Thursday, March 25, 2010

ቶም እና ጄሪ


«ቶም እና ጄሪ» ፊልም ዊልያም ሐና እና ዮሴፍ ባርባራ በተባሉ ባለሞያዎች ለሜትሮ ጎልድዊን ካምፓኒ የተሠራ ተከታታይ የካርቱን ፊልም ነው፡፡ የቤት ውስጥ ድመት በሆነው በቶም እና በተንኮለኛዋ አይጥ በጄሪ መካከል በማያቋርጥ ቅንቃኔ እና ጠላትነት እየተቀጣጠለ የሚሄደው ይሄ ፊልም፣ አስገራሚም አስቂኝም ነው፡፡ በ1940 እኤአ የተጀመረው ቶም እና ጄሪ፣የአኒሜሽኑ ኩባንያ እስከ ተዘጋበት እስከ 1957 እኤአ ብቻ 114 ያህል ተከታታይ ፊልሞችን በሐና እና በባርባራ ደራሲነት እና አዘጋጅነት አቅርቧል፡፡

በ1960 እኤአ በአዲስ መልክ ፊልሙ እንደ ገና መዘጋጀት እና መታየት ጀመረ፡፡ ዛሬ በታይም ዋርነር ካምፓኒ ባለቤትነት እና በዋርነር ብሮስ አከፋፋይነት የተያዘው የቶም እና ጄሪ የካርቱን ፊልም 162 ተከታታይ ፊልሞችን ያጠቃልላል፡፡

ቶም እና ጄሪ አብረው በአንድ ሰው ቤት ውስጥ የሚኖሩ ነገር ግን መቼም ቢሆን ተስማምተው የማያውቁ ፍጡራን ናቸው፡፡ አልፎ አልፎ በጥቅም ምክንያት ሲስማሙ እንኳን በአከፋፈሉ ምክንያት ለመጣላት ጊዜ አይወስድባቸውም፡፡ ሁለቱንም የሚቃረን ነገር ከመጣ ግንባር የሚፈጥሩት ቶም እና ጄሪ፣ የጋራ ጠላታቸውን ለየራሳቸው ምክንያት ሲሉ ካጠቁ በኋላ እንደገና እርስ በርሳቸው መጣላት ይቀጥላሉ፡፡

ይህ፣ መቼም የማያባራ የቶም እና የጄሪ የቅንቃኔ እና የጠላትነት ፊልም፣ በባለቤቶቹ ዘንድ የታወቁ 162 ተከታታይ ፊልሞች አሉት ቢባልም ጠቅላላ የፊልሞቹ ብዛት ግን ከዚህ ሳይበልጥ አይቀርም፡፡ ለምሳሌ 163ኛው ፊልም የሚዘጋጀውም፣ የሚሠራውም፣ የሚቀርበውም እኛው ሀገር ነው፡፡ ፊልሙን የደረሱትም፣ የሚያዘጋጁትም፣ የሚተውኑትም የ1960ዎቹ የኢትዮጵያ ትውልዶች ናቸው፡፡

ቶም እና ጄሪ በአንድ ሰው ቤት የሚኖሩ ባላንጣዎች ናቸው፡፡ የ1960ዎቹ የሀገራችን ትውልዶችም በአንድ ወቅት የተነሡ የአንዲት ሀገር ልጆች ናቸው፡፡ የተነሡበት ዓላማም ተመሳሳይ ነው፡፡ እነርሱ በሚያስቡት መንገድ ብቻ ሀገሪቱን ማሳደግ፡፡ የርእዮተ ዓላማቸውም ቤቱ ተመሳሳይ ነው፡፡ ያም የብዕር ስሙ ይለያይ እንጂ ከኮሚኒስታዊ አስተሳሰብ አይዘልም፡፡ ፀር፣ትግል እና ግንባር ይወዳሉ፡፡

ዛሬ በሀገሪቱ የወዲህም ሆነ የወዲያ ጎራ፣በድጋፍም ሆነ በተቃውሞ፣ በሀገር ውስጥም ሆነ በዲያስጶራ የሚገኙ፤ የፖለቲካው እና የቤተ እምነቱን መዘውር የሚዘውሩ አካላት በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ከ1960 እስከ 1970 ዓም ባለው ጊዜ ውስጥ የተነሡ፤ በዚያ ዘመን በነበሩ የፖለቲካ አስተሳሰቦች የተማረኩ፣ የዚያን ዘመን የፖለቲካ አመለካከቶችን ሲያቀነቅኑ የነበሩ ናቸው፡፡

ወይ ኢሕአፓ፣ወይ ኢዲዩ፣ወይ መኢሶን፣ወይ ኢሠፓ፣ወይ ኢጭአት፣ወይ የተማሪዎች ንቅናቄ፣ ወይ የሠራተኞች ንቅናቄ፣የላብ አደር ፓርቲ፣ኢማሌድኅ፣ሰደድ ወዘተ ውስጥ ገብተው ሲቆራቆሱ እና ሲተረማመሱ፤ አንዱ ሌላኛውን ለማጥቃት ቀይ ሽብር እና ነጭ ሽብር ሲያካሂዱ፣ አብዮታዊ ርምጃ ሲወስዱ እና ተቀናቃኞቻቸውን አብዮታዊ ምት ሲመቱ የነበሩ ናቸው፡፡

በውይይት ክበብ፣ በማሌ ጥናት፣በስብሰባ አካሄድ፣በፓርቲ አመሠራረት፣ጭቁኑን ሕዝብ በማታገል መርሕ አልስማማ ብለው ወይ ተጣልተዋል፣ ወይ ተኳርፈዋል፣ ወይ ተለያይ ተዋል፣ወይ ተፈላልገዋል፣ወይ ቂም ተያይዘዋል፣ ወይ ጥርስ ተነካክሰዋል፡፡ ስለዚህም እንደ ቶም እና ጄሪ አንዱ ሌላውን በጠላትነት እያየ ከመቀናቀን የተሻለ ሌላ ፊልም ለመሥራት ያዳግታቸዋል፡፡

«የምጠላው ወይም የምቃወመው አታሳጣኝ» ብለው የተሳሉ ይመስል ያለ ጠላት መኖር አይችሉም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ቶም፣ ድሮ ጄሪ ያደረገችበትን ተንኮል ፊልሙን መልሶ እያየ ይበሳጫል፡፡ ከመበሳጨትም አልፎ ለመበቀል እርሷን ፍለጋ ይሄዳል፡፡ እነዚህም ከስድሳ ስድስት እስከ ሰባ ዓም የተቀረጸውን የደም መፋሰስ ፊልም ደጋግመው እያዩ አንዱ ሌላውን በኋላ ታሪኩ ምክንያት ለማጥቃት ይፈላለጋሉ፡፡

162 ፊልሞች ሲሠሩ ቶምም ሆነ ጄሪ አሁንም የፊልሙ ዋነኛ ተዋናዮች ናቸው፡፡ አልተ ቀየሩም፡፡ ከ1940 እስከ 2009 ፊልሙን የሚሠሩት ቶም እና ጄሪ ናቸው፡፡ አልተለወጡም፡፡ በ1960ዎቹ የነበሩት ልጆች ያዩት የቶም እና ጄሪ ፊልም ዛሬም በሃያኛው መቶ ክፍለ ዘመን ያሉ ልጆችም ያዩታል፡፡ በኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክም ፊልሙ እንደ ቶም እና ጄሪ አልተቀየረም፡፡ ያው ነው፡፡ በ1960ዎቹ የነበሩት የሀገራችን የፖለቲካ ቶም እና ጄሪዎች ዛሬም አሉ፡፡ የፖለቲካው ፊልም ዋነኛ ተዋናዮች እነርሱው ናቸው፡፡ አሁንም ሀገሪቱ ከ1960ው ትውልድ ተጽዕኖ መላቀቅ አልቻለችም፡፡ መቼ ይሆን ከስድሳዎቹ ወጥተን ወደ ሰባዎቹ፣ ወደ ሰማንያዎቹ፣ ወደ ዘጠናዎቹ እና ወደ ሁለተኛው ሺ የምንገባው? አሁንምኮ በየፖለቲካው መድረክ የምናያቸው ትክለ ሰብእናዎች የዛሬ ሠላሳ ዓመት የነበሩትን ነው፡፡

አዲሱ ትውልድም የቶም እና ጄሪ ፊልምን ስለለመደ በተመሠረቱት ነገሮች ሁሉ እነዚህን አካላት ካላካተተ፤ ወይንም እነዚህ አካላት ቡራኬ ካልሰጡት በቀር ይሳካል ብሎ ማመን ያቆመ ይመስለኛል፡፡

ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ

መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ

ተብሎ በተዘፈነባት ሀገር፣ዛሬ ዛሬ ገበየሁም አይሞት ባልቻም አይተካ፡፡

ቶም እና ጄሪ ቦታ ይቀያየራሉ እንጂ ስልትም መንገድም አይቀይሩም፡፡ ውጭ የነበረው ቶም ቤት ሲገባ ጄሪ ከቤት ትባረራለች፣ያለበለዚያም ጄሪ ቤት ገብታ ቶም ይባረራል፡፡ ዛሬ የአንድ ፓርቲ ሊቀመንበር የነበረው ነገ የሌላ ይሆናል፤ የአንድ ፓርቲ ልሳን ሲያዘጋጅ የነበረው ምንም ዓይነት የአመለካከት ለውጥ ሳያደርግ ሌላው ጋር ይቀላቀላል፡፡ ደንበኛ ጥናት አድርገን ብንፈትሽ ዛሬ የቆሙለትን ዓላማ ደግመው ደጋግመው ሲቃወሙት የነበሩ አስገራሚ ቶም እና ጄሪዎችን በሀገራችን ታሪክ እናገኝ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች የፖለቲካ አመለካከታቸው የሚወሰነው እንደሚያምኑበት ነገር ሳይሆን እንደ ሚገቡበት ድርጅት እና እንደሚሠጣቸው ሥልጣን ነው፡፡

ቶም እና ጄሪን የሚያስማሟቸው ሁለት ነገሮች ብቻ ናቸው፡፡ የመጀመርያው ጥቅም ሲሆን ሁለተኛው የጠላት መኖር ነው፡፡ በኛም የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ይሄው ፊልም እንደ ቀጠለ ነው፡፡ ቶሞች እና ጄሪዎች አንድ የሚሆኑት ጥቅም እስከተገኘ ድረስ ብቻ ነው፡፡ ጥቅም ከተገኘ በርእዮተ ዓለሞቻቸው ላይ እንኳን የረባ ውይይት ሳያደርጉ፤ የቱጋ የአቋም ለውጥ እንዳደረጉ በሚገባ ሳይረዱም ሳያስረዱም በቅጽበት ይቀናጃሉ፣ ይተባበራሉ፤ ይዋሐዳሉ፣ግንባር ይመሠርታሉ፡፡ አከፋፈል ላይ ሲለያዩ ደግሞ የተባበሩ ቀርቶ የተጎራበቱ መሆናቸውን እስክንጠራጠር ድረስ ይናከሳሉ፡፡

ቶም እና ጄሪ ጠላት መጣብን ብለው ሲያስቡ አንድ ሆነው ያባርሩትና ከጠላታቸው በባሰ መልኩ እርስ በርሳቸው ይባላሉ፡፡ የሀገራችን ቶሞች እና ጄሪዎችም ሊያጠፋን ነው ብለው የሚያስቡት ጠላት ሲያጋጥማቸው አብረው ይሰበሰባሉ፣ይወስናሉ፣መግለጫ ያወጣሉ፣ ይሰለፋሉ፡፡ በኋላ ግን ጠላት ነው ብለው ከሚያስቡት አካል በባሰ ሁኔታ እርስ በርሳቸው መበላላት ይቀጥላሉ፡፡

ለቶም እንደ ጄሪ፣ለጄሪም እንደ ቶም የሚቀርባቸው የለም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለቶም እንደ ጄሪ፣ ለጄሪም እንደ ቶም የሚጎዳቸው የለም፡፡ የኛም ፖለቲከኞች ይህንኑ ፊልም በመሥራት ላይ ናቸው፡፡ 163ኛውን ክፍል፡፡

ባለፈው ጊዜ የዘመን አቆጣጠራችንን ብቻ ተመልክተን ሁለተኛውን ሺ አከበርነው እንጂ የፖለቲካ አቆጣጠራችን ብናየው ኖሮ ወደ ሁለተኛው ሺ ለመግባት ቢያንስ ገና ሠላሳ ያህል ዓመታት በቀሩን ነበር፡፡ አሁንም ተቃውሞ እና ጠላትነትን አልለየንም፣ አሁንም ገና ደጋፊነትን እና ምእመንነትን አልለየንም፡፡ ተቃዋሚያችን ምንም ዓይነት በጎ ነገር ቢያስብ ከመቃወም አንመለስም፤ ጠላትነት እንጂ ተቃውሞ አናውቅማ፡፡ የምንደግፈው አካልም ምንም ዓይነት ጥፋት ቢያጠፋ ከማመስገን ወደ ኋላ አንልም፤ ምእመንነት እንጂ ድጋፍ አናውቅማ፡፡ አይቶም እና ጄሪ፡፡

ሰሞኑን እዚህ ኔዘርላንድ በአንዳች ምክንያት የተጣሉ ሁለት ኢትዮጵያውያን ጎራዎችን ለማስታረቅ የተሰየሙ የሀገሬ ሽማግሌ ያሉኝን እዚህ ላይ ብጠቅሰው እንዴት ጥሩ ነው፡፡ አንደኛው ወገን ከሌላው ወገን ጋር ለመታረቅ በቅድመ ሁኔታነት አሥራ አምስት ነጥቦችን ያስቀምጣል፡፡ ሽማግሌዎቹም ይህንኑ ይዘው ወደዚያኛው ጎራ ይሄዱና ጉዳዩን ያቀርባሉ፡፡ እነዚህኞቹም ቡድኖች ከተወያዩ በኋላ አሥራ አምሱንም ነጥቦች በሙሉ እንቀ በላለን ብለው መልስ ይሰጣሉ፡፡ ሽማግሌዎቹም ድካማቸው ፍሬ በማፍራቱ ተደስተው ወደነዚያኞቹ ይሄዱና «እነዚያኞቹ በሃሳባችሁ ሙሉ በሙሉ ተስማምተዋል» ይሏቸዋል፡፡ ሰዎቹ አላመኑም «አሥራ አምስቱንም ነገር ተቀበሉት?» ይላሉ፡፡ «አዎ ሁሉንም ተቀብለዋል»፡፡ «እንዴት አንድ ሁለቱን እንኳን አልተቃወሙም፤ አንዳች ነገር ቢያስቡ ነውና እንዲያውም አንታረቅም» ብለው መልሱን አሉኝ፡፡

እውነታቸውን ነው፡፡ ቶም እና ጄሪአይደሉ፤ አንዳች የሚያጣላ፣ የሚያቆራቁስ፣ ለፓል ቶክ፣ ለዌብ ሳይት እና ለወሬ የሚሆን የጠብ መነሻማ ያስፈልጋቸዋልኮ፡፡ ተስማምተው ከሠሩ ምን ሊውጣቸው ነው? በኋላ በምን ተለያየን ሊሉ ነው፡፡ አይ ቶም እና ጄሪ፡፡

ኢትዮጵያዊውን የቶም እና ጄሪ ፊልም ከቁጥር አንድ ጀምራችሁ የምትተውኑ የፖለቲካ ቶም እና ጄሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትራችን እንዳሉት በቃን ብትሉ ምናለ? ቢያንስ ለአፋችሁ ያህል፡፡ ሀገሪቱ 1960ዎቹን ለቅቃ ወደ ሃያኛው ክፍለ ዘመን ትገባ ዘንድ ብትረዷት ምናለ፤ በአንድ ወቅት በአንድም በሌላም መልኩ የቶም እና ጄሪን ፊልም የጀመራችሁ ተዋንያን፣ እባካችሁ ሌላ ፊልም እንይበት፡፡ የመነካከስ እና የመበላላት፣ የማያቋርጥ ቅንቃኔ እና ጠላትነት ተከታታይ ፊልም ሰልችቶናል፡፡

ሮተርዳም፣ኔዘር ላንድ

6/30/2009

39 comments:

 1. it is good view. it is what we want. BUT WHO WILL HERE. ADMACH BELELEBET MENAGER MIN TIKIM YAMETAL..but things may be changed one day

  ReplyDelete
 2. Wey daniel, geta yeredah, yemewgiawen ... Betekawem leraseh yebesebehal. Pls atasadew.

  ReplyDelete
 3. thier scrap still to continue because some people are enjoying thom and jerry's fight. citizen's mind need to be cleaned out not to enjoy them anymore, as the result they will be run out of script for thier divergence play.

  ReplyDelete
 4. I appreciate the view. Though the "1960 th" are not listening, the youth shall discuss and learn from the failures of that generation. And we have to start thinking on the right way.
  Thank you Daniel!! Keep on.

  ReplyDelete
 5. Dear Dn Daniel, may be they are searching for any escaped or hiding enemy!!! Thanks for speaking my mind better than I could have imagined!!!

  ReplyDelete
 6. excellent critic, as usual. Semi joro yalew yisma !!!!

  ReplyDelete
 7. Many have expressed their disappointment by Tom and Jerry directors of our past and with those who are still directing. Let me mention just one comment from another blog
  “በ 'ያ -ትውልድ ' ዘመን ውስጥ የታየ እልቂት (በቀይ ሽብር፣ በጦርነት፣ በርሀብ፣ በስደትና በሌሎችም) በየትኛውም ትውልድ ያልታየና በዓለማችን ከታየው የዘር እልቂት (በነ ርዋንዳና ብሩንዲ ) በላይ እንጂ የማይተናነስ ነው:: … እርስ በርስ መስማማት የማይችል ትውልድ ላለመስማማት መፍትሄው በፓርቲም ይሁን በሀገር ደረጃ መለያየት ወይም መገንጠል ብቻ የሚል በሽታ የተጠናወተው ካንሰር ትውልድ ሲወድም አገር ትነሳለች!!”
  I am poor at history and have little experience of the 1960’s but I strongly believe that a chance should be given for the generations that follow them. Otherwise we keep going in the old track always complaining and waiting the hands of our Western leaders and donors.
  “የብር ጥገኝነት የመጣው ከቲዮሪና ከንድፈ -ሀሳብ ጥገኝነት ነው:: ስለዚህ የቲዮሪ ፈጠራ ያስፈልገናል ::”
  And for that we need new directors who can write another script different from Tom & Jerry even if no one denies the experience of our old directors is important for the new.

  ReplyDelete
 8. ዉድ ወንድማችን ዲ/ን ዳንኤል፤
  በጣም ጥሩና ወቅታዊ እይታ ነዉ፡ ዳሩ ግን ምን ያደርጋል...የተማሩ ናቸዉ ብለን ተስፋ የጣልንባቸዉም እንዳልሆሉ ሆነዉ ሲበተኑ..ፖለቲካና ትምህርት ለየቅል ናቸዉ ብለን ትተናል፡ ጥሩ መሪ እንዳማረንና እንደተመኘን ቀረን... የኢትዮጵያ (የአፍሪካ) ፊልም ግን የሚያልቅ አይመስልም...163ኛ፤ 164ኛ፤...የትየሌለ። ብቻ ተስፋ አንቆርጥም...ቢያንስ ለልጅ ልጅ ...ልጆቻችን። አንተ ግን ቀጥልበት ፡ ማን ያዉቃል እይተዎችህ አንድ የለሰለሰ መሬት ላይ ይወድቅና...

  መልካም ሰንበት

  ReplyDelete
 9. but this generation is the passive one due to many reasons specially by using CHAT.i dont know what to say..but what i know is that, eventhough the generation is passive it is better than those tom and jerries.

  ReplyDelete
 10. Daniel i am proud of my brother keep going they should learn more from you instade of talking to much.

  ReplyDelete
 11. Thanks Danie for sharing this: Well it made me laugh out loud. Honestly, this is the exact resemblance of what I see in my city among Ethiopian Community. With some reason, we as a people have made this opposing to everything, not coming to an agreement as part of our tradition. The “15 point agreement points” proposal example of the Netherland is the exact copy of my experience. I am glad that we found the movie title finally ...Keep the good work! What I learn from life is, be that good person who does the right things for the country and for his people, don’t expect it from others. We don’t have any control over others but we do have control on ourselves. If we are the good ones now, the next generation will become better.

  ReplyDelete
 12. tom and Jerry has a lot experiance how to spoile this generation idea... all the field is for them ...we only have one thing we shouldn't support any of them time will clean them out unless we don't know the Game over there we will be victim at the end..life is beautifull gift of God. "spend time to know something than learning through the process could lost ur self for no reason"... libona yistachew

  ReplyDelete
 13. "...አሁንም ተቃውሞ እና ጠላትነትን አልለየንም፣ አሁንም ገና ደጋፊነትን እና ምእመንነትን አልለየንም፡፡ ተቃዋሚያችን ምንም ዓይነት በጎ ነገር ቢያስብ ከመቃወም አንመለስም፤ ጠላትነት እንጂ ተቃውሞ አናውቅማ፡፡ የምንደግፈው አካልም ምንም ዓይነት ጥፋት ቢያጠፋ ከማመስገን ወደ ኋላ አንልም፤ ምእመንነት እንጂ ድጋፍ አናውቅማ፡፡...." 10000% true.

  Bless you.It was nice shot Daniel.

  ReplyDelete
 14. Yeah, we are really sick of all these common faces playing games on us and on our beloved country. At least, we need new Toms and new Jerry's if we can't get rid of the movie at all. We need to harbor new politicians and community organizers. Let's go people.

  ReplyDelete
 15. Hi Dani, that is an intersting deeds.

  May God of our fore fathers blessing be with you.

  Abate.Canada

  ReplyDelete
 16. ዉዱ ዳንኤል ክብረት፣
  ጠንካራ እንደብረት፣
  ፈጣሪ ያደለዉ አስተዋይ ልቡና፣
  የሀገር ተቆርቐሪ የሃይማኖት ጀግና፣
  እነሆ ብቅ አለ በኢንተርኔት ልያስተምር፣
  ልያስቃኘን ቁምነገር፣
  ሁሌም አዲስ ነገር።

  ወንድሜ አይዞህ፣
  በጀመርከዉ ጽና ብርታቱን ያድልህ፣
  መዉጣት መዉረድህን አምላክ ይቀበልህ።
  እኛም እናስተዉል አንባቢ ብቻ አንሁን፣
  የዳንኤልን ዋጋ እናሳይ ፍሬዉን።

  ከለንደን

  ReplyDelete
 17. Dearest Dn/Daneil,
  God may bless you and your family and hoping not only tom and jerry act on a feature film(163 part) but also scriptwriters shooters, editor and directors also work with true love and unity. God is love and we should pray for tom and jerry to understand this source of Love so they can be loved one another, For God so loved (agape) the world, that He gave His only begotten Son, that whoever believes in Him should not perish, but have eternal life john 3;16
  Affectionately

  ReplyDelete
 18. Dearest Dn/Daneil,
  God may bless you and your family and hoping not only tom and jerry act on a feature film(163 part) but also scriptwriters shooters, editor and directors also work with true love and unity. God is love and we should pray for tom and jerry to understand this source of Love so they can be loved one another, For God so loved (agape) the world, that He gave His only begotten Son, that whoever believes in Him should not perish, but have eternal life john 3;16
  Affectionately

  ReplyDelete
 19. Dearest Dn/Daneil,
  May our Lord Jesus Christ bless you and hoping not only tom and jerry act on the film(163 part) but also script writers shooters, editor and directors also work with true love and unity. God is love and we should pray for tom and jerry to understand this source of Love so they can be loved one another, For God so loved (agape) the world, that He gave His only begotten Son, that whoever believes in Him should not perish, but have eternal life john 3;16
  Affectionately

  ReplyDelete
 20. thanks Dn. Daniel

  ReplyDelete
 21. ወንድማችን ዲ/ን ዳንእል

  እያንዳንዳችነ ፤ራሳችንን፤እንድንመረምርና ፤ እንድናስተካክል ፤የሚረዳን ፤ነዉ
  ለተግባራዊነቱ ፤የሁሉንም ፤ጥረት ፤ይጠይቃል።
  እግዚአብሒር ፤ከቶምና ፤ከጄሪ አስተሳሰብ ፤ያላቀን።
  ልቦናችንን ፤መልሶ ፤በፍቅሩ ፤አንድ ፤ያድርገን።

  ከሆላንድ

  ReplyDelete
 22. Thank you Dn Danial
  what you said is 100% right keep up the good work.
  My God be with you and Our church tewhedo

  ReplyDelete
 23. Excellent you are really wise person thank you very much

  ReplyDelete
 24. ዲያቆን ዳንኤል ቢገባቸዉ የአሜሪካን ቤተክርስቲያን መሪ ነን ባዮች ጥሩ ነበረ ነገር ግን የቆሙለትን ወይም የቆሙበትን የማያዉቁ ዛሬም በመተማና በሱዳን በረሀ ያሉ የሚመስላቸዉ የጸሎት ቤቱን ሳሎናቸዉ ሊያደርጉት የሚፈልጉ እግዚያብሔርን የማያዉቁ የእግዚያብሔር ሰዎች አሁንም እያመሱን ይገኛሉ
  ልብ ይስጥልን

  ReplyDelete
 25. if we work together and sit together to discuss and God helps us , it may be the end in 163 parts. we r boring to watch it. we have try to do a films like romeio and juliet.
  God bless Ethiopia

  ReplyDelete
 26. i like it please continue we all here eager to see your post

  ReplyDelete
 27. ya that is true
  we need new film.
  change,change,change

  ReplyDelete
 28. God Bless Ethiopia !
  No less No more. For Ethiopia, God is the only answer.

  ReplyDelete
 29. ኢትዮጵያዊውን የቶም እና ጄሪ ፊልም ከቁጥር አንድ ጀምራችሁ የምትተውኑ የፖለቲካ ቶም እና ጄሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትራችን እንዳሉት በቃን ብትሉ ምናለ?

  ReplyDelete
 30. Where shall we get people who can replace our “Tom and Jerry” Dani?
  “Ke zinjero konjo men yemeraretu” nen eko.
  The thinking that kills the “Historical Ethiopia” is selfishness.
  Have a look at most of us/yourself and your friends/ in a simple family matter.
  How do we react to situations? Most of us respond poorly for such silly things. And we dare go and say vote for us we are ready to solve the “big” country wide problems.
  We surely know what we are capable of, but dare take responsibilities that are beyond our capacity. Can you tell why? It is because we think only for ourselves. If we get such a position, we get a larger income, so we can get rich…very silly material needs. SELFISHNESS
  What we need is ethics. We must have thinking for all not for oneself.

  ReplyDelete
 31. it is good view

  ReplyDelete
 32. Its Nice. But what makes the 1960's different from the former and the later?

  Lets move forward.

  NB: a cat is always a cat, it cant be a Lion. Erkusuna Kidusu hulem alu....I dont like to blame the olds...they did what the can, through thier eyes.

  Better to stand firm...need change? if yes face it. Unless dont talk to the cat b/c it is deaf. Use sign language or physical contact lol

  Love u Daniel

  ReplyDelete
 33. I am beginning to love the author!

  ReplyDelete
 34. ተካልኝ ጅ.ዩDecember 6, 2012 at 9:52 PM

  የ1960ዎቹ ብዙዎቹ አዋቂዎች ናቸው። ግን አስተዋዮች አይደሉም።

  ReplyDelete
 35. ተብሎ በተዘፈነባት ሀገር፣ዛሬ ዛሬ ገበየሁም አይሞት ባልቻም አይተካ፡፡

  ReplyDelete