Wednesday, March 24, 2010

ለምጣዱ ሲባል

በትግራይ የሚነገር አንድ ብሂል አለ፡፡ አንድ ባል እና ሚስት አንዲት ትንሽ አይጥ አስቸገረቻቸው፡፡ አንድ ቀን ባል እና ሚስቱ ዱላ ዱላቸውን አንስተው የቤቱን ዕቃ ሁሉ ገልብጠው አይጧን ማሳደድ ጀመሩ፡፡ በዚህ ሲሏት በዚያ፣ በዚያ ሲሏት በዚህ ብዙ እያለች በጣም አደከመቻቸው፡፡ በመካከሉ ሚስቲቱ አይጧን ስታባርር አይጧ ዘልላ ምጣዱ ላይ ወጥታ ቁጭ አለች፡፡ ሚስቲቱም የሠነዘረችውን ዱላ ወደ ኋላ መልሳ፣ አይጧን በአግራሞት ማየት ጀመረች፡፡ ባልዋም የሚስቱን ሁኔታ ተመልክቶ «ምነው ትቆሚያለሽ አትያትም ወይአላት፡፡ ብልኋ ሚስትም «መምታቱ አቅቶኝ አልነበረም ነገር ግን «ምእንቲ ምጎጎ እታ አንጭዋ ትሕልፍ» አለችው ይባላል፡፡ «ስለ ምጣዱ ሲባል አይጧ ትለፍ ብዬ ነው» ማለቷ ነው፡፡


ለዚያች እናት ምጣዱ የትዳሯ ትልቁ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ እንዲህ እንደ ዛሬ እንጀራ ተገዝቶ መበላት ሳይ ጀምር በፊት ያልጋገረ ሰው እንጀራን አያገኘውም፡፡ ከዚያውም በላይ ደኅነኛ ምጣድ ከገበያ እንደ ልብ አይገኝም፡፡ ቢገኝም ማሟሸቱ ብዙ ሞያ እና ድካምን ይጠይቃል፡፡ እናቶቻችን ወዝ የለመደ ምጣድ የሚሉት አላቸው፡፡ የጋጋሪዋን ወዝ የለመደ፣ ጋጋሪዋም ጠባዩን የለመደችው ምጣድ ማለት ነው፡፡ እንዲያውም እንዲህ ያለው ምጣድ የትም ስለማይገኝ ለድግስ ሥራ ሲጠሩ የራሳቸውን ምጣድ ይዘው ሄደው የእነርሱን ድርሻ በለመዱት ምጣድ የሚጋግሩ እናቶች ነበሩ፡፡ አሉም፡፡ ለዚህ ነው ያቺ እናት «ምእንቲ ምጎጎ እታ አንጭዋ ትሕልፍ» ያለችው፡፡

ገበሬ እንኳን እርሻውን ሲያርም ሁሉንም ነገር አያርመውም፡፡ አንዳንዱን አረም ተስማሚውን ጊዜ በመፈለግ ያልፈዋል፡፡ አንዳንዱ እንደ እንክርዳድ ያለው አረም ከእህሉ ጋር ሥር ለሥር ይያያዝና ለእርማት ያስቸግራል፡፡ አንዳንዱም በጣም ጥቃቅን አረም ከመሆኑ የተነሣ ያንን አረም በማረም የሚፈጀው ጊዜ አረሙ ቢታረም ከሚያስገኘው ጥቅም ስለሚበልጥበት ይተወዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ዋና ዋናውን አረም ያርምና ያንን ያልፈዋል፡፡ የማሳ እና የሰው ንጹሕ የለውም ነውና የገበሬው ብሂል፡፡ እንክርዳዱን እንነቅላለን ስትሉ ስንዴውንም አብራችሁ እንዳትነቅሉት እንደተባለው፡፡ እንዲህ ያለውን አረም ከእህሉ የሚያስወግደው በመከር ጊዜ እያበራየ ነው፡፡

በትዳር ውስጥ ያሉ ባል እና ሚስት ትዳራቸውን አጽንተው ለመኖር ከፈለጉ ከሌሎች ብዙ ነገሮች ጋር ሊከተሉት የሚገባው ነገር አንዱ «ምእንቲ ምጎጎ እታ አንጭዋ ትሕልፍ» የሚለው ነው፡፡ የተጋቡት ሰዎች ፍጹማን እና እንከን የለሾች አይደሉም፡፡ በእያንዳንዷ ስሕተት እና ጉድለት ላይ በመነታረክ፣ እያንዳንዷን ጥፋት እየቆጠሩ ነጥብ በማስቆጠር፤ ትዳርን አጽንቶ ማኖር ከባድ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለምጣዱ ሲባል አይጧን ማሳለፍ የሚገባበት ጊዜ አለ፡፡ ሰው በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚሠራው ይሳሳታል፡፡ ዐውቆ የሠራውን በተግሳጽ ሳያውቅ የሠራውን ግን አሳልፎ በመነጋገር መፍታቱ የተሻለ ነው፡፡

በተለይም ሰው በተሳሳተበት ጊዜ ቢነግሩት የማይሰማቸውን ጉዳዮች አውለው አሳድረው ፣ነገር አብርደው እና ዘና አድርገው ቢነግሩት ነጠብጣብ እንደ ወረደበት መሬት በሚገባ ይቀበለዋል፡፡ እሳትን በእሳት ማጥፋት፤ ውኃንም በውኃ ማቆም አይቻልምና፡፡ ትዳርን ያህል ትልቁን ምጣድ ላለመስበር ሲባል ሊያልፉ የሚችሉትን ትናንሽ አይጦች ማሳለፍ ይገባል፡፡ ምክር የሚፈታው ችግር አለ፡፡ ተግሣጽ የሚፈታው ችግር አለ፣ ማሳለፍ የሚፈታውም ችግር አለ፡፡ አይጧን የሚያመጣውን ጉዳይ ሳንፈታ ወደ ቤት የሚመጡትም አይጦች በመግደል ብቻ አይጦችን ማጥፋት አይቻልም፡፡

እንኳንስ ዐዋቂዎቹ ባል እና ሚስት ቀርተው ሕፃናትን እንኳን በየአንዳንዱ በሚያጠፉት ጥፋት የምንናገራቸው ከሆነ ይደንዛሉ እንጂ አይሰሉም፡፡ በየደቂቃው የምትጠጣ ነጠብጣብ ውኃ ጥም እንደ ትቆርጠው ሁሉ በየደቂቃው ተው፣ እረፍ፣ እንዲህ አድርግ፣ እንዲያ አታድርግ፣ እያሉ መናገር ልጅን አያርመውም፡፡ አባቴ ልማዱ ነው፣ እናቴም ልማዷ ነው እያለ ሰምቶ እንዳልሰማ ያልፈዋል እንጂ፡፡

ዐፄ ቴዎድሮስ ደብረ ታቦር ላይ ቆመው እያሉ አንድ ገበሬ ሰክሮ በአጠገባቸው ያልፋል፡፡ ያም ገበሬ ወደ ንጉሡ ጠጋ ይልና «በቅሎው ይሸጣል» ይላቸዋል፡፡ የዐፄ ቴዎድሮስ ጋሻ ጃግሬዎች እነ ገብርዬ ሰይፍ መዝዘው «እንዴት ንጉሡን በድፍረት ይናገራል፤ እንበለው» አሏቸው፡፡ ንጉሡም ትእግሥት አድርገው «ተውት፣ ይሂድ፡፡ ነገር ግን የሚገባበትን ቤት ተከታትላችሁ ተመልከቱት አሏቸውና ተከታትለው ተመለከቱት፡፡

በማግሥቱ ያንን ሰው ንጉሡ አስጠሩት፡፡ እየፈራ እየተንቀጠቀጠ መጣ፡፡ «ትናንትና እነዚህ ሁሉ ሰዎች ባሉበት በቅሎዬን ለመግዛት ጠይቀህ ነበርና እንድንስማማ ነው ያስጠራሁህ» አሉት፡፡ ሰውዬው ግን ማመን አልቻለም፡፡ የንጉሥ በቅሎ፣ ያውም ታጠቅ የተባለውን የዐፄ ቴዎድሮስን በቅሎ ለመግዛት የምጠይቅ እኔ ማነኝ ብሎ ደነገጠ፡፡ «የለም ንጉሥ ሆይ እኔ ብቻዬን ሆኜ እንዲህ ያለውን ሃሳብ አላስበውም፡፡ ይህንን ጥያቄ ያቀረብነው ከጓደኞቼ ጋር አብረን ሆነን ነውና ከእነርሱ ጋር ተማክሬ መልስ ልስጥ» ብሎ ጠየቀ፡፡

ንጉሡም «ትናንትና ስናይህ ብቻህን ነበርክ፡፡ ሌላ ጓደኛ አልነበረህም፡፡ ከየት አምጥተህ ነው የምትማከረውሲሉ ገርሟቸው ጠየቁት፡፡ ያም ገበሬ «ንጉሥ ሆይ አላዩዋቸውም እንጂ አብረውኝ እነ ብቅል፣ ጌሾ፣ እነ ደረቆት፣ እነ ጠጅ፣ እነ ጠላ፣ እነ አረቄ ነበሩ፡፡ እነርሱ በሌሉበት ይህንን ነገር ብቻዬን አልናገረውም» ብሎ አሳቃቸው፡፡ ንጉሡም በአነጋገሩ ተገርመው ምሕረት አደረጉለት ይባላል፡፡ ለዚህ ነው ለምጣዱ ሲባል አይጧን ማሳለፍ የሚጠቅመው፡፡ ያንን ድፍረት የደፈረው ገበሬው ብቻውን አይደለም፡፡ እነ አረቄ፣ ጠላ፣እና እነ ጠጅ ናቸው፡፡ ስለዚህም አይጧን ከምጣዱ ለይቶ መምታቱ መልካም ነው፡፡

ሰዎች በማኅበርም ሆነ በድርጅት፣ በኮሚኒቲም ሆነ በፓርቲ ለአንድ ዓላማ፣ በተወሰኑ መሠረታውያን ነገሮች ላይ ትስማምተው አብረው ይሠራሉ፡፡ ሰዎች አብረው ለመሥራት በሁሉም ነገር ላይ የግድ መስማማት የለባቸውም፡፡ ሌላው ቀርቶ በአንድ ቤት፣ አንድ አካል ሆነው የሚኖሩት ባል እና ሚስት እንኳን በመሠረታውያን ነገሮች ላይ እንጂ በሁሉም ነገሮች ላይ መስማማት አይችሉም፡፡ ሁለት ከመሆን የተነሣ የሚመጡ ልዩነቶች አሉና፡፡ ቢያንስ በምግብ ምርጫ ሊለያዩ ይችላሉ፡፡

እነዚህ ማኅበራት፣ ተቋማት፣ ድርጅቶች እና ፓርቲዎች አንዳንድ ጊዜ ለምጣዱ ሲባል አይጧን ማሳለፍ አለባቸው፡፡ በትንሽ በትልቁ በመጨቃጨቅ እና ባለመስማማት፣ በሆነው ባልሆነው በመለያየት እና እንደ አሜባ በመከፋፈል ምጣዱን የሚሰብሩት ከሆነ በውኑ ይህች ሀገር ተስፋዋ ምንድን ነው? ሰዎች ሲሠሩ ይሳሳታሉ፡፡ ከዕውቀት ማነስ ይሳሳታሉ፣ ከመቸኮል ይሳሳታሉ፣ ትክክለኛ ነገር የሠሩ መስሏቸውም ይሳሳታሉ፡፡ ማናቸውንም ዓይነት የሰዎችን ስሕተት ለመታገሥ የማንችል ከሆነ ሰዎችን የሚያሰባስቡ ተቋማትን መመሥረት የለብንም ማለት ነው፡፡ እናም መጀመርያ እኔ በእነርሱ ቦታ ብሆን ኖሮ ምን አደርግ ነበር? ብሎ ራስን መጠየቅ ቀጥሎም፣ ልናልፈው የሚገባንን ነገር ልንናገርበት እና ልንከራከርበት ከሚገባን ነገር ለመየት አለብን፡፡

አካሄዳችን እና እርማታችን ዋናው ዓላማው ያቋቋምነውን ድርጅት፣ ማኅበር፣ ፓርቲ፣ ተቋም ማነጽ፣ ማጠናከር፣ እና የተሻለ ማድረግ ከሆነ ማናቸውም ነገራችን ምጣዱን የማይሰብር መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ያለበለዚያ ግን አንዳንድ ጥቃቅን የስሕተት አይጦችን እናጠፋለን ብለን የደከምንበትን፣ ስንት ወዝ እና ልፋት የፈሰሰበትን፣ ስንቶች እንደ እሳት ነድደው ያሟሹትን፣ የስንቶች ድካም እና ሞያ የፈሰሰበትን፣ምጣድ መስበር ይመጣል፡፡

ዛሬ በታላላቅ ቤተ እምነቶች የምናየው ጠባይ ለአይጧ ሲባል ምጣዱ ይሠበር የሚል የሞኝ አሠራር እየሆነ ነው፡፡ አይጧን ከምጣዱ ለይተው መምታት አቅቷቸው ለብዙ ዓመታት የተደከመባቸው ትልልቆቹ ምጣዶች እየተሠበሩ ነው፡፡ ያች ገበሬ እናት ትእግሥትን ገንዘብ አድርጋ፣ ለትልቁ ምጣድ ሲባል እስኪ ለጊዜው አይጧን ላሳልፋት ያለችው አይጧ ታስፈልጋለች፣ችግር አትፈጥርም፣እያደረገችው ያለው ነገር ትክክል ነው፣ ቤቱን ማውደሟ፣ ያልለፋችበትን ነገር መብላቷ፣ ቀበኛ መሆንዋ ተገቢ ነው፤ በዚህ ሁኔታም መኖር አለባት ብላ አይደለም፡፡ ምጧዷን አትርፋ አይጧን ብቻ የምትመታበትን ተስማሚ ጊዜ ለማግኘት እንጂ፡፡ በአንድ ጊዜ ሁለት ጥፋት ላለማጥፋት፡፡

የሃይማኖት አባቶች የዚህችን እናት ጥበብ እና ብልሃት ዛሬ ከወዴት ባገኙት?

የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት አንግበው የተነሡ ኃይላትም ኢትዮጵያን ያህል ብዙ ትውልድ ደክሞ ያሟሻትን ምጣድ፣ ስንቶች እንደ እሳት የተማገዱባትን ምጣድ፣ ስንት የማንነት፣ የታሪክ፣ የባህል፣ የቅርስ፣ የእምነት እና የወግ እንጀራ ሲጋገርባት የኖረችውን ምጣድ፤ እናጠፋቸዋለን ብለው ለሚያስቧቸው አይጦች ሲባል እንዳይሰብሯት መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ሀገር ከፖለቲካ አመለካከት፣ ከርእዮተ ዓለም፣ ከፍላጎት፣ ከአስተሳሰብ እና ከምኞት ሁሉ ትበልጣለች፡፡

የችግር፣ የኋላ ቀርነት፣ የግፍ፣ የጭቆና፣ የመብት ረገጣ፣ የፍትሕ ማጣት፣ የእኩልነት ማጣት፣ የሰብአዊ መብት ማጣት የምንላቸው አይጦች መጥፋት አለባቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ለዕድገታችን ዕንቅፋቶች፣ለኋላ ቀርነታችን ምንጮች መሆናቸውን የሚክድ የለም፡፡ መጥፋት የለባቸውም ብሎ የሚከራከርም የለም፡፡ ነገር ግን ምጣዱ ሳይሰበር መሆን አለበት፡፡ እነዚህን አይጦች እናጠፋለን ብለን ዛሬ ከአንዳንድ ኃይሎች ጋር የምንመሠርተው ግንኙነት፣ የምንፈጥረው ኅብረት እና የምንዋዋለው ቃል ኪዳን አብሮ ምጣዱን የሚሰብር እንዳይሆን ደግሞ ደጋግሞ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡

በታሪካችን ውስጥ ያለፍንባቸው ብዙ አሳዛኝ እና ክፉ ነገሮች አሉን፡፡ እነዚህን ዛሬ ሁላችንም የምንጸየፋቸውን እና እንዳይደገሙ የምንታገላቸውን የትናንት ጠባሳዎች ለማረም የምናደርገው ሂደታችን አይጧን በማጥፋት ሰበብ ምጣዱን የሚሰብር እንዳይሆን ጥንቃቄ ያስፈልገናል፡፡ ሰው ጠባሳውን አጠፋለሁ ብሎ ቆዳውን አይልጥም፡፡ የሀገሪቱን አንድነት፣ የሕዝቦችን በተዋሕዶ እና በተገናዝቦ መኖር፣ የነገን አዲስ ራእይ እና የትውልዱን የወደፊት ጉዞ የምንጋግርባትን ኢትዮጵያ የምትባለውን የተሟሸች ምጣድ፣ እዚህም እዚያም የሚያስቸግሩንን እና አንዳንድ ጊዜም ልናልፋቸው የሚገቡንን አይጦች በማጥፋት ሰበብ መስበሩ ለጫማ ሲባል እግርን እንደመቁረጥ ያለ ነው፡፡

እናም እስኪ አንዳንድ ጊዜ «ምእንቲ ምጎጎ እታ አንጭዋ ትሕልፍ ለምጣዱ ሲባል አይጧ ትለፍ» እንበል፡፡

61 comments:

 1. +++
  ውድ ዲያቆን ዳናኤል

  ለረዢም ጊዜ «ምናለ ዳንኤል ይህንን ነገር ቢያደርግ» እያልኩ ስመኘው የነበረውን ነገር ዛሬ አድርገኸው በማየቴ በጣም እጂግ በጣም ደስ ብሎኛል። «የእነ እገሌም አለ ገና» እያልኩ የምጠብቃቸው ሌሎች ሁለት ደግሞ አሉ፤ አንድ ከአውሮፓ አንድ ከአሜሪካ።

  መድኃኔዓለም ብርታቱን ይስጥህ! መስጠትስ ሰጥቶሃ ያጽናልህ

  ሠናይ

  ReplyDelete
 2. I always enjoy reading your articles. And now, you have taken yet a step ahead to start blogging. It is great. And I look forward to reading more of your pin-pointing ideas and comments.
  Yeah, it is real. We Ethiopians didn't get it. Or I should say we are losing it. We don't entertain other people's ideas that don't resemble ours. Even worse, we tend to hate people who happen to think differently than we do. If only we knew, the advanced world is shaped by ideas fighting against each other not people fighting one another.

  ReplyDelete
 3. 10q daniel u and your fan become connect tanks for technology

  ReplyDelete
 4. As usual this is full of wisdom with an incredible flow.... I can only say "Amen". Thanks Dani, the Master Thinker of Ethiopian Social Discourse.

  ReplyDelete
 5. lib lemil Ejig astemari new.

  yerasihim mekane dir lemekifet bemechalih betam des bilonal.

  Egziabher abizto yibarkih!!

  ReplyDelete
 6. +++
  Dear Dn.Daniel,
  Wisdom is from God and I can say He gave you that so that people could change their attitude and be positive and courageous.
  We have so many mystereous sayings and tales in our Country which could be preached or taught for our spiritual as well as social life. That is what you are doing. Keep it up and pray to God so that He continues to grant you the wisdom.

  May God be with all of us.

  ReplyDelete
 7. ከወልደ ሲራክ
  መልካም ጅምር
  በእውነቱ እጅግ በጣም ደሰ የሚል ጅምር ነው በቅን ልቦና እና መንፈስ እውነትን ለሚፈልግ ስው እንደዘህ ያሉ በሀገር በባህል በትውፊት በእምነት እና በፖለቲካ እንዲሁም በማኅበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የእብረተሰባችንን አመለካከት ወደ አንድ መንገድ ለማቀራረብ የተለያዪ ሰዎችን አመለካከት ለማስማማት እንድችል በህውቀታቸቀው ለሀገራቸው ፍሬ ሊያፈሩ የሚችሉ ለወገን የሚጠቅሙ ዛሬም እንደጥንቱ አባቶቻችን ተአምር መስራት የሚችሉ የብዙ ምሁራን መፍለቂያ ሀገራችንን የወላድ መካን ከመሆን ለታደጋት የሚችል እውነተኛ ትውልድ ለማፍራት አቅጣጫን ለማመላከት ይረዳል እና ልዪነታችን ውበታችን ውበታችን ንድነታችን ስለሆነ የሁሉንም ምልከታወዎችን ማሰቃኘት ወደ ተሻለው ወደ እውነተኛው መንገድ ያመራል እና ሁላችንም የምንናፍቃት ሰላም የሰፈናባት መቻቻል የነገሰባት ወድቷ ሀገራችንን ለማየት እንዲያበቃን እየተመኘው አዘጋጁን ዲ.ዳንኤል ክብረትን ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን ሳቀርብ ፍጻሜውን እዲባርከልን ምላካችን ይርዳን

  ReplyDelete
 8. I was asking my self all the time "why he don't have wave site?" not only you ephrem,....finally you did it is very very interesting bcos right know to many ppl using nternet so they have chane to read your articles.Remenber,how many ppl have chance to get news paper,book,pamplate etc this is very easy wsy i need to say a lot but this is enough.I said good job Daniel!!!
  Mar/24/10 W.DC wendemu

  ReplyDelete
 9. Egzer Yatsnahe!!!

  ReplyDelete
 10. Wey Dn. Daniel,
  This was what I was looking...
  You know what I will not forget your Sibketoch I attended back home 14 years back. at AAU Now I need that to attend again, and again and again through this enabling tech.

  ReplyDelete
 11. I am always interested to read your articles; keep it up bro. May God be with you all the time! Amen.

  Kassahun

  ReplyDelete
 12. Dear Dn. Daniel.
  I thank to GOD who gave you His wisdom to teach us.I appreciate you effort to reach ur ppl through web again.May the help of GOD with you always.Beside spiritual books,it was Addis Neger that enables us to share your smart ideas.
  In the internet few of the society can get u.
  think of how to reach the mass(who couldn't get internet access).
  Thank you brother.

  ReplyDelete
 13. each and every articles u used to write @ Addis Neger, The most prominent independent newspaper, were awsome beyond giving lessons. Keep on enlightening and giving us lessons. thank you and God bless you

  ReplyDelete
 14. Gudd new..... beEnglizegna new eshi?!! belela sew "blog" siyamuh yeneberu ahun bante "blog" memtatachew ayikerim. Ahun fetena kehone Fetari yaberitah... Hulu lebego silehone Berta.

  Amlake Kidusan Tsinatun yistih, adera Tsihufih endayikomibin tadiya. .....Jemiro kere endayibal.

  D keAmerica.

  ReplyDelete
 15. Of course there are many silly mistakes and troubles (‘rats’) that we face in our day to day life. Some (little foxes) has a huge impact when repeated and it may be costly to ignore them. But as Dn. Daniel explained it well, we should calculate its risk (breaking the ‘mitad’) which is more serious than the small foxes. We have to be patient to set the right time & place for tracking the rats. How many small assignments (political, social, religious…) that should have to be solved at the right time and place have blown to the public unnecessarily and become unfair hot issues? Many! Sadly most of them for the sake of dignity and personal benefits and that competition left a wound on the ‘mitad’.

  There are also some ‘mistakes’ made in the past and now there are groups who tried to break their ‘mitad’ which are also our ‘mitad’ whether we like it or not. All in all we should care for the big ones and there is a famous quote of Pope Shenouda that goes something like: "You can't stop a bird from flying over your head, but you can stop it from making a nest there." Let us all stand for resisting the nest rather than complaining for the flying.

  I hope I have read it in Addis Neger but it is new again and a good lesson for every one of us.

  ReplyDelete
 16. I am so HAPPY to see that you have a blog! I always enjoy reading your articles. God Bless you!

  ReplyDelete
 17. እግዚአብሔር ስራህን ይባርክ፡ ለፍሪም ያብቃልህ::

  አንባቢዎችህ አዲስ ነገር ማውጣትህን በቀላሉ እንድናውቅ ጹሁፎችን ወይም አዲስ ጹሁፎችን እንዳወጣህ የሚገልጽ ነገር በፌስ ቡክህ ላይም ብትጨምር መልካም ነው።

  አሁንም እግዚአብሔር ዕውቀቱን ያብዛልህ::

  ReplyDelete
 18. Dn Danel,

  Egziabher Kebetsebk gar birtata yisth, I will join you soon , in other corner,

  ReplyDelete
 19. Dear D/n Daneale
  I am very happey b/c of you i think now we can do every thing i pray for you always pleas be strond, and you can do lot of thing more than our bishop's!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 20. Dear Dani,

  Egziabhere yetebeqeh Tsinatun yesteh. Lerejim ametat yenafekut negegerh tawesegn............. Ye sidist kilo gibi gubae, Ye entoto Raguel guzo, lelochum. Berta wondeme. Yequrte qen lij mehone yasfelegal. Ethiopia ena betekrstiyan endezih aynet jegnoche yasfelguachewal. Ayzohe ke ante gar yalut ejig bizu nachew.

  H.

  ReplyDelete
 21. Kale Hiwot yasemalin Dn Daniel...lebelete ageliglot yazegagih !!

  ReplyDelete
 22. I wonder when I got your profile message. MAY GOD BLESS YOU DANI, to keep it up more and more.
  Melkam mistrawi megeletochn eyengerken edmehn lebelete ewket Egziabher abzto yist'h.
  Enkye K.

  ReplyDelete
 23. Nice to get this. Lets use it for good. Can every body of us think what is expected from us. We shouldn't only appreciate once job. do your own best that is how we can make changes in our church and country. Thank u Dani. You showed us many ways.

  ReplyDelete
 24. Great Job Danie!It is what we was seeking for a long time.

  ReplyDelete
 25. Selam Dani,

  Melkam gimaro newu ... please keep it up! God will also help you. Ya-hulgizie yemtamnew yeabatoch tselote yetebikh...

  By the way, could you post your articles from "addis Neger" here? pls do it if it's possible and when you have the chance to do so... As you see from those comments, people will expect more and you might not have enough time to satisfy them. Besides, it’s a good idea to make your wooonderful ideas accessible anytime...

  Pls, therefore, post one by one, but frequently, from your archives. Will wait "benafkot" to read those woooonderful ideas....May God bless you!

  ReplyDelete
 26. Like Dn Daniel, I hope to read articles of Abiy, Mesfin and Tamrat on the internet.

  ReplyDelete
 27. It's my first time to visit your web...
  would you tell me what the eagle mean there?
  Thanks

  ReplyDelete
 28. according to our traditional commentaries, eagle can see every small particles up from the sky. it is the symbole of seeing things critically.
  daniel kibret

  ReplyDelete
 29. Ejig tiru Jimer new Dani, It is what we was seeking for a long time.

  ReplyDelete
 30. ለምን እንደሆነ ባላውቀውም ፍርሃት ፍርሃት ይለኛል!!!

  ReplyDelete
 31. it may be good but not as earlier time for the church. now you start writing politics also,which is not good for others not onlu for you. i think you are understanding what i am talking.

  ReplyDelete
 32. ዳኒ
  እጄ ላይ ገብተው ያነበብኳቸውን ጽሑፎችህን በሙሉ እወዳቸዋለሁ:: ትምህርቶችህንም ጽሑፎችህንም በጣም እወዳቸዋሁ::ዛሬ በራስህ የጡመራ ገጽ ላይ ስላግኘውህ ተደሰትኩ !!!!
  በርታ!
  ልዑል እግዚአብሔር ያበርታህ !

  ReplyDelete
 33. ዲ.ዳንኤል
  አሁን በጀመርከውም ሆነ ከዚህ ቀደም በሰራሀቸው ስራዎች ብዙ ቁምነገርን አግኝቻለሁ።"መማር(ማወቅ) ለሚፈልግ ሰው" ብዙ ቁምነገር አላቸው።
  መልካም ነገር ሁሉ ከእግዚአብሔር ነውና በጸሎት እየበረታህ እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚለውን ማስተላለፍህን በትጋት ቀጥል።እግዚአብሔር ሕዝቡን ለዘለዓለም አይረሳምና ሁላችን እግዚአብሔር ይምረን ዘንድ በጸሎት እየተጋን በእውቀት እንደግ!

  ReplyDelete
 34. Danel,

  I am pleased to see your work on the web. I enjoy reading your articles very much. If you are kind enough to consider, I have three suggestions to forward:

  1. Please consider posting some of your articles that you wrote in Addis Neger Newspaper in this blog . It would be helpful for many people that don’t get a chance to read them (Especially those living abroad).
  2. Invite some other writers with the same caliber and attitude like yours to write in this blog. It may make your blog more interesting and various ideas may be entertained that in turn help in reaching different audiences.
  3. As much as possible keep please focus on the social, cultural and economic issues of our country(as you usually do) it is an area that barely discussed in both electronic and print media of our country unlike sport and politics.

  I know I am nobody to suggest this for a wise man like you but I feel it is something important.

  Thanks

  Henok B.

  ReplyDelete
 35. Danel,

  I am pleased to see your work on the web. I enjoy reading your articles very much. If you are kind enough to consider, I have three suggestions to forward:

  1. Please consider posting some of your articles that you wrote in Addis Neger Newspaper in this blog . It would be helpful for many people that don’t get a chance to read them (Especially those living abroad).
  2. Invite some other writers with the same caliber and attitude like yours to write in this blog. It may make your blog more interesting and various ideas may be entertained that in turn help in reaching different audiences.
  3. As much as possible keep please focus on the social, cultural and economic issues of our country(as you usually do) it is an area that barely discussed in both electronic and print media of our country unlike sport and politics.

  I know I am nobody to suggest this for a wise man like you but I feel it is something important.

  Thanks

  Henok B.

  ReplyDelete
 36. Sintayehu/chebuda/March 26, 2010 at 4:21 PM

  ohhhh its good idea and gerat work we will excpect more and more coz dis is daneil
  dont give up dear

  God belss u and ur family

  ReplyDelete
 37. Great article! God be with you.

  ReplyDelete
 38. This is you job. You got it.
  Yours

  ReplyDelete
 39. It is an article which catches my attention until I finished it. We have lots of proverbs which express powerful messages within a single phrase. Dn. Daniel draw our attention to one of them, it is a wonderful start and may God give you the strength to keep it up. I believe you will show us how our similarities outweigh our differences, a point nowadays we all fail to notice. I am looking forward to read your next article.
  Cher yakoyen

  ReplyDelete
 40. wow! Finally, we got you here! Thank you for Technology. Particularly me, I am eager to read more religious and cultural views from Ethiopia.
  I called you "Ager bekel Ethnographer!" Keep it up!

  afomia

  ReplyDelete
 41. ቆንጆ ታሪክ እና ትምህርት ነው። አመሰግናለሁ

  ቶቶ አደፍርስ

  ReplyDelete
 42. Finally you did it. Thanks God. Keep it up.

  ReplyDelete
 43. I’m so happy to find your article hear in your blog. Please keep continue I wish God be with U.

  ReplyDelete
 44. serk
  Daniel thank you much for all your work. i am learinining a lot of things from each of your article and preching. i'm knoking my self to weak up for a change. We are very bless to have you us brother. god bless you forever!!!!!

  ReplyDelete
 45. AgnaTi'wos Zegascha'April 16, 2010 at 10:22 PM

  Dn.Daniel, what you have written about "Columbus's dicovery of america" and the definition of discovery is a very interesting and broad idea. There is nothing new dicovered after it was created by God once in the begining. Therefore, your article will rectify the wrong assumptions of "American Discovery by columbus." I hope that your article will pave the way for historians to look back the history again and match with the reality.
  Keep it up Dn. Daniel
  May God Bless you and your work...

  ReplyDelete
 46. ምክር የሚፈታው ችግር አለ፡፡ ተግሣጽ የሚፈታው ችግር አለ፣ ማሳለፍ የሚፈታውም ችግር አለ፡፡

  ReplyDelete
 47. good beginning and we expect from U
  THANK u

  ReplyDelete
 48. wondem D.Daniel
  I really appreciate ur idea,thanks for all ,Our GOD gives u wisdom and intellectual capacity to serve our peoples with loyality and honesy

  ReplyDelete
 49. yemimar hulu yimar , lantem birtatun yistih. enameseginihalen

  ReplyDelete
 50. አመሰግናለሁ

  ReplyDelete
 51. dear Dn Daniel
  firest hou are you.you are playing a great role in announcing the Ethiopian orthodox church to the young ppl. I say with help of god and saint marry continue your task then you get the result from the owner not from the ppl.
  Ewuketu linger
  D/Markos university employer

  ReplyDelete
 52. I read interstingly your "Yehulet Haweltoch wog" book. I can say it was the most intersting boook I have ever read. Would you please publish also the next. God bless you

  ReplyDelete
 53. it is a good message for this time to keep the country safe. hailu

  ReplyDelete
 54. ለምጣዱ ሲባል አይጧ እንድታልፍ መፍቀዱ ጥሩ ነው::ለምጣዱ ተብሎ እንድትኖር የተፈቀደላት አይጥ ጉድጓዳ ገብታ ትፈለፍላለች::ያኔ ምጣዱን ከልጆቿ ጋር ትሰብረዋለች::ስለዚህ አይጧን ምጣዱ ላይ አይደለም ባሏ አናት ላይም ብታገኛትም መምታት ግድ ይላታል::ሳይደርቅ በእርጥቡ:ሳይርቅ በቅርቡ::በተለይ በተለይ ለአገራችን ዘረኛ ፖለቲከኞች ይህ አይሰራም::የባህር በር አሳጡን:በዘር ከፋፈሉን:በገዛ አገራችን የበይ ተመልካች ሆንን:መታወቂያችን እየታየ ታሰርን:ተገደልን:...ምን እስክንሆን/እስኪያደርጉን ነው የምንጠብቃቸው::አባባሉ ግን ለትዳር እና ለሌላ ማህበራዊ ግንኙነት በጣም ይሰራል::እናመሰግናለን::

  ReplyDelete
 55. oh I have no words to say any more in short long live Daneil

  ReplyDelete
 56. እስከ መጨረሻ ያጽናህ።
  ከከንቱ ውዳሴ ይጠብቅህ።

  ReplyDelete
 57. የኢትዮጵያውያንን ወኔ የእምቢ ባይነትና አትንኩኝ ባይነትን ባሕል በተለያዩ መንገዶች በመስለብ ሕዝቡ በተለይም ወጣቱ ትውልድ በሃገሩና በእምነት ተቋማቱ ላይ የተፈጸመውን እና እየተፈጸመ ያለውን ወደር የሌለው ጥቃት እንዳይከላከል ከሚደረግባቸው ዋነኛው መንገዶች አንዱ የተለያዩ የሃይማኖት ድርጅቶችን እና መምህራንን በመጠቀም ነው። እነኝህ የሃይማኖት ማኅበራትና ታዋቂ ሰዎች የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ በየጊዜው የሚተላለፉ መልእክቶች ከኢትዮጵያውያን ታሪክ ጋር ፈጽሞ የሚጋጩና ያለቦታቸው የሚነገሩ በአሁኑ ጊዜ በሃገሪቱ ላይ ያለውን አፍራሽ ኃይል የጥፋት ሥራዎች ሰዎች እንዳይቃወሙት ለማድረግ ሆን ተብሎ እየተረገ ያለ ዘመቻ ነው። የሚገርመው በአንድ በኩል እንደ ቀድሞው አባቶቻችን እምነታችንን ባሕላችንን ጠብቀን ማስጠበቅ አለብን በማለት የኅዝቡን ስሜት ይቆጣጠሩና በሌላ በኩል ግን ሃገራችን ስትጠቃ ሃይማኖታችን ሲደፈርና ሲዋረድ ዝም ብላችሁ እዩ በጸሎት ብቻ እንጂ በሌላ መንገድ ይህን የጥፋት ድርጊት መከላከል የተረገመ ነው ሃጢያት ነው በማለት ሕዝቡን እያደነዘዙ ካደሩለት አጥፊ ክፍል የሚያገኙት ጥቅማቸው እንዳይጎድል እዚህም እዚያም ሲጽፉና ሲቀባጥሩ ይስተዋላሉ። ኢትዮጵያ በታሪኳ እንዲህ አይነት በደል ደርሶባት አያውቅም። ዛሬ ኢትዮጵያን የሕዝቡ የረዥም ጊዜ አብሮ መኖር እና የሃገር ፍቅር ስሜቱ በግድ አንድ ሃገር አድርጎ አቆያት እንጂ እንደጥፋቱ ሃይልና ምኞት ሃገሩቷ ዛሬ ተበታትና እንደዩጎዝላቪያ ወይም ሱማሊያ በሆነች ነበር። እንግዲህ ይህን አይነት እቅድ ያላቸውን ሰዎች ነው እቅዳቸው እስኪሳካላቸው ድረስ ዝም ብለን ማየት የሚገባን? በጣም ይገርማል! መለኪያው ኦርቶዶክስ የነበረውን ሰብረነዋ ሲባል ዝም፣ ዋልድባን ያህል ጥንታዊ ገዳም የአባቶች መምህራን ምንጭ ሲደፈር በዙሪያው ያሉ ቤተክርስቲያናት ፈርሰው ግድብና የሸንኮራ እርሻ ቦታ ሲሆኑ ዝም፣ የሃገሪቱ ድንበር ተላልፎ ለሱዳን ሲሰጥ ዝም፣ የተለያዩ የሃገሩቷ ብሔረሰቦች በዘራቸው ምክንያት ብቻ በገፍ ሲፈናቀሉ ሲገደሉና ሲሰደዱ ዝም፣ አሁንም የፈለጉትን ቢያደርጉ ዝም ዝም ዝም...። ምንም አይነት ጥፋት በዛች ታሪካዊት ሃገር እና ቤተክርስቲያን ላይ ሲፈጽም እንደትናንቱ ዛሬም ዝም በሉ እያሉን ነው አሁንም ብእረኞቹ ሞራል የሚሰልቡቱ በጸሎት ነው እያሉ የሚያዘናጉቱ ። ይገርማል! በእውነት ግን ምጣዷን እየሰበረ ያለው ከቻለም እንክት እንክትክት ለማድረግም ምንም ርህራሄ የሌለው ማን ነው? ለኢትዮጵያ ፈጽሞ የማይስማማው በመናፍቃንና በኮሚኒስቶችና የሚመራው ኃይል አይደለምን? እንኪያስ በዚህ ሰአት ሁሉም ሰው ተነስቶ አሁንስ በቃ ከላችን ወግዱ ብሎ ሃገሩን ለማዳን መሰለፍ ያለበት ጊዜ አይደለምን? ታዲያ ምነው ይህን ተነሳሽነት እንደመፍጠር እንደተለመደው ያለቦታቸው በሚነገሩ ይትባህሎች ለመስለብ መሞከር!? ይህ የወንጀል ወንጀል ነው!!! በአሁኑ ሰአት ኢትዮጵያዊ ነኝ ከሚል ወገን ሁሉ የሚጠበቀው ቆይ ዝም በል ጅቡ እየበላ ያለው የእኔን እግር ነው አይነት እባባል ሳይሆን ጅቡ ከእግር ወደ ራስ ሳይሸጋገር በጊዜ ራስን መከላከል ነው። ደግሞስ ለምጣዷ መሰበር ከአጥፊው ኃይል ሌላ ተጠያቂ ማንን ለማድርረግ ነው? ይህ ጥፋት ኃይል ያቀደውን ከመፈጸም በምንም መንገድ ወደኋላ የማይል በአገሪቷ ታሪክ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ያለው እና በአመራር ላይም ያሉት ሰዎች በአመለካከታቸውና በእምነታቸው በአገሪቷ ታሪክ ውስጥ መልካም ሥፍራ የሌላቸው የኢትዮጵያ የታሪክ ጠላቶች ስሪቶች ናቸው። ይህ የአይጧና የምጣዷ ምሳሌ አሁን እየሆነ ላለው ሃገርን የማጥፋት እቅድና በተቃራኒው ሃገርን የማዳን ተግባር ፈጽሞ የማይሆን ያለ ጊዜው ያለ ቦታው የቀረበ ነው። በርግጥ ለትዳር እንዲሁም ሕብረትንና አንድነትን ለመፍጠር ባለው አካሄድ ውስጥ ሊሰራ ይችላል። የአጥፊውን ኃይል ለማስወገድ እየተደረገ ያለውን ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ ግን ለመግታት እና በዛም ውስጥ የህዝብን በተለይም የወጣቱን ተሳትፎ ለመስለብ ከሆነ ግን የለም ተነቅቷል አይሰራም።

  ReplyDelete
 58. የኢትዮጵያውያንን ወኔ የእምቢ ባይነትና አትንኩኝ ባይነትን ባሕል በተለያዩ መንገዶች በመስለብ ሕዝቡ በተለይም ወጣቱ ትውልድ በሃገሩና በእምነት ተቋማቱ ላይ የተፈጸመውን እና እየተፈጸመ ያለውን ወደር የሌለው ጥቃት እንዳይከላከል ከሚደረግባቸው ዋነኛው መንገዶች አንዱ የተለያዩ የሃይማኖት ድርጅቶችን እና መምህራንን በመጠቀም ነው። እነኝህ የሃይማኖት ማኅበራትና ታዋቂ ሰዎች የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ በየጊዜው የሚተላለፉ መልእክቶች ከኢትዮጵያውያን ታሪክ ጋር ፈጽሞ የሚጋጩና ያለቦታቸው የሚነገሩ በአሁኑ ጊዜ በሃገሪቱ ላይ ያለውን አፍራሽ ኃይል የጥፋት ሥራዎች ሰዎች እንዳይቃወሙት ለማድረግ ሆን ተብሎ እየተረገ ያለ ዘመቻ ነው። የሚገርመው በአንድ በኩል እንደ ቀድሞው አባቶቻችን እምነታችንን ባሕላችንን ጠብቀን ማስጠበቅ አለብን በማለት የኅዝቡን ስሜት ይቆጣጠሩና በሌላ በኩል ግን ሃገራችን ስትጠቃ ሃይማኖታችን ሲደፈርና ሲዋረድ ዝም ብላችሁ እዩ በጸሎት ብቻ እንጂ በሌላ መንገድ ይህን የጥፋት ድርጊት መከላከል የተረገመ ነው ሃጢያት ነው በማለት ሕዝቡን እያደነዘዙ ካደሩለት አጥፊ ክፍል የሚያገኙት ጥቅማቸው እንዳይጎድል እዚህም እዚያም ሲጽፉና ሲቀባጥሩ ይስተዋላሉ። ኢትዮጵያ በታሪኳ እንዲህ አይነት በደል ደርሶባት አያውቅም። ዛሬ ኢትዮጵያን የሕዝቡ የረዥም ጊዜ አብሮ መኖር እና የሃገር ፍቅር ስሜቱ በግድ አንድ ሃገር አድርጎ አቆያት እንጂ እንደጥፋቱ ሃይልና ምኞት ሃገሩቷ ዛሬ ተበታትና እንደዩጎዝላቪያ ወይም ሱማሊያ በሆነች ነበር። እንግዲህ ይህን አይነት እቅድ ያላቸውን ሰዎች ነው እቅዳቸው እስኪሳካላቸው ድረስ ዝም ብለን ማየት የሚገባን? በጣም ይገርማል! መለኪያው ኦርቶዶክስ የነበረውን ሰብረነዋ ሲባል ዝም፣ ዋልድባን ያህል ጥንታዊ ገዳም የአባቶች መምህራን ምንጭ ሲደፈር በዙሪያው ያሉ ቤተክርስቲያናት ፈርሰው ግድብና የሸንኮራ እርሻ ቦታ ሲሆኑ ዝም፣ የሃገሪቱ ድንበር ተላልፎ ለሱዳን ሲሰጥ ዝም፣ የተለያዩ የሃገሩቷ ብሔረሰቦች በዘራቸው ምክንያት ብቻ በገፍ ሲፈናቀሉ ሲገደሉና ሲሰደዱ ዝም፣ አሁንም የፈለጉትን ቢያደርጉ ዝም ዝም ዝም...። ምንም አይነት ጥፋት በዛች ታሪካዊት ሃገር እና ቤተክርስቲያን ላይ ሲፈጽም እንደትናንቱ ዛሬም ዝም በሉ እያሉን ነው አሁንም ብእረኞቹ ሞራል የሚሰልቡቱ በጸሎት ነው እያሉ የሚያዘናጉቱ ። ይገርማል! በእውነት ግን ምጣዷን እየሰበረ ያለው ከቻለም እንክት እንክትክት ለማድረግም ምንም ርህራሄ የሌለው ማን ነው? ለኢትዮጵያ ፈጽሞ የማይስማማው በመናፍቃንና በኮሚኒስቶችና የሚመራው ኃይል አይደለምን? እንኪያስ በዚህ ሰአት ሁሉም ሰው ተነስቶ አሁንስ በቃ ከላችን ወግዱ ብሎ ሃገሩን ለማዳን መሰለፍ ያለበት ጊዜ አይደለምን? ታዲያ ምነው ይህን ተነሳሽነት እንደመፍጠር እንደተለመደው ያለቦታቸው በሚነገሩ ይትባህሎች ለመስለብ መሞከር!? ይህ የወንጀል ወንጀል ነው!!! በአሁኑ ሰአት ኢትዮጵያዊ ነኝ ከሚል ወገን ሁሉ የሚጠበቀው ቆይ ዝም በል ጅቡ እየበላ ያለው የእኔን እግር ነው አይነት እባባል ሳይሆን ጅቡ ከእግር ወደ ራስ ሳይሸጋገር በጊዜ ራስን መከላከል ነው። ደግሞስ ለምጣዷ መሰበር ከአጥፊው ኃይል ሌላ ተጠያቂ ማንን ለማድርረግ ነው? ይህ ጥፋት ኃይል ያቀደውን ከመፈጸም በምንም መንገድ ወደኋላ የማይል በአገሪቷ ታሪክ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ያለው እና በአመራር ላይም ያሉት ሰዎች በአመለካከታቸውና በእምነታቸው በአገሪቷ ታሪክ ውስጥ መልካም ሥፍራ የሌላቸው የኢትዮጵያ የታሪክ ጠላቶች ስሪቶች ናቸው። ይህ የአይጧና የምጣዷ ምሳሌ አሁን እየሆነ ላለው ሃገርን የማጥፋት እቅድና በተቃራኒው ሃገርን የማዳን ተግባር ፈጽሞ የማይሆን ያለ ጊዜው ያለ ቦታው የቀረበ ነው። በርግጥ ለትዳር እንዲሁም ሕብረትንና አንድነትን ለመፍጠር ባለው አካሄድ ውስጥ ሊሰራ ይችላል። የአጥፊውን ኃይል ለማስወገድ እየተደረገ ያለውን ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ ግን ለመግታት እና በዛም ውስጥ የህዝብን በተለይም የወጣቱን ተሳትፎ ለመስለብ ከሆነ ግን የለም ተነቅቷል አይሰራም።

  ReplyDelete