Sunday, March 28, 2010

መመረሽ፣መፈረሽ፣መደንበሽመጀመርያ ወደ ሱዳን ኤምባሲ ሄዳችሁ ሱዳን የመግቢያ ቪዛ ታወጣላችሁ፡፡ ከዚያ በጎንደር በመተማ በኩል ወደ ሱዳን ትገሠግሣላችሁ፡፡ ‘የሱዳን ሕዝብ ጥሩ ነው፣ለስደተኞች ይራራል‘ ይላሉ ጣልያን የገቡት ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች፡፡ እዚያ የታወቁ ሁለት አሸጋጋሪዎች አሉ፡፡ በአካል አታገኟቸውም፡፡ ስልካቸውን ከሀገር ሳትወጡ ይዛችሁ መሄድ አለባችሁ፡፡ አለበለዚያም ጣልያን የገባ ሰው ሊነግራችሁ ይገባል፡፡

አንዳች ሰዋራ ሥፍራ ተደብቃችሁ በስልክ ታገኟቸውና የጉዞ ዋጋ እና ቀን ትነጋገራላችሁ፡፡ እነርሱም ገንዘቡን ይዛችሁ የምትመጡበትን ቦታ እና ቀን ይነግሯችኋል፡፡ በተባላችሁት ሌሊት እቦታው ስትደርሱ እንደ እናንተ በቀጠሮ የመጡ ሌሎች ስደተኞችን ጨምረው በጭነት መኪና ወደ ሊቢያ ድንበር ትወሰዳላችሁ፡፡ ጉዞው ሌሊት ሌሊት፣ ያውም አብዛኛው በእግር፣ ጥቂቱ ደግሞ በመኪና ስለሆነ ከሃያ ቀን እስከ አንድ ወር ይፈጃል፡፡

ሊቢያ ድንበር ስትደርሱ የሱዳን አሸጋጋሪዎች ለሊቢያ አሸጋጋሪዎች ያስረክቧችኋል፡፡ ዋጋ ተነጋግራችሁ አሁንም ጉዞ ትጀምራላችሁ፡፡ ግማሹን በእግር ግማሹን በፒክ አፕ መኪና፡፡ ደረቅ ዳቦ እና ውኃ ይሰጣችኋል፡፡ መንገድ ላይ የሚሞቱ ልጆች ይኖራሉ፡፡ አሸዋውን ማስ ማስ አድርጎ በመቅበር ጉዞ መቀጠል ነው፡፡

«በእግር ወይንም በመኪና ስትጓዝ በእንጨት የመስቀል ምልክት የተሠራበት ነገር ካየህ እዚያ ቦታ አንድ አበሻ ስደተኛ ተቀብሯል ማለት ነው፡፡» ብሎኛል ጣልያን ያገኘሁት ልጅ፡፡ «ሰው ከታመመ እንደ በሽታው ነው፡፡ መጠነኛ ከሆነ በድጋፍ ይሄዳል፡፡ ከባድ ከሆነ ግን ቁርጥ ወገን ያስፈልገዋል፡፡ ከቡድኑ ከተቆረጥክ ችግር ስለሚያጋጠምህ አንዳንዱ ትቶህ ይሄዳል፡፡ ብዙ ጊዜ ግን የቂርቆስ ልጆች ይተዛዘናሉ፡፡ እንዲያውም

ከቂርቆስ ልጅ ጋራ አብረው ቢሰደዱ

ቢያገኝም ያበላል ቢያጣም ያዝናል ሆዱ

ተብሎ ተዘፍኖላቸዋል፡፡» አለኝ ሮም ያገኘሁት የአዲስ አበባው የቂርቆስ ልጅ፡፡ አዲስ አበባ ስለ ቂርቆስ ሠፈር ልጆች አያሌ አስገራሚ እና አስቂኝ ነገሮች እሰማ ነበር፡፡ እዚህ ጣልያን ደግሞ አገር ጉድ የሚያሰኝ ገድላቸውን መስማት ጀምሬያለሁ፡፡

ሊቢያ ስትገቡ የተቀበሏችሁ አሸጋጋሪዎች ከትሪፖሊ አጠገብ የገጠር መንደር ውስጥ በተሠራ አዳራሽ አስገብተዋችሁ ይጠፋሉ፡፡ ከዚያ ሌሎች አሸጋጋሪዎች ደግሞ ይመጡና «ትሪፖሊ ሩቅ ስለሆነ እንድንወስዳችሁ መቶ መቶ ዶላር ክፈሉ» ይሏችኋል፡፡ ታድያ የቂርቆስ ልጆች ምን አደረጉ መሰላችሁ፡፡ የተወሰኑት ልጆች ሌሊት ተደብቀው ይወጡና እግራቸው ወዳመራቸው ሲጓዙ ለካስ ትሪፖሊ ቅርብ ነው፡፡ ተመልሰው ይመጡና ሌሎችን ልጆች ነጻ ያወጧቸዋል፡፡ ከእነርሱ በኋላ ለሚመጡት ስደተኞች ደግሞ ግድግዳው ላይ በአማርኛ እንዲህ ብለው ይጽፋሉ «እንዳት ሸወዱ፣ ትሪፖሊ ቅርብ ነው፡፡ ብር ስጡን ቢሏችሁ አትስጡ፡፡ በዚህ እና በዚያ አድርጋችሁ ጥፉ» ይሄ ማስታወቂያ አያሌ ስደተኞችን ታድጓቸዋል፡፡ አይ የቂርቆስ ልጆች፡፡ ነፍስ ናቸውኮ፡፡

ትሪፖሊ ገብታችሁ የመርከብ ወረፋ መጠበቅ ነው፡፡ ክፉ ፖሊሶች ካገኟችሁ በመኪና ጭነው እንደ ገና ወደ ሱዳን ድነበር ወስደው ያሥሯችኋል፡፡ እዚያ እሥር ቤቱ በጣም አሰቃቂ ነው፡፡ እዚያም ቢሆን የቂርቆስ ልጆች ካሉ መከራው ይቀልላል፡፡ ከእሥር ቤቱ ለመውጣት የገንዘብ ጉቦ ያስፈልጋል፡፡ ያንን ደግሞ ለማግኘት ወይ አስቸጋሪ ሥራ መሥራት ያለበለዚያም ደውሎ ከዘመድ ማስመጣት ያስፈልጋል፡፡

እዚያ እሥር ቤት ብዙ ልጆችን ያስፈታ አንድ የቂርቆስ ልጅ ነበር፡፡ ሥራ ይወዳል፡፡ ሲጋራ፣ ብስኩት እና ሳሙና እየሸጠ ይኖር ነበር፡፡ በዚያ እሥር ቤት ብዙ ጊዜ የቆየው ሌሎችን ሲያስ ፈታ ገንዘቡ እያለቀበት ነው ይባላል፡፡ ሌሎች ደግሞ በሌላ ነገር ይተርቡታል፡፡ ከእሥር ቤቱ ሊወጣ በር ላይ ሲደርስ «አንድ ሲጋራ አለህ» የሚል ገዥ ሲመጣ ለርሱ ሊሸጥ እየተመለሰ ነው፡፡ እንዲያውም አንድ ጊዜ በአጥር ዘለሎ ሊያመጥ ሁሉም ነገር ተስተካክሎለት ነበር፡፡ ሊዘልል አንድ እግሩን እንዳሣ «አንድ ሲጋራ አለህ» የሚለውን ሲሰማ ተመልሶ መጣ ይባላል፡፡

በቤንጋዚ ወደብ አሻጋሪዎች እና ተሻጋሪዎች አይገናኙም፡፡ ሃያ እና ሰላሣ ሰው እስኪሞላ የሚመዘግቡ ሰዎች አሉ፡፡ የቡድኑ አባላት ሲሟሉ ገንዘብ ይከፍሉና ወደሚሻገሩበት ወደብ ይወሰዳሉ፡፡ የመሻገሪያዋ ጀልባ ብዙ ጊዜ ከቆርቆሮ እና ከእንጨት የምትሠራ ናት፡፡ ለአንዱ ስደተኛ አሻጋሪዎቹ የመርከቧን አነዳድ ያሳዩታል፡፡ ትምህርቱ ቢበዛ ከአንድ ቀን በላይ አይሰጥም፡፡

ለዚያ መከረኛ «ካፒቴን» የጀልባዋን ኮምፓስ አሥረው ካርታውን ያስረክቡታል፡፡ ምግብ እና መጠጥ ይጫናል፡፡ እንደ ጀልባዋ ስፋት ከሃያ እስከ ሠላሳ ስደተኛ ይሳፈራል፡፡ በሌሊት የጣልያንን መብራት በሩቁ እያዩ ጉዞ ይጀመራል፡፡ አሻጋሪዎቹ ጀልባዋ ስትነሣ ይመለሳሉ፡፡ ከዚህ በኋላ ዕዳው የስደተኞቹ ነው፡፡

ጉዞው እስከ አስራ ሰባት ሰዓት ይፈጃል፡፡ የአንዱ እግር ከሌላው ጀርባ ጋር ተሰናስሎ ተኮራምቶ መጓዝ ብቻ ነው፡፡ ሙቀቱ እና ተስፋ መቁረጡ አንዳንዶችን ራሳቸውን ወደ ባሕሩ እንዲጥሉ ያደርጋቸዋል፡፡ በተለይም መርከቡ መንገድ ከሳተ፡፡

የሚያስጎበኘኝን የቂርቆስ ልጅ «ለምንድን ነው ጣልያን ውስጥ የቂርቆስ ሠፈር ልጆች የሚበዙት፡፡ እንዲያውም ሮም ውስጥ የቂርቆስ ልጆች ብቻ ያሉበት አንድ ሕንፃ አሳይተውኛል፤» አልኩና ጠየቅኩት፡፡ «ምናልባት የሱዳን ኤምባሲ ሠፈራችን ውስጥ ስለሆነ ይሆናል በሱዳን በኩል እያቋረጥን የመጣነው» አለና ቀለደብኝ፡፡ «ቆይ ግን ለመንገዱ ብዙ ዶላር ያስፈልጋል ሲባል ነበር የምሰማው፤ እንዴት ነው ጉዳዩ» አልኩት፡፡ «ቂርቆስ የድኻ ሠፈር ነው ብለው ስማችንን ያጠፉትኮ የቦሌ ልጆች ናቸው፤ እነርሱ አውሮፕላን ሲያዩ ስለሚውሉ የገዙ እየመሰላቸው ነው፤ እንዲያውምኮ መንግሥት ሀብታም ገበሬዎችን ብቻ ሳይሆን እኛንም መሸለም ነበረበት፤ የመረጃ እጥረት ነው» አለኝ፡፡

«እንዴት?» አልኩት፡፡ «እስኪ ተመልከት እኛ የቂርቆስ ልጆች የመንግሥትን እጅ ሳንጠብቅ፤ አነስተኛ ፣ጥቃቅን ሳንል፤ ራሳችንን በራሳችን ረድተን እዚህ መድረሳችን አያሸልመንም» አለና ሳቀ፡፡ «ሀብታም ገበሬዎች ራሳቸውን ቻሉ እንጂ የሕዝብ ቁጥር አልቀነሱም፤ እኛ ግን ራሳችን ንም ቻልን፣ከሀገር በመውጣታችን ደግሞ የሕዝብ ቁጥር ቀነስን፡፡ ከዚህ በላይ ምን የሚያሸልም ነገር አለ፡፡ አየህ እኛ እንደ ቦሌ ልጆች ጆግራፊን በቲቪ ሳይሆን በተግባር ነው የምንማረው»

«ደግሞምኮ የአባቶቻችንን ደም የመለስን እኛ ነን» አለኝ እየሳቀ፡፡ «እንዴት?»

«ጣልያን ባሕር አቋርጦ ሀገራችንን ወረረ፡፡ እኛ ደግሞ የአባቶቻችንን ደም ለመበቀል ባሕር አቋርጠን ሀገሩን ወረርነዋ፤ አንተ ቂርቆስኮ የጀግና ሠፈር ነው» አለና ሳቀ፡፡

«እውነት ግን ለምንድን ነው የቂርቆስ ልጆች እዚህ የበዛችሁት?» «ምን መሰለህ ይህንን በረሃ ለማቋረጥ ከሁለት እስከ ሦስት ወር ይፈጃል፡፡ የገንዘብ፣ የምግብ፣ የውኃ ችግር አለ፡፡ ካልተዛዘንክ በቀር ይህንን በረሃ ልታልፈው አትችልም፡፡ እኛ ደግሞ ከልጅነታችን ተዛዝነን መኖር ለምደናል፡፡ ስለዚህ እየተደጋገፈክ መጓዝ ነው፡፡ ያው እንግዲህ ባሕር ኃይልም አየር ኃይልም እየመጣ ይቀጥላል»

«የቀድሞ ወታደሮችም ይመጣሉ ማለት ነው» «አይ እነርሱ አይደሉም፡፡ በአውሮፕላን ጣልያን የገባው ስደተኛ አየር ኃይል ይባላል፡፡ በባሕር የገባው ደግሞ ባሕር ኃይል ይባላል፡፡ ታድያ አየር ኃይሉ ባሕር ኃይሉን ይንቀዋል፡፡»

«ለምን?» «ያው መከፋፈል ለምዶብን ነዋ፤ አታይም መንገድ ላይ እንኳን ጉስቁል ያለ አበሻ ካዩ ሰላም አይሉንም፡፡ ጣልያኖች እንደሆኑ አየር ኃይልም ሆንክ ባሕር ኃይል ሚኒስትር አያደርጉህም፤ ሁሉም ያው ሲኞራ ቤት ነው የሚሠራው፡፡

«ሲኞራ ቤት ደግሞ ምንድን ነው?» «ሰው ቤት ተቀጥሮ መሥራት ማለት ነው፡፡ እዚህ ብዙው አበሻ እንደዚያ ነው የሚሠራው፡፡ ያውም ለሴቶች እንጂ ለወንዶች ሥራ አይገኝም፡፡ ድድ ስታሰጣ መዋል ነው፡፡»

«ግን ምን ላይ እየኖርክ ድድ ታሰጣለህ» አልኩት፡፡ «እዚህ አበሻ ከድንኳን ሰባሪነት ወደ ሕንፃ ሰባሪነት ተሸጋግሯል» «እንዴት እንዴት ሆኖ» «ያንን ሁሉ በረሃ አቋርጠህ፤ ባሕር ሰንጥቀህ ጣልያን ስትገባ ምንም ነገር አታገኝም፡፡ ከምግብ በቀር ቤት እንኳን የሚሰጥህ የለም፡፡ ለተወሰነ ጊዜ መጠለያ ውስጥ ያስገቡህና በኋላ ሠርተህ ብላ ብለው ያሰናብቱሃል፡፡ ያን ጊዜ ችግር ውስጥ ትወድቃለህ፡፡ አበሻ ታድያ ይሰባሰብና በልዩ ልዩ ምክንያት የተዘጋ ሕንፃ ያስሳል፡፡ የተወሰነ ጊዜ ሁኔታውን ታይና ሃያ ሠላሳ ሆነህ በሩን ሰብረህ ትገባለህ፡፡ ከዚያ ክፍሎቹን መከፋፈል ነው፡፡»

«ባለቤቶቹስ» «ባለቤቶቹ ኡኡ ይላሉ፡፡ ፖሊስ ይመጣል፤ ግርግር ይፈጠራል፡፡ የሰው ልጅ ሜዳ ላይ ወድቆ እንዴት ሕንፃ ተዘግቶ ይኖራል ብለህ ትከራከራለህ፡፡ መቼም የሰው መብት በመጠኑም ቢሆን የሚከበርበት ሀገር ነውና የሰው መብት ተከራካሪድር ጅቶችም አብረውህ ይጮኻሉ፡፡ በመጨረሻ ታሸንፍና ትኖርበታለህ፡፡»

«መብራት እና ውኃ አይቆርጡባችሁም» ?«ብዙ ጊዜ መብራቱን እንጂ ውኃውን መቁረጥ ያስቸግራቸዋል፡፡ የሮም ሕንፃዎች የድሮ ሕንፃዎች ናቸው፡፡ የውኃ መሥመሩ በቀላሉ አይገኝም፡፡ መብራቱን ግን ቢቆርጡትም እንቀጥለዋለን፡፡ አንድ ልጅ እንዲያውም በዚያ ምክንያት ሥራ አግኝቷል፡፡»

«መብራት በመቀጠል?» «አዎ፤ የቤቱን መብራት ሲቆርጡት በመንገድ ከሚያልፈው መብራት ሌሊት ቀጠለው፡፡ ፖሊሶቹ ሲመጡ ይበራል፡፡ ሄደው ከዋናው ማጥፊያ ቢያለያዩትም ይበራል፡፡ አይተው ስለማያውቁ ግራ ገባቸው፡፡ በኋላ ከመንገዱ መብራት መቀጠሉን ሲያዩ እንዴት ሊቀጠል እንደቻለ ማመን አልቻሉም፡፡ እና ትተውት ሄዱ፡፡ ይሄው ፏ ብሎልሃል፡፡ ልጁም ታድያ ኤሌክትሪክ ሠራተኛ ሆኖ ቀረ»

«ሴቶች ሲኞራ ቤት ይሠራሉ አልከኝ፤ ወንዶችስ ምን ይሠራሉ?» «ወንድ ከሆንክ አልፎ አልፎ ነው ሥራ የምታገኘው፡፡ ችግር አለ፡፡ አንዱ አበሻ ሲርበው ሴት ነኝ ብሎ ሲኞራ ቤት ተቀጥሮ ነበር አሉ፡፡» «እውነትክን ነው ወይስ ቀልድ ነው» «እኔ ሲያወሩ ነው የሰማሁት፡፡» «እሺ ከዚያስ» «ልጁ ጢም የለውም፤ መልኩ የሴት ድምጽ ነው፡፡ እንዲያው ልጆች በሌላ ነገር ይጠረ ጥሩታል» «ምን ብለ» «ነገርዬው የለውም ይሉታል» «እሺ»

«እና ጉልበታም ነው፤ ሥራዋን ፉት፣ ጭጭ ነበር አሉ የሚያደርጋት፡፡ አንድ ቀን የሽንት ቤቱን በር ሳይዘጋው ረስቶት፣ ቆሞ ሽንቱን ሲሸና ሲኞራው በሩን ሲከፍት ፌንት ወጣ አሉ፡፡ ነፍሷ ደሞዟን ሳትቀበል ከቤት ወጥታ ጠፋች፡፡ በኋላ ግን እንደዚያ ያደረገው ሥራ ስላጣ መሆኑን ሲኞራው ሲሰማ አድንቆ ካምፓኒው ውስጥ ቀጠረው አሉ»

«ተው እባክህ፤ ይሄን የመሰለ ፊልም አይቻለሁ፤ ሲኮምኩ ይሆናል» «ኩምክና አይደለም፤ የሆነ ነው ብለውኛል»

«እሺ ይህንን ሁሉ ባሕር አቋርጦ የመጣ ሰው መጨረሻው ምንድን ነው?»

«ወይ ትመርሻለህ፣ ወይ ትፈርሻለህ፣ ወይ ትደነብሻለህ» «ምንድን ነው መመረሽ፣ ምንድን ነው መደንበሽ፣ ምንድን ነው መፈረሽ»

«ጣልያን ለመኖር የሚመጣ የለም፣ ስለዚህ ትንሽ ገንዘብ ነገር ቆጣጥረህ ወደ እንግሊዝ ትሻገራለህ፤ ይኼ መመረሽ ይባላል፡፡ ያለበለዚያ ደግሞ እዚሁ የመኖርያ ፈቃድ አወጥተህ የተሻለ ሥራ ካገኘህ ትኖራለህ፤ ይኼ ደግሞ መፈረሽ ይባላል፡፡ ሁለቱም ካልሆነልህ ደግሞ ትጀዝብና ደንብሸህ ትኖራለህ፡፡ ሚላኖ፣ ጣልያን  40 comments:

 1. Lekas Yesedetem Aynet Alew, Bemesedede Betam Azene Neber, Lekas Yebasem Ale. Negerochen Endastewlachew Seleredahegn Keleb Amesegenalehu.

  ReplyDelete
 2. Dani, The only thing that I can say God bless your work like Habibe Gewergies's, who has changed the History of Eskindirya orthodoxs Church some years ago.

  ReplyDelete
 3. ውድ ዳ/ን ዳንኤል
  የቂርቆስ ልጆች ሌቦችም ናቸዉ:: አንዱ ያዉም ዳያቆን ተብየዉ የአሰሪዉን $22000 ባንክ አስገባ ተብሎ ይዞ ጠፍቶአል:: ከዚህ በላይ ገንዘብ በታማኝነት ያስገባ የነበረ ነዉ::
  ወላጆቹ ና ጎረቤቱ ሁሉ አፍረዉበታል:: ምንትለዉአለህ?

  ከሱዳን

  ReplyDelete
 4. +++

  Dear Dn Daniel,

  Have you heard that Ye kirkos lijoch have prepred very big pray (Tselot fitata)in UK( Sep 2009)for those lost during the migration.

  Why do you think these people leave their beloved country?

  Melakm beal

  ReplyDelete
 5. Wey yehagere lijoch. Beka yegna eta fanta yihie hono kere malet new???

  where ever u go, the story being told about us is so bitter. South Africa, Djibouti,Sudan, Yemen and else where.

  I was reading one article about refugee and immigration. Before some 30 years,the number of asylum seeker and /or refugee from Ethiopia to USA and other European countries was the least of all the other countries. Now we are the second from Africa.
  meeche yihon ye Ethiopia tinsae? meftihewis min yihon???

  ReplyDelete
 6. tanks to GOD for giving the strength to Dn.Danil to share to us a lot of thought & different point of views.

  in my personal opinion in A.A Ethiopia this was written already but it's good for those u who do not have a chance to read it but what about the new idea seekers? it's for Dn.Danil thanks.

  ReplyDelete
 7. ውድ ወንድማችን ዳያቆን ዳንኤል

  ስለ ብሎግህ ጎደኛህ በሆነው ወንድሜ ነው ያወኩት እግዚአብሄር ያበርታህ መጣጥፎቹን ግን በዛ አድርጋቸው ሃይማኖታዊ መጣጥፎቹን በዛ አድርግልን በነገራችን ላይ በአማርኛ ፊደል ቻት ለማድረግም ሆነ በአማርኛ አስተያየት ለመስጠት http://freetyping.geezedit.com/
  መጠቀም ትችላላችሁ

  መልካም በአል

  ምረተአብ

  ReplyDelete
 8. We are brave people, aren't we? But, in most cases for unfortunate reasons. When is this gone end? Never mind, never!!! Or it will end for others, you know what I mean!!!

  ReplyDelete
 9. dani berta ante srahn sra lelaw yawra

  ReplyDelete
 10. +++
  Dear Dn. Daniel.

  I don't know what to say. Roma silalu Ethiopiyawiyanin neger litsaf kalk "Abayin Bechilfa" belew.

  Ene ke Ayer Hiyilochu budin negn. And bekirbet yemitawukew wondimachen yeserawun jebdu lakaflih ene degimo. Negeru endih newu.....

  Endemitawukewu yeRoma ketema wusti guzo beAutobus (Tram) newuna.....yebus tiket kelelehina, Tiket tekotatari kagegneh kitatum chan yilal alu. Ena yihe wondimachin 10 ticket yigezana bus yisaferal. Tadiya tiketun layi milikit lemasdereg mashinu wusti siketu hulunem andi layi yiwosdibetina 10unim tiket bande yicherisibetal. Keziya bezih yinadedina lela ken minim tiket sayiyiz bus sisafer endagatami hono police yiyizewal.

  Ahun bemin kuwankuwa yigbabu...esu Metenegna engilizegna tenagari newu polisu degimo Italiyanigna bicha newu yemichilewu. Keziya wede police tabiya yiwesdewuna...yiteyekal.

  Dokument (Metawekya) amta, lemindinewu tiket yematitekemew tebilo yiteyekal. Keziya yesu mels yawu be Engilizegna newu engidih..."Your father father father..Mosoloni come Ethiopia, ....no document, no ticket! So, I come Roma, no document no ticket!" ,....ha ha ha ha. Keziya polisu "Bravo Signor" bilot be10 ticket sitota shegnewu yibalal. Yihe newu Yekirkos lij.

  Dn. Daniel, Esti Sile CATACOMBE tinish asnebiben sefa adrigeh. Ye Metsihaf kidus ketemoch yalkew metsihafih layi yalewunim bihon...

  Cher Yigtemen!

  ReplyDelete
 11. Good work Dani. Thanks.

  ReplyDelete
 12. አምደማርያምMarch 29, 2010 at 7:56 AM

  ዲ/ን ዳኒኤል
  በመጀመርያ ምስጋናና ክብር ለመድሐኒያለም ይግባውና ! አንተን የመሰለሊቅ ወንድም ሰጠን.
  ተባረክ ቤተሰቦችህን ያንተ የሆነውን ሁሉ ይባርክልህ.አንዲህ ነው የስባኪ ወጉ
  ሁልገዚም ከምእመናን በልጦ መገመኘት ይኖርብናል በርታ
  ሐይለአጋንንትን ይሰርልህ .
  ወስብሐት ለ እግዚአብሔር
  አምደማርያም

  ReplyDelete
 13. It is very sad that the exodus becomes the fate of Ethiopians for several reasons. A lot has been said about exodus and of course I know similar real examples like Daniel’s narration who scrambled to reach their dream destiny. One of the words from Daniel article which touch my heart is
  “ካልተዛዘንክ በቀር ይህንን በረሃ ልታልፈው አትችልም፡፡ እኛ ደግሞ ከልጅነታችን ተዛዝነን መኖር ለምደናል፡፡ ስለዚህ እየተደጋገፈክ መጓዝ ነው፡፡”
  That is why life is a school from which you never graduate. And this is maturity that you get with life challenges and experiences and I like this behavior of “Ye Cherkos lejoch”. I feel that you can get real friends during such odd times and there is a speculation that many Ethiopians and Eritreans are real friends with such incidents.
  «ጣልያን ባሕር አቋርጦ ሀገራችንን ወረረ፡፡ እኛ ደግሞ የአባቶቻችንን ደም ለመበቀል ባሕር አቋርጠን ሀገሩን ወረርነዋ፤ አንተ ቂርቆስኮ የጀግና ሠፈር ነው» የሚለውን አስቂኝ ሳነብ አንድ ነገር ትዝ አለኝ፡፡
  በአዲስ አበባ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ የሚያስተምር የህንድ አስተማሪ ነው፡፡ አንዱ ተማሪ በክፍል ውስጥ ጥፋት አጥፍቶ አስተማሪው ተንበርከክ ሲለው ልጁም “እንኳን ለህንድ ለጣልያንም አልተንበረከክንም” ብሎት እርፍ፡፡ እንዲህ ነው እንጂ ጀግንነት!

  ReplyDelete
 14. sorry for our brothers

  ReplyDelete
 15. D/n Daniel
  I really appreciated ur current views on migration, reside and abdicated or abandoned. migration is not something newly introduced phenomenon but rather happens to be practised by any group or individuals or particles for survival and continuity based on my understanding but I would say depending on ur writing the cost of migration weighs differently contingent on de situation, migrants who crossed the open sea without trained captain, necessary equipments and health and safety assessment paid a lot relatively, my frustration will be des is a dynamic process which has no end because as we can learn from the exodus, which is the product of a famine caused the Hebrew tribes migrate to Egypt.
  Thank u

  ReplyDelete
 16. +++

  Dani,

  Pls try to minimize your time in Cyber. You need to concentrate on the ground work, what you started. I hope you will understand me what I mean.

  Thanks

  ReplyDelete
 17. It was interesting story.
  Bless u Daniel.
  Brother MihretAb...thank you for indicating the Geezediting page. It was really helpful.

  ReplyDelete
 18. if one reads and makes sense of what u r writing, i think he/she will be forced to appriacte the way of writing and the issues being raised. Thanks a lot and God Bless you

  ReplyDelete
 19. Ha ha ha very funny

  ReplyDelete
 20. Thanks for sharing, I heard a number of migration history but this is the worst. Traveling on water for many hrs, by a captain who trained for one day, with a handmade boat is the scariest of all. The part that saddened me the most is the end result of most the immigrants in Italy after the long and horrific travel.

  ReplyDelete
 21. ውድ ዳንኤል እንዴት ደስ የሚል አዝናኝና ቁምነገር አዘል ጽሁፍ ነው ያስነበብከን? እጅግ በጣም ወድጄዋለሁ ፡፡ በርታ በዚሁ ቀጥል
  አመሰግናለሁ
  ራሔል

  ReplyDelete
 22. Solomon. G from aauApril 22, 2010 at 6:51 PM

  Why do peoples always shy away from the reality? Dani all what said about you wrongly was, because of evil spirit who try's to block the real teaching of "Kiristos", But this is and will remain impossible. So pleas dani don't hesitate to tell the reality for ignorant.
  May God bless You!!!

  ReplyDelete
 23. Daniel Kibret's Views would be better as "The Views of Danial Kibret."

  ReplyDelete
 24. ውድ ዳንኤል በዚህ ቀጥል ወይ የጨርቆስ ልጆች ይገርማሉ?

  ReplyDelete
 25. በአማርኛ ለመጻፍና ኢንተርኔትም ላይ በዓማርኛና እንግሊዝኛ ከጉግል ለመፈለግ
  በአማርኛ "Search" ላይ ተጭኖ ሳጥኑ ውስጥ በአማርኛ መጻፍ። በእንግሊዝኛ ለመፈለግ "Alphabet" ከእዚያ "Latin" መምረጥ። ጥያቄ ለዶ/ር አበራ ሞላ
  http://freetyping.geezedit.com/

  ReplyDelete
 26. በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

  ReplyDelete
 27. continue with this GOD bless you

  ReplyDelete
 28. LIDETU DAGNE FROM KIRKOS hi daniel how are you ,i read your essay carefully and i am happy by that of the kirkos village boys,kirkos boys are very interesting in sudan, libya & italy except AKLILU POPO

  ReplyDelete
 29. selam Egziabher lenanite yhun lemtsifu ena lemitanebu .sile wendime yesafew chigir be,Sudan,Libya,Malta,Italiy.motn be aynih ayte malefi new beza yemisekayu wendimochi ahunm alu silez ebakachu be selot asibachew.yarefutn nefisachew ykebeli Geta Medihanealem be hiwet yalu degimo beselam yawtachew.we sibht le Egziabher ykoyen Amen

  ReplyDelete
 30. dear Daniel i read ur book.betam aref view alehe.keep it up& ye sedetu tarik leb yenekal .egzehabeher kanet gar yehun.

  ReplyDelete
 31. ስደት ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ ያስገነዝባል፡፡

  ReplyDelete
 32. thank u for ur inf. last time I and my friend decided to go europe through libiya but now i haved decided to work hard here.

  ReplyDelete
 33. awo dani ulum ewnet new enam yeza ager sew neg sedet le wendemochachen be italiy wesy yekebdal. gen yhan ulu menged akwartew metew erasachewen tesfa koreten bemil astesaseb sebelashu ayalu...............be hewetachen west ulugezam le egzyabhare bota enstew .....mengedachene lesu adera enstew.menfesaw botawochen enazwtre ..ketsfa mkuret yadenenal.

  ReplyDelete
 34. በጣም ደስ ይላሉ የመረዳዳት ባህላችንን በጣም ጠብቀው ይዘውታል American ላለነው ኢትዮጵያዊያን ለምንበላላው ትልቅ ትምህርት ነው፡፡

  ReplyDelete
 35. በእውነት ጥሩ እይታ ነው::በቄርቆስ ልጆች ገድል የስደትን አስከፊነት ሸንቆጥ አድርገሃል::

  ReplyDelete