ‹‹ይህ ዓይነቱ ሐሳብ ጦሩን ያዳክማል፤ ጠላትን ያስደስታል፤ መደፋፈር ያመጣል፤ ለሌሎች ክፉ አርኣያ ይኾናልና ወታደሩም ይቀጣ፣ ሐሳቡም ስሕ ተት መኾኑ ይነገር›› ብለው የጦር ጄኔራሎቹ እስክንድርን ወጥረው ያዙት፡፡

ታላቁ እስክንድርም ‹‹እንደ ንጉሥነቴ ይህ ሰው ጥፋተኛ ነው፤ የሰነዘረውም አስተ ያየት ስሕተት ነው፤ እንደ እውነቱ ከኾነ ደግሞ ይህ ሰው ትክክል ነው፤ እኛ ጥፋተኞች ነን፡፡ እኔ ደግሞ እንደ ንጉሥነቴ ሳይኾን እንደ እውነቱ ፈርጃለሁ›› ብሎ ተናገረ፡፡

እኛስ?


32 comments:

 1. እኔስ? እኔስ? እኔስ?

  ReplyDelete
 2. Dn. Daniel, I read your article and loved it very much. I really appreciate your dedication to contribute your part so as to solve contemporary problems. But I wonder what is the value of admiring some one for his spiritual services. People whom we know through their spiritual cassettes are becoming busy in telling us their mighty. Hence, I am becoming reluctant to appreciate any one. The goal of spiritual services is in no way personal pride. In fact, it is this stand of yours that I inferred from your various writings that made me your fan [not just your fan but a fan of anyone who really stands for the truth in our church].

  May I advise you one thing? Please turn a deaf ear to the mindless criticism of 'tehadiso menafikans'. We [true believers] appreciate what your are doing now. We value people not by their name,race, pride...but with their actual contribution for the betterment of our church.

  With love and respect!

  ReplyDelete
 3. this will be a big chalenge for our brother daniel, we can help him by creating blog praying session or atlest one abune zebesemayat,pleas, we should stand beside him for the seccuse of his spritual carier.bro, we thanks God for his aim on you. good job take care

  ReplyDelete
 4. እኛማ? …… ብቻ እስቲ ትንሽ ልበል፡፡
  በእርግጥ ይህ ጽሁፍ አብዛኞቻችን የሚዳስስ ይመስለኛል፡፡ ብዙዎቻችን አንዳንድ ጊዜ ላላመንብት ነገር ‘ለመኖር’ ስንል ብቻ ካመኑበት ጋር ተቀላቅለን ከነእሱ ብሰን እንታያለን፡፡ በእውነት ስንቱ ነው በማያምንበት እምነት ገብቶ ከኔ በላይ ላሳር የሚለው? ስንቱስ ነው ለግዜያዊ ጥቅም ብሎ የፈረንጅ ቅጥረኛ በመሆን የነሱ ገዳይ ተልኮ አስፈፃሚ የሆነው?( Many examples of missionaries effect) ኸረ ስንቱ ነው ያላመነበትን የፖለቲካ ድርጅት ተቀላቅሎ በሌሎች ላይ ቀንበር የሚጭነውና ‘አስተኳሽ’ የሆነው?
  ሌላው ደግሞ ብዙ ጊዜ ከማህበረሰባችን የወጡና የተወገዙ ነገሮች እንኳን ሲፈጸሙ በምንቸገረኝና በኔ ላይ አልደረሰብኝ በሚል ሁኔታ ያላመንበት ነገር ሲፈጻም ዝም የምንል ብዙዎች ነን፡፡ እጅግ ብዙ ምሳሌዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡ በወቅቱ "ይህ ነገር እንዴት ነው ?" ሊባልባቸው የሚገቡ ነገሮች ነበሩ :: ነገር ግን በአይናችን : በጆሮዋችን ደጋግመን ስለሰማናቸውና ስላየናቸው ትክክልና ጥሩ ነገር አድርገን ተቀበልናቸውና አሁን ሊመጣ ስለተዘጋጀው ጋጠ ወጥነት ቀስ በቀስ መንገድ ተከፈተላቸው::
  በእርግጥም እንደተባለው “ሰው በመኖር ብቻ ሳይኾን በመሞትም ያሸንፋል፡፡” ያንንም ያረጋገጡልን ብዙ ሰማዕታት አሉ፡፡ ግን ሰማዕትነት ቀላል ነገር አይደለም፤ ዋጋ ይስከፍላል፡፡
  በመጨረሻም የታላቁ እስክንድርን ፍርድ ሳስብ ከዚህ በፊት ይምርሐነ ክርስቶስን አስመልክቶ በተፃፈው ላይ አስተያየት የሰጠሁበትን በከፊል አመጣዋለሁ፡፡ ንጉሱና ካህኑ ይምርሐነ ክርስቶስ ቀን ቀን ሰዎች በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ተጣልተው ወደርሱ ሲመጡ በእውነት ዳኝቶ ጥፋተኛው ላይ ቅጣት ይጥላል :: ማታ ግን ሁለቱን ወገኖች አስታርቆ ቅጣቱ በተበዳዩ ፈቃድ እንዲነሳ አድርጎ አስማምቶ "እምማእሰረ -ኃጥያት እግዚአብሔር ይፍታ !" ብሎ ያሰናብታቸው ነበር ! ስለነሱም ጽሎት ያደርግ ነበር ! እውነትና ምሕረት አንድ ሆኑ ..... ያለው መጣፉይህን ለማመልከት ሳይሆን ይቀራል ? ሕግና ይቅርታ ሁለቱም ሳያኮርፉ ታርቀውባት ነበር በኢትዮጵያ ! አሁንስ?...

  ReplyDelete
 5. ዲያቆን ጅማሬህ መልካም ነው ብዙ ነገሮችን እንድናስተውል እየረዳን ነው፡፡ ራሳችንና ዙሪያችን እንድንፈትሽ ጥሩ ትምህርት እያገኘንበትም ነው በርታ፡፡

  ReplyDelete
 6. hi dani 10Q very much for ur interesting idea.Go ahead teaching the generation!!!

  ReplyDelete
 7. Good one!
  "When money speaks, truth keeps silent." Say the Russians.
  "The pure and simple truth is rarely pure and never simple." Truth demands price...But it is always prudent to speak the truth and react accordingly to avoid any later regrets. What ever goes wrong, an honest person has nothing to fear.Life gets meaning if we dwell in truth and in what we believe.
  Speak the truth and sleep well...avoid sleeping pills.

  Egziyabher yistlen Daniel!

  ReplyDelete
 8. dani ebakh yene jegna tsefew

  ReplyDelete
 9. hi dani please post yenejegnaand all works thank you.

  ReplyDelete
 10. Ummm.
  Pilatosim huket endijemer enji andach endayireba baye gizie wuha ansito
  ENE KEZIH TSADIK SEW DEM NITSUH NEGN, ENANTE TETENKEKU SIL BEHIZBU FIT EJUN TATEBE. HIZBUM MELSEW DEMU BEEGNA ENA BELIJOCHACHIN LAY YIHUN ALU
  yematewos wengel 27:24

  ReplyDelete
 11. wey Dn. Daniel,
  Now you told me who I am , and asked me to ask my self where I am going and how?

  Ebakih Tsafilign... Enanbib.

  Egziabher Betesebihin Yibarkilih,

  ReplyDelete
 12. A good lesson as usual from our Brother, Dn Daniel!

  By the way, did I learn at church that Pilatos ended being a Martyr to his Christianity? It is at least good that he learnt from his mistakes and paid the sacrifice.

  MELKAM SEMUNE HIMAMAT
  HGEORGIS

  ReplyDelete
 13. Kale Hiwot Yasemalin!

  ReplyDelete
 14. this is what we all should do. most of the time we prefer to speak only to live for today but as time goes our speech will be headache for our self. why we should not have our own satnd always. most of the time we want to blow to wards the good for today. but we will never be beneficiary for tommorow. ‹ጥርሱ እየበቀለ፣ ፀጉሩም ብቅ እያለ› ...yea when things come to the truth we will suffer alot. please we we speak about some thing let us judge our selve first. any one who can speak the truth may be ignored with other for the time but nevere fails. for this Daniel kibret is my hero. he write always what he belives. he is accused for what he write,specially about tehadiso in harar. i always hear the comment of the people about him until now (b/c i was in harar for six years even though i am not there now.)THEY dislike him in early time for what he wrote. but those who was against him are now wondering him for what he did. they know now it was true.it is not fictious. so let us judge things before speaking,if it it is true don't afraid to speak...EWNETINA ena NIGAT EYADER ...YIBAL YEL

  ReplyDelete
 15. This comment has been removed by a blog administrator.

  ReplyDelete
 16. the last anonymous i don't know what you want to write. ምን አልባት ለመቀለድ ወይም ለመሳደብ ምትናገር ይመስላል። ማንንም ኦርቶዶክሳዊ ድንግል ማርያም ፈጠረችጝ አይልም ስለዚሀ ለማለት የፈለከወን ነገር በግልጥ ብትናገር መልካም ነው። ደግሞ ዳንኤል ኢየሱስ ጌታየ አምላኬ መድሃኒቴ የሚሉትን ያባርራል ያለህ ማነው.please when we try to comment be reasonable, don't be only negative thinker and posting only something we heard. we should know what to speak and write.ተምሬአለሁ አወካልሁ ክሚል ትውልድ አይጠበቅም። we should have proof for all things we speak. any ways ክፉ ከመናገር እግዚአበሔር ይጠብቀን።

  ReplyDelete
 17. dear the last anonymous,please leave the blog and write on other blog

  ReplyDelete
 18. Last Anonym,
  Dingil Maryam Alfeterechwumna, do not say like that. Getchin Fetrotal.... Sirwun gin ahunim yibarkilet

  ReplyDelete
 19. You are correct doing what you promised is difficult unless you never said hesitate. Especially in Ethiopia every institutions /political party, religious institution and almost every one/ say what they want to say to get the attention of the people. But they are not respect their promise and even they didn’t approach to their promise .at least pilatos feel bad thing about his incorrect decision but I don’t think that our institution feel what they are doing because 'who cares and who is going to ask them' if you say his/her mind. I assure you that all of them have already lost their mind.
  That is good topic Brother:
  Pilatos
  berta wendmachen ataqemama atafegfeg wedfit ketil
  happy easter lehulachen

  ReplyDelete
 20. i loved it Dani...a lot. this specially should be dedicated to all "Churches" in America.

  ReplyDelete
 21. The Last "Anonymous"(the one commented before me) What are you you talking about??? Are you relealy know True Jesus Christ. Based on your comment I don't think you know Jesus or His Mother. Sorry if I offended any body.

  To Dn. Daniel please keep it up. God bless you

  ReplyDelete
 22. always like ur view & z way u use stories(from everywhere) to pass ur idea. bertalign Dani

  ReplyDelete
 23. Opsssssss..., yehe bene leke yetesefa tsehufe mehone alebete!!! I know it all size fit, interesting write-up and that is why I like your blog. Because you are not afraid of reminding me who I am? It is true the world is full of Pilothouse and I am one of them!!!! Geta hoye ye'abatochene qorate lebe setegne ebakehe??? Be be'ementena ena be'metamane yatsenane!!!

  ReplyDelete
 24. dear damiel

  sirah enditkeber adrgohal ahunm kiber yemerkeb gazeta azegaj kinat endih endemiyadergew yetaweke new daniel minim hone bilo bitsef manim aysemawim egiziabhern enji sewn anamelkim dani amlk keante gar yehun dingle mariyam bemiljaw atleyeh.betekirtiyanachenen titebikelin amen.

  ReplyDelete
 25. Erimat? ኢየሱስ ክርስቶስን ገርፌ ልስቀልላችሁ›› ????

  ReplyDelete
 26. Correction on!!!
  ኢየሱስ ክርስቶስን ገርፌ ልስቀልላችሁ›› ???

  ReplyDelete
 27. SELAMAWI

  በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

  ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ጸጋና ሰላም ይብዛልህ መናፍቃን በየአቅጣጫው ስለነሱ የሚጻፉትን ጽሁፎች እየተመለከቱ ሁሉንም አንተ እንደምትጽፍባቸው በመገመት ሁሌ ሲኮንኑህ እንሰማ እናይ ነበር አሁን ግን በፊት ለፊት የምትገኝበት አደባባይ ፈጥረህላቸዋል አሁን እውነተኛ የሆነ ሁሉ ጥያቄውን ማቅረብ ይችላል ስምን እየደበቁ መሳደብ ግን የሰይጣን ስራ ስለሆነ ከመንፈሳዊ ሰው አይጠበቅም የሰላም አምላክ ሰላሙን ይስጠን
  ወልደ መድህን

  ReplyDelete
 28. kalehiwot yasemalign wudu ethiopiaw

  ReplyDelete
 29. ebakih Dani, ene jegna yemhonibetin mistir tsafilign. be'DINGIL' gebremikael@ymail.com

  ReplyDelete
 30. ነገር ግን ‹‹ከጣሊያን የምናገኘው ጥቅም ይበልጥብናል›› ብለው ባይዘምቱ ኖሮ ታሪክ በተቀየረ ነበር፡፡ ታዲያ ዛሬ እነዚያ ዘማቾች ያልዘመቱበትን ምክንያት ቢያስረዱን እንኳን የዐድዋን ድል ሊተካው አይችልም፡፡ህሊና....በቻ ዘም በሉ መደመጥ በበዙ መልኩ ይሻላል..የተባለዉ ነገረ አወነት ነዉ በ የመስረቤቱ እኮ ሰንተ ሰዉ ነዉ የመይመሰል ሰራ ከአቀሙበላየ...የለአገባበብ ሲተዘዘና ሰበዘበዝ የሚኖረዉ ቀ እኔም አንዱ ነኝ..የህ ሁሉ...ለመኖር ሲል...የሚያደረገዉ ቢሆንም..ሰወችም አንደንዴ ከለመደከበት ወትሀ ነሮ ነረ በትለዉ...

  ReplyDelete
 31.  እንግዲህ የሰዉ ማንነት የሚፈተነዉ በዚህ ግዜ ነዉ!! እንደዚህ አይነት ሰዎች ፍሬዉ በእሾክ መሀል ወደቀ የተባለላቸዉ ጋር እነንመደብ ይሆነንን!!

  ReplyDelete