Tuesday, March 23, 2010

ይምርሃነ ክርስቶስ- የተሠወረ ሥልጣኔያችን


ከአዲስ አበባ በባሕርዳር፣ ጎንደር፣ ላሊበላ በኩል ወደ አኩስም የሚወስደውን የተለመደውን የቱሪስቶች የጉዞ መሥመር ተከትለን ነበር የተጓዝነው፡፡ እኛ ላሊበላ ላይ ወርደን ጉዟችንን ወደ ይምርሃነ ክርስቶስ አደረግን፡፡

ወደ ይምርሃነ ክርስቶስ ለመድረስ ከላሊበላ ወደ ሰቆጣ የሚወ ስደውን መንገድ ይዘን ለ30 ኪሎ ሜትር ከተጓዝን በኋላ ብል ብላ ከተባለችው ከተማ ደረስን፡፡ ከዚያም ዋናውን መንገድ ትተን ወደ ምሥራቅ ተገነጠልን፡፡ መንገዱ ወደ ይምርሃነ ክር ስቶስ ቱሪስቶችን ለማጓጓዝ እንዲረዳ በአካባቢው መስተዳድር የተጠረገ መንገድ ነው፡፡ ከብልብላ በኋላ 7 ኪሎ ሜትር እንደ ነዳን ጥንታዊውን የንጉሥ ይምርሃነ ክርስቶስ ከተማ ዛዚያን በሩቁ አየናት፡፡ አሁን ለምልክት ከሚታየው እና የኢያቄም ወሐና ማኅበር በብረት ፍርግርግ ለማስታወሻ ካሠራው አነሥተኛ ጎጆ እና በዙርያው ካለው ዐጸድ በስተቀር ሌላ ምልክት አይታይበትም፡፡ቀሪውን ስድስት ኪሎ ሜትር ስናጠናቅቅ ከፊታችን ጥቅጥቅ ያለው ደን ገጭ አለ፡፡

1526 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው እና በተራራው ላይ የተዘረጋው ጥንታዊ ደን በሀገር በቀል ጽድ እና ወይራ የተሞላ ነው፡፡መነኮሳቱ ደኑን የተከለው ንጉሥ ይምርሃነ ክርስቶስ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ከመኪና ወርደን ባሕል እና ቱሪዝም ባሠራው የእግረኞች መንገድ በኩል ተራራውን መውጣት ጀመርን፡፡ጸጥ ባለው አካባቢ የአእ ዋፍን ድምጽ ብቻ ነው የምትሰሙት፡፡1ኪሎ ሜትር ያህል እየተጠማዘዛችሁ ተራራውን ትወጣላችሁ፡፡


የእግር መንገዱን አጠናቅቃችሁ ከተራራው ወገብ ስትደርሱ «ውግረ ስሂን» የሚባለውን ዋሻ ከሩቁ ታዩታላ ችሁ፡፡የወለል ስፋቱ 50 ሜትር በ38.75 ሜትር የሆነው ይህ ሰፊ የተፈጥሮ ዋሻ ዙርያው በቋጥኝ የታ ጠረ ነው፡፡በስተ ምዕራብ በኩል የዋሻው ከፍታ እስከ 7.7 ሜትር ይደርሳል፡፡በስተ ምሥራቅ በኩል ዋሻውን ውስጥ ለውስጥ እስከ አቡነ ዮሴፍ ተራራ የሚያገናኝ የውስጥ ለውስጥ መንገድ እንዳለው መነኮሳቱ ይናገራሉ፡፡ የገዳሙ ዲያቆናት ችቦ አብርተው የዋሻውን መጨረሻ ለማግኘት ገብተው ነበር፡፡ውስጥ ለውስጥ አራት ሰዓት ተኩል ያህል ከተጓዙ በኋላ ችቦው እያለቀባቸው ሲመጣ ጊዜ መመለሳቸውን የአካባቢው ሰዎች ይተርካሉ፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የውስጥ ለውስጥ መንገዱ መግቢያ በደለል እየተደፈነ ይገኛል፡፡በአስቸኳይ ጥናት ማድረግ ካልቻልን እንደተሠወረ የሚቀር ብዙ ታሪክ አለ፡፡

ዋሻው የታጠረበትን የ1979ዓም የብሎኬት አጥር አልፋችሁ ስትገቡ ዓይናችሁ ሊነቀልበት የማይችለውን የ12ኛው መክዘ ሥልጣኔያችንን ታያ ላችሁ፡፡

የቤተ መቅደሱ ድንቅ ጥበብ በውኃ ላይ ከመሠራቱ ይጀምራል፡፡ ዋሻው ውስጥ ተዘርግቶ የነበረው ሐይቅ በላዩ ላይ በእንጨት እና በድንጋይ ተረብርቦ ነው ቤተ መቅደሱ የተሠራው፡፡ የኋላ ዘመን ትውልድ አያምነንም ብለው አስበው ይመስለኛል ከሥሩ የሚገኘውን የውኃ አካል ለማየት እንዲቻል ስትገቡ በስተ ግራ በኩል በእንጨት በር የሚዘጋ ጉድጓድ ትተውልናል፡፡ የአካባቢው ሰዎች እንደሚሉት እና በመጠ ኑም ማየት እንደሚቻለው በባሕሩ ላይ እንጨት፣ በእንጨቱም ላይ ሣር፣ በሣሩ ላይ ጭቃ፣ በጭቃውም ላይ ደረቅ አፈር፣ በአፈሩ ላይ ንጣፍ ድንጋይ ተደል ድሎ ነው የተሠራው፡፡ ወደ መቅደሱ ገብታችሁ በባዶ እግራችሁ ከቆማችሁ ቅዝቃዜው ይሰማችኋል፡፡

በባሕሩ ላይ የተረበረበው እንጨት በምን መሠረት ላይ ቆመ በእውነትም እንጨት ከሆነ ለአንድ ሺ ዓመታት እንዴት ቆየ? ተመራማ ሪዎችን የሚፈልጉ ጥያቄዎች ናቸው፡፡

የይምርሃነ ክርስቶስ ቤተ መቅደስ ውቅር አይደለም፡፡ጥንታዊው የኢትዮጵያውያን የሥነ ሕንፃ ጥበብ የተንፀባረቀበት ግንባታ ነው፡፡ ውጫዊ ስፋቱ 12.22 በ9.54 ሲሆን ከወለሉ እስከ ጣራው ያለው ከፍታ ደግሞ 5.88 ሜትር ያህላል፡፡ ከዕጽዋት፣ ከወጥ ድንጋዮች እና ከኖራ መሰል ነገር የተሠሩ 26 መስኮቶች ዙርያውን አስውበውታል፡፡ እነርሱም በሰሜን 8፣ በምሥራቅ 6፣ በደቡብ 7፣ በምዕራብ 5 ናቸው፡፡ ጠቢቡ አምስት ስድስት፣ ሰባት እና ስምንት ቁጥሮችን በቅደም ተከተ ላቸው የመረጠበት ምክንያት ምን ይሆን? ከ26ቱ መስኮቶች መካከል 22ቱ ሲከፈቱ አራቱ ግን አይከፈቱም፡፡ የአንዱ መስኮት ዲዛይን ከሌላው መስኮት ዲዛይን ስለሚለያይ ለሃያ ሁለቱ መስኮቶች ሃያ ሁለት ዓይነት ዲዛይን ነው የምናየው፡፡ የዘመኑ ጠቢባን ጥበባቸውን ለማሳየት ምን እንደተጠበቡ ያመላክታል፡፡

ቤተ መቅደሱ ደቃቅ፣ መጠናቸው የተመጣጠኑ ጥቋቁር ድንጋዮች በጭቃ እየተጣበቁ ነው የተገነባው፡፡ እንዴት ይሆን ጭቃ እና ድንጋዩን አቡክተው ያጣበቋቸው? የጭቃው ግንባታ ለ25 ሳሜትር ያህል ወደ ላይ ከተጓዘ በኋላ በአራት መዓዝን የተጠረበ ወጥ እንጨት ይገባበታል፡፡ እንዲህ እያለ ድንጋይ፣ ጭቃ እና እንጨት በጥበብ ተስማምተው ይምርሃነ ክርስ ቶስን ለሺ ዓመት ያህል አቁመውታል፡፡ እኔን የገረመኝ ነገር ቢኖር ዛሬ ዛሬ በስሚንቶ እና በድንጋይ የተሠሩት ሕንፃዎቻችን ዓመት ሳይሞላቸው ሲሰነጠቁ ጭቃውን ከድንጋይ እና እንጨት ጋር አዛምደው ይህንን ያህል ዘመን ያቆዩበት ጥበብ ምን ይሆን? የሚለው ነው፡፡ እንዲህ እየተያ ያዘ የተገነባው ግድግዳ ኖራ በሚ መ ስል ነጭ ነገር ከውጭ እና ከውስጥ ተለስኗል፡፡ የልስኑ ንጣት እና የእንጨቱ ወርቃማ ቀለም ለቤተ መቅደሱ ውጫ ዊ ገጽታ ዓይን እንዳይነቀል የሚያደርግ ውበት ሰጥቶታል፡፡

በምዕራብ እና በምሥራቅ ሁለት ሁለት ፎቆችን ያዘለው ሕንፃ ወለሉ እጅግ ለስላሳ በሆኑ ድንጋዮች ንጣፍ የተሠራ ነው፡፡ እጅግ የሚያስደንቀውን ሌላ ጥበብ የሚያዩት ደግሞ ወደ በሩ ስትዞሩ ነው፡፡ ከአንድ ወጥ እንጨት የተሠራው በር፣ ከግድግዳው ጋር አንድ ሺ ዘመን በሆናቸው ብሎኖች እየታሠረ በታጣፊ ብረት ተያይዟል፡፡በዚያ ዘመን እንጨት ሠርስረው የሚገቡ ብሎኖችን የመሥራት ጥበብ ነበረን ማለት ነው? በሩን ለመዝጋት ከእንጨት የሠሩት ጥንታዊ ቁልፍ እጅግ አስደናቂ ነው፡፡ የቁልፉ መግቢያ ቀዳዳ እንደ ዘመ ናዊው ቁልፍ የተገለበጠ ቅል ቅርጽ አለው፡፡ በዚያ ዘመን የነበረውን የቁልፍ ቴክኖሎጂ የታሪክ ምሥክር ሆኖ ያሳየናል፡፡

የቤተ መቅደሱን ውስጣዊ ጥበብ ለማየት ከአንድ ወር በላይ ይፈጃል ባይ ነኝ፡፡ የዘመኑ ጠቢባን ያለ ጥበብ ያለፉት አንድም ክፍት ቦታ አይገኝም፡፡ጣራው፣ ግድግዳው፣ ወለሉ፣ ዓምዶቹ በሮቹ እና መስኮቶቹ ሁሉ አንዱ ከሌላው የማይገናኝ ጥበብ ፈስሶበታል፡፡ የመቅደሱ መካከለኛ ቦታ ከተጠረበ እና ለስላሳ ከሆነ እንጨት የተገጣጠመ ሲሆን ክብ ሆኖ የታነፀ ነው፡፡ ውስጡ በመንፈሳዊ ሥዕሎች ያጌጠ ሲሆን የሚዘጋው በመጋረጃ ነው፡፡

የቤተ መቅደሱን ጣራ የተሸከሙት ዓምዶች በባለሞያ ከተጠረቡ ለስላሳ፣ ጠንካራ፣ ሰፋፊ እና ከባድ ከሆኑ የከበሩ ድንጋዮች የታነጹ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ዓምድ ልዩ በሆነ ሐረግ እና ሥዕል የተጌጠ ነው፡፡ የአንዱ ዓምድ ዲዛይን በምንም መልኩ ከሌላው ጋር አይያያዝም፡፡ የቅድስቱ ጣራ በስምንት ክፍል የተከፈለ እ ያንዳንዱ ጣራ የራሱ የሆነ ልዩ ዲዛይን እና ሥዕል አለው፡፡ አሁን አሁን ከአቧራ እና ከክብካቤ እጦት የጣራው ላይ ድንቅ ሥዕሎች እና ቅርጾች እየደበዘዙ ናቸው፡፡

በጣራው ውስጣዊ ገጽታ ከጣራው ጋር ተያየዘው ወደ ታች በወረዱ አራት መዓዝን በሆኑ ሁለት የእንጨት ገመዶች የተን ጠለጠሉ ዕንቁዎች አሉ፡፡ ከሁለቱ በአንደኛው ገመድ ላይ የተንጠለጠሉትን ዕንቁዎች በ1986 አካባቢ ሌቦች የወሰዷቸው ሲሆን እንዳይታወቅ ተመሳሳይ ነገር ተክተውበት ነበር፡፡
ውሳጣዊውን ክፍል ስታዩ በዚያ ዘመን የነበሩ ሰዎች ዘጠና፣ አርባ አምስት እና አንድ መቶ ሰማንያ ዲግሪዎችን ጠብቀው የጣራውን ክበብ፣ የዓምዶቹን መዓዝን እና የመስኮ ቶችን ቅርጽ ለመሥራት የተጠቀሙበት የጂ ኦሜትሪ ጥበብ ምን ይሆን? ምናለ ሕንፃውን እን ዳገኘነው ሁሉ ጥበቡንም አብረን ባገኘው? ያሰኛ ችኋል፡፡ ለመሆኑ ይህንን ሕንፃ ከማነፃቸው በፊት ዲዛይኑን በምን ሠሩት? ጣራውን ሲያንፁ የተጠቀሙበት የመደገፊያ እና የኮንክሪት ጥበብስ ምን ይሆን?

ቤተ መቅደሱ ውስጥ ሁለት ጥንታውያን የእንጨት ሳጥኖች ይገኛሉ፡፡ ዛሬ ዛሬ ለዕቃ ማስቀመጫነት በሚጠቀሙባቸው እነዚህ ሳጥኖች ላይ የሚታየው ቅርጻ ቅርጽ እና በሕንፃው ጣራ ላይ የሚታየው ቅርጻ ቅርጽ ተመሳሳይነት አለው፡፡ እንደ እኔ ግምት ከሆነ እነዚህ ሳጥኖች የሕንፃው ንድፍ የተቀመጠባቸው ሳጥኖች ይመስሉኛል፡፡ ጠቢቡ ሕንፃውን ሲያንፀው ምናልባት በእንጨቱ ላይ የሠራውን ዲዛይን እየተከተለ ይሆናል፡፡

ከቤተ መቅደሱ ጎን ያለው፣ዛሬ በዕቃ ቤትነት የሚያገለግለው እና ይምርሃነ ክርስቶስ በቤተ መንግሥትነት ይጠቀምበት ነበር የሚባለው ሕንፃ ግን እጅግ ተጎድቷል፡፡ ሌላው ቀርቶ አቧራውን እንኳን በዘመናዊው የአቧራ መጥረጊያ ማሽን በአንድ ቀን ማስለቀቅ በተቻለ ነበር፡፡ በዚሁ ከቀጠለ ከአሥር ዓመታት በኋላ የምና ገኘው አይመስለኝም፡፡

ይምርሃነ ክርስቶስ በ939 ዓም አካባቢ ተወልዶ በ1036ዓም አካባቢ ያረፈ የዛግዌ ሥርወ መንግሥት ንጉሥ ነው፡፡ የነገሠው በ996 ዓም አካባቢ ሲሆን ቤተ መቅደሱን ያነፀው በ1018 ዓም አካባቢ መሆኑ ይነ ገራል፡፡ የላሊበላ አብያተ መቅደስ ተጠናቀቁበት ከሚባ ለው ዘመን 1193 ዓም ጋር ስናስተያየው ቢያንስ የሰባ ዐመት ቅድሚያ አለው ማለት ይቻላል፡፡

ይምርሃነ ክርስቶስን የሥነ ሕንፃ፣ የአርክቴክቸር እና የአርኬዎሎጂ ባለሞያዎች ሊጎበኙት ለዛሬው ሥራችን የሚጠቅምም ሀገራዊ ጥበብ ሊሸምቱበት ይገባል ባይ ነኝ፡፡ የባለ ሞያዎችን ጥናት እና ምላሽ የሚፈልጉ አያሌ ጥበቦች የፈሰሱበት ሕንፃ ነው፡፡ በተለይም ቦታው ዋሻ ውስጥ በመሆኑ እና ከተራራ ግርጌም በመደበቁ ከብዙዎቹ የእርስ በርስ ጦርነቶች ተርፎ ታሪኩን እንደያዘ ይገኛል፡፡በመሆኑም ከአካባቢው የተሻሉ መረጃ ዎችን ይሰጣል ባይ ነኝ፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለአካባቢው ታሪክ እና ቅርስ ትኩረት በመስጠት መንገዱን ለማ ሠራት፣ አካባቢውን ለመጠበቅ፣ለማስተዋወቅ እና ለመከባከብ የክልሉ ባሕል እና ቱሪ ዝም የሰጠው ትኩረት የሚደነቅ ነው፡፡

74 comments:

 1. Keep it up, I hope this will be an ideal blog reaching many.

  ReplyDelete
 2. Here we go. The much awaited action from our brother! I pray that you will unfold lots of original stories, commentaries and analyses - successfully defending sometimes ignoring some possible naughty comments which might come along your way.

  Great...Go on brother!!!!

  ReplyDelete
 3. May God give you and those who serve our church the wisdom and strength as always.

  ReplyDelete
 4. Good job we expect a lot from you brother! I agree with the above comment. Keep up the good job you are always doing and ignore the nuisance.

  ReplyDelete
 5. It's truly amazing finding our brother, May the almighty God always be with you.
  Please continue to educate the people on desert (where there is always work...work...work...) but there is no life (ethernal life) our work will not be a life, most of us discuraged because we see people and distance our self from our mother church the fact is we will be away and grife each and every day what happen to our church, I think God may have choosen you to guide the young generation the light at the end of the tunnul.
  May the mercy of God be with us always again.

  ReplyDelete
 6. God blesse you and your famly, may God will be leeding you at all your job and life , this is truly amzing. you belong there, please don't think to come here to the plece which hiding all of us who are lost form mother of church.
  GOD blesse you agin

  ReplyDelete
 7. Keep it up! we have been looking forward to seeing you in such a venue for long. I want your and readers comments in my blog mistiretewahedo too.visit it @mistiretewahedo.blogspot.com

  ReplyDelete
 8. God bless you!! Keep your good work and expect response from God. A lot of ugly and 'discouraging' comments may follow. Please please i am begging you, don't let those evil comments on your site. If there are Christian critics it's very welcome. But there are some inhuman comments.

  Egziabher Melkam Yimensemabet Medrek Yadrgilin

  ReplyDelete
 9. Dear Daniel,

  Good job. Let the God of our fathers be with you. Amen

  ReplyDelete
 10. Good job dany.you are wonderful son for our church.merte yetewahedo leje.God bless you and your family.

  ReplyDelete
 11. Dear Daniel,
  Good job. I am very happy for you. Let the God of Our Fathers be with you.

  ReplyDelete
 12. ለጅማሬ ያበቃህ አምላከ ቅዱሳን ብርታቱን እና ትጋቱን አድሎህ ለሰው ልጆች በሙሉ የመልካም ነገር መማሪያ የሚሆን "Blog" ያድርግልን:: እንደ ዘመኑ ትውል በጅማሬ ውይም በመሃል የሚቀር እንዳይሆን እያልኩህ ከቀደምት አባቶቻችን ጋር አስጀምሮ ለፍጻሜ ያበቃቸው እግዚአብሔር ከአንታም ጋር ይሁን።
  ሀጥኡ የሆንኩኝ ታናሹ ወንድምህ ነኝ
  [ካለሁበት ከስደት ዓለም]
  [መጋቢት ፲፬/፳፻፪ ዓ.ም.]
  አምላከ ቅዱሳን በምህረቱ አይለየን።

  ReplyDelete
 13. I hope this blog will be a venue where we learn more and plan more for our church and country. Hope we will discuss more. Le'yikun le'yikun. Amen

  ReplyDelete
 14. I alwyas feel that you have good talent and knowledge that should be shared with us. And this blog will be one way to leave good foot print for generation and for us to learn more from you.
  May GOD Bless your service.

  ReplyDelete
 15. Bless you Dn Daniel...Good job. I am very pleased to read your blogs. Would it be possible to forward and get answers to some question here too?
  May this prophecy in the Lord fulfilled in us "And they shall rebuild the old ruins, they shall raise up the former desolations, and they shall repair the ruined cities, the desolations of many generations" Isaiah 61:4.

  "ከጥንትም ጀምሮ ባድማ የነበሩትን ይሠራሉ ከቀድሞ የፈረሱትንም ያቆማሉ፤ ባድማ የነበሩትንና ከብዙ ትውልድ በፊት የፈረሱትን ከተሞች እንደ ገና ይሠራሉ።"

  Medihanit Alem Eyesus Kirstos kante ga yehun!

  Blessings!

  Welde Silasse!

  ReplyDelete
 16. ow my goodness eureka. i will be very glad on getting your update. wonderful! keep it up! i hope God will be with you on the way forward. let us read something truth from you.

  ReplyDelete
 17. Great. May God be with you and all your works.
  Halftwo

  ReplyDelete
 18. That is good news and good Job .I am sure that most people will apperciate your effort.You are also expected to promote it in ethiopia so as to get many reader.
  don't hesitate

  ReplyDelete
 19. +++
  Dear Daniel

  That is interesting and I like it. I hope you keep it up.

  I stopped reading when I reached the following paragraph.

  ''በባሕሩ ላይ የተረበረበው እንጨት በምን መሠረት ላይ ቆመ በእውነትም እንጨት ከሆነ ለአንድ ሺ ዓመታት እንዴት ቆየ? ተመራማ ሪዎችን የሚፈልጉ ጥያቄዎች ናቸው፡፡''

  Because it enlighten me on the issue within me for the last 12 years that I couldn't put in words/practice. I opened my MS word and put the following title

  ''Evaluation of the Mysteries of Ethiopian Ancient Monasteries from Engineering Perspective.''

  One of the mysteries is the one mentioned in your article. Though it would be inmature at these stage, as an Engineer, I have some hypothesis for it. (Mind I haven't visited the place yet)

  1. The entire foundation may be under water.
  In this case, keeping the timber below the ground water level will protect the timber against decay and putrefaction.

  2. Timber piles may be used to trasfer the load to the ground under water.

  3. If not (2) that would be interesting and our fathers could understand Law of Bouyancy that time. εὕρηκα

  Don't forget God's miracles also.

  ECCLE

  ReplyDelete
 20. As almost everyone above mentioned it is really my pleasure to read such kind of multipurpose articles and hope you will continue building on it.
  After I said that let me add something about Yemrehane Kirstos that I got from one forum. An individual asked who is the Ethiopian leader that you prefer and one mature sister wrote the following.

  ከቅርቦቹ ብዙም የምመርጠው የለኝም - ከዱሮዎቹ ካህኑን ንጉሥ ይምርሐነ ክርስቶስን እመርጣለሁ!
  ቀን ቀን ሰዎች በተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ተጣልተው ወደርሱ ሲመጡ በእውነት ዳኝቶ ጥፋተኛው ላይ ቅጣት ይጥላል :: ማታ ግን ሁለቱን ወገኖች አስታርቆ ቅጣቱ በተበዳዩ ፈቃድ እንዲነሳ አድርጎ አስማምቶ "እምማእሰረ -ኃጥያት እግዚአብሔር ይፍታ !" ብሎ ያሰናብታቸው ነበር ! ስለነሱም ጽሎት ያደርግ ነበር ! እውነትና ምሕረት አንድ ሆኑ ..... ያለው መጣፉይህን ለማመልከት ሳይሆን ይቀራል ?
  ሕግና ይቅርታ ሁለቱም ሳያኮርፉ ታርቀውባት ነበር በኢትዮጵያ !
  እስከቅርብ ጊዜ በይምርሀነ ክርስቶስ መቃብር ዙርያ ሰዎች እየዞሩ ኃጥያታቸውን እየተናዘዙ "ይፍቱኝ አባቴ " ይሉ ነበር :: ድምጽም ከመቃብሩ እየወጣ "እግዚብሔር ይፍታ " ሲል ይሰማ ነበር :: ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቀረ ያ ድምጽ ! እግዜር ይሁነን!

  ReplyDelete
 21. God bless you and be with you. you are teaching and transfering great message to me who made my self unable in serving of my mother church. please keep it up!!

  ReplyDelete
 22. Dear Daniel,

  God Bless you and keep it up .I always think about you and your friends/brothers
  contributions to our church.I know the road
  is full of challenges but I am confident enough
  to belive that everything will be possible with help of GOD.Wish you all the best!thanks!!

  ReplyDelete
 23. Great action from Dani, at least for .09% of the ppl accessing the internet.hopefully others will follow his footsteps

  ReplyDelete
 24. ውድ ወንድሜ ዳንኤል
  ብሎግህን በማየቴ እጅግ ደስ ብሎኛል። እግዚአብሔር አምላክ ፍጻሜውን ያሳምርልን። በርታ… ይህች ቤተክርሲቲያን ካንተ ብዙ ብዙ ትጠብቃለችና… የመረጠክ አምላክ ሁሌም ካንተ ጋር ነው…ወላዲተ-አምላክ ካንተ ጋር ትሁን

  ReplyDelete
 25. once again Brother Daniel good to have u!!! may God shines upon u can't wait to read the next

  ReplyDelete
 26. sinatyehu /chebuda/March 24, 2010 at 3:18 PM

  dear D.daniel
  realy am very happy ur blog God never let u down, He alwayes wiz u ...dont give up we will waite more and more ....
  churche yasetemarechen tarike meserat new enji metechate ayedelem bereta
  God bless u and ur family

  ReplyDelete
 27. +++
  Selam Dani,
  This is a great start!! May God be with you in all walks of your life.

  ReplyDelete
 28. Good to know this blog. Hope you will add knowledge to Ethiopians both in respecting their country and faith. God Bless you and your work.

  Brothers and Sisters please visit my blog also:

  www.wongelforall.wordpress.com

  ReplyDelete
 29. I took it as a good start. As the title tells, it will have both arenas related to our mother church. I will say avery comfortable way of telling the way you look it. It is kind of confidence in the teachings of our mother church and I am happy with it. Thank you brother and keep it up.

  ReplyDelete
 30. Great job!!! Melkam gemare new!!! Fesamewen yasamerew!!!

  ReplyDelete
 31. Really happy to see u here. May God be with u and always keep u in with his grace.

  ReplyDelete
 32. Dear Daniel,

  I am very happy to see your work out there for people in written. You are born for this. You are born to read, write, transfer knowledge and help people see the world in different way. You can't be quiet. I always adore your analysis, teachings and comments. Keep the good work! Stay strong! God bless you, your family and your work.

  ReplyDelete
 33. +++
  ዲ/ን ዳንኤል በርታ ሰዉም ሁን: ጥሩ የሆነ ህያዉ ሥራ እግአብሔር አስጀምሮሃል እግአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን:: እንደ መጀመሪያቱ የማህበሩ ቤት ያለ ብርታት ይስጥህ:: አሜን

  ከዝዋይ

  ReplyDelete
 34. May God Bless you a lot, keep it up your Good job.

  ReplyDelete
 35. +++

  Dear Dn. Daniel,

  I'm happy to read your blog. Thanks to the God of our fathers who gives you the time and courage to serve our church and to share your knowledge to us. I expect a lot from you.Keep it up! Dingil tabertah.

  ReplyDelete
 36. የተከበርው ውድ ወንድሜ ዳንኤል
  ስራህን ሁሉ እግዚአብሔር ይባርክልህ አምላከ ቅዱሳን በስራህ ሁሉ ካንተ ይሁን
  መዝሙር ፻፴፫- ፩
  ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው።

  ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስስ፥ እስከ አሮን ጢም፥ በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው።


  በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፤ በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዝዞአልና። ኁይለማሪያም ዘፍራንፈርት

  ReplyDelete
 37. Dear Dn. Daniel,

  Bless you Dear bro. Myself Fiseha and Tsehay Simeneh from Roma (Italy).

  ReplyDelete
 38. I am extremely pleased to see your webpage
  Please continue to share your wisdom with the whole world

  ReplyDelete
 39. ዲ,ዳንኤል, የጅማሬም የፍጻሜም ባለቤት ቸሩ መድሀኒ ዓለም በረድኧት አይለይህ::
  I will be expecting more from you. It will be one of my blogs which I will visit before I go bed.

  Rediate Egziabhere Ayileyegne!!! Amen!

  ReplyDelete
 40. Thank you very much Dn Daniel.You can teach and reach more Christians by using such technology.
  Please keep it up.

  ReplyDelete
 41. Dear Dn. Daniel
  I am happy to see your effert to make glorify our church.Your Blog will initiate others.
  Be stonge to make real your dream!!!

  i missed your words in Addis Neger Newspaper.
  But now i can get every thing from your blog

  Tesfaye

  ReplyDelete
 42. Dn Daniel, thank you very much. While appreciating his effort I call up on others to use any necessary mechanism to spread this wonderful message as far as we can!!! We can use FB or e-mail, or any other mechanism. yalewene yewerewere nefuge ayibaleme ayidele teretuse!!! Am exited to hear more of your thoughts brother!!!

  ReplyDelete
 43. This is rely what I want. I want to learn from You. God keep us from all unseen challenges.

  Weldmariam(WM29)

  ReplyDelete
 44. God Bless u our brother!!!Keep the good work flow
  like a river!!!

  ReplyDelete
 45. dani i am so happy to read your blog,god bless you....

  ReplyDelete
 46. dani i am so happy to read your blog god bless you..

  ReplyDelete
 47. I was expecting this for long time and here is now.this is the right time searching our history and at the same time to let the world know that how civilized people we are at any point.I belive that you have a full potential to do that specially for diaspora.we are confused and we are in the middle of no where.we ignoring and losing our identity. may GOD be with you.

  ReplyDelete
 48. Here you go this is what we call it "Hamanot enedeabatocahiehn seltane endezemnachin".
  Dear Dn Dainel May God give you more wisdom & talent like the one who has 5 talents & he profit another 5 & God gave him more because he did his job.
  Enberehan titebikeh

  ReplyDelete
 49. Dear Brother,

  I praise our Lord for the special provision given to you. I also praise him more that you never hide this provision. No fear, no boundary and no burden or fear prevent you to deliver his message. No matter how and where you write or say it is always Godly word from spiritual brother.

  May the Almighty continue blessing you with grace, strength and means to spread his word more and more.

  you and your lovely family remain blessed.

  ReplyDelete
 50. Hul gize yemigermegn yeneza Kidusan Abatoch lijoch mehonachin new.Eski bereketachew yidresen.
  Antenim Yasjemereh AMLAK yasfetsimih
  kale hiwotin yasemalin
  I hope we'll get more from ur site
  God bless u again

  ReplyDelete
 51. thank u very much

  ReplyDelete
 52. May God be with you.

  ReplyDelete
 53. This is great, keep your effort up
  you are the only best

  ReplyDelete
 54. እግዚያብሔር ብርታቱንና ፀጋውን ያድለህ፡፡
  ሁልጊዜ ያልሠራኸውንና የሚቀርህን አስብ የበለጠ ትሠራለህ
  Bwalelegne

  ReplyDelete
 55. Dear Dn. Daniel

  Well done. May God be with you in everything. We need more from you so just remember this and Keep it going.

  ReplyDelete
 56. ውድ ወንድሜ ዲ/ዳንኤል እግዚአብሔር ማስተዋሉን አሁንም ያብዛልህ፡፡ የድካምህን የሚከፍልህ ቸር አምላክ ነው፡፡ አብዝቶ ያትረፍርፍልህ በርታ እጅህን ለምንም ለማንም አትስጥ፡፡ አምላከ ቅዱሳን ይጠብቅህ አሜን፡፡
  ወለተ ሥላሴ

  ReplyDelete
 57. HI D/N DANIEL
  YOU ARE EXTRA ORDINARY MAN. YOU ARE DOING SOME THING MARVELOUS PLEASE KEEP IT UP.
  HOPE YOU WILL NEVER FALTER AND WAVER. FOR HELP HOPE EVERYONE IS ON THE SIDE OF YOU AND I'M THE VANGUARD ONE. TRUTH IS STUBBORN THINGS. LET IT GO.
  TRUTH HAS NO PHASE BUT FALSE.
  YOU ARE THE PIONEER I MEAN TRAILBLAZER BUT PLEASE I IMPLORE YOUR BLOG SHOULD CONTAIN MUCH ABOUT RELIGIOUS MATTER. I FOND OF IT WITHOUT AFFECTING THE DIVERSIFICATION.

  ReplyDelete
 58. ለአሳቦች ዋጋ ቢሰጣቸው ዋጋቸው እጅግ በጣም ውድ ስለሚሆኑ ሊገዙም ሆነ ሊሸጡ አይችሉም ሊሰጡ ብቻ እንጂ
  አሳቦች ከአንዱ ሰው አእምሮ ወደ ሌላው ሰው እና ከአንዱ ሰው ልብ ወደሌላው ብርሃን የሚያበሩ ሻማዎች ናቸው
  ይህን የብርሃን ጮራቸውን በሚወዶአቸውና ሂስ በሚሰጡዋቸው ሰዎች ላይ ይፈነጥቃሉ

  ዲ\ዳንኤል መልካም ጅማሮ ብያለሁ እንግዲህ በስብከቶችህም በመፅሃፍቶችህም ብዙ አሳቦችና እይታዎችን በነፃ
  ስታበረክትልን ቆይተሃል አሁን ደግሞ በበለጠ ነፃነት ይህንን አጋጣሚ የፈጠረ እግዚአብሔር አንተን ምክንያት
  አድርጎልናልና ሁላችንም ባለንበት በፀሎትም በሃሳብም እናግዘው እላለሁ

  ብርታቱን ይስጥህ


  ኢዮሲያስ

  ReplyDelete
 59. Dear Dani,

  Thanks a lot for inviting me for the new blog which I & many others
  could share ideas. I appreciate the angles from which you approach/see
  things. MAY GOD BE WITH U ALL THE TIME! I REMEMBER YOU IN MY PRAYERS
  ALWAYS. I'M SO
  HAPPY BECAUSE I COULD GET YOUR VIEWS IN THIS WAY AFTER MISSING YOU
  alot FROM THE MEDIA THAT I USED TO GET YOUR VIEWS BEFORE. MAY GOD OF
  OUR FATHERS BE WITH YOU AND STRENGTHENS YOUR HANDS FOR SUCH SACRED
  CAREER! I BEG HIM NOT TO MISS YOUR VIEWS AGAIN! WORDS LACK TO EXPRESS
  MY GRATITUDE! THANKS AGAIN

  ReplyDelete
 60. እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሆን በጣም አስተማሪ ነው ፡፡ ከወሎ መንደር ፡፡

  ReplyDelete
 61. This comment has been removed by a blog administrator.

  ReplyDelete
 62. ዲ/ን ዳንኤል :--- ቃለ ህይወት ያሰማህ
  ዘመኑን ይበልጥ ዋጀው ቅደመው :: እኔ የአባታችንን ጥበብ አይቸዋለሁ :: እንደሰው አስተሳሰብ ማለትም ዲዛይን (design), ግንባታ(construction) እና ፍፃሜ(finishing) በፍፁም አይደለም:: እነዚያ እንቁ የከበሩ ድንጋዮችን ማን ሁለተኛ ፎቅ ላይ አወጣቸው? እንዴትስ ወጡ? በሩ ከግድግዳው ጋር የተያያዘበት ቡሎን (Connection, Bolt) እንዴት ተሰራ? የውስጥ የላይኛው ክፍል ዲዛይን (design), ግንባታ(construction) እና ፍፃሜ(finishing) ሌላው ይቅርና መደገፊያው (formwork) ምንድን ነበር? ከየት መጣ? ሁሉም ከምድራዊው የምህንድስና (engineering) ሥነ ጥበብ (architecture) ሥነ ምድር (geology) ጥናት ጋር የሚያገናኘው አንዳች ነገር የለም :: በእነዚህ የት/ት ዘርፎች የአባታችንን ጥበብ እንመርምር እናረጋግጥ ለማለት አይሞከርም:: ያ ከእውቀት በላይ ነውና:: የእምነት ጉዳይ ብቻና ብቻ ነው::
  Generall it is MIRACLE, MYSTRY AND “”TSEGA‘ (ተአምር ምሥጢረ እና ፀጋ ነው:: እኝህ ደግሞ የሰው ልጅ ሀብቶች አይደሉም::) ”የጥበብ አገሯ ወዴተ ነው? መገኛዋሰ?‘ ማለት ይህ አይደል!!!------ቅዱስ ኤጲፋኒዮስ

  የጥበብ ባለቤት ጥበብን ይግለጽልህ
  ዮሴፍ ነኝ ከመቀሌ ዩኒቨርስቲ

  ReplyDelete
 63. ይህን የመሳሰሉ ታሪኮችን በተከታታይ ብትጽፍልን የቤተክርስቲያናችንን ታሪክ ለማወቅ ስለሚዳን በርታ፡፡
  ከአ.አ

  ReplyDelete
 64. እንዲህ ነው በአባቶች ፈንታ መወለድ! ለቀደምት አበው እውቀትን ጥበብን ማስተዋልን የሰጠ ልዑለ ባሕርይ አምላከ ቅዱሳን ሕያው እግዚአብሔር ይጠብቅህ፡፡ ማስተዋልና ጥበቡንም ይስጥህ፡፡

  መጣዓለም አ. ከደቡብ ወሎ ኮምቦልቻ

  ReplyDelete
 65. ‹‹ልጁ ቁርጥ የአባቱ ልጅ ነው›› እንድል አስገደድከመኝ የአቶ ክብረት(መዕረገ ክህነት ካላቸው ይቅርታ ይደረግልኝ) ሳይሆን የቀደሙት ኢትዮጵያውያን፡፡ ዳንኤል እግዚአብሔ ጸጋህን ያብዛልህ

  ReplyDelete
 66. በጣም የሚያስደንቅ ነገር ነው የእግዚአብሔር ቸርነት የበዛበት ሀገር ላይ በመኖራችን እለት እለት አምላካችንን ማመስገን ይገባናል አሁን እስኪ ውሃና እንጨት ተዋደው ለ1000 ዘመናት ያህል ይቀመጣሉ ብሎ ማን ያስባል;
  አሁንም የእግዚአብሔር ፀጋው ይብዛልን
  አንተንም አምላክ ይባርክህ ዲ.

  ReplyDelete
 67. I don't think its a miracle.its the amazing engineering achievement of our fathers.

  ReplyDelete
 68. daniel ene betam yemigermegn yemetetsfachew tsehufoch gezeachewen tebekew memetachew new ene tumerahen zegeyeche bayewem honom lagerachen poleticians tiru eyetan befeterilachew beye new ante atakewem malete ayedelem yemerane kirstos kegibtsoch gar endet yenegager endeneber malete new abyen bemegedeb endet yepolticawen sera yesra endeneber yahunochu poletician yehen kete yametut yemeselehal

  ReplyDelete
 69. egiziaber edemena tena yestehe keep up pls!!

  ReplyDelete
 70. 10q dani ,GOD bless u

  ReplyDelete
 71. በባሕሩ ላይ የተረበረበው እንጨት በምን መሠረት ላይ ቆመ በእውነትም እንጨት ከሆነ ለአንድ ሺ ዓመታት እንዴት ቆየ? ተመራማ ሪዎችን የሚፈልጉ ጥያቄዎች ናቸው፡፡

  ReplyDelete
 72. God bless Ethiopia!!! 10Q Daniel. we have a lot of things but.....

  ReplyDelete
 73. God bless Ethiopia!!! 10Q Daniel.

  ReplyDelete
 74. የሚያስገርም ድንቅ ስራ ነው.ለአንድ ሺ ዓመታት የቆየ ያውም በእንጨት...አመሰግናለው ዲያቆን ዳንኤል እኔስ ራሴን ታዘብኩት

  ReplyDelete